ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
28.2K subscribers
302 photos
10 videos
85 files
2.48K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
Audio
የአል አጅዊበቱል ሙፊዳ ኪታብ ደርስ ክፍል 10 ከቢዳዓ ሰዎች በሚያስጠነቅቁበት ጊዜ መልካም ስራውን መጥቀስ ያስፈልጋል ወይ ለሚለው ጥያቄ ከተሰጠ መልስ የቀጠለ
Live stream finished (1 hour)
Audio
የከሽፉ ሹቡሃት ኪታብ ደርስ ክፍላ 03 የቀብር አምላኪዎችና ነብዩ ከመላካቸው በፊት የነበሩት አጋሪያን የሚገናኙበት ነጥብ
📢አስደሳች ዜና

ልዩ የኮርስ ዝግጅት

🗓 ከቀን ሐምሌ 20 እለተ ሀሙስ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ልዩ የኮርስ ዝግጅት

🕰 ከመግሪብ ጀምሮ…

በወንድማችን ዑስታዝ ሻኪር ሱልጣን(ሀፊዘሁላህ)

ኮርስ የሚሰጥበት ኪታብ

الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله السلطي حفظه الله
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ስልጢ ያዘጋጁት መዳሂሉል ሸይጧን
የሚለው ኪታብ ነው

📢በፍጥነት ይሰራጭ፣ በስልክም ተደዋውላችሁ ላልደረሰው በማድረስ በጊዜ እንገኝ #Share_ሼር  ይደረግ

ማሳሰቢያ:-
ኪታቡ እዚያው መስጅድ ይገኛል


አድራሻ:-
🕌 ቦታው፦ ከቡታጅራ ወደ ስልጢ መውጫ (ሴራና አካዳሚ) አካባቢ ወደ ፀሀይ መውጫ ገባ ብሎ
#ቡታጅራ ገተማ መንደር/ቀጠና

🔎 ለተጨማሪ መረጃ
የኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድ አቅጣጫ (location map) በካርታ ለማየት/ለማወቅ የሚያስችል ሊንክ ነው።
ተጫኑት -ባረከላሁፊኩም-
👇👇👇

https://maps.app.goo.gl/Xy9umwAkJsLpkiYF7

📲 ለበለጠ መረጃ፦
Tel:
0911117603 አንዋር አብዶ
0927096517 ሻፊ ዐሊዩ

وبــلله التــــــوفــيق والســــلام عليـــكم ورحــــمةالله وبــــركاتـــه

የኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድና መድረሳ ጀማዕ የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/butajira_akababi
👉 ሺዓዎችና ዓሹራእ

ዓሹራእ ሲታወስ በዋነኝነት የሚታወሰው የሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ከርበላእ ላይ መገደል ነው ። ሑሰይን ከርበላእ ላይ የተገደለው ሙሐረም 10/61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር ።
የሑሴይን መገደል መንስኤ የነበረው ለየዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ሙባየዓ አላደርግም ማለቱ ነበር ። በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሐሰን ኢብኑ ዐልይ ለሙዓዊያ የመሪነቱን ቦታ መልቀቁ ( ተናዙል ) ማድረጉ ነው ። ዑስማን ኢብኑ ዐፋን በዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲይ የተንኮል መረብ ከተገደለ በኋላ ዐልይ የኸሊፋነቱን ቦታ በሶሓቦች ግፊትና ውትወታ ተረክቦ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ሙዓዊያ የሻም ዋሊ ( አስተዳደር ) ነበርና ለዐልይ የዑስማን ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ ያቀርባል ። ዐልይም መጀመሪያ ሙባየዓ ማድረግ እንዳለበትና ሁኔታዎች ከተረጋጉና ገዳዮቹ በህዝብ ውስጥ ተደብቀው ስላሉ መለየት በሚቻልበት ወቅት ለፍርድ እንደሚቀርቡ ይገልፅለታል ። ሙዓዊያም ምናልባት መዲና ያለው ሁኔታ ካልተረጋጋና አቅም ከሌለው ሀላፊነቱን ለሱ እንዲሰጠውና እሱ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ በሚችልበት አቅምና አቋም ላይ መኖሩን በመግለፅ ይህ ሳይሆን ሙባየዓ እንደማያደርግ ለዐልይ ይገልፅለታል ። ይህ አለመግባባት ሳይፈታ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል ኻሪጂ ይገደላል ። በቦታው ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ሙባየዓ ተደረገለት ኸሊፋም ሆነ ። ነገር ግን ከሙዓዊያ ጋር የነበረው አለመግባባት በቀላሉ የሚፈታ አልነበረምና ሐሰን ለሙዓዊያ መሪነቱን አስረከበ ።
ይህ የሐሰን ተግባር ለሑሰይን አላስደሰተውም ። ነገር ግን ታላቁ ነውና ምንም ማድረግ አልቻለም ለሙዓዊያ ሙባየዓ አደረግ ። በዚህም ሀገር ሰላም ሆነ ሙስሊሞች ኡፈይ አሉ ። በዚህ ሁኔታ ነገሮች እየሄዱ እያሉ ሙዓዊያ መሪነቱን ለልጁ የዚድ አሳልፎ ሰጠ ። የዊላያት መሪዎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም ታዋቂ ሶሓባዎች ለልጁ ሙባየዓ እንዲያደርጉ ጠየቀ ። ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ለየዚድ ሙባየዓ እንደማያደርግ ግልፅ አደረገ ። በዚህን ጊዜ የዚድ ለመዲናው አስተዳዳሪ ከሑሰይን ሙባየዓ እንዲቀበልለት ትእዛዝ አስተላለፈ ። ሑሰይንም ሁኔታው ስላላማረው መዲናን ትቶ ወደ መካ ተሰደደ ። የዚህን ጊዜ ኢራቅ ያሉ የሙዓዊያ ተቋዋሚ ፋርሳዊያን ( ሺዓዎች ) ሑሰይንን ወደ እነርሱ እንዲመጣና መሪያቸው እንዲሆን መወትወት ጀመሩ ። ሑሰይንም ለመውጣት አሰበ የኩፋ ሰዎች በየቀኑ ወደ ሑሰይን ይልካሉ ። ይህ ሁኔታ ያላማረው የዚድ የሑሰይንን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረ ።
ሑሰይንም የአጎቱን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዓቂልን ወደ ኩፋ ሄዶ ነገሮችን እንዲያጣራ ላከው ። ሙስሊም ኩፋ እንደደረሰ በጣም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት ለሑሰይን ሙባየዓ አደረጉ ። የዚህን ጊዜ ለሑሰይን መምጣት እንዳለበትና ሙባየዓ እንደተደረገለት ገልፆ ላከለት ።
የዚድ የሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ኩፋ መግባትና ሰዎች ( ሺዓዎች ) ለሑሰይን ሙባየዓ እያደረጉ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድን የበስራና የኩፋ መሪ አድርጎ በመሾም ወደ ኩፋ እንዲሄድና የሆነውን ነገር አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ላከው ። ወደ መዲናና መካ የሚገኙ ትላልቅ ሶሓቦችም ሑሰይንን ወደ ኩፋ እንዳይወጣ እንዲመክሩትና ሙባየዓ እንዲያደርግ እንዲነግሩት መልእክት ላከ ።
ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ኩፋ እንደመጣ ለወታደሮች በጣም ከፍተኛ ስጦታ ሰጠ ። ታዋቂ ሰዎችን አስጠርቶ ከሱ ጋር እንዲሆኑ የፈለጉት ነገር እንደሚያደርግላቸው ካልሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ገለፀላቸው ። ማንኛውም ሰው አዲስ ሰው እንዳያስጠጋ አስጠግቶ የተገኘ እርምጃ እንደሚወስድበት ተናገረ ። ቀጥሎ በስራና ኩፋ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘዘ ። ማንኛውም አዲስ ሰው ከተገኘ ወደርሱ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ ። ቀጥሎ አሉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎችን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዝ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት እንዲያደርሱትና ከሱ ጎን የቆሙ ሰዎችን እንዲለዩለት አደረገ ።
ወዲያውኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት ቦታ ጦቀሙት ። ወደ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ጉዞ ቀጠለ ደረሰበትም ። ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል የተከሰተው ነገር ሲያይ ማመን አቃተው እነዚያ ቃል የገቡና ሑሰይንን እንዲያስመጣ ያዘዙት ሺዓዎች ክደውታል ። ዑበይዱላህ እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው አላደረገውም ተገደለ ። የሚቀጥለው ስራ የሑሰይንን መምጣት መጠበቅ ነው ። በተለያዩ መንገዶች ጠባቂ አደረገ ። ስለሙስሊም መገደል እንዳይደርሰው አደረገ ።
ሑሰይን ከመካ ወደ ኩፋ እንቅስቃሴ ጀመረ ። ትላልቅ ሶሓቦች እንዳይሄድ ከለከሉት ። ከእነዚህ ውስጥ : –
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር
– ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላሂ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር
– አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ
እና ሌሎችም ግን አልተሳካም ።
የሑሰይን መንቀሳቀስ ተሰማ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ 1000 ፈረሰኛ እሱን ለመጠባበቅ ላከ ። ሌላ ጦር ደግሞ ዑመር ኢብኑ ሰዕድን መሪ አድርጎ ላከ ። ለዚህ ጦር እጅ ከሰጠ ይዘው እንዲያቀርቡት ካልሆነ እንዲገሉት ትእዛዝ ሰጠ ። ሑሰይን ወደ ኩፋ በቀረበ ጊዜ የአጎቱ ልጅ መገደል ፣ የኩፋ ሰዎች ከዑበይዱላህ ኢብኑ የዚድ ጎን መቆማቸውንና የአጎቱን ልጅና እሱንም እንደካዱዋቸው የሙስሊም ኢብኑ ዑቅባ ደጋፊዎች ሀኒእ ኢብኑ ዑርዋን ጨምሮ ሁሉም መገደላቸውን ሰማ ። ብዙም ሳይቆይ ከዑመር ኢብኑ ሰዕድ ጦር ጋር ተገናኘ ። እነዚያ ወትውተው ከመካ ያስወጡት ሺዓዎች አዘጋጅተው ለጅብ ሰጥተውታል ።
የዚህን ጊዜ ከሱ ጋር ያሉትን ማስጨረስ አልፈለገም ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ ሶስት አማራጭ ለዑመር ኢብኑ ሰዕድ አቀረበለት ። አማራጮቹ የሚከተሉት ነበሩ : –
– እንዲተውትና ወደ መካ እንዲመለስ
– ወደ ድንበር ሄዶ እንደማንኛውም ሙስሊም ድንበር እንዲጠብቅ ( ሀገር ጠባቂ ወታደር እንዲሆን )
– ወደ ሻም ሄዶ ከየዚድ ጋር ተነጋግሮ እንዲግባባ የሚል ነበር ።
ዑመር ይህን ሲሰማ በጣም ደስ ብሎት ለዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ላከለት ። ይሁን እንጂ በሙስሊሞች ደም የሚታጠበው ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ እጅ ካልሰጠ እንዲገድለው አዘዘ ። ዑመር ለሑሰይን እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው ሑሰይንም አይደረግም አለ ። በሙሐረም 10 ኛ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጅሪያ ሺዓዎች ከመካ መሪያችን ሁን ብለው አውጥተው ከርበላእ ላይ እንዲገደል አደረጉት ።
ይህን ቀን ነው ሺዓዎች ከርበላእ ላይ ራቁታቸውን ሆነው ራሳቸው እየገረፉ ለሑሰይን ሞት ሐዘን እያሉ ያ ሑሰይን ብለው የሚጮኹት ።

https://t.me/bahruteka
🛑 ሀይላኛ ሙቀት የጀሀነም ትንፋሽ ነው ።

عن أبي هريرة – رضي الله عنه – عن النبي – صلى الله عليه وسلم – قال : 

« إِذَا اشْتَدَّ الحَرُّ فَأَبْرِدُوا بِالصَّلاَةِ، فَإِنَّ شِدَّةَ الحَرِّ مِنْ فَيْحِ جَهَنَّمَ، وَاشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ: يَا رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ: نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ، وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَهُوَ أَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ »

متفق عليه

🔹 አቡ ሁረይራ – ረዲየላሁ ዐንሁ – ከአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ይዞ ባወራው ሐዲስ እንዲህ ይላል :–

" ሙቀት በበረታ ጊዜ ሶላትን እስኪቀዘቅዝ አቆዩ, ምክንያቱም የሙቀት መበርታት የጀሀነም ትንፋሽ ነውና ። ( የጀሀነም ) እሳት ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች ። እንዲህም አለችም : – ጌታዬ ሆይ ከፊሌ ከፊሌን በልቶታል ። ሁለቴ እንድትተነፍስ ተፈቀደላት ። አንደኛው በበጋ ሌላኛው በክረምት ። ይህም የምታገኙት ሀይለኛ ሙቀትና ሀይለኛ ቅዝቃዜ ( ዘምኸሪር የሚባለው) ነው "።

↪️ በተለያዩ የአውሮፓና የዐረብ ሀገራት ያላችሁ ወንድምና እህቶች አሁን ያለንበት ጊዜ ሀይለኛ የሙቀት ጊዜ ነው ። በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎችና የአየር ሁኔታው ተመሳሳይ የሆኑ ሀገራት ላይ ደግሞ ክረምትና የሀይለኛ ቅዝቃዜ ጊዜ ነው ። ከላይ እንዳየነው ሁለቱም የጀሀነም እስትንፋሶች ናቸው ። ይህ የጀሀነም እስትንፋስ ምን ያክል ጊዜ ቀንሶ እንደሆነ አላህ ነው የሚያውቀው ። ሙቀት በበዛ ጊዜ እንዴት እንደሚጨንቅና ትንፋሽ እንደሚያጥር ሰውነት በላብ ውሀ እንደሚጥለቀለቅ ለሚያይ ሰው ይህ እስትንፋሱ ከሆነ የጀሀነም እሳት እንዴት ይሆን ብሎ አላህን ከጀሀነም እሳት እንዲጠብቀው እንዲለምነው ያደርገዋል ። ልክ እንደዚሁ ሀይለኛ ቅዝቃዜም ሀገራችን ላይ ደብረብርሀንና የመሳሰሉ አካባቢዮች ቧንቧ በረዶ ሆኖ ፀሀይ ወጥታ እንኳን አቅም አጥታ በረዶ ሳይቀልጥ ዙህር ሲደርስ ያየ እንዲሁም ሳውዲ የተለያየ ቦታ ላይ ያለውን ቅዝቃዜ ያየ የአኼራው ምን አይነት ይሆን ብሎ ወደ አላህ ይጠጋል ።
ስለዚህ ወንድምና እህቶች ከእነዚህ የሙቀትና የቅዝቃዜ ወቅቶች ለአኼራችን ስንቅ ልንሰንቅባቸው ይገባል ። ውዱእ ስናደርግ ገላችን ሲቆራረጥ ስናይ የጀሀነም ሰዎችን ልናስታውስና አላህን ልንለምን ግድ ይላል ። ሌላው ክረምትና በጋ አላህ የሚቀያይራቸው ወቅቶች ስለሆኑ ከመሳደብ መጠንቀቅ አለብን ።

አላህ በእዝነቱ ከጀሀነም ሙቀትና ቅዝቃዜ ይጠብቀን ።

https://t.me/bahruteka
🚫 ከሰጋጆች ስህተቶች
❨¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯❩


ብዙ አባቶችና ወንድሞች ላይ ከሶላት ጋር የተገናኙ መስጂድ ሲገባ ጀምሮ በጀማዓም ይሁን በግል በሚሰገድበት ጊዜ የሚስተዋሉ ስህተቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ዱዓቶችና ኡስታዞችም ጭምሮ የሚሰሩዋቸው ይገኙበታልትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግን ትኩረት ያጡ ሆነው ይስተዋላሉ። ከእነዚህ ሶላት ውስጥ ከሚታዩና ልናስተካክላቸው ከሚገቡ ስህተቶች ውስጥ፦
❶ኛ በሶላት ውስጥ አለመረጋጋት
♻️ ይህ የሶላት ሩክን ሆኖ ሳለ ብዙዎች ጋር የሚታይ ስህተት ነው። ሩኩዕ ላይ፣ ከሩኩዕ ቀና በሚባልበት ጊዜ (ኢዕቲዳል) ላይ፣ ስጁድ ላይ፣ በስጁድ መካከል መቀመጥ ላይና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ መረጋጋት ግዴታ ነው። ካልሆነ ሶላት ያበላሻል።

❷ኛ እንቅስቃሴ ማብዛት
↪️ ይህ ኹሹዕ ከማጣት የሚመጣ ከሶላቱ ጋር በሚገናኝ ጉዳይና ሸሪዓዊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በጣም የተጠላ ነው።

❸ኛ ኢማምን መሽቀዳደም
♻️ ኢማምን መከተል ግዴታ ሲሆን እሱን መሽቀዳደምና ቀድሞ መነሳት፣ ሩኩዕ ማድረግ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለትና ከስጁድ መነሳት የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ሶላት ያበላሻሉ።

❹ኛ ኢማሙ የሁለተኛውን ተስሊም ሳይጨርስ ያመለጠን ለሞሙላት መነሳት

❺ኛ በንያ ድምፅ አውጥቶ መናገር
ንያ ቦታው ቀልብ ስለሆነ ድምፅ አውጥቶ መናገር አያስፈልግም

❻ኛ መስጂድ ገብቶ ኢቃም እስከሚባል ቆሞ መጠበቅ
♻️ አዛን ከተባለ በኋላ መስጂድ የገባ ሰው ወዲያውኑ ሁለት ረካዓ መስገድ ይኖርበታል። ነብዩ ﷺ በሁለት አዛኖች (በአዛንና ኢቃም መካከል ሶላት አለ) ስላሉ ቆሞ መጠበቅ አያስፈልግም። ቀብልያ ያለው ሶላት ሆነም አልሆነም ለተሒየቲል መስጂድ ለሱነተል ውዱእና ለሱናውም ይሆንለታል።

❼ኛ መስጂድ ገብቶ ኢማሙ ስጁድ ላይ ወይም ተሸሁድ ላይ ከሆነ ቆሞ መጠበቅ
ይህም በጣም ስህተት ነው። ኢማሙ ባለበት ሁኔታ ተከትሎ ያመለጠውን ኢማሙ ሲጨርስ ሞሙላት ነው ያለበት።

❽ኛ በስጁድና ሩኩዕ ላይ ቁርኣን መቅራት

ኛ አይንን ግራና ቀኝ ወይም ወደ ሰማይ ማድረግ
↪️ ሶላት በምንስግድበት ጊዜ ወደ ስጁድ ማድረጊያ ቦታ ማየት ነው የሚያስፈልገው። ሸይጣን ሶላታችንን እንዳይሰርቀን!

❿ኛ በሁለት እግሮች ተረከዝ ላይ ቁጭ ብሎ ስጁድ ላይ ሁለት እጆችን እስከ ክርን መሬት ላይ መዘርጋት

⓫ኛ በሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ማለፍ (ሶላት ማቋረጥ)

⓬ኛ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ሆኖ ደርሶ ተክቢረተል ኢሕራም ሳያደርጉ ጎንበስ ማለት
⓭ኛ ሶላት ላይ ዐይኖችን መጨፈን
⓮ኛ በስጁድ ላይ የእግር ጣቶችን ማንሳት
⓯ኛ ስጁድ ሲያደርግ መሬቱን መሳም
⓰ኛ ሶላት ላይ ሲቆም ቀኝ እጅ በግራ ላይ አድርጎ አንገት ስር ማውጣት
⓱ ስጁድ ሲወረድና ከስጁድ ቀና ሲል ሁለት እጆችን ማንሳት
⓲ኛ በግንባር፣ በሁለት መዳፎችና፣ በሁለት ጉልበቶችና በሁለት አውራ ጣቶች (በሰባት አካላት) ስጁድ አለመውረድ
ሴቶች ሽቶ ተቀብተው መስጂድ መምጣት
ሴቶች በሚሰግዱበት ጊዜ እግራቸውን አለመሸፈን

♻️ እነዚህ ከብዙ ስህተቶች ጥቂቶቹ ናኛቸው ራሴንና አማኞችን ለማስታወስ እነዚህን ጠቀስኩ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።

https://t.me/bahruteka
ሙብተዲዕን ያዳመጠ የአላህ ጥበቃ ይነሳበታል

قال محمد بن النضر الحارثي – رحمه الله :-
"من أصغى سمعه إلى صاحب بدعة، وهو يعلم أنه صاحب بدعة، نزعت منه العصمة، ووكل إلى نفسه".
الإبانة (471)

🔹 መሐመድ ኢብኑ ነድር አል ሓሪሲ – ረሒመሁላሁ – የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል፦
"ወደ ቢዳዓ ባለቤት የቢዳዓ ባልተቤት መሆኑን እያወቀ ጆሮውን ሰጥቶ ያዳመጠ የአላህ ጥበቃ ከሱ ላይ ይነሳል። ወደራሱም ይጠጋል"።

↪️ አብዛኛዎች ሰለፍዮች ከቢዳዓ ባልተቤቶች መራቅ ሲባል በአካል አለመገናኘት ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ከሙብተዲዕ መራቅ ሲባል በአካል መራቅን፣ ትምህርቶቹን በማንኛውም መንገድ አለማዳመጥን፣ ፁሑፎቹን አለማንበብን፣ ከግሩፑም ይሁን ከቻናሉ መራቅን ያካትታል።
ይሁን እንጂ ብዙ ሰለፍዮች የቢዳዓ ባልተቤቶች ናቸው ብለው የሀገራችን ዑለሞች ያስጠነቀቁዋቸውን ሰዎች ቻናል ተቀላቅለው የተለያዩ ፁሑፎችን ሲያነቡና ድምፆችንም ሲሰሙ ይታያል ለምን ሲባሉ ምን እንደሚል ለመስማት ነው ይላሉ!!!።
♻️ ይህ ፍፁም የተሳሳተ ሀሳብ ነው። ምክንያቱም ሀገራችን ውስጥ ያሉ ሙኻሊፎች የሚያሰራጩዋቸው ሹብሀዎች እራሳቸው ከትክክለኛ አቋም እንዲንሸራተቱ ያደረጉዋቸው ሹብሀዎች ናቸውበመሆኑም በፍፁም ለእንደዚህ አይነት የሸይጣን ጉትጎታ መንገድ መክፈት አያስፈልግም። በመረጃ ያወቅነውን ዐቂዳና ሚንሀጃችን ካፒታላችን ነውና እንጠብቀው።

https://t.me/bahruteka
የምን ፕራንክ ነው!? እንዴ!!!
መሰልጠን እና መሰይጠን ለዩ

       ❪„„„„„„„„„„„„„„„„„❫

ባለንበት የተደበላለቀ ዘመን የጠራ እውቀት ላይ ሆኖ ዲኑን እና ክብሩን የጠበቀ ታድሏል።

♻️ በአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን ሰው busy ካደረጉት የምዕራባውያን ኮተቶች መካከል “ፕራንክ” ❮prank❯ የሚሉት ነው።
➲ Prank ማለት ራሳቸው ምዕራባውያን እንደሚከተለው ይተረጉሙታል፦
«Prank is a mischievous trick or practical joke.»
ፕራንክ ማለት የተሳሳተ ተንኮል ወይም ተግባራዊ ቀልድ ነው።


ይህ የተሳሳተ ተንኮል ሰዎች ባለወቁበት መልኩ የሚያስደነግጥ ነገር ይተገበርባቸዋል። ከደነገጡ ብሎም ካለቀሱ በኋላ prank ይባላሉ። በዚህ ተግባር በርካታ አላስፈላጊ ኮተቶች አሉ።

↪️ ሙስሊሞች በዚህ ተግባር መሳተፍ የለባቸውም በፍፁም አንዳንድ ሙስሊሞች ተሳትፈውበታል። የድሮ ፍቅረኛዬ ምናምን እያሉ ወንደላቸውን በሚዲያ የበተኑ ሙስሊም ሴቶችን  አስተውያለሁ። ካፊር ሴት እያቀፈ የሚጃጃል ወንድም ተመልክቻለሁ። ሌሎችም

ስለዚህ ከዚህ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አስፈላጊ ነው። የዚህን መሰል ፈሳድ ካፊሮች ሲያመጡ መከተል እነሱን ከመወዳጀት  ነው። ይህ ደግሞ አደጋ መሆኑ ግለሰፅ ነው።

«وَمَنْ يَتَوَلَّهُمْ مِنْكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ»
[المائدة: 51]
ከእናንተ የተወደጃቸው ሁሉ እኮ እርሱ ከእነርሱ ነው❞

♻️ ነብዩ ﷺ ይህን አይነት መመሳሰል በግልጽ ማውገዛቸው ከማናችንም የሚሰወር አይመስለኝም።

عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ:- قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:- "مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ".
(صحيح أبي داود)
حسنه الألباني (3401)


ኢብኑ ዑመር  ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፦
“ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው”
[ሶሂህ አቡ ዳውድ]

ፕራንክ የምዕራባውያን ፍብርክ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ተግባር መሰለፍ ከእነሱ መመሳሰል ነው። ሲጀመር በውስጡ ያሉ ፈሳዶች ❪ጥፋቶች❫ ፕራንክ መራቅ ካሉብን ተግባራት መሆኑን ይጠቁሙናል።

ሌላ አንድ ሀዲስ እንጨምር፦
«عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:- ((لَتَتْبَعُنَّ سَنَنَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ شِبْرًا شِبْرًا وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ دَخَلُوا جُحْرَ ضَبٍّ تَبِعْتُمُوهُمْ)). قُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى قَالَ:- ((فَمَنْ)).»
رواه البخار ٧٣٢٠

↪️ አብደላህ ብን ኹድሪይ እንዳስተላለፈው ነብዩ ﷺ የሚከተለውንብለዋል፦
“ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የአርጃኖ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቦጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!”
  [ቡኻሪ፡ 7320]

ከዚህ ሀዲስ አንፃር የት ነን!? በፕራንክ ጉዳይ busy የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ሀዲስ ልትገሰፁ ይገባል። እስከመቼ ይሁዳ እና ነሷራ ተከትለን እንጓዛለን!? ደግሞ ሙሉዕ የሆነ ዲን እያለን!!! እስልምና ያጓደለው ምንም የለም።  እስልምና ያልስተማረው ካለ ካለና ከሰራነው በትክክል ጥመት ነው። በጥመት ተግባር መሳተፋችንንም ማወቅ አለብን። ነገሮችን ቀለል ማድረግ ትተን ከፕራንክ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አለብን።

↪️ በነገራችን ላይ በዚህ ፕራንክ በሚሉት ኮተት ብዙ ጊዜ የሚከሰቱበት ሁለት ተግባሮች አሉ እነሱም፦
❶ኛ ሰዎችን ማሸበር ወይም ማስደንገጥ እና
❷ኛ በውሸት ቅንብር ማሳቅ ነው።


☑️ እነዚህ ሁለት ተግባራት ደግሞ በእስልምና የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃዎችንእንመልከት፦

የመጀመሪያውን በተመለከተ ሙስሊም ሌላ ሙስሊምን ማስጨነቅ ወይም ማሸበር አይፈቅድም፦

عن عبدالرحمن بن أبي ليلى قال:-  قال رسول الله ﷺ "لا يحلُّ لمسلمٍ أن يروِّعَ مسلمًا"
       صححه الإمام  الألباني 
         سنن أبي داود


አብዱረህማን ኢብኑ አቢ ሌይላ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"አንድ ሙስሊም ሙስሊምን ማሸበር አይፈቀድለትም"
ሱነን አቢ ዳውድ
ኢማም አልባኒ ሶሂህ ብለውታል


ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ»

"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"

አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ
ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡


በሌላ በኩል ደግሞ የሚከተለውን ሀዲስ እናገኛለን፦
عن أبي أمامة رضي الله عنه قال:- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم:-
"أنا زعيم ببيت في ربض الجنة لمن ترك المراء وإن كان محقا، وببيت في وسط الجنة لمن ترك الكذب وإن كان مازحا، وببيت في أعلى الجنة لمن حسن خلقه".
 سنن أبي داود
وحسنه الألباني.


♻️ አቡ ኡማማህ ረዲየሏሁ ዐንሁም እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፡-
"እኔ እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን ለተወ ሰው በጀነት ዙሪያ ወይም ዳርቻ ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ስነ ምግባሩ ላማረለት ደግሞ በጀነት የላይኛው ክፍል ውስጥ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።"
ሱነን አቢ ዳውድ
አል-አልባኒ ሀሰን ብለውታል።


➲ በዚህ ሀዲስ ❸ ነጥቦች ጎልተው ተጠቅሰዋል።
❶ኛ ክርክር
❷ኛ ውሸት
❸ኛ ስነ-ምግባር

ውዱ ነብይ ﷺቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።❞ በማለት በቀልዳችን መዋሸት እንደሌለብን አስረድተዋል። ስለዚህ ውድ እህት ወንድሞች በፕራንክ ቀልድ የሚደረጉ ውሸቶች ትክክል አይደሉም። እኛም ተጠንቅቀን ሌሎችንም ልናስጠነቅቅ ይገባል።

📝 አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
Live stream scheduled for
Live stream finished (53 minutes)
ሰዎችን በጭፍን አትከተል!!
—————
ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው።

ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ነው።
ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል።

ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

«ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67

ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል። በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!።

በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!።

በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!።

ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: -
ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” ረዱል ጀዋብ 54

»» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!።
ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!።
አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!! የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!!

✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

#join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
  👉 ቢዳዓ ቀልብን ሲያቃጥል ከእሳት ነበልባል ይበልጣል ።

قال الإمام ابن بطة   — رحمه الله —
 
" فَاللَّهَ اللَّهَ مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ, لا يَحْمِلَنَّ أَحَدًا مِنْكُمْ حُسْنُ ظَنِّهِ بِنَفْسِهِ, وَمَا عَهِدَهُ مِنْ مَعْرِفَتِهِ بِصِحَّةِ مَذْهَبِهِ عَلَى الْمُخَاطَرَةِ بِدِينِهِ فِي مُجَالَسَةِ بَعْضِ أَهْلِ هَذِهِ الْأَهْوَاءِ, فَيَقُول: أُدَاخِلُهُ لأُنَاظِرَهُ, أَوْ لأَسْتَخْرِجَ مِنْهُ مَذْهَبَهُ, فَإِنَّهُمْ أَشَدُّ فِتْنَةً مِنَ الدَّجَّالِ, وَكَلامُهُمْ أَلْصَقُ مِنَ الْجَرَبِ, وَأَحْرَقُ لِلْقُلُوبِ مِنَ اللَّهَبِ, وَلَقَدْ رَأَيْتُ جَمَاعَةً مِنَ النَّاسِ كَانُوا يَلْعَنُونَهُمْ, وَيَسُبُّونَهُمْ, فَجَالَسُوهُمْ عَلَى سَبِيلِ الإِنْكَارِ, وَالرَّدِّ عَلَيْهِمْ, فَمَا زَالَتْ بِهِمُ الْمُبَاسَطَةُ وَخَفْيُ الْمَكْرِ, وَدَقِيقُ الْكُفْرِ حَتَّى صَبَوْا إِلَيْهِمْ ".

الإبانة ( 2/470 )

🔹 ታላቁ የሰለፍ ሊቅ የሆነው ኢማም ኢብኑ በጧህ – ረሒመሁላሁ – ስለቢዳዓ አደገኝነት አስመልክቶ እንዲህ ይላል : –

" ሙስሊሞች ሆይ በአላህ አስጠነቅቃችኋለሁ ከናንተ ውስጥ አንዳችሁንም በራሱ ላይ ያለው መልካም ጥርጣሬና የመዝሀቡ ( የዐቂዳው ) ትክክለኛነት ማወቁ እነዚያን የስሜት ( ቢዳዓ ) ባልተቤቶችን በመቀማመጥ ዲኑን አደጋ ላይ እንዲጥል እንዳያደርገው ።
ወደርሱ ሄጄ አናግረዋለሁ ወይም ውስጡ ያለውን ( መጥፎ ዐቂዳ) መዝሀቡን አሰወጣለታለሁ እንዳይል ። እነርሱ ፈተናቸው ከደጃል ይብሳል ። ንግግራቸው ከቆዳ በሽታ የበለጠ ይጣበቃል ። ልብን ለማቃጠል ከእሳት ነበልባል ይበልጣል ። ብዙ ሲሰድቡዋቸውና ሲረግሙዋቸው የነበሩ ሰዎችን አይቻለሁ ። ረድ ልናደርግባቸውና ስራቸውን ኢንካር ልናደርግ ነው በሚል ተቀማመጡዋቸው ። በዚህ መልኩ እያሰፉ ሄዱ የተደበቀው ሴራቸውና ረቂቅ የሆነው ኩፍራቸው ሳይገባቸው እሳካፈሰሱባቸው ድረስ "።

https://t.me/bahruteka
Audio
የአል ኢርሻድ ኪታብ ደርስ ክፍል 66 አራተኛው አስል አል ኢማን ቢሩሱል ( በሩሱሎች ማመን)
Audio
አል ኡሱሉ አስ–ሲታ ኪታብ ደርስ ክፍል 07 አምስተኛው መሰረታዊ ነጥብ በአላህ ወልዮችና በሸይጧን ወልዮች መካከል ያለው ልዩነት
ጀርህ_እና_ተዕዲል_ምግብ_ውስጥ_እንደሚጨመር_ጨው_ዓይነት_ነውን.pdf
566.9 KB
አዲስ መፅሐፍ

"ጀርህ እና ተዕዲል ምግብ ውስጥ እንደሚጨመር ጨው ዓይነት ነውን"

#ጀርህ_እና_ተዕዲል_በኢኽዋን_አልሙስሊሚን_ጎዳና_ተፅእኖ_ያደረባቸው_አንዳንድ_ግዴለሽ_ሰዎች_እንደሚሞግቱት_ምግብ_ውስጥ_የሚጨመር_ጨው_አይነት_ሳይሆን_አላህ_ሸሪዓውን_ለመጠበቅ_ሰበብ_ካደረጋቸው_እና_ከነሲሀ_(ከዲናዊ_ምክክር)_መሆኑ_የሱና_ዑለሞች_ስምምነት_ነው::

በሸይኽ ሑሴን ብን ሙሐመድ አስስልጤ ተዘጋጅቶ

በአቡ ዓብዱልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ወደ አማረኛ የተመለሰ

በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq