ምራቅ እየተፋ እያለ ስቀለው
ባደባባይ መኃል ለሚፈርድብኝ ሰው
አንተ አትቸገር እኔው እበቃለው
ብቻ ግን
ይሁዶች በበዙባት በዚች በኛ አለም
በዚች በኛ ሀገር በዚች በኛ ቀየ
ወዳጅ በስሎ ቁሞ ስሞ ከሚሸጠኝ ጠብቀኝ ጌታየ
ባደባባይ መኃል ለሚፈርድብኝ ሰው
አንተ አትቸገር እኔው እበቃለው
ብቻ ግን
ይሁዶች በበዙባት በዚች በኛ አለም
በዚች በኛ ሀገር በዚች በኛ ቀየ
ወዳጅ በስሎ ቁሞ ስሞ ከሚሸጠኝ ጠብቀኝ ጌታየ
👏6🥰4❤2
💧አንድ የታክሲ ሹፌር አንድ ተሳፋሪ ጭኖ ወደ መድረሻው እየተጓዘ ሳለ፣ በመንገድ ዳር አንዲት የዓይን ስውር ሴት በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ የታክሲ ምልክት ስታሳይ ተመለከተ። ሹፌሩም አብሮት ያለውን ተሳፋሪ በትህትና “ጌታዬ፣ እቺን ሴት ብንጭናት ይከፋዎታል?” ሲል ጠየቀው። ተሳፋሪውም “ችግር የለም፣ ጫናት” በማለት ፈቀደ።
💧ሹፌሩ ከመኪናው ወርዶ ወደ ሴትየዋ ቀረበና “ጤና ይስጥልኝ፣ የታክሲ ሹፌር ነኝ፤ እርዳታ ትፈልጊያለሽ?” አላት። ሴትየዋ በእፎይታ ፈገግ ብላ “ከልብ አመሰግናለሁ! ለሰዓታት ብቆምም ማንም ሊያቆምልኝ አልቻለም ነበር” ስትል በምሬት ተናገረች።
አብረው ከተጕዙ በኃላ መድረሻዋ ቦታ ስትደርስ “ሒሳቡ ስንት ነው?” ስትል ጠየቀች። ሹፌሩም “10 ዶላር ብቻ” አላት። እርሷም በኪሷ ያለውን ገንዘብ ሁሉ አውጥታ “እባክህ 10 ዶላር ብቻ መርጠህ ውሰድ” አለችው።
💧ተሳፋሪውም ሹፌሩን በትኩረት ይከታተለው ነበር። ሹፌሩ ግን ከእጇ ላይ 20 ዶላር አነሳ። ተሳፋሪው በልቡ “የማታይ ስለሆነች ሊያታልላት ነው” ብሎ አሰበ። ነገር ግን ሹፌሩ “20 ዶላር ወስጃለሁ፣ ይሄውልሽ መልስሽ” በማለት ሁለት ባለ 100 ዶላር ወረቀቶችን (200 ዶላር) እጇ ላይ አኖረላት። ሴትየዋም በደስታ አመስግና ወረደች።
💧መኪናው ጉዞውን ሲቀጥል፣ ተሳፋሪው በመገረም “ለምንድነው ካለህ ላይ ቀንሰህ ተጨማሪ ገንዘብ የሰጠሃት?” ሲል ጠየቀው። ሹፌሩም ፈገግ ብሎ “እኔ ገንዘብ ለማግኘት አቅሙም ጤናውም አለኝ፤ ለእሷ ግን ህይወት ከባድ ነው” ሲል መለሰለት።
💧ተሳፋሪው መውረጃው ጋር ደርሶ ሳይከፍል የወረደ መሰለ። ሹፌሩ ዞር ሲል ግን በመቀመጫው ላይ 2,000 ዶላር ተቀምጦ አየ። ደንግጦ “ጌታዬ! ሒሳብዎ እኮ 20 ዶላር ብቻ ነው” ብሎ ተጣራ። ተሳፋሪውም ዞር ብሎ ፈገግ አለና “ለእኔም ገንዘብ ማግኘት ቀላል ነው፤ ይሄ ለአንተ ይሁን። ትልቅ አክብሮት አትርፈሃል” አለው።
====================================================
💧ሁሉም ሰው ለመቀበል በሚተጋበት ዓለም ውስጥ፣ አንተ ለመስጠት የምትተጋ ደግ ሰው ሁን።
ደግነት ሰንሰለት ነው፤ ለአንዱ ስታደርግ ሌላው ለአንተ እንዲያደርግ የፈጣሪ መንገድ ይከፈታል።
ከገንዘብ በላይ የሰው ልጅ ትልቁ ሀብቱ ለተቸገሩት የሚያሳየው ርህራሄና ንጹህ ሰብዕናው ነው።
📖ማጋራት አይዘንጋ!
📖 @atronosee

🥰14❤8👍5
#ተማሪዋ!
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በጥላሁን
፡
፡
ራመድ ራመድ እያልኩ ወደሆቴሉ ዘው ብዬ እንደገባሁ ፊት ለፊት ባየሁት ነገር ልቤ ስንጥቅ አለች። ወይኔ አምላኬ ምንድን ነው የማየው ? ጭራሽ እኔ የገዛሁላትን አዲሷን ልብስ••• እያልኩ በሁለቱም እጆቼ ሁለት ሁለት ባዶ የቢራ ጠርሙዝ እንዳንጠለጠልኩ ድንጋጤዬ አብረክርኮት አልራመድ ያለኝን እግሬን በግድ እየጎተትኩ በቀስታ ወደ ተቀመጡበት ወንበር ተጠጋሁ••
••••
በሆቴሉ ውስጥ ጭልም ደሞ ብርት የሚሉ ሲበሩም ደብዛዛ ብርሀን የሚፈነጥቁ ጌጣማ አንፖሎች እዛም እዛም ተሰቅለዋል ፣
ቀረብ ስል ግራ ገባኽ አብሯት ያለው ወንድ ፊቱ በደንብ ታየኝ። ዛኪ አይደለም።ገዘፍ ያለ ነው። አስተያየቱ ደሞ ያስፈራል። ገልመጥመጥ ሲያደርገኝ እነሱን እያየሁ በቀጥታ ወደነሱ መሄዴን ቀየር አደረኩና እንደማለፍ ብዬ አየት ሳደርግ ልጅቷም ቃልዬ አይደለችም። ቀሚሱዋም ዲዛይኗ የቃልዬ አይነት ቢሆንም ' ከለሯ 'በተወሰነ መልኩ ይለያል።
የስራሽን ይስጥሽ ቃልዬ፣ ግራ የገባኝ ደግሞ ተከትያት ሀረር ከመጣሁ በሁዋላ የተጠናወተኝ በቅርብ ርቀት ያየኋት ሴት ሁሉ ቃልዬን የምትመስለኝ በሽታ ነው ፣ ይሄ መታመም ካልሆነ ምን ይሆናል ? እያልኩ ቢራውን ገዝቼ ተመለስኩ።
የግቢው ጥበቃ የቀራቸውን ምርቃት ሁሉ አሟጠው መረቁኝ።
"የእኔን እድሜ ያድለህ ፣ ጧሪ አያሰጣህ፣ የማታ እንጀራ ይስጥህ፣ የልጅ ልጅ ያሳይህ•••••" ሌላም ሌላም ብዙ ምርቃቶች።
"አባባ " አልኳቸው እንደጨረሱ።
"ወዬ የኔ ልጅ"
"ፍቅር ይዝለቅልህ!" ብለው ይመርቁኝ አልኳቸው እንባ እየተናነቀኝ።
"ፍቅር ይዝለቅልህ ፣ የወድድካትን ያፈቀርከትን ክፉ አይይብህ ፣ ትዳርህን ይባርክልህ !
" አሜን አሜን አሜን አባቴ" አልኳቸው ዋናው እሱ ነው ። እኔ የልጅ ልጅ ማየት የምፈልገው ከቃልዬ ነው። ከቃልዬ ከነጠለኝ በሁዋላ ረጅም እድሜ ምን ሊጠቅመኝ። እያልኩ ቢራውን ሰጥቻቸው ወደ ክፍሌ ገባሁ።
ቃልዬ ከዛኪ ጋር ማደሯን ማሰብ አስፈሪ እንደሆነብኝ ድካምና ረሀቡ ነው መሰለኝ የወደቅኩበትን ሳላውቅ ነጋ።
ጥዋት ወደ ድሬ ዳዋ ስመለስ ቃልዬ እራሷ እስክትደውል ላልደውልላት በናቴ ማልኩ።
ሳትደዉል መሸ፣ ሳትደውል ነጋ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ቀንም እንደዛው ልደውል ስልኬን ካወጣሁ በሁዋላ በናቴ መማሌ ትዝ ሲለኝ ስልኬን ወደ ኪሴ እመልሰዋለሁ።
በአራተኛው ቀን ደወለች ።
"ይቅርታ ኤፍዬ በዚህ ምርቃት ሰበብ ተዋክቤ፣ ቻርጀሬ ጠፍቶ ፣ ባትሪ ዘግቶ••••" ብዙ ብዙ አለች ፣ ለመጥፋቷ ብዙ ምክንያት ብዙ ሰበብ ተናገረች ቃል። ዝም ብዬ ሰማኋት።
ስትጨርስ አንድ ነገር ብቻ ተናገርኩ አንድና አንድ ነገር ብቻ አልኳት።
"ችግር የለውም ቃልዬ በጣም ላገኝሽ እፈልጋለሁ መች ይመችሻል?" የሚል ጥያቄ ብቻ ሰነዘርኩላት። ድምፄ መሰባበሩ ለኔ ቢታወቀኝም ለሷ አላታወቃትም አልያም አላስተዋለችውም።
"ኤፍዬ አብረን ለመዋል ከሆነ ነገ ፣ ለማደር ከሆነ ግን ከነገ ወድያ"
"አይ ችግር የለውም አብረን ውለን ትሄጃለሽ"
"በቃ ነገ ከሰአት ደውልልኝ "
የቃልን ስልክ እንደዘጋሁ ጌትነት ስልክ ላይ ደወልኩ።
እቤቱን ለአንድ ቀን እንደምፈልገው ነገርኩት።
"ችግር የለውም ኤፍዬ ማደርም ትችላለህ እኔ ጀለሶቼ ጋር እሄዳለሁ" አለኝ።
ቃልዬን ላመጣት ስሄድ ለጌትነት ደውዬ ልመጣ ነውና ቁልፉን አስቀምጠህልኝ ሂድ አልኩት።
ደረስኩ ተገናኘን ። ስማኝ ከጀርባ ገባች። ደንዝዣለሁ። ምንም አላወራም ቃልዬ ግን ምን ያህል እንደናፈቅኳት ፣ ስለሰሞኑ የምርቃታቸው ወከባ ምን ያህል ግዜ እንዳሳጣት እያወራችልኝ የማውራት እድል ሳትሰጠኝ እነ ጌትነት ቤት ደረስን። የማውራት እድል ብትሰጠኝ ምን እንደማውራ አላውቅም።
ገብተን ትንሽ እንደቆየን ከምን እንደምጀምር ምን እንደምላት ጨነቀኝ።
ካንድም ሁለት ሶስቴ ልጀምር እልና የሆነ የሚረብሽ ስሜት እየተናነቀኝ አቋርጠዋለሁ። ተነስቼ ወደ መታጠቢያ ቤት እሄድና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጥቤ እመለሳለሁ።
ቃልዬ ቡና ለማፍላት እየተንጎዳጎደች ሁኔታዬን ማስተዋል አልቻለችም።
አቦሉን እንደጠጣን •••
"በቃ ሁለተኛውን አታፍይ ይቅር " አልኳት።
"ለምን ኤፍዬ?" አለችኝ ፊት ፊቴን እያየች።ፊቴ ልክ እንዳልሆነ ያስተዋለችው ያኔ ነበር። መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች።
"ምን ሆነሃል ኤፍዬ ችግር አለ?" አለችኝ አገጬን ይዛ ወደግራም ወደቀኝም ገልበጥ ገልበጥ እያደረችኝ።
"አዎ ችግር አለ ቃል"አልኳት አገጬ ላይ ያለውን እጇን ይዤ ከአገጬ ላይ እያወረድኩት።
"ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ልቧን በግራ እጇ ደገፍ አድርጋ እየተመለከተችኝ። ልቧ ነገራት ብዬ በውስጤ እያሰብኩ ዝም አልኩ።
"ኤፊዬ!" ብላ ተጣራች።
"ወዬ ቃል"
"ምን ሆነሀል ?" ምን ሆንኩ እንደምላት ቸገረኝ።
"ቃልዬ" አልኳት።
"ውዬ"
"ታፈቅሪኛለሽ?"
"ምን እሚሉት ጥያቄ ነው እስከዛሬ ምን ያህል እንደማፈቅርህ አታውቅም እና ነው ቆይ ምንድን ነው የሆንከው ፊትህ እኮ ልክ አይደለም?"
"ፊቴ ብቻ አይደለም ሁሉ ነገሬ ልክ አይደለም ቃል እባክሽ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ብቻ መልስ ስጪኝ አንቺ ምንም ነገር አትጠይቂኝ"
"እሺ"
"ታፈቅሪኛለሽ ቃል"
"አዎ ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ"
"ዛኪንስ ታፈቅሪዋለሽ ቃል?"
ስላት ፊቷ ላይ ያየሁት ድንጋጤ እኔኑ አስደነገጠኝ።
ያ ድንጋጤዋ ነበር የመጨረሻውን መርዶ ያረዳኝ። በቃ የቃልዬን መልስ ድንጋጤዋ ውስጥ አየሁት።
ቃልዬ ብዬ ጠራሁዋት አይን አኗን እየተመለከትኩ።
ወዬ ማለት አልቻለችም። በቃ አቃታት። የኔም የሷም አይኖች እኩል እንባ አቀረሩ።
" ቃልዬ!" ብዬ ደግሜ ጠራኋት።
አይን አይኔን ከማየት ውጪ አቤትም ወዬም ማለት ተሳናት ቃል አፏ ተለጎመ። የስረኛው ከንፈሯ ይንቀጠቀጥ ጀመር።
ጣቶቼን በጣቶቿ እያፍተለተለች ተለጎመች የኔ ቃል።
ሁሉን ነገር እንደደረስኩበት ውስጧ ነግሯታል።
ይህን ሳስብ አመመኝ ።
ቃልዬ ሁኔታዋ አንጀት ይበላል።
የሚታዘንልኝ እኔ ሆኜ ሳለሁ ቃልዬ በዛ ልክ ጭንቅ ጥብብ ሲላት ሳይ አሳዘነችኝ።
ያን ሲተናነቀኝ የነበረውን እውነት መናገር ጀመርኩ•••
ቃልዬ አውቃለሁ ሁሉን አውቃለሁ። ከቀናት በፊት ሀረር እስከሄዳችሁባት አስቀያሚ ቀን ድረስ ይቺ ቅፅበት በኔና ባንቺ መሀል እንዳትፈጠር ስሸሻት ኖሪያለሁ።
ነገር ግን እውነትን መሸሽ ከሞት እንደማያድነኝ ተረዳሁ። አዎ ቃልዬ አንቺን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ፣ መሞት አልፈልግምና አንቺን ማጣት እፈራለሁ።
እኔ ስለፈራሁት እኔ ስለሸሸሁት የሚቀር ነገር የለም።
ሁሌም አፈቅርሻለሁ። ምንም ብትበድይኝ ምንም ብትጎጂኝ አንቺን አለማፍቀር እስክችል ድረስ አፈቅርሻለሁና ዛሬም ቢሆን አንቺን ክፉ የምናገርበት አንደበት የለኝም።
ክፉ ይናገረኛል አልያም ይጎዳኛል ብለሽ እንዳታስቢ እሺ? ፣ እኔ አንቺን የማፈቅርሽ የእውነት ነው ፣ የማፈቅርሽ ግን የኔ ስለሆንሽ ብቻ አይደለም።
ዛሬም የማልፈልገው አንቺን አለማፍቀር ሳይሆን እየታመምኩ፣ እየተረበሽኩ፣ እንቅልፍ እያጣሁ፣ የተበዳይነት፣ የተገፊነት ስሜት እያንገላታኝ ማፍቀርን ነው።
ነገ ከነገ ወድያ ላጣሽ ልትለይኝ እንደምትችይ እያሰብኩ ማፍቀር ደከመኝ ቃልዬ።

❤22👍1
አብሬሽ ሆኜ የተሰቃየሁት ስቃይ አጥቼሽ ከምሰቃየው ጠናብኝ ቃልዬ ።
ሀለቱም ለኔ ህመም ቢሆንም ከእውነት ጋር መታመም ይሻላል እውነትን ሸሽቼ የማላመልጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁና የምደበቅበት የምሸሽበት የለኝም እውነቱን ልጋፈጠው የተገደድኩት ሁሉ ነገር ካቅሜ በላይ እስከሚሆን ታግሼ ነውና በውሳኔሽም በውሳኔዬም እንደማልፀፀት ተስፋ አደርጋለሁ።
አንድም ቀን በዚህ ልክ ትጎጂኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ቃልዬ።
ዛሬ እውነቱን ካንቺ አንደበት ሰምቼ ሀቁን ልጋፈጠው ወስኛለሁ። ስለትናንት አልወቅስሽም፣ ስለነገም አላውቅም አሁን የምፈልገው በራስሽ አንደበት እውነቱን እንድትነግሪኝ ብቻ ነው ቃልዬ።
" ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል ቃል?"
"እ ቃል እባክሽ ንገሪኝ ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል?"
ቃልዬ መልሷ ማልቀስ ብቻ ሆነ። ከጎኔ ቁጭ ብላ ስታለቅስ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። እራሴን ፈራሁት። ስሜታዊ ሆኜ ቃልዬ ላይ እጄን እንደማልሰነዝር ባውቀውም እራሴን ፈራሁት ከአጠገቧ ተነስቼ በመራቅ ፊት ለፉቷ ተቀመጥኩ።
አቀርቅራ ስታለቅስ ቆየችና ድንገት ቀና ብላ
"ኤፍዬ ይቅርታ!" አለችኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። ቤቱ የሚሽከረከር መሰለኝ። ከተቀመጥከበት እንዳልወድቅ አይኔን ጨፍኜ ግርግዳውን ተደገፍኩ።
"ኤፍዬ ይቅርታ !" አለች በድጋሚ። መልስ አልሰጠኋትም።
ቃልዬ ቀጠለች ••••
"እኔና ዛኪ እዚህ ግቢ ትምህርት እንደጀመርኩ የዛሬ ሶስት አመት ነው በፍቅር አብረን የሆነው ፣ " ስትል ገና ከግር ጥፍሬ ጀምሮ ሁለመናዬን ወረረኝ። እያየኋት ልሰማት አቅም አጣሁ። ጭንቅላቴን ጉልበቶቼ መሀል ደፍቼ አቀረቀርኩ ። ቃልዬ ቀጠለች
"ፍቅር ጀምረን ወራት ያህል እንደቆየን ስለሱ ብዙ ነገር እሰማ ጀመር ከብዙ ሴት ጋር እንደሚቀራረብ ባውቅም አምነው ነበር። ሁሉንም ነገር የምሰማው በውሬ ነው። ስጠይቀው ይክደኛል ። ያን ቀን አንተና እኔ በተገናኘንበት ምሽት አንዷ ሴት ጋደኛዬ ዛኪ ከሌላ የግቢ ሴት ጋር ያለበትን ሆቴል ነግራኝ ነበር ሳንቲም እንኳን ሳልይዝ አለ ወደተባለበት በርሬ የሄድኩት።
ግን አጣሁት መመለሻ ሳንቲም እንኳን ልነበረኝም ። ዛኪን ከዛ በኋላ አብሬው ላልቀጥል ወስኜ ነበር። ለምን በዛ ሰአት እዛ ሆቴል በር ላይ እንደቆምኩ አንተ ስጠይቀኝ ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ ነበር ያልኩህ። ዛኪን አየሁት ብላ የደወለችልኝ ሴት ያንን አጋጣሚ ተጠቅማ አብረዋት ከነበሩ ሁለት ወንዶች መሀል ከአንደኛው ጋር ልታቀራርበኝ ስትሞክር ተናግሪያት ወጣሁ። በዛ ሰአት ነበር አንተ መጥተህ ፊት ለፉቴ የቆመከው ። ይህንን ደሞ በመጠኑም ቢሆን ነግሬሀለሁ። ኤፍዬ የኔና ያንተ ነገር ከተዋወቅንባት ምሽት ጀምሮ መቀራረባችን እና ወደ ፍቅር መግባታችን እንዴት እንዴት እንደፈጠነ ታውቃለህ።
እኔና አንተ ወደፍቅር በገባንባት ሁለት ወር ውስጥ ከዛኪ ጋር ተኮራርፈን ነበር ።ድጋሚ የምታረቀውም አልመሰለኝም ነበር።
ነገር ግን ልጅቷ ሆን ብላ እኔን ለሌላ ወንድ ለማጣበስ ስለሱ መጥፎ እያወራች እንዳጣላችን በየቀኑ እየመጣ ይነግረኝ ነበር። መውጫ መግቢ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ። ካንተ ጋር ሆኜ እንኳን ስንቴ እንደሚደውልና ስንቴ ተነስቼ ካጠገብህ እየሄድኩ እንደማዋራው ታስታውሳለህ።
በቃ ታረቅን። እኔና እሱ ስንታረቅ በጣም ተጨነቅኩ። ዛኪን የታረቅኩት ትምህርቴን ተረጋግቼ ለመጨረስ ብቻ ነበር።
አንተን ልጎዳ ብዬ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ። ከዛኪ ጋር እዛ ግቢ ውስጥ እስካለሁ ድረስ መውጫ መግቢያ ስለሚያሳጣኝ መለያየት ከባድ ቢሆንም አብረን እንደማንዘልቅና ከተመረቅን በኋላ እንደምንለያይ እርግጠኛ ነኝ። አንተን •••ብላ ልትቀጥል ስትል መስማት አቅለሸለሸኝ።
" ምን እያልሽ እንደሆነ እንኳን ለኔ ለራስሽም የሚገባሽ አይመስለኝም ቃልዬ ፣ ዛሬም ዛኪን እንደምታፈቅሪው ብቻ ነው የገባኝ አሁን ያልሽኝን ልረዳውም ላምንሽም አልችልም ።
መቼም እንዳላምንሽ አርገሽ ልቤን ሰብረሽዋል አሁን የምፈልገው ከዚህ በላይ ምንም ክፍ ቃል ካፌ ሳይወጣ እንድትሄጅልኝ ብቻ ነው" አልኳት። ቀና ብዬ ቃልዬ ስትሄድ ላለማየት እንዳቀረቀርኩ።
ረጅም ደቂቃ እያለቀሰች ቆየች። ከዝምታ ውጪ ምንም አላልኩም።
"ኤፍዬ ይቅርታ እሺ" ብላኝ እያለቀሰች ቤቱን ለቃ ወጣች።
እኔም ወጣሁ። ታምሜ ተኛሁ።
አስር ቀን ሙሉ ምን እንወሆነ በማይታወቅ በሽታ ታመምኩ ስራ አልሰራሁም ። የቃልዬ ምርቃት ቀን እንደምንም ተነስቼ ቀደም ብዬ የገዛሁላትን ስጦታ እና አበባ ይዤ ወደ ግቢ ሄድኩ።
ከቤተሰቦቿ መሀል ሆና ከግቢ እንደወጡ ከጀርባ ጠጋ አልኩና
"ቃልዬ" ብዬ ጠራኋት።
ዘወር ብላ እንዳየችኝ ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም ። ቤተሰቦቿ ወደፉት እየሄዱ ነው። ቃልዬ እዛው ቆማ እያየችኝ በዝግታ እየተራመድኩ አጠገቧ ስደርስ እነዛ አይኖቿ ላይ ያቀረረው እንባ በጉንጯ ላይ ቁልቁል ወረደ።
ስጦታዋን ሰጠኋት። ተቀበለችኝ። አመሰግናለሁ ሳይሆን ምናልባትም ለአስረኛ ግዜ•••
"ኤፉዬ ይቅርታ እሺ" ነበር ያለችኝ።
ፊቴን መልሼ ካጠገቧ ሄድኩ። ምናልባት ቃልዬም ከአንድ ከሁለት ቀን በሁዋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትሄዳለች።
ህይወት ፣ ምኞት፣ ደስታ ፣ ስራ፣ ተስፋ ሁሉ ፣ እራሱ መኖር ትርጉሙ አልገባህ አለኝ። ለምን እንደምኖር እራሴን ስጠይቅ ለመኖር የሚያስገድደኝ አንድ ምክንያት ብቻ ነበር ያገኘሁት። እሷም እህቴ ነች።
የምኖረው ለኔ ብዙ ለደከመችው ለእህቴ ስል ብቻ ነበር።
የናትና ያባቴ ምትክ እህቴ እኔን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ አልችልም። ለሷ ስል እኖራለሁ። ሂወት ቀጠለ።
ለወራት የክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰን ሳላስብ ትተሽኝ የሚለውን ሙዚቃ ሳላዳምጥ ተኝቼ አላውቅም።
ከስምንት ወር በሁዋላ አይቼው የማላውቀውን የፌስቡክ አካውንቴን ከፍቼ ስመለከት መጀመሪያ ላይ የመጣው ፎቶ ቃልዬ ከሁለት ቀን በፊት የለጠፈችው ቀለበት ስታስር የተነሳችው ፎቶ ነበር። ቀለበት ያሰረችው ግን ከዛኪ ሳይሆን ከሌላ ወንድ ጋር ነው።
"ቃልዬ ከተመረቅን በሁውላ ከዛኪ ጋር አብረን እንደማንቀጥል እርግጠኛ ነኝ " ያለችው እውነት ነበር ማለት ነው አልኩ። ስልኬን ወርውሬ ግርግዳው ላይ ለጠፍኩት ፣ብትንትኑ ወጣ።ከተበታተነው የስልኬ ስብርባሪ መሀል ግን የቃልዬ የቀለበት ፎቶ ቅዳጅ አልነበረም።
ዳግም ህመም ዳግም ግርሻት ፣ ዳግም ስቃይ። አወይ ፍቅር ግርሻቱም አይጣል ነው ለካ።
ስልኬን ከሰበርኩት ከአንድ ወር በሁዋላ እህቴ ከወራት በፉት በገዛችልኝ ሚኒባስ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሰው እስኪሞላ መሪው ላይ ተደፍቼ እየጠበኩ ነው።
መኪና ውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶችን እያዞረ የሚሸጥ አንድ እድሜው ከአስራ አራት የማይበልጥ ልጅ እግር በጋቢናው በኩል መጥቶ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች በቅናሽ ዋጋ እያለ የያዛቸውን ጥቅሶች ተራ በተራ እያነበበ ነው ። አራት ጥቅሶችን አንብቦ አምስተኛው ላይ ሲደርስ እንደመባነን ብዬ ከመሪው ላይ በፍጥነት ቀና አልኩና•••
"እስቲ ቆይ ቆይ አሁን ያልከውን ድገመው !" አልኩት። ደገመው ከጠየቀኝ ሂሳብ በላይ እጥፉን ከፍዬ ጥቅሱን ገዛሁትና መኪናዬ ዳሽ ቦርድ ላይ ለጠፍኩት።
ወረቀቱ ላይ የተፃፈው ••••
"ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢልም ፣ ለባልጀራህ ሁሉን ሚስጥርህን ንገረው ግን አይልም"
የሚል ጥቅስ ነበር ። መታሰቢያነቱ ለኪያ።
✨ተፈፀመ✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
@atronosee
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍24❤16😢16
ቀብር የሌለው ፍቅር......
አንዳንድ ፍቅር ማጠቃለያ
የለውም .....የመጨረሻ
መሰናበቻ ሳይኖረው
በቀስታ ይሞታል......
ልክ ሩቅ ቦታ ላይ
እንደሚሰማ ሙዚቃ
ቀስ እያለ ይጠፋል!!!
አንዳንድ ፍቅር ማጠቃለያ
የለውም .....የመጨረሻ
መሰናበቻ ሳይኖረው
በቀስታ ይሞታል......
ልክ ሩቅ ቦታ ላይ
እንደሚሰማ ሙዚቃ
ቀስ እያለ ይጠፋል!!!
👍5❤2🔥1
መኖር ደጉ እልፍ ያሳያል :
ሰው ታውሮ ሞት ይመኛል :
ሁሌ ላይኖር መሰንበቱ :
ምን ያጓጓል ስንብቱ :
ማን ከረመ ዘላለሙን :
ማን አስቀረ መሄጃውን :
ማን ቀየረ ቀን ማብቂያውን :
ሰው ቢኖር ነው አንድ እድሜውን :
ስቃይ ሳቁ ለቅሶ ደስታ :
ማግኘት ማጣት ዕድል ፈንታ :
ይካተታል በመኖር ድል :
ሞትስ ያለው በኑሮ አይደል !?
እስኪ እንኑር ለሞት እንቆይ :
በአለው ጊዜ ያልቅ የለ ወይ ።
ሰው ታውሮ ሞት ይመኛል :
ሁሌ ላይኖር መሰንበቱ :
ምን ያጓጓል ስንብቱ :
ማን ከረመ ዘላለሙን :
ማን አስቀረ መሄጃውን :
ማን ቀየረ ቀን ማብቂያውን :
ሰው ቢኖር ነው አንድ እድሜውን :
ስቃይ ሳቁ ለቅሶ ደስታ :
ማግኘት ማጣት ዕድል ፈንታ :
ይካተታል በመኖር ድል :
ሞትስ ያለው በኑሮ አይደል !?
እስኪ እንኑር ለሞት እንቆይ :
በአለው ጊዜ ያልቅ የለ ወይ ።
👍9👏5❤2
📖 አንባቢ ለመሆን የሚረዱ 6 ቀላልና ተግባራዊ ሕጎች!
«ማንበብ እፈልጋለሁ ግን ጊዜ የለኝም» ወይም «አንድ መጽሐፍ ጀምሬ መጨረስ አልቻልኩም» ብለው ያውቃሉ? እንግዲያውስ እነዚህ 6 ቀላል ሕጎች የንባብ ህይወትዎን ሙሉ በሙሉ ይቀይሩታል! 👇
1️⃣ The 10-Pages a Day Rule (የ10 ገጽ ሕግ)
በአንድ ጊዜ 100 ገጽ ለማንበብ አትሞክሩ። በቀን 10 ገጽ ብቻ አንብቡ—ይህ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስደው!
💡 በቀን 10 ገጽ = በወር 300 ገጽ (1 ሙሉ መጽሐፍ) = በዓመት 12 መጻሕፍት ያለምንም ድካም!
2️⃣ Habit Stacking (ልማድን ከልማድ ጋር ማያያዝ)
ንባብን ሁልጊዜ ከሚያደርጉት ቋሚ ልማድ ጋር አያይዙት።
☕️ «የጠዋት ቡናዬን ስጠጣ 5 ገጽ አነባለሁ»
🛌 «ማታ ከመተኛቴ በፊት አልጋ ላይ ሆኜ ለ10 ደቂቃ አነባለሁ»
ይህ ዘዴ አእምሮአችሁ ሳያመነታ ንባብን ልማድ እንዲያደርግ ይረዳዋል።
3️⃣ The 50-Page Rule (የ50 ገጽ ሕግ)
አንድን መጽሐፍ እስከ 50 ገጽ አንብባችሁ ካልጣማችሁ በግድ መጨረስ የለባችሁም፤ አስቀምጡትና ወደ ሌላ ይለፉ! የማይስብን መጽሐፍ በግድ ለማንበብ መሞከር የንባብ ፍላጎትን ይገድላል።
4️⃣ Replace Scroll with Page (ስክሮልን በገጽ መተካት)
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምናጠፋውን ጊዜ መጽሐፍ ለማንበብ እንጠቀምበት! ስልካችሁን አንስታችሁ ፌስቡክ ወይም ቲክቶክ ከመክፈታችሁ በፊት፣ መጽሐፋችሁን ገልጣችሁ 2 ገጽ ብቻ የማንበብ ልማድ ይኑራችሁ።
5️⃣ Always Carry a Book (ሁልጊዜ መጽሐፍ መያዝ)
ቦርሳችሁ ውስጥ ሁልጊዜ አንድ መጽሐፍ (ወይም በስልካችሁ PDF/e-book) ይኑራችሁ። ታክሲ እየጠበቃችሁ፣ ተሰልፋችሁ ወይም ሰው ስትጠብቁ ለጥቂት ደቂቃዎች ማንበብ ከንባብ ጋር በቀላሉ ያላምዳችኋል።
6️⃣ Read What You Love (የሚወዱትን ያንብቡ)
ሰዎች ስለወደዱት ብቻ ለእርስዎ የማይመች መጽሐፍ አያንቡ ታሪክ፣ እድገት (Self-help)፣ ሳይንስ ወይም ልብወለድ ደስ የሚልዎትን ዘውግ በመምረጥ ይጀምሩ!
💡 «ዛሬ የምታነበው ነገር ነገ የምትሆነውን ሰው ይወስናል!»
🔄 ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ

❤5👍4
📌 ደፋር መሆን ይኖርብናል!🔸
ያልተሄደበትን መንገድ ለመሄድ መድፈር፣
🔸 ትእቢትን፣ እልህን፣ ጥላቻን እና ይሉኝታን ለመተው መድፈር፣
🔸 ራስን ለማዳመጥ መድፈር!
አዎ... ብዙ በደል ፈፅመሃል፤ ተፈፅሞብሃል። ብዙ ሰው ጠልተሃል፣ ተጣልተሃል፣ ተጠልተሃል፤ ልብህ ተሰብሯል፣ ልቦችንም ሰብረሃል። ግን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጋር ታርቀህና ራስህን አስታርቀህ—
ዳግም ለመውደድ፣
ዳግም ለማዘን፣
ዳግም ለመርዳት፣
ዳግም እርዳታ ለመጠየቅ፣
እና በቅንነትና በፍቅር ለመኖር ድፈር!
🛑 መጀመሪያ ግን ከራስህ ጋር ለመታረቅ ድፈር!ራስህን ከነሙሉ ስህተቶቹ፣ ግድፈቶቹ፣ እንከኖቹ፣ ውሸቶቹ፣ ቅጥፈቶቹ እና አስመሳይነቶቹ ሁሉ ለመቀበል፣ ለማዳመጥና ለመውደድ ድፈር።
የ«ፍቅር እና የይቅርታ ዘመን ነው» ሲባል ወደ ሰማይ አታንጋጥ፤ ወደ ጎረቤቶችህና «ጠላቶቼ» ብለህ ወደ ፈረጅካቸው ሁሉ አታፍጥጥ።
መጀመሪያ ከራስህ ጋር ለመታረቅ ወደ ውስጥህ ተመልከት፤ ወደ ራስህ ተመለስ። ውስጥህን፣ ልብህንና ህሊናህን አጽዳ። ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ!
💡 ራስን መመልከት...ራስን መመልከት ራስን ወደ መሆን የሚያደርስ ወሳኝ መንገድ ነው። ራስህን ስትመለከት የወንድምህን ጉድፍ ሳይሆን፣ የአንተን ተራራ ታስተውላለህ።
በዚህ ውስጥ ደግሞ ተራራህን እየነቀልክ ራስን ወደ መሆን ታድጋለህ። ራስህን ስትሆን ብዙ ነገሮችን ታሸንፋለህ፤ መሰናክሎችን በቀላሉ አልፈህ፣ የነከሰህን የመከራ ጥርስ ውኃ የማድረግን ጥበብ ትጎናጸፋለህ።
🔑 ብቻ ምን አደከመህ? ራስህን ስትሆን ብዙ የደረብካቸውን አላስፈላጊ ኮተቶች ከራስህ ላይ አውርደህ፣ ንጹህ አንተነትህን ብቻ ያነገበ ማንነት ስትገነባ ያን ጊዜ ሰው መሆን ትጀምራለህ።
እናም... ራስህን ለመውደድ ድፈር!
"ትልቁ ድል ከውጭ ጠላት ጋር መዋጋት ሳይሆን፣ ከራሳችን ድክመት ጋር ታርቆ መኖር ነው።"
"ዛሬ ከራስዎ ጋር ለመታረቅ ምን ለመተው ወሰኑ? ሐሳብዎን በኮሜንት ያጋሩን! 👇"
🔄 ለወዳጅ ዘመደዎ ያጋሩ!

❤6👍4
ባሻዬ! በአርሲ ወገኖቻችን ላይ በተደጋጋሚ ለደረሰው ግድያ እንዲሁም አገራችን አሁን ላለችበት ምስቅልቅል መንግሥታችንን ለምን ተጠያቂ ታደርጋለህ? መንግሥታችን ምን ያድርግህ?
ቆይ ቆይ! ጄሊፊሽ ስለተባለው የባህር እንሰሳ ተፈጥሮ አንድ ነገር ልንገርህ፣
ጄሊፊሽ አጥንት የለውም፣ አንጎል የለውም፣ ልብ የለውም፣ ዓይን የለውም እንዲሁ በደመነፍስ ይኖራል። ታዲያ ጄሊፊሽ የሆነውን መንግሥት ምን አድርግ ነው የምትለው?
🗡በተስፋዬ ኀይለማርያም

😢10❤3
#ባለ_ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
ፀጥታ በወረሰው በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ፡አንድ ሰው የሆነ ቦታ ለመድረስ ይጣደፋል ፡የሆነ አላማ ያለው ይመስላል አንዳንዴ እንደ መደናቀፍ ይላል ኮሮኮንቻማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ በጣም አስቸግሮታል ፡ትዕግስት የለሽ ቢጤ ነው ቶሎ ቶሎ ይናደዳል አጠገቡ ማንም ባይኖርም አልፎ አልፎ ይራገማል ፡ይሳደባል ፡እንዲ እንዲ እየተቻኮለ ተጉዞ ያን አስቀያሚ ጨለማ ሰፈር ጨርሶ ሲወጣ ድምፅ አውጥቶ
"የማይረባ አገር ሁሉን ነገር ማጨለም ቲ!"አለ እናም ቀኝ እግሩን ከመሬቱጋር አጋጨው
መብራት የለም፡ ውሃ የለም፡.....ችግር ቲ ፡አሁን እኛ ጠግበን ሳንበላ ጤፍ ጤፍ እንኳ በአቅሙ ለውጭ ይሸጣል ፡መብራት መብራት በስርሃት ሳናበራ ፡ለውጭ ይሸጣል ቲ! ኧረ ስንቱን ስንቱን ትሸጣለች..... !ነጋዴ አገር! ግን ያላተረፈች ! ቲሽ፡ ባዶ ባዶ ፡ሰርተህ ባዶ ፡ነግደህ ባዶ ፡ሰርቀህ ባዶ .... ኪኪኪኪኪ ...ነገሩ የሚሰረቀውን ሰው ጠንቅቆ ያለማወቅ እራሱ ባዶነት ነው ኪኪኪኪኪ.... ስንት ሙሰኛ በተንጣለለ ጊቢ ውሻና ዘበኛ ሰብስቦ የሚኖረውን ትቶ እነማዘር በመከራ ያገኟትን ሳንቲም ከነቦርሳው መንትፎ መሮጥ መስረቅ ነው እንዴ ኪኪኪኪኪ ..... ኧረረረ ከሰረቁ አይቀር እንደኛ የጀግና ተልእኮ ማካሄድ ነው ኪኪኪኪኪ!!" እያለ ለብቻው እየለፈለፈ እየሳቀ በብርሃን ወደ ተሞላው ግን ፀጥ እረጭ ካለው ፕሮግራሙ ውስጥ ከከተተው ሰፈር ደረሰ ፡
ቆም ብሎም አካባቢውን በጥሞና ማስተዋል ጀመረ ፡እናም ሰሞኑን ጊዜ ወስዶ ሲያጠናው ወደሰነበተው ፡አንድ ትልቅ ነጭ በጥቁር የተቀባ ብረት በር ላይ አተኮረ "፡አንድ ዘበኛ፡ ሁለት ውሻ አንድ እማወራ ፡አንድ አባወራ ፡አራት ሴት ልጆች ኪኪኪኪኪኪ.. ይሄ ሌባ አባወራ ቲ አራት በሙሉ ሴት ይወልዳል የማይረባ በደንብ አይሰራም ነበር ኪኪኪኪ ይሄኔ ሙስናውን ቢሆን በደንብ ይሰራው ነበር ፡ልክ የአንዱን ንብረት ለአንዱ እየሰጠ እንደሚያስተላልፈው ሁሉ ፡ሁለቱን ሴቶች ፡ከኛቤት አባወሮች ጋር ፡እኔን በመሰለ ጀግናና በዛ ጅል መንትያ ወንድሜ በቀየረ ነበር ኪኪኪኪኪ ..."እያለ ብቻውን ገለፈጠ ፡መልሶ አፉን እንደመያዝ አድርጎ እራሱ በራሱ ላይ አለመጠ ፡ለሱ ይሄ ጉዳይ ምንም አይነት መረበሽን ባያስከትልበትም ፡ፀጥታው ግን የሞት ያህል ያስፈራል ፡ቀስ እያለ የግቢውን ዙሪያ ዞር ዞር ካለው በዋላ ከለበሰው ጥቁር እረዥም ካፖርቱ ውስጥ የፊት መሸፈኛ የሹራብ ጭንብል አውጥቶ አጠለቀ ለአይኖቹ ብቻ የሚታዩትን ቀዳዳዎች በትክክል ካደረጋቸው በዋላ፡ አንዲት አነስተኛ ሽጉጥ በማውጣት በሁለት እጁ እያቀያየረ አሻሻት እናም ፈገግ አለ ፡እናም ከሌላኛው ኪሱ ውስጥ በላስቲክ የተጠቀለለውን በመርዝ ያበደ ስጋ አወጣ ፡በጊቢ ውስጥ ዘበኛው ልክ ከለሊቱ 6:00ሰሃት ላይ የሚፈታቸው ውሾች እንደሚንቀሳቀሱ ያውቃል ፡ዘበኛውም በዚ ሰሃት አሳቡን ለውሾቹ ጥሎ ለሽ እንደሚልም ያውቃል ፡ስለዚ የስጋዎቹን ቁርጥራጮች ይወረውረው ጀመር ወደጊቢው ፡ድምፆች ተሰሙት፡ባሰበውልክ ሁኔታዎች እየሄዱ መሆኑንም ተገነዘበ ለራሱ 'አዎ እንደሱ!'አለ እናም ለጥቂት ጊዜ ወደዛ ወደዚ እያለ ጠበቀ ፡
አዎ በዚያ አስፈሪ ለሊት ከጨረቃና ጭል ጭል ከሚሉት ክዋከብት በስተቀር አንዳች ታዛቢ በሌለበት ብቻውን ፡በድፍረት ከዛቤት ለመግባት ቆርጧል ፡ እናም ውሾቹ ዝም ማለታቸውን ሲያረጋግጥ እንደጦጣ እየተንጠላጠለ ቀልጠፍ ብሎ ወደ ጊቢው ገባ ዘበኛው እንደተኛ ነው ውሾቹ ተራርቀው በድካም ተንጋለዋል መርዙ ስራውን እንደሰራ አወቀ ፡ 'እንግዲ መሆን ስላለበት እንጂ ፀቤ ከናንተ አይደለም ብሎ ውሾቹን አልፎ ወደ ሚያምረው ቪላ ተጠጋ እናም ብዙም በማትከብደዋ አነስተኛ መስኮት እጁን ሰደድ በማድረግ ፈተሻት እንደገመተው ነበርና ያለችግር ከፈታት ፡እናም በቀስታ ወደውስጥ ዘለቀ ፡እናም በመጀመሪያ እነዛ ልዕልት ወደመሰሉት እህትማማቾች ክፍል ነው መሄድ ኪኪኪኪ እያንዳንዳቸውን ነው መጎብኘት ኪኪኪኪ መቼም እንግዳ አቀባበሉ አይጠፋቸውም እንዴ ሳኩ እንዴ ምን አባቴ ነው የምሰራው ፡ አለ ለራሱ እናም እንዳለው በመጀመሪያ የቤቱ ታላቅ ወደሆነችው ሮዛ መኝታ ክፍል ዘው አለ በፀጥታ እግሮቿን አጣጥፋ ተኝታለች ፡'ስታምር ' አለ እናም ትቷት ወጣ ቀጥሎ ከሮዛ ጎን ወዳለው ክፍል ቀስ ብሎ ገባ ፡በአልጋው ላይ ሊያና ራሔል ጎን ለጎን ተኝተዋል ብዙጊዜ ራሔል የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንም ብቻዋን መተኛት ከመፍራቷ የተነሳ የቤቱ መጨረሻ ከሆነችው ሊያ ጋር ነው የምታድረው ፡ባለጭንብሉ ፡ለብቻ ለብቻ ነበር መተኛት የነበረባቹ ቲ 'ግን ይህ የማይረባ እንዴት ነው ዘሩ እንዲ የሚያምረው 'አለ እናም ዞር ዞር እያለ ውበታቸውን አደነቀ ፡በመጨረሻም፡ የሊያ ታላቅ የቤቱ ሦስተኛ ልጅ ወደሆነችው ሲፈን ክፍል ገባ ፡እንደገባ ለራሱም ያስገረመው ድንጋጤ ተሰማው፡ሲፈን በጀርባዋ ተንጋላ ነው የተኛችው የለበሰችው ሰፊ ቢጃማ በከፊል ተገልፆ እርቃኗ ይታያል እረዥም ፀጉሯ ወዲያና ወዲ ተበታትኖ በሚያምረው ፊቷ ላይ ሳይቀር ነስነስ ብሏል ፡ባለጭንብሉ ፡ትንፋሹ ፀጥ አለ ለረዥም ደቂቃ በመገረም አያት እናም ቀስእያለ ደመነፍሱን ተጠጋት ....ቀስስ እያለ እያለ.
እየቀረባት ሲመጣ የልብ ምቱም አብሮ ጨመረ ፡እጆቹን በቀስታ ወደ ተራቆተው ጡቷ ሰደድ አደረገው መልሶ በፍጥነት እሳት እንደነካ አይነት ሰበሰበው እንደገና በፊቷ ላይ የተነሰነሰውን ፀጉር ወደጎን ወደጎን እያደረገ አስተካከለው ፡ይህን ሲያደርግ ውበቷ የበለጠ ቁልጭ ብሎ ታየው ከንፈሮቿን መሳም ፈለገ እናም ቀረብ አላት ፡ሲፈን በሆነ ታምር ያወቀች ይመስል ተገላበጠች ባለጭንብሉ በድንጋጤ ወደዋላው አፈገፈገ እንቅስቃሴው ፡የረበሻት ይመስል ፡ከእንቅልፏ ተቀሰቀሰች ፡አይኖቿ ተከፈቱ ፡ፊትለፊት ባለ ጭንብሉን ከለላ ሲፈልግ አየችው፡ሲፈን ከመቅፅበት አልጋው ላይ ያለውን አንሶላ ወደራሷ በመሰብሰብ ቁጭ አለች ፡ሰውነቷ በድንጋጤ ደረቀ፡ባለጭንብሉ ፡ቀጥሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለገባው ፡እራሱን አረጋጋ ፡ቀረብ አላትና ፡ልትጮህ ያሰናዳችውን አፋን በሰፊ መዳፉ በማፈን ፀጥ አደረጋት "ስሚ አንዳች እረብሻ አስነሳለው ብትዪ ሁሉንም ቤተሰብ ችግር ውስጥ ነው የምትከቺው !ገባሽ! ተመልከች እዚች ሽጉጥ ውስጥ አምስት ቀልሃ አለ ለአምስቱ ቤተሰቦችሽ በቂ ነው፡ ዝም ብትዪ ላንቺ ነው የሚጠቅመው!!!"አላት በጭንብሉ ቀዳዳ የፈጠጡ አይኖቿ ውስጥ እየተመለከታት፡ሰውነቷን ብርድ ብርድ አላት መንቀጥቀጥ ጀመረች፡'ማነው !ይህ ሰው ምን ፈልጎነው?እህቶቼ ደና ይሆኑ ?እማሚ እና አባቢስ ውሾቹ እንዴት አስገቡት ?ዘበኛውስ ? በሩስ እንዴት ተከፈተለት?በምን በየት በኩል...?!!'የጭንቀት ጥያቄዎች በተራበተራ አይምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ፡ፍርሃቷ ወደር አጣ፡ባለጭንብሉን አፋን እንዳፈናት አልጋዋላይ ፈርከክ ብሎ ዝም እንድትል ሲያስጠነቅቃት እያየችው ነው ጥቁሩ የሹራብ ጭንብል ይበልጥ አስፈራራት ትዝ አላት ፊልም ላይ ያየቻቸው የመደፈር አደጋዎች በርቀት ትሰማቸው የነበረ የሴቶች ጥቃት ፡እያንዳንዱ ፡ሲታወሷት፡ዛሬ በሷ ላይ ለዛውም በገዛ አልጋዋ ላይ ፡ምን አይነት የቀን ጎዶሎ ነው እዚ ሴጣን ላይ የጣለኝ አለች ስቅቅ ብላ፡፡ባለጭንብሉ ዝም እንዳለች ለመፈተሽ ይመስል ቀስ ብሎ ለቀቅ ፡ሲያደርጋት ፡በተከፈቱት እግሮቹ መሃል ጉልበቷን በማስገባት፡እንትኑን ክፉኛ አገኘችው፡እንደማቃሰት ብሎ ለቋት ወደዋላው በመሸሽ ፡አጉተመተመ ፡ለጥቂት ሰከንድ፡ አፉን ከፍቶ ተሰቃየ ፡ሲፈን እንደምንም እራሷን አበርትታ ከክፍሏ ለመውጣተሸ ወደበሩ

❤22🤔2
ተንቀሳቀሰች ፡ባለጭንብሉ
"ቁሚ የማትረቢ ጨዋታውን አበላሸሺው እንቀሳቀሳለው ብትዪ እተኩሳለው !ተመለሽ አፍሽን ዝጊና ከነበርሽበት ተመለሽ!!"አለ ሽጉጡን ደቅኖ
ሲፈን ወደነበረችበት ተመለሰች፡ይበልጥ እየተንቀጠቀጠች፡ለመነች ፡ባለጭንብሉ ፡የለበሰውን ካፖርት አወለቀው ካወለቀው በዋላ ኪሱ ውስጥ በመግባት ብላስተር አወጣ ብላስተሩን በመፍታት ባጭሩ ቆረጠው፡
"እባክህን ምንድነው የምትፈልገው ፡አንተማነህ ተው እኔ ምንም አልጮህም ተወው ፕላስተሩን.."አለች ሲፈን በልመና
"አሃ ካንቺ ጋር የምስማማበት ምንም ምክንያት የለም ፡የምፈልገውን ላንቺ መንገርም አይጠበቅብኝም !!"አለ በቁጣ እናም የሱሪውን ዚፕ ፈታው ሱሪውን ወደታች ዝቅ በማድረግ ወደሲፈን በመጠጋት"ማንን እንዳስቆጣሽ አየሽ! ተመልከች !ተመልከች! ይህ እራስሽ የፈጠርሺው ግርግር ነው እና ስለዚ እራስሽ ታስተካክይዋለሽ!እይው እይው!"አለ ባለ ጭንብሉ በማስገደድ ፡ሲፈን ፡አለቀሰች ፡እንደመሸሽ እየለች ከአልጋው ኮርነር ተጣበቀች ፡ባለጭንብሉ እይ ምን እነደሰራሽ እያለ ተከተላት ፡አናም እግሯቿን ጎትቶ በመክፈት ወደራሱ አስጠጋት፡ፊቷን በተሸፋፈነው ፊቱ መተሻሸት ጀመረ ለማን ለምን ነካሽብኝ እንደዛ ማድረግ አነበረብሽም አለደጋግሞ ቁረጥ ቁርጥ በማል ድምፅ ፡ሲፈን ከእግሮቿ መሃል የገባውን ሰውነቱን ለመሸሽ ተንፈራፈረች እጆቿን ለመከላከል ወደፊቷ የቀረበውን ጨንቅላቱን ለማራቅ ስትጠቀምባቸው ድንገት ጨንብሉን ከፊቱ ላይ አወለቀችው፡ባለጭንብሉ ካሰበው ቅጣት ሳይደርስ በድንጋጤ ፡ተስፈንጥሮ ተነሳ ፡ሲፈን እግሮቿን በፍጥነት ሰብስባ ፡የባለ ጭንብሉን የተጋለፀ ፊት ላይ አፈጠጠች፡እሱም እንደዛው፡ በጣም ተናደደ ፡ፊቱን ስላየችው፡ እንደሚገድላት ዛተ በቃ፡በዝች የማትረባ ከምጋለፀ ፀጥ አድር ጌያት፡ ወደዋናው አላማይ መጓዝ አለብኝ ፡ብሎ ሽጉጡን በማንሳት፡ፊት ለፊቷ አቀባበለባት፡ሲፈን አለቀሰች መጮህ አማራት፡መልሳ እህቶቿን እንደምታጣ እንዲሁም ወላጆቿን የነገራትን አስታውሳ ድምፀጿን ቀንሳ እያለቀሰች ተማፀነችው፡
"እባክህ አትግደለኝ እባክህ የምትፈልገውን ሁሉ ውሰድ እኔ እረዳሃለው እባክህ!!"
"አይ ፊቴን ማየት አልነበረብሽም ፡ብተውሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም፡አንቺ በሕይወት እድትኖሪ መፍቀድ በራሴላይ ታናዳፊ እባብ የመጠምጠም ያህል አደጋ አለው !ይቅርታ አድርጊልኝ! "አለና ትራስ ይዞ ተጠጋት የመሳሪያውን ድምፅ ለማፈን እንዲ ጠቅመው
ሲፈን እንደ እፃን ልጅ እጇን ዘረጋች "በናትህ እኔ መሞት አልፈልግም እህት የለህም ..በበናት ትህ እእእእ መሞት አአአልፈ ፈልግምም እእእእ እፈራለው መሞ ት እእእእ በፈጣሪ ይ"ቁጭ ብድግ እያለች ለመነች ፡የባለጭንብሉን ቆንጆ እና ጠይም ምንም ወንጀለኛ የማይመስል ፊት፡ እያየች፡
"አይ ነገረኩሽ ባታይኝ ጥሩ ነበር "ብሎ በመጠጋት ትራሱን ወደፊቷ አቅጣጫ አደረገው፡
ምትለው ግራ ገባት በሕይወት ለመትረፍ ምን አይነት የመለመኛ ቃላት እንደምትጠቀም ጠፋት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጣ ተንዘፈዘፈች፡ በዛ በለሊት፡ ምን አይነት ሴጣን ነው፡ እሷን ብቻ መርጦ ሕይወቷን ሊነጥቃት የመጣው፡ ካሁኑ ቤተሰቦቿ ናፈቋት የእንስፍስፍ እናቷ ፍቅር የአባቷ ኮራ ያለ ትእዛዝ የእህቶቿ ውበት ከነሳቃቸው ከነጨዋታቸው እንባዋ የባስ ዱብ ዱብ አለ
"ወንድሜ እባክህ እኔ እኔ.......እእእእ ከደጅ የእግር ኮቴ ተሰማ ባለጭንብሉ ትራሱን አልጋው ላይ ወርውሮ ወደበሩ በመሄድ በሩን ከውስጥ ቀስብሎ ዘጋው ፡እናም ኮቴው እየቀረበ መጣ " እናም ከሲፈን አጠገብ ያለው በር ሲጢጢ ብሎ ተከፈተ ትነሽ ቆይቶ ተመልሶ የመዘጋት ድምፅ አሰማ ቀጥሎ ሌላኛው ክፍል ተከፈተ መልሶም ተዘጋ ፡ቀጥሎ የሲፈን ክፍል ተገፋ ባለጭንብሉ መውጫ ቀዳዳ አማተረ ምንም መደበቂያ አጣ ፡ኮስተር ብሎ ወደሲፈን በማየት አስጠነቀቃት ጠጋብሎም
"አፍሽን ብትከፍቺ እንጨራረሳለን !"አላተ ቀስ ብሎ
"እማዬ ናት ሁሌም ለሊት ላይ ለሽንት ስትነሳ ታየናለች ለዛ ነው በር የማንዘጋው፡የኔበር ሲዘጋ አዲስ ስለሚሆንባት መረበሿ አይቀርም"
"እና ምን ይሁን ነው የምትይው?!"
"ቀስ ብለህ ክፍት አድርገውና ጥግ ላይ ተደበቅ!"
እሺ ብሎ ሊከፍት ሲጠጋ በሩ መንኳኳት ጀመረ ለስለስብሎ ኳኳኳኳኳ ቀጠለ የሮዛ እናት ፡የሲፈን በልተለመደ ሁኔታ በር መዝጋት ደስ አላሰኛቸውሙ ከሮዛ ጀምረው ሁሌም እንደሚያደርጉት ልጆቻቸውን በተራ ተራ አይተው ብርድልብሱን ለበስ አድርገው ነው ወደቀረቻቸው ሲፈን የመጡት በሯ ተዘግቷል
እንዴት............ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ ጨመረ ማንኳኳቱ ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ...
✨ይቀጥላል✨

❤8👍7
📘 የ17 ግመሎች ውርስ… (አስተማሪ ታሪክ)
አንድ ሰውዬ ሲሞት 17 ግመሎች እና ሦስት ልጆች የነበሩት። የሞቱት አባት ኑዛዜ ሲነበብ፦
🐪 የግመሎቼን ግማሽ ለመጀመሪያው ልጄ፣
🐪 አንድ ሦስተኛውን (1/3) ለሁለተኛው ልጄ፣
🐪 የግመሎቹን አንድ ዘጠነኛ (1/9) ለሦስተኛው ልጄ ተናዝዣለሁ” ይላል።
ልጆቹ እጅግ ግራ ተጋቡ! የ17 ግመሎች ግማሽ ለመጀመሪያው ልጅ ይሰጥ ከተባለ... አንዱን ግመል ለሁለት ሰንጥቀው ይካፈሉ?
ይሄንንም ቢያደርጉ እንኳ መፍትሄ አይሆንም፤ ምክንያቱም የግመሎቹ 1/3 እና 1/9 ተብሎ ሲሰላ ግመሎቹ ተቆራርጠው አለቁ ማለት ነው!
🧠 የምሁሩ እና የአዛውንቱ ልዩነት ልጆቹ ለጉዳዩ መፍትሄ ለማግኘት ወደ ከተማዋ የታወቀ ምሁር ዘንድ አመሩ። ምሁሩም በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ካሰበ በኋላ፦
“እኔ በሕይወቴ ቁጥሮችን እንጂ ግመሎችን አካፍዬ አላውቅም። ኑዛዜው በትክክል መተግበር ካለበት ግመሎቹን መሰንጠቅ የግድ ነው” አለ።
ልጆቹ ግን የምሁሩን ምክር አልተቀበሉትም። ይሄኔ አንድ ሰው መጥቶ፣
"ከቁጥር ይልቅ ስለግመሎች የሚያውቅ ሰው ብታማክሩ ይሻላችኋል" አላቸው።
ልጆቹም በሰዎች እያጠያየቁ፣ አንድ እርጅና የተጫጫነው፣ ያልተማረ፣ ግን ከሕይወት ልምዱ ብልህነትን የቀሰመ አዛውንት ዘንድ ሄደው ችግራቸውን ነገሩት።
አዛውንቱ ሰው በቁም ነገር ሳይሆን በፈገግታ፦ “አይዟችሁ አታስቡ፣ ነገሩ ቀላል ነው” አላቸው።
💡 የጥበብ ፍቺ!አዛውንቱ የራሱን አንድ ግመል ለልጆቹ አበደራቸው፤ በዚህም የግመሎቹ ቁጥር 18 ሆነ።
በውሉ መሰረትም፦
ለመጀመሪያው ልጅ: የግመሎቹ ግማሽ (የ18 ግማሽ) = 9 ግመሎች ተሰጡት (ተደሰተ!)
ለሁለተኛው ልጅ: የ18ቱ አንድ ሦስተኛ = 6 ግመሎች ደረሱት (ተደሰተ!)
ለሦስተኛው ልጅ: የ18ቱ አንድ ዘጠነኛ = 2 ግመሎች ተሰጡት (ተደሰተ!)
ድምራቸው ሲታይ፦ 9 + 6 + 2 = 17 ግመሎች ሆኑ!
አዛውንቱ ያበደራቸው አንድ ግመል ሲቀነስ እርሱም የራሱን ግመል መልሶ ወሰደ!
🔑 ዋናው መልዕክት
ተራ ዕውቀት (Knowledge) ተግባራዊ አይደለም፤ ተጨባጭነት ይጎድለዋል። ተራ የቃላት ጨዋታ ነው።
በልምድ የቀሰመ ጥበብ (Wisdom) ግን ወደ መሬት የወረደ፣ ተግባራዊ እና ተጨባጭ ከሕይወት ልምድ የተጨለፈ ነው።
እናም ጥበብ ከዕውቀት ትበልጣለች!

❤10👍2👏2
#ባለ_ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
...የበሩ መንኳኳት ከሚገባው በላይ አሰለቸው ፡ተቅበዘበዘ ፡እቺ ሴትዮ ምንድነው እንዲ ችክ የሚያረጋት ፡በቃ ተኝታለች፡ለምን አትሄድም፡እንዴ በለሊት እየዞረች ምን ያስረብሻታል፡ፀጥ ካለች ተኝታነው ብላ አትሄድም እንዴ!!
ኳኳኳኳኳኳኳ....... ፈጣሪዬ ትዕግስቴን ልታስጨርሰኝ ነው አለ በውስጡ ሽጉጡን በጎን በኩል ከራስ ፀጉሩ ላይ እያሻሸ ፡አልፎ አልፎ ሁሌም ጭንቅ ሲለው እንደሚያደርገው በግራ እጁ ጀሮውን ሳብ ሳብ ያደርጋል፡ የሮዛ እናት ወይ ፍንክች ፡ልጃቸው ሲፈን በሩን የዘጋችበትን ምክንያት ሳያውቁ እንዴት ይተኛል ያሉ ይመስላል ፡አዲስ ነገር ነዋ ፡ኳኳኳኳኳኳ .. ባለጭንብሉ ቱግ አለ ፡ሽጉጡን በበሩ ትክክል ደቀነው፡ሲበሳጭ፡እንዲ ነው፡ለውሳኔ ይቸኩላል፡ ሲፈን በድንጋጤ ቃላት አመለጣት
"በፈጠረህ!"ብላ ለእናቷ ለመከላከል ጮኸች ፡ባለጭንብሉ ክው አለ ወይኔ ይች የማትረባ ፡ብሎ ሽጉጡን አልጋው ላይ በፍጥነት አስቀምጦ ፡ፕላስተር በመፍታት አፏን ደፈነው፡እንደገናም እጅና እግሯላይ በችኮላ በፕላስተሩ አቆላልፎ ጠመጠመባት፡ሲፈን ድምፅ ለማውጣት ሞከረች፡ከደጅ የሮዛ እናት ማንኳኳታቸውን አቁመው ፀጥ ብለዋል ወዴት ገቡ፡ባለጭንብሉ ተጠራጠረ ፡ለምን ዝም አሉ፡የሲፈንን ድምፅ አልሰሙ ሆነው ነው፡ ወይስ ?....
ትንሽ በዚ ሁኔታ ከቆዩ በዋላ "ሲፈን ሲ ፈን"ብለው በሹክሹክታ ተጣሩ፡ባለጭንብሉ እሰካሁን የት ሄደው ነው፡በድንጋጤ ይሆን ዝም ያሉት፡ምናልባት በህልሟ የተናገረች መስሏቸው ይሆን ለማጣራት ብለው....እንደዛ አስበው መሆን አለበት ብሎ ተመኘ ፡ቀስብሎ ጭንብሉን በማንሳት አጠለቀው ሽጉጡን ያዘ እናም በሩን ከፈት አደረገው የሮዛ እናት በተከፈተው በር ዘው ሲሉ ባለጭንብሉ በፍጥነት አናታቸውን በሽጉጡ ጫፍ መቶ ጣላቸው ፡ሴትዮዋ ከአልጋው ጋር ተገጫጭተው መሬት አረፉ ሲፈን የታፈነ የስቃይ ጩኽት አሰማች፡ባለጭንብሉ ወደሴትዮዋ አጎነበሰ፡በዛው ፍጥነት ፡ከደጅ የሚያርበደብድ ወፍራም አስፈሪ ድምፅ ተሰማ
"እንዳትነቀሳቀስ ባለህበት ሆነህ ሽጉጥህን ጣል፡!!"አቶ ይፍሩ ነበሩ የሲፈን አባት የቤቱ አባወራ፡በደንብ የተዘጋጁበት ይመስላል ፡የሮዛ እናት በትክክል የልጃቸው ሲፈንን ድምፅ በትክክል መስማታቸውን፡እና ባለቤታቸውን እንደቀሰቀሱና እንዳዘጋጁአቸው፡ባለጭንብሉ ተረዳ፡በራሱ በሸቀ፡ሽጉጡን ወደጎን ወረወረው ፡አቶ ይፍሩ ግዙፍ እና ደንደን ያሉ የ55አመት ጠንካራ ሰው ናቸው ፡ሽጉጡን ጠጋብለው፡ በእግራቸው በመምታት ወደ አልጋው ስር አስገቡት ባለጭንብሉ ተሰፋ ቆረጠ "ተነስ አንተውሻ እንዴት አባክ አድርገ እዚ እንደገባህ ትናገራለህ፡እገልሃለው!፡ ውጣ !"አሉ በጣም ተናደዋል እንዴት ተደፈርኩ በሚል ስሜት ጨሰዋል፡ባለ ጭንብሉ በተሸናፊነት ስሜት፡አንገቱን አቀርቅሮ፡ወጣ አቶ ይፍሩ ባለቤታቸውን፡ተመለከቱ ለክፉ አይሰጡም፡ወደልጃቸው፡አዩ፡ግን ለጊዜው፡የሚቀድመው፡ የባለጭንብሉ ጉዳይ ነው፡ማነው የላከብኝ፡በቅርቡ በህገወጥ መልኩ አንድ ቢዝነስ ፡ሰርተዋል ከጓደኞቻቸው ጋር፡ግን ለምን ሶስታችንም፡በድርሻችን ፡አልተከፋንም፡አቶ የሱፍ ይሆን፡በጭራሽ፡ጠዋት አግኝቼው ነበር ፡ምንም አይነት ቅሬታም አላየውበት ደሞስ ለምን ቅር ይለዋል አይ አይ እሱ ሊሆን አይችልም ይርጋ ይሆን፡እሱም በድርሻው ተስማምቷል!! አይ ሊሆን አይችልም ይህ የዘረፋ ጉዳይ አይደለም ፡ይሄ ሴቶችን በመድፈር የሚረካ አንድ አለሌ ብቻ ነው፡የገንዘብ ጉዳይ ቢሆን፡የሲፈን ክፍል ምን ይሰራል ፡አዎ ይሄ ሴሰኛ በልጄ ላይ ነው የመጣው እንዴት ቢደፍረኝ ነው አያውቀኝማ!አሉ "አንተ ውሻ ይሄ የፊት ጌጥህን አንሳና በዚ በኩል ሂድ!"አሉት ግቢውስጥ ሲደርሱ ወደ ቀኝ በኩል ካለው በጊቢ ውስጥ እራቅ ብሎ ከሚገኘው መጋዘን እያሳዩት ፡ግቢው እንደዚ ሰፊ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየ መሰለው፡ በራሱ ከሚገባው በላይ አፍሯል የመጣበትን አላማ በመተው፡የተልከሰከሰበትን ሁኔታ ሲያስተውሰው እራሱን ጠላ'፡ምን አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገባውት ፡እኚ ሰውዬ ከገመትኩት በላይ ክፉ ሳይሆኑ አይቀሩም ፡መጋዘን ውስጥ ሊቆልፉብኝ ነው ማለት ነው፡በቃ ጉድ ሆኛለው ፡የልጃቸው ሁኔታ እንኳ አልገረማቸው የናትየው እራሳቸውን ስቶ መውደቅም ቁብ የሰጣቸው አይመስልም የነሱን ደህንነት ሳያረጋግጡ እኔን አንዳች ነገር ለማድረግ ብቻ መቸኮላቸው ፡ጭካኔ ያቸውን ያሳብቃል፡'እያለ በውስጡ እያወራ ፊትፊት ሄዶ መጋዘን መሰሉ ቤት ጋር ደረሰ አቶይፍሩ በጥንቃቄ በሩን ከፍተው ወደውስጥ እንዲገባ አስገደዱት፡ወደውስጥ ሲገባ አይለኛ ቦክስ ሰነዘሩበት ወጣቱ ባለጭንብል ያላሰበው ስለነበር መቋቋም አልቻለም ወደቀ በወደቀበት ደጋግመው ፊት ለፊታቸው ባገኙት ብረት ሰባበሩት ፡ባለጭንብሉ በህመሙ መጠንከር የተነሳ ጮኽ ሁሁታውን አቀለጠው አፉን በቦክስ መቱት ጥርሱ የተነቃነቀ መሰለው፡
"አንተ ሌባ አንተ ሙሰኛ አንተ አጭበርባሪ ሽማግሌ!!"ባለጭንብሉ እልህ ያዘው ለመነሳት ሞከረ እዛው እረግጠው ያዙት"አጭበርባሪ ነው ያልከው ማነው የላከህ ፡ተናገር!!"አሉት አሃ ለልጄ ሳይሆን ለኔነዋ የመጣው ዱላውን አባሱት ፡ባለጭንብሉ በዱላብዛት በደም ተጨማልቆ እራሱን ሊስት ሆነ ያጠለቀውን ጭንብል ከፊቱ ላይ በማውለቅ አዩት ፊቱ ደም በደም ስለሆነ ማንነቱን መለየት አቃታቸው ወደጥግ በመሄድ በሀይላንድ የነበረ ውሃ አምጥተው ፡ፊቱላይ አፈሰሱት፡ውሃው ደሙን እያጠበው ወረደ ፡አሁን ፊቱን በግልፅ ማየት ጀመሩ ፡ይህንልጅ ሰሞኑን አይተውታል የመብራት ቆጣሪያችሁን ለማየት በሚል ሰበብ መጥቶ አዎ በትክክል አይተውታል፡እንደውም፡ እንደቤቱ ትልቅነት አይደለም ፍጆታቹ ብሎም አሰቋቸው ነበር፡አሃ አሉ አሃ ጥናት ላይ ነበርክ፡ልጆቼ ላይ ነው እኔ ላይ አንላቀቃትም፡አሉ አቶይፍሩ
፡ከደጅ "ማነው ማነው እዚ የገባ ሰው አለ !!"እያለ... ዘበኛው ወደመጋዘኑ ገባ "አፈር ጉድጓድ ግባ ቤቴ በሌባ ሲደፈር አንተ ተኝተሃል አንተም ውሾቹም አንድ ናቹ ቀለብ ብቻ!!"አሉ አቶ ይፍሩ "ኧረ ለወትሮ ውሾቹ ኮሽታ ሲሰሙ ይቀሰቅሱኝ ነበር !እእኔ በውነት በዬት አድርጎ እንደ ገገባ እእ ሁለቱም ውሾሾች ሞተዋልእእ !!"አለ እርብትብት እያለ "እነሱ ፍንችር ማለታቸውን ባይ ጊዜ እኮ ነው አንዳች ነገር እንደተፈጠረ በመጠርጠር ግቢውን ስዞር እርሶ ከዚ ነዎት!"አለ እንደጨነቀው አንዴ የወደቀውን ወጣት የት ነበር የማውቀው በሚል ለማስታወስ እየጣረ በሌላበኩል አቶ ይፍሩ የያዙትን በደም የራሰ ብረት እየተመለከተ ገለውታል በቃ አይተርፍም በሚል፡ጨካኔያቸውን እያደነቀ፡"አንት ውሻ ውሾቼን ገድለሃቸዋል ለዚ ጥፋትህ አሰከፍልሃለው!"ብለው ፊቱን ደግመው እረገጡት፡እናም "አንተ የማትረባ ይሄ ነገር ከኔና አንተ ውጪ እንዳይወጣ በጭራሽ ፡ነግሬሃለው ፡ገና ማን እነደላከው ሳይናገር በሕይወት ከዚ መጋዘን አይወጣም ፡በሩን በደንብ መዝጋትህን አረጋግጥ ፡አንተ ጠብደል ከዛሬ ጀምሮ የሱና የሱ ጠባቂ ነህ ፡ለጊቢው ሌላ ዘበኛ እቀጥራለው አንድም ሰው ወደዚ መጋዘን ድርሽ እንዲል እነዳታደርግ ፡አንተ እራስህ በፊለፊት ሳይሆን በዋላበር ነው መውጣት ያለብህ አስታውስ ፡አንዲት ስህተት ባይ ወዳንተ ነው የምዞረው ታውቀኛለህ!!"አሉ አቶ ይፍሩ በጭካኔ ፡ዘበኛው ክንዴ ደጋግሞ እሺ እሺ አለ አቶ ይፍሩን በፍርሃት እያየ እናም እሳቸውን ለማስደሰት ይመስል፡ባለጭንብሉን ሆድ ሆዱን እረገጠው ወጣቱ አጥወለወለው ማስመለስ ጀመረ ፡እንደማሳል አለ ፡ አቶ ይፍሩ "ይበቃል ትፋቱን ሲጨረስ ወደጥግ ወስደ አስረ አሰቀምጠው "ብለው

❤14👍1
ማስጠንቀቂያውን አብዝተው አስተላልፈው ወደነ ሲፈን ተመለሱ:: ማነው የላከብኝ? ማን.. ማን.......
=======
የጠዋት ፀሐይ ከወደ ምስራቅ ብቅ እያለች ነው ፡ሰውም የተለመደ ስራውን ለማከናወን ነቃ ነቃ እያለ ነው ፡እትዬ ፅጌም በላስቲክ ቆሻሻ ይዘው ወደገንዳው በመድፋት ወደቤታቸው ያገኙት የጎረቤት ሰው ደና አደራቹ እያሉ ሰላምታ እየሰጡ ተመለሱ ፡ወደ ውስጥም በመግባት
"ኤዶም ኤዶሜ አንተ ተነስ አስኪ ይበቃል ወንድምህንም ቀስቅሰው፡!"እያሉ ተጣሩ ከመንትያ ልጃቸው አንዱን "እእ እሺ እማ እየተነሳው ነው "አለ ኤዶም እትዬ ፅጌ እጃቸውን እየተጣጠቡ ያ እብድ ወንድምህ ምነው ዛሬ እንቅልፋም ሆነ!"አሉት ኤዶም መጥቶ ከፊታቸው ሲቆም "አይ አይ እማዬ አዳም ትላንት ወደ አምስት ሰአት አካባቢ እነ ብሩክ እየጠበቁኝ ነው ብሎ ላንቺ እንዳል ነግርሽ አስጠንቅቆኝ ነው የወጣው ስገምት ብሩክ ጋር ነው ያደረው "አለ ኤዶም "ኧረ እንዴት በል ደውልለት ከሆነም "
እሺ ብሎ ሞባይሉን አንስቶ ደወለ ፡ብሩክ አንስቶ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ "አዳም አነተጋር ነኝ ብሎነበር ?"
"ኧረ በጭራሽ አላገኘውትም"
"እውነት"
"አዎ እኔጋር አልመጣም"
"እሺ ብሩክ ደናዋል"ብሎ ዘጋው ወደናቱ ተመለከተ፡እናት ተጨነቀች
"ለምንድነው በራሱ ስልክ የማትደውለው "
"አይሰራም"አለ ኤዶም ፍርሃት ፍርሃት እያለው
"ልጄ የፈለገ ቢያመሽ አድሮ አያውቅም አባትህ ጋር ደውል!"
"አባባ ወጥቷል እንዴ?ግን እማዬ ይቅር ይደነግጣል ትንሽ እንጠብቅ !"አለ ኤዶም፡
እትዬ ፅጌ ተረበሹ መንትያው የት ነው አዳም የት ነው ያደረው እንዴት በለሊት ወጣ.. የት ነው መንትያው?...እትዬ ፅጌ ግራ ግብት ብሏቸዋል ፡አንዴ ይቆማሉ አንዴ ይቀመጣሉ፡ይወጣሉ ይገባሉ፡መላ አተዋል ፡'የት ገባ ይባላል !በጨለማ ሲጓዝ አንዱ ደፍቶብኝ ይሆን !እንደው ምን አድርገውት ይሆን፡እንዴት በጤናው አድሮም ቀኑን ሙሉ ሳይመጣ ይቀራል፡አንዳች ነገርማ አለ!'እያሉ በጭንቀት ያምሰለስላሉ ፡ኤዶም ቆይቷል ከቤት ከወጣ ወንድሙን ፍለጋ ፡የአዳም ጓደኞችን ሁሉ ካሉበት ድረስ እየሄደ ፡ጠይቋል ግን አንዳቸውም አየነው አላሉትም፡ ኤዶም ገራገር ቢጤ ነው፡ በዛላይ ብዙም ከሰው ጋር አይቀርብም፡ ትንሽ ትንሽም አይናፋርነት አለችበት፡ ከወንድሙ አዳም አንፃር፡ተቃራኒ ነው፡ አዳም ሁሌም ሊያበሳጨው ሲፈልግ፡ 'አንተ ጅል፡እኔና አንተ አንድ ቦታ መሰራታችንን እጠራጠራለው፡መልክህ እኔን ከመምሰሉ ውጪ በጭራሽ ውስጣዊ አሰራራችን ይለያያል!'ይለዋል ፡ኤዶም ለሱ መልስ ሳይሰጥ
'እማዬ አየሺው እንዴት እንደሚናገረኝ ይሄ ስረሃት አልባ ልጅሽ፡አንቺ ነሽ እያቀበጥሽ ፡እንደፈለገ እንዲሆን የምታደርጊው፡ አፉን አዘጊልኝ አለበለዚያ ...!'ይላል ወደ እናቱ እያየ አዳም በማልመጥ
እያሽካካ'ኧረ ሼባው አልቀረቦትም ልታስፈራራኝም ያምርሃል !' ይለዋል ፡ኤዶም እንዲም ሆኖ ግን፡መንትያውን ከልቡ ነው የሚወደው፡ ለዛም ነው፡ብዙ ችግሮቹን የሚሸፍንለት ፡ሲመሻሽ ተነስቶ መውጣቱን ከቅርብጊዜ ወዲ የተለመደ ቢያደርገውም፡ ኤዶም ጨርሶ ለወላጆቹ ነግሮ አያውቅም፡ሊነጋጋ ሲል ሲመጣ፡ቀስብሎ በር ከፍቶ ያስገባዋል፡ ዛሬግን አዳም አልመጣም፡ ስልኩ እንኳ ዝግ ነው፡ኤዶም የት ብሎ እንደሚፈልገው ግራ ገባው እሱ የሚውልበት አይውል፡ እንዲው ቢጨንቀው መንገድ ለመንገድ ሲዞር ውሎ ወደቤቱ ተመለሰ ፡እትዬ ፅጌ ኤዶም ሲገባ ብድግ ብለው ቆሙ "ኤዶሜ ምንም አላገኘህም!አየው የሚል ጠፋ ልጄን? ነው የደበከኝ ነገር አለ እባክህ !" ብለው አስጨነቁት
"እባክሽ ፅግዬ፡ልጄን አታስጨንቂው፡ኤዶም አዳም ከሚውልበት አይውል፡ደሞስ አንድ ቀን ቀረ ብለሽ፡ምን እንዳይሆን ነው ወንድ ልጅ አደል እንዴ፡እስኪ ተረጋግተን እንጠብቅ!" አሉ
የመንትዮቹ አባት አቶ አይሉ "አንተ ዝም በለኝ መጥተህ አንድ መፍትሔ ታመጣለህ እላለው እዚ ተጎልተህ ምን እንዳይሆን ነው ትላለህ እሬሳውን እስኪሰጡኝ ነው የምጠብቀው !"
"እባክሽ ፅጌ ተይ ካልሆነ ካልሆነ ነገ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ አመለክታለው!"አሉ አቶ አይሉ ለሚስታቸው እየተጠነቀቁ፡ "ኧረ እንዴት ልሁነው ልቤ አንዳች ነገር እንዳለ ነው የሚነግረኝ"አሉ እናት ሆዳቸውን ጭምቅ እያደረጉ፡ኤዶም በናቱ ሁኔታ አዘነ ሄዶ አቀፋቸው"እማ ይመጣል አይዞሽ ፈጣሪ ያውቃል !"አለ ፡ግን ይህን ይበል እንጂ ውስጡ ፈርቷል፡ይሄ በድብቅ በለሊት የመውጣቱ አባዜ፡አንድ ቀን ችግር እንደሚያመጣ ጠርጥሮ ነበር፡ በራሱ አዘነ ይህን ሁኔታ ለወላጆቹ ነገሮ ማስቆም ነበረበት፡የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው፡እራሱንወቀሰ የኔ ስህተት ነው፡አለ፡ኤዶም
"እንደው አይልዬ ለምን አሁኑኑ ከኤዶሜ ጋር ፖሊስ ጣቢያ ሄዳቹ አታመለክቱም?!" አሉ እናት
"አይ ፅግዬ እነሱም እኮ አካሄድ ይኖራቸዋል ዛሬን አድረን ነገ ሁኔታውን አይተን ይሻላል እሺ በይኝ ፅግዬ እናቴ!"አሉ አቶ አይሉ ሚስታቸውን በፍቅርና በጨንቀት እያባበሉ ሚስት ባይዋጥላቸውም እሺ አሉ ፡እናም እጥፍጥፍ ብለው ዱካ ወንበር ላይ ተቀመጡ ፡ልጄ እምን ውስጥ ገብተህ ይሆን ...ልጄ.....አዬ ጉዴ ....ብቻ ክፉ ነገር አታሰማኝ... ፈጣሪዬ ....ፈጣሪዬ.......እህህህ

❤16👍5
በዚች ሰፊ ዓለም መሄጃ ሲታጣ ያልጠበቅነው ችግር በድንገት ሲመጣ እንዳሰብነው ሳይሆን ነገር እና ዓለሙ ትርጉሙ ሲጠፉ የመኖር ጣዕሙ እውነት ነው ይጨንቃል ግን እግዚአብሔር ያውቃል?
🔘በረከት ዘውዱ🔘
🔘በረከት ዘውዱ🔘
❤5👍1🥰1