አትሮኖስ
228K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ደቡብ ኮሎምቢያ/የአማዞን ደን
ዳግላስ አንድ ወር ከራቀበት የግል ግዛቱ ሲመለስ ፍፁም የሆነ ደስታ ነው የተሰማው፡፡ከመኪናው ወረዶ የቅፅር ግቢውን አፈር እንደረገጠ በውስጡ ጎድሎ የነበረው ኀያልነቱ መልሶ ሲሰርግበት ተሰማው፡፡አፉን በደንብ ከፈተና አየሩን ወደውስጥ ምጎ በመሳብ በአፍንጫው አስወጣው፡፡.አሁን ያለበት የግል ግዛቱ የሆነው እንደቤተመንግስቱ የሚያየው ስፍራ አስር ሺ ካሬ ላይ ያረፈ ቅፅር ግቢ…ወደ ሰሜን አቅጣጨ ጠጋ ብሎ በአንድ ሺ ካሬ ሜር ላይ ያረፈ ግዙፍ ባለአንድ ፎቅ ህንፃ ሲኖር.. ህንፃው….ከመሬት በታች አንደርግራውንድ ቤት ሲኖረው ሙሉ በሙሉ መግቢያው በጀርበ በኩል ሚስጥራዊ መሹለኪ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ በውስጡ ሀያ የሚሆኑ ሳይንቲስቶች ከነረዳቶቻቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያለእረፍት ይሰሩባታል፡፡ ምን አልባትም በአለም ግዙፍ የተባለው የኮኬይን ቅመማ የሚካሄድበት የተሞላ የላባራቶሪ እቀዎች የተተከሉበት….በየወሩ አንድ 100 ኩንታል ኮኬይን ተቀምሞ፤ ተመርቶና በተለያየ መጠን በጥንቃቄ ታሽጎ በኮሎምቢያ …ፓናማና… ሚክሲኮን በመሸገር በአሜሪካ የሚገባበትና የሚሰራጭበት እስከአውሮፓ የሚዘልቅ  ሰንሰለት ያለው ውስብስብ ስራ ነው፡፡
ኮኬይኑ እዛ ደርሶ ከተሰራጨ በኃላ ከሽያጩ ሚሰበሰበው ረብጣ ዶላል ለሁሉም ተወናዬች የየድርሻቸውን በማክፋፈል የቀረውን ዳጎስ የለ ድርሻ ለዳግላስ ተመልሶ የሚመጣበት አሰራር ነው ያለው፡፡ዳግለስ ለዚህ የኮከዬን ምርት ሚሆነውን የኮካ ዛፍ ምርት የሚያገኘው እዚሁ አሁን ካለበት ተያይዞ ካለ መቶ ሺ  ካሬ ሜትር የእርሻ መሬት ነው፡፡ቀሪውን 60 ፐርሰንት ግን ከአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ በአማዘን ደን ወስጥ ሆነ ከዛ ውጭ ተበትነው በሚገኙ ከግለሰብ ሆነ ከብድን እምራቾች ጋር በፈጠረው የንግድ ስምምነት ይሰበስብና ጉድለቱን ያሟላል፡፡
ይሄን ጥሬ እቃውን ከእርሻ ቦታም ሆነ በክፍያ ከሚሰበሰብበት ቦታ የሚሰበበስቡ እንዲሁም የቢዝነሱን ሆነ የእሱን ድህነንት የሚጠብቁ…ግደሉ ሲላቸው የሚገድሉ፤ ሙቱልኝ ሲላቸው የሚሞቱላት በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች አሉት፡፡የህንፃው ግራውንድ ላይ ደግሞ እታች ቤዝመንት ውስጥ ለሚሰሩት ሳይንቲቶችና ዋና ዋና የታጣቂ አዛዦች መኖሪያነት ያገለግለል፡፡ከላይ ያለው የመጀመሪያው ፍሎር ግን ለደግላስ የግል ቤተመንግስቱ ነው፡፡አንድ ግዙፍ ሳሎን፤30 የሚሆኑ መኝታ ቤቶች፤ከአምስት በላይ ቢሮዎችና በአጠቃላይ ከ50 በላይ ክፍሎች ከነቅንጡ እቀዎች ያሉበት ዘመናዊ ቤት ነው፡፡እዛው ቤት ውስጥ ደግላስና አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት አገልጋዬቹ ብቻ ናቸው የሚኖሩበት፡፡ከዛ ውጭ እሱ ኖረም አልኖረም ሳይፈቅለድት ወደ እዛ ህንፃ ለመውጣት የሚደፍር ሰው የለም፤ካለም በደግላስ ጥይት ወይ ግንባሩ ይፈረከሳል ወይ ደግሞ ደረቱ ይነዳላል፡፡
ሌላው የህንፃ ጣሪያ ከላይ እይታ እንዳይስብ  አረንጓዴ ሳርና ቋጥኝ መሰል ተክሎች እንዲለብስ ተደርጎ ሙሉ በሙሉ እይታው ከአማዞን ደን ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎል፡፡
የዳግላስን ወደቤቱ መምጡት አስመልክተው በስልፍ ሆነው የእንኳን በሳላም መጣህ አቀባበል ሊያደርጉለት እየጠበቅ ያሉትን ታጣቂዎችና ሌሎች ሰረተኞችን ቀላል እና አጭር ሰላምታ ሰጠና ቀጥታ አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሔደ፡፡ከዛ ወደዋናኛ መኝታ ቤቱ ነው የገባው፡፡አሁንም ያቺ ጠፋች የተባለችው ኢትዬጵያዊት ሴት በአእምሮው እየተመላለሰች ነው፡፡እሷን እንዳገኞት እስክያበስሯት ድረስ ተረጋግቶ ስራውን በስርአት መስራት እንደማይችል ገብቶታል፡፡ደህንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ ስልኩን አወጣና መልሶ ላንቲኒያ ወደሚገኙ የእሱ ሰዎች ደወለ ‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹ሁሉንም ሰው አስማሪቼለው..እስከአሁን አዲስ ነገር አላገኘንም፡፡››

‹የልጅቷ እቃዎች አሉ?››ሲል ያልጠበቀውን ጥያቄ ጠየቀው፡፡
‹‹የእጅ ቦርሰዋን ይዛ ነው  የሄደችው… የልብስ ሻንጣዋ ግን አሁንም ከእኛ ጋር ነው፡፡››
‹‹ውስጡ ምን አለ?››

‹‹እኔ እንጀ! እስከአሁን ከፍተን አላየነውም፡፡››

‹‹ክፈተው››

‹‹እሺ…››

ከተወሰነ ደቂቃ ዝምታና መተረማመስ በኃላ…‹‹ሻንጣው ተቆልፏል እንዴት ላድርግ?››የሚል ቃል ተሰማ፡፡
‹‹አንተ ጀዝባ …ስረህ አልመሆኔ በጀህ እንጂ በዚህ ጥያቄህ ግንባርህን ነበር የመነድልልህ…በጩቤ ዘንጥለህ ክፈተው››አንቦረቀበት፡፡
እንዳለው ከጎኑ የሻጠውን ጩቤ አወጣና የኑሀሚ ሻንጣ ከጉን በኩል ቦትርፎ ከፈተው፡፡ ውስጥ ያለውን እቃ እንዳለ ወለሉ ላይ ዘረገፈ…ቀሚሶች..ጅንስ ሱሪ…ፓንቶች…ጡት ማስያዣ… ማስተወሻ ደብተር……በቀ ይሄው ነው ያለው፡፡››
‹‹በቃ..››በብስጭት ጠየቀ
‹‹አዎ ..ቆይ…ሌላ አንድ አይፓድ አለ፡››

‹‹አዎ እንደእሱ አይነት እቃ ነው የምፈልገው…ክፈተው፡፡››

‹‹እ››ብሎ ለመክፈት ማከረ..ግን አልሆነለትም፡
‹‹አበራሁት …ግን ልከፍተው አልቻልኩም… ፓስ ወርድ አለው››

‹‹በቃ..በቃ አሁኑኑ..ተነስና ለሊቱንም ተጉዘህ ወደእኔ ይዘኸው ና…..ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ አይፓዱን ካላገኘው..በቃ ሟች ነህ››አለና ስልኩን ዘጋው፡፡
ታጣቂው ወዲያው ነበር ጊዜ ሳያባክን አይባዱን እና የቦተረፈውን ሻንጣ መልሶ ከፍቶ እቃዎችን ወደውስጥ በመመለስ ይዞ ከአካባቢ ገበሬ አንድ ፈረስ ተውሶ ዳግለስ ወደሚገኝበት ሳንቹዋሪ ሽምጥ መጋለብ የጀመረው፡፡
ዳግላስ ጥዋት በጠበቀው ሰዓት አይፓዱ ደረሰው፡፡ እዛው የእሱ ሰረተኛ በሆነ የኮምፒተር ባለሞያ ሀክ አስደርጎ ፓወርዱን ካሰበረ በኃላ ውስጡን ማየት ጀመረ፡፡
የፎቶ አይነት ..እርቃኗን የተናሳችውን ጭመር ..ቪዲዬዎች..፡፡አብዛኛዋቹ ፎቶዎቸና ቪዲዬዎቸ በእሷ አድሜ አካባቢ ካለ ወጣት ጋር አብራ ስትስቅ ..አልያም እላዩ ላይ ተንጠልጥላበት..አዝላው ወይም አዝሏት የተነሱት ወይም የተቀረፁት ነው፡፡ፍቅረኛዋ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ፡፡አይፓዱን ከኢተርኔት ጋር አገናኘና የተላኩላትን ብዙ መልእክቶች ተመለከተ፡፡ግን በማያውቀው ቋንቋ ስለሆነ መረዳት አልቻለም፡፡ወደጎግል ገበና የኢትዬጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ምን እንደሆነ ጠየቀ፡፡አማርኛ የሚል መልስ አገኘ፡፡አማርኛ የሚባል ቋንቋ መኖሩን እራሱ አያውቅም ነበር፡፡የሀገሬው ቋንቋ እንደሆነ ተረድቷል፡፡ በጣም ነው የተገረመው፡፡በደቡብ አሜሪካ ያሉትን ሀገሮች አሰበ…ፔሩ ፤ኮሎምብያ፤ አርጀንቲና ብሄራዊ ቋንቋቸው እስፓኒሽ ነው..ብራዚል በፖርቹጊዝ ቋንቋ ነው የምትገለገለው፤ኢጎና እንግሊዘኛ ነው ..እንደዛ እያለ ይቀጥላል፡፡ቢያስብ ቢያስብ አንድም ሀገር የራሱን ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋው አድርጎ የሚጠቀም ሊያስታውስ አልቻም፡፡ሀሳቡን ተወና ጎግል ትራንስሌት ከፍቶ መልእክቶቹን ኮፒ ፔስት እያደረገ ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ በመቀየር ለመረዳት ሞከረ፡፡በጣም ነው የተገረመው፡፡ያ ሁሉ መልእክት ከወንድሟ እንደነበረ..እና እሷ በመጥፋቷና አድረሻዋን ሊያገኝ እንዳልቻለ በመጨነቅ በተደጋገሚ ጊዜ የላከላት መልእክት ነው፡፡…ፍቅረኛዋ ነው ብሎ ያሰበው ወንድሟ መሆኑን ሲያውቅ ደስ አለው፡፡በዚህ መጠን የሚተሳሰቡና የሚወደዱ ወንድም እና እህት  መኖራቸውን  ተጠራጠረ…የእሱን  የራሱን  ወንድምና   እህቶች   አሰበና በመሀከላቸው ያለውን መግባባትና ፍቅር መዝኖ ፈገግ አለ፡፡በዘ ቅፅበት ያላሰበው ተንኳል በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡ይህቺ ሴት አምልጣ የመንግስት ተቋም ያለበት አካባቢ በህይወት መድረስ ብትችል እንኳን
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ምስራቅ ኮስተር ብላ ‹‹አትልፈስፈስ…ጠንከር ብለህ መሆን ስለሚገባው ነገር ብቻ እንነጋር፡፡››አለችው፡፡

ናኦልም‹‹ምን የሚሆን ነገር አለና እንነጋራለን…በዚህ ምድር ላይ አንድ አለቺኝ የምላት እህቴን እንዲህ ባለ ሁኔታ አጥቼያት እኔስ በህይወት መኖሬን ቀጥላለው?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹አይዞህ ኑሀሚ እንደዚህ ካሉ ብዙ አደጋዎች ሰርቫይቭ የማድረግ ልምድ ያላት ልጅ ነች፤ደግሞ በምድር ላይ ያለችህ እሷ ብቻ አይደለችም..እኔም እኮ ስላለሁ መሰለኝ አሁን በዚህ የሀዘንህ ወቅት አጠገብህ ያለሁት፡፡
‹‹እሱማ እውነትሽን ነው፡፡››
‹‹እኮ ..በል ተነስና መልስ እንመልስለት፡፡››
ከተዘረፈጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ‹‹ምን ብለን?››
‹‹ያልከኸውን አደርጋለው..ለማንም ሳልናገር ያልከው ሀገር ድረስ እመጣለሁ..ግን እህቴ በህይወት መኖሯን በምን አውቃለሁ?አንድ ማረጋገጫ ስጠኝ፡፡››
‹‹አዎ እንደዛ ብንለው ይሻላል አይደል…?ወይ ተጨማሪ ፎቶ ወይ ቪዲዬ ይልክልናል፡፡ወይ ደግሞ በስልክም ሊያገናኘን ይችላል፡፡››
‹‹በቃ ራስሽ ፃፊው››

እንደማሰብ አለችና ፃፈችና ላከች፡፡መልስ እስኪመጣ ለመጠበቅ ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ፡፡ለሁለቱም የሚጠጣ ቢራ አቀረበና እሱን እየጠጡ በትካዜ በስልኩ ከአሁን አሁን የሚላከውን ኢሜል መጠበቅ ቀጠለ፡፡
ከሶስት ሰዓት በኃላ ተጨማሪ ፎቶ ተላከላቸው፡፡እንሱ ያላወቁት እነዛ ፎቶዎች የተመረጡት ከኑሀሚ ስልክ ውስጥ በፔሩ ቆይታዋ በተያዩ ጊዜያቶች ከተነሳቸው ውስጥ የተመረጡትን ነው፡፡
ከፎቶ ጋር አጭር መልዕክት ተልዕኮል
‹‹ባቀረብንልህ ሀሳብ ከተስማማን አሁኑኑ አሳውቀን፡፡››ይላል፡፡

‹‹እ ምን አሰብሽ? ››አለት፡፡ ከምስራቅ የተሻለ ሀሳብ ለማግኘት እየተመኘ ጠየቃት.. ምርጫ የለንም ‹‹ተስማምቼያለሁ ብለህ ላክላቸው፡፡››እንዳለችው አደረገ፡፡
በል የጉዞ ሰነዶችህን አዘጋጅ…በሶስት ቀን ውስጥ አስፈላጊውን ገንዘብ ስለምንልክልህ ሙሉ ስምህን እና አስፈላጊ መረጃዎችን ላክልን፡፡እንደተነጋገርነው ግን ይሄንን ሚስጥር ሌላ ለሶስተኛ ወገን ለመንግስት አሳልፈህ ብትሰጥ ነገሮች ሁሉ ያከትምላቸዋል….ከዛ በኃላ
እህትህን በዚህ ምድር ላይ ዳግመኛ የማግኘት እድልህ ከዜሮ በታች ይሆናል…በል ፍጠን ይላል፡፡
‹‹አነበብሽው አይደል?››
‹‹አዎ ..አነበብኩት..››አለችና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
‹‹ምነው? ››
‹‹ልሄድ ነው፡፡››
‹‹ልሄድ ነው በእንደዚህ አይነት በተሰባበርኩበት ሁኔታ ላይ ሆኜ ጥለሺኝ ልትሄጂ ነው….፡፡››
‹‹ጎረምሳው ተረጋጋ እንጂ ..ይልቅ እራስህን ለረጅምና አስቸጋሪ ጉዞ አዘጋጅ፡፡እኔ ሄጄ ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ፖስፖርትና ቢዛዎችን ላዘጋጅ፡፡ ታውቃለህ እነዚህን የጉዞ ሰነዶች በአሁኑ ጊዜ በስድስት ወር ውስጥም ማግኘት አይቻልም፡፡አኔ ደግሞ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማግኘት

አለብኝ፡፡ ለዚህ ደግሞ ደቂቃዎችን ሳላባክን ከአሁን ያለኝን ኃይልና መስመር ሁሉ ተጠቅሜ ማሳካት መቻል አለብኝ…እ ምን ትላለህ ጎረምሳው?››
ተንደረደረ ሄደና ተጠመጠመባት፡፡እሷም እጆቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመቻቸው… ጭምቅ አደረጋት፡፡
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ሁሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ዘላለም በእቅፍሽ ውስጥ መኖር ነው ምኞቴ…በጣም ነው የምወድሽ….››አላት
‹‹….ተራጋጋ፡፡ከዚህ በላይ ከወራን እንባዬ ያመልጠኛል፡፡››አለችና ከእቅፉ ወጥታ ፈዞ በቆመበት ፊቷን አዙራ ወጥታ ሄደች፡፡በቦዘዙ አይኖቹ በስስት እያያት በሀሳቡ ሸኛት፡፡..
///

ከሶስት ቀን በኃላ በአለምአቀፍ የሀዋላ አስተላላፊዎች አማካይነት 50 ሺ ዶላር ተላከለት፡፡ያልጠበቀው ነገር ነበር፡፡ብሩ ሲደርሰው ነገሩ ሲሪዬስ እንደሆነ እሱ ብቻ ሳይሆን ምስራቅም ተገነዘበች፡፡ሁለቱም መመለስ ያቃቸው ይሄ ሁሉ አጋቾቹ ይሄን ሁሉ ኢንቨስትመንትና ጥረት የሚያደርጉት ከእሷ ምን ፈልገው ነው? የሚለውን ነው ፤የእሱንስ ወደፔሩ መሄድ ለምን ፈለጉት?››በተለይ ይሄን ጥያቄ ከአንደበቷ አውጥታ ለእሱ አትንገረው እንጂ ምስራቅንም በጣም ነው ያሳሰባት፡፡
ናኦል ገንዘቡ እንደደረሰው ካወቀ በኃላ እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም፡፡ሰዓቱ ገፍቶ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኖኛል በተኛበት አልጋ ላይ እየተገላበጠ በትዝታ ወደኃላ ወደልጅነታቸው ተጓዘ፡፡ምስራቅ እሱና ተወዳጅ እህቱን ከጎዳና አንስታ እንዴት ሰላይ እዳደረገቻቸው በዝርዝር ትዝ አለው፡፡
ከ15 አመት በፊት ምስራቅ የወንድሜ ቤት ነው ብላ ከጓዳና አንስታ ጎተራ የሚገኝ ኮንደምንዬም ቤት ከወሰደቻቸው በኃላ ከአዛው ቤት ሳይወጡ ሁለት ወር ሙሉ ቆይተው
ነበር፡፡ በሶስተኛው ወር ግን ማታ እራት በልተው ቴሌቬዥን እያዩ እያለ ድንገት ሪሞቱን አንስታ ቴሌቪዝኑን አጠፋችና ፊት ለፊታቸው ቁጭ አለች፡፡
እህትና ወንድም እርስበር ተያዩ ፡፡የሆነ ነገር ልትነግራቸው እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡፡ግን የጠረጠሩት በቃ እስካሬ ለሁለት ወር በምቾትና በድሎት በወንድሜ ቤት አኑሬያችኋለው፤ ከአሁን በኃላ ግን ምትኖሩበት ቦታ ፈልጉ ›› ትለናለች ብለው ነበር የጠበቁት፡፡ይሄንን ጉዳይ እሷ ቤት በማትኖርበት ጊዜ እያነሱ ተወያይተውበታል..ለዛ ነው በፍጥነት ወደሁለቱም ምናብ ሀሳቡ የመጣው፡፡
‹‹ልጆች በጣም እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ አይደል?››

‹‹አዎ እናውቃለን፡፡ እኛም በጣም እንወድሻለን››ሲል የመለሰላት ናኦል ነበር፤ኑሀሚ ግን ይሄንን ቤት ለቀው ከወጡ በኃላ ምን ማድረግ እንዳለበባቸው ስታሰላስል ነበር፡፡ደግማኛ ወንድሟን ይዛ ወደበረናዳ ለመመለስ ፈፅሞ ፍቃደኛ አልነበረችም፡፡ትንሽም ቢሆን የራሳቸው ቤት ተከራተው መኖር እንዳለባቸው ከወሰነች ሰነባብታ ነበር፡፡ለዛ ኪራይ ቤት ክፍያ ሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ደግሞ ማንኛውንም ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ነበረች፡፡ ለወንድሟ ስትል ብትሰርቅም ብትገድልም ግድ አልነበራትም፡፡
ምስራቅ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ይሄውላችሁ ምን መሳላችሁ…አንደእኔ እንደእኔ ዘላለም እዚሁ አንድ ላይ እንዲህ እየተሳሰብን በፍቅርና በደስታ መኖር ብንችል ደስ ይለኝ ነበር… ግን ያው ታውቃላችሁ አይደል?››
ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባች‹‹ማለት የምትፈልገውን ፍርታ ማለት ባለመቻሏ ሁለቱም ላይ ጭንቀት ፈጠረች…ኑሀሚ ፈጠን አለችና‹‹ይገባናል..እስከዛሬ ስለተንከባከብሽንና በዚህ ሁኔታ እንድናገግምና ስለወደፊታችን እንድናስብ ስላደረግሽን የላለም ባለውለታችን ነሽ፤ግን ወንድሜን ይዤ ወደበረንዳ መውጣት አልፈልግም…ከቻልሽ ለእኛ ምትሆን ትንሽ ቤት
ተከራይተን መኖር እንድንችል አግዢን፡፡ማንኛውንም ያገኘነው ስራ በመስራት የቤት ኪራዩን በመክፈል እራሳችንን ማኖር አያቅተንም…እቤት ካገኘን ነገ ተነገ ወዲያ እንሄዳለን..አንቺ አታስቢ››
ምስራቅ ፈገግ አለች‹‹እንዳዛ ማለቴ አይደለም፡፡እኔ እንደምታዩት እዚህ የምኖረው ብቻዬን ነው፡፡ ቤቱም ሰፊና ለሁላችንም የሚበቃ ነው፡፡እዚህ ከእኔ ጋር በመኖራችሁ በጣም ተጠቃሚው እናናተ ሳትሆኑ እኔ ነኝ….ግን ለእናንተ የወደፊት ህይወት ሲባል የተለየ መንገድ መከተል አለብን፡፡››
ሁለቱም  ስሜታቸው  ይበልጥ  ተናቃቃ፡፡የምትላቸው  በፍፅም እየገባቸው  አይደለም፡፡
‹‹አልገባንም›› አለች..ኑሀሚ፡፡
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከምስራቅ ካር ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ይገጥመናል ከሉት በላይ በጣም የተወሳሰበ ነገር ነበር የገጠማቸው፡፡በመጀመሪያ የት እንደተወሰዱ ያለማወቃቸው ነበር ከባድ ነገር፡፡ መስታወቱ ድፍን ጥቁር ሆኖ ወደውጭ በማያሳይ መኪና ውስጥ ተከተው…ለአንድ ሰዓት ለበለጠ ጊዜ ሲጓዙ ከቆ በኃላ መኪናዋ ቆመችና ሲወርዱ አምስት የሚሆኑ ባለአምስት ፎቅ ዘመናው ህንፃዎች ያሉበት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፤ የመረብ ኳስ እና የመሳሰሉት ሜዳዎች ያሉበት ዙሪያውን በደን የተሸፈነ እና ቢያንስ 3 ሜትር ሚሆን ከኮንክሪትና ከብሎኬት የተሰራ አጥር ….በአጥሩ ጫፍ ላይ አደገኛ ሽቦ የተጠመጠመበት በጣም አስፈሪ ድባብ የተላበሰ ግዙፍ ስፍራ ነው፡፡በዛ ላይ  .በተወሰነ ሜትር ርቀት በየሰዓቱ በሚቀያየሩ ቆፍጣና የጥበቃ ወታደሮች የሚታዩበት አስፈሪ ግቢ ውስጥ ነው ይዘዋቸው የገቡት፡፡
ይዞቸው ከመጡት መካከል አንድ ወደአንደኛው ፎቅ ይዟቸው ሄደና ወዳአንድ ቢሮ  አስገባቸውና  ምንነቱን ያለወቁት የሆነ ወረቀት አስፈርሞ በማስረከብ ቀሪውን ያዘና አነሱንም ልክ እንደወረቀቱ እዛው ጥሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዛ ከእነሱ ስለሚጠበቀው ነገር፤ ስለዋና ዋና የግቢው ህግ፤ማድረግ ስለሚገባቸው መድረግ ስለሌለባቸው ነገር የአንድ ሰዓት ገለፃ ከተሰጣቸው በኃላ ናኦል ወደ ወንዶች ህንፃ ኑሀሚም ወደ ሴቶች ህንጻ ተወሰድና ከሌላ ከአንድ ሰው ጋር የሚጋሩት የራሳቸው መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡በዚህ ሁኔታ አዲሱን ህይወታቸውን አህዱ ብለው ጀመሩ፡፡
ወደእዛ ግቢ ገብቶ በቃችሁ ውጡ ከመባሉ በፊት ለመውጣት መሞከር መጨረሻው ሞት ብቻ እንደሆነ ያወቁት ግቢውን በረገጡ በቀናቶች ውስጥ ነበር፡፡እንደተባለውም ስልጠናው የተለየ እና በእነሱ ዕድሜ ደረጃ ላለ ወጣት ይቅርና ለሙሉ ወጣትም የማይሞከር ነበር….ግን ስልጠናውን በቃኝ አልቻልኩም ማለት እራስን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ሌላ የሚያሰገኘው ነገር የለም፡፡ስለዚህ የማይቻለን መቻል የግዳቸው ነበር፡፡ወታደራዊ ስልጠናው ብቻ ሳይሆን መደበኛ ትምህርቱ እራሱ በጣም ጥብቅ በሆነ ስነምግባር የሚሰጥ ነበር፡፡አንድ ልጅ እዛ ግቢ ሲገባ ሶስተኛ ክፍልም ይሁን ስድስታኛ ክፍል የ5 አመቱን የሥልጠና ጊዜ ጨርሷ ከዛ ጊቢ ተመርቆ ሲወጣ የ12ተኛ ክፍል ማትሪክ ወስዶ መሆን አለበት ፡፡በዛ የተነሳ በአመት ሁለት ክፍሎችን መማር የግድ ይላል፡፡ደግነቱ የትምህርት አሰጣጡ እጅግ ዘመናዊና ሁሉ ነገር የተሞላለት አስተማሪዎቹ ልክ እንደእነሱ በልዩ ችሎታቸውና ብቃታቸው የተመረጡ ጂኒዬሶችና ነገሮችን በቀላሉ በማስረዳት ችሎታቸው የተመሰከረላቸውና ስለሆኑ ጫናዎቹ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይከብዳቸው ያግዛቸዋል፡፡በዛ ላይ እያንዳንዱ ሰልጣኝ እንደ ዝንባሌው በተለያዩ የስፖርት አይነቶቹ መሳተፍና የቋንቋ ስልጠናውም በተመሳሳይ ሁኔታ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡በተለይ ከውጭ ቋንቋ እንግሊዘኛና አረብኛ ሲማሩ ከሀገር ውስጥ እንደየ ምርጫቸው ከሚያውቁት በተጨማሪ ሁለት ቋንቋ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
ይሄ በሀገሪቱ የደህነነት መስሪያ ቤት በልዩ ፕሮጀክት እቅድ ተነድፎለት በጀት ተይዞለት እየተካሄደው ያለው ልዩ ስልጠና ለመጀመሪያው አንድ አመት ለሁሉም ተማሪዎች በጣም ከባድ አካልንም መንፈስንም በእኩል ደረጃ የሚያዝል ነበር፡፡ለዚህም ማሳያ በተቀመጠው ክራይቴሪያ ከተለያ ቦታ በተለያየ ዘዴ ተሰብስበው ከገቡ 80 ተማሪዎች መካከል በአመቱ መጨረሻ 17 ቱ መቋቋም አቅቶቸው ሞተው ነበረ፡፡ናኦልም እህቱ ከጎኑ ኖራ በየጊዜው ብርታት ባትሰጠው ኖሮ ከሞቾቹ መካከል መሰለፉ አይቀርም ነበር፡፡ለዚህ ነው መጀመሪያውኑ ሰልጣኞቹ ሲመለመሉ  አስፈላጊው ክራይቴሪያ ዘመድና ጠያቂ የሌላቸው እንዲሆኑ የሚፈለገው፡፡
ኑሀሚ ግን ከሶስት ወር በላይ አልተቸገረችም ነበር….ካዛ በኃላ በየዲሲፕሊኑ ከፉክከሩ መድረክ ከፊት የምትሰለፍ፤ ለሁሉም ሰልጣኞች ምሳሌና ብርታት ሆና ነበረ የቀጠለችው፡፡አመስት አመቱ አልቆ ሲመረቁ ከአንድ ወንድ ጋር በእኩል ነጥብ አንደኛ በመሆን የወርቅ ዋናጫውን ተቀበለች፡፡ወንድሟ ናኦል 53 ተኛ ወጥቶ ተመረቀ፡፡እና 5 አመት ከኖሩበት ከእዛ ማሳልጠኛ ውስጥ ልክ እንደአገባባቸው በጨለማ መኪና ውስጥ ተሳፍረው እንዲወጡ ተደረገ.፡፡ከሰዕታት ጉዞ በኃላ ግን ልክ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናዋ ቆማ ስታወርዳቸው የተቀበለቻቸው ምስራቅ ነበረች፡፡
በወቅቱ ሁለቱም ያለልዩነት ነበር የተጠመጠሙባት፡፡እሷም በደስታ እና በከፍተኛ እርካታ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡ስታያቸው ከበፊቱ በጣም አድገው ሙሉ ወጣት ሆነው ስላየቻቸው እጅግ ተደስታ ነበር፡፡ከዛ መኪና ውስጥ አስገባቻቸውና ቀጥታ ወደወላጆቻቸው ቤት ነበር የወሰደቻቸው፡፡ከመኪና ስትወርድ አብረዋት ወረዱ…ሰፈሩን ሲያዩና የቆሙበትን ሲረዳ ሁለቱም ደንዝዘው ነበር..ቀጥታ ሁለቱንም መሀከላቸው ገባችና ግራና ቀኝ እጃቸውን ይዛ ወደ ግቢው በራፍ ይዛቸው ሄደች…ሁለቱም በዝምታና በድንዛዜ ተከተሏት..ካዛ አንኳኩታ ሰውዬው ሲወጣ የሆነ ነገር ትለዋለች ብለው ሲጠብቁ..ኪሶ ገባችና ቁልፍ በማውጣት..‹‹ይሄው ቃል በገባሁት መሰረት የወላጆቻችሁ ቤት ቁልፍ ››ብላ ኑሀሚ እጅ ላይ አስቀመጠችላት፡፡ኑሀሚ አላመነችም፡፡ በድንዛዛ እጇን አንቀሳቀሰችና ቁልፉን ከፈተች.. አሸከረከረች… ተከፈተ.. ተንደርድራ ወደውስጥ ገባች፡፡ ወንድሟም ተከተላት፡፡ በረንዳው ላይ እስኪደርሱ አልቆሙም…የሳሎኑን በራፍ ስትገፋው ተዘግቷል፡፡ እጆ ላይ ባለው ቁልፍ ሞከረች ፤ተከፈተ……፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እነሱ ምንም ሳይለፉና ሳይጥሩ ነበር በምስራቅና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ጥረት የወላጆቻቸው ቤት የተረከቡት፡፡
ከዛ ሁለት ወር ሰይቆይ ኑሀሚ በስልጠናዋ ባስመዘገበችው ብቃት ምክንያት ለተጨማሪ የሶስት አመት ስልጠና ወደ ራሺያ ተላከች፡፡
ናኦል ደግሞ ቤተሰቦቹ ቤት እየኖረ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን እየተማረ በተደራቢነት ከምስራቅ  በሚሰጠው መመሪያና ተልዕኮ መሰረት የፊልድ ስረዎችን እንዲላመድ ተደረገ፡፡
ናኦል ከትዝታው ባኖ ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ሰዓት ሲያይ በጣም ነበር የተገረመው….ከለሊቱ10፡20 ሆኗል …ላለፉት አራት ሰዓት በላይ ባለፈ ታሪኩ ውስጥ ሰምጦ በትዝታ ሲዋልል ነበረ፡፡አካሉም ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ዝሏ ነበር ፡፡
/////
ኮሎምቢያ/አሞዞን ደን ውስጥ
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባነነ እና አይኖቹን ገለጠ፡፡በድቅድቁ ጨለማ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ግዙፍ ዛፍ ላይ ቆንጆና ወጣት ልጅ ደረቱ ላይ ተኝታ ነው ያገኘው…ያለበትን ሁኔታ አሰበና ፈገግ አለ፡፡ቀስ ብሎ ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ ሲያስነሳት ነበር ከገባችበት ጥልቅ ትዝታ የነቃችው፡፡
‹‹ወይ ሀሳቤን ጥዬ ተንፈላሰስኩብህ አይደል?››አለችው፡፡

‹‹አይ የተፈጥሮ ጥሪ አጨናንቆኝ ነው››

‹‹ማለት?››

‹‹ሽንቴን…ኩላሊቴ ልትፈነዳ ነው››

‹‹እ ..ነው..ወርደህ ልትሸና ነው?፡፡

‹‹አይ ምን አስወረደኝ..ብወርድ ሽንት ቤት የለ ..ሜዳ ላይ ነው የምሸናው፡፡ ማይደብርሽ ከሆነ እዚሁ ሆኜ ልለቀው ነው፡፡››
በጨለማ ውስጥ የማይታየውን ፈገግታዋን እየለገሰችው‹‹ምን ቸገረኝ..ልቀቀው.››አለችው

‹‹አመሰግናለው ››አለና ቆመ፡፡ ዚፕን መክፈት ሲጀመር.

‹‹እንዴ…››ብላ አጉረመረመች

‹‹ምነው?››
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ብራዚልና ኮሎምቢያ ድንበር/አማዞን ደን ውስጥ

‹‹ካርሎስ››

‹‹አቤት››

‹‹ሀገሬ ኢትዬጵያ አባ..ይን ጨምሮ የብዙ ወንዞች ባለቤት ነች..ማለት የፈለኩት ብዙ ወንዞችን አይቼ አውቃለው…እና አማዞን እጅግ ገራሚ ከሆኑ ጥቂጥ ተፈጥሮዎች መካከል አንዱ ሆኖ ነው ያገኘሁት››
‹‹ምኑ ነው ያስገረመሽ?››

‹‹አማዞን አንዴ ወንዝ ይመስላል….አንዴ ደግሞ ሀይቅ ይሆናል ፣አሁን ተሸገርኩት ብለህ ለሳዕታት ከተጓዝክ በኃላ መልሶ ፊትህ ይጋረጣል››
‹‹ጥሩ ታዝበሻል፡፡አማዞን እና ገባር ወንዞቹ በአጠቃላይ ከ25,000 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው የውስጥ የውሃ መስመሮች መገናኛ ዋና ደም ስር ነው።ይህ ወንዝ ከተለያዩ ሀይቆች ጋር በሚገናኙበት ጊዜ, የወንዙ ጥልቀት 100 ሜትር ይደርሳል፡፡በበጋ ወቅት አማዞን 11 ኪሎ ሜትር ስፋት ሲደርስ 110 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ቦታን ያካልላል፡፡ዝናብ ሲሆን ደግሞ ስፈቱና ጥልቀቱ በሶስት እጥፍ ይጨምራል፡፡ በዚህ ወቅት የወንዙ ውሃ እስከ 20 ሜትር ከፍ ብሎ ስፋቱ ደግሞ 350 ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር መሬት ይሸፍናል፡፡በአማዞን እና ገባር ወንዞቹ ውስጥ ወደ 3,000 የሚጠጉ የዓሣ ዝርያዎች አሉበት››
ስለአማዞን ጥልቅ የሆነ እውቀት እንዳለው አመነች፡፡ ርእሱን ቀይራ‹‹እንስሳቱ ግን አያሳዝኑም››ስትል ጠየቀችው

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹አንድ አንድን ሲበላ …ጠገብኩ እፎይ ብሎ አረፍ ሲል በሌላው ደግሞ ሲበላ…››

‹‹አዎ ሁሉም እንስሳት ሰውንም ጭምር… ሁለችንም ለመብላትም ለመበላትም ነው የተፈጠርነው…፡፡››
‹‹የሰው ልጅ ደግሞ ይበላል እንጂ ይበላል እንዴ?››

‹‹አዎ … ወይ ቀን ሲጥለው ወይ ደግሞ ቀነ ሲጥል ይበላል፡፡አሁን እኔና አንቺ እዚህ ደን ውስጥ ስንት ቀን ከአውሬ መበላት ተርፈናል…ቀን ቢጥለን መበላታችን ይቀር ነበር…ባለፈው ከጓደኞቼ አንዱ በአናኮንዳ ሲበላ አላየሽም?፡፡
‹‹ያ እኮ ተዲያ ከመቶ ሚሊዬን አንድ የሚያጋጥም ነው፡፡››

‹‹አዎ ..ይሄ የሆነው የሰው ልጅ የሚያስብ እንስሳት በመሆኑ እራሱን ከዚህ አደጋ ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንዳለበት እያሰበ እያሰበ መጣና እራሱን ከእንስሳ መኖሪያ እያራቀ መንደርና ከተማ እየሰራ ደህንነቱን ለማስጠበቅ ቻለ..እንደዛም ሆኖ ግን እድሜውን ማርዘም ቻለ እንጂ ሄዶ ሆዶ ከመበላት አይተርፍም….አሁን ስንቶቻችን ነን እርስ በርስ እየተባላላን ያለነው…?እኛ አሁን እዚህ ደን ውስጥ መከራችንን እያየን ያለነው ለምንድነው? በመሰል የሰው ልጆች ላለመበላት አይደል፡፡መበላት ሲባል የግድ ሰጋችንን ፈጭተው መዋጥ የለባቸውም …ከገደሉንና ከህይወት መስመር አንሸራተው ካስወጡን በሉን ማለት ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነህ፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነኝ፡፡ ግን ደግሞ ሁሉም እንስሳት እኩል የመብላትና መበላት እጣ አላቸው ማለት አይደለም፡፡የጫካው ህግ የምግብ ስርዓት ልክ እንደፒራሚድ ነው፡፡ከፒራሚዱ የስረኛው ወለል ያሉ መበላት የየእለት ጭንቀታቸውና እጣቸው ነው፡፡የፒራሚዲ ጫፍ ያሉት ደግሞ እነአንበሳ ነብር የመሳሰሉትና ማለቴ ነው..ማደን መያዝና መዘንጠል የየእለት ስራቸውና ተግባራቸው ነው፡፡››
‹‹ተመስገን እኛ የሰው ልጅ እንደዚህ አለመሆናችን፡፡››
ፈገግ ብሎ ሳቀባት፡፡
‹‹ምነው ትክክል አይደለሁም እንዴ?››

አይ እንደውም ይሄንን ፒራሚዱን የምግብ ስርዓት ከእንስሳቱ ኮርጆ የራሱን ማሻሻያ አድርጎበት በጥበብ ነው እየተገበረ ያለው፡፡የአለም 90 ፐርሰንት ሀብት በ10 ፐርሰንት በሚሆኑ ቱጃሮች እጅ ነው ያለው ..ያ ማለት በሰው ልጅ ኪንግደም ውስጥ 10 ፐርሰንቱ የፒራሚዱ ጫፍ ላይ ያሉት ናቸው፡፡እነሱ የ90 ፐርሰንቱን ላብና ወዝ በተለያ ሚስጥራዊና ዘዴ ቅርጥፍ አድርጎ ይሰለቅጡታል፡፡››
አይን አይኗን በስስት እያያት‹‹ስለአንቺ ሳስብ ምን እንደሚገርመኝ ታውቂያለሽ?››አላት

የተወሰነ ጉጉት በሚታይበት የስሜት መነቃቃት‹‹እስኪ ምንድነው ንገረኝ ልስማው ››ስትል መለሰችት
‹‹ያንቺ ነፍስ ያንቺ ብቻ እንዳልሆነች ነው እንድረዳ ያደረግሺኝ..የነፍስሽ ክፍያ የወንድምሽ ንበረት ነው የሚመስለው፡፡አደራ አንቺ ጋር አስቀምጪልኝ ብሎ እንደሰጠሸና ያንን አደራሻን ላለመብላት የመጨረሻውን ጥረት እየጣርሽ እንደሆነ ነው፡፡ያ ነው እንዲህ ብርቱና ጠንካራ እንድትሆኚ ያደረገሽ….››
‹‹ጥሩ ገልፀሀዋል..ግን ይሄ የእኔ ብቻ ችግር አይመስለኝም፡፡የሰው ልጅ ሁሉ ለቤተሰቡ ይብዛም ይነስ እንጂ ተመሳሳይ አይነት እይታ አለው፡፡ማንም ቢሆን ነፍሱ የእሱ ብቻ አይደለም…እሱ ሲያመው የሚያማቸው እሱ ሲደሰት ደስ የሚላቸው ቤተሰቦች ይኖሩታል፡፡ለእነሱ ሲል እራሱን ከአደጋ ይጠብቃል..ለእነሱ ሲል ጠንክሮ ይሰራል፡፡አዎ ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር ያለው ሰው ጠንካራ ስብዕና ይኖረዋል፡፡እነሱ በህይወት ጉዞ ትክክለኛውን መስመር መርቶ እንዲጓዝ ብርታትና ጥንካሬ ይሆኑታል፡፡.አብዛኛው ሰው የሚኖርላቸው የሚወዳቸውና የሚወዱት አምስት ወይም አስር ሰዎች ይሩታል፡፡እኔ የእኔ የምለው አንድ ወንድሜ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ያለኝን ፍቅር ጠቅላላ ተሰብስቦና ተከማችቶ አንድ ወንድሜ ላይ ስላረፈ ነው፡፡››
‹‹ገባኝ ..ጥሩ ገልፀሸዋል….ቀናሁበት››

‹‹ግድ የለህም አትቅና፡፡ ፍቅር ከመጠን ሲያልፍ ትንፋሽ ይነሳል…እንዲህ እንደምታስበው ጥሩ ጎን ብቻ አይደለም ያለው፡፡ወንድሜ የ10 ደቂቃ ታላቄ ወይም በሌላ አገላለፅ መንትያዬ ነው፡፡አንድ ማህፀን ውስጥ አንድ አይነት ሰዓት አንድ አይነት ምግብ እየተመገብን ነው የኖርነው…ከተወለድንም በኃላ እንደዛው… ቢሆንም በተለይ ወላጆቻችን ከሞቱ በኃላ ልክ እንደታናሽ ወንድሜ ነው የምቆጣጠረው፡፡የት ገባህ?የት ወጣህ….?በዚህ ግባ በዚህ ውጣ..አንዳንዴ ጭቅጭቄ ለእኔ ለራሴ ይሰለቸኛል..የሚገርመኝ እሱ ግን የእኔን ጭቅጭቅ የሚታገስበት የሚገርም ትእግስት አለው….ዝም ያልኩት ቀን እንደውም ምን ነካት ብሎ ይንቆራጠጣል….፡፡››


አዲስአበባ
///
ናኦል  ከምስራቅ  ጋር እንደተቃጠሩት  በማግስቱ ምሽት  1፡30 ነበር ቦሌ የደረሰው፡፡
‹‹ለሁለት 10 ጉዳይ ሲል ልደውልላት ወይስ ሁለት ሰዓት ይሙላ?›› እያለ ከራሱ ጋር ሲሞገት ከፊት ለፊት ሽክ ያለ አለባበስ ለብሳ በአስፈሪ ግርማ ሞገሶ አንድ መለስተኛ ዘመናዊ ሻንጣ በእጇ በመጎተት እያሽከረከረች ወደእሱ ስትቀርብ ተመለከተ፡፡ፊቱ ሁሉ አንፀባረቀ፡፡
‹‹እሺ..ቀድመህ ነው የደረስከው››አለችው፡፡
‹‹አዎ መቅደምም ነበረብኝ…ግን ሻንጣው ለምን አስፈለገ …?የሚያስፈልጉኝን ነገሮች እንደማልይዝ ጠርጥረሽ ነው አይደል? ዝም ብለሽ ነው የሰጋሽው፡፡››አለ፡፡እሱ ..ሻንጣውን ለእሱ ብላ የሚያስፈልጉትን እቃዎች ይዛበት የመጣች ነው የመሰለው፡፡
‹‹አይ ጎረምሳው ተሳስተሀል..ይሄ ሻንጣ የእኔ ነው፡፡››
‹‹የእኔ ነው ማለት?››
‹‹የእኔ ነዋ …እኔም ተጓዥ ነኝ፡፡ይልቅ ና እንግባ፡፡›› አለችና ከፊቱ ቀደመች፡፡

‹‹ወደየት ልትሄጂ ነው.?በአንድ ቀን ሁለታችንም ከአገር እንደምንወጣ አላወቅም ነበር፡፡››
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ብራዚል/ፔሩ
ናኦል እና ምስራቅ የወደቧ ውብ ከተማ ሪዬ ዲጄኔሮ እንደደረሱ ቀጥታ ታክሲ ይዘው ወደ ሆቴል ነው ያመሩት፡፡ለሁለትም እንዲህ አይነት ረጅም የአየር ላይ ጉዞ ሲጓዙ የመጀመሪያቸው ስለሆነ ድካሙ ከልክ ያለፈ ነበር..በተለይ ናኦል ከሀገር ውስጥ በረራዎች በስተቀር ድንበር ሲሻገር እራሱ የመጀመሪያው ገጠመኙ ሰለሆነ ጉዞ እንደህልም ነው የሆነበት ፡፡ሁለቱ ከአየር መንገድ ወጥተው ታክሲ ተሳፍረው ወደሆቴል እየሄዱ እያሉ ከሻንጣዋ የጎን ኪስ አንድ ወረቀት አወጣችና አቀበለችው፡፡
ተቀብሎ እያያት‹‹ምንድነው?፡፡››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አንብበው፡፡››
የተጣጠፈውን ወረቀት ገለጠና አየው..ከወረቀቱ ጫፍ በግራ በኩል የእሱ ፎቶ ተለጥፎበታል፡፡ በተመሳሳይ መስመር በቀኝ በኩል ደግሞ የራሷ የምስራቅ ፎቶ አለበት፡፡በመደነቅ እንደተሞላ ማንበብ ጀመረ‹‹ሁለቱ ባልና ሚስት እንደሆኑ የሚያወራና ያንንም የሚያረጋግጥ ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት ነው፡፡ባለማመን አይኑን ጨፈን ገለጥ ጨፈን ገለጥ በማድረግ ደጋግሞ አየው፡፡ትክክል ነው፡፡
‹‹ውይ እኔ እኮ በጣም እድለኛ ሰው ነኝ ..መቼ ነው ህልሜ እንዲህ ያሳከሁት?መቼ ነው በአለም ላይ እጅግ የማደንቃትንና የምወዳትን የህልሜን ሴት ያገባሁት….?እስኪ ንገሪኝ መቼ ነው ?››
‹‹ጎረምሳው አረጋጋው..ይሄ ኑሀሚን በመፈለግ ሂደት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ይሄንን ተልዕኮችን እስኪጠናቀቅ እኔና አንተ ባልና ሚስት ነን፡፡የተጋባንበትን ቀን በቃልህ ሸምድደው..ሁለት ወር ሆኖናል፡፡ገና ትኩስ ባለትዳሮች ነን፡፡እንኳ…ደግሞ ቀለበትን በትከክለኛ እጣትህ ላይ አጥልቀው›› አለችናን እጇ ላይ ካለው ሁለት ቀለበት መካከል አንድን አቀበለችው፤ ሁለተኛውን እራሷ ጣት ላይ አጠለቀች፡፡ተቀበላትና በሚፍለቀለቅ ፈገግታው ታጅቦ ቀለበቱን አጠለቀው፡፡
‹‹…ይሄው..አሁን ሁሉ ነገር ውብና ፍፅም ትክክል ሆኗል…ግን ይሄንን ሰርተፍኬት እኔ ጋር ቢሆን ምን ይመስልሻል?››
‹‹ግድ የለም ያዘው ..የረሴ ድርሻ አለኝ..››አለችው በፈገግታ፡፡
ከዛ ሆቴል ደርሰው በባልና ሚስት ተመዝግበው አንድ አልጋ ያለው መኝታ ክፍል ያዙ፡፡ከምስራቅ ጋር በጣም በርካታ ቀናቶች ተመሳሳይ ቤት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችና የተለያዩ አልጋዎች ላይ የመተኛት አጋጣሚ ቢኖራቸውም እንዲህ አንድ አልጋ ላይ የመተኛት እድል አጋጥሞት አያውቅም….አሁን ያ እድል እውን ሊሆንለት እንደሆነ ሲያስብ ልቡ በውስጡ መፈንጠዝ ጀመረች፡፡
///
በማግስቱ ከብራዚል ወደፔሩዋ ከተማ ሊማ ተጓዙና ምንም ሳያርፍ ቀጥታ ወደኢኩዬቶስ በረሩ…እንደደረሱ ለኡበሩ ሹፌር የተነገራቸውን ሆቴል ስም ነገሩና ወደዛው ወሰዳቸው፡፡ልክ ከኡበሩ የየራሳውን ሻንጣ ይዘው ወረዱና ወደሆቴል መጓዝ ሲጀምሩ‹‹እንግዲህ ከእስከአሁኑ በላይ በጣም ጠንቃቃ ሁኑ ..ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በእርግጠኝነት በእነሱ ሰዎች እይታ ስር ነው ያለነው…ሆቴሉ ውስጥም ሆነ የምንገባበት መኝታ ቤት ውስጥ ካሜራ እንደሚያስቀምጡ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው፡፡
‹‹ገባኝ..እጠነቀቃለሁ፡፡››
‹‹ሆቴል ብክ አደረጉና ፅዱ የሆነ ባለአንድ አልጋ መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡ገብተው ዕቃቸውን አመቻችተው እንዳስቀመጡ..‹‹የእኔ ፍቅር ትንሽ ሞቆኛል ሻወር ልወስድ ነው..አስከዛው ጋደም ብለህ ጠብቀኝ ..››አለችና እዛው እያያት ልብሷን በማወላለቅ እርቃኗን ሰውነቷ ላይ በቀረ ሰማያዊ ፓንት ብቻ ወደ ሻወር ቤት ሄደች፡፡እሱም በፍዘት ሲያያት ቆይቶ ሻወር ቤት ገብታ እስክትሰወርበት እየተመለከታት ነበር.፡፡ሌላ ቀን እዛ ሀገራቸው ምድር ላይ ሆኖ እንደዚህ ፊት ለፊቱ ልብሷን አወላልቃ እንዲህ እርቃኗን ቆማ አይቷት ቢሆን ኖሮ ወይ ተንደርድሮ ሄዶ ይጠመጠምባታል..ወይ ደግሞ እራሱን ስቶ መሬት ይዘረር ነበር፡፡አሁን ግን ከደቂቃዎች በፊት ያስጠነቀቀችውን እያሰበ እራሱን በትልቅ ጥረት ተቆጣጥሮ በትግስት ባለበት መርጋት ቻለ..፡፡
እሷ እየሰራች ያለውን ድራማ ይበልጥ ሊያደምቀው ወሰነና ልክ እሷ እንዳደረገችው ልብሱን አወላለቀ እና በፓንቱ ብቻ ወደሻወር ቤት ሄደና ገርበብ ያለውን በራፍ ገፋ በማድረግ ወደውስጥ ገባ ፡፡አልጠበቀችም ነበርና ስታየው ደነገጠች፡፡ሰውነቷን ስታሽበት የነበረው ሳሙና ከእጇ ተንሸራተተና ወደወለሉ ወደቀባት፡፡
‹‹የእኔ ፍቅር ላሽሽ እኮ ነው የመጣሁት…››አለና ሳሙናውን ጎንበስ ብሎ በማንሳት ሰውነቷን በአራፋው ያዳርስ ጀመር፡፡እሱ ብቻ ሳይሆን እሷም እጆቹ ሰውነቷ ላይ ሲሽከረከሩ ድንዝዝ እያለች ነው፡፡ልትቆጣጠረው የማትችል ስሜት በውስጧ ሲንተከተክና ልቧን ድክምክም ሲያደርጋት እየታወቃት ነው፡፡በዚህ ስሜት ተሸንፋ ዝልፍልፍ ብላ ክንዱ ላይ ከመውደቋ እና ባሳደገችው ልጅ ፊት ከመዋረዷ በፊት የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ተሰማት፡፡‹‹የእኔ ፍቅር አሁን ደግሞ ያንተ ተራ ነው..አምጣ ሳሙናውን ልሽህ፡፡››አለችና ከስሩ ሸሸት ብላ ሳሙናውን ከእጁ ተቀበለች፡፡የሻወሩን ውሀ ከፈተችና ሰውነቱን በውሀ እንዲያስመታ ዞር አለችለት፡፡ከፀጉሩ ጀምሮ ሳሙና አስመታና ‹‹በይ እሺኛ ››በማለት ደረቱን ዘርግቶ ወደእሷ ተጠጋ…
‹‹የእኔ ፍቅር ደረትህንማ አንተው በቀላሉ ማሸት ትችላለህ..ጅርባህን ዙርና እሱን ልሽህ››አለችው፡፡እንዳለችው በዝምታ ዞረ፡፡ ጀርባውን ከትከሻው ጀምሮ የፓንቱ ጠርዝ እስኪሚታይበት እስከመቀመጫው ድረስ አሸችውና..‹‹እንካ ጠጋ በልና ፊት ለፊትህን ሰሙና ምታው ..እስከዛ እኔ ልለቃለቅ›› ብላ ሳሙናውን አቀበለችውና የሻወሩን ቧንቧ በመክፈት ሰውነቷን ተለቃለቀች፡፡ድምፅ ሳታወጣ በምልክት ፊቱን ከእሷ እንዲያዞር አዘዘችው…ቅር እያለው ዞረ ፡፡ፓንቷን አወለቀችና መስቀያው ላይ አንጥልላ አንድ ፎጣ ከመስቀያው ላይ አንስታ በእጇ በመያዝ ባዶ መቀመጫዋን እያማታች ከሻወር ቤት ወጣች…እሱም ጥላው እንደወጣች ሲያውቅ ፈጠን አለና ሰውነቱን የሰተለቀለቀውን ሳሙና መለቃለቅ ጀመር…፡፡

ፎጣውን አገልድማ መውጣት እንዳለባት ታውቃለች.፡፡ግን ደግሞ እሷ እንደገመተችው እዚህ ድረስ ያስመጧቸው ሰዎች እዚህ ክፍል ውስጥ ካሜራ ካስቀመጡና እየተከታተሏቸው ከሆነ ከናኦል ጋር ባልና ሚስት እንደሆኑ ይበልጥ ማሳመን አለባት፡፡እርግጥ ለማንም ሰው በተለይ ለአንዲት ሴት በሆነ ቴክኖሎጂ ሰዎች ከርቀት ሆነው እየቀረፃት እንደሆነ እየተጠራጠረች , እርቃኗን በነፃነት የምታሳይ ሴት አትገኝም፡፡እሷ ግን ለዚህ የሰለጠነች ነች፡፡የሆነ የተሰማራችበትን ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ እስከጠቀመ ድረስ ማንኛውንም አይነት የተቀናጀ ተግባሮችን መፈፀም እንዳለባት ታውቃለችም ..ያንን ብዙ ጊዜ ተግባራዊ አድርጋ ውጤት አስመዝግባበታለች…አሁንም እያደረገችው ያለው ተመሳሳይ ነው…የትኛውም ወንድ እንዲህ የሴት እርቃን ገላ እየተመለከተ ጥርት ያለ ሀሳብ ሊያስብ አይችልም፡፡ስሌቷ እንደዛ ነው፡፡

ሰውነቷን በፎጣው አደራረቀቸና ሌላ ቅያሪ ፓንት ከቦርሳዋ አውጥታ እየለበሰች ሳለ ..እሱም ልክ እንደ እሷ በቅጡ ያልተላጨ የተሸፈነ እንትኑን እያማታ መጣ፡፡በቆሪጥ አይታው ወደሻንጣዋ አቀረቀረችና የምትለብሰውን ልብስ መምረጥ ጀመረች፡፡ተጠቅማ ጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠችውን ፎጣ እያነሳ…‹‹ማሬ ሰውነቴን በዚህ ላደራርቅ እንዴ?›› ሲል ጠየቃት..፡፡
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከተማው ውስጥ ሲዞዞሩና በከፊል የተጨነቀ በከፊል ደግሞ በከተማዋ ውበት ልብ የተሰረቀ ጥንድ ባልና ሚስቶችን ገፀ ባህሪ እየተጫወቱ አመሹ ፡፡ምሽት ላይ አዛው አልጋ የያዙበት ሆቴል መጠጥ እየቀማመሱና እየተጫወቱ ሰዓቱን ከገፉት በኃላ አራት ሰዓት አካባቢ ከተወሰነ ሞቅታ ጋር ወደ መኝታቸው ተመለሱ፡፡እንደገቡ እሷ የለበሰችውን ልብስ አውልቃ ስስ ቢጃማ ቀሚሶን ለበሰችና ተበትኖ የዋለውን ፀጉሯን አንድ ላይ አሲዛ በጨርቅ በማሰር አንሶላውን ገልጣ ከውስጥ ገባች..እሱም በተመሳሳይ የለበሰውን ልብስ አወላለቀና ወደሻንጣው ሄደ፡፡ ሀሳብ እሷ እንዳደረገችው ቢጃማ ፈልጎ ሊለብስ ነበር…ግን በህይወቱ ቢጃማ ለብሶ የመተኛት ልምድ ስለሌለው ቀጥታ ሰውነቱ ላይ በቀረው ፓንት ብቻ ወደአልጋው ሄደ፡፡ ብርድልብሱንና አንሶላውን ገለጠና ከስር ገባ …ወደእሱ ዞረች…ሰውነታቸው ሲነካካ የሁለቱም የሙቀት መጠን ወደላይ ተስፈነጠረ፡፡እሱ ክንዶቹን በአንገቷ ስር ሰቅስቆ አስገባና አቀፋት ..አንገቷን ከትራሱ ላይ ቀና አደረገችና ደረቱ ላይ ተኛች፡፡በአንገቷ ስር የተሻገረው እጁ ተመለሰና በከፊል የተጋለጠው ቀኝ ጡቷ ላይ አረፈ…፡፡ጭንቅላቷ ድረስ ነዘራት፡፡
አካሄዱ ስላላማራት በጥበብ አእምሮውን በመበታተን ልታስቆመው አሰበች..‹‹የእኔ ፍቅር ኑሀሚ እዚህ ከተማ ያለች ይመስልህል?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እዚህ ያለች ይመስለኛል››በእርግጠኝነት መለሰላት፡፡
‹‹ታዲያ ለምን ዛሬውኑ ሳያገናኙን?››
‹‹ያው ምንም ቢሆን እነሱ ባሉት መሰረት ብቻችንን እንደመጣን እስኪያረጋግጡ መሰለኝ››
‹‹እንዴ ምን ነካሽ? በእህታችን ነፍስ እንዴት ቁማር መጫወት እንችላለን…?የአካባቢው መንግስት አቅም ቢኖረው እኮ እስከአሁን ያገኛትና ወደሀገሯ ይመልሳት ነበር፡፡››
‹‹እሱስ እወነትህን ነው..ይሄንን ምናውቀው ግን እኛ ነን..እነሱ የሆነ ነገር ያደርጋሉ ብለው ቢጠረጥሩ ስህተት አልሰሩም፡፡››
‹‹ይሁን እንዳልሽ፡፡እርግጠኛ ነኝ ነገ ብቻችንን መሆናችንን በራሳቸው መንገድ ያረጋግጡና ከእህቴ ያገናኙኛል የሚል እምነት አለኝ››
‹‹አንተ ..››አለችና በድንጋጤ ከደረቱ ላይ ተነሳታ ንግግሯን አራዘመች‹‹ሚስቴ አብራኝ ትመጣለች ብልህ ነግረሀቸዋል እንዴ?››ያላሰበውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

እሷ ድራማውን በደንብ አድርጋ እየተጫወተችና እነሱ ጋር እንዲደርስላት የምትፈልገውን መልእክት እንዲናግር ሂሳቡን በመስራት ነበር ጥያቄዎችን የምታቀርብለት..እሱ ግን የእሷ ከእሱ ተከትሎ ፔሩ ድረስ መምጣት ከሰዎቹ ጋር ባደረገው በእስከአሁኑ ንግግራቸውም ሆነ ስምምነታቸው ላይ ስላልነበረ..ይሄ በራሱ እንቅፋት እንዳይሆንባቸው ስለፈራ ደነገጠ፡፡
‹‹አንቺ እስከአሁን ማሳወቅ ነበረብኝ…ምን አይነት የማረባ ሰው ነኝ››አለና ከተኛበት በመነሳት አልጋውን ለቆ ወረደ…
‹‹ወደየት ልትሄድ ነው?››

‹‹ነገ ሲመጡ አይተውሽ ሌላ አለመግባባት ውስጥ ከምንገባ አሁኑኑ በኢሜል ላሳውቃቸው፡፡››
ከተኛችበት ሆና ‹‹ጥሩ አስበሀል ማሬ… ፃፈላቸው፡፡››ስትል ፍቃድ ሰጠችው፡፡
እስከአሁን ሳልነግራችሁ የዘነጋሁት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ይቅርታ..ባለቤቴ ወደማላውቀው ሀገር ብቻዬን ልትልከኝ ፍቃደኛ ስላልሆነች አብራኝ ተከትላኝ መጥታለች..ቀድሜ ላሳውቃችሁ ብዬ ነው፡፡››
ብሎ ፃፈና ላከው፡፡እና ሞባይሉን ይዞ ወደአልጋው ተመልሶ በመሄድ ከውስጥ ገብቷ ተኛና ምስራቅን መልሶ አቀፎት ለላከው መልዕክት መልስ ይጠብቅ ጀመር፡፡ወዲያው የኢሜሉን መልእክት መልስ መጣለት፡፡
ቀድመህ ልታሳውቀን ይገባ ነበር…ደግመህ ከተስማማንበት ውጭ የሆነ አንዲት ቅንጣት ነገር ብታደርግ እህትህን ማግኘቱን እርሳው፡፡ለጊዜው የሚስትህን መምጣት ተቀብለነዋል፡፡ግን ደግሞ ለአንተ የነገርናቸውን ማስጠንቀቂያዎች እሷም እንድታከብር የማድረግ ኃላፊነቱ ያንተው ነው፡፡
ይላል ፡፡ምስራቅንም አስነበባትና ስልኩን አስቀምጦ መብራቱን አጠፋና አቅፎት ተኛ… ወደጆሮዋ ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ‹‹ደህና እደሪ››አላት
‹‹እንቅልፍህ መጣ እንዴ?››
‹‹አይ አልመጣም..የሚመጣም አይመስለኝም..እኚ ሰዎች እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ያመኑን አይመስለኝም፣ማለቴ ባልና ሚስት መሆናችንን›› አለችው፡፡
ጆሮዋ ላይ ተለጥፎ‹‹አረ ያምኑናል…እንዲህ እየሆን እንዴት ላያምኑን ይችላሉ? ››
‹‹ባልና ሚስቶች እንዲህ ብቻ አይደለም የሚሆኑት፡፡ይህንን አታውቅም እንዴ? ››
ምን ለማለት እደፈለገች ቢገባውም ያልገባው ለመምሰል ሞከረ ‹‹እንደምታውቂው ከዚህ በፊት አግብቼ አላውቅም… እንዴት ላውቅ እችላለሁ?››
‹‹ለማወቅ እኮ ማግባት አይጠበቅብህም››አለችው በሹክሹክታ
‹‹ታዲያ ምን ይሻለናል እያልሽ ነው?››
‹‹ኑሀሚን አደጋ ላይ የሚጥል ምንም አይነት ስህተት መስራት የለብንም፡፡ አሁን እንተሻሻለን››
..ቀስ ብዬ ልብሴን አወልቅና ወደወለሉ ወረውራለው፡፡ አንትም ፓንትህን ታወልቃለህ ….እኔ ጭን መካከል ትገባለህ..ልክ ወሲብ እንደሚያረግን ባልና ሚስት በንቅናቄና በድምፅ ማስመሰል እንቀጥላለን..ግን በምንም አይነት ሁኔታ እትንህን ጭኔ ውስጥ የእውነት ለመክተት እንዳትሞክር››
‹‹ተንሸራቶ ከገባብኝስ?››
‹‹ወደሀገራችን ስንመለስ ግንባርህን በሽጉጥ አፈርሰውና ባርቆብኝ ነው ብዬ ቃል እሰጣለሁ፡፡››
‹‹ተስማምቼለሁ›› አለና ሙሉ በሙሉ ወደእሷ በመዞር ከሰውነቱ አጣብቆ ያሻት ጀመረ..እሷም ቀስ በቀስ እያደገ እና እየጨመረ በሚሄድ በተቆራረጠ ድምፅ በማጀብ እጆቾን በእርቃን ሰውነቱ ላይ ታመላለስ ጀመር…ድምፃቸው ምን አልባት እየቀረፃቸው ያለው መቅራጫ በጭለማ ምስል ማስቀረት ባይችል እንኳን ወሲብ ላይ መሆናቸውን የሚያበስረውን ድምጽ በትክክል ማስቀረት ስላለበት በደንብ ነበር የተወኑት ፡፡ከ10 ደቂቃ መተሻሸት በኃላ እሷ ቀድማ ከእቅፉ ወጣችና የለበሰችውን ቢጃማ ሆነ ፓንት አወቀለቀችና ወለል ላይ ወረወችው..እሱም ፓንቱን አወለቀና ተመሳሳዩን አደረገ ..ሙሉ በሙሉ እርቃናችውን እርስ በርስ ተጣበቁ ..እሱ ግን የተሰጠውን ትዕዛዝ ማክበር አልቻለም፡፡ከ5 ደቂቃ መፋተግ በኃላ የእሷም ብልት በፈሳሽ መረጣጠቡን ተከትሎ ሙከራው ከሸፈበትና ብልቱ አዳልጦት ከማንነቷ ጋር ሙሉ በሙሉ ተዋሀዳት..ሁለቱም የሆነውን ያወቁት የመጨራሻ ጡዘት ላይ ደርሰው በእርካታ ወደ ስሜታቸው ስክነት ከተመለሱ በኃላ ነው፡፡ምንም አላላች፡፡ከተወሰነ ደቂቃዎች እረፍት በኃላ ሰውነቷ ላይ የነበረውን ብርድልብስ ገፋ አስወገደችና ከአልጋው ወርዳ ወደግድግዳው በመሄድ መብራቱን አበራችው..ይሄንን ሆነ ብላ ነው ያደረገችው..ናኦል ዝርግትግት ብሎ እርቃኑን አልጋው ላይ ተኝቷል ..ቀጥታ ወደሻወር ቤት ሄደች፡፡
ሻወር ቤት ገባችና ውሀውን ከፈተች፡፡ መሀከል አናቷን ማስመታት ጀመረች…አሁን ያደረገችው ነገር ምን እንደሚያመጣባት ምንም እርግጠኛ መሆን አልቻለችም…እሷ በህይወቷ ከመቶ በላይ የማትፈልጋቸውን ወሲባዊ ተራክቦ ከብዙ የማትፈልጋቸው ሰዎች ጋር አድርጋ ታውቃለች፡›ቀድሞውንም አእምሮዋን አሳምና ስለምትከውነው ምንም አይነት የመንፈስ ቁስለት ሆነ ፀፀት አስከትሎባት አያውቅም ነበር፡፡ይሄ የአሁኑ ግን ከአነዛ በጣም የተለየ ነው፡፡ በመጀመሪያ ይሄን ልጅ ገና ከ12 ዓመቱ ጀምሮ ታውቃዋለች፡፡ እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ለውጡን እድገቱን በቅርበት ስትከታተል ነው የኖረችው…ልክ እንደታላቅ እህቱ ስትንከባከበው እና ስትጠብቀው ነው
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ብራዚል/አማዞን ወንዝ አቅራቢያ

ኑሀሚ በሶስተኛው ቀን የሽሽት ጉዞ በህይወትና በሞት መካከል ሆና የመጨረሻዋን ትንፋሿን ለመሳብ ከፍተኛ ጥረት የምታደርግበት ሁኔታ ላይ ወደቀች፡፡ይሄ የሆነው ድንገት ነው፡፡በብራዚል አማዞኑያ ክልል እየጠለቁ ገብተው የአማዞን ደን እየተሸለከለኩ ሰው ያለበት ቦታ ለመድረስ ጥረት ላይ እያሉ ድንገት የሚያምር ቀይና ውብ አበባ አይታ እሱን ለመቀንጠስ እጇን ስትዘረጋ አበባውን ከያዘው የግንድ ቅርንጫፍ ተለጥፎ ያለ እሾክ ነገር ጠቅ አደረጋት፡፡ትንሽ ነው የደም ጠብታ የታየው፡፡ግን ልብላቤው የተለየ የንብ መነደፍ አይነት ነበር፡፡ግን ደግሞ ብዙም ልታካብድ ስላልፈለገች ለጓደኛዋ እንኳን አልነገረችውም ነበር፡፡ከ10 ደቂቃ በኃላ ግን እግሯ መደናቀፍ ስውነቷ መዛል እና በሙቀት መንደድ ጀመረ…ከዛ በግንባሯ ላብ መንቆርቆር ጀመር…
ካርሎስ ድንገት ወደኃላ እየቀረች ስታስቸግረው ዞር ብሎ ሲያያት በጣም ነው የደነገጠው፡፡

‹‹እንዴ ምን ሆነሻል?››

ለመተንፈስ እንኳን እየተቸገረች..‹‹እኔ እንጃ አራሴን ማንቀሳቀስ እያቃተኝ ነው›››

‹‹ታዲያ አትነግሪኝም እንዴ?››አለና ወደእሷ በመጠጋት ደግፎ ለማረፍ ምቹ ወደሆነ ቦታ ወሰዳት እና ምቹ ቅጠል ጎዝጉዞ አስቀመጣት፡፡
ግንባሯን በእጆቸ እየደበሰ ሙቀቷን መለካት ጀመረ…. ‹‹የወባ መከላከያ አልወሰድሽም እንዴ?››
‹‹አረ ወስ..ጄ..ለሁ››በተቆራረጠ ትንፋሽ መለሰችለት፡፡

ግራ ገባው…‹‹.እስቲ ግንዱን ደገፍ በይ…››አላት፡፡
ደገፍ እንድትል ሲረዳት የቀኝ እጇን የመሀል እጣት ተመለከተ ….ለብቻው ተነርቶ አብጧል፡፡‹‹እንዴ እጣትሽን ምን ሆነሽ ነው?››
እይኗን ወደእጣቷ ወረወረችና አየችው…ደነገጠች‹‹ወይኔ ከደቂቃዎች በፊት እሾክ ወግቶኝ ነበር፤ቀላል አድርጌ ነበር የወሰድኩት፡፡››
አስከአሁን ከደነገጠው በላይ ደነገጠ፡፡ትከሻው ላይ ያለውን ጠመንጃ አወረደና አቀባብሎ ስሯ አስቀምጦ በእጇ አስያዛትና ‹‹የሆነ ነገር ካየሽ ተኩሺ… ስለምሰማ በአስቸኮይ እመጣለሁ…መድሀኒት መፈለግ አለብኝ …. ከዚህ እንዳትንቀሻቀሺ ››አለና፡፡ ጓዙን ጠቅላላ ከጎኗ አስቀምጦ ሽጉጡንና እና ጩቤውን ይዞ ሄደ….ከ15 ደቂቃ አታካች እና አድካሚ ፍለጋ በኃላ ነው የሚፈልገውን ቅጠል ያገኘው፡፡በጥንቃቄ ቆረጠውና ተመልሶ ሲመጣ እሷ ሙሉ በሙሉ እራሷን ስታ ተዘርራ ነበር፡፡
ቶሎ አለና ትንፋሿን አዳመጠ፤በትንሹ ቲር ቲር እያለች በውስጦ ትንፈራገጣለች፡፡ እጇን አነሳና ጉልበቱ ላይ አስተካከሎ አስቀመጣት፡፡ወገቡ ላይ የሻጠውን ጩቤ ከጎኑ አወጣና የተመረዘውን የመሀል እጣቷን ሸረከተው፤ጥቁር ደም ከውስጡ መንፎልፎል ጀመረ፡፡ይበቃል በሚለው መጠን ካፈሰሰ በኃላ የጨቀጨቀውን ቅጠል እየጨመቀ ፈሳሹን ወደውስጥ ያንጠባጥብ ጀመረ፡፡ከዛ ሙሉ የእጇን መዳፍ ውጩንም ውስጥንም በቅጠሉ ጠቀለለውና ከስር የለበሰውን ካኔቴራ አውልቆ በመቀዳደድ ልክ እንደፋሻ ጠቀለለውና በቀስታ አስተካክሎ ሰውነቷ ላይ አስቀመጠው፡፡ እሷን ፎጣ ነገር አልብሶት ወደቦታዋ መልሶ አስተኛትና ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ…በጣም ተጨንቋል፡፡ይህቺን ልጅ በዚህ ደን ውስጥ ካጣት ከዛ በኃላ ያለው ህይወት እንዴት ሊቀጥል እንደሚችልም ምንም አያውቅም…ከሳምንት በፊት ያወቃት ሳይሆን እድሜ ልክ በልቡም በነፍስም የነበረች ሴት እንደሆነች ነው እያሰበ ያለው፡፡አሁን እጁ ላይ ከሞተችበት ልቡም ሆነች ነፍሱ ከዚህ በፊት ቦዳ ከሆነችው በላይ በጥልቀት ባዶ ትሆናለች፡፡ለመኖር ወኔም ፍላጎትም አይኖረውም፡፡በዚህ እርግጠኛ ስለሆነ ውስጡን በረደው፡፡
ስለእሷ እያሰበ የእሷን መንቃት እየተጠባበቀ ሳለ የሆነ ጆሮው ላይ ሿሿሿ የሚል ድምጽ ሰማ…ይሄ ድምፅ የወንዝ መስገምገም ድምፅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ጆሮውን በደንብ ቀስሮና ስሜቱን ሰብስቦ እርግጠኛ ለመሆን አዳመጠ፤ትክክል ነው….ተነሳ ቆመ፡፡ የእሷን ቦርሳም ሆነ እሱ ይዞ የነበረውን ሻንጣ ውስጥ ከተተ፡፡ ሽጉጡንም ከተተና በተከሻው አዘለው…ከዛ ጎንበስ አለና እሷን ልክ እንደተወዳጅ ልጁ በጥንቃቄ ከስር ሰቅስቆ ያዛትና አቅፎ ወደላይ አነሳት፡፡የገመተውን ያህል አልከበደችውም….‹‹ድሮስ በፍቅር የተሸከሙት ሸክም የክብደቱን ያህል መች ይፈተናል?››አለና በውስጡ አሰበ ፡፡እሷን ተሸክሞ ከሀረጋ ሀረጎች እና ከጥሻዎች ጋር  እየታገለ  ለ15  ደቂቃ  ወንዙ  ሿሿሿታ  ወደሚሰማበት  አቅጣጫ  ይዞት  ተጎዛ፡፡ የሚንፎለፎለው ወንዝ የአይኖቹ እይታ ውስጥ ሲገብ ውስጡ በእርካታ ሀሴት አደረጋች፡፡ወደወንዙ ዳርቻ ተጠጋና ምቹ ያለውን ቦታ መርጦ ቀስ ብሎ ተንበረከከና አስቀመጣት ››ወዲያው ደህና ደህና ችካል መሰል እንጨቶችን መርጦ ጉድጎድ በመቆፈር አስተካክሎ ተከላቸው፡፡በአግዳሚ ማገር አራቱንም ኮርነር አገናኛና አርብራብ ሰራላቸው…እዛ እርብራብ ላይ ምቹና ለስላሳ ቅጠል ለምልሞ ጎዘጎዘበት፡፡በመቀጠል ረጃጅም ቋሚዎቹን ቆራረጠና አራት ቦታ ተክሎ ልክ እንደጎጆ ቤት ከላይ ጫፋቸውን አንድ ላይ ሰበሰባና በሀረግ አሰራቸው፡፡ከዛ እንደክብ ዙሪያውን እያሽከረከረ አሰረና አጠናካረው.፡፡ከዛ ኮባ መሳይ ሰፊ ቅጠሎችን በመመልመል አለበሰውና በግማሽ ቀን ውስጥ የሚያምር ጊዜያው ጎጆ ሰራ፡፡ከዛ ኑሀሚን ከመሬት ላይ አንስቶ በጥንቃቄ ወደጎጆው አስገባትና ያዘጋጀላት ርብራብ ላይ አስተኛት፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ኑሀሚ ከገባችበት ሰመመን አልነቃችም..ጥሩ ነገር ግን ሙቀቷ በመጠኑ ቀንሶ  አተነፋፋሶም እየተስተካከለ መጥቶ የሰላም እንቅልፍ የተኛች መስላለች፡፡ስለዚህ ሰውነቷ ለመድሀኒቱ ለመልስ እየሰጠና በሰውነቷ የገባው መርዝ እየተዳከመ እና እየተወገደ እንደሆነ ስላመነ ተረጋግቷል፡፡
ልብሱን አወላልቆ ወደወንዙ ውስጥ ገባና እየዋኘ በዛውም አራት የሚሆኑ አሳዎችን አሰገረና ከወንዙ ወጥቶ ልብሱን በመለባበስ ወደሰራት ጎጆ ተመልሶ እንጨት እርስ በርስ በማፋተግ እሳት አቀጣጥሎ ዓሳውን መጥበስ ጀመረ፡፡ልክ የመጀመሪያውን ዓሳ አብስሎ ጨርሶ ሁለተኛውን እያዘጋጀ ሳለ ኑሀሚ አይኖቾን ገለጠች፡፡ብዣ እንዳለባት ነው፡፡ሞት ጫፍ ላይ ደርሶ መመለስ አይነት ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ዙሪያውን ስትቃኝ ጥቅጥቅ የአማዞን ድን ሳይሆን አዲስ የተሰራ የገጠር ጎጆ ቤት ነው የሚታያት፡፡አይኖቾን ስታሽከከረክር በጎጆዋ በራፍ አሻግራ ስታይ ሰማያዊ የጠራ መልክ ያለው ወራጅ ወንዝ ይታያታል..ከወንዙ ማዶ ግን መልሶ በግዙፍ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተዋቀረ ጥቅጥቅ ደን ነው የምታያት…እይታዋን ወዳለችበት ስታጠብ ጭስ ነገር አየች…ቀስቀስ ስትል ድምፅ ስለሰማ የያዘውን ነገር ጣጣለና ተፈናጥሮ ተነስቶ ስሯ ቆመ….‹‹ነቃሽ…?እንዴት ነሽ ..?አሁን ምን ይሰማሻል?››በጥያቄ አጣደፋት፡፡
‹‹በጣም ደህና ነኝ..ፍፁም ሰላም ነው እየተሰማኝ ያለው…እንዴት እዚህ መጣን …?የሆነ ዛፍ ስራ አልነበርኩ..?ወንዙ ከየት መጣ?፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ…በአካባቢው ወንዝ እንዳለ ሳውቅ ወደእዚህ ይዤሽ መጣሁና ይህቺን ጎጆ ሰራሁ..አሁን ቆንጆ የዓሳ ጥብስ ሰራቼለው፡፡እሱን ስትበይ ደግሞ ጠንካራ ትሆኚያለሽ››
‹‹ይዤሽ መጣሁ ስትል..እንዴት አድርገህ…?መቼስ በእግሬ መንቀሳቀስ አልችልም ነበር..አይደል እንዴ?››
‹‹ያው አቀፍኩሽና አመጣሁሽ..እሩቅ እኮ አይደለም..አንድ ሶስት ኪሎ ሜትር ቢርቅ ነው፡፡››
ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ልጅም ቶሎ ያንጠለጠለውን የእጅ ቦርሳ ጠረጴዛ ላይ አደረገና ከብር የተሠራ የሚመስል ሁለት የእጅ ብራስሌት መጀመሪያ ምስራቅ እጅ ላይ ቀጥሎ ናኦል እጅ ላይ አጠለቀና ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ በማብራት ሲነካካ እጃቸው ላይ ያጠለቀላቸው ብራስሌት ቀለሙን ከብራማነት ወደ ደማቅ ሰማያዊነት ቀየረ።ዝም ብሎ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ዳግላስ መናገር ጀመረ
"አሁን እንግደህ እህታችሁን እኔ ሳልሆን ለእናንተ ማመጣላችሁ ..እናንተ ናችሁ ለእኔ የምታመጡልኝ..." ብሎ ኑሀሚ የእሱን ሰው ገድላ ከሌላ ከእሱ ሰው ጋር እንደኮበለለች...እስከአሁንም በመላው አማዞን ደን ውስጥ ቢያስፈልጋት ሊያገኛት እንዳልቻለ...እሷን መሞቷን ካላረጋገጠ ወይም በህይወት እጅ ካላስገባት የሰላም እንቅልፍ እንደማይወስደው..ወንድሟን ያስመጣበት ምክንያት ተሳክቶላት እንኳን ማምለጥ ብትችል ለወንድሟ ደህንነት ስትል በፍቃዷ መልሳ እጅ እንድትሰጥ አቅዶ ያደረገው እንደሆነ አብራርቶ ከአሁን ሰዓት በኃላ እዛው እሱ የሚኖርበት ወለል ላይ የራሳቸው ክፍል እንደሚሰጣቸው እና እጃቸው ላይ በተጠለቀላቸው አንባር ሙሉ የ24 ሰዓት ክትትል እንደሚደረግላቸው ነገራቸው። እሷ መጥታ በፍቃዷ እጇን እስክትሰጥ ወይንም መሞቷ እስኪረጋገጥ ድረስ ከክፍላቸው መውጣት እንደማይችሉ...ፀባያቸውን እስካሳመሩና ችግር ለመፍጠር እስካልሞከሩ ድረስ የሚፈልጉት ነገር እንደሚያሟላላቸው አብራርቶላቸው.. ወደክፍላቸው እንዲወስዳቸው አዘዘ...።የታዘዘውም ታጣቂ እየጎተ ወሰዶ አንድ ለቀቅ ያለ ሻወርና ማንበቢያ ክፍል ያለው ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ አስገብቶ ከውጭ ዘጋባቸው..
እቤት ውስጥ ከገብ በኃላ እንኳን ናኦል እና ምስራቅ  ለረጅም ደቂቃ ደንዝዘውና ፈዘው ማህል ወለል ላይ በዝምታ ተገትረው ነበር።

ናኦል እንባ እየተናነቀው"ምስራቅ ምን ውስጥ ነው የገባነው..?ይሄ ሰውዬ ተጫወተብን"አላት ።
ምስራቅም ወደእሱ ተንደረደረችና  አቀፈችው ።አንገቱ ስር ሽጉጥ ብላ በጆሮው "አትደንግጥ...እቅድ አለኝ"አለችው።

ዝም አለ...ከዚህ ለመውጣት ምን አይነት ተአምራዊ ዕቅድ ሊኖራት እንደሚችል ምንም ሊገለፅለት አልቻለም።ቢሆንም ከሞስራቅ ጋር ባሳለፋቸው በርካታ አመታት ብዙ ተአምር መሳይ ነገሮችን ስትከውንና ደጋግሞም ሲሳካላት ታዝቦልና የተናገረችው ነገር ንቆ ሊያልፈው አልደፈረም።...
ብራዚል/አማዞን ደን ውስጥ
አካባቢው ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡ጨረቃዋም በሰማይ ላይ ብርሀን አልፈነጠቀችም፡፡ከዋክብቱም የከሰሙ መስለዋል ፡፡ኑሀሚ ካርሎስ የሰራላት የአንጨት ርብራብ አልጋ ላይ ተኝታ የእጇ ጥዝጣዜ ታዳምጣለች፡፡እርግጥ ከትናንቱ የተሻ ጤንነት ላይ ብትገኝም ሰውነቷ ግን ሙሉ በሙሉ እደዛለ ነው፡፡በህይወቷ በእንዲህ አይነት ደካማንትና አቅመ ቢስነት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ ካርሎስ በሶስት ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ እደምታገግም ነግሯት ነበር ፡፡ አሁን አሁን ያለችበት ሁኔታ ስታስበው በሶስት ወር ተሽሏት ከዚህ አካባቢ የምትንቀሳቀስ እየመሰላት አይደለም፡፡ያም ሆኖ ግን ትናንትና ጉሮሮዋን ፈጥርቆ ነፍሷን ሊነጥቃት የነበረው ሲኦላዊ ህመም ዛሬ በሙሉ አቅሙ የለም፡፡ያ የሆነው ደግሞ ካርሎስ እጇ ላይ ባሰረለት የባህል መድሀኒት ምክንያት ነው፡፡
እንደምንም አንገቷን ወደ ዳር ሸርተት አድርጋ አየችው፡፡ እዛው ርብራብ አልጋ ጎን ባለ ጠፍጣፍ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ አንገቱን በካኔቴራው ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ የእንጨት አልጋውን ቋሚ ተደግፎ ጨልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ አሳዘናት፡፡ቢቻላት ኩርምት ብሎ በተቀመጠበት እንቅልፍ የወሰደውን ይሄን መልካም ሰው ጎትታ ወደራሷ ስባ እሷ የተኛችበት የእንጨት ርብራብ ላይ ከጎኗ ሽጉጥ አድርጋው ብትተኛ ደስ ይላት ነበር ፡፡
ወዲያው ሀሳቧን ሳትጨርስ ነጎድጓድ በሰማዩ አንፀባራቂ ብርሀን እየረጨ ያንቧርቅ ጀመር፡፡የሚያስፈራ ደራጎናዊ ድምፅ አካባቢውን ያናጋው ጀመር፡፡ ኑሀሚ እንኳን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ቦታ ሆና ይቅርና በሀገሯ ሰማይ ስር በገዛ ቤቷ እያለች ሳይቀር እንዲህ አይነት ነጎድጎድ በጣም ነው የሚያስፈራት፡፡፡እንደምንም ደካማ እጃን አንቀሳቀሰችና ትከሻው ላይ አኑራ በመወዝወዝ..‹‹ካርሎስ ካርሎስ›› ስትል ጠራችው፡፡

በርግጎ ተነሳ‹‹..ምን …አመመሽ እንዴ?››
‹‹አይ ነጎድጎድ ፈራለሁ››
ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተንቀሳቀሰ….ርብራቡ ጠርዝ ላይ ከጎኗ ተቀመጠና እጆቿን በእጆቹ ውስጥ አስገብቶ ያሻሽላት ጀመር፡፡ከእሱ ሰውነት ወደእሷ እየተላለፈ ያለው ሙቀት ብቻ ሳይሆን ብርታትና ጥንካሬ ጭምር ነው፡፡
በድጋሚ‹‹በጣም እኮ ነው የፈረሁት››አለችው፡፡
‹‹አይዞሽ…ስጋታችን፤ፍረሀቶችንና እና ጥርጣሬዎቻችን ሰው በመሆናችን የተሰጡን ፀጋዎች ናቸው፡፡ካለበለዚያማ እህያና በቅሎ መሰል አይነት ስሜቶች ስለሌላቸው ከእኛ የተሻሉ እደለኞች ናቸው ልንል መሆኑ ነው?፡፡››
‹‹እሱስ እውትህን ነው››አለችና ይበልጥ ተለጠፈችበት

ወዲያው ሰማዩን አግቶ ይዞ የነበረውን ዝናብ ዘረገፈው፡፡የተሰራችው ጊዜያዊ ጎጆ ሙሉ በሙሉ በዛ ድቅድቅ ጨለማ የሚወርደውን የዝናብ ውሀ አግዳ ለማስቀረት ጥንካሬው አልነበራትም፡፡ሁለቱም በ5 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዝናብ ራሱ፡፡እሷ ከህመሙና የሰውነት ጥንካሬዋ በመዳከሙ የተነሳ ዝናቡንና ቅዝቃዜውን መቋቋም ስላልቻለች ትዘፈዘፈች፣ካርሎስ የሚያደርገው ጠፋበት፡፡ ሙሉ በሙሉ ወደእንጨት አልጋው ወጣና ከእሷ ተስተካክሎ ተኛ…አቀፋትና ወደራሱ አስጠግቶ ከሰውነቱ ለጠፋት፡፡የናፈቀውን የእናቱን ጡት እንዳገኘ ህፃን ልጥፍ አለችበት፡፡የተሻለ ምቾት ተሰማት፡፡ከዝናብ ውርጅብኝ የምትሸሸግበት መጠለያ ዋሻ ያገኘች አይነት ስሜት ተሰማት፡፡ እጆቹን በረጠበ ልብሷ ስር ሰቅስቆ በማስገባት ሰውነቷን ላይ አሳረፈና ይዳብሳት ጀመር..፡፡ከዛ ቀስ እያለ ከንፈሩን ከንፋሯ ላይ አሳረፈና በቀስታ ይመጣት ጀመር፡፡አሁን ከውስጧ እየተቀጣጠለ ያለው ሙቀት ወደላይኛው የሰውነት ቆዳ በመድረስ ከላይ የሚያርፋባትን ዝናብ የሚያስከትልባትን ቅዝቃዜ እያተነ የሚያስወግድላት እየመሰላት ነው፡፡ጭልጥ ያለ ምናባዊ ህልም ውስጥ ነው የገባችው፡፡ከንፈራቸው ሳይላቀቅ ዝናቡም ከመቆሙ በፊት እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡

ስትነቃ ጎጆዋ በጥዋት የደመቀ የፀሀይ ፈንጣቂ አድምቋታል፡፡ሁሉ ነገር ብሩህ ፣ ሁሉ ነገር ዳማቅ ሆኖ ነው እየታየ ያለው፡፡እራሷን ለማንቀሳቀስ ሞከረች፡፡ አሁንም ሰውነቷ እንደተሳሰረ ነው፡፡ወደ ጎን አንገቷን መልሳ ተመለከተች፡፡ ለሊት ጎኗ ተኝቶ የነበረው ጉብል አሁን የለም፡፡አይኖቾን ብታንከራትትም ጎጆው ባዶ ነው፡፡ አንደምንም እራሷን አበረታታ ከተኛችበት ተነሳች፡፡ ዱላ መሰል እንጨት ተደግፋ እንደምንም እግሮቾን እየጎተተች ወደጎጆዋ በራፍ ሄደች፡፡ፊት ለፊቷ ያለው አማዞን ወንዝ እየተገማሸረ ጥሩ አቋም ላይ አንዳለ የማራቶን ራጭ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡አካባቢውን የሞሉት ውብና ማራኪ ወፎች ወዲህና ወዲያ አክሮባት እየሰሩ ይዝናናሉ.. አይኖቾን አሩቅ ስታማትር ካርሎስ በ500 ሜትር ርቀት በፓንት ብቻ አማዞን ወንዝ ውስጥ ጠልቆ ገብቶ ዓሳ ላመስገረ ሲዳክር ተመከተችው፡፡ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ተመለሰች፡፡ወደ ሻንጣቸው ተጠጋች ፡፡ውሀ የማያሳገባውን የሻንጣ ዚፕ ከፍታ ውስጥ ያለውን የካርሎስን ማስታወሻ ደብተር ከእነእስኪሪብቶው አወጣች፡፡እዛው መሬት ይዛ ተቀመጠችና ለመፅሀፍ ተዘጋጀች፡፡
#ኢትዬጵያዊ_ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ካርሎስና እና ኑሀሚ በአምስተኛ ቀናቸው ነበር ከአከባቢው የተንቀሳቀሱት፡፡በዛን ወቅት ኑሀሚ የተመረዘችው መርዝ ሙሉ በሙሉ ከሰውነቷ ተወግዶ… የሟሸሸ የነበረም ሰውነቷ ተነቃቅቶ….ጥንካሬዋም በተወሰነ ፐርሰንት ተመልሶ ነበረ፡፡ ባለውለታቸውን የሆነችውን ጎጆ በፍቅር ተሰናብተው አካባቢውን ለቀው የአማዞንን ወንዝ ደርቻ ተከትለው በምስራቅ አቅጣጫ ለአንድ ሰዓት ተኩል በእግር ከተጓዙ በኃላ አንድ እሮጌ ጀልባ የያዘ ግለሰብ አጋጠማቸው፡፡ከእሱ ጋር በገንዘብ ተደራደሩና ታብቲንጋ ከተማ ድረስ እንዲያደርሳቸው ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ፡፡የዛኑ ቀን አመሻሽ ላይ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
‹‹ይህቺ ከተማ የአየር ትርንስፓርት አገልግሎት አላት ነው ያልከኝ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ አላት..ማኑሳ ድረስ መሄድ ይቻላል፡፡››
‹‹ታድለን…በቃ ነገሮች ወደመጨረሻው ምዕራፍ እየተቃረበ ነው ማለት ነው…ተዲያ ወደከተማው እንግባና የአየር ትኬት ካገኘን እንሞክራ››
‹‹አይ ወደከታማ መግባት አንችልም..፡፡እንደምታያት ይህቺ አንስተኛ የጠረፍ ከተማ ብራዚል ውስጥ ትገኝ እንጂ ለኮሎምቢያ ቅርብ መሆኗን እንዳትረሺ..ያ ማለት ደግሞ የዳግላስ ተፅእኖ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይኖራል ማለት ነው፡፡ በተለይ ወደ ብራዚል ከገባን ቀጥታ የአየር ትራንስፖርት የሚገኝባት ከተማ ይህቺ ስለሆነች ቀጥታ ወደእዚህ እንደምንመጣና ወደአየር መረፊያ ጎራ እንደምንል በቀላሉ ይገምታል..ስለሆነም ከተማው ውስጥ ዋና ዋና ቦታዎች እና በተለይ ደግሞ አየር ማረፊያ ላይ ሰዎቹን እንደሚያስቀምጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹እና ምን ይሻለናል?፡፡››በስጋት ጠየቀችው፡፡
‹‹ረጅሙን መንገድ ነው የምንመረጠው..ማለት አሁንም ወደ ምስራቅ ጉዞችንን እንቀጥልና ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ ነው የምንሄደው፡፡››
‹‹ቤንጃሚን ኮንስተንት ደግሞ ማን ነች?››
ቤንጃሚን ኮንስተንት አማዞን ደን ውስጥ ከበቀሉ የብራዚል የጠረፍ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን ከተማዋ ጃዋሪ በተባለ ወንዝና በአማዞን ወንዝ ተከባ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ከዚህ አሁን ካለንበት ከተማ በጀልባ የሁለት ሰዓት ቢፈጅብን ነው፡፡ማንም ወደ ዛች ከተማ ይሄዳሉ ብሎ እይገምተንም…እዛ ከደረስን በኃላ የተሻለ የተባለ ዘመናዊ ጀልባ እንከራይና ቀጥታ ወደ ማናአስ እንጓዛለን፡፡
‹እንዳልክ …ግን የሆነ ቻርጅ ያለበት ቦታ ፈልግን ስልኬን ቻርጅ ማድረግ አለብኝ፡››የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹ምን ሊያደርግልሽ?››
‹‹ትቅዳለህ..ለወንድሜ ደውዬ ቢያንስ እስከሁን በጤና መሆኔን ላሳውቀው ነዋ፡፡››
‹‹አይ አይሆንም…ስልክሽን አብርተሸ ለወንድምሽ ደወልሽለት ማለት ያለሽበትን አካባቢ ቀጥታ ለሀገርሽ መንግስት እናም ጉደዩን ለሚከታተሉ ለአካባቢው መንግስታት አሰወቅሽ ማለት ነው..ያ ሆነ ማለት ደግሞ ዳግላስም በቀላሉ ዜናውን አገኘ ማለት ነው፡፡እና ሁሉም እኛን ለማግኘት በአካባቢው አሰሳ ይጀምራሉ…ከዚህ በፊት እንዳለኝ ልምድ ደግሞ ከየትኛውም መንግስት ቀድሞ ደጋላስ አፈፍ እንደሚያደርገን እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና ምን ይሻላል?››
‹‹የሚሻለውማ..ማናስ እስክንገባ መቻል….ነው…ወንድምሽም ዘላለም ከሚያጣሽ…ስድስት ሰባት ቀን በናፍቆት እና በትካዜ ቢሰቃይ ይሻላል፡፡አሁን አንቺ እዚሁ አካባቢ እራስሽን ከሰው እይታ ከልለሽ ትጠብቂኛለሽ… እኔ እራሴን ለውጬ ከታማ ገብቼ እመለሳለሁ››
‹‹እንዴ… እኔን እዚህ ብቻዬን ጥለኸኝ ምን ትሰረለህ?››
እጁን ወደኪሱ ሰደደና የሆነ መሀረብ አውጥቶ ቋጠሮውን ፈታና ሁለት የጨው አንኳር የሚመስል አብረቅራቀ መአድን አነሳና በእጇ መዳፍ ላይ አስቀመጠ፡
‹‹ምንድነው?››በመገረም እያየች ጠየቀችው፡፡
‹‹እንቁ ነው..በደኑ ውስጥ በአጋጣሚ በስራ ላይ እያለው በእጄ የገባ ነው..እንደዚህ አይነት ንብረት በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆንም በእጅ ከገባ ለገዛ ጥቅም ደብቆ መስቀመጥ በሞት የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው..በወቅቱ ለዳግላስ ማሰረከብ ነበረብኝ…እኔ ግን ደመነፍሴ አንድ ቀን አጣብቂኝ ውስጥ ስገባ  ይጠቅምሀል ብሎ ሹክ ስላለኝ..የመጣው ይምጣ ብዬ ደብቄ አስቀምጬው ነበር፣.እና አሁን ወደከተማ ሄጄ ወደገንዘብ ልቀይረው...እረጅም የጀልባ ጉዘ ስለሚጠብቅ ብዙ ገንዘብ ያሰፈልገናል…››
መጀመሪያ እንቁውን መለሰችለት..መልሶ በመሀረቡ ቋጠረውና ወደኪሱ ከተተው..፡፡
ከሷ የእጅ ቦርሳዋን አነሰችና ዚፕን ከፈተች፣ከላይ ያሉትን እቃዎች አወጣች ፡፡ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል ከስር እንደታሸገ የተቀመጠውን ዶለር መዥርጣ አወጣችና እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡
‹‹ይሄ አይበቃም?››
አይኖቹ በመገረም ደመቁ‹‹አንቺ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽ?››
የዛሬን አያድርገውና ሀለቃህ ዳግስ ነበር የሰጠኝ..እና አይበቃም›››….ብላ እንዴት እንዳገኘች ታሪኩን አስረዳችው
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ይሄ እኮ በጣም ብዙ ብር ነው….በይ አሁን ጀልበ እንፈልግ››አለና ብሩን መልሶላት ቦርሳ ውስጥ ከከተተ በኃላ ተያይዘው ወደፊት ለፊት መራመድ ጀመሩ፡፡
እንደተነጋገሩት እዛው አድረው ንጊት ላይ ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ በጅልባ ተጓዙ፡፡ እዛ አንድ ሰዓት ብቻ በማሳለፍ ሌላ ዘመናዊ የተባለ ጀልባ ተከራዩና ወደአማዞኒያ ግዛት ዋና ከተማ ማናአስ ጉዞ ጀመሩ፡.ያው ጉዞ ቀላል አልነበረም….6 ቀን ነው የፈጀባቸው ፡፡ግን ደግሞ በህይወት ረጅም ዘመን ለመኖር ስድስትና ሰባት ቀን መስዋት ማድረግ ያን ያህል ክፉ የሚባል ስላልሆነ አላማረረችም ፡፡
…ታብቲንጋ….ሳኦ ፍረንሲስኮ…ኮረንቲዛ….ዲ አማተራ…ሳኦ ዶሚንጎ….ሳንታ አንቶኒኦ….ሳኦ ፍሊክስ… ሳንታ ሉዚያ… የመሳሰሉን አያሌ ታዋቂ ቦታዎችንና የኣማዞን ወንዝ ዳር ከተሞችን አቋርጠው ማናአስ ከተማ ደረሱ ፡፡
ማናአስ(Manaus) በሀገረ ብራዚል የኣማዞኑያ ግዛት ዋና ከተማ ነች፡፡በብራዚል 2.2 ሚሊዬን ኑዋሪዎች የሚኖሩበት 7ተኛው ትልቋ ከተማ ስትሆን ከተማዋ በአማዞን ደን ውስጥ ከተቆረቆሩ ከ1 ሚሊዬን በላይ ኑዋሪዎች ካሏቸው ሁለት ትልልቅ ከተሞች መካከል አንዶ እና ዋነኛዋ ነች.››
በዛ ላይ የአማዞን ደንን እና የአማዞን ወንዝን ሚስጥር ለመበርበር እና ጥናት ለማጥናት ከመላው አለም የሚሰባበሰቡ ሳይንተስቶችና ተመራማሪዎች በዋናነት የሚከትሙባት ከተማ ነች፡፡በዚህ የተነሳ የአማዞን ልብ የሚል ቅፅል ስም ይሰጧታል፡፡በተጨማሪ አንዳንዶችም የትርፒካሎ ፓሪስም እያሉ ያሞካሻታል፡፡
ማናአስ  ከተማና አካባቢው በኬሚካል ፕሮጀክት..በለውዝ ምርት ….በሳሙና ምርት….በመርከብ ግንባታ እና በጎማ ተክል ምርት በጣም የታወቀች ነች፡፡፡በተለይ በጎማ ምርት ከ1800 አመት በፈት ጀምሮ የታወቀች በመሆኗ ከሀገሪቱ ሀብታም ከተሞች ግንባር ቀደሞ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ማናአስ ከተማ በ2014 እ.ኤ.አ የአለምን ዋንጫ ካስተናገዱ 12 የብራዚል ከተሞች አንዷ እንደሆነች ይታወቃል፡፡በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ድፍርሱ የኒግሮ ወንዝ እና ሰማያዊው የሶሊመስ ወንዝ አንድ ላይ ተቀላለቅሎ ወደአማዞን በገባርነት የሚፈስባት ልዩና አስደማሚ ስፍራንም በመደመም ማየት ይቻላል፡፡
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)፡


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሁለቱም እርቃናቸውን ተኝተው ፊት ለፊት እየተያዩ ማውራት ቀጠሉ?

"የሆነ ነገር ትጠይቀኛለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር  ግን ማድረግ አልቻልክም"አለችው

እንደመደንገጥ ብሎ ፀጉሯን በእጆቹ እየላገ"ምንድነው የእኔ ፍቅር?ምን ልጠይቅሽ?"

"ከዚህ በፊት የዛሬ ሳምንት አካባቢ ከዚህ ደን በሰላም ከወጣን ደግመህ ጠይቀኝ ብዬህ ነበር...አሁን ሳስበው ግን ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ረስተኸዋል…በፊትም ከልብህ አልነበረም የጠየቅከኝ ማለት ነው "አለች እንደማኩረፍ ብላ።
"አንቺ በጣም ተሳስተሻል...ያንን ጥያቄ ለደቂቃም ረስቼው አላውቅም..አሁን ደግሜ ብጠይቃትና እምቢ ብትለኝ እንዴት ነው የምቋቋመው?"ብዬ ሰግቼ ነበር ...
"እና "

"እናማ...አንቺ ቆንጆ ጠይም ወጣት ወደሀገርሽ ይዘሽኝ ብትበሪ ምን ይመስልሻል?"

"ይዞ መሄድን ይዤህ ሄዳለው።ግን ልመለስ ብትል ማንም አይሰማህም"

"ይሁን ተስማምቼያለው...አልፎ..አልፎ ሀገሬ ሲናፍቀኝ ይዘሽኝ መጥተሽ እንደምታሳይኝ እተማመናለው።››
"እሱን ፀባይህ እየታየ የሚወሰን ነው።"ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃን ገላዋን ለእሱ እይታ አጋልጣ ወረደች..ቀጥታ ወደሰካችው ስልኳ ሄደችና ነቀለችው።ተመልሳ መጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ወደሀገር ቤት ወንድሟ ጋር ደወለች.፡፡ከሰከንዶች በኃላ የወንሟን ተወዳጅ ድምፅ በጆሮዋ ሲንቆረቆር ልትሰማ እንደሆነ ስታስብ ሰውነቷን ሌላ ዙር ሙቀት ወረራት...ግን እንዳሰበችው የወንድሟ ሞባይል ሊጠራ አልቻለም...ደግማ ሞከረች።በሁለተኛ ቁጥሩም ሞከረች ተመሳሳይ ነው።
"ብሽቅ...በዚህ ቀን ሞባይሉን ያጠፍል"ተበሳጨች።ሌላ ተለዋጭ ሀሳብ መጣላት።የምስራቅ ቁጥርን ከሞባይሏ ፈለገችና ደወለች።ልክ እንደወንድሟ ስልክ የእሷም አይሰራም።
‹‹የሰዎቹ ስልክ ሁሉ አይሰራም"በተኛበት አይኖቹን እያቁለጨለጨ እየተመለከታት ለነበረው ካርሎስ ነገረችው። ከተኛበት ተነሳና ከአልጋው ወርዶ አልጋ ልብሱን ከአልጋው ላይ ገፎ እርቃን ሰውነቷን በማልበስ"አይዞሽ ተረጋጊ...አህጉር አቋራጭ ጥሪ እኮ ነው እያደረግሽ ያለሽው፡፡ ኔትወርኩ ችግር ሊኖርበት ይችላል...አሁን ባይሆን ጥዋት ሲነጋ ሊሰራ ይችላል...ካልሆነም ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን።››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡
ሌላ ዘዴ ሲላት በአእምሮዋ ተለዋጭ ዘዴ ብልጭ አለባት፡፡ ለወንድሞ...ነፃ እንደወጣችና ከቀናት በኃላ ወደሀገሯ እንደምትመለስ ልትፅፍለት ወሰነችና ኢሜሏን ከፈተች። ከአለም እይታ በተሰወረችባቸው 20 በሚሆኑ ቀናቶች በርካታ ኢሜሎች ተልከውላታል።አብዛኛዎቹ ከወንድሟ.. ከዛም ከመስሪያ ቤቷ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ግን የተላከላት ከማትጠብቀው ሰው ነበር… በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነስታ ስትቆም ካርሎስ አልብሷት የነበረው አልጋ ልብስ ከላዩ ላይ ወደቀና እርቃኗን ቀረች...
‹‹ምንድነው ፍቅር...?››

‹‹ሰውዬው ተደጋጋሚ መልዕክት ልኮልኛል?››
ግራ ገባው"የትኛው ሰውዬ?"
"ሀለቃህ...ዳግላስ?"

ከመደንገጡ የተነሳ ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና ሞባይሉን ከእጇ ተቀበላትና ኢሜሉን ተራ በተራ እየከፈተ አየ...ከዛ በድንጋጤ እግሮቹ ዝሎ ወለሉ ላይ ተዘረፈጠ..ኑሀሚም ድንጋጤው ክፍኛ አዝሏት ስሩ ተንበረከከች፡፡
ስልኩን ተቀብላው ኢሜሉን በማንበብ የሆነውን ለመረዳት የሚያስችል ጥንካሬ ከውስጧ ማግኘት አልቻለችም።ሽው እያለ መጥቶ እርቃን ሰውነቷን የሚገርፋት እርጥብ አየር ነፍሷን ጭምር እያቀዘቀዘው ነው።
"ምንድነው የሆነው?"ጥንካሬዋን አሰባስባ የሆነውን ሁሉ ከእሱ አንደበት ለመስማት ጠየቀችው።ስልኩን መልሶ ከፈተና በኢሜሏ የተላከለትን ፎቶዎች አወጣና"ወንድምሽ...እዚህ መጥቷል"አላት
"ወንድሜ ?እዚህ እንዴት?››ካርሎስ የሚያወራው ነገር ምንም እየገባት አይደለም፡፡

"አላውቅም ግን..እይ ተመልከቺ ዳግላስ እጅ ነው ያለው...ፎቶውን ወደእሷ አቅርቦ እያሳያት"ይሄውልሽ...ይሄንን ቦታ በደንብ አውቀዋለው፡፡ ማንም ሊደርሶበት የማይችለው የዳግላስ ምሽግ የሆነው ሳንቹዋሪ ነው።››
ፎቶውን ተቀበለችና በፍዘት ትመለከተው ጀመር...ዥውውውው አለባትና ቀድሞ ስልኩ ከእጇ ላይ ተንሸራቶ ወደቀባት...ፈጠን ብሎ ሊደግፍት ሲንቀሳቀስ ቀድማ ወደኃላዋ እራሷን ስታ ተዘረረች...በፋጥነት ተነሳና አፋፍሶ አቅፎ አልጋ ላይ አስተኛት።ልብስ ደራርቦ አለበሳትና ከድንጋጤ እስክትወጣ መጠበቅ ጀመረ።
###
ኮሎምቢያ/አማዞ ደን ማህፀን ውስጥ
ካርሎስ በተሰበረ ልብ ምርጫ አልባ ሆኖ በህይወቱ የመጨረሻውን ፍቅር ያፈቀራትን ይቺን ጠይም ኢትዬጵያዊ ሴት ሳይወድ በግድ ከማናአስ ወደ ቲጎና በፕሌን… ከዛ ደግሞ በጀልበ ከብራዚል ድንበር ወደኮሎምቢያ አሻግሯትና ላቲሲያ ከተማ ጫፍ ድረስ ሸኛት፡ከዛ እሱ ከዳግላስ የንፍስ ጠላቶች ጋር ለመደራደር ደቡብ ምእራብ ኮሎምቢያ ድንበር ተጠግታ ወደምትገኘው የቪንዚዎላዋ ሳና-ካርሎስ ከተማ ጉዞ ጀመረ …፡፡
ይህቺን ያፈቀራትን አፍሪካዊ ሴት ማዳን ማለት እራሱን ማዳን ማለት ነው፡፡ሰው እራሱን ለማዳን ደግሞ ምንም ያደርጋል፡፡ዳግላስን ያገኙትን ማንኛውንም አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያጠፉት የሚፈልጉ የቢዝነስ ተፎካካሪዎች እንዳሉት ያውቃል..እሱ ደግሞ ስለ ዳግላስ የቢዝነስ ሚስጥሮች ፤ መግቢያ መውጫውን ፤ድክመትና ጥንካሬውን በደንብ ያውቃል…አሁን የሚያገኛቸው ሰዎቹ ደግሞ ሃይልና ብር አላቸው….እነሱ እሱን አምነውት ከተቀበሉትና አብረውት ለመስራት ከወሰኑ ዳግላስን እስከወዲያኛው አስወግዶ ኑሀሚንና ወንድሟን ነፃ ለማውጣት የሰለለችው ቢሆን ተስፋ አለው፡፡ያ ተስፋ ካልተሳካ ነፍሱን እንደሚያስከፍለው ያውቃል…ቢሆንም ግድ የለውም…ያቺ የሰለለች ተስፋ ከመቶ አንድ ፐርሰንት ብትሆንም እንኳን  ከመሞከር ወደኃላ አይልም..ለዛ ነው እሷን ወደዳግላስ ልኮ እሱ የዳግላስን ጠላቶች አግኝቶ ለመደራደር ጊዜ ሳያባክን ጉዞ የጀመረው፡፡
ኑሀሚ ካርሎስ እንደነገራት ላቲሲያ ከተማ በተቀመጠችበት ሆቴል ነው አንድ ሰዓት እንኳን ሰትቆይ የዳግላስ ሰዎች በቁጥጥር ስር ያዋሏት፡፡በመጀመሪያ እዛ ላቴሲያ ከከተማው ወጣ ብሎ አማዞን ወንዝ ደር ካለ ወደ አንድ  ሰዋራ ቤት ነበር የወሰዷት፡፡ለአራት ቃናት ያህል እዛው አስቀመጧት፡፡በየቀኑ የሚያስፈልጋትን ያህል ምግብ ፤ልብስ እና መጠጥ ያቀርቡላታል፡፡ግን ማንም ሊናግራት የሚደፍር ፤ብታናገራቸውም የሚመልስላት አልነበረም፡፡በየቀኑ ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የሚያስፈልጋትን ነገር የሚያመጡ ሁለት ሰዎች አሉ….መጥተው እቤቱ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠውላት ይሄዳሉ….ብታናግራቸው አይመልስላትም፡፡ጠባቂዎቾ እርስ በርስም ቁጥብ ቃላትን ሲለዋወጡ ብትሰማ እንኳን በማይገባት ቋንቋ ስለሆነ ምንም መረዳት የምትችለው ነገር አልነበረም ፡፡ይበልጥ ልትቆጣጠረው የሚከብዳት ጥልቅ ድባቴ ውስጥ እየገባች መጣች፡፡እሷ ካለችበት ቤት አስር ሜትር እርቃ ባለች ጎጆ አንድ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ ጎረምሳ ሁሌ ንቁ ሆኖ ሲጠብቃት  ታየዋለች…ወደእሷ መጥቶ ለማውራት   አይሞክርም…እሷም ወደእሱ ለመቀረብ ምንም ጥረት ኣላደረገችም፡፡ይህን ጠበቂ ወይ ጥላው ወይ ገድላው በቀላሉ ማምለጥ እንደምትች ታውቃለች…..ግን ያ አይደለም እቅዷ፡፡ አሁን ሂጂ አምልጪ የሚላት አዛኝ ሰው ቢኖር እራሱ እሺ ምትልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለችው፡፡አሁን የእሷ ጥረት ወደፊት ስምጥ ወደሆነው የአማዞን ደን ማህፀን ውስጥ ገብቶ ወንድሟን ማግኘት ነው…ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላት ግድ የላትም፡፡እንደው ወንድሟንና ምስራቅን የማትረፍ እድሉ ባይኖራት እንኳን የዩትን መከራ አብራ አይታ የሚጎነጩትን
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አራት
፡፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የተወሰነ አርፈው ናፈቆታቸውን ካቀዘቀዙ በኃላ ናኦል‹‹እህቴ ዛሬ ቀኑን ታውቂያለሽ….››ሲል ግራ ያጋባትን ጥያቄ ጠያቃት፡፡
ወንድሜ ደግሞ መንጋትና መምሸቱን ካልሆነ በስተቀር እለቱና ቀኑኑ መለየት ካቀምኩ ቆየሁ…ለካ በህይወታችን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ነገሮች በመከራ ቀኖቻችን ውስጥ ስንሆን ትርጉም አይኖራቸውም፡፡››
‹‹እንግዲያው ልንገርሽ ዛሬ ጥር 11 ነው …ልደታችን ነው፡፡››

ያልጠበቀችውን ዜና ነው የነገራት….መላ ሰውነቷን ነው የወረራት‹‹ኦ …ደሰስ ይላል…››መልሰው ተንጫጩ …..
ምስራቅ‹‹እናንተ ለምን እነዚህ አስተናጋጆቻችንን ጥቂት ውለታ አንጠይቃቸውም…››የሚል ድንገቴ ሀሰብ አቀረበች፡፡
‹‹ምን ››

ልደታችሁን  ለማክበር  የሚሆን  ጥቂት  ሻማ  …የተወሰነ  ከረሜላ  ካለ…ኬክም  ቢገኝ አንጠላም…ኮኬይንም  ቢያቀርቡልን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው…››አላች…ተሳሳቁ፡፡
‹‹ሌላውን አላውቅም.. ኮከይኑ ግን አይጨክኑብንም…..›› ምስራቅ ወደ መጥሪያው ሄደችና ተጫነችው…
‹‹እንዴት ፍቅር ምን ፈልገሽ ነው››ናኦል ምስራቅን ጠየቃት..ኑሀሚ ሁለቱንም አፈራረቀች ና       በገረሜታ ታያቸው ጀመር..ምስራቅ የእሷን ምልከታ ሳታስተውል ‹‹ትቀልዳላችሁ እንዴ.. ከመጠየቅ ደጅ አዝማችነት ይቃራል፡፡ሲባል አልሰማችሁም፡፡››በማለት በራፉ በድጋሚ ለማንኳኳት እጇን ስትሰነዝር  ….በድንገት በራፉ ተከፈተ…፡፡
ኑሀሚን ያመጣት ወጣቱ ልጅ ነው በራፉን የከፈተው…. የሚፈልጉትን ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሀለቃዬን ጠይቄ ከፈቀደ የሚሆነውን አደርጋለው››ብሎ መልሶ በራፉን ዘግቶ ሄደ….፡፡ኑሀሚ ግን  በነበረችበት እንደፈዘዘች ነው፡፡
‹‹ምንድነው ያፈዘዘሽ››

‹‹የእኔ ፍቅር አለሽ እኮ…አንቺም ወዬ አልሺው ››

‹‹እና ›

‹‹እኔ እዚህ በአማዞን ጫካ ከአውሬውም ከሰው አውሬውም ለማምለጥ በመጣር ፍዳዬን በማይበት ሰዓት እናንተ ፍቅሬ ማሬ መባባል ጀመረችሁ››
‹‹ታዲያ በመሀከላችን ያለውን ለዘመናት የታፈነ ፍቅር ጭረን ካላቀጣጠልነው አንቺን ለመፈለግና ለማግኘት የሚያስችለንን ብልሀትና ጥንካሬ ከየት እናመጣን…. በነገራችን ላይ ያው አንቺ ወደ እዚህ እንደመጣሽ ሰሞን ነው የተጋባነው…››
‹‹የተጋባነው››

አዎ …ወዳሻንጣዋ ሄደችና የጋብቻ ሰርተ ፍኬታቸውን አውጥታ አሳየቻት…..ማመን አልቻለችም…ምስራቅ የሚያደርጉትን ሆነ የሚያወሩትን ሁሉ ሰዎቻቸው እየተመለከቷቸው እንደሆነ ታውቃለች….የጀመሩትን ማስመሰል አስከወዲያኛው መቀጠል አለባቸው….አዎ ከዚህ እስኪወጡ ከናኦል ጋር ባልና ሚስቶች ናቸው….ከወጡስ በኃላ አንዴት ይሆናል የሚለውን እርግጠኛ አይደለችም…..ልጁን በፊት ከምትወደው በተለየ መንገድ ወዳወለች…..ጠረኑ ክፉኛ ለምዳዋለች…..ፍቅሩ ልቧ ውስጥ እየተንጠባንጠበ ነው…..ይሄንን የጋብቻ ሰርተፍኬት እንደቀልደ በቃ አሁን ጉዛችን አበቅቶለታል ብላ ቀዳዳ የወረቀት ቅርጫት ውስጥ ለመክተት ጥንካሬው መቼም ቢሆን የሚኖራት አይመስላትም፡፡
ከተረጋጉ በኃላ ኑሀሚ ሰውቷን ለመታጠብ ፈለገች እና ወደሻወር ቤት ገባች፡፡ታጥባና ነፅታ ስትወጣ ክፍላቸው ውስጥ የተለየ ነገር ነበር የጠበቃት….በርከት ያሉ የሴት ቀሚሶች እና ሙሉ የወንድ ሱፍ ሱሪ የያዘ ተሸከርካሪ የልብስ መደርደሪያ ወለሉ መሀከል ላይ ተቀምጦ ናአልና ምስራቅ ፊት ለፊቱ  ቆመው በአድናቆት እየተመለከቱት ደረሰች፡፡
ያገለደመችውን ፎጣ በደንብ አጥብቃ አሰረችና ‹‹ምንድነው ይሄ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹ይህን ያመጣው ልጅ..በጠየቃችሁት ጥያቄ መሰረት ልዳታችሁን ለማክበር ተፈቅዷል…..ከዚህ የሚሆናችሁን ልብስ መርጣችሁ ልበሱና ልደቱ ወደሚከበርበት ቦታ ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥቼ ወስዳችኃላው›› ብሎል፤ብለው አስረዷት፡፡
‹‹አንቺ ሰዎቻችን ደግ ናቸው…….መጀመሪያ በደንብ አስደስተውን የምንፈልገውን ነገር እንድናደርግ ከፈቀዱልን በኃላ ከዛ አመስግነናቸው እንድንሞት ነው የፈለጉት፡፡››አለች ምስራቅ፡፡
‹‹እሱስ ቢሆን ማን አየበት  ይመስገን ነው››….ብላ ካመጣጡላቸው ቀሚሶች መካከል ለእሷ
የሚሆናትን መምረጥ ጀመረች….በሀያ ደቂቃ ውስጥ ሶስቱም ልክ እቤተ-መንግስት ከንግሱ ጋር የእራት ግብዣ እንዳላባቸው መኮንንቶች ሽክ ብለው ዘንጠውና አምረው በቀጣይ
የሚሆነው መጠበቅ ጀመሩ፡፡

እንደተባሉት ያው ልጅ ቤቱን ከፍቶ ይዞቸው ወጣ፡፡ቀጥታ ከህንፃው በጎሮ በኩል ካለ እስካአሁን ካላዩት በአበቦች ያሸበረቀ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ስፋት ያለው የተንጣለለ  የመዋኛ ገንዳ ያለበት ቦታ ነው የወሰዳቸው፡፡ ገንዳው ዳር ባለ በሰራሚክ ንጣፍ ባማረ ጎጆ የምግብ አይነትና፤ የመጠጥ አይነቶች ሞልተውበታል….ዙሪያውን መቀመጫዎች ሲኖሩ አስተናጋጅ መሰል ሁለት ሴትና አንድ ወንድ ዝግጅቱን ለማሳመር ከላይ ወደታች ይሯሯጣሉ፡፡ይዞቸው የመጣው ሰው ለገንዳው እይታ ምቹ የሆነ መቀመጫ ሰጣችውና ሶስቱም በተርታ ተቀመጡ፡፡
..በትካሻቸው ከባድ መሳሪያ የተሸከሙ ሰዎች በአከባቢ ራቅ ካለ ስፍራ በየተወሰነ ርቀት ፈንጠር ፈንጠር ብለው ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲቃኙ ይታያል ፡፡ጥርት ካለው ከአማዞን ደን ሚነፍሰው ልስልና እርጥብ አየር ጋር አብሮ የሚነፍስ ጥኡም የላቲን ሙዚቃ እየተሰማ ነው፡፡በአካባቢው ሌላ ሰው የለም፡፡ድንገት ከገንዳው ብልቅ ብሎ ወደ ዳር የሚወጣ ሰው ተመለከቱ… ከእነሱ በ5 ሜትር  ርቀት ላይ ስለሆነ ማንነቱ ጥርት ብሎ ይታያቸዋል፡፡
ወደ ኑሀሚ በፈገግታ እየተመለከተ‹‹በሰላም ተመልሰሽ ወደቤትሽ በመምጣትሽ ደስ ብሎኛ››አላት፡፡
‹‹እንዴት አልመጣ ….ብጨክን ብጨክን ባንተ ጨክኜ መቅረት እችላላሁ››ብላ ምፀቱን በምፀት መለሰችለት…መልሷ በጣም አሳቀው፡፡
‹‹በጣም ናፍቀሺኝ ነበር….በህይወቴ እንደአንቺ ለማግኘት ያስቸገረኝ ሰው የለም….ድሮም ውድ ነገር ለማግኘት በጣም ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል…ለማንኛውም መልካም ልደት ለሁለታችሁም…..ሰዎቹ  መሰናዶቸውን እስኪያጠናቅቁ ትንሽ ልዋኝ.. ከመሀከላችሁ መዋኘት    …የሚፈለግ ሰው ካለ ግን መጥቶ መወኘት ይችለል፡፡››ብሎ ወደገንደው መሀል እየዋኘ ሄደ፡፡
ምስራቅ ብድግ ብላ ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች….ሁለቱም መንትያዎች ‹‹ሴትዬዋ አበደች እንዴ›› የሚል እይታ አፍጥጠው ያዮት ጀመር…፡፡
‹‹ፍቅር..ምን እየሰራሽ ነው››ናኦል ነው የጠየቃት…በእነዚ ሰው በላ አውሬ በሆኑ ሽፍቶች ፊት እርቃን ሰውነቷን ማሳየቱን ጥሩ ሆኖ አላገኘውም፡፡፡
‹‹ምን ነካችሁ ዛሬ እኮ የአናንተ ልደት ብቻ አይደለም..ጥምቀትም ጭምር ነው..ታዲያ ባገኘነው አጋጣሚ ብንጠመቅ ምን ይላችኃል?፡፡›› ብላ ጎንበስ በማለት ጫማዋን አወለቀችና ወለሉን እየነካካች ወደ ገንደው ተንቀሳቀሰች….ኑሀሚ ተነሳችና እሷ አንዳደረገችው ልብሷን በፍጥነት አወላለቀች.‹‹ሴቶቹ ጤናም የላቸው እንዴ››በማለት አልጎምጉሞ ባለበት መንቋራጠጡን ቀጠለ…ኑሀሚ ልብሷን አውልቃ እንዳጠናቀቀች ሄደችና ምስራቅ ጎን ቆመች…ዳግላስ ገንዳው መሀከል ባለ ከመነደሪ ላይ ተኝቶ ጭንቅላቱን በክንዱ ደገፍ በማድረግ አይኖቹን ሁለቱ እንሰት ላይ ተክሎ በገረሜታ ከሩቅ ይመለከታቸው…እንዲሁ ለማለት ያህል ጋበዛቸው እንጂ ያደርጉታል ብሎ አልጠበቀም ነበር…የኑሀሚን ሙሉ ተክለ ቁመና ሲያይ በሰውነቱ ሁሉ ሙቀት ተረጨና ውጥርጥር አለ…ለሳምንታት ሲያልመውና ሲመኘው የነበረው ገላ ይሄው በእሱ ቁጥጥር ስር ሆኖ ከፊት ለፊቱ እየታየው ነው….እሱ የእዚህ አካባቢ ገዢና አስተዳዳሪ ብቻ ሳይሆን የዚህ አካባቢ አምላክ ..ሁሉን አድራጊ..ሁሉን ፈጣሪ እንደሆነ ነው
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ  ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው  ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን ወለል ላይ ተቀምጦ ይታያል…እሬሳውን ጭኖ ወደኢትዬጵያ የሚበረው አውሮፕላን በሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ይታያል…እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ለዘላለም አሸልባ  የተኛችው ምስራቅ ነች፡፡

ናኦል እና ኑሀሚ ከዳግላስ ወጥመድ አምልጠው የሲኦል ወጥመድ ከሆነው ከእዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ወጥተው እንሆ አስተማማኝን ቦታ ላይ ቆመዋል…ከአንድ ሰዓት በኃላ በአገራቸው አየር መንገድ ወደሀገራቸው ለመብረር ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል…ግን እዚህ ለመድረስ የከፈሉት መሰዋዕትነት ሁለቱንም እስከወዲያኛው ያፈራረሳቸው ነው፡፡አሁን በድናቸው ነው የሚንገዋለለው፡፡እግዚያብሄር በእድሜያቸው መጀመሪያ በዛ በህፃንነታቸው ጊዜ  ሚወዱዋቸውን ወላጆቻቸውን በመንጠቅ አሸማቆቸው ነበር  በእድሜያቸው አጋማሽ ደግሞ በእድሜ ልካቸው አብራቸው የነበረችውን፤ ከጎዳና አንስታ ህይወት የሰጠቻቸውን፤የተዘረፈውን  የወላጆቻቸውን ንብረት ያስለመለሰልችላቸውን.. እናም ከዛም አልፍ እሷን ለማትረፍ አህጉር አቆርጣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የገባችላቸውን የዚህችን  ሴት ህይወት ማጣት ለሁለቱም ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ለናኦል ደግሞ ነገሩ የተለየ ነው….ይህቺን ሴት ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ እዛ በረንዳ ፤ላይ ካያት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ይወዳት ነበር…እዚህ ነገር ውስጥ ያስገባት እራሱ ነው፡፡እህቴ ጠፋችብኝ አፋልጊኝ ብሎ ደወላላት..እሱን ለመርዳ ከጎሬዋ ወጣች..ለብቻው ልትተወው ስላልፈለገች አህጉር አቋርጣ ተከትላው መጣች ..አንድ ወር ሊደፍን ትንሽ ቀን ለቀረው ቀናት በመከራና በስጋት ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እጅግ ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ህይወት አሳልፈዋል….የህይወትን ጣእም እና የፍቅርን ትርጉም አሳይታዋለች ..አስተምራዋለች፡፡….ከእሷ ጋር የመሰረቱት የውሸት ትዳር ለእሱ በህይወቱ ካጋጠመው ተጨባጭ እውነቶች መካከል ምን እልባትም ዋነኛው  ነው…በሰላም ወደሀገራቸው ሲመለሱ ለምኖና እግሯ ላይ ወድቆ ጋብቻቸው ባለበት እንዲቀጥልና በእሷ እቅፍ ውስጥ ለዘላለም መቅለጥ ነበር የሚፈልገው፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር….ብቸኛ ምኞቱም ያ ነበር..፡፡ግን አሁን ሁሉ ነገር እንዳልነበረ ሆኗል….፡፡በሰልም እየሰቀችና እተፍለቀለቀች አብራው የመጣችው ሴት ይሄው ህይወት አልባ በድን እሬሳ ሆነ  በሳጥን ውስጥ ታሽጋ  ወደሀገሯ እየተመለሰች ነው፡፡እና ደግሞ በጣም እያበሳጨው ያለው ነገር  ምንም እንዳልተፈጠረ በህይወት ቆሞ አየር እየሳበ መሆኑን ሲያስብ ነው….ደግሞ እኮ የእሱን ሞት ነው ሞተችው፡፡
ነገሩ እጌት ነው  የተከሰተው  ብለን ወደኃላ ዞረን ስናስታውስ……
..
ከአራት ቀን በፊት  ነው፡፡ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ  የታገቱበት ክፍል ተከፈተ….የመጣው  የተለመደው የዳግላስ ተላላኪ ነው፡፡
ወደኑሀሚ አትኩሮ እየተመለከተ ‹‹ጌታዬ እየጠበቀሽ ነው››አላት፡፡

ኑሀሚ ከ30 ደቂቃ በፊት አምጥቶ የሰጣትን ውብ የራት ቀሚስ ለብሳና ተዘጋጅታ  የጠበቀችው ነበር፡፡ምስራቅንና ወንድሟ ናኦልን ተራ በተራ ጉንጫቸውን ሳመችና በዝግታ እርምጃ ልጁን ተከትላ ወጣች፡፡ቀደም ብሎ የተላከላትን ቀሚስ ለብሳ ወደታባለችው የእራት ግብዣ መሄድ የምርጫ ጉዳይ አይደለም…ግዴታ ነው..፡፡በሰዓቱ እያስጨነቃት የነበረው  ከእራት ቡኃላስ ሚለው ነበር?….ወደአልጋ እንሂድ ቢለኝስ?እንደዛ ስታስብ ዝግንን የሚያደርግ ቀፋፊ ስሜት ነበር የተሰማት፡፡እሷ ግን እኮ እንደዛ አልነበረችም፡፡ለአላማዋ ጥቂትም ጥቅም ይኑረው እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ተጋድሞ ወሲብ መፈፀም ልክ እንደካርታ ጫወታ  ዘና ብላ ምትፈፅመው ቀላልና ትርጉም የማይሰጣት ጉዳይ ነበር…ደግሞም በሰላይነት ሕይወቷ እንዲጠቅማት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ በቂ ስልጠና ወስዳለች…አሁን ግን አንድ ነገር ገብቷታል..ለካ በዛን ጊዜ ነገሩ ቀላልና የማያስጨንቅ ሆኖ የሚታያት  ስለሰለጠነችበት ብቻ አልነበረም…ልቧ ኦናና ባዶ ስለነበረ ነበር እንጂ፡፤አሁን ግን አንድ ሰው ገብቶበታል…ያ ሰው ደግሞ እሷን ለማዳን በቅርብ ርቀት ባለ ጫካ ውስጥ ሆኖ እቅዱን ስለሚያሳካበት ዘዴ እየተጨነቀና እያሰበ ነው…እና  እሷ ካለፍላጎቷም ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ወደአልጋ የመሄድን ጉዳይ በቀላሉ ምታየው አይደለም….ይሄ ነው ያስጨነቃት…የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ ስትገባ ግዙፉ ጠረጴዛ በምግብና በመጠጥ ተሞልቶ ተመለከተች፣አንድ ሴትና ሁለት ወንድ አስተናጋጆች ፈንጠር ብለው ግድግዳውን ተደግፈው ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው…እንደገባች ዳግላስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተራመደ…ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው…ከላይ ሰማያዊ ሸሚዝ ከዳለቻ ጅንስ ሱሪ ጋር አድርጎል…በፈገግታ ተጠጋትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት…ፈራ ተባ እያለች እጇን ሰነዘረችና ጨበጠችው፡፡

እጇን ሳይለቅ እየጎተተ ወደ ጠረጴዛው ወሰዳትና  ወንበር ስቦ አስቀመጣት..ከዛ ራመድ አለና  ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ወዲያው ለአስተናጋጆች በእጁ ምልክት ሲያሳይ ተንደርድረው መጡና ብርጭቆቸውን በመጠጥ ሞልተውላቸው ወደቦታቸው ተመለሱ፡፡
ከተቀዳለት መጠጥ አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ‹‹እንዴት ነው ቆይታ ?››ሲል ጠየቃት፡፡
ያለምንም ማስተባበል‹‹በጣም አሰልቺ ነው››ስትል ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ለስራ ጉዳይ ወጣ ማለት ነበረብኝ…አሁን ግን ተመልሼለው…ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ፍፅም ደስተኛ እንድትሆኚ የተቻለኝን አደርጋለሁ…ከነገ ጀምሮ የአማዛንን ድንቅ ውበት ጎዲያ ጎድጓዳዋን እያዞርኩ አሳይሻለው..እንስሳቱን ፤ወፎችን ፤ፏፏቴዎችንና ወንዙን ሁሉንም አንድ በአንድ አሳይሻለው..እናም ከቦታው ጋር በፍቅር እድትተሳሰሪ የተቻለኝን እጥራለው..ከቦታው ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር ፍቅር እንዲይዝሽ እፈልጋለው››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ ከአንተ ፍቅር እንዲይዘኝ ማድረግ ትችላለህ?››
‹‹እንግዲህ እቅዴ እንደዛ ነው››
‹‹ጥሩ ነው››ብላ በአጭሩ መለሰችለት
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››በጫወታው እንዲገፉበት ስለፈለገ ጥያቄውን ቀጠለበት፡፡
‹‹እስከማውቅህ ድረስ ሁሉንም ነገር    በጉልበትና በማስግደድ ነው የምታደርገው…..ቡኃላ እንዳፈቅርህ ማድረግ ሲያቅትህ እንዳትተኩስብኝ ነው የምፈራው…፡፡››ስትለው ከጣሪያ በላይ ተንከትክቶ ሳቀ..‹‹በይ በባዶ ሆዴ ከዚህ በላይ መሳቅ አልችልም ..እራት እንብላና ወደበረንዳ ወጣ ብለን መጠጣችንን እየተጎነጨን የጀመርነውን ጫወታ እንጨርሰዋለን…››አለና ሰሀን አነሳ …እሷም እንደእሱ አደረገኝ..እራት በልተው አስኪያጠናቅቁ ሀያ ደቂቃ አካባቢ የፈጀባቸው ሲሆን በዛን ጊዜ ውስጥ ብዙም የረባ  ነገር እልተነጋገሩም…፡፡.እራቱ እንደተጠናቀቀ ዳጋላስ እጁን ሊታጠብ ቀድሞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ …ወዲያው ከአስተናጋጆቹ አንዱ እቃ የሚያነሳሳ መስሎ ተጠጋት እና ጎንበስ ብሎ‹‹ነገ በዚህን ሰዓት››አላት፡፡፡አልገባትም‹‹ዋት››አለችው፡፡ደገመላት‹‹ነገ በዚህን ሰዓት..ተዘጋጁ››ብሎ የተበላበትን  ሰሀን ሰበሰበና እንዳቀረቀረ ከሳሎን ወጥቶ ሄደ፡፡
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)

#የመጨረሻ_ክፍል


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹በል አስወጣቸው››ዳግላስ አንቦረቀ፡፡
‹‹ምን እየሆነ ነው ምን አጠፋን?››ኑሀሚ በተመሳሳይ የድምፅ ቃና  ጠየቀችው፡፡
‹‹ጠላቶቼ ይሄንን ቦታ እንዴት ሊያውቁት ቻሉ?››
‹‹እኛ ታዲያ ምን እናውቃለን? የራስህን ሰዎች አትመረምርም››
‹‹መሳሪያውን ወደ ግንባሯ ደቀነና‹‹እንደንዴቴ ሶስታችሁንም እዚህ ግንባር ግንባረችሁን ደፍቼያችሁ እሄድ ነበር፡፡ግን እንዳደረሳችሁብኝ ኪሳራ በሰላም እና በቀላሉ መሞት አይገባችሁም…ሶስታችሁም እባክህ ግደለን እያላችው በየቀኑ እንድትለምኑኝ ነው የማደርገው…በተለይ አንቺን…በሉ ያዟቸው..››

እሱን ከበው የነበሩ ጋንግስተሮች ወደቤት ውስጥ ገቡን ሶስቱንም እየገፈተሩ ወደውጭ አስወጣቸው…..በኮሪደሩ አልፈው ሳሎን ገቡ …ከዛ በደረጃው ወደግራውንድ ይዘዋቸው ሄዱ…ሰው ሁሉ ይተረማመሳል….መሳሪያዎች ከመጋዘን እየወጡ ይታደላሉ..ሀገር ወራሪ መጥቶ ለፊልሚያ እየተሰናዱ ነው የሚመስለው….ወደምድር ቤት ይዘዋቸው ወረዱ….ምድር ቤት ያለው  ትርምስ ከግራውንዱም ይብሳል….የተመረቱትን ኮኬይን አሰተካክለው ካርቶን ውስጥ በማስገባት ያሽጋሉ… ሌሎች ደግሞ የታሸገውን ወደጥግ እየወሰዱ ይደረድራሉ….ዳግላስ  እነኑሀሚን ለጠባቂዎቹ ተዋቸውና እያንቧረቀ ትእዛዝ በመስጠት ወደሰራተኞቹ ሄደ፡፡
‹‹እንዴ ይሄን ሁሉ ኮኬይን የሚደረድሩት እንዴት ሊየደርጉት ነው?››ምስራቅ ነች በሹክሹክታ የጠየቀችው፡፡
ኑሀሚን‹‹አልገባኝም ….ምን አልባት…..››ብላ ግምቷን መናገር ስትጀምር ያልጠበቁት ነገር ከፊት ለፊታቸው ተመለከቱ፡፡ የምድር ቤቱ ጥግ ላይ ያለ ወለል እንዴት አድርገውት እንደሆነ አይታወቅም ሲከፈት አዩ…
‹‹እንዴ!! ከዚህ በታች እቤት አለ እንዴ?››ናኦል ነው በገረሜታ የተናገረው፡፡
‹‹አይ እቤት አይመስለኝም….ከዚህ አካባቢ                                   ማምለጫ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ነው፡፡
‹‹አንቺ እውነትሽን ሳይሆን አይቀርም…››
ስትል ሰዎች በካርቶን የታሸገውን ካርቶን እየተሸከሙ በተከፈተው ወለል በመሄድ እንደመሰላል  ባለ ብረት እየተንጠለጠሉ ወደታች መውረድ ጀመሩ፡፡፡
‹‹ሰዎች ትክክል ነኝ…ይሄ ከዚህ ስፍራ ማምለጫ የምድር ውስጥ መንገድ ነው….እናም እኛንም በዛ ውስጥ ይዘውን ሊሄዱ ነው››ኑሀሚ ነች ተናጋሪዋ፡፡
ምስራቅ‹‹የሆነ ነገር ማድረግ አለብን ..እዛ ውስጥ ይዘውን ገብተው ከዚህ ካስመለጡን እንዳለው ለወራት አስቃይቶ ነው የሚገድለን..መሞታችን ካልቀረ ደግሞ እዚሁ ለማምለጥ እየሞከርን ብንሞት ይሻላል››
‹‹ትክክል ነሽ ለማምለጥ መሞከሪያ ጊዜው አሁን ነው››ናኦልም በምስራቅ ሀሳብ ተስማማች፡፡
ምስራቅ ‹‹ናኦል››ስትል ተጣራች፡፡
‹‹በጣም ነው የምወድህ እሺ፣ማለቴ አፈቅርሀለው››አለችው፡፡
‹‹አውቃለው እኔም አፈቅርሻለው…ግን እያስፈራሺኝ ነው››
‹‹አትፍራ….ኑሀሚ አንቺንም ወድሻለው››
አቦ አንቺ ደግሞ አትረብሺኝ …ኑዛዜ አስመሰልሺው….ትኩረቴን እየበታተንሺው ነው…..ተመልከቱ እነዛ ሁለት ሰዎች ለእያንዳንዱ ሰው የእጅ ቦንብ እያደሉ ነው….ሲቀርብን በፍጥነት የተወሰነ ቦንብ በእጃችን ማስገባት አለብን…ከዛ…..››ኑሀሚ ንግግሯን ሳታገባድድ ምስራቅ ወደጎን ተስፈንጥራ  ጠረጴዛ ስር ሾልካ በመግባት ስትሰወር እነሱን ሲጠብቁ የነበሩ ጠባቂዎች የሚወስዱት እርምጃ ግራ ገብቷቸው ወዲህ ወዲያ ሲራወጡ ኑሀሚ የናኦልን ክን ድ ይዛ በግራ በኩል ስትሮጥ ከጠባቂዎቹ አንዱ ተወርውሮ የናኦል እግር ላይ ተጠምጥሞ አስቀረው….ኑሀሚ ወንድሟን ለቃ ሩጫዋን ቀጠለችና ከኮኬይኑ ካርቶን ጀርባ ተሰወረች….አንዱ መሳሪየውን ደቅኖ ተከተላት…በአየር ላይ ተንሳፈፈችን ጉሮሮውን ዘጋችለት…እጥፍጥፍ ብሎ ስሯ ወደቀ..መሳሪያውን ተቀበለችና ምላጩን ተጭና ዝም ብላ አንደቀደቀችው…እቅዷ ትርምስ መፍጠር ነው…ያሰበችው ተሳካላት፡፡ ሰው በፊትም ስጋትና ድንጋጤ ላይ የነበሩ ሰራተኞች የመሳሪያ መንደቅደቅ ሲሰሙ ሚይዙት የሚጨብጡት ጠፍቷቸው ከወዲህ ወዲያ መተረማመስ ጀመሩ ፡፡ይህ ደግሞ ለነኑሀሚ ጥሩ ሁኔታ ፈጠረላቸው፡፡
///
ወደቀኝ ታጥፋ ጠረጴዛ ተከልላ የተሰወረችው ምስራቅ ተንሸራታ ቦንብ የምታድለው እንስት ላይ ነው የተከመረችባት …ልጅቷ በድንጋጤ ቦንብ ያለበትን ካርቶን ለቀቀችው፡፡ መሬት ወድቆ ተዘረገፈ….ምስራቅ ልጅቷን በአንድ እጇ ይዛ በሌላ እጆሶስት ሚሆኑ ቦንቦችን ያዘች….ከግራ በኩል ይተኮስባት ጀመር..ምርጫ ስላልነበራት ልጅቶን ከፊት ለፊቷ  አቆመቻት…የሚተኮሰው ጥይት ሁሉ ልጅቷ ሰውነት ውስጥ ተሰገሰገ….ምስራቅ ወደኃላ አፈገፈገችና ቦታዋን ለቀቀች….ተኳሹ መሬት ላይ ከተዘረገፍት ቦንቦች አንድን አገኘው….አካባቢው ባልተጠበቀ ፍንዳታ ተናጋ…ዋና ዋና መብራቶቹ ጠፉና ጭላንጭል ድንግዝግዝ ብርሀን ብቻ ቀረ… ምድር ቤቱ በጥቁር ጭስ ተዋጠ…ምስራቅም ኑሀሚም በየፊናቸው  ናኦልን ሲፈልጉ ድንገት ተገናኙ….

‹‹ናኦልን አይተሸዋል…?››ኑሀሚ ነች ጠያቂዋ፡፡
‹‹አላየሁትም እየፈለኩት ነው፡፡ወደውጭ ይዘውት ወጥተው ሊሆን ይችላል›››ምስራቅ መለሰች፡
‹‹አይ በምድር ውስጥ ይዘውት ገብተው ከሆነስ..?እኔ ወደእዛ ልሂድ አንቺ ወደውጭ ውጪና ፈልጊው፡፡››
‹‹እርግጠኛ ነሽ….?››
‹‹አዎ ጊዜ አናጥፋ…››ተስማሙ……
ምስራቅ ወደውጭ መውጫው ከሚራኮቱት ሰዎች ጋር እየተጋፋች ስትሄድ ኑሀሚ ደግሞ ወደውስጠኛው የምድር ውስጥ መሹለኩያ ሮጠች…..፡፡
ኑሀሚ አስር ሜትር ርቀት ሲቀራት ወደእሷ ተተኮሰባት… ወደግራዋ ተስፈነጠረችና የሆነ የብረት ካዝና ስር ከለላ ይዛ እራሷን ለመከላከከል መተኮስ ጀመረች…

‹‹አንቺ ሸርሙጣ..ነይ ውጪ››የዳግላስ ድምፅ መሆኑን ለየች….እልክ ተናነቃት፡

‹‹እየተኮሰች ተሸለክልካ በመሀከላቸው ያለውን ርቀት ወደሳባት ሜትር አጠበበች…፡፡አሁን በግልፅ እየታያት ነው….አልማ ተኮሰች…ሆዱን ቦተረፈችው…አጎራና መሬት ተዘረረ…..፡፡ከግራና ከቀኝ ጠባቂዎች ወጡና ግማሹ ወደእሷ እየተኮሱ ለጓደኞቻቸው ሽፋን መስጠት ጀመሩ፡፡ ሁለቱ ደግሞ በደም የጨቀየውን ዳግላስን  እየጎተቱ ወደተከፈተው ጉድጎድ አስገቡት…ወደታች ይዘውት ወረዱ.፡፡ከዛ  እነሱ ተከተሉ…አንዱን ግንባሩን ብላ አስቀረችው፡፡ወደጉድጓዱ ተስፈነጠረች…ወንድሟን ይዘውት ሄደው ከሆነ መከተል አለባት…አንድ እርምጃ ሲቀራት እንዴት እንደሆነ በማታውቀው ዘዴ ወለሉ ተመልሶ ተዘጋ ፡፡ወደውስጥ የሚያሾልክ ምንም አይነት ቀዳዳ ሆነ ክፍተት በአካባቢው የለም፡፡መሳረያውን በወለሉ ላይ አርከፈከፈች…በንዴትና ተስፋ መቁረጥ በጉልበቷ ተናበረከከች…በዚህ ጊዜ ከኃላዋ አንድ በጣም ደስ የሚል ከገነት የመሰላ የጥሪ ድምፅ ሰማች‹‹…ኑሀም ኑሀሚ››
‹‹ዞር አለች››
‹‹ኑሀሚ ካርሎስ ነኝ››
ተንደርድራ ድምፅ ወደሰማችበት አካባቢ ተስፈነጠረች…..ኦ እራሱ ነው….በወገቡ ዙሪያ ቦንብ ደርድሮ  እንደዘንዶ የተጠመዘዘ ዝናር በጀርባው አንጠልጥሎ ዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪውን ደቅኖ አገኘችው…ተጠመጠመችበትና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀች….