Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.76K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን  ለ1499ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!

መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን !
👍8👎3
ለባሸዋም ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፡ ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ ፡

የትምህርት ቤታችን 25ኛ አመት የምስረታ በዓል እና ለ2017ዓም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሰን - አደረሳችሁ እያልን ፡

የ2017ዓም ትምህርት ከኬጂ ( ቅድመ አንደኛ) እስከ 12ኛ ክፍል ረቡዕ መስከረም 8/2017ዓም የሚጀመር መሆኑን እያሳወቅን፡ ተማሪዎች ለትምህርት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ( ቁሳቁስ) አሟልተው እንዲመጡ እናሳስባለን።

ትምህርት ከጠዋቱ 2:30 ስለሚጀመር ተማሪዎች ቀደም ብለው ትምህርት ቤት መገኘት ይኖርባቸዋል ።
👍9🤔4
👍14👎10
ለባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪዎች ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ ፡

ውድ የባሸዋም ተማሪዎች እና ወላጆች እንኳን ለ2017ዓም የትምህርት ዘመን እና የትምህርት ቤታችን 25ኛ አመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡ እያልን ከዚህ በታች ባለው መመሪያ መሰረት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን ።

የ2017ዓም ትምህርት ከኬጂ (ቅድመ አንደኛ) እስከ 12ኛ ክፍል ነገ ረቡዕ መስከረም 8/2017ዓም ይጀምራል ።

መስከረም 8 - 10/2017ዓም ትምህርት የሚሰጠው ለግማሽ ቀን በመሆኑ ወላጆች ልጆቻችሁን ከቀኑ 6:40 ትምህርት ቤት በመምጣት እንድትወስዱ እናሳስባለን ።

ትምህርት ከጠዋቱ 2:30 ስለሚጀመር ተማሪዎች ቀደም ብለው ከጠዋቱ 2:00 በፊት ትምህርት ቤት መገኘት ይኖርባቸዋል ።

ከኬጂ( ቅድመ አንደኛ) እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፡ ወላጆች ትምህርት ቤት በመምጣት ልጅዎን በየክፍሉ ለተመደቡ ረዳት መምህራን በአግባቡ እንዲያስረክቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

ከቅድመ አንደኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ምሳ እቃ እና ቦርሳቸው ላይ ስማቸው መፃፍ አለበት ።

ሁሉም ተማሪዎች የተማሪ የደንብ ልብስ Uniform አሟልተው መምጣት አለባቸው ፡ ዩኒፎርም ሳይለብስ የሚመጣ ተማሪ ትምህርት ቤት ውስጥ የማናስገባ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ።

ማንኛውም ተማሪ ከመስከረም 9/2017ዓም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት የሚገባው የተማሪ መታወቂያ በማሳየት በመሆኑ ልጅዎ መታወቂያ ይዞ(ዛ) ወደ ትምህርት ቤት መምጣቱን(ቷን) እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን ።

ጀማሪ ተማሪዎች መታወቂያቸውን አንገታቸው ላይ ማንጠልጠል አለባቸው ። ወላጆች ትምህርት ቤት ሲመጡ የህፃኑን(ኗን) መታወቂያ መያዝ አለባቸው ።

የትምህርት ቤት የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ተጠቃሚ ወላጆች ወይም መጠቀም የምትፈልጉ ፡ ረቡዕ መስከረም 8/2017ዓም አገልግሎት መስጠት ስለምንጀምር፡ መጠቀም የምትፈልጉ መስከረም 8 እና 9/2017ዓም በአካል በመምጣት ፋይናንስ ክፍል እንድትመዘገቡ እና ክፍያ እንድትፈፅሙ እናሳስባለን።

ባሸዋም ትምህርት ቤት ፡ "ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ ነን"።

መስከረም 7/2017ዓም
👍18👏7
👍16👎3
👎17👍15
👍18👎17
👎23👍19
👎26👍24