አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
2.53K subscribers
510 photos
20 videos
53 files
992 links
መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።
ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot
ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot
https://telegram.me/atronss
Download Telegram
የቤተክርስቲያን ታሪክ በዘመነ ሐዋርያት
ዘመነ ሐዋርያት ብለን የምንጠራው ዘመን በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ለ120ው ቤተሰብ ከወረደ በኋላ ያለውን ነው፡፡ ሐዋርያት በሁሉም አቅጣጫ ወንጌልን በመስበክ ጨለማው ዓለም ብርሃን የሆነበት አልጫው የጣፈጠበት የክርስቶስ አምላክነት ለዓለም የተነገረበት በአጠቃላይ የድኅነት ዓለም ምስጢር በስብከተ ወንጌል ስርጭት ገሃድ የሆነበት፣የወንጌል ዘርና መከር ወቅት ነው፡፡
ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ከታጠቁ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሂዱና አስተምሩ በጨለማ የነገርኳችሁን በብርሃን ተናገሩት በጆሮአችሁ በሹክሹክታ የነገርኳችሁን በሰገነት ላይ ስበኩት፡፡"ማቴ 10÷26 ሲል የሰጣቸውን ትእዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ ወጡ ፣ መልካሙን የምስራች ዜና አወሩ የሕይወትንም ቃል ለዓለም አሰሙ፡፡ የዓለምን ጨለማ ለማራቅና አልጫ የሆነውን ዓለም ለማጣፈጥ የሚቻልበትን የብርሃንና የጨውነት ተግባር ፈጸሙ፡፡ ቃለ ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ላይ የተዘራውና ይህ የሕይወት ፍሬ የተመሠረተው በእነዚህ ሐዋርያት የወንጌል ግብርና ስለሆነ ዘመነ ሐዋርያት በእርግጥ ዘመነ ዘርና ዘመነ ፍሬ እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡
የ12ቱ ሐዋርያት የ72ቱ አርድዕት የ36ቱ ቅዱሳን አንስት በአጠቃላይ በዘመኑ የነበሩትን የ120ውን ቤተሰብ ስም ዝርዝር እንመለከታለን
12ቱ ሐዋርያት
#1 ጴጥሮስ (ስምኦን ወይም ኬፋ)
#2 እንድርያስ እኅሁ ለጴጥሮስ
#3 ያዕቆብ ወልደዘብዴዎስ
#4 ዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ
#5 ፊሊጶስ
#6 በርተለሜዎስ
#7 ቶማስ ዘህንደኬ ዲድሞስ
#8 ማቴዎስ (ቀራጭ የነበረው)
#9 ያዕቆብ ወልደእልፍዮስ
#10 ታዲዎስ (ልብድዮስ)
#11 ስምዖን ቀነናዊ (ናትናኤል)
#12 የአስቆሮቱ ይሁዳ (በማትያስ ተተክቷል)
እነዚህ ከዓሳ አስጋሪነት፣ ከቀራጭነትና ከግብር አስገባሪነት እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሥራ መስክ የተመረጡ ናቸው፡፡ ለነዚህም ሥልጣን ሰጣቸው ተአምራትም እንዲያደርጉ ኃይል ተሰጣቸው፡፡ ማቴ 10÷2 ፣ ማር 6÷7 ፣ ሉቃ 9÷1 ፣ ሐዋ 1÷23
ሐዋርያት
ሐዋርያት የሚለው ቃል የሐዋርያ ብዙ ቁጥር ሲሆን ሐዋርያ ማለትም ሖረ ሄደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው ትርጉሙም የተላከ፣ሂያጅ፣ልዑክ ማለት ነው፡፡ ወንጌለ መንግስትን ፣ድኅነተ ዓለምን ለመላው ዓለም ሊያውጁ ወይም ሊያበስሩ ተልከዋልና፡፡ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዘመኑ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ 40 ቀንና 40 ሌሊት በገዳመ ቆሮንቶስ ከጾመ ከጸለየ በኋላ የማስተማር ሥራውን ሲጀምር አስቀድሞ ያደረገው ነገር ቢኖር ቃሉን ሰምተው ፣ ተአምራትን አይተው ፣ በአለም ዞረው ወንጌልን የሚሰብኩ ደቀመዛሙርት መምረጥ ነበር፡፡ እነዚህ ደቀመዛሙርት ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ ማር 3÷13

ጌታችን ሐዋርያትን ከድሆችም ከሀብታሞችም መርጦአል፡፡ እነ ቅዱስ ጴጥሮስን የመሰለ ደሀ ዓሳ አጥማጅ ሲጠራ እነ ቅዱስ ማቴዎስን የመሰለ በቀረጥ ብር የከበሩትንም አልተዋቸውም፡፡ ሁሉም በእግዚአብሔር ዘንድ እኩል ናቸውና፡፡ሁሉም ደግሞ ያላቸውን ትተው ተከትለውታል ማቴ 4÷20 ማቴ 9÷9፡፡ ከተማሩትም ከማያምኑትም ወገን መርጧል፡፡ ዮሐንስንና ያዕቆብን ጌታ የጠራቸው ከአባታቸው ጋር ዓሳ ሲያጠምዱ ነው፡፡ ሌላ ትምህርት አልነበራቸውም ነገር ግን አልናቃቸውም፡፡ የቀናተኞች አይሁድ ወገን በመሆኑ በዚያን ዘመን ሮማውያንን ለማስወጣት ውስጥ ውስጡን በምድረ ፍልስጥኤም ይካሄድ የነበረው አመጽ ተካፋይ የነበረው ስምኦንን ከዚያ ግርግር አውጥቶ የሰላምና የጸጥታ ወደብ ወደ ሆነው ወደ እርሱ ጠርቶታል፡፡
ቤተእስራኤል ስትመሠረት 12ቱ አበው እየተባሉ በሚጠሩት ከያዕቆብ አብራክ በተከፈሉ አሥራ ሁለቱ ነገድ አባቶች ነበር፡፡ አሁንም በክርስቶስ ፈቃድ የእስራኤል ዘነፍስ ማኅበር ቅድስት ቤተክርስቲያን በ12ቱ ሐዋርያት ተመሠረተች፡፡
ሐዋርያት እስከ መጨረሻው በመጽናት ለክርስቶስ ምስክር ለመሆን የበቁባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች
በዓይናቸው አይተውታልና
በእጃቸው ዳስሰውታልና
ትምህርቱን በጆሮአቸው ሰምተውታልና(ዮሐ 1÷2)
በእርሱ ተልከዋልና (ማቴ 10÷1-4)
ከትንሳኤው በኋላም አይተውታልና(ዮሐ 21)
በስሙ ተአምራት ሲፈጽሙ ኖረዋልና (1ቆሮ 12÷12)
ከዚህ በፊት በሌዋውያን ዘር ይወርድ የነበረውን የብሉይ ኪዳን ሥልጣነ ክህነት በአዲስ በመተካት ለእነርሱ ሰጣቸው፡፡ ዮሐ 20÷22 እነርሱም ጌታችን እንዳስተማራቸውና ቃል ኪዳን እንደገባላቸው ለተከታዮቻቸው ይህንን ሥልጣን በአንብሮተ ዕድና በንፍሐት በመሾም አስተላለፉ፡፡ ማቴ 28÷20 ፣ ሐዋ 9÷12 በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተዋጀችውን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በስብከታቸው በሰጣቸው ሥልጣን ባደላቸውም ጸጋ ጠብቀው አቆዩአት፡፡ የመጀመሪያ ስራቸውንም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 3ሺህ ምዕመናንን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በማስገባት በይፋ ጀመሩ፡፡ ከዚያም ዓለምን ዕጣ በዕጣ ተካፍለው ተዘዋውረው አስተማሩ፡፡ ወንጌልን ሰብከው ቤተክርስቲያንን አነፁ፡፡ አምልኮ ጣዖትን አጠፋ፡፡ ርኩሳን አጋንንትን አሳደዱ፡፡ በመስቀል እርፍ አርሰው ንጹሕ ዘር ወንጌልን ዘርተው በደማቸው አተሙ፡፡ ለአስተማሩት ሕዝብ ለእምነቱ ማጽኛ የሚሆኑ መልእክታትን ጻፉ፡፡ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ደነገጉ ከጌታ የተማሩትን ያዩትንና የሰሙትን ለተከታዮቻቸው በቃልም በኑሮም በመጻሕፍትም አውርሰው በተጋድሎ ዐረፉ፡፡
ኪዳነ ምህርት ማለት ምን ማለት ነው 16
#ኪዳነ_ምህረት ማለት፦የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡
<<ኪዳነምህረት በምልጃዋ ትጠብቀን>>
የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ታሪክ
አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ትውልዳቸው ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እሥራኤል ነው ጴጥሮስና ወንድሙ እንድርያስ አባታቸው ከነገደ ሮቤል ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከነገደ ስምኦን ናት፡፡ ያዕቆብ ፣ ወንድሙ ዮሐንስ አባታቸው ከነገደ ይሁዳ ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከነገደ ሌዊ ናት፡፡ ፊልጶስ ከነገደ ዛብን ፣ በርተሎሚዎስ ከነገደ ንፍታሌም ፣ ቶማስ ከነገደ አሴር ፣ ማቴዎስ ከነገደ ይሳኮር ፣ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ከነገደ ጋድ ስምኦን ቀነናዊ (በኋላ ናትናኤል የተባለው) ከነገደ ብንያም ፣ ታዲዎስ የተባው ልብድዮስ ከነገደ ዮሴፍ ፣ በይሁዳ ምትክ የገባው ማትያስ ከነገደ ዳን ናቸው፡፡
#1 ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ (ስምዖን/ኬፋ)
ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ነው፡፡ የአባቱ ስም ዮና ይባላል፡፡ ጌታን ከመከተሉ በፊት ከአምስት አመት ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጎልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ አጥማጅ ነበር፡፡ ማር 1÷16-18 ለደቀመዝሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው 55 ዓመት እንደነበር ይነገራል፡፡ የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ጌታችን ጴጥሮስ ብሎታል፡፡ በላቲን ቋንቋ አለት በአረማይክ ኬፋ በግዕዝ ኰኩሕ ማለት ነው፡፡ ማቴ 16÷17 የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ተሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጥኤም ፣ በልዳ ፣ በኢዮጴ ፣ በቂሳርያ ፣ በሶርያ ፣ በጳንጦን ፣ በገላትያ ፣ በቀጳደቅያ ፣ በቢታንያ ፣ በሮሜና በተለያዩ ሀገሮች እየተዘዋወረ አስተምሮ አሳምኗል፡፡ ሐዋ 2÷41 ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም ንጉሠ ነገሥት ኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግስት በክርስቲያኖች ላይ በተነሳው ስደትና መከራ በመስቀል ተሰቅሎ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የቤተክርስቲያን ጸሐፊ ቅዱስ ጴጥሮስ በቫቲካን ኮረብታ ጳውሎስ ደግሞ በሮም በአስቲያ መንገድ መቀበራቸውን መስክሯል፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የእነዚህን ታላቅ የቤተክርስቲያን መሠረቶች የሆኑ ቅዱሳን አባቶች የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ሐምሌ 5 ቀን ተከብራለች፡፡
#2 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
ቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሳ ያጠምድ ነበር፡፡ ማር 1÷19-20 ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችንን እንዲያገለግላት አደራ የተሰጠው ለዮሐንስ ነው፡፡ ዮሐ 19÷26 ጌታ ይወደው የነበረው ዮሐንስ በፍልስጥኤምና በሌሎች ቦታዎች ክርስትና እንዲስፋፋ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በመተባበር አስተምሯል፡፡ ሐዋ 4÷1-22 ፣ 8÷14 ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፈሶን በመሄድ በታናሿ እስያ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማር ሲያገለግል ቆይቶ በድምጥያኖስ ዘመነ መንግስት ወደ ደሴተ ፍጥሞ ተሰዶ በግዞት ሳለ ራዕየ ዮሐንስን ጽፏል፡፡

#3 ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ (ወልደ ዘብዴዎስ)
ቅዱስ ያዕቆብ የዮሐንስ ወንድም ሲሆን የመጀመሪያ ሥራው ከአባቱ ጋር ዓሳ ማጥመድ ነበር፡፡ ማር 1÷19 ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በተመሠረተችው ቤተክርስቲያን መሪ ሆኖ በማስተማር ከፍ ያለ አገልግሎትን አበርክቷል፡፡ በስፔን ሀገርም እንደሰበከ በቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ይነገራል፡፡ የክርስትናን ትምህርት በስፋት በማስተማሩ በአይሁድ ዘንድ እንደ ወንጀለኛ ይቆጠር ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሄሮድስ አግሪጳ አይሁድን ለማስደሰት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በ44 ዓ.ም አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ሐዋ 12÷2 ቅዱስ ያዕቆብ የኖረውም ያረፈውም በኢየሩሳሌም ከተማ ነው፡፡ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል መጀመሪያ ሰማዕትነትን የተቀበለ ሲሆን ይህም በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈለት ብቸኛ ሐዋርያ ነው፡፡
እነዚህ እስካሁን ከላይ ያየናቸው ሶስት ሐዋርያት ማለትም ጴጥሮስ ፣ ዮሐንስና ያዕቆብ አዕማደ ሐዋርያት (የምስጢር ሐዋርያት) ይባላሉ፡፡ ገላ 2÷9
#4 ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ
ቅዱስ እንድርያስ የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ሲሆን ትውልዱም በቤተሳይዳ ነው፡፡ በዓሳ ማጥመድ ተግባር ላይ ሳለ በጌታ ቃል በመጀመሪያ የተጠራ ነው፡፡ ዮሐ 1÷35-45 ጌታን ከመከተሉ በፊት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነበር ዮሐ 1÷41 ቅዱስ እንድርያስ መጀመሪያ የስብከት ሥራውን በፍልስጥኤም ጀመረ፡፡ የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ የነበረው አውሳብዮስ እንደገለጠው እንድርያስ በሩስያ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ቀጥሎም በቢታንያ ፣ በገላትያ ፣ በሩማንያ ፣ በመቄዶንያ ፣ በታናሽ እስያ ፣ በግሪክ አገሮች አስተምሯል፡፡ የቁስጥንጥንያን ቤተክርስቲያን የመሰረተና የቁስጥንጥንያ የመጀመሪያ ሊቀጳጳስ መሆኑ በቤተክርስቲያን ታሪክ ይነገራል በመጨረሻም ግሪክ ውስጥ ምትሩ ለምትባለዋ ሀገር ሲያስተምር በጣዖት አምላኪዎች እጅ "ረ" የሚመስል ቅርጽ ባለው መስቀል ተሰቅሎ በድንጋይ ተወግሮ ታህሳስ 4 ቀን በ80 ዓ.ም በሰማዕትነት አርፏል፡፡
#5 ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ
ቅዱስ ፊልጶስ ሀገሩ ቤተሳይዳ ነው፡፡ ዮሐ 1÷14 ጌታ ተከተለኝ ባለው ጊዜ ወዲያውኑ ጥሪውን በመቀበል ጌታን ከመከተሉም በተጨማሪ ናትናኤልን ወደጌታ ያቀረበ (የጠራ) እርሱ ነው፡፡ የሐ 1÷46-47 ጌታችንን ለማየት የፈለጉት ከአህዛብ ወገን የነበሩት ግሪኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርበው የተማሩት በፊልጶስና በእንድርያስ አቅራቢነት ነበር፡፡ ዮሐ 12÷2-22 ሐዋርያው ወንጌልን በታናሽ እስያ ውስጥ በምትገኘው በፍርግያ አስተምሯል፡፡ በመጨረሻም በታናሽ እስያ ሲያስተምሩ በተቃዋሚዎች እጅ ተሰቅሎ ዐርፏል፡፡
#6 ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ /ዲዲሞስ/
ሐዋርያው ቶማስ በፋርስና በሕንድ አስተምሯል፡፡ ሕንድ የደረሰው በ46 ዓ.ም ገደማ ነው፡፡ ጌታ ከሙታን እንደተነሳ ለሐዋርያት በተገለጠበት ጊዜ ቶማስ ስላልነበረ ከሞት መነሳቱን ሐዋርያት ሲነግሩት ሳላይ አላምንም አላቸው፡፡ ጌታ ሁሉም ባለበት እንደገና ተገልጦ ቶማስ በጣቱ የጌታን የተወጋ ጎኑን ፣ የተቸነከረውን እጅና እግሩን ዳስሶ አምኗል፡፡ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎም መስክሯል ዮሐ 20÷14-29 መምልኪያነ ጣኦት በ86 ዓ.ም የቅዱስ ቶማስን ቆዳውን ገፈው ስልቻ በመስራት በሰውነቱ ላይ ጨው ነስንሰው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉት ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ገጽ 336-341
ይቀጥላል ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያድርሱ


" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ "
ሉቃ 1፥19

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ
ህዳር 21 አክሱም ፅዮን እንኳን አደረሳችሁ
በዚህች ቀን የእስራኤላውያን መመኪያ በእመቤታችን ስም የተሰየመችው ታቦተ ጽዮን ዳጐን በተባለው ጣኦት ላይ ኃይሏን ክብሯን የገለጸችበት ቀን ነው፤ ቤተክርስቲያን ጽዮን ማርያም ስትል ዕለቱን ታከብረዋለች። ታሪክ : - አክሱም ጽዮን እንደዛሬው ድርቅ ያለ መሬት አልነበረም ባህር ነበር እንጂ፤ አብርሃና አጽብሃ ለታቦተ ጽዮን ምን ዓይነት ቤተክርስቲያን ነው የምንሰራላት ቦታውስ የት ጋር ነው የሚሆነው እያሉ ሲጨነቁ ጌታችን ተገለጸላቸው ድንጋይ ላይ ቆሞም አዩት፤ ቤተክርስቲያኗን እዚህ ባህር ላይ ስሩት ስሟንም በእናቴ ስም ሰይሟት፤ ይላቸዋል ጌታ ሆይ ይህ እኮ ባህር ነው ይሉታል ቅዱስ ሚካኤልን ከገነት አፈር ይዞ እንዲመጣ ያደርገዋል ባህሩ ላይ ነሰነሰው ደረቀ የዛሬውንም ቅርጽ ያዘ ይላል ጌታችን የቆመበት የእግሩ ምልክት ዛሬም ድረስ ይታያል ፤ ምንጭ ድርሳነ ጽዮን፤ ዳግመኛ በዛሬዋ ዕለት ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ይለዋል የእረፍት ቀኑ ነው፤ አገሩ ቢሉ ሮም ነው የተማረ ግብረ ገብ ነው፤ዓለም ያልፋል ይጠፋል ብሎ መንኖ ገዳም ገባ በተጋድሎም ኖረ፤ በወቅቱ የነበረው ኤጲስ ቆጶስ በሞተ ጊዜ በምትኩ ጎርጎርዮስን ሊሾሙ አባቶች ተሰበሰቡ እርሱ ግን ሹመት አልፈልግም ብሎ ከመካከላቸው ተሰወረ፤ እርሱ በሌለበት ወንበር ዘርግተው ወንበሩን ካባ ላንቃ አልብሰው የጎርጎርዮስን ስም እየጠሩ ጸሎት አድርገው ይሾሙታል ህዝቡም 3 ጊዜ ይደልዎ ይደልዎ ይላል፤ ይገባዋል ማለት ነው፤ ከዚህ በኃላ የእግዚያብሔር መልአክ ተገልጾ ከዚህ ገዳም ውጣ ሹመትህን ተቀብለህ ህዝቡን አገልግል ይለዋል፤ እንደተባለውም አደረገ ለ 45 ዓመት በሹመት ህዝቡን አገልግሏል፤ ብዙ ተግሳጻትን ድርሳናትን ደርሷል፤ ከነዚህ አንዱ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ነው፤ በሰሞነ ሆሳህና የሚቀደስ ቅዳሴ ነው፤ ለምን ጎርጎርዮስ ገባሬ መ
አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
#ኅዳር_21_የቅድስት_ድንግል_ማርያም_እና_የታቦተ_ጽዮን_በዓል_እንኳን_ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_አደረሳችሁ፡፡

በዛሬው እለት ከማኅበራዊ ድረገጽ ያገኘሁትን ታቦተ
ጽዮን ታላቅ ተአምራትን በዳጎን ላይ ማድረጓን
የሚገልጸውን ሥዕል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን በፎቶ የተነሣ ሥዕል በማግኘቴ
ላካፍላችሁ ወደድኩ

“እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም
ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።ይህች
ለዘላለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች
አድራለሁ።አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥
ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።ካህናቶችዋንም
ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ
ይላቸዋል።” መዝ 131:13
“ጽዮን” ማለት “ጸወን – አምባ – መጠጊያ” ማለት
ነው:: አንድም በምሥጢሩ “ማሕደረ አምላክ”
ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ
ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ
ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና
ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::
ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ
የምናከብርበት ምክንያት፡-
1. በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ
ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል
የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ
ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ
ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
4. ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
5. ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
6. ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
7. አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ
አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ
ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን
ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ
ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ
ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት
አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት
በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን
ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡
የወላዲተ አምላክ አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት
ከእኛ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡
ወለወላዲቱ ድንግል፡፡
ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸውና። ወደ ህይወት የሚወስደው ደጅ መንገዱም የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
👉#የማቴዎስ_ወንጌል 7:13_14
ጠባብና ቀጭን መንገድ ያላት ተዋህዶ
ሀይማኖታችን ለዘላለም ትኑር🙏🙏🙏💖💖https://telegram.me/atronss
የጌታ ልጅ ነኝ አባቴ ጌታ ነውና፤
የመለኮት ልጅ ነኝ አባቴ አምላክ ነውና፤
የንጉሥ ልጅ ነኝ አባቴ ንጉሥ ነውና፤
የብርሃን ልጅ ነኝ አባቴ ብርሃን ነውና፤
የኤልሻዳይ ልጅ ነኝ አባቴ ሁሉን ቻይ ነውና፤
የአዶናይ ልጅ ነኝ አባቴ አዶናይ ነውና፤
የደሙ ፍሬ ነኝ በደሙ ገዝቶኛልና፤
በደሙ ተገዝቼ፣ በጥምቀቱ ተወልጄ፣ በቅዱስ መንፈሱ በቅዱሱ ቅብዓት ታትሜ፣ በቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የዘላለም ሕይወትን ያገኘሁ የማይሽሩት ንጉሥ የማይሾሙት ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጅ ነኝ

አቤቱ ጌታ ሆይ ሳይገባኝ እንዲህ ያከበርከኝ ዘላለም ክበርልኝ።
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
አቤቱ ተወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፦
የምንኮራበት ክብራችን የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤
ጌታችን ሆይ፦ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡ እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን፤ ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፡፡

https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
እውነተኛ ፍቅር

1ጢሞቴዎስ /10/

“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው” 1ጢሞ. 1፡5 ።

አይሁዳውያን በአንድ እግርህ ቆመህ የምትናገረው የሚል አባባል አላቸው ። በአንድ እግር ቆመው የሚናገሩት እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ መውደድና ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ነው ። “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለውን ቃል ደግማችሁ አስቡት ። ባልንጀራን እንደ ራስ የምትወዱ ከሆነ እግዚአብሔርን ከራሳችሁ በላይ መውደድ አለባችሁ ማለት ነው ። እግዚአብሔርን አልጠላም ማለት እግዚአብሔርን መውደድ አይደለም ። እግዚአብሔርን የምንወዳቸውን ያህል መውደድም እግዚአብሔርን ትልቅ ለማለት መፈተን ነው ። እግዚአብሔርን የራስ ያህል መውደድም ራስንና እግዚአብሔርን ማምለክ ነው ። እግዚአብሔርን ከራስ በላይ መውደድ እርሱ እውነተኛ አምልኮ ነው ። የሮማን ፍሬ አንድ ነው ፤ በውስጡ ግን ብዙ ፍሬዎችን ይዟል ። የምንጠራው ግን አንድ ሮማን ብለን ነው ። ፍቅርም እንደ ሮማን ፍሬ ነው ። በውስጡ ብዙ የሕግና የትእዛዝ ፍጻሜዎች አሉ ። ፍቅርን ገንዘብ ያደረገ ሁሉንም ትእዛዛት ፈጸመ ። ፍቅር አባ ጠቅል ነው ።

ሕግ ማለት የአታድርግ መመሪያ ነው ። ትእዛዝ ግን የአድርግ መመሪያ ነው ። ባለማድረግ መቀደስ አለመስረቅ ፣ አለመግደል ነው ። በማድረግ መቀደስ ግን መስጠት ፣ ለሌሎች ቸርነት ማድረግ ነው ። ሐዋርያው ስለ ሕግ እየነገረን አይደለም ። ሕግን የጨዋ ልጆችም ይጠብቃሉ ። አይገድሉም ፣ አይሰርቁም ፣ አይሳደቡም ። ከክርስቲያን ከዚያ ላቅ ያለ ነገር ይፈልጋል ። በእውነት ክርስትና ከጨዋነት በላይ ነው ። ክርስቲያን የሆነው ፖሊስ ላለማስቸገር አይደለም ። የዓለምን ሕመም ለመቀነስም ነው ። የዓለምን ሕመም የምንቀንሰው የሚያለቅሱትን እንባቸውን በማበስ ፣ ያዘኑት በማጽናናት ፣ የወደቁትን በማንሣት ነው ። በፍቅር ሕግን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ትእዛዛትን መፈጸም እንችላለን ።

ፍቅር ከሦስት ምንጮች ከተቀዳ ያን ጊዜ እውነተኛ እየሆነ ይመጣል ። ትእዛዛትንም ይፈጽማል ። እነዚህ ምንጮች ንጹሕ ልብ ፣ በጎ ኅሊናና ግብዝነት የሌለበት እምነት ናቸው ።

በየዕለቱ ልባችን እየደፈረሰ ተቸግረናል ። አንደኛውን ስህተት ይቅር ለማለት ታግለን እንደ ምንም ይቅርታ ካደረግን በኋላ የዚያኑ ቀን ሰዎቹ ሌላ ጥላሸት ይቀቡናል ። እንደ ገና ይቅርታ ባይገባቸውም ለራሳችን ሰላም ስንል ያንን ጥቁር ቀለም ለማጥፋት በጸሎት ፣ በቃሉ ፣ በምክር ፣ ያልበደሉንን ሰዎች በማሰብ ፣ የቀደመውን ጥሩ ጊዜ በማስታወስ ለማጽዳት እንሞክራለን ። ሰዎቹ ግን መልሰው አሁንም ልባችንን ያቀልሙታል ። ተሰብረን ስለምንኖር ይሰብሩናል ። ካልፈቀድንላቸው ግን አይሰብሩንም ። ሞተን ካልጠበቅናቸው አይገድሉንም ። ሞተን ስንጠብቃቸው ግን ገደልን ብለው ይፎክራሉ ። ንጹሕ ልብ በየቀኑ የምንቸገረው ነገር ሁኗል ። ያለፉት ዘመናት የጣዖትና የዓለማዊነት ትዝታዎችም ድቅን እያሉብን ንጹሕ ልባችንን እንከስራለን ። የምናየውና የምንሰማውን ስለማንመርጥም ልባችን ይቆሽሻል ። ሁልጊዜ በተግባር አንበድልም ። በአሳብ ግን ስንበድል እንኖራለን ። አሳባችን ሁሉ ቢከናወን አወይ ሰው ነኝ ለማለት ባልበቃን ነበር ።

እጅ እግር የሌለው ፣ ተግባር የጎደለው ፍቅር በዓለም ላይ አለ ። ይህ ፍቅር ንጹሕ ልብ ስለሌለው ነው ። በጥርጣሬ የሚታመስ ፍቅር በጎ ለማድረግ ይዘገያል ። “እባብ ያየ በልጥ ይደነብራል” እንዲሉ በትላንት ገጠመኙ የዛሬ ፍቅሩን የሚለካ ሰውም አፍቅሮም ፈሪ ነው ። ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል ማለት ብከዳ ፣ ብጎዳ አይልም ማለት ነው ። ምክንያቱም ምንጊዜም ተጎጂው አፍቃሪው ሳይሆን ፍቅርን የገፋው ሰው ነው ። ልቅሶ ቦታ ተለዋውጦ እንጂ ማልቀስ ያለበት ከዳተኛው ነው ። ከንጹሕ ልብ የማይወጣ ፍቅር በጎነት የለውም ። በእጁ አይሰጥም ፣ በእግሩ አይደርስም ። ንጹሕ ልብ የሌለው ፍቅር አካለ ጎዶሎ ነው ።

ፍቅር ማለት ቃላት ሳይሆን ተግባር ነው ። እውነተኛ ፍቅርም ከስሜት ይልቅ ለተግባር የሚያደላ ነው ። ሰዎች ተግባራዊውን ፍቅር አይወዱትም ። ከዚያ ይልቅ የሚያቆላምጣቸውንና የሚያጫውታቸውን ዱርዬ ይወዳሉ ። እውነተኛ ፍቅር ግን ተግባራዊ ነው ። እግዚአብሔር ከረዳን የቃልና የስሜትን ፍቅር ትተን ተግባራዊውን ፍቅር መከተል አለብን ። ወላጆቻችን አንድ ቀንም እወዳችኋለሁ ብለውን አያውቁም ። ፍቅራቸው ግን ተግባራዊ ነው ። ቀላል ልብ ያለው ሰው በድለላ ይሸፍታል ። ዛሬ እስቲ እናስተውል በተግባር የሚወዱን እነማን ናቸው ? ብለን እናስብ ። እኛም በተግባር የምንወዳቸውን ለማሰብ እንሞክር ። እውነተኛ ፍቅር ተግባራዊ ነው ። “እንደምትወደኝ አትንገረኝ ፣ እንደምትወደኝ አሳየኝ” የሚል አባባል አስታውሳለሁ ።

ፍቅር ተግባራዊ እንዳይሆን ሁለተኛው መሰናክል “በጎ ኅሊና” ማጣት ነው ። ዛሬ በዓለም ላይ ትልቁ የሰላም ምሥጢር በጎ ኅሊና እንደሆነ ታምኗል ። የዘወትር ጸሎታችንም ሊሆን የሚገባው፡- “አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” የሚለው ነው ። መዝ. 50፡10 ። ደጋግመን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እንደምንለው ደጋግመን ይህን ጸሎት መጸለይ ይገባናል ። የቀና መንፈስ ፣ ቀናነት ፣ ለነገሮች በጎ ትርጉም መስጠት የደስታ መሠረት ነው ። ቀናነትን በተፈጥሮ የታደሉ ጥቂቶች ናቸው ። ቀናነትን ለማግኘት ብዙ ተጋድሎ ያስፈልጋል ። ንጹሕ ልብ ለራስ ሲሆን ቀናነት ግን ሰዎችን የምናይበት መነጽር ነው ። በሰለጠነው ዘመን “ሰዎች ለምን ክፉ ሆኑ ? ምን ዓይነት ጉዳት ቢደርስባቸው ነው ?” ተብሎ ታሪካቸው ይጠናል ። እርዳታ ለማድረግ ይሞከራል ። ክርስትናችን ግን ከሥልጣኔ አንሶ ቅንነት አልባ ሁኗል ። በጎ ኅሊና ከምቹ ትራስ ይልቅ ዕረፍት እንደሚሰጥ ይነገራል ። አዎንታዊነትን ማዳበር ከክርስትና አልፎ ዘመናዊነት እየሆነ ነው ። ፍቅር ተግባራዊ እንዲሆን በጎ ኅሊና አጋዥ ነው ።

ግብዝነት የሌለበት እምነት ለተግባራዊ ፍቅር ወሳኝ ነው ። ተዋንያን በሰዓት ሲሠሩ በሃይማኖት ስፍራ ያሉ ግብዞች ግን ለዘመናት የመተወን አቅም አላቸው ። ተውኔት በመድረክ እንጂ በሕይወት ሲሆን ከባድ ነው ። ከእውነተኛነት ግብዝነትን የሚያከብር ማኅበረሰብ ቢፈጠርም እውነት ግን ከእግዚአብሔር ጋር የምታገናኝ ድልድይ ናት ። ጽድቃቸውን ከሚነግሩን ድካማቸውን የሚነግሩን እውነተኞች እነርሱ ተስፋ ይሰጡናል ። መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአተኞችን የሚረዳ መጽሐፍ የሆነው ስለ ሰዎች ፍጹምነት ሳይሆን ስለ ድካማቸው ስለሚነግረን ነው ። የዳዊትን መግደልና ምንዝርና ፣ የጴጥሮስን መካድ ፣ የጳውሎስን ፀረ ክርስቲያንነት የሚነግረን ፤ ውድቀት መጨረሻ አለመሆኑን ተረድተን እንድንነሣ ነው ።

“በፍቅር ኃጢአቶቻችን ሁሉ ይቅር ይባሉልናል ።” ፍቅር ካለንም የሌሎችን ኃጢአት ይቅር እንላለን ። እውነተኛ ፍቅር ሦስት ምንጮች አሉት ። ንጹሕ ልብ ፣ በጎ ኅሊናና ግብዝነት የሌለበት እምነት ናቸው ። እኛ የጎደለን የቱ ይሆን ?
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss


ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። ኦሪት ዘሌዋውያን 20:13



እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 1:18-28



ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:9-11



ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24



ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:3



መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ወደ ዕብራውያን 13:4
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
ተክልዬ አባቴ 24 እንኳን አደረሳችሁ🙏
አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በጥቂቱ
አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የክርስቶስ ፍቅር ብልጫ ሆኖባቸዋልና ፡ ክርስትናቸውም የጣኦትን አምልኮ ተፀይፋለችና እኔ ክርስቲያን ነኝ በማለት የወንጌሉን የቃል ትምህርት በህይወት እየኖሩ አልጫ ለሆነው አለም ጨው ፡ በጨለማ ላለው ህዝብ ብርሃን ሆነው በኢትዮጵያ ከሰሜን እስከደቡብ ከምእራብ እስከ ምስራቅ ወንጌልን በቃልና በተግባር እያስተማሩ ዞሩ ፤ አለምን ንቀዋታልና ሃብትንና ስልጣንን ገፍተው ስለክርስቶስ በዱር በገደል በገዳም በዋሻ ይኖሩ ዘንድ ራሳቸውን ግድ አሉ፡፡ በነገስታት ቤት በቅምጥል ከመኖር ይልቅ ስለክርስትናው የነፃነትና የህይወት ምስክርነት በጣኦት አምላኪወች ፊት በሃዋርያት ድፍረት በሰወች ፡ በእንስሳትና በእፅዋት ላይ አድሮ ክርስቶስን ያስካደውን ፡ እግዚአብሄርን ያስረሳውን የዲያቢሎስ ሰራዊት በፅድቅ ታገሉት ፡ በወንጌሉ ሃይል ድል ነሱት ፡ በክርስቶስ ቃል አሳፈሩት ፡ በጨለማ ይንከላወስ ለነበረው ህዝብም ክርስቶስን ሰበኩላቸው ፡ በስላሴ ስም አጠመቋቸው ፡ የክርስቶስን ቅዱስ ስጋ ክቡር ደም አቀበሏቸው ፡ ዳግመኛም ቤተክርስቲያንን አሳንፀው ፡ ምእመናን መልሰው ወደጣኦት አምልኮ ወደሃጢአትም እንዳይመለሱ ፡ ካህናት አባቶችን እንዲጠብቋቸው እያዘጋጁላቸው ለህዝቡ ሁሉ ሃዋርያ ሆነው ኖሩ፡፡
ለሰውነታቸው እረፍትን ለስጋቸው ምቾትን ያሳዩአት ዘንድ አልወደዱም ፡ መከሩ ብዙ ሰራተኛው ግን ጥቂት እንደሆነ ተገንዝበዋልና ፡ ለሁሉ ክርስቶስን ሰብከው ፡ ሁሉን ክርስቲያን አድርገው እስኪጨርሱ ድረስ ተጋድሏቸውን አስረዘሙ ፡ የክርስቶስ ቅናት ግድ ብሏቸዋልና ፡ የዲያቢሎስ በህዝቡ ላይ መሰልጠን ልቦናቸውን አስቆጥቶት ነበርና ስጋቸው ያርፍ ዘንድ አልወደዱም፡፡ “የሁሉ ፈጣሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው” እያሉ ባላመኑት ፊት ፡ በሚያስፈሩት ፊት ፡ ዲያቢሎስ በሚመለክበት ፡ አስማት ጥንቆላ በገነነበት ፡ ሰው መግደል ቀላል በሆነበት ፡ ክፋት በነገሰበት ፊት ለስጋቸው ሳይሳሱ መሰከሩ ፤ መገረፍን እየታገሱ ወንጌልን መሰከሩ ፡ ወንጌልን በቃል በግብር መሰከሩ ፡ ወርቅ ሃብትን እየናቁ ክርስቶስን ሰበኩ ፡ ክርስትናን ሰበኩ፡፡
ዲያቢሎስ ግን ታገላቸው ፡ የሰውን ልብ አራዊት እያደረገ ፡ በምትሃትና በማስመሰል የሰውን ህሊና እየተቆጣጠረ ፡ በግልፅና በስውር ታገላቸው ፡ ክርስቶስን መስበክ ያቆሙ ዘንድ በሃብት በጥጋብ በምቾት ያታልላቸው ዘንድ በአለማዊ ቅምጥልና ታገላቸው ፡ የውሽት ወሬን እያስወራ ፡ የሃሰት ምስክሮችን እያቆመ ፡ መልካሙን ስራቸውን እያክፋፋ ታገላቸው ፡ ዲያቢሎስ በሰው አድሮ ታገላቸው ፡ የዲያቢሎስ ትግል ግን አባታችንን ብቻ አልነበረም ፡ ክርስትናውም እንዳይሰበክ ታገለ እንጂ ፡ ክርስቶስ እንዳይመለክ ታገለ እንጂ ፡ መልካምነት እንዳይሰለጥን ታገለ እንጂ ፡ ዲያቢሎስ አባታችንን ታገላቸው ፡ አስገረፋቸው ፡ አሰደዳቸው ፡ ወደ ጥልቁ አስወረወራቸው ፡ በእጅጉ ታገላቸው ፡ አባታችን ተክለሃይማኖት ግን በክርስቶስ ሃይለኛ ነበሩ ፡ የሃዋርያትን መንፈስ የያዙ ነበሩና ፡ ስለሚያስተምሩለት ፡ ስለሚደክሙለት የምስራች ፅኑ እምነት ነበራቸውና ፡ የቆሙበት መሰረት ክርስቶስ ነበርና ፡ ዲያቢሎስን ድል ነሱት ፡ የመንፈስን ጦር ታጥቀው ነበርና ፡ በወንጌል ቃል ስለትነት ዲያቢሎስን ድል ነሱት ፡ ከሰለጠነበት ሻሩት ፡ የማረከውን አስመለሱት ፡ ለእርሱ ይገብሩ የነበሩትን ሁሉ ለክርስቶስ አስገበሩ፡፡
በዘመናቸው ክርስትና ደመቀች ፡ ክርስቶስ ከበረ ፡ ወንጌል ተሰበከች ፡ የዲያቢሎስ ሃይል ደከመ ተሻረ ፡ አብያተ ጣኦታት ተዘጉ ፡ አብያተ ክርስቲያናት ተከፈቱ ፡ ካህናተ ጣኦታት ተሻሩ ካህናተ ክርስቶስ ተሾሙ ፡ በአባታችን ፅኑ የምትመስል የወንጌል ቃል በህይወት ታየች ፡ በተግባር ተዳሰሰች ፡ ክርስቶስ ከበረባት ፡ ዲያቢሎስ ወደቀባት ፤ እኔን ብቻ ይድላኝ ይሙቀኝ ብለው በአለማዊ ቅንጦት ይኖሩ ዘንድ አልወደዱምና ፡ ለብዙወች ተረፉ ፤ መስቀሉን ተሽክመው ክርስቶስን ተከተሉት ፡ በዚህም ብዙወችን አስከተሉ ፡ በፆም በፀሎት በትህርምት ፡ በበጎነት ፡ በሃይል በስልጣን ፡ በእምነት በፀጋ ፡ ወንጌልን ለብሰው ብርሃን ሆነው ታዩ ፡ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ እንደማትችል ፡ ፀሃይም ብርሃኗን ስትሰጥ ለመደበቅ እንዳይቻላት የአባታችን የተክለሃይማኖትም ፅድቅ ሊደበቅ አይቻለውም ፡ ብርሃን ነውና ለሁሉ አበራ ፡ ጨው ነውና ሁሉን አጣፈጠ ፡ መርከብ ነውና በማእበል የተገፉትን አሻገረ፡፡
አቡነ ተክለሃይማኖት በረከት ይደርብን

https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
https://telegram.me/atronss
#አጭር__ታሪክ
"አቤል ለምን ወንድሙን ቃኤልን ገደለው ???

አቤል እና ቃኤል የመጀመሪያው #ሰው የመጀመሪያ ልጆች ናቸው #ብዙ_ተባዙ የሚለው ቃል የተፈጸመው አዳም እና ሔዋን እኒህን ልጆች
ከወለዱበት ጀምሮ ሲሆን ……

የሰው ልጅ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነም ማሳያዎች ናቸው
አቤልና ቃየል ወንድማማች ሲሆኑ ሁለቱም መንትያ እህቶች ነበሯቸው የመንትዮቹም እህቶቻቸው ስም ሉድና አቅሌማ ይባላሉ ።
አዳም አቤልና ቃኤል ሉድና አቅሌማ ስለተወለዱለት እጅግ ደስተኛ ነበር ይሁን እንጅ በአንጻሩ ደግሞ ልጆቹ ባጠፉት ጥፋት አዝኗል ታሪኩ እንዲህ ነው፦

አቤልና ቃኤል ለአቅመ አዳም ሲደርሱ አባታቸው አዳም ልጆቹን ትዳር ማስያዝ ፈለገ ሆኖም እግዚአብሄር የሚሠራው የጋብቻ ሕግ ለአዳም ተገልጾለት አራርቆ ለማጋባት ሲል
የአቤልን መንትያ ለቃኤል
የቃኤልን መንትያ ለአቤል አድርጎ ለማጋባት ወሰነ በዚህ ጊዜ የጋብቻውን ነገር የሚቃወም
የአባቱን ምክር ያልተቀበለ ቃኤል አኮረፈ የአባቱንም ውሳኔ ላለመቀበል በዓመጽ ቃል ተናገረ።

አዳም ለልጁ የማይጨነቅ ሰው ሆኖ ሳይሆን ልጁ ለአባቱ የማይታዘዝ በመሆኑ ነው

ዛሬም እኮ የአባታቸውን ትእዛዝ የማይቀበሉ በስሜት እንጅ በዕውቀትና በእውነት የማይጓዙ ለጊዜያዊ እርካታ ሲሉ ዘላለማዊውን ክብር የዘነጉ የእግዚአብሔርን ቃል የጣሱ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣረሱ ለስጋቸው የኖሩ በነፍሳቸው የከሰሩ ለዓለም የሚሮጡ ለክፉ ምኞት የተሰጡ
በሰይጣን ሐሳብ የቀለጡ በዲያብሎስ ምክር የተቀጠቀጡ በስጋ ስራ የተዋጡ በመንፈሳዊ የታጡ
ብዙዎች አሉ
ከመልካም ነገር የለዩ የምድርን እንጅ የሰማዩን ክብር የማያዩ አሉ ከዚህ አይነት ሕይወት ይጠብቀን
የአባትን ትእዛዝ ማክበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማክበር ነው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማክበር ደግሞ የመንፈሳዊ ሰው መገለጫ ነው

ታድያ የአባቱን ትእዛዝ ያላከበረው የቃኤል ምክንያት የቁንጅና ጉዳይ ነበር ምክንያቱም የቃኤል መንትያ መልከ መልካም ስትሆን የአቤል መንትያ ደግሞ መልከ ጥፉ/የማታምር ነበረች በዚህም ምክንያት የእኔን መልከ መልካም ለወንድሜ ሰጥቶ
የወንድሜን መልከ ክፉ ለእኔ እንዴት ይሆናል?

የሚል ሐሳብ ነበር ያቀረበው የልጁን መከፋት የተመለከተው አዳምም ሁለታችሁም መስዋዕት አቅርቡ እግዚአብሔር የፈቀደለት መልካሟን ሊያገባ ይችላል በማለት ሁለቱም የእግዚአብሔርን ፈቃድመጠየቅ እንዳላባቸው ነገራቸው
በአዳም ትእዛዝ መሠረት ሁለቱም ከእግዚአብሔርን ፈቃድ አግኝተው ለማግባት መስዋዕት
ለማቅረብ ተዘጋጁ በዚህ ጊዜ

#አቤል በግ ጠባቂ ነበርና
ከበጎቹ ቀንዱ ያልከረከረውን ጸጉሩ ያልዘረዘረውን
የሚያምር በግ ለመስዋዕት አቀረበ

#ቃኤል ደግሞ ገበሬ ነበርና ከአዝርእቱ ያገኘውን ምንም ሳይመርጥ እግዚአብሔር እንደሆነ ወርዶ አይመገበው በማለት በቸልተኝነት ድብልቅልቁን አቀረበ

በዚህ ሰዓት እግዚአብሔር ወደ አቤል ና
ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ ወደ ቃኤልና ወደ መስዋዕቱ ግን አልተመለከትም ምክንያቱም አቤል እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ነውና ንጹሕ ነገር ሊያቀርቡለት ይገባል በማለት ተገቢውን መስዋዕት ሲያቀርብ ቃኤል ግን እግዚአብሔር አይበላው በማለት የተገኘውን ግብስብስ ነገር በማቅረቡ ለእግዚአብሔር ከልቡ
አለመገዛቱን ያመለክታል በዚህ የቃኤል መስዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም

የሰው ልጅ ገንዘቡን
ከመስጠቱ በፊት ራሱን ለፈጣሪው ሊሰጥ ይገባል ገንዘብን ከመስጠት ራስን መስጠት ይቀድማልና
ደግሞም የሰው ልጅ የሚፈልገውን ለማግኘት እግዚአብሔርን መጠየቅ እንደሚገባ እንማራለን
ከእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ሁልጊዜም መልካም ነውና

ታድያ በዚህ ጊዜ ቃኤል መስዋዕቱን ስላልተቀበለው አዳም ቢፈርድ ለአቤል እግዚአብሔር ቢፈርድ ለአቤል ብሎ በወንድሙ ላይ ቂም ያዘበት ወንድሙንም ለመበቀል ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ይከታተል ጀመር

ዓለም ሁልጊዜም በዓመጽ የተሞላች የክፉዎች መንገሻ
የንጹሆች መርከሻ ነችና
ጌታችንም ደቀ መዛሙርቱን
"ከዓለም አይደላችሁምና ዓለም ይጠላችኋል" ያላቸው በምድር አትኖሩም ለማለት ሳይሆን በምድር
ሲኖሩ ምድራዊ ስራ አለመስራታቸውን ያመለክታል እነርሱ በዓለም ተገፉ እንጅ ዓለምን አልገፉም ተገረፉ እንጅ አልገረፉም ተገደሉ እንጅ አልገደሉም የእውነት ጉዞ ሁልጊዜም ከዝቅታ ወደ
ከፍታ ነውና ይህም ሰማያዊ ዋጋን ያሰጣልና

ይሁን እንጅ ወንድሙን ለመበቀል የተመቻቸ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ እንቅልፍ አልነበረውም የሚገርምና የሚያሳዝን ልብን የሚነካ ነገር ነው
ሰው እንዴት ወንድሙን ለመግደል ይህን ያህል ያደባል ?ደግሞም በአንጻሩ አቤል ወንድሙ
ቃኤልን እጅግ ይናፍቀው ይንከባከበው ይጨነቅለትም ነበር

ዓለም በገዳይ እና በተገዳይ በአሸናፊና በተሸናፊ የተሞላች ነች አንዱ ሲያገኝ አንዱ
ሲያጣ አንዱ ሲደሰት ሌላው ሲከፋ አንዱ ሲስቅ አንደኛው ሲያለቅስ አንዱ ሲሾም ሌላኛው ሲከብር አንዱ ሲከብር ሌላኛው ሲዋረድ ነው ዓለም ሁሉንም በእኩልነት
አስተናግዳ አታውቅም የቃኤል ቅናት ወደ ገዳይነት ከፍ ስላለ ይህን ለማድረግ እንዲህ ብሎ አሰበ ወንድሙን ወደ ውጭ ወስዶ ለመበቀል
ወንድሙ አቤልም የቃኤልን ክፋት ስላላወቀ ከወንድሙ ጋር ጉዞ አደረገ
ብዙ ጊዜ እንደ አቤል በደግነት ምንም አይነት ክፉ ስራ ሳይሰሩ በመኖራቸው ከኃጢአት ጋር ባለመተባበራቸው የተወነጀሉ ብዙዎች ናቸው አቤል ልቡ ንጹሕ ነው ቃኤል ግን ቂም ይዟል ወንድሙን በአንደበቱ እንደሚወደው ይነግረዋል በልቡ ግን ሊገድለው ተዘጋጅቷል "በአፉሆሙ ይድኅሩ ወበልቦሙ ይረግሙ"በማለት በአንደበታቸው የሚመርቁ በልባቸው ግን የሚራገሙ ሰዎች እንዳሉ ቅዱስ ዳዊት ተናግሯል ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ምግባር ነው "አፍኒ ወልብ ኅቡረ ይእመኑ =አንደበትና ልቡና በአንድነት ይመኑ ይህ ካልሆነ ግን መልካም ስራ መስራት አይቻልም የአቤልና የቃኤል ኑሮ በአንደበት እንጅ በልብ የተለያዩ ነበሩ
ይህ የዘመናችን የብዙዎች ችግር ነው
ባል ከሚስቱ ባልንጀራ ከባልንጀራው
የማይግባባው በአንደበት እንጅ በልብ መግባባት ስላልተቻለ ነው ይህንን የልዩነት መንፈስ እግዚአብሔር ከምድራችን ያስወግድልን

ቃኤልም የልቡን ምኞት ለመፈጸም
ወደ ወንዝ ዳር ወንድሙን ወስዶ ውሀ በሚጠጣበትሰዓት በድንጋይ ቀጥቅጦ እንደዕባብ
ገደለው ከዚህች ዕለት ጀምሮ
ቃኤል ሰላሙን አጣ ተቅበዝባዥ ሆነ የሚያየውን ሁሉ
ተጠራጣሪ ተንከራታች ሆነ ደግሞስ ሰው ወንድሙን ገድሎ ምን ሰላም ይኖረዋል?

እግዚአብሔርም የቃኤልን ስራ ተመለከተ በመጥፎ ስራውም አዘነ እንዲህም አለው አቤል ወንድምህ የት አለ?አለው ቃኤልም እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?አላውቅም በማለት በትእቢት ቃል መለሰ መጽሐፍ "እስመ እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ" =ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል ማቴ12፥33 እንዳለ በክፉ ስራው ምክንያት ክፉ መልስ ለፈጣሪው መለሰለት

ሁልጊዜም ስራው ክፉ የሆነ ሰው
ከአንደበቱ መልካም ነገር ማፍለቅ
አይችልም ከኩርንችት በለስ እንደማይለቀም ሁሉ ከክፉ ሰውም መልካምነትን ማግኘት ፈጽሞ አይቻልም
እንግዲህ ወንድሙን በበቀል በድንጋይ የገደለው ቃኤል ዘመኑን በሙሉ በጭንቀት ኖረ አቤል አንድ ቀን ሞተ ቃኤል ግን በክፋቱ ምክንያት ቀን በቀን በስሜት እንደሞተ የሰቀቀን ዘመን ኖሮ በመጨረሻው እራሱ የሚኖርበት ቤት ተጭኖት ወንድሙን በድንጋይ እንደ ገደለው እሱም በድንጋይ ሞተ
" የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው"ሮሜ6፥23 እንዳለው በኃጢአት ከመሞት አምላካችን ይጠብቀን ዘመናችንን የፍቅር እድሜያችንን የበረከት ያድርግልን

"አምላኬን ሆይ ሕይወቴን በበረከት ባርክ ከክፉ ምኞት አ