ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
28.9K subscribers
325 photos
12 videos
86 files
2.55K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
👇
ልዩ የኮርስ ዝግጅት በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
:
🕰የፊታችን እሁድ ሐምሌ 2/2015 ከጠዋቱ 3:00 ሰኣት ጀምሮ በእለቱ የሚጠናቀቅ ልዩ ኮርስ እንዳያመልጦት!!

من كتاب عيسى ـ عليه السلام ـ في ميزان الإسلام

لفضيلة الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله السلطي حفظه الله
ኮርሱ የሚሰጥበት ኪታብ
"ዒሳ - ዐለይሂ ሰላም- በኢስላም ሚዛን" ከሚለው ኪታብ
ما أسباب الارتداد عن دين الإسلام؟
"ሰዎች ከእስልምና እምነት ወጥተው ወደ ኩፍር የሚሄዱበት ምክንያት ምንድነው?"
የሚለውን ክፍል ይሆናል

አዘጋጅ:- ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ)

ኮርስ ሰጪ:- በኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ) ሀፊዘሁላህ

📖ኮርስ የሚሰጥበት ኪታብ ቦታው ላይ ይገኛል

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ አለምባንክ አደባባይ አካባቢ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊትለፊት ከዱና ዳቦ ጀርባ 2ኛው ቂያስ ላይ ያገኙናል
📞Tel:+251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
Audio
የአል ኢርሻድ ኪታብ ደርስ ክፍል 64 ሁለተኛው መሰረታዊ ነጥብ በመላኢካዎች ማመን
يقول إبن بطة – رحمه الله –

" ومن السنة مجانبة كل من اعتقد شيئاً مما ذكرناه
(أي: من البدع)، وهجرانه، والمقت له، وهجران من والاه، ونصره، وذب عنه، وصاحبه، وإن كان الفاعل لذلك يظهر السنّة"

الإبانة : ص (282)


🔹 ኢብኑ በጣህ የተባለ ዓሊም – ረሒመሁላሁ –እንዲህ ይላል፦

"ከጠቀስነው ነገር አንዳችም ዐቂዳ አድርጎ የያዘ (ቢዳዐን) እሱን ማኩረፍ (መራቅ)፣ መጥላት፣ የተወዳጀውን መራቅና ማኩረፍ፣ የረዳውን፣ ለሱ ጥብቅና የቆመን፣ ጓደኛ ያደረገውን፣ ይህን የሚያደርገው ሱና ላይ ነኝ ቢል እንኳን ማኩረፍ ከሱና ጭምርት ነው"።

http://t.me/bahruteka
Forwarded from أبو عبيدة بحرو تكا
الحاجة_إلى_الجرح_والتعديل_كالحاجة_إلى_الملح_في_الطعام.pdf
513 KB
ጀርሕና ተዕዲል ለምግብ ጨው በሚያስፈልገው ልክ ነው የሚያስፈልገው ለሚሉ አካላት የተሰጠ ምላሽ ።
በዶክተር ሑሴን ሙሐመድ ( ሐፊዘሁላህ )

https://t.me/bahruteka
Audio
የአል አጅዊበቱል ሙፊዳ ኪታብ ደርስ ክፍል 09 በቢዳዓ አንጃዎች ላይ ረድ ሲደረግና ከእነርሱ በሚያስጠነቅቁበት ጊዜ መልካም ስራቸውን መጥቀስ ያስፈልጋል ወይ ከሚለው ጥያቄ መልስ የቀጠለ
Live stream scheduled for
Live stream finished (56 minutes)
Audio
በአቡ በከር አሕመድ ላይ ረድ ክፍል አንድ

– አቡበከር አሕመድ እስልምናና ክርስትናን አንድ ለማድረግ ( ለማቀራረብ) በቀባጠረው ቅጥፈት ላይ የተሰጠ ምላሽ
– አበቡበከር አሕመድ ጅህልናውን ግልፅ አደረገ
– አላህ ካለ ወደፊት ሌሎች ጥመቶቹን በመረጃ ግልፅ እናደርጋለን ።

https://t.me/bahruteka
👉 የአቡ በከር አሕመድ ጅህልና
ክፍል አንድ

አላህ እስልምናን ለወደዳቸውና ለመረጣቸው ባሮቹ የሚሰጠው እሱ የመረጠው ዲን ነው ። የእስልምና እምነት መርህና አስተምሮ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆነው የአላህ ቃል የተገለፀና የአላህ መልእክተኛ ያብራሩት የማንንም የአእምሮ ጭማቂ የማይቀበል ጥብቅ ዲን ነው ። ከየትኛውም እምነት ጋር በይዘቱም በአስተምሮቱም የማይገናኝ እንከን የለሽ ከአምላካችን የተሰጠን እምነት ነው ። ከተ ትኛውም እምነት ጋር የማይገናኝ ለየትኛውም እምነት ትክክል ነው ብሎ እውቅና የማይሰጥ ይልቁንም ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶችን ትክክል ናቸው ብሎ ማመንን ከእስልምና የሚያስወጣ መሆኑን በግልፅ የሚያስቀምጥ ዲን ነው ።
ይህን መርህ ተላልፎ እስልምናን ከሌሎች እምነቶች ጋር ለማመሳሰልና ለማቀራረብ መሞከር ከእስልምና የሚያወጣውን ቀይ መስመር መተላለፍ ነው ። በአሁኑ ጊዜ የኢኽዋን አንጃዎች ወደ ስልጣን ለመዳረስ የሚያደርጉትን ጥረት ክርስቲያኖችም ሆነ ምእራባዊያን እንዲቀበሉት ከሚሰሩዋቸው እስልምናን የሚፃረሩ ተግባራቶች አንዱ የእስልምናን እምነት ከሌሎች እምነቶች ጋር አንድ ለማድረግና ለማቀራረብ የሚያደርጉት ጥረት ነው ። ይህ ተግባር ፍፁም እስልምናን የማይወክልና እስልምናም የማይቀበለው ይልቁንም የዚህ አይነቱ ተግባር ከእስልምና የሚያወጣ መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ግልፅ ያደረገው ነው ። ሀገራችን ላይ ከእነዚህ የኢኽዋን መሪዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አቡ በከር አሕመድ በሚሊኒየም አዳራሽ ላይ በስሜት ሰክሮ እስልምናና ክርስትናን ለማቀራረብ ወይም የተቀራረቡ እምነቶች መሆናቸውን ለማሳየት ሲኳትን አይተናል ። ለዚህም ታላቅ የእስልምናን መርህ የመናድ ተግባሩ የቁርኣን አንቀፅን እንደመረጃ ለማቅረብ ሞክሯል ።
የሁለቱ እምነቶች ተቀራራቢ መሆናቸው አላህ መወዳ በሚለው ቃል ገልፆታል ይልና መወዳ የሚለው ቃል ቁርኣን ላይ ሁለት ቦታ ብቻ ነው የተገለፀው ይልና ይኸውም በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል መቀራረብ መኖሩን ለማመልከትና ቀጥሎ በባልና ሚስት መካከል ውዴታ መኖሩን ለመግለፅ ነው ካለ በኋላ ይህ የሚያሳየው ለነገሩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ነው ይላል ።
በመጀመሪያ ደረጃ አቶ አቡ በከር አሕመድ ቁርኣንን ጠንቅቆ የሚያውቀው ለመምሰል ያቀረበው መረጃ ውድቅ ነው ። እሱም ቁርኣን ላይ መወዳ የሚለው ቃል ሁለት ቦታ ብቻ ነው የሚለው ትልቅ ውሸት ነው ። የሰውየውን አላዋቂነትና ከቁርኣን ጋር የማይተዋወቅ መሆኑን ማሳያ ነው ። ምክንያቱም ቃሉ ቁርኣን ላይ የተጠቀሰው 7 ቦታ ነውና !!!!!! ። እነርሱም በሚከተሉት ምዕራፎች ውስጥ : –
1ኛ – አንኒሳእ 73ኛው አንቀፅ
2ኛ – አል ማኢዳ 82ኛው " "
3ኛ – አል አንከቡት 25 ኛው " "
4ኛ – አርሩም 21 ኛው " "
5ኛ – አል አሽሹራ 23ኛው " "
6ኛ – አል ሙምተሂና 1ኛና 7 አንቀፅ ላይ ነው የተጠቀሰው ። አቶ አቡበከር 5ቱን ምን አድርጓቸው ይሁን ? የሉም ወይስ እሱ አያውቃቸውም ? መልሱ ለራሱና ለተከታዩቹ ትቼዋለሁ ።
እሱ ያላቸው ሁለቱና እምኖቶቹን ለማቀራረብ የሞከረባቸውን የቁርኣኖቹን መልእክቶችን እንመልከት በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል የሚለው አንቀፅ የሚከተለው ነው : –

« لَتَجِدَنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَدَاوَةً لِّلَّذِينَ آمَنُوا الْيَهُودَ وَالَّذِينَ أَشْرَكُوا ۖ وَلَتَجِدَنَّ أَقْرَبَهُم مَّوَدَّةً لِّلَّذِينَ آمَنُوا الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّ مِنْهُمْ قِسِّيسِينَ وَرُهْبَانًا وَأَنَّهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ »

المائدة ( 82 )

" አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ኾነው በእርግጥ ታገኛለህ ፡፡ እነዚያንም «እኛ ክርስቲያኖች ነን» ያሉትን ለእነዚያ ለአመኑት በወዳጅነት በእርግጥ ይበልጥ የቀረቧቸው ኾነው ታገኛለህ ፡፡ ይህ ከእነሱ ውስጥ ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነሱም የማይኮሩ በመኾናቸው ነው ፡፡

ባልና ሚስትን አስመልክቶ የወረደው ደግም የሚከተለው ነው : –

« وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ »

الروم (21 )

" ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው ፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ "፡፡

አቶ አቡበከር በነዚህ ሁለት አንቀፆች ውስጥ መወዳ የሚለው ቃል አንድ አይነት መልእክት እዳላቸው ለማሳየት ነው እንደመረጃ ያቀረበው ያውም እነዚህ ሁለቱ ብቻ ናቸው ቁርኣን ውስጥ ያሉት ከማለት ጋር !!!!! ። አሁንም መወዳ የሚለው ቃል በሁለቱ ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ መልእክት ነው የያዙት መልሱ ለተከታዮቹ ትቼዋለሁ ።
ሌላው ሁለቱን እምነቶች ለማቀራረብ የተጠቀመው ሁለቱም ፍቅርን የሚያስተምሩ እምነቶች ናቸው ብሎ ነው ። ይህ ንግግር ክርስቲያኖችን በማስደሰት ክሬዲት እንዲያዝለት ብሎ ያደረገው ይመስላል ። ከዚህ በላይ ግን ሰውየው በእስልምና እምነት መርህ ላይ ጃሂል መሆኑ ለዚህ ሊዳርገው እንደሚችል ግልፅ ነው ።
የኢስላም አስተምሮ ዋናውና ቁንጮ የአላህን ብቸኛ ተመላኪነት ማረጋገጥ ነው ። አላህ የላካቸው 124 ሺ ነብያቶች በሙሉ የጥሪያቸው ወይም መልእክታቸው ዋነኛው ነጥብ ለሰው ልጆች አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩና ሽርክን ( ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አካላትን እንዲርቁ ማስተማር ) ነበር ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል : –

« وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ ۚ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ »

النحل ( 36 )

" በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል ፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ "፡፡

ይህ በመቶዎች ከሚቆጠሩ አንቀፆች አንዱ ነው ። ለማሳያ ያክል በቂ ነውና ሁሉንም መዘርዘር አያስፈልግም ።
የክርስትና እምነት ዋነኛ አስተምሮ ዒሳ የአላህ ልጅ ነው ወይም ዒሳ አምላክ ነው ወይም ዒሳ የአምላክ 1/3 ነው እና የመሳሰሉ በአላህ ላይ መካድን ነው ። ይህ ሆኖ ሳለ ሁለቱም ፍቅርን ነው የሚያስተምሩት ብሎ ለማቀራረብ መሞከር ትልቅ ቅጥፈት ነው ። አላህ በተከበረው ቃሉ ዒሳ አላህ ነው የሚሉ አካላት ከሀዲያን መሆናቸውን እንዲህ ብሎ ይነግረናል :–

« لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ »

المائدة ( 72 )

" እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ ፡፡ አልመሲህም አለ ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት ፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም "፡፡

በዚሁ ምዕራፍ ላይ አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው የሚሉ አካላትን አስመልክቶ እንዲህ ይላል : –

« لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ ثَالِثُ ثَلَاثَةٍ ۘ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۚ وَإِن لَّمْ يَنتَهُوا عَمَّا يَقُولُونَ لَيَمَسَّنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ »

المائدة ( 73 )

" እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ ፡፡ ከአምላክም አንድ አምላክ እንጅ ሌላ የለም ፡፡ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል "፡፡

በመጨረሻም አንድነት ከተፈለገ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት አላህ ለነብዩ በማያሻማ ቃል ለአዩሁዶችና ነሳራዎች ( ክርስቲያኖች ) እንዲህ በላቸው ነው የሚለው : –

" قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ "

آل عمران ( 64 )

" የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው ፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው "፡፡

አቶ አቡበከር ሆይ የቁርኣን ተንታኝ የሙስሊሞች መሪ ነኝ ማለቱን ተወውና ተውበት አድርገህ ተመልሰህ ቁጭ ብለህ እስልምናን ተማር ።

ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች ትክክል ናቸው ብሎ ማመን እስልምናን የሚያበላሽ መሆኑን በሚቀጥለው ክፍል አላህ ካለ እናያለን

ለዛሬ አበቃሁ

https://t.me/bahruteka
Forwarded from Shakir Sultan (Channel)
🔈#ሙመይዓዎች ቡታጅራ ከተማ ውስጥ የሄዱበትን ደረጃ እውነታውን ግልፅ ማድረግ


🔈 -كشف حقيقة مراحل أهل التمييع ومكرهم في مدينة بتاجرا

27 ذو الحجة 1444 هـ
الموافق 15 يوليو 2023

🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3
https://is.gd/o4EPx5

🔶በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ኹለፋ አል-ራሺዲን መስጂድ የተደረገ ሙሓደራ።

🎙 أستاذ شاكر بن سلطان - حفظه الله تعالى

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ

👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan
Audio
የአቡ በከር አሕመድ ጅህልና

በአቡ በከር አሕመድ ላይ ረድ
ክፍል ሁለት
➶➶➶➶
ክፍል አንድን ለማግኘት ⬇️
https://t.me/bahruteka/3734

አቡ በከር አሕመድ ከሚቀጥፋቸው ቅጥፈቶች ውስጥ
– የሳውዲ ስርኣት የመደንይ ስርኣት ነው
መደንይ የሚለውን በንጉሳዊ አገዛዝ መተርጎሙ ቀጥሎ
የመደንይ ስርኣት ማለት ሰው በሰውመቱ፣ በእምነቱ፣ በአስተሳሰቡ የማይወገዝበት ሁሉን አካታች ስርኣት ነው ይላል። (ይህ ነው ትክክለኛ ትርጉሙ)
– የመደንይ ስርኣት ሸሪዓ የሚያዝበት ነው
ኢትዮዽያ ውስጥ ኢስላማዊ ሸሪዓ አይታሰብም ማሰቡም ወንጀል ነው
– ኢትዮዽያ ውስጥ ኢስላማዊ ስርኣት እንዲመጣ የሚያስብ ካለ ወንጀለኛ ነው ብለን እናምናለን
– የመደንይ ስርኣት (ሰው በሰውነቱ፣ በእምነቱ፣ በአስተሳሰቡ፣ የማይወገዝበት ስርኣት) ከመጣ እምነቴን (እስልምናን) ይወክላል

https://t.me/bahruteka
👉 የአቡ በከር አሕመድ ጅህልና

ክፍል ሁለት

በአቡ በከር አሕመድ ቅጥፈት ላይ የተሰጠ ምላሽ ።

የአቡ በከር አሕመድ የጅህልና ጉዞ ቀጥሎ በጣም የሚገርም ደረጃ ላይ ደርሷል ። አቶ አቡ በከር ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚመራና ለእስልምና የሚታገል በማስመሰል አብዛኛዎች ነገሮችን በቃላትና ትረካ የሚመዝኑ ተምረናል የሚሉ አካላትን ከጎኑ በማሰለፍ የንግዱን መህበረሰብና ወጣቱን ተከታዮቹ ለማድረግ በሚዲያ ሽፋን በመታገዝ የገነነ ሲሆን እነዚህ ተከታዮቹ አእምሯቸውን ለሳምፕል አስቀምጠው የሱ የጅህልና ጉዞ ተከታዮች ሆነዋል ። በመሆኑም የፈለገውን ሲናገር ፣ ያሻውን ሲያፀድቅና ያሻውን ሲሽር ተው የሚለው አጥቷል ። ይህም በመሆኑ ይህ ግለሰብ ሀገራችን ላይ የሙስሊሞችን ጫንቋ ከሚደርስባቸው ጭቆና ለፃ ማውጣትና ሀገራችንን የሸሪዓ ሀገር ለማድረግ ነው የምንታገለው በሚል ህዝቡን ከዳር እስከዳር እንዲነሳ በማድረግ አቡ በከር አሕመድና ግብረ አበሮቹ ለሚያመጡት ለውጥ ተብሎ ሆ ብሎ የወጣው ሙስሊም ማህበረሰብ የህይወት ፣ የገንዘብ ፣ የአካል መጉደል ዋጋ ከከፈለ በኋላ ጨቋኝ የነበረውን ወዳጅ አድርገው ከዚህም በላይ በዛው ሙስሊም ማህበረሰብ ፊት ለፊት እጅ ለእጅ ተያይዘው ዑመር ገነቴን ዳግም በማንገስ አሳፋሪ ተግባር ፈፀሙ ። በዚህም አቡ በከር አሕመድና ግብረ አበሮቹ የሚታገሉለት ዐቂዳ እንደሌለና የሚከፈለው ዋጋ ለእነርሱ ገናናነት መሆኑ ታየ ።
አሁንም የተኛው ማህበረሰብ አልነቃም ። ኡስታዝ እያለ ቀጠለ እሱም ህዝቡን ወደ ጅህልናና ኩፍር መምራቱን ተያያዘው ። እየሱስ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው አለ አላቆመም ክርስትናም እስልምናም ፍቅር ያስተማሩ እምነቶች ናቸው ብሎ ሁለቱን እምነቶች ለማቀራረብ ቁርኣን ውስጥ መወዳ የሚለው ቃል በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል ያለውና በባልና ሚስት መካከል ያለውን ፍቅርን ለመግለፅ ነው ብሎ ክርስቲያኖችን እንደሚስቱ እንደሚወዳቸው ቁርኣንን መረጃ ለማድረግ ሞከር
ድርጊቱ ከዛ በፊት የተፈለመ ቢሆንም ዛሬ የምናየው እስልምና የመደንይ ስርኣት ነው የሚለውን ለሙስሊሙ ሲግት መስማታችንን ነው ። ይህ የሆነው ከጋዜጠኛ እናንተ የሙስሊም መንግስት ለመመስረት ነው የምትንቀሳቀሱት ይባላል እንዴት ነው ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እንዲህ ይላል : – ቃል በቃል ሳይሆን ግርድፍ ሀሳቡን ነው የማስቀምጠው ቃል በቃል ንግግሩ መስማት የፈለገ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል ያገኘዋል ።
– የጥያቄው መልስ እንዲህ የሚል ነበር :–
" እንኳን ግማሽ አካልህ የሌላ እምነት ተከታይ በሆነበት ሀገር ቀርቶ መቶ በመቶ ሙስሊም ማህበረሰብ ያለባት ሳውዲ እንኳን ኢስላማዊ መንግስት የላትም ። የመደንይ ስርኣት ነው ያለው ። ንጉሳዊ አገዛዝ እኮ ነው የለም እኮ አይታሰብም ። ሸሪዓዊ መንግስት ለማምጣት ማሰቡ ራሱ ወንጀል ነው ። የሚያስብ ካለ ወንጀለኛ ነው ብለን ነው የምናምነው አለ ። ቀጥሎ እኛ መደንይ የሆነ ስርኣት እንዲመጣ ነው የምንታገለው ይህ ስርኣት ከመጣ እምነቴን ( እስልምናን ) የወክልልኛል እያለ ቀጠለ " ።
የመደንይ ስርኣት የሚለውን ሲያብራራም
" ሰዎች በሰውነታቸው ፣ በእምነታቸው ፣ በአስተሳሰባቸው የማይገፉበት ሁሉን አካታች የሆነ ስርኣት ነው " ይላል ። ይህ የመደንይ ስርኣት ማብራሪያ ትክክል ነው ። እስልምናን ይወክላል የሚለው ግን ባጢል ነው ይልቁንም በእስልምና ልይ ያለውን ጅህልና የሚያሳይ ነው ።
እስልምና ሰዎች የፈለጉትን እንዲያመልኩ አይፈቅድም ። ቢፈቅድም በዛቻ መልኩ ነው ። ሐቁ ግልፅ ሆኖለት አልቀበልም አሻፈረኝ ያለ አካል የፈለገውን ያምልክ ( ይካድ ) መጨረሻ ላይ አሳማሚ ቅጣት አዘጋጅተናል በሚል መልኩ ነው ። ኢስላም ሰው የፈለገውን እንዲያመልክ በፈለገው እንዲያምን ቢፈቅድ ኖሮ የመልእክተኞች መላክና መፅሐፍቶች መውረድ ፋይዳው ምን ይሆን ነበር ? !!!!!
ስለዚህ ኢስላም የመደንይ ስርኣት ወይም የዲሞክራሲ ስርኣት ( ህዝብ የፈለገውን በድምፅ ብልጫ እንዲወስን መፍቀድን ) ኩፍር ነው ብሎ ነው የሚያስተምረው ። ምክንያቱም በመደንይ ወይም በዲሞክራሲ ስርኣት የወንድ ለወንድ ጋብቻ የድምፅ ብልጫ ካገኘ ይቻላል ። ምእራባዊያን ጋር እንዳለው ። ኸምር ፣ ዝሙት ፣ ወለድ እና የመሳሰሉ ተግባራት የድምፅ ብልጫ ካገኙ የተፈፈቀዱ ይሆናሉ ። ይህ ማለት ኢስላም የሚያዘው ቂሷስን ( በቅጣት ማመሳሰል ) ውድቅ ይሆናል ማለት ነው ።
አቶ አቡበከር ኢስላም ይህን ያስተምራል እያለን ነው ። ይህ ስርኣት እስልምናን ይወክላል እያለን ነው ። የዚህ ግለሰብ አስተምሮ በቁርኣን አስተምሮ እንየው እስኪ አላህ የሰው ሰራሽን ህግ አስመልክቶ ሙስሊሞች ሊኖራቸው የሚገባውን ዐቂዳ ( እምነት) ሲነግረን በሱረቱል አንኒሳእ 60ኛው አንቀፅ ላይ አልህ እንዲህ ይላል : –

« أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ يَزْعُمُونَ أَنَّهُمْ آمَنُوا بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوا إِلَى الطَّاغُوتِ وَقَدْ أُمِرُوا أَن يَكْفُرُوا بِهِ وَيُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُضِلَّهُمْ ضَلَالًا بَعِيدًا »

" ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት ፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ ፡፡ ሰይጣንም (ከእውነት) የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል "፡፡

አሁንም በሱረቱል አሕዛብ 36ኛው አንቀፅ ላይ አማኞች አላህና መልእክተኛው ከወሰኑ በኋላ ይህ አልተመቸኝም በድምፅ ብልጫ ይወሰንልኝ ማለት እንደሌለባቸው ሲነግረን እንዲህ ይላል : –

« وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُّبِينًا »

" አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም ! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ " ፡፡

እነዚህ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ የሆኑ የአላህ ቃሎች ሙስሊሞች የሰው ሰራሽ ህግ ባጢል መሆኑን እንዲያምኑ አላህና መልእክተኛው በሚወስኑትና በሚያዙት ነገር እንዲመሩና ( " መ " ንና "ረ " ን በማጥበቅና በማላላት በማንበብ ) ነው ። ይን ነው ኢስላማዊው መርህ ።
አቶ አቡበከር ይህን እስልምና ነው ከዲሞክራሲና መደንይ ስርኣት ጋር የሚያገናኘው ። የመደንይ ስርኣት ማለት ከእምነት ነፃ የሆነ ሁሉንም ትክክል ነህ የሚል በዘር በቀለም በእምነት በአመለካከትና አስተሳሰብ ሁሉንም ሳይለይ ለሁሉም እውቅና የሚሰጥ ስርኣት ነው ። ይህ ስርኣት በተለይም የእስልምናን ሸሪዓ ለመዋጋት የተረቀቀ ስርኣት ነው ። ምክንያቱም ኢስላም ሁሉም እምነት ትክክል ነው ብሎ አይቀበልም ። ለሁሉም የፈለገውን የመናገር መብት አይሰጥም ከንግግሮች ውስጥ የሚያከፍሩ ስላሉ ። ለሁሉም የአመለካከትና አስተሳሰብ እውቅ አይሰጥም ። የአላህን ስምና ባህርይ
ውድቅ የሚያደርግ እንዲሁም ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለም ለሚል አካል መብትህ ነው አይልም ። ባጠቃላይ ኢስላም የሰውን ልጅ እምነት ፣ አነጋገርና አመለካከት ትክክልና ውድቅ ብሎ መረጃ አስቀምጧል ። ይህም የአላህ ቃልና የነብዩ ሐዲስ በሶሓቦች ግንዛቤ ( አረዳድ ) መከተልና መተግበር ነው ።

አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።

ለጊዜው እዚህ ላይ አበቃሁ

https://t.me/bahruteka
Live stream scheduled for
Live stream finished (57 minutes)