መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
235 subscribers
144 photos
1 video
120 links
Download Telegram
https://youtu.be/YL2XVocBG1k?si=DKo24xPT5wx5GLk1

የመዳን እውነት ሲገለጥ
ምስክርነት ክፍል አንድ
እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በአሜሪካን

በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት እና በአካባቢው የሚገኙ ማህበረ ምዕመናን ባደረጉት መንፈሳዊ አገልግሎት ጥሪ መሠረት ከግንቦት 4 እስከ 6 may 12 To 14 የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል ትምህርትና የፈውስ የጠበል አገልግሎት ለሶስት ተከታታይ ቀናት የጠዋት እና የማታ ጉባኤ ይከናወናል! ይህንን መንፈሳዊ አገልግሎት ከመላው አህጉራት እና ከተማ ለመሳተፍ የምትመጡ ምዕመናን አገልግሎት የሚከናወንበት የቦታ አድራሻ ሜሪላንድ 1600 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን

አዘጋጅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማህበረ ምዕመናን ኮሚቴ


ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም ብቻ የሚሰራ ስልክ ቁጥር ( valid only telegram & WhatsApp) 🇪🇹 +251932176757 & Email - memehirhailemelekotgirma@gmail.com

ሰው የቆፈረው ጕድጓድ መልሶ ያስጠማል ። ጥያቄው መልስ ካገኘ በኋላ መልሱ ጥያቄ ይሆናል ። የሰው ዓለም ምኞት እስኪሆን መቅበዝበዝ ፣ ከሆነ በኋላ እንደ ገና መመኘት የሞላበት ፣ ፍለጋ የማያልቅበት ፣ ሕልምና ፍችው የተሰወረበት ነው ። ዛሬም በኑሮው ከተደሰተ ያዘነ ፣ በእሴቱ ካመሰገነ የተማረረ ይበዛል ። የሰው ልብ ሁልጊዜ መንገደኛ ነው ። ወደቡን አያውቀውም ሁልጊዜ ቀዛፊ ነው ። እፎይ የሚያሰኘውን ሕይወት የሚሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ያ የሚያረካው ምንጭ ነው ። የሚፈለግ ሳይሆን በሆድ ውስጥ የሚፈልቅ ነው ። ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባ ሳይሆን ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስስ ነው ።
ቤተ ክርስቲያን ማለት ምእመናን ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተዋጁ የሕያዋን ስብስብ ናት፡፡ እነዚህ ምእመናን በግጭትና ፤ በትዳር አለመግባባት በዓለም ፍርድ ቤት በዲያቢሎስ ተይዘው መቆም አይገባቸውም፡፡
https://vm.tiktok.com/ZMM4m2Jdf/
ሞቶልኝ ነው እንጂ ገድለውት አይደለም!
በዛሬው እለት ግንቦት 4 / 2016 ዓ.ም May 12 2024 በአሜሪካ ሜሪላንድ 16000 Croom Airport Road Upper Marlboro MD 20772 የተከናወነው የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ እና የመልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል ።

በህዝቡም ጥያቄ መሰረት የማታ’ ጉባኤ እና ነገ May 13 እና May 14 እንደቀጠለ ነው ። እናመሰግናለን በነጻ ማስታወቂያ የምትሰሩልን ሰዎች!

ባልታጠቡ ጋኖች ላይ ወይኑ አይሞላም፡፡ ከክፋት ባልጸዳ ልብ ላይ ሰማያዊ ጥበብ አይኖርም፡፡ ከምቀኝት ባልወጣ አስተሳሰብ ላይ ብልጽግና አይመጣም፡፡ ከተንኮል ባልተለየ እቅድ ላይ ስኬት አይኖርም፡፡ ንስሐ ባልገባ ክርስትና ላይ የአምላክ ንጹሕ ሥራዎች አይጸኑም፥ ኃጢአት እያጎመዘዘ ያናውጣቸዋልና፡፡

የአዲሱ አቁማዳ ባሕሪይ አዲሱን የወይን ጠጅ ይቀበላል፡፡ አዲሱም የወይን ጠጅ አዲሱ አቁማዳ ይስማማዋል፡፡ ሁለቱ እርስ በእርስ ይጠባበቃሉ፡፡ ንስሐ የገባ ሕይወትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ በእርግጥም እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ፡፡ ሕግ በሰው ትከበራለች፥ ሰውየውም በሕጊቱ ይከብራል፡፡ ወንጌል በምዕመን ትገለጻለች፥ ምዕመንም በወንጌል ይገለጻል፡፡

ስለዚህ ጠላት ልክ ነዋ! ለምን ታሰቃየኛለህ ትለው ዘንድ አትችልም፡፡ ፈቃዱን፣ ስሜቱን፣ ጠባዩንና ሥርዓቱን እስከጠበክለት ድረስ፤ እርሱ ደግሞ አንተን በክፋት ይጠብቅብህ ዘንድ መብት አለው፡፡ በጎነትን ሳታስቀድም፣ ርኅራኄን ሳትወደው፣ ምቀኝነትን ሳትተወው፣ ጉቦን ሳትጠየፈው .. በጠቅላላው ኃጢአትን ሳትናዘዘው፤ "ከክፉ ሁሉ አድነኝ" እንጂ ብለህ መጸለይ መንፈሳዊ ስላቅ ይሆንብሃል፡፡ ከተኩላው በረት ሰተት ብለህ ገብተህ ከተኩላ አስጥለኝ እንደምን ትላለህ?