የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥናትና ምርምር መጽሔት ስራዎች
4.01K subscribers
634 photos
27 videos
390 files
300 links
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥናት እና ምርምር ጽሁፎች የታተሙ ያልታተሙ ጆርናሎች ችግር ፈቺ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ዳሰሳዎች መጽሐፎች ይቀርቡበታል
Download Telegram
ያስደንቅ ትልቅ ዜና ነው፡፡
መጻጉዕ ‹ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸከም አለኝ› አላቸው፡፡
እስቲ በደንብ አስተውሉ፡፡ እነዚህ ሰዎችይህን በሽተኛ ፈጽሞ
አያውቁትም ነበር እንበል፡፡ እንደዛ ከሆነ ‹ያዳነኝ ሰው›
ሲላቸው ‹ከምንድን ነው የምትድነው? ምን ሆነህነበር? ከየት
ነው የመጣኸው?› ይሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠንቅቀው
ያውቁታል፡፡ መዳኑን ማየት አልፈለጉም እንጂ ማን እንደሆነ
ጠንቅቀውያውቁታል፡፡ ከዚያም ‹‹ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን
ተሸከም አለኝ›› ሲላቸው ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ያለህ
ሰው ማን ነው?››ብለው ጠየቁት፡፡ እስቲ ጥያቄና መልሱ
ውስጥ ያለውን ሽሽት እንመልከት፡፡ ‹‹ያዳነኝ ሰው አልጋህን
ተሸከም አለኝ›› ለሚለው መልስተከታዩ ጥያቄ ‹ማን ነው
ያዳነህ?› የሚል ነበር፡፡ እነሱ ግን የጌታንየማዳን ሥራ
ላለመስማት ጆሮአቸውን ደፍነው ስለነበር ‹አልጋህን ተሸከም
ያለህ ማን ነው?› አሉ፡፡ የማዳኑን ሥራ እያዩ ከማመንይልቅ
መከራከር ፣ ከማድነቅ ይልቅ የትችት ሰበብ መፈለግ
እንግዲህጌታን የሰቀሉ የአይሁድ ጠባይ ነው፡፡
የመጨረሻው ነገር መጻጉዕ ከዚህ በኋላወደ አይሁድ ሄዶ
ጌታን መክሰሱና ለጌታ ሞት የመማከራቸው ምክንያት መሆኑ
ነው፡፡ ይህ ሰው ‹የሚብስ እንዳይገጥምህ ደግመህ
ኃጢአትንአትሥራ› ብሎ ጌታ ቢያሳስበውም አልሰማም፡፡ ጌታ
በተያዘበት በምሴተ ሐሙስ ለሊቀ ካህናቱ አግዞ ጌታችንን
በጥፊ መታው፡፡ ጌታችንም‹‹ክፉ ተናግሬ እንደሆነ ስለ ክፉ
መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ?››
አለው፡፡ (ዮሐ.18፡23) ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ከማለት
በቀር ክፉቃል ተናግሬህ ከሆነ መስክርብኝ ፤ የተናገርኩህ
መልካም ሆኖ ሳለ ስለምን ትመታኛለህ›› ማለቱ ነበር፡፡
ጌታችን በማግሥቱ ያ ሁሉጅራፍና ግርፋት ሲደርስበት አንድም
ጊዜ ‹‹ለምን ትመታኛለህ›› ብሎ አልተናገረም፡፡ የመጻጉዕ
ጥፊ ይህን ያህል ዘልቆ የተሰማውለምንድር ነው?
የመጀመሪያው ምክንያት ከቤተ ሳይዳ ከበጎች በር ጋር
የተያያዘ ነው፡፡ ጌታችን የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
የእግዚአብሔር በግ ነው፡፡ በበጎች በር አልፎ የመጣውንጹሐ
ባሕርይ እንደሆነ ለማስረዳት ነበር፡፡ ለዚህም ንጽሕናው
ዋነኛው ምስክር ፈውስን የሠጠው ይህ በሽተኛ ነበር፡፡ እሱ
ግን መታው፡፡‹‹በቤተ ሳይዳ ክፉ ቃል ተናግሬህ ከነበር
መስክርብኝ› ማለቱ ‹ነውርየሌለብኝ ፣ ለመሥዋዕት
የተዘጋጀሁ በግ ነኝ ለምን ትመታኛለህ?› ማለቱ ነበር፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሮማውያን ግርፋት በላይለጌታ
ዘልቆ የሚሰማው ባዳነው ሰው መመታቱ ስለሆነ ነው፡፡ ውድ
አንባቢያን መጻጉዕ ከሠላሳ ስምንት ዓመት በሽታ ብቻ ዳነ ፣
እኛግን የዳንነው ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በሽታ
ነበር፡፡ ጌታችን እኛን ያስነሣን ከሲኦል አልጋ ነው፡፡ ከሌላው
ሰው ይልቅእግዚአብሔር የእኛ ዱላ ይሰማዋል፡፡ ይህም ዱላ
ኃጢአታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር ዛሬም ድረስ ለእያንዳንዳችን
ይጠይቃል፡፡ ‹‹ለምን ትመታኛለህ?››
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🐾🐾 የይሁዳ እግሮች 🐾🐾

ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመሥጠት ከአይሁድ ጋር የተስማማው ረቡዕ ዕለት ነበር፡፡ ይህን ስምምነት አድርጎ እንደጨረሰ ወደ ጌታና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ማኅበር ተመለሰ፡፡ ከረቡዕ ጀምሮ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስም ከጌታ ፊት ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ አሳለፈ፡፡ ይህ በትክክል ይሁዳ ምን ዓይነት አስመሳይና ክፉ ሰው እንደነበረ ያሳያል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁኔታዎች አስፈርተውት ጌታውን ለሦስተኛ ጊዜ አላውቀውም ብሎ ከካደ በኋላ ጌታችን ለአንድ አፍታ ቀና ብሎ ስለተመለከተው ብቻ የጌታውን ፊት በድፍረት ለመመልከት አቅም አጥቶ መራራ ልቅሶን እያለቀሰ ከአጥር ውጪ ወጥቶ ነበር፡፡ ይሁዳ ግን አሳልፎ ሊሠጠው ከተስማማባት ሰዓት ጀምሮ ድምፁን አጥፍቶ ከጌታችን ጋር እንደ ወትሮው አብሮ ሲቀመጥ አንድ ጊዜ እንኳን አልተሸማቀቀም፡፡
🍇@deaqonhanok
ልብ አድርጉ! በራሱ ሃሳብ አመንጪነት ፣ ራሱ ወደ አይሁድ ሸንጎ ሔዶ ፣ ብር ለመቀበል ተስፋ ተቀብሎ ከመጣ በኋላም የጌታችንን ዓይኑን እያየ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› ብሎ ለመጠየቅም ድፍረት ነበረው! በዚያች ሰዓት እንደ ዳታንና አቤሮን መሬት ተሰንጥቃ ስላልዋጠችው ፣ ምላሱ ከጉሮሮው ጋር ስላልተጣበቀ ፣ በድፍረትና በመናቅ በእውነተኛው ጌታ ላይ የተናገሩት የሽንገላ ከንፈሮቹ ዲዳ ባለመሆናቸው የፈጣሪን ትዕግሥቱን እናደንቃለን፡፡ ሁሉን የሚያውቀው ጌታ ግን ይሁዳ ሊሸነግለው መሞከሩን ቢያውቅም ‹አንተ አስመሳይ!› ብሎ አላዋረደውም፡፡
🍇@deaqonhanok
የእግዚአብሔር ነቢይ ኤልሳዕ ሎሌው ግያዝ የማይገባውን ገንዘብ ከለምጹ ከነጻው ከሶርያዊው ንዕማን ተቀብሎ ቤቱ ወስዶ ከሸሸገ በኋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ከፊቱ መጥቶ ሲቆም ‹ግያዝ ሆይ ከወዴት መጣህ?› ብሎ ጠይቆት ነበረ፡፡ ግያዝም ‹‹እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሔድሁም›› አለ፡፡ ኤልሳዕም ፡- ‹‹ልቤ ከአንተ ጋር አልሔደምን?›› ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ይጣበቃል ብሎ ረግሞት እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ወጣ፡፡ (፪ነገሥ. ፭፥፳‐፳፯)
🍇@deaqonhanok
ሐዋርያው ጴጥሮስም ሐናንያና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስት ገንዘባቸውን ከቤታቸው ሸሽገው መንፈስ ቅዱስን ሊያታልሉና በማስመሰል በፊቱ ሊቆሙ ሲሞክሩ ‹እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሻችሁም› ብሎ በካህን ቃሉ ተናግሮ ተቀሥፈው እንዲሞቱ አድርጓቸዋል፡፡ (ሐዋ. ፭፥፩-፲)

የነቢያትና የሐዋርያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኤልሳዕና ከጴጥሮስ በላይ የልብን የሚያውቅና መቅጣት የሚቻለው ነው፡፡ ሆኖም ከአይሁድ ጋር ሊሸጠው ተዋውሎ የመጣው ይሁዳ ዓይኑን በጨው አጥቦ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› እያለ ሲዘብትበት በታላቅ ትዕግሥት ዝም አለው፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን ሊያታልሉ የሞከሩ ሰዎች እንዲህ ከተቀጡ የነቢያትን አምላክ ሊያታልል የሞከረ ‹‹…እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?›› (ዕብ. ፲፥፳፱)
🍇@deaqonhanok
ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬) በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ሥራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉሥ ግን በትሕትና እንደ ሎሌ ሆነ፡፡ (፩ሳሙ. ፳፭፥፵፩)
🍇@deaqonhanok
ጌታችን አጎንብሶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግሥት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው፡፡ ‹‹ወኀፀበ እግረ ይሁዳ አስቆሮታዊ ዘያገብኦ›› ‹‹የሚያስይዘውን የአስቆሮቱ የይሁዳንም እግር አጠበ›› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ)
🍇@deaqonhanok
ከአንድ ቀን በፊት ክፋትን ለማሴር ወደ አይሁድ ካህናት ግቢ የሮጡትን የይሁዳን እግሮች ጌታችን አጎንብሶ አጠባቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሊያስይዘው ወደ አይሁድ የሚሮጥባቸውን እግሮች ፣ የሚይዙትን ወታደሮች እየመራ ወደ እርሱ የሚመለስባቸውን እግሮች አጠበለት፡፡ ምንም እንኳን በነገው ዕለት እግሮቹን እንዲቸነከር አሳልፎ የሠጠው መሆኑን ቢያውቅም ሰውን ወዳጁ ክርስቶስ ግን የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመጨረሻ ጊዜ እግሩን አጥቦ ተሰናበተው፡፡
🍇@deaqonhanok
እንደ ነቢዩ ዳዊት ‹‹አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ!›› ከማለት በቀር በምን አንደበት ልንናገር እንችላለን? (መዝ. ፴፮፥፯) ‹‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ያለን ጌታ አሳልፎ የሚሠጠውን የይሁዳን እግር ሲያጥብ ከማየትስ በላይ በቂም በቀል ለሚቆስለው ልባችን ምን መድኃኒት ይኖር ይሆን?
🍇@deaqonhanok
ይሁዳ ሆይ እስቲ አንድ ጊዜ ንገረን ፤ ጌታ አጎንብሶ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት አስቻለህ? ‹እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ› የሚሰገድለት አምላክ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት ትንሽ እንኳን አልተሰማህም? አንተ እግሩን ልታጥበው እንኳን የማይገባህ ፈጣሪ እግርህን ሲያጥብህ እያየህ እንዴት ልብህ ደነደነ? መጥምቁ ዮሐንስ ‹የጫማውን ጠፍር ልፈታ አይገባኝም› ያለው ጌታ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት ልብህ በጸጸት አልተሰበረም? ረቡዕ አሳልፈህ ልትሠጠው ተስማምተህ መጥተህ ሐሙስ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት አልጨነቀህም? ከአይሁድ ጋር የተስማማኸው ነገር ‹ይቅርብኝ› ለማለት ጌታችን ከእግርህ በታች ዝቅ ብሎ ካጠበህ ሰዓት የተሻለ ማሰቢያ ጊዜ ከየት ይገኛል? በፍቅሩ ውስጥ ክፋትህ ፣ በትሕትናው ውስጥ ትዕቢትህ እንዴት አልታየህም? እንዴትስ እግሮችህን ሠጥተህ ያለ አሳብ ታጠብህ?
🍇@deaqonhanok
ቅዱስ ጴጥሮስ እንኳን ‹‹ጌታ ሆይ አንተ [እንዴት] የእኔን እግር ታጥባለህ?› ብሎ ተጨንቆ ጠይቆ ነበር፡፡ ‹የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም› ብሎ ተከላክሎም ነበር፡፡ ልበ ደንዳናው ይሁዳ ግን ዝም ብሎ እግሮቹን ሠጠ፡፡ የከዳውን ጌታ የቁልቁል እየተመለከተ ለአፍታ እንኳን ልቡ አልተመለሰም፡፡ ሐዋርያት ጌታ ባጠበው እግራቸው ለጊዜው ፈርተው ቢሮጡም በኋላ ግን በጸጸት ተመለሱበት፡፡ በአምላክ እጅ በታጠበ እግራቸው ያለመሰልቸት ዓለምን ዞረው ወንጌሉን አስተምረው እስከሞት ድረስ ታመኑ፡፡ በእግራቸውም እንደ ስማቸው ሐዋርያት (ተጓዦች) ሆኑበት፡፡ ይሁዳ ግን በአምላክ እጅ በታጠበው እግሩ ወደ አይሁድ ገስግሶ ጌታ ለሚያንገላታው ጦር መንገድ እየመራበት ተመለሰ፡፡

‹‹ኦ እግዚኦ ዘኢትደፈር ይሁዳ ደፈረከ››
‹‹አቤቱ የማትደፈር አንተን ደፋር ይሁዳ ደፈረህ!››
(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፩፥፳፩)

"ሕማማት" ከተሰኘው የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተወሰደ ምንባብ,
(ሕማማት ባለ ስድስት ምዕራፍ፣ ባለ 528 ገጽ መጽሐፍ ነው)

🍇🍇 @deaqonhanok 🍇🍇
🍇🍇 @deaqonhanok 🍇🍇
🍇🍇 @deaqonhanok 🍇🍇
ለመቀላቀል 👆👆 ይጫኑ
ጌታ ሆይ ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለህ፣ ሳታጎድል ለሁሉ ትመግባለህ፣ ዝም ሳትል ለሁሉ ታስባለህ፣ ሳትነጥፍ ለሁሉ ታረካለህ። ሳትተኛ ሁሉን የምትጠብቅ፣ ሳትዘነጋ ሁሉን የምታሥብ ሆይ አይሁድ በመስቀል ትሞት ዘንድ ፈረዱብህ።
የጥበብ ነገር የምክር ቃል የረድኤት መዝገብ የደስታ መኖሪያ ሆይ ስለሰው ልጅ እራስህን ቤዛ አደረግህ።

የወለደችው ማርያምም በመስቀሉ አንፃር ቆማ ትጮሀለች። በምድር ላይ አባት የሌለህ ልጄ ልጄ። የታሰርክ የተቸነከርክ ልጄ ልጄ። ልጄ የማንን ገንዘብ ቀማህ። ልጄ የማንን ሹመት ቀማህ። አሸናፊ ልጄ ማን ያዘህ። ልጄ ኃጥያትህ በደልህ ምንድነው። ጉተናህ የተደመደመ ልጄ የእሾህ አክሊል አቀዳጁህን። የቄዛፍ ወርቅ ራስህ በብትር ይደበደባልን።
አበባ የመሰሉት ፊቶችህ ጥፊውን ቻሉትን። የለሰለሱ መዳፎችህ የብረቱን ችንካር ታገሡትን። እንደ ባሪያ በጀርባህ ግርፋቱን በእግሮችህም ችንካሮችን ቻልክን።

ልጄ ልጄ አንተ የሞትህን መስቀል ተሸከምክ ሆዴ ተቃጠለች አንጀቴም እንደ እሳት ነደደ።
ልጄ ነገርከኝ በኩሬ መለስክልኝ የማህፀኔ ፍሬ ተናገርከኝ። አንተን ካላዳንኩ የግብፅን ሀገሮች ለምን ሄድኩ። አንተን ካላዳንኩ በደብረ ቁስቋም ውሥጥ ለምን አደርሁ እያለች ታለቅሳለች።
እመቤታችን ይህን በተናገረች ጊዜ የልቅሶዋ ጩኸት ሠማይ ተሠማ የልቅሶዋም ጩኸት እሥከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።
ብዙ ኃጢአቶችንና ወንጀሎችን የሠራ አንድ ሰው ለሠራው ኃጢአትና ወንጀል ሳይቀጣ ሲቀር አይተን ብዙዎቻችን እንበሳጫለን፡፡ ያ ሰው እንዲጠየቅና እንዲቀጣ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይኾን ከቀረ ግን ቅር እንሰኛለን፤ እንናደዳለን፡፡
እንዲህ የምንኾነው ግን የገዛ ራሳችንን ግብር ስለማንመለከት ነው፡፡ መበሳጨትና መናደድ ቅርም መሰኘት የሚገባን በገዛ ራሳችን ላይ ነውና፡፡ እያንዳንዳችን ለራሳችን እንዲህ ብለን ልንጠይቅ ይገባናል፦ "በሌሎች ሰዎች ላይ ስንት በደል ፈጸምሁ? ለዚህ በደሌስ ስንቴ ሳልቀጣ ቀረሁ?"
በራሳችን ላይ ብዙ ምሳሌዎችን እንደምናገኝ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህን ማወቃችን ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ የተቆጣነው ቁጣና የተበሳጨነው ብስጭት እንደ ጢስ ተኖ እንደ ትቢያ በንኖ እንዲጠፋ ያደርጓል፡፡ ከዚህም በላይ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር እንድናዞር ስለ በደልነውም በደል ይቅርታንና ቸርነትን እንድንለምን ያደርገናል፡፡

እንዲያውም እኛ በበደልነው በደልና ሌሎች ሰዎች በሠሩት ኃጢአት ልዩነቱን እናስተውለው ይኾናል፡፡ ምናልባት የእኛ በደል የተሰወረና ለሌሎች ሰዎች የማይታይ ሕቡዕ ይኾናል፤ በአንጻሩ ደግሞ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የሚታይ ይኾናል፡፡

ታዲያ በዚህ ኹኔታ የእኛ በደል ንኡስ፥ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት ግን ዐቢይ እንደ ኾነ ልናስብ ይገባናልን? በጭራሽ! ምክንያቱም በስውር የሚሠ'ራና ሌላ ሰው የማያየው በደል ብዙውን ጊዜ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ስርቆትንና ቀማኛነትን የመሳሰሉ በግልጽ የሚታዩ ኃጢአቶች ኃጢአት መኾናቸው በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ መታወቃቸው ብቻም ሳይኾን በቀላሉ ንስሐ ሊገባባቸውና ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ውሸትን፣ ሐሜትንና በስውር ማታለልን የመሳሰሉ በስዉር የሚሠሩ በደሎች ግን በደል መኾናቸውን ለማወቅም ስለ እነዚህ ንስሐ ገብቶ ለማስወገድም እጅግ ክቡዳን ናቸው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
+ደብረ ዘይት +
በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ደብረ ዘይት ጌታችን ያረገበትና ስለ ዓለም ፍጻሜ ምልክቶች ያስተማረበት በወይራ የተከበበ
ተራራ ነው
ደብረ ዘይት ተብሎ በተራራው ስም ይጠራ እንጂ የጌታችን በዓለ ምጽአቱን የምናስበበት
በዓል ነው
ደብረ ዘይት ከጌታችን ከ18ቱ በዓላት አንዱ ነው
በደበረ ዘይት ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን አስተምሯቸዋል
1የምጽዓቱን ምልክቶች
2 የምጻቱን ምሳሌዎች
3 የአመጣጡን ሁኔታዎች
1የምጽአቱ ምልክቶች
የሐሰተኞች ነቢያት በክርስቶስ ስም መነሳት
ልዩ ልዩ የጦር ዓይነት መሰራት
የጦርና የጦር ወሬ መብዛት
የርሀብ መከሰት
የቸነፈር ብዛት (አዳዲስ ህመሞች መምጣት)
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መነሳት
መንግሥት በመንግሥት ላይ መነሳት
ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን መካድ
የአመጻ መብዛት
ከሰው ልብ ውስጥ የፍቅር መቀዝቀዝ
ቅዱስ ወንጌል በዓለም መሰበክ
ርኩሱ በቅዱሱ ስፍራ መቆም
ደጋግ ሰዎች ለመከራ ተላልፈው መሰጠት መገረፍ መሞት
እነዚህና የመሳሰሉት የምጽአቱ ምልክቶች ናቸው
2 የምጽአቱ መቅረብ ምሳሌ
የበለስ መለምለም
በለስ በክረምት አትለመልምም በበጋ ነው የምትለመልመው
የበለስ መለምለም የክረምቱን ማለፍ የበጋውን መምጣት ወይም የመከሩን መድረስ
ታስረዳለች
የበለስ መለምለም የመከር መድረስ ምልክት እንደሆነ
የምጥ ጣር መጀመሪያም ምጽአት እንደ ቀረበ ያስረዳል
3 የአመጣጡ ሁኔታዎች
1 እንደ መብረቅ
መብረቅ በዝናም ጊዜ ሳይታሰብ እነደሚመጣ ሁሉ
ክርስቶስም እንዲሁ ባልታሰበበት ሰአት ይመጣል
2 እንደ ሌባ
ሌባ በሌሊት ባለቤቱ ባላሰበበት ባልጠበቀበት ሰአት ይመጣል የቤት ባለቤት ሌበው መቸ
እንደሚመጣ ቢያወወቅ ተዘጋጂቶ ይጠብቅ ነበር
ክርስቶስም መቸ እንደሚመጣ አይታወቅም ተዘጋጅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል
3 እንደ ኖህዘመን የጥፋት ውሃ
የጥፋቱ ውሃ በኖህ ዘመን ለነበሩ ሰዎች ባላሰቡት ባልጠበቁት ሰዓት መጥቶ
አጥፍቶቸውዋል
ክርስቶስም ባልታሰበበት ሰአት መጥቶ ይህን ዓለም ያሳልፈዋል
+የምጻቱ ፍጻሜ
የፀሐይ መጨለም የጨረቃ ደም መሆን የከዋክብት መርገፍ (ማለፍ)
ያንግዜ የሰው ልጅ ምልክቱ በሰማይ ይታያል
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ሙታን ይነሳሉ አውሬ የበላው ውሃ የወሰደው በጦር የሞተው
በምንም ዓይነት ሞት የሞቱት ሁሉ ይነሳል ሴቶች እንደሄዋን 15 ዓመት ሁነው ወንዶቹ እንደ
አዳም የ30 ዓመት ሁነው እንደ ዓይን ጥቅሻ እንደ ከንፈር ንክሻ ፈጥነው ይነሳሉ
ምድር አደራዋን ትሰጣለች
በነፋሳት እንደኳስ ትጠቀለላለች
ከነበረችብት ወዳልነበረችበት ይወስዳታል
የነፍስ ስራዋ ይገለጻል
ኀጥአን በገራው ጻድቃን በቀኙ ይቆማሉ
ስድስቱ ቃላተ ወንጌል ለመስክርነት በጥያቄ ይቀርባሉ
ለጻድቃን ይፈርድላቸዋል የአባቴ ቡሩካን ወደእኔ ኑ ይላቸዋል ከጸሐይ ሰባት እንጅ አብርተው
አምላካቸውን መስለው ወደ መንግሥተ ሰማያት ይሄሉ;;
በኀጥአን ይፈረድባቸዋል
ይፈርድባቸዋል እናንተ ርጉማን ሂዱ ይላቸዋል ከቁራ ሰባት እጅ ጠቁረው አለቃቸው
ዲያብሎስን መስለው ወደ ገሃነም ይሄዳሉ
በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
መጋቢት 1/2010
እግዚአብሔር በወዴት ይገኛል ቢሉ፡-

በደዌ ደኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘዉ በሚማቅቁ፣ አስታማሚና ጠያቂ አጥተዉ ዕለተ ሞታቸዉን በሚናፍቁ ምስኪን ህሙማን መካከል እግዚአብሔር ይገኛል፡፡

በባዶዉ አስፋልት ላይ ካርቶን አንጥፈዉ በሚተኙ ዝናቡ፣ ቁሩ፣ ዋዕዩ በሚፈራረቅባቸዉ፣ ቆሻሻ ገንዳ ላይ ተንጠላጥለዉ የበሰበሰ ፍራፍሬን ቀለባቸዉ ባደረጉ፣ ችጋር ጠንቶባቸዉ መማሪያ ክፍል ዉስጥ እንዳሉ በረሀብ በሚያሸልቡ የድሃ ድሃ ልጆች መካከል እግዚአብሔር ይገኛል፡፡

በግፈኞች ፍትህ ተንጋዶባቸዉ ባልዋሉበት እንደዋሉ፣ ባልሰሩት እንደሰሩ ተደርገዉ በጨለማ እስር ቤት በተወረወሩ፣ብረት በተቆለፈባቸዉ የህሊና ታሳሪዎችና የህዝብ ጠበቆች መካከል እግዚአብሔር ይገኛል፡፡

በእኩይ ባሎቻቸዉ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊም ጥቃት በደረሰባቸዉ፣ እጅግ የከበደዉን መከራ መቋቋም ተስኗቸዉ ቀኑ በጨለመባቸዉ እንዲሁም ቢጮሁ ቢጮሁ ሰሚ አጥተዉ ሌት ተቀን በሰቆቃ በሚባዝኑ አንስቶች መካከል እግዚአብሔር ይገኛል፡፡

ለዚህች ሀገር የሚችሉትን ሁሉ አበርክተዉ አቅማቸዉ ሲደክም ጉልበታቸዉ ሲከዳ ጧሪ ቀባሪ ጧሪ ቀባሪ በማጣት ቤታቸዉ በፈረሰባቸዉ እንዲሁም ለልመና እጅ በሰጡ አዛዉንት አባቶችና አሮጊት እናቶች መካከል እግዚአብሔር ይገኛል፡፡

ታዲያ እነዚህን አካላት ሲራቡ በማብላት፣ ሲጠሙ በማጠጣት፣ ሲታሰሩ በመጠየቅ፣ ሲታረዙ በማልበስ፣ ሲያዝኑ በማጽናናት ሲታመሙ በመንከባከብ በመርዳት ከጎናቸዉ ሆነን ችግራቸዉን ከተካፈልን ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን ምክንያቱም የእርሱ ቦታዉ እዚህ ነዉና ሁሌም በፍቅሩ ይጎበኘናል እኛ አናየው ይሆናል እንጂ እርሱ ሁሌም በፍቅር ይመለከተናል መሻታችንን ሁሉ ይፈጽምልናል የሚበልጠዉንም ያደርግልናል፡፡
«ሰው ተዘክሮተ ሞትን ገንዘብ ሲያደርግ ዘላለማዊ ቅጣትም እንዳለ ሲገነዘብ እግዚአብሔርን መፍራት ይማራል። በእያንዳንዱ ምሽት ቀኑን እንዴት ማሳለፍ እንዳለበት በእያንዳንዱ ቀንም ምሽቱን እንዴት ማሳለፍ እንዳለበት ይገነዘባል።»
.
/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
ፈቃደ እግዚአብሔር
ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
በአሁኑ ጊዜ በምንኖረው ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ግራ መጋባት ከሚፈጥሩብን ነገሮች ፈቃደ
እግዚአብሔርን የተመለከተው ቀዳሚ ሥፍራ የሚወስድብን ይመስለኛል፡፡የምናዝንባቸው፣
የምንበሳጭባቸው፣ መደረጋቸውን መቀበል እስከሚያቅተን ድረስ የምንረበሽባቸው ድርጊቶች
በተፈጸሙ ጊዜ መፈተናችን ይጨምራል፡፡ ነገሮቹ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሲሆኑ ደግሞ
የበለጠ እንፈተናለን፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወይ እምነታችን የተሳሳተ ካለበለዚያም
እግዚአብሔር የእኛን ጸሎት መስማት ያቆመ ይመስለናል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ደግሞ
መቋሚያቸው ይህ ብቻ አይደለም፤ ከፍተኛ ጥራጣሬ ላይ ጥለውን ብቻ ሳይሆን ደስታችንንም
ሰርቀውብን አጎረምራሚና ወቃሽ አድረገውን፤ በቤተ ክርስቲያናችንና በአንዳንድ የቤተ
ክርስቲያን አካላትም ላይ እንድናኮርፍ አድርገውን በአጠቃላይ መንፈሳዊ ሕይወታችንም ላይ
ከፍተኛ ጫና ፈጥረውብን ያልፋሉ ወይም እኛን ወደ ሌላ ሕይወት ያሳልፉናል፡፡ በተለይ
በእነዚህ ጊዜያት ‹‹ የእግዚአብሔር ፈቃድ›› ነው ተቀበሉ የሚል ሰው ከገጠመን
ልናደምጠው እንቸገራለን፤ አንዳንዴማ ልባችንን ዘልቆ ከገባው ሐዘን የተነሣ የሚናገርን ሰው
ሞኝነቱ ብቻ ሳይሆን በእኛ ኅሊና የተሳለው አላዋቂነቱም እየታየን ብስጭታችን ሊጨምር
ይችላል፡፡ ለመሆኑ ክፉ ሰዎች ግፍ ሲፈጽሙ ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማታለልና ተንኮል
የተፈጸመ ሲመስለን ይህን ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ብሎ መቀበል ይቻላልን?
ለመሆኑ የፈቃደ እግዚአብሔር ድንበሩ ምንድን ነው? ክፉ የሚመስሉን ሰዎች ሲሾሙ፣
በሀገርና በሕዝብ ላይ አስከፊ ነገር ሲፈጸም ፣ አደጋና ጥፋት ሲደርስስ ፈቃደ እግዚአብሔር
ነው ማለት ይቻላል? የምንፈልገው መልካም ነገር የማይፈጸመውስ ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር በጎው እንዲፈጸም አይወድምን? ወይስ ፈቃዱ የሚሆነው መቼ ነው? እነዚህ
ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጥያቄዎች ሆነው የሚያስቸግሩበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡
ጉዳዮቹን በቀጥታ ከማየታችን በፊት ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመቀበል የሚፈትኑን ነገሮች
እናስቀድም፡፡ ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር ካሉን የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ጥቂቶቹ
1) ክፉው ከእግዚአብሔር አይደለም
የፈቃደ እግዚአብሔርን ምንነት እንዳናውቅ የሚጋርዱ ብዙ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች
በውስጣችን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ከእነዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው ክፉው ከእግዚአብሔር
አይመጣም የሚለው ነው፡፡ቅዱሳት መጻሕፍት ግን ይህም ቢሆን ከእግዚአብሔር ነው
ይሉናል፡፡ ‹‹ ደዌና ጥዒና(ጤና)፣ ሞትና ሕይወት፣ ብልጽግናና ችግር መገኛቸው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው›› /ሲራ 11፤14-16/፡፡ በትንቢተ አሞጽም ላይ ‹‹ ወይስ ክፉ
ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?›› /አሞ 3፡6/
ይላል፡፡ በአጭሩ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ይመጣል፡፡ ለምን እንደሚመጣ ምክንያቱን
ለጊዜው አቆይተን የክፉ ወይም የማንፈልጋቸው ነገሮች መፈጸም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው
እንዴት ሊባል ይችላል? የሚለውን እንመልከት፡፡ እግዚአብሔር ክፉ አድራጊውን ክፉ
እንዲሆን አላደረገም፤ አያደርግምም፡፡ በሚፈጽሙት ማንኛውም ክፉ ነገርም ፈጻሚዎቹን
መጠየቁም አይቀርም፡፡ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የሚከፍል አምላክ ነውና፡፡ ክፉው
በሚደርስባቸው ሰዎች ላይ ግን የሚፈጸምባቸውን ነገር እንዳይደርስባቸው ሁልጊዜም
አይከላከልላቸውም፡፡ ይህም የሚሆነው ስለ ሦስት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያውና
ዋናው ከበጎ ብቻ የማንማርና የማንጠቀም ሰዎች ስላለን ነው፡፡ ሰዎች በባሕርያችን ደካሞች
ስለሆንን ብዙ ጊዜ በጎውን ነገር ባገኘን ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት አንችልም፡፡ ለእኛ
መልካም የመሰለን የሚደረግ ከሆነም ያ ነገር ሌሎቹን የሚጎዳ እንኳ ቢሆን ስለሌሎቹ
አንጨነቅም፡፡ ሌላው ቀርቶ መልካም የመሰለንና እስኪደረግልን የጓጓንለት ነገር በተፈጸመ
ጊዜ ከፈነጠዝን በኋላ ያሰብነውን ያህል እንዳልተጠቀምን በተረዳን ጊዜ እንደገና
እግዚአብሔርን ለመውቀስ ወደ ኋላ አንልም፡፡ ምክንያቱም ጥቅም የሚገኝ የሚመስለን እኛ
በጎ ነው ብለን በምናስባቸው ነገሮች መፈጸም ብቻ ስለሚመስለን ነው መጥፎ ከምንላቸውና
ከማይጠቅሙ ነገሮች ጥቅም እንደሚገኝ ካለማወቃችን በላይ እግዚአብሔር ከነዛ
የሚገኘውን ጥቅም ሊሰጠን ሲፈቅድም በመቃወማችን ብቻ ሳንጠቀም እንቀራለን፡፡ ሆኖም
እግዚአብሔር የሚጠቅሙን እስከሆነ ድረስ ክፉ የምንላቸውንም ማምጣቱ አይቀርም፡፡
በአንድ ወቅት በአንድ የቁሪት (ለራሳቸው የሚሆነውን ምግብና ምርት በየራሳቸው ሠርተው
በሚኖሩበት) ገዳም ውስጥ በሚኖሩ አባቶች የተፈጸመው ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን
ይችላል፡፡ በገዳሙ ከሚኖሩ አባቶች ውስጥ ሁሉም በሚባልበት ሁኔታ ምርታቸው በቂ
ስለማይሆንላቸው ይቸገራሉ፡፡ በተለይ ድርቅ በሚሆንበት ጊዜ የሚላስ የሚቀመስ
አስከማጣት ስለሚደርሱ ድርቅ እንደ እሾህ ይፈራሉ፡፡ ከዚህ የተነሣ በየዓመቱ እግዚአብሔር
ድርቅ እንዳያመጣ ብቻ ሳይሆን ጊዜውን ጠብቆ እንዲያዘንም፣ ነፋሳቱን እንዲያፈራርቅና
አስፈላጊውን ሁሉእንዲያደርግላቸው በምሕላ በሱባዔ እግዚአብሔርን በኅብረት ይለምናሉ፡፡
ይሁን አንጂ በአብዛኛው ድርቅ ይመታቸዋል፡፡ እነርሱም ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ
ያጎረመርማሉ፡፡ አንድ ነገር ደግሞ ሁልጊዜም ያስገርማቸዋል፡፡ በገዳማቸው ከሚኖሩት
አባቶች የአንዱ ምርት ሁልጊዜም ከፍተኛ ነው፡፡ ድርቅም ቢሆን ዝናብም ቢበዛ፣ ተምችና
አንበጣ ቢመጣ፣ ውርጭና በረዶ ቢፈራረቅ የዚህ አባት ምርት ሁልጊዜ ተመሳሳይ ነው፡፡
በዚህ ምክንያት አንዳንዶቹ ከመደነቅም አልፈው ይህ ሰው ምን የተለየ ነገር አለው እያሉ ወደ
መጠራጠርም ሔደው ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ጠየቁት፡፡እርሱም ምስጢሩን ነገራቸው፡፡ እኔ
ለሱባኤ ስንሔድ እግዚአብሔርን የምለምነው እኛ የምንፈልገውን ሳይሆን የሚጠቅመንን
እንዲያደርግልን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ድርቅ በሆነ ጊዜም እግዚአብሔር ድርቁን ያመጣው
ከዝናቡ ይልቅ ድርቁ ቢጠቅመን ነው ብየ ከልቤ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ በአንዳንዱ ዓመት
በዝናባማ ጊዜ ከማገኘው የተሻለም በድርቁ ጊዜ አገኛለሁ፡፡ በዚህም ድርቁ የመጣው
በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በሌላውም ጊዜ ቢሆን ማንኛውም ነገር ሲከሰት
አላጉረመርምም፤ ምክንያቱም ባይጠቅመን ኖሮ እግዚአብሔር አያመጣውምና አላቸው፡፡
እነርሱም የችግራቸው ምንጭ ድርቁ ወይም ሌላው ሳይሆን እነርሱ ክፉ የመሰላቸውን
ድርቁን በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አለማመናቸው መሆኑን ተረድተው ለንስሐ በቁ፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ በኢሳይያስ አድሮ ‹‹ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም
ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር
እኔ ነኝ›› /ኢሳ 45፤7/ የሚለንም በክፋት ፈጣሪነቱ ለመመካት ወይም ‹‹ ምን
ታመጣላችሁ›› ለማለት ሳይሆን ከሚደርስብን ክፉ ነገርም መጠቀም የምንችል መሆናችንን
ለመንገር ነው፡፡ በርግጥም እግዚአብሔር በብርሃኑ ብቻ ሳይሆን በጨለማውም የብርሃኑን
ያህል እንደጠቀመን እንደሚጠቅመንም ማመን ይገባናል፡፡ ክፉው እንዲገጥመን ፈቃዱ
የሚሆንበት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ነጻ ፈቃድን ሊሸራርፍ ስለማይወድ ነው፡፡
እግዚአብሔር ክፉዉንና በጎውን፣ ሩቁንና ቅርቡን የሚለይ አእምሮ ሰጥቶ ከፈጠረንና
እያንዳንዳችንም እንደ ሥራችን እንደሚከፈለን ከነገረን በኋላ በእያንዳንዷ ሥራችን ላይ
ጣልቃ እየገባ ይህንን ወይም ያንን አድርጉ፣ አታድርጉ አይልም፤ እንድናደርግ ወይም
እንዳናደርግም አያስገድድም፡፡ ይህ ሁሉ እንዲሆን ፈቃዱ ነው የሚባለውም በክፉው ነገር
መፈጸም የሚ
ደሰት ሆኖ ሳይሆን ክፉዎችን ለይቶ ያሰቡትን እንዳያደርጉ ስለማይከለክል
ነው፡፡ ነጻ ፈቃዳችንን ተጠቅመን እንድነሠራ አንድ ጊዜ ለሁላችንም ፈቅዷልና፡፡ አንዳንድ
ሊቃውንት ይህንን ፈቃዱን የእግዚአብሔር የፍጹምነቱ መገለጫ አድርገው የሚያቀርቡትም
ፍትሑን ረስቶ ፈቃዳችንን ጨልጦ ገርኝቶ አስትቶ እንደ ቁስ አካል በሠሪው ፈቃድ ብቻ
የማይጠቀምብን (ምንም እንኳ ከየትኛውም ድርጊታችን የሚጠቀመው ነገር ባይኖርም
ነጻነታችንን የማይጋፋ) መሆኑን ስለሚያሳይ ነው፡፡
ከዚህም አልፎ ክፉው ሳይደርስብን ብቻ ሳይሆን ደርሶብንም መጠቀም እንደምንችልና ሰዎች
ሌሎችን ለመጉዳት ሆነ ብለው ከሚፈጽሙት ክፉ ድርጊት እንኳ እግዚአብሔር ወዳጆቹን
እንዴት ፍሬያማ ማድረግ እንደሚችልና ሁሉን ቻይ መሆኑንም የሚያስተምረንም ከእነዚህ
መሰል ድርጊቶች ነው፡፡ ለምሳሌ በኢዮብ የደረሰውን መከራ ስንመለከት እንዴት
እግዚአብሔር እንዲህ ያደርጋል ሊያሰኘን ይችላል፡፡ በተለይ በቅዱስ መጽሐፍ ሳይጻፍ በእኛ
ዘመን ለሁላችን በታወቀ ሁኔታ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ‹‹ እግዚአብሔር ወዴት አለ?›› ልንል ሁሉ
እንችላለን፡፡ ኢዮብ ግን ያለው ‹‹እግዚአብሔር ሰጠኝ የሳባም ሰዎች ወሰዱብኝ›› ሳይሆን ‹‹
እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሣ ›› ነው፡፡ ይህን ያለው የሳባ ሰዎችን እግዚአብሔር
ልኳቸዋል ወይም በክፋታቸውና በግፋቸው እግዚአብሔር ይደሰታል ብሎ ሳይሆን
ፈቃዳቸውን እንዲፈጽሙ ያልከለከላቸው እነርሱ ካደረሱብኝ ግፍም እግዚአብሔር የሚሰጠኝ
በጎ ነገር አለ ብሎ ከልቡ በማመኑ ነው፡፡ በርግጥም ኢዮብ ከነበረው ሁለት እጥፍ ያገኘውና
ከቀደመ ክብሩ ወደሚበልጥ ክብር የተሸጋገረው እግዚአብሔር በክፉውም ውስጥ ያለውን
የማዳን ኃይል በማመኑ ነው፡፡በአንድ ወቅት በአንድ ገዳም በሚኖሩ አባቶችም ተመሳሳይ
ታሪክ ተፈጽሞ ነበር፡፡ በገዳሙ ካሉት አባቶች አንዱ ብዙ ተአምራቶችን የሚያደርጉ በተለይ
አጋንንትን በማስወጣት በፈውስ ታላቅ ሀብት የነበራቸው አባት ነበሩ፡፡ ገዳማቸው ደግሞ ብዙ
ጊዜ በሽፍቶች ይዘረፋል፤ ይቃጠላል፤ መነኮሳቱም ይደበደባሉ፤ ብዙ መከራም ይቀበላሉ፡፡
ከዚህ የተነሣም ብዙዎቹ ያማርራሉ፤ ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉ፡፡ ይህ ተአምራት ሚያደርግ አባት ግን
ምንም አይልም፡፡ በሁኔታው የተገረሙት መነኮሳቱም ለምን ዝም ይላል ብለው በአበ ምኔቱ
እንዲጠየቅ አደረጉት፡፡ ያ አባትም እነዚህ ሁሉ መከራዎች የሚመጡብን የእግዚአብሔር
ፈቃዱ ስለሆነ ነው፡፡ የሚደጋገሙብን ግን እናነተ ፈቃዱ ነው ብላችሁ ስለማታምኑና
ከአንዱም ለመማር፣ ከመከራ ከሚገኘው ጸጋም ለመሳተፍ ፈቃደኞች ስላልሆናችሁ ነው፡፡
መከራውን ያላቆመውም እግዚአብሔር ከዚህ የምታገኙት ጥቅም እንዳይቀር ቸል ባይላችሁ
ነው አለው፡፡ አበ ምኔቱም እግዚአብሔር ለዚያ አባት ተአምራት ማድረግን የሰጠው ክፉዉንም
ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ብሎ በመቀበሉ እንደሆነ ተረድቶ ተመለሰ ይላል፡፡ ስለዚህ ክፉ
ነገር ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጎጂ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚም ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ይህ
ማለት ግን እንዲያው እንደ ፊልምና ልቦለድ ወይም እንደ ነነዌ እሳት አይተነው ደንግጠን
ወይም አዝነን ብቻ በዚያው የሚቀርልን ነው ማለት አይደልም፡፡ በትክክል ደርሶብን
ሥጋችንንም ቆንጥጦን ተሰምቶን አንዳንድ ጊዜም እንደ ኢዮብ አስጨንቆንም የሚያልፍ
መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ ወደ ሦስተኛው ከመሸጋገራችን በፊት ግን ከላይ በተጠቀሱት
ሁለቱ ምክንያቶች የሚጠቀሙት እነማን እንደሆኑ ጠቆም አድርጌ ልለፍ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ በጻፈው መልእክቱ ‹‹ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ
አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን›› /ሮሜ 8፤28/ ብሏል፡፡ ስለዚህ
ከክፉው እንኳ ሳይቀር መልካም ፍሬ ማፍራት የሚቻላቸው ክፉው የደረሰባቸው ሁሉ
አይደሉም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ‹‹ ነገር ሁሉ ለበጎ›› የሚሆንላቸው ‹‹እግዚአብሔርን
የሚወዱትና እንደ አሳቡም የተጠሩት›› ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ ጥቅሱን ስላስታወስንና
የተረበሹ ሰዎችን ለማረጋጋት ስንል ‹‹ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው›› ስላልን ብቻ ነገር ሁሉ ለበጎ
ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን የሚወዱት ደግሞ ትዕዛዙን የሚጠብቁት ናቸው። እኛ
ትእዛዙን ሳንጠብቅ ወይም እግዚአብሔርን ሳንወድ ልክ እንደ መለወጫ ማሽን ክፉውን በጎ
የሚያደርግልን ኃይል ሊመጣ አይችልም፡፡ ስለዚህ ነገር ሁሉ ‹‹ ክፉውም ጭምር ›› ለበጎ
እንዲሆንልን የምንፈልግ ከሆነ የመጀመሪያው ደረጃ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሳንልከሰከስ
መጠበቅ ይገባናል፡፡ ሁሉተኛውና ከባዱ ግን ‹‹ እንደ አሳቡም የተጠሩት›› የሚለው ነው፡፡
ነገሩ እንደ አሳቡ እንደ ፈቃዱ መኖር ማለት ነው፡፡ ይህም በአጭሩ ከላይ በበረሐውያን
አባቶች መፈጸሙን እንዳየነው ድርቁንም ውርጩንም ሕማሙንም ድብደባ መከራውንም
እግዚአብሔር እንድቀበለው ፈቃዱ ከሆነ እርሱ ይሻለኛል ብሎ የሚቀበል ልቡና ወይም
ፍጹም እምነት ላይ መድረስን ይጠይቃል፡፡ በአጭር ቃል ከክፉው ለመጠቀም እንዲህ ያለ
እምነትና ተእዛዛተ እግዚአብሔርን መፈጸምን ወይም እግዚአብሔርን መውደድን ገንዘብ
ሳያደርጉ የሚያገኙት ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ክፉ ነገር ደርሶብን
ሳንጠቀም እንቀራለን፤ መጠቀም ስላልቻልንና ይሔ ስላልገባንም ገና አልገባቸውም
ተብሎም አይቀርልንም ማለት ነው፡፡
ሦስተኛው እግዚአብሔር ክፉ ነገርን የሚያመጣበት ምክንያት ደግሞ ከኃጢአታችን የተነሣ
ለመቅጣት ነው፡፡ ለምሳሌ ወዳጁን ዳዊትን እንዴት እንደቀጣው ማስታወስ እንችላለን፡፡ ‹‹ …
ናታንም ዳዊትን አለው። ያ ሰው አንተ ነህ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ
ይላል። በእስራኤል ላይ ንጉሥ ልትሆን ቀባሁህ፥ ከሳኦልም እጅ አዳንሁህ ፤ የጌታህንም ቤት
ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት
ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር። አሁንስ በፊቱ ክፉ
ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥
ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።
ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ
ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥
ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም
እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። አንተ ይህን በስውር
አድርገኸዋል እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሐይ ፊት አደርገዋለሁ ›› /2ኛ ሳሙ
12፤ 6 – 12/ ተብሎ እንደተጻፈው በዳዊት ላይ የመጣው ነገር ሁሉ ከክፉ ሥራው የተነሣ
እግዚአብሔርም በማያሻማ መንገድ ‹‹ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ›› ያለው
ለመቅጣትም ክፉ ነገርን የሚያመጣ እርሱ ስለሆነ ነው፡፡ እንዲያው በዚህ ዓይነት የበቀል
ጊዜ ክፉ ሰዎችን ወደጆቹን እንዲቀጡ ያነሣሣቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ‹‹ በተጎበኛችሁበት
ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለረድኤትስ ወደ ማን
ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?›› / ኢሳ 10፤3/ እያለ የሚዘልፋቸውን
እሥራኤልን ሊቀጣ በወደደ ጊዜ ስላስነሣው ስለ አሦር ‹‹ ለቍጣዬ በትር ለሆነ፥ የመዓቴም
ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት! እርሱንም በዝንጉ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፥ ምርኮውንና
ብዝበዛውንም ይወስድ ዘንድ እንደ አደባባይም ጭቃ የተረገጡ ያደርጋቸው ዘንድ
በምቈጣቸው ሰዎች ላይ አ
ዝዘዋለሁ። እርሱ እንዲሁ አያስብም፥ በልቡም እንዲህ
አይመስለውም፤ ነገር ግን ማጥፋት፥ ጥቂት ያይደሉትንም አሕዛብን መቍረጥ በልቡ አለ ›› /
ኢሳ 10፤ 5-7/ እያለ የሚናገረው ተበቃዩን አስነሹም እርሱ ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ግን
ደግ የነበረውን ሰው ለመበቀል ሲል እርሱ አከፍቶታል ማለት አይደለም፡፡ ‹‹ጥቂት
ያይደሉትንም አሕዛብን መቍረጥ በልቡ አለ›› ተብሎ እንደ ተጻፈው በሰውየው ዘንድ ማጥፋ
ወይም ክፋት ነበረ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ያን ክፉ ሰው ቀደም ብለን እንደገለጽነው ክፋቱን
ይፈጸም ዘንድ ካለመከልከሉ በላይ ልቡን ሌሎቹን ከማጥፋት እግዚአብሔር ሊቀጣቸው ወደ
ፈቀደው ወደ እሥራኤል አነሣሣው ማለት ነው፡፡ ‹‹ እርሱ እንዲህ አያስብም፤ በልቡም
እንዲህ አይመስለውም›› የተባለውም ሰውየው ቀድሞ ይህን የመሰለ ክፋት ማድረግ በልቡ
ስላለ ባጠፋ ጊዜ እግዚአብሔር በእኔ አድሮ አጠፋ ብሎ ሊያስብ አይችልም፤ ምክንያቱም
ክፋቱ የራሱ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህን ክፋቱን እርሱ ሊቀጣቸው በወደደው ሕዝብ ላይ
እንዲፈጽም በማድረግ አሦርም ክፋቱን እግዚአብሔርም ቅጣቱን በአንድ ሕዝብ ላይ አደረጉ
ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሔር አሥራኤልን በአሦር መቅጣቱ አሦርን ከፍርድ ነጻ
የማያደርገው፡፡ ‹‹ ለቍጣዬ በትር ለሆነ፥ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት!›› /
ኢሳ 10፤5/ ተብሎ የተጻውም ለዚህ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የቀጭወቻችን ወይም መከራ
የሚያመጡብን ሰዎች ከሐዲነትና ክፋት እኛን ጻድቅ አያደርገንም ወይም ደግሞ መከራውንና
ስቃዩን የማይገባን ሊያደርገው አይችልም፤ እግዚአብሔር ለእነርሱ ፈቅዶ እኛን እንድንቀጣ
ማድረጉም ቀጭዎቹን ጻድቃን ወይም እግዚአብሔርንም የተሳሳተ አያደርገውም፡፡ ስለዚህም
ክፉ ሰዎችን አስነስቶ የሚቀጣ፣ መከራና ስቃይ የሚያመጣም እግዚአብሔር ነው ማለት
ነው፡፡ አማኞች የሆኑ ሰዎች ግን ከዚህም መንፈሳዊ ፍሬን ሊያጭዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ
ከላይ በጠቀስነው የቅዱስ ዳዊት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ዳዊት ተነግሮትና ጥፋቱንም አምኖ
የተቀበለው ስለሆነ በሁለት መንገድ ተጠቅሟል፡፡ በመጀመሪያ ቅጣቱን ወይም መቅሰፍቱን
ይገባኛል ብሎ ስለተቀበለ መንግሥቱ ጸንቶለታል፤ እጂግ ከከፋ መከራም ድኗል፡፡
ሁለተኛውና ዋናው ጥቅሙ ግን እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍላልና ኃጢአቱ
የምታመጣበትን ፍዳ በምድር ላይ በመቀበሉ ስለ ኃጢአቱም ሥርየት በማግኘቱ በሰማይ
ሊገጥመው ከሚችለው የዘላለም ቅጣት አመለጠ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም በምድር
የገጠመችው ቅጣት ሊነጻጸር ከማይችል ዘላለማዊ የነፍስ ቅጣት ስላዳነችው ከፍተኛ
ተጠቃሚ ሆኖአል፡፡ ‹‹ እንደ አሳቡም ለተጠሩት›› የሚለው የሐዋርያው ቃል ከተፈጸመላቸው
ሰዎችም አንዱ ዳዊት ነው፡፡ እንደርሱ የእገዚአብሔርን አሳብ ወይም ፈቃድ የሚቀበል ሰው
አልነበርምና፡፡ ይህም ሳዖል ያህልን አሳዳጁን ሁለት ጊዜ ለመግደል ተመቻችቶ ባገኘው ጊዜ
ከዘፈረ ልብሱ እየቆረጠ ማድረግ የሚችል መሆኑን እያሳየ ለፈቃደ እግዚአብሔር ሲል
(ቀብቶ ያነገሠውን አልገድልም) ብሎ የተወ በርግጥም እንደ እግዚአብሔር አሳብ የሚኖር
ሰው ነበርና፡፡ እንኳን እግዚአብሔር ለቀባው ለሳዖል ይቅርና ለፍልስጤማውያንም ‹‹ ልሂድን?
እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ እግዚአብሔርም
ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው›› /1ኛ ሳሙ 23፤2/ ብሎ
ይጠየቅ ነበርና፡፡ እግዚአብሔርም ለዳዊት ‹‹እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ
የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ›› /ሐዋ 13፤22/ ሲል የመሰከረለት የዳዊት ጦርነትና ግድያ
የእግዚአብሔርን አሳብ የተከተለ እንጂ እንደነ አሦር በጭካኔና ለራሱ ገናንነት ሲል
የሚያደርገው ስላልነበረ ነው፡፡
በዚህ ዘመን የምንኖር እኛ ፈቃደ እግዚአብሔር ሳናውቅ አሳቡንም ሳንረዳ የምንኖረውና
የምንቸገረውም ስለ ክፉ ነገሮች ካለን የተሳሳተ አሳብ የተነሣ ነው፡፡ እኛ ምቾትን እንደ ነዌ
ጽድቅንም ወይም በአብርሃም እቅፍ መቀመጥንም እንደ አልዓዛር የምንፈልግ ሰዎች ነን፡፡
ይህ ደግሞ ከባድ ነገር ነው፡፡ ለመጽደቅ የግድ እንደ አልዓዛር መደኸየትም በደዌ
መሰቃየትም የማያስፈልግ ቢሆንም ቢያንስ ግን ስለ ኃጢአታችን የሚመጣውን መከራና
ስቃይ ለመቀበል ፈቃደኞች ካልሆንን ስለጠላነው ብቻ ክፉው እንዴት ሊቀር ይችላል?
ክፉዎችንስ በክፋት እንዴት ልናስወግዳቸው እንችላለን? ዘዴያችን እንደ አታላይ ፖለቲከኞች፣
ሀሳባችን እንደ ብልጦች ሆኖ ጽድቃችን እንደነ ዳዊት እንዴት ሊሆን ይችላል? ኃጢአታችን
እንደ ሰዶም እንደ ገሞራ ሰዎች፣ ቸልተኝነታችንም እንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች መሆኑ ፍጥጥ ብሎ
እየታየ መሪዎቻችን እንደ ዳዊት እንደ ሰሎሞን በረከቱና ሰላሙስ እንደ ብሔረ ሕያዋን እንዴት
ሊሆን ይችላል? የምንሠራውን ሥራና ያለንበትን ሕይወት እንደ ጽድቅ ቆጥሮ እግዚአብሔርን
እንበደለኛ ከመቁጠርስ የሚበልጥ ምን ድፍረት አለ? ትልቁ ፈቃደ እግዚአብሔርን
ለላማወቃችን መጋረጃ የሆነብንንም ይሔው እየደረሰብን ነው የምንለውን ክፉ ነገር ፈቃደ
እግዚአብሔር ነው ብለን መቀበል አለመቻላችን ነውና
Forwarded from ገብረ እግዚአብሔር ኪደ (ገብረእግዚአብሔር ኪደ)
እግዚአብሔር ከአባት፣ ከእናት፣ ከጓደኛ፣ ወይም ይወደናል ከምንለው ከሌላ ከማንም ሰው በላይ ይወደናል፡፡ ከእነዚህ ኹሉስ ይቅርና፥ እኛ ራሳችንን ልንወደው ከምንችለው መጠን በላይም በኾነ መውደድ ይወደናል፡፡
@yohansafework
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብርሔር
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ሔር (ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ
ያገኘበትም ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ሔር ወገብር
ምእመን ገብር ዘአስመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ
ነው፡፡ ገብርሔር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ
ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡
ምስባክ መዝ. 39÷8
"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"
ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ።
ወንጌል
ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ
ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ
ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄደ፤
ነግዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡
አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታዉን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ጊዜም
በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ ተቈጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም
ቀረበና፡- አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ ብሎ አምስት
መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ
ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም
መጥቶ፡- አቤቱ÷ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን
አተረፈሁ አለ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለ
ሆንህ በብዙ አሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለውም
መጣና እንዲህ አለ፡- አቤቱ÷ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ÷ ካልበተንህበትም
የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን
በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ÷ መክሊትህ፡፡ ጌታውም መልሶ አለው፡- አንተ
ክፉና ሰነፍ አገልጋይ÷ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ÷ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ
ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ
መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡
ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፤ ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት
ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን
ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን÷ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ
አለ ጨለማ አውጡት፡፡
ዲያቆን (ምንባብ)
2ኛ ጢሞ.2÷1-15 ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ
ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች
እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ
ተቀበል፡፡ ወደ ሰልፍ የሚሄድ÷ አለቃውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ነው እንጂ የዚህን ዓለም ኑሮ
አያስብምና፡፡ የሚታገልም ቢሆን እንደ ሕጉ ካልታገለ አክሊልን አያገኝም፡፡ የሚደክም አራሽም
አስቀድሞ ፍሬውን ሊያገኝ ግድ ነው፡፡ ያልሁህን አስተውል፤ እግዚአብሔርም በሁሉ ነገር
ጥበብን ይስጥህ፡፡
በወንጌል እንደምሰብከው÷ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ
ክርስቶስን አስበው፡፡ ስለ እርሱም እንደ ወንጀለኛ አስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤
የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም፡፡ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን
ሕይወትና የዘለዓለም ክብር በሰማያት ያገኙ ዘንድ÷ ስለ ተመረጡት ሰዎች በሁሉ ነገር
እታገሣለሁ፡፡ ነገሩ እውነት ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት
እንኖራለን፡፡ ብንታገሥም ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው ግን እርሱም ይክደናል፡፡
ባናምነውም እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይቻለውምና፡፡
እንግዲህ ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ÷ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ
ምንም የማይጠቅም÷ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና፡፡የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት
አቃንቶ ሲያስተምር እንደማያፍር ሰራተኛ ሆነህ ፣ራስህን የተመረጠ አድርገህ ለእግዚአብሔር
ታቀርብ ዘንድ ትጋ።
ንፍቅ ዲያቆን (ምንባብ)
1ኛ ጴጥ.5÷1-11 እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷
ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን
እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤
ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ
እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡ ለመንጋዉ ምሳሌ ሁኑ እንጂ ሕዝቡን በኀይል
አትግዙ፡፡ የእረኞችም አለቃ በተገለጠ ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡
እንዲሁ እናንተ ጐልማሶች ሆይ÷ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ልበሷት፤
እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳልና፤ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትን ግን ያከብራቸዋል፡፡
እንግዲህ በጐበኛችሁ ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርጋችሁ ዘንድ ከጸናችው ከእግዚአብሔር ክንድ በታች
ራሳችሁን አዋርዱ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡
እንግዲህ ዐዋቂዎች ሁኑ፤ ትጉም፤ ጠላታችሁ ጋኔን የሚውጠውን ፈልጎ÷ እንደሚያገሳ
አንበሳ ይዞራልና፡፡ እርሱንም በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፤ እንዲህም ያለ መከራ በዓለም
በአሉ ወንድሞቻችሁ ሁሉ እንደሚፈጸም ዕወቁ፤ ፍቅርንም አጽንታችሁ ያዙአት፡፡ በኢየሱስ
ክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን
ከተቀበላችሁ በኋላ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ልባሞችም ያደርጋችኋል፡፡ለእርሱ
ክብርና ኅይል እስከ ዘለአለም ይሁን፤አሜን።
ንፍቅ ቄስ (ምንባብ)
የሐዋ.1÷6-8 እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች
መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ
ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ
በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና
እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"
ቅዳሴ
ዘባስልዮስ
ብሒለ አበው በእንተ ጸሎት

❖ ለአምላካችን መዓዛ ያለው ሽታ ፊጣሪን የሚያመስግን ልብ ነው፡፡
/ ቅድስ አግናጥዮስ/
❖ ለመጸለይ የሚስችል እድልን ባገኘህ ጊዜህ ለመጸለይ ወደ ኋላ አትበል አትቦዝንም፡፡
ከዚህ የተነሣ ጊዜህን አላግባብ ከማጥፋት ይልቅ በፀሎት መጠቀም ትችላለህ ፡፡
/ አቡነ ሺኖዳ/
❖ እነዚህ ኸሉም ጸሎታት ግን ያለመሰልቸት በእግዚአብሔር ፊት መቆምንና ሌሎች
ጸሎቶችን ከማድረስ የሚያግድ አይደሉም ፡፡
/ አቡነ ሺኖዳ/
❖ ሰው ጸሎትን በተወ ጊዜ የሞት መሣሪያውን መሥራት ይጀመራል ፡፡
/ ቅድሳን አብው /
❖ ጸሎት ለሚወዱ ሰዎች እግዚአብሔር ያድርባቸዋል... መከራ ከሚመጣባቸው
ከሚያሳዝናቸው ከሰይጣን ያሳርፋዋል፡፡
/ አረጋዊ መንፈሳዊ /
❖ በጸሎት ልብ እግዚአብሔር ጋር አንድ ይሆናል ፈጣሪውን ይመስላል፡፡ ብዙውን ሀብት
ገንዘብ ይደርጋል ፡፡ ምሥጠራት ከእርሱ ይገኛሉ፡፡ በጸሎት ሀብታት ምሥጠራት ይገለጽለታል
፡፡ ሀብታት ምሥጠራትን ደስ እያለው ገንዘብ ያደርጋል ፡፡
/ አረጋዊ መንፈሳዊ /
❖ የማይጸልይ ሰው ቅጽር የሌላትን ሀገር ይመስላል ፣ ያን ማንም እየገባ እንዲዘርፈው
እርሱም የተሰጠውን ፀጋ ያጣል
/ ማር ይሰሕቅ/
❖ ከሕፃንነት ያለፈ ሰው ሁሉ ለመዳን ፀሎት የግድ እንደሚያሰፈልገው የሃይማኖት
ትምህርት ነው ፡፡
/ ፈሊክሰዮስ /
❖ ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ፀሎት ናት ፡፡
/ አረጋዊ መንፈሳዊ/
መልካም ዕለተ ሰንበት
🔺 ኑ እና እንዋቀስ!!!📜🔺

እጅግ አስተማሪ ትምህርቶችን በዚህ ዘመን ባሉ የቤተክርስቲያን ፈተናዎችን ከቅዱስ ወንጌሉ ጋር አስማምተን እንማማራለን።
🔴ኑ እና እንዋቀስ🔴
@bahiretibebat
ኑ እና እንዋቀስ 📜

*ርግብ ሻጮቹ*
ከዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
ጌታችን ወደ ቤተ መቅደስ ከገባ በኃላ ሻጮችን ሆነ ገዥዎችን አባሪሯል። ወደ ርግብ ሻጮቹ
መቀመጫ ከደረሰ በኃላ ግን ገበታቸውን ገልብጦ "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ
ተጽፋል እናንት ግን የወንበዴዋች ዋሻ አደረጋችሁት " ብላል በዚህ ንግግሩ ወንበዴዌች
ያላቸው። ርግብ ሻጮች መሆናቸው ይታወቃል።
ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንደተረጎሙት"ርግብ" የመንፋስ ቅዱስ ምሳሌ ስለሆነች
<< ርግብ ሻጮች >> ተብለው ጸጋ መንፋስ ቅዱስ ሀብተ ክህነትን ለምድራዊ መኖርያ ብቻ
የሚገለገሉባት ናቸው። እነዚህ ደሞ ከጥንት ጀምረው ገበታቸውን ደርድረው በቤት መቅደስ
አካባቢ ሲሸጡ ይኖራሉ። ክህነታቸው የተሰጣቸው ፀጋና የቤተክርስቲያን ሀላፊነት ሁሉ
ለገንዘብና ለገንዘብ ብቻ የሚጠቁሙ ሁሉ የዘመናችን ርግብ ሸጫች ናቸው። የነዚህን ሰዎች
ገበታ ጌታ ይገለብጠዋል ፤ ያባራቸዋል። "እውነት እውነት እላችሀለሁ አላውቃችሁም። /
ማቴ 7፥22/ እላችዋለው ብላልና።
በርግጥ ይህን ነገር አገልግሎት ፈጽመው ከቤተክርስቲያን ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ
የሚቀበሉትን የሚመለከቱ እንደልሆን ማስተዋል ተገቢ ነው። እንዚህ "የሚያበረየውን በሬ
አፋን አትሰር "1ኛ ቆሮ.9፥9 / የተጻፈላቸውን አገልጋዮች ናቸውና አይመለከታቸውም።
እርግብ ሻጮች እነማን ናቸው ?
በፈውስና በታአምራት ስም የቤተክርስቲያንን ዓውደ ምህረት ይዘው ንግዳቸውን የሚያጠፉ
አይደለምን ? በመንፈሳዊ ዛር ከብረው ሰውን ሁሉ በቅቻለሁ እያሉ ባለ ትዳሩን እያፋቱ
እጮኛሞችን እያለያዩ በሀብተ መንፋስ ቅዱስ የሚነግዱ አይደለምን። ? ቤተክርስቲያን
በመርዳት ገዳማትን በመሣሰሉት እያሳበቡ። የራሳቸውን ቤቶች የሚነግዱ በክህነት
በአገልግሎት ሰበብ ፖለቲካቸውን የሚቸረችሩ አይደሉም ? በቤተ ክርስቲያን ሰበብ ራሳቸውን
የሚያለሙ አይደለምን ? እኔን እግዚአብሔር ያመለክተኛል እኔ በማዝህ ብቻ ስራ እያሉ ከባለ
ጸጎች ተጠግተው ቤት አስርተው የጸሎት አባት እየተባሉ በሀብተ መንፋስ ቅዱስ በበቁት
ቅዱሳን ስም የሚነግዱት የእየ አንዳንዱ ባለጸጎች የግል ጠንቋዮች አይደለምን ? የሰውን
አለማወቅ ተጠቅመው ለንስሀ እንኳ ትልልቅ ገንዘብን የሚሰበስቦችን አይደለምን ? እስከ ዛሬ
በክህነቱ የማይነግድበት የተባረከ ማን ይሆን። የተሰጣቸውን ጸጋ እስከዛሬ ድረስ ለጥቅሙ
የማያመቻችስ ? እረ ለመሆኑ ዛሬ በእኛ ዘመን በእጅጉ የሚከፋቸው መቼ ነው ?
የቤተክርስቲያን ክብር ሲዋረድ ወይስ የእኛ ክብር ትንሽ ሲነካ ? ማን ይሆን ዛሬ ርግብ
የማይሸጥ ? በየሰበካው ያሉ ጠቦቶች ምክንያት ምን ይሆን ?አንዱ ተባሮ አንዱ የሚመጣበት
ምክንያቱ ?
ርግብ ጸጋ እግዚአብሔር እንደዚህ ዘመን በቤት ክርስቲያን የሚሰጥበት ዘመን ይኖር ይሆን ?
እኔ እንጃ ! በእርግጥ ርግብ ሻጫች ዘመን። ለዚህ ነው ጌታ በዚህ የተጠምድትን ሁሉ
የወንበዴ ዋሻ አደረጋችሁት ያለው። ምክንያቱም ሰዎች ወንበዴም ቢሆኑም የሚፈጽሙት
ተግባር መንፈሳዊ የሚያስመስል ቅባት ስለተቀባ። "ዋሻ "መደበቂያ ማታለያ ለመሆን
በቅታለች። ስለዚህ ዋሻ ያላት ግብሪችሁ የወንበዴ ቢሆንም አንደኛ ክህነታቸው
ከእግዚአብሔር ስለሆነች እውነትኛ መስላቸሁ ትኖራላችሁ ለማለት ነው። አሁን እየሆነ
ያለው ይሄ ይመስላል ጌታ ጅራፉን ገምዶ በሚመጣ ጊዜ ግን የሚያቆመውን እንጃ።
እርሱም ይህን አውቆ ይመስላል ፤ እንክርዳዱን እንነቅለዋለን ስትሉ ስንዴውን አብራችሁ
እንዳትነቅሉት ተውት እስከመከር ድረ ስ አብሮ ይቆይ። /ማቲ 13፥ 29 /ሲል ያዘዘው። ልክ
ነው ሁሉም እስከ እርሱ መምጣት በትእግስት ይጠበቃል። እንክርዳዱን ከስንዴው
፣ምርቱንም ከገለባው የሚለየ ባለ መንሹ እርሱ ነውና። ልክ ነው እርሱ ገበታቸውን
እስኪገለብጥ ድረስ ርግብ ሻጮች የሆነን በቤት መቅደስ እንኖራለን። ፥የዋሁን ምእመንም
እግዚአብሔር ያገኙ እርሱንም ያገለገሉ እየመሰላቸው ርግብ ሻጪዎችን ሲያከብሩ ይኖራሉ።
ለነገሩ ባለቤቱ "በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ለህዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው
ጻሀፍትና ፋሪሳዊያን በሙሴ ወንበር ተቀሞጠዋል። ስለዚህ የያዛችሁትን ሁሉ አድርጉ
ጠብቁም። ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ "/ማቴ23፥1-3/
ሲል ያሰጠነቀቀንም። ክህነትንና ሰብአዊ ባህርያት ለይተን ተረድተን ስህተት የመሰለንን
እያወራን እርሱ በሰጠው ጸጋ ሳንጠቀም እንዳንቀር ነውና እውነቱን የሚያስፈልገንን
ተጠቅመን ለመንግስቱ እንድንበቃ ቸርነቱ ይርዳን
አንድ ክርስቲያን መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ኹለት መንገዶች አሉት፡፡ አንደኛውና ተመራጩ ምንኩስና ነው፡፡ ኹተኛው ደግሞ የጋብቻ ሕይወትን መርቶ ነው፡፡ ጋብቻው ራሱ መንግሥተ ሰማያትን ዓላማ ያደረገ ካልኾነ ኦርቶዶክሳዊ ትዳር አይባልም፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኑ እንዋቀስ
ለሰዎች ምሕረትን እናሳያለን?
ደጉ ሳምራዊ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ እንጂ በተግባር ከእኛ ልብ ወጥቷል፡፡
እነሆም አንድ ሕግ አዋቂ ፈሪሳዊ ኢየሱስን ሊፈትነው ተነስቶ፦ “መምህር ሆይ የዘለዓለምን
መንግስት እንድወርስ ምን ላድርግ?” አለው። “እርሱም በሕግ የተጻፈው ምንድር ነው?
እንዴትስ ታነባለህ?”አለው። ፈሪሳዊውም መልሶ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣
በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህም ውደድ፣ባለእንጀራህን እንደርስህ ውደድ”አለው።
ኢየሱስም “እውነት መለስህ ይህንን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ” አለው። ፈሪሳዊው ግን
ራሱን ሊያጸድቅ ወዶ ነበርና ኢየሱስን “ባለንጀራየስ ማን ነው ? ” አለው። ኢየሱስም መልሶ
እንዲህ አለ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ
ወደቀ፤እነርሱም ደግሞ ገፈፉት፤ደበደቡትም፤በህይዎትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።
ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ፤አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ። እንዲሁም አንድ
ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ
መጣ አይቶትም አዘነለት፤ቀርቦትም ዘይትና የወይን ጠጅ በቁስሎቹ ላይ አፍስሶ
አሰራቸው፤በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች መቀበያ ወሰደው ጠበቀውም።
በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና 'ጠብቀው ከዚህም በላይ
የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ' አለው። እንግዲህ ከእነዚህ ከሦስቱ
በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመልሃል? ” አለው እርሱም
“ምህረት ያደረገለት”አለ። ኢየሱስም “ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ”አልው።
የደጉ ሳምራዊ ታሪክ በአዲስ ኪዳን በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 10፡ 25 – 37 ድረስ ባለው
ክፍል ውስጥ ይገኛል።