መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
245 subscribers
75 photos
1 video
76 links
Download Telegram
ቤተ ክርስቲያን ማለት ምእመናን ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተዋጁ የሕያዋን ስብስብ ናት፡፡ እነዚህ ምእመናን በግጭትና ፤ በትዳር አለመግባባት በዓለም ፍርድ ቤት በዲያቢሎስ ተይዘው መቆም አይገባቸውም፡፡
https://vm.tiktok.com/ZMM4m2Jdf/
ሞቶልኝ ነው እንጂ ገድለውት አይደለም!
በዛሬው እለት ግንቦት 4 / 2016 ዓ.ም May 12 2024 በአሜሪካ ሜሪላንድ 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 የተከናወነው የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ እና የመልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል ።

በህዝቡም ጥያቄ መሰረት የማታ’ ጉባኤ እና ነገ May 13 እና May 14 እንደቀጠለ ነው ። እናመሰግናለን በነጻ ማስታወቂያ የምትሰሩልን ሰዎች!

ባልታጠቡ ጋኖች ላይ ወይኑ አይሞላም፡፡ ከክፋት ባልጸዳ ልብ ላይ ሰማያዊ ጥበብ አይኖርም፡፡ ከምቀኝት ባልወጣ አስተሳሰብ ላይ ብልጽግና አይመጣም፡፡ ከተንኮል ባልተለየ እቅድ ላይ ስኬት አይኖርም፡፡ ንስሐ ባልገባ ክርስትና ላይ የአምላክ ንጹሕ ሥራዎች አይጸኑም፥ ኃጢአት እያጎመዘዘ ያናውጣቸዋልና፡፡

የአዲሱ አቁማዳ ባሕሪይ አዲሱን የወይን ጠጅ ይቀበላል፡፡ አዲሱም የወይን ጠጅ አዲሱ አቁማዳ ይስማማዋል፡፡ ሁለቱ እርስ በእርስ ይጠባበቃሉ፡፡ ንስሐ የገባ ሕይወትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ በእርግጥም እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ፡፡ ሕግ በሰው ትከበራለች፥ ሰውየውም በሕጊቱ ይከብራል፡፡ ወንጌል በምዕመን ትገለጻለች፥ ምዕመንም በወንጌል ይገለጻል፡፡

ስለዚህ ጠላት ልክ ነዋ! ለምን ታሰቃየኛለህ ትለው ዘንድ አትችልም፡፡ ፈቃዱን፣ ስሜቱን፣ ጠባዩንና ሥርዓቱን እስከጠበክለት ድረስ፤ እርሱ ደግሞ አንተን በክፋት ይጠብቅብህ ዘንድ መብት አለው፡፡ በጎነትን ሳታስቀድም፣ ርኅራኄን ሳትወደው፣ ምቀኝነትን ሳትተወው፣ ጉቦን ሳትጠየፈው .. በጠቅላላው ኃጢአትን ሳትናዘዘው፤ "ከክፉ ሁሉ አድነኝ" እንጂ ብለህ መጸለይ መንፈሳዊ ስላቅ ይሆንብሃል፡፡ ከተኩላው በረት ሰተት ብለህ ገብተህ ከተኩላ አስጥለኝ እንደምን ትላለህ?
https://www.youtube.com/live/SJUCB0lxLi0?si=984LP7eSjriU4_px
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ Live YouTube ገብተዋል

ልዩ ትምህርት ርዕስ 1 እንዳያውቁት አይናቸው ተይዞ ነበር! ርዕስ ክፍል 2 ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸው! በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ

በአሜሪካ ሜሪላንድ በ 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 ማህበረ ምዕመናን ባዘጋጁት መንፈሳዊ ጉባኤ ግንቦት 4 / 2016 ዓ.ም May 12 / 2024 የተከናወነ የወንጌል ትምህርት እና የፈውስ አገልግሎት