Bi/ga/wo/ji/pa/we/li/bo/mine
6 subscribers
77 photos
3 links
Duuchunku hadaarini wedella horaamesa assa!!!!
Download Telegram
አምስቱ የመፍትሄ ቁልፎች ፦

1ኛ. ውይይት
👉 ለሰላም፣ አብሮ ለመኖር መፍትሄው ንግግር ብቻ ነው። ስልጣን ለመጋራት፣ ህገ መንግስት ለመቀየር ለሁሉም ነገር የሚያስፈልገው ውይይት ነው። ከዚያ ውጪ በጉልበት ከሆነ ብዙም አያዋጣም።

2ኛ. ልማት
👉 በየቀኑ ልማት ላይ ካልሰራን፣ አሁን ባለው ድህነት፣ አሁን ባለው ፍላጎት ልማት ላይ ትኩረት ካላደረግን በስተቀር አንዘልቀውም።

3ኛ. ዲሞክራሲ
👉 ነገር በክላሽ ሳይሆን በምርጫ፣ ነገር በሃይል ሳይሆን በህግ ማስፈጸም ነው። ዲሞክራሲን መንግስትም፣ ተቃዋሚም፣ ወጣትም፣ አዛውንትም መለማመድ አለበት። በህግና በህግ ብቻ ሀገር መምራትን መለማመድ ያስፈልጋል።

4ኛ. መከላከል
👉 ሀገራችንን፣ የሀገራችንን ጥቅም፣ ህልውናችንን፣ ሉዓላዊነታችንን መከላከል አለብን። ለዚህ ደግሞ ተቋም ያስፈልጋል።

5ኛ. ዲፕሎማሲ
👉 እርስ በእርስም፣ ከጎረቤትም፣ ከሩቅም ዲፕሎማሲ ያስፈልጋል።

- የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ