መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
252 subscribers
75 photos
1 video
76 links
Download Telegram
ድ ን ቅ ፡ ፍ ጥ ረ ቱ ን ፡ በ ል ጅ ነ ት ፡ አ ደ ሰ ው ፡ ፡ የእግዚአብሔር ሥራ እንደሆነ መሰራቱ የግድ ነው፡፡
በቃ የግድ ነው!

በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ሜሪላንድ እና ላስ ቬጋስ የነበረን የ አምስት ቀን የቀን እና የማታ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው እለት ግንቦት 13 2016ዓ.ም ( May 21 ) በልዑል እግዚአብሔር ፍቃድ በሰላም ተጠናቋል! አገልግሎታችን ብዙ ህዝበ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ኃይል ለዘመናት ከተተበተቡበት ከመተተኛው ፤ ከደብተራው ከጠንቋዩ ክፉ የዲያቢሎስ እስራት ብዙ ምዕመናን የተፈቱበት ዲያቢሎስ በዘመናችን ምን ያህል የጥፋት መረብ ዘርግቶ እንደሚራመድ ከቤተእግዚአብሔር ቤት ጀምሮ የራሱን የጥፋት መረብ በሰዎች እየዘረጋ እንዴት የክፋት የዘረኝነት ፤ የአድመኝነት ፤ የግፍ ፤ የጥላቻ ፤ የፍቅረነዋይ ስራውን እንደሚሰራ በጥልቀት የተረዳንበት ቅዱሱን ወንጌል በሰፊው የተማርንበት ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው! ይህን አገልግሎት ( kesis Hailemelekot Girma )https://youtube.com/@kesishailemelekotgirmatube7285?si=xv1p4AA05ECjcHaY በሚለው YouTube channel በተከታታይ በቅርቡ እንደምንለቅላችሁ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን!

እንደግሌ እምነት ሰዎች በክፉ መናፍስት በኩል ያለባቸውን ጦርነት በሚገባ በመገንዘብ በአንፃሩም ደግሞ እግዚአብሔር ለኛ የሰጠውን የፍቅር ስጦታና የጸጋ ኃይል ከመግለጥ አኳያ በሁለት እግራቸው ቆመው ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ቦታና ክፍል አሳድገው እንዲመላለሱ ማድረግ በተቀዳሚነት የቤተክርስቲያን ተልዕኮና ራእይ ነው፡፡
ከስሟ እንደምንረዳው ቤተክርስቲያን <<የክርስቲያን ቤት>> ነች፡፡ ክርስቲያን የሚለው ከወጣ ቤት የሚለው ብቻ ይቀራል፡፡ የቤተክርስቲያን መቆምና መኖር ለእግዚአብሔር አይደለም፡፡ ለሰዎች ነው፡፡ ሚሊዮን ቤተክርስቲያናት ቆመው የእግዚአብሔርን ስምና ኃይል የማይጠሩ ሰዎች አንድም ከሌሉ እንግዲያው የሰማዩ አምላክ ማረፊያው የት ነው?

አንድ ወቅት ላይ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮናስ ከሰማይ አምላክ ፊት ሸሽቶ በመርከብ በኩል ለማምለጥ ወደ ታቺኛው የመርከቢቱ ክፍል ወርዶ ተኛ፡፡ ማዕበልም መጥቶ መርከቢቱ በወጀብ ስትናጥ አገልጋዩ ተኝቶ ነበረ፡፡

ዛሬም የሆነው ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከመረጣቸውና የአገር ቁጭት ካደረባቸው አገልጋዮች በተለየ ብዙ አገልጋዮች የሕዝበ ክርስቲያኑ እሮሮና ሰቆቃ አይሰማቸውም፡፡ ሕመማቸው አያማቸውም፡፡ ትርምሱን የሚያስቁሙበትን ሰማያዊ ጉልበት መያዝ እንዳይችሉ እየሄዱ ግን በቁማቸው ወርደው ቀንም ማታም ተኝተዋል፡፡ በማረ ድምፅና ገጽታ አውደምሕረት ላይ ይቆማሉ፡፡ በየመድረኩ ይሰብካሉ፡፡ በእልልታና ጭብጨባ በተለይ ታጅበው ቃሉን ይናገራሉ፡፡ ግን ጧፍ አብርቶ ጉባዔው ሲያልቅ ያበራውን ጧፍ አጥፍቶ የተበተነው ሕዝብ፤ ቤቱ ሲገባ እንዳጠፋው ጧፍ የጠቆረና የከሰለ ኑሮ እንደሚመራ አልተረዱለትም፡፡ ቢረዱም እዚህ ግባ የሚባል ሁለንተናዊ መፍትሔ እንደአገልጋይነት ማምጣት አቅቷቸዋል፡፡ የእነርሱ ስራ አጋንንት ዘራቸው ሲነካ ለምን ይነካል በማለት እራሳቸው ተሰደው ማሳደድ እና ብዙ ምዕመናን ላያቸው በነጭ ነጠላ በርቶ ቢታይም፤ ልብና ሕሊናቸው ውስጥ ባህሪያቸውን ተለማምዶ ከሚያንከራታቸው የጨላማ ኃይል ጋር የሚያሳልፉት የመከራ ጊዜ ለአገልጋዮችም ሆነ ለበረቱ ምዕመናን አይታያቸውም፡፡ ዘምረውና 'ቃለ ሕይወት ያሰማልን' ብለው የገቡት ምዕመኖች፤ የኑሮን ጣዕመ ዜማን አጥተው፤ 'ቃለ ሕይወት ያሰማልን' ያሉትን የሕይወትን ቃል በአኗኗራቸው መተርጎም አቅቷቸው እንደሚባትቱ ለመረዳት የሚችሉበትን ልብ አልያዙም፡፡ ስለዚህ የሚተረክ እንጂ የሚኖር ክርስቲያንነት ከባህሪያችን፣ ከጠባያችን፣ ከቤታችን፣ ከኑሮአችን አልገለጥ አለ፡፡ ነጠላ ሲውልቅ አብሮ በሚወልቅ ሃይማኖት ታጅረን የኛም የብዙዎቻችን ጊዜና በረከት ውልቅልቁ ወጣ፡፡ በየቤቱ ቢታይ ከችግርና ትንቅንቅ ኑሮ ጋር ግብግብ ያልገጠመ ክርሰቲያን ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ይኼ እንግዲህ ነባራዊው የሚመረው እውነታችን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር አንፃር ሲታይ ሁላችንም ሊባል በተቃረበ ደረጃ የወደቅንበትን ኑሮ እንካደው ካላልን በቀር ዘመንና ትውልዳችን የሚያሳየው ይኼንኑ የሕይወት ምስክርነት ነው፡፡

እኛ ግን በተገፋን ቁጥር በረከትና ጸጋችን በሚታይ ተግባር እየጨመረ ስለሄደ በርቱ! ክርስቶስን አይሁዳውያን አስረው ሲጎትቱት የሚፈልጉትን እያደረጉ መስሎ ነበር የታያቸው፡፡ እርሱ ግን የመጎተቱ መጨረሻ እስከ መሰቀል ድረስ ቢያደርሰው ግዜ ለሁሉ ድኅነት ሆኖ ሰው አደረገን፡፡ ስለዚህ መውጊያውን ብታቃወሙ በራሳችሁ ይብሳል እንጂ የእግዚአብሔር ሥራ እንደሆነ መሰራቱ የግድ ነው፡፡

ሁላችንም ሰብሰብ ብለን ወደ ልባችን፤ እስኪ እንዴት ነው ሕይወቴ? ምንድነው እያሳለፍኩ ያለሁት? ምን አይነት ነገር እየገጠመኝ ነው ብሎ መጠየቅና እነዚህን መልስ ለማግኘት ከንጹሕ ልብና ታማኝነት ጋር ወደ እግዚአብሔር እውነት መጠጋት መጨረሻው እንደ ቀኙ ወንበዴ በዳግም ምጽዕት መታሰብ ነው፡፡

እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከመልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
14/09/2016 ዓ.ም ከአሜሪካ 🇺🇸 Las Vegas
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
መልካም ልደት አባት
ብዙ ልል ጀምር እና ቃላቶቹ አንሰውብኝ በቃላቶቹ መልሼ እናደዳለሁ .... ምክንያቱም ያንተ እውነት ለዚህ ዘመን ፤ ትውልድ ከቃላቶች በላይ ነው። እኔ ስለምሰስተው ሰው መናገር አልወድም ምክንያቱም የምወደው ሰው እጅግ ውድ ስለሚሆንብኝ ... የውድነትህን መጠን ማን ይረዳልኛል ???? እውነቱን ለማወቅ ጎጆህን ተግባርህን ማየት በቂ ነው። እንደኖህ እግዚአብሔር ወደምድር ሲያይ ደስ የሚሰኝብህ ታላቅ አባት ነህ!!!!! 🙏🙏🙏
አባቴ አርዓያዬ ፤ መሪዬ ፤ ጠባቂዬም ነህ ....
ደግሞ እኮ የኔ ብቻ አይደለህም የሚሊዮኖች ነህ!
እንኳን ተወለድክልን የሚሊዮኖች አባት🙏
💚💚 💛💛
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ ግንቦት 29 የተወለዱበት ቀን ነው! 65ኛ ዓመታቸውንም ይዘዋል!
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ

የመልአኩ ምልጃው ቃልኪዳን በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን ሀገራችንን ሰላሙን ይሰጠን ዘድ አሳስብልን&#33;

ከቤተ-ሳይዳ የመጻሕፍትና የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ መደብር

አድራሻ ፦ 22 ማዞሪያ ጌታሁን በሻህ ሕንፃ ፊት ለፊት ከአክሱም ሆቴል ወረድ ብሎ ሀኮማል ባስራው አዲሱ ትጋት የገበያ ማእከል (አዲስ ቀይ ህንጻ) የመጀመሪያው ፍሎር ከንብ ባንክ ጎን ያገኙናል። ለበለጠ መረጃ ለዚሁ አገልግሎት ብቻ የሚውል በእዚህ ስልክ መደወል ይቻላል 0919959995 P.O.Box 25084 Code 1000 ይህ ስልክ ሌላ አገልግሎት አያስተናግድም

እናንተም በቤተ ሳይዳ እየተገኛችሁ የቱባረከ መንፈሳዊ መሳሪያዎችን እየወሰዳችሁ ፍቅር፣ሰላም፣ደስታ፣ የነሳንን ጠላት እየተፋለማችሁ ወድ ክርስቶስ መንግስት የሚወስደውን መንገድ እንድትይዙ አደራ እላለሁ።

የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የለወጠው፥ ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ፈተና የታደጋት፥ የእግዚአብሔር የሆኑትን ሁሉ የሚረዳና የሚጠብቅ ገናናው ሊቀ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በአገራችን፥ በሕዝባችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተጻፈውን የደብተራውን ፤ የጠንቋዩን ፤የሟርተኛውን ክፉ ሴራ ሁሉ ይበጣጥስልን።

+++ወስብሐት ለእግዚአብሔር+++
የዩቲዩብ ቻናላችን 100ሺህ የደንበኝነት ተመዝጋቢዎችን አግኝቷል፣
https://youtube.com/@kesishailemelekotgirmatube7285?si=eW-zIn0smfa4xU9g

ለአመታት ለምትሰጡን ድጋፍ እናመሰግናለን፣ ያለእርስዎ ይህንን ማድረግ አንችልም። እናከብራቹሀለን፡፡

ውድ ተመልካቾች ከዚህ በኋላ ቤተሳይዳ ቲቪ በአዳዲስ ዝግጅቶች እና አቀራረብ በተጠናከረ አገልግሎት አብራን ትቆያለች፡፡ አብሮነታችሁ አይለየን፡፡ እዚህ ቻናል ውስጥ ታዲያ የሚተላለፈውን አንድ ትምህርት፤ መንፈስ ቅዱስ ሦስት ቦታ እየበተነ ለሁሉም በሰዓቱ የተፈቀደለትን ያህል እንዲገነዘብ የእግዚአብሔር ኃይል ድንቅ ሥራውን ያከናውናል፡፡

በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን!

We Are Truly Grateful For You
Our YouTube channel just hit 100k subscribers, and we wanted to take a moment and just say thank you. Thank you for the support you have given us through all of the years, we truly couldn't do this without you.

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከመልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
14/10/2016 ዓ.ም
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯