Call for KA171 2024 Project Mobilities: Sivas Cumhuriyet University (SCU), Türkiye
As a part of Bahir Dar University’s ongoing partnership with Sivas Cumhuriyet University, Türkiye, the External relations and Partnership Directorate is pleased to announce the call for KA171 2024 Project Mobilities for yet another year.
Please find the call at https://erasmus.cumhuriyet.edu.tr/2501-erasmus-incoming-staff-mobility-call-2022-2023-2024-ka171/ and apply ONLY starting from 27th January 2025.
Applications will be received by the host institution (SCU) on their system. Any application other than those in their system will not be taken into consideration.
Please Note:
- All mobilities are to be realized within the framework of the 6th International Staff Week (ISW) that will be held from 12- 16 May 2025
- Should you have any questions or need further information, please write your queries to sisayayalew21@gmail.com.

SCÜ Erasmus+ Kurum Koordinatörlüğü
Erasmus+ Incoming Staff Mobility Call (2022, 2023, 2024 KA171) [Call No: 2501] - SCÜ Erasmus+ Kurum Koordinatörlüğü
#Update
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከጥር 8-14/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et
ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራችሁ ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በተከታዮቹ አማራጮች ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡
Email: ngat@ethernet.edu.et
☎️ 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683
Note:
➫ የመፈተኛ User Name እና Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ይሆናል።
➫ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምዝገባ ማድረግ የሚቻለው በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ብቻ ነው፡፡
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share

exam.ethernet.edu.et
Ministry of Education
Ministry of Education | National GAT
Bahir Dar University,Ethiopia pinned «#Update በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከጥር 8-14/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራችሁ ጥያቄ…»
የሞገደል ተፋሰስ ሞዴል መንደር ልማት ፕሮጀክት የአጋር አካላት ውይይት ተካሄደ
*****
ጥር 9/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የሞገደል ተፋሰስ ሞዴል መንደር ልማት ፕሮጀክት አጋር አካላት የፕሮጀክቱን የስራ ሂደት አስመልክቶ በማሕበራዊ እና ምጣኔ ሐብት፣ በተፈጥሮ ሕብት፣ የሰብል ልማት እና አትክልትና ፍራፍሬ እና በእንስሳት ሐብት ልማት ዙሪያ በተሰሩ ጥናታዊ ፁሁፎች ላይ በጥበብ ሕንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የአንድ ቀን ውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ፕሮፌሰር መልካሙ አለማየሁ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ እንደማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመማር ማስተማር፣ በምርምር ፣በማህበረሰብ ተሳትፎና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በትኩረት በመስራ በግብርናው ዘርፍ ለሀገራችን እደገት መሰረት የሆነውን በእውቀትና በክህሎት የዳበረ የተማረ የሰው ሃይል በማብቃት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮሌጁ በምርምር ዘርፉ የኮሌጁን እና የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ በሚችሉ የተለያዩ ምርምሮች ላይ በመሳተፍ በምርምር የተገኙ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ በማድረግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ከፍ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት አበርክቶው የላቀ መሆኑን የሞገደል ተፋሰስ ሞዴል መንደር ልማት ፕሮጀክት ማሳያ መሆኑን ፕሮፌሰር መልካሙ ገልፀዋል፡፡
የሞገደል ተፋሰስ ሞዴል መንደር ልማት ፕሮጀክት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራት በተፋሰሱ አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ በማድረግ ለሦስት ዓመት የግብርና እና የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬን መሰረት አድርጎ መሰራቱን ተናግረዋል፡፤
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ተሳትፎና ኢንዱስትሪ ትስስር ኮርፖሬት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ንጉስ ጋብዬ በበኩላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ከማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ወደ ማህበረሰብ ተሳትፎ በማሻሻል በብር አዳማ፣ በቆለላ፣ በባህር ዳር ዙሪያ እና በቅርቡ በሚጀምረው የጣና ቂርቆስ ገዳም አካባቢ የግብርና እና የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ጠንካራ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሞገደል ተፋሰስ ሞዴል መንደር ልማት ፕሮጀክት የአጋር አካላት ውይይት መድረክ ላይ የፕሮጀክቱን የሦስት ዓመት የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ በማሕበራዊ እና በምጣኔ ሐብት፣ በተፈጥሮ ሐብት፣ የሰብል ልማት እና አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳት ሐብት ልማት ጥናታዊ ፁሁፎች ቀርበው በውይይቱ ተሳታፊዎች የጋራ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ ተሳትፎ ም/ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እንየው አድጎ በበኩላቸው ተመራማሪዎች ለምርምር ከሚያነሷቸው ችግሮች ይልቅ አርሶአደሮች ለሚያነሷቸው ችግሮች የምርምር መነሻ ሐሳብ በማድረግ ጥናቶችን በማካሄድ አርሶአደሩ ዘላቂ መፍትሄ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
በጋራ የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ የግብርና ቢሮ፣ የግብርና መምሪያ፣ አርሶአደሮች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮ ኃላፊዎች እና መምህራን ተገኝተዋል፡፡

ሥርዓተ-ፆታ ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት ተካሄደ
***
ጥር 10/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BDU-IUC) ፕሮጀክት ከዩኒቨርሲቲው የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የሥርዓተ-ፆታን ምንነትና በኤች አይቪ ኤድስ ላይ ያለውን አሁናዊ ግንዛቤና ጭብጥ የተመለከተ የሁለት ቀን አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡
በአውደ ጥናቱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BDU-IUC) ፕሮጀክት ማናጀር ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው፤ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተቀዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጎጃም ወንድይፍራው፤ የግቢ ዲኖች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በመድረኩ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ስለ (BDU-IUC) ፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ እና ስለ መርሀ-ግብሩ አላማ ገለጻ በማድረግ መልዕክት ያስተላለፉት የBDU-IUC ፕሮጄክት ማናጀር ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው እንደተናገሩት በስርአተ ጾታ ላይ ያለው የተዛባና ሚዛኑን ያልጠበቀ አረዳድና አሰራር አንዲሻሻል በግለሰብ፤ ቤተሰብና ማህበረሰብ ድረስ ዘላቂነት ያለው ግንዛቤ የማስጨበጥና የተግባራዊ እንቅስቃሴ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
እንደ ትምህርት ተቋምም የመማር ማስተማር ስራዎች እና የምርምር ስራዎች ሲሰሩ የስርአተ ፆታን ጉዳይ ማለትም የሴቶችና የወንዶች እኩል ተሳታፊነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ይህም ሲባል እያንዳንዱ ተቋም እቅዶቹን ሲያቅድና ስራዎችን ሲሰራ የጾታን ጉዳይ ታሳቢ ያደረገ፤ አካታችና አሳታፊ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ብለዋል ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተቀዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጎጃም ወንድይፍራው በበኩላቸው አውደ ጥናቱ ከBDU-IUC ፕሮጄክት ጋር በመተባበር ስርአተ ጾታና ኤችአይቪ ኤድስ ላይ በአሁኑ ወቅት በተቋማችን አመራሮች በተለይም የግቢ ዲኖች ፤ተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ ያለው አስተሳሰብና ግንዛቤ እንዲሁም የሚደረገውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መርሀ ግብር ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሙሉጎጃም አክለውም ሥርዓተ-ፆታ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይትና ምክክር ማድረግ አጀንዳ የሆነበት ምክንያት በስርአተ ጾታ ላይ ያለውን የተዛባ አረዳድ ሚዛናዊ በማድረግ በተለይም ሴቶች በሁሉም ስራና ተግባር ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ለሀገራዊ እድገት የሚያበረክቱትን ወሳኝ ሚና አጉልቶ ለማሳየትና የተቋማት የትኩረት ነጥብ ለማድረግ በመፈለግና ቅንጅታዊ አሰራርን ለመመስረት በማለም ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ ሦስት ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በዶ/ር ሰውመሆን ደምሴ፤ የሥርዓተ-ፆታ ኦዲት (Gender auditing) ገላጭ ጥናት፤ በአቶ ዮሃንስ መርሻ ሥርዓተ-ፆታን ማካተት (Gender Mainstreaming) እና በአቶ ምክሩ ሽፈራው HIV Mainstreaming በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ከታዳሚው ሰፋ ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው በጽሁፍ አቅራቢዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡