መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
235 subscribers
143 photos
1 video
119 links
Download Telegram
በዛሬው እለት ግንቦት 4 / 2016 ዓ.ም May 12 2024 በአሜሪካ ሜሪላንድ 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 የተከናወነው የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ እና የመልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል ።

በህዝቡም ጥያቄ መሰረት የማታ’ ጉባኤ እና ነገ May 13 እና May 14 እንደቀጠለ ነው ። እናመሰግናለን በነጻ ማስታወቂያ የምትሰሩልን ሰዎች!

ባልታጠቡ ጋኖች ላይ ወይኑ አይሞላም፡፡ ከክፋት ባልጸዳ ልብ ላይ ሰማያዊ ጥበብ አይኖርም፡፡ ከምቀኝት ባልወጣ አስተሳሰብ ላይ ብልጽግና አይመጣም፡፡ ከተንኮል ባልተለየ እቅድ ላይ ስኬት አይኖርም፡፡ ንስሐ ባልገባ ክርስትና ላይ የአምላክ ንጹሕ ሥራዎች አይጸኑም፥ ኃጢአት እያጎመዘዘ ያናውጣቸዋልና፡፡

የአዲሱ አቁማዳ ባሕሪይ አዲሱን የወይን ጠጅ ይቀበላል፡፡ አዲሱም የወይን ጠጅ አዲሱ አቁማዳ ይስማማዋል፡፡ ሁለቱ እርስ በእርስ ይጠባበቃሉ፡፡ ንስሐ የገባ ሕይወትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ በእርግጥም እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ፡፡ ሕግ በሰው ትከበራለች፥ ሰውየውም በሕጊቱ ይከብራል፡፡ ወንጌል በምዕመን ትገለጻለች፥ ምዕመንም በወንጌል ይገለጻል፡፡

ስለዚህ ጠላት ልክ ነዋ! ለምን ታሰቃየኛለህ ትለው ዘንድ አትችልም፡፡ ፈቃዱን፣ ስሜቱን፣ ጠባዩንና ሥርዓቱን እስከጠበክለት ድረስ፤ እርሱ ደግሞ አንተን በክፋት ይጠብቅብህ ዘንድ መብት አለው፡፡ በጎነትን ሳታስቀድም፣ ርኅራኄን ሳትወደው፣ ምቀኝነትን ሳትተወው፣ ጉቦን ሳትጠየፈው .. በጠቅላላው ኃጢአትን ሳትናዘዘው፤ "ከክፉ ሁሉ አድነኝ" እንጂ ብለህ መጸለይ መንፈሳዊ ስላቅ ይሆንብሃል፡፡ ከተኩላው በረት ሰተት ብለህ ገብተህ ከተኩላ አስጥለኝ እንደምን ትላለህ?
https://www.youtube.com/live/SJUCB0lxLi0?si=984LP7eSjriU4_px
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ Live YouTube ገብተዋል

ልዩ ትምህርት ርዕስ 1 እንዳያውቁት አይናቸው ተይዞ ነበር! ርዕስ ክፍል 2 ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸው! በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ

በአሜሪካ ሜሪላንድ በ 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 ማህበረ ምዕመናን ባዘጋጁት መንፈሳዊ ጉባኤ ግንቦት 4 / 2016 ዓ.ም May 12 / 2024 የተከናወነ የወንጌል ትምህርት እና የፈውስ አገልግሎት
አገልግሎታችን በ Las Vegas እንደቀጠለ ነው!

ለ ሶስት ተከታታይ ቀናት በሜሪላንድ የነበረንን መንፈሳዊ አገልግሎት በ እግዚአብሔር ፍቃድ በሰላም ጨርሰናል!

ቅድስናን ስናሞግስ ርኩሰትን በማውገዝ ነው፤ መልካምን መልካም ያልነው ከመጥፎው ለይተን ነው፤ ነግቷል እኮ ያስባለን የለሊቱ ማለፍ ነው፤ መጠንን ትንሽ ብለን የመዘንነው ከትልቁ አንጻር ነው:: .. [ከፀሐይ በታች ያለቺው] ዓለም እንደዚህ ናት::

አዳም ክፉና ደጉን የሚለይና የሚስማማ ባሕሪይ ይዞ ምድራዊ ኑሮውን ከጀመረ ወዲህ ሰውነት በሁለት መስተቃርን ዋልታዎች መካከል የሚባትት ሕልውና ሆኗል:: (ዘፍ. 3፥22) መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው ታሪክ አንስቶ የሚነግረን ይህንን ነው:: ከእናንተ መካከል ከዚህ እውነት ውጪ የሆነ የመጽሐፍ ታሪክ የሚያነሣልኝ አለ?

ስለ አዳም ስናወራ ስለ እባብ ተንኮል እናነሣለን:: ስለ አቤል ደግነት ስናነብ ድንጋይ ስለ ጨበጠው ቃየንም እናውቃለን:: ስለ ኖኅ መርከብ ለማውራት የኖኅ ጎረቤቶች ያስፈልጋሉ:: ስለ አብርሃም ጥሪ ስንማር ዙሪያውን ስለ ከበበው ባዕድ አምልኮት መገንዘብ ግድ ይላል:: ሙሴን ስንተርክ ፈርዖንን ማውጣት አንችልም:: ዳዊትን ከጎልያድና ከሳዖል ውጪ ማንሳት ታሪኩን አያሟላም:: ወደ ሐዲስ ኪዳንም አለፍ ብንል ያለው ይኸው ነገር ነው:: ሰብአ ሰገል ሲታሰቡ ሄሮድስ አይዘነጋም:: ለተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጅነትን ሰጣቸው ያለው የገዛ ወገኖቹ እንዳልተቀበሉት ነግሮን ሲያበቃ ነው:: (ዮሐ.1፥11-12) በአጠቃላይ የጽድቅ ዕሴቶችን የሚያበረታታው መንፈሳዊው ዓለም ከኩኔው ጎራ ያሉትን በአንድም በሌላም መንገድ ሳይጠቅሳቸው አያልፍም:: ታዲያሳ ትሕትናን ለማስተልቅ ትዕቢትን ካላሳነሱ እንደምን ይሆናል?
የትኛውም ሰባኪ (መምህርና መጽሐፍ) ስለ እግዚአብሔር ሲናገር ዲያቢሎስንም አይተወውም:: በቀጥታ ሰይጣን አሊያ አጋንንት ባይል እንኳ ስለ ክፉዎቹ ግብር ወዲያም አለ ወዲህ ያነሣል:: ስለ ውሸት፣ ክሕደት፣ ምቀኝነት፣ ዘርኝነት፣ አድመኝነት፣ ንፉግነት፣ ሌብነት፣ ግዴየለሽነት፣.. ሳይገሥጽ የሚሰብክ መንፈሳዊ ትምህርት አለ ይሁን?

እንግዲያስ ዲያቢሎስ ማለት በነዚህ ክፉ ባሕሪያት የሚገለጽ ፍጡር ማለት እኮ ነው:: ችግር የሆነው ይህንን ክፉ ከነስሙና የውጊያ ስልቶቹ ስለተማማርነው ነው? እኔ ሐሰትን ለብቻ ሰይጣንን ለብቻ አድርገው የሚያዩና ይህን ዕይታቸውን የሚያስፋፉ ሰዎች ይደንቁኛል:: ብቻም ሳይሆን ወንጌል "[ዲያቢሎስ] ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል" ስለማለቷ ያነበቡ፥ ካነበቡም እንደሚገባ ያጤኑ አልመሰለኝም:: (ዮሐ. 8፥44)
በዛሬው እለት ግንቦት 12 / 2016 ዓ.ም May 20 2024 በአሜሪካ ላስ ቬጋስ 3950 south Jones Blvd las vegas NV,89103 የተከናወነው የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ እና የመልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል ።

በህዝቡም ጥያቄ መሰረት የማታ’ ጉባኤ እና ነገ May 21 የሚቀጥል መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን! ። እናመሰግናለን በነጻ ማስታወቂያ የምትሰሩልን ሰዎች!

ሰይጣን አካል አይደለም፡፡ የራሱ የሆነ የለውም፡፡ አካል ያለው የመንፈሳዊ ሲሆን ሥጋዊ ፍጥረት(ሰው) ጥላ እንጂ፡፡ - ይኸውም ሀሳባቸው ውስጥ ነው፡፡

ለዚህ ነው ፍትህ በፍርድ ሲገለጽ አጠፋፉ እንደ ጢስ ከፍታ በመትነን ነው ሚባለው፡፡

ታሪካዊ መንፈስ ታውቃላችሁ ወይ?
ለዘላለም የሚኖረው ነው 33ዓመት የኖረው።

አብዛኛው ሕብረተሰብ የእግዚአብሔርን የማዳን ነገር ዋጋ ሳይሰጡና በበጎነት ሳይመለከቱ፤ የራሳቸውን ምክንያት በመደርደር፤ ሰው ላይ የሚታየውን ችግር ፋይዳ ቢስ አድርገው፤ ባዶነታቸውን ሳይመለከቱ እንደ ነፍሳቸው ምኞት ይናገራሉ፡፡ “እንዲሁም ክፋትን ይጎነጉናሉ” ብዙው ሰው ረጅሙን ዕድሜ ያሳለፈው በምስጋና፣ በፀሎትና በአምልኮት ሳይሆን፤ በጥላቻ፣ በመለያየት፣ በመሰሪነትና አንዱን አንዱ ጥሎ በማለፍ ስለሆነ፤ በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ሆኖ ኃጢአያትን በመለማመድ፤ ደፋር፣ ኩሩ፣ ቀማኛና ነጣቂ በመሆን፤ ክፋትና ጥፋትን ለማቆየት እየሠራ ይገኛል፡፡
እኛም ታዲያ የምናስበው፣ የምናቅደውና አመለካከታችን ከክፋት ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ የብዙውን ትውልድ ዕድል አጥፍተን፤ ብዙ ከሃዲዎችን ማፍራታችን አንዱ የግፍ ሥራችን ምልክት ነው፡፡ በጎና ቅን ሆነን በመንፈስ ቅዱስ ተዋጅተን ወደ ሰው የምንሄድበት ሕሊና ስላጣን፤ ነገር እየጎነጎንን መሰሪ እቅድ ኑሯችን ውሰጥ ተክለን፤ ከጀርባችን ብዙ ክፋቶችን አዝለን እንኖራለን፡፡

ከእነሱ ሁሉ የተሻለው እንደ አሜኬላ ነው” ያለው የነብዩ ቃል፤ አሜኬላ ተደብቆ የሚወጋ ከታች ስትረግጠው ከላይ የሚቧጥጥ፣ ጫማ አልፎ የሚያቆስል፣ የሚያደማ፣ የማያስሮጥ፣ ቁስል የሚሆን፣ እግርን የሚቆጠቁጥ፣ የሚያም፣ የሚያስጨንቅ፣ አረማመድን የሚገታ፣ የወደፊት ተስፋን የሚያመክን እና ቁልቁል የሚያሽከረክር ነው፡፡ ዛሬም የተሻለ የተባለው ሰው ሁሉ ልክ እንደ እሾህ የሚዋጋ ሆኖ በሥልጣን፣ በማዕረግ፣ በከፍታ ለሌላው ሰው እንደ አሜኬላ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉ ቅን የሆነውም፤ እንደ ኩርንችት ነው፡፡ ኩርንችት ደግሞ እንደ ደበኛ አድፋጭ፣ ተንኮለኛ፣ ምቀኛና ነገረኛ ምሳሌ በመሆን፤ በተፈጥሮ ሂደትም በምትረግጥበት ስፍራ ላይ እግርህንና ኮቴህን ተደብቆ የሚወጋ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ኩርንችትና አሜኬላ በሁሉም አቅጣጫ በኑሮችን ውስጥ የተለመደ አድርገን፤ በክፋትና በግፍ አሠራር የሌሎችን ሕይወት በግልጽና በስውር ስንጎዳ ይታያል፡፡

እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!