https://youtu.be/YL2XVocBG1k?si=DKo24xPT5wx5GLk1
የመዳን እውነት ሲገለጥ
ምስክርነት ክፍል አንድ
እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!

ምርጫው ላይ እንወስን!
የሞተን አሳ ብቻ ነው ባህሩ እንደፈለገ የሚወስደው!
በአሜሪካ አገልግሎት ጨርሰን በጉብኝት ላይ…
በርባንና ክርስቶስ ዛሬም ግራና ቀኝ ቆመዋል፡፡ እናስተውለው ዘንድ የሚያስፈልገው ነገር፤ ይሄ ምርጫ ዘወትር በየቀኑ እንደየሕይወታችን አጋጣሚ መቅረቡን ይቀጥላል፡፡ ሰላም ሰጪነትን እና ሰላም ነጣቂነትን የሚወስኑ ሁነቶች በየቀኑ ምርጫ ሆነው አሉ፡፡ መታገስ እና አለመታገስን የሚፈትኑ ነገራት ዘወትር አሉ፡፡ ቁርጠኝነትን አሊያ ግዴየለሽነትን የሚያስመርጥ አጋጣሚ በየዕለቱ ወደኛ ይመጣል፡፡ ይቅርታ ማድረግ እና በደልን መመዝገብ አሁንም ምርጫችን ነው፡፡ ቸርነትና ንፉግነት በየኑሮአችን መስመር ላይ ተራርቀው ቆመው መልሳችንን ይጠብቃሉ፡፡ ስለዚህ እንወስን፡፡ ማንን መርጠናል? በርባንን ነው ክርስቶስን?
ልብ እንበል! ዓለም፤ የምርጫ ኮሮጆዋን ለበርባን ከሰጠች ቆይታለች፡፡ ያኔ በዘመነ ክርስቶስ፤ የበዙት ሰዎች ስለ በርባን እንደጮኹ ሁሉ፤ ዛሬም ይኸው ጊዜ ራሱን ሲደግም ብዙ ሰዎች ወደ ተገለጠው በርባን ይጮኹ ዘንድ ውስጣቸው ያለው ያልተገለጠው በርባንን ጥፋትን፣ ግፍን፣ አመፃን፣ ስግብግብነትን፣ ትምክህትን፣ ግንፍልተኝነትን፣ ቸልተኝነትን፤ እየመራ፥ የብዙሃን ድምፅ የአንድነት ፍላጎት ሆኗል፡፡
እንኪያስ፥ ምርጫችን ክርስቶስ ከሆነ ዘንዳ፤ ከውስጥ ካለው በርባን ጋር በየሰኮንዱ ልንታገል ግድ እንደሚያስፈልገን እናስተውል፡፡ 'የዓለም መናኝ' ሆኖ ለመኖር በመጀመሪያ ከውስጥ ያለው በርባን በየቀኑ መታሰሩን ማረጋገጥ ግድ ነው፡፡ አለበዚያ ሁለት ዛፍ በአንዴ እንወጣ ስንል፤ መድረሻ ማረፊያችን የሚሆነው ሁለቱንም ዛፍ አለመውጣት ነው፡፡ ሁለቱንም አለመውጣት ሆነ የግራው ዛፍ ላይ መገኘት ደግሞ የውስጠኛው በርባን ፍላጎት ነው፡፡ "በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ።

በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።" (የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 3፥5-6)
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከ መልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
20/06/2016 ዓ.ም
February / 28 / 2024
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከ መልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
20/06/2016 ዓ.ም
February / 28 / 2024
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
በአሜሪካ የነበረንን መንፈሳዊ አገልግሎት ጨርሰን የካቲት
28 /2016 ዓ.ም ወደ ሀገራችን
ኢትዮጵያ 🇪🇹 በሰላም ገብተናል!
እግዚአብሔር ይመስገን!
ሰው ከእግዚአብሔር ሲሸሽ እንቅልፍና መኝታ ለጊዜው ይመቸዋል፤ የሚያስጨንቅና የሚያሳስብ ችግር ለጊዜው አይታየውም፡፡ ይህ ትውልድ ዜግነቱን በመለወጥ አልረካም፤ ማንነቱን በመጥላትና በመርሳት፤ የታከተና የሰለቸ ሕሊና፣ በስውር የቆሰለ ልብ እያለው ወርዶ ተኝቷል፡፡ ለስግደት እና ለፀሎት ጊዜ የለውም እግዚአብሔር አምላክ ይሰውረን!
<< በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። >> መጽሐፈ ኢያሱ 1 ፤ 5
28 /2016 ዓ.ም ወደ ሀገራችን
ኢትዮጵያ 🇪🇹 በሰላም ገብተናል!
እግዚአብሔር ይመስገን!
ሰው ከእግዚአብሔር ሲሸሽ እንቅልፍና መኝታ ለጊዜው ይመቸዋል፤ የሚያስጨንቅና የሚያሳስብ ችግር ለጊዜው አይታየውም፡፡ ይህ ትውልድ ዜግነቱን በመለወጥ አልረካም፤ ማንነቱን በመጥላትና በመርሳት፤ የታከተና የሰለቸ ሕሊና፣ በስውር የቆሰለ ልብ እያለው ወርዶ ተኝቷል፡፡ ለስግደት እና ለፀሎት ጊዜ የለውም እግዚአብሔር አምላክ ይሰውረን!
<< በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። >> መጽሐፈ ኢያሱ 1 ፤ 5
https://youtu.be/YL2XVocBG1k?si=DKo24xPT5wx5GLk1
የመዳን እውነት ሲገለጥ
ምስክርነት ክፍል አንድ
እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!
የመዳን እውነት ሲገለጥ
ምስክርነት ክፍል አንድ
እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በአሜሪካን
በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት እና በአካባቢው የሚገኙ ማህበረ ምዕመናን ባደረጉት መንፈሳዊ አገልግሎት ጥሪ መሠረት ከግንቦት 4 እስከ 6 may 12 To 14 የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል ትምህርትና የፈውስ የጠበል አገልግሎት ለሶስት ተከታታይ ቀናት የጠዋት እና የማታ ጉባኤ ይከናወናል! ይህንን መንፈሳዊ አገልግሎት ከመላው አህጉራት እና ከተማ ለመሳተፍ የምትመጡ ምዕመናን አገልግሎት የሚከናወንበት የቦታ አድራሻ ሜሪላንድ 1600 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን
አዘጋጅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማህበረ ምዕመናን ኮሚቴ
ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም ብቻ የሚሰራ ስልክ ቁጥር ( valid only telegram & WhatsApp) 🇪🇹 +251932176757 & Email - memehirhailemelekotgirma@gmail.com
ሰው የቆፈረው ጕድጓድ መልሶ ያስጠማል ። ጥያቄው መልስ ካገኘ በኋላ መልሱ ጥያቄ ይሆናል ። የሰው ዓለም ምኞት እስኪሆን መቅበዝበዝ ፣ ከሆነ በኋላ እንደ ገና መመኘት የሞላበት ፣ ፍለጋ የማያልቅበት ፣ ሕልምና ፍችው የተሰወረበት ነው ። ዛሬም በኑሮው ከተደሰተ ያዘነ ፣ በእሴቱ ካመሰገነ የተማረረ ይበዛል ። የሰው ልብ ሁልጊዜ መንገደኛ ነው ። ወደቡን አያውቀውም ሁልጊዜ ቀዛፊ ነው ። እፎይ የሚያሰኘውን ሕይወት የሚሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ያ የሚያረካው ምንጭ ነው ። የሚፈለግ ሳይሆን በሆድ ውስጥ የሚፈልቅ ነው ። ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባ ሳይሆን ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስስ ነው ።