Atrafi Solution / አትራፊ
15K subscribers
302 photos
31 videos
2 files
276 links
እናሳድጎታለን !
Download Telegram
ሰላም ለእናንተ ይሁን ።
በአትራፊ የቤት መፍትሄ የ3ኛ ዙር ቤት ተመዝጋቢዎች የመመስረቻ ጉባኤያችንን ቅዳሜ ሐምሌ 15/2015 በካፒታል ሆቴል ውስጥ አድርገናል ።

የመስከረም ፀሐይ ከመውጣቱ በፊት የመሬት ባለቤት መሆንና ሁለት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የቤት ባለቤት መሆን ከፈለጉ በቀጣይ ሊንክ ባለው ፎርም ይመዝገቡና ፣ ግራ ቀኝ ሳይሉ አዲስ ዓመትን በስኬት ይጀምሩ ።

https://forms.gle/6ugckcQUGkBHcQYv7
👍2
አቢሲንያ ባንክ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

ሰላም ለእናንተ ይሁን ።
በአትራፊ የቤት መፍትሄ የ3ኛ ዙር ቤት ተመዝጋቢዎች የመመስረቻ ጉባኤያችንን ቅዳሜ ሐምሌ 15/2015 በካፒታል ሆቴል ውስጥ አድርገናል ።

የመስከረም ፀሐይ ከመውጣቱ በፊት የመሬት ባለቤት መሆንና ሁለት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የቤት ባለቤት መሆን ከፈለጉ በቀጣይ ሊንክ ባለው ፎርም ይመዝገቡና ፣ ግራ ቀኝ ሳይሉ አዲስ ዓመትን በስኬት ይጀምሩ ።

https://forms.gle/6ugckcQUGkBHcQYv7
15👍4
ስኬት ለራቃራቃችሁ
ኑሮ ኡኡኡ ላስባላችሁ
ተስፋም ለራቃችሁ

ምን አስባችሁ ነው ግን በዚህ ሙድ መኖር የተመቻችሁ ?

አረ ማርሽ ቀይሩ ወይ ቦታ ልቀቁ ?
ዝም ብሎ ያለስኬት መኖር አይደብርም ?

እና ምን እናርግ ብለህ ትጠይቀኝ/ቂኝ ይሆናል
መልሱ እንዲ ነው ።

እንዴት ነው ችስታነት ተመችቶካል ?
እንዴት ነው ማማረር ተመችቶካል ?
እንዴት ነው ከሰው በታች መሆን ተመችቷችዋል?
ብዬ እኔም እጠይቅካለው ?

መልስ አጣው እንጂ እንደ አንተ ጠያቂ መች ጠፋ የምትለኝ ከሆነ ?

ሀብታምነት በነፃ አይገኝም  😂 ከፍለክ ውሰደው ፤
ደስ ይበልህ ዛሬ የቦነስ ቀን ነው ሀብታምነትን እንካ በነፃ !

መጀመሪያ ድህነት ምርጫ ነዉ ፤
ለዛ ነዉ ደሃ የሆንከው ፤
መቼም አታፍርም ሀብታም ለመሆን ልስረቅ ትል ይሆናል ።

አጨበጨብኩልህ ስረቅ እዛዉ ቂሌንጦ ጊዜ ካለኝ መጥቼ እጠይቅካለው ።

እኔን ከጠየከኝ ስኬት እንደዚህ ነዉ ።፦
የሚያዉቁት ሰዎች ድብቅ ስላረጉት ዋጋዉ ዉድ ነዉ።

እንደ እኛ ያሉ ደጋጎች ግን ሁሉም ሰዉ እንዲሳካለት ስለሚፈልጉ በነፃ ይለግሱካል ።

የመጀመሪያ  የስኬት መስፈርት ከራስክ ጋር ታረቅ አንተ ፦ አንተ ብቻ ነክ ፤ ሰዎችን ሌሎችን ልትመስል አትችልም ።

ሁለተኛዉ ደሞ .........
👍32🔥54💯4😱3🎉3
ሁለተኛዉ የስኬት መንገድ መቼም እስክታነቡ ሆዳችሁን ቆርጦት ይሆናል  ።

እዉነት ነዉ ማን ስኬትን ይጠላል ?
እነዛ ከወር እስከ ወር ከዓመት እስከ ዓመት ፈልሰስ ብሎ መኖርን ማን ይጠላል ?

ክራይ መጣ አልመጣ ፣ ግብር ጨመረ ቀነስ ፣ ትምህርት ተወደደ ረከሰ ብሎ ሳይጨነቁ መኖርን ማን ይጠላል ?

ሁለተኛዉ ጋር ከመግባታችን በፊት ግን ራስን መሆን በደንብ ገብቶናል ?

ራስን መሆን ማለት ሰዉን በፍጹም አለመምሰል ማለት ነዉ ።
ሰዉን አለመምሰል ሲባል ቡዙዎች የማናስተዉላቸዉን ነገሮች እንመልከት :-

አለመምሰል ማለት አለመኖር ማለት ነዉ ። ስንኖር  ግን ማንን ነዉ የመሰልነዉ ?
ማንን ነዉ የሆነዉ ብሎ መጠየቅ ? ደሞ የአባት ነዉ ።

በሌላዉ መልካም ሰዎችን መምሰልም እንዳለም አንርሳም ማለት ነዉ  ፦

አንድ መንፈሳዊ አስተማሪ የሚለዉ ነገር አለ
አስተማሪክ የገባበትን ትገባለህ ፣ የሆነዉን ትሆናለህ ይላል ።

ያዉ ሲኦል ከገባ ወይም ገነት ትከተለዋለህ ለማለት ፈልጎ ነዉ ።

ወደ ምድሩ ሀሳብ ስንመልሰዉ የምትከተለዉ መምሰል የፈለከዉ ሰዉ የሆነዉን ትሆናለህ ።

ለዛ ነዉ ባደጉት አገሮች መካሪ (mentor) የሚያረጉ ሰዎች በብዛት የምናየዉ ፦

➯ የምትሰማዉ አማራሪዉን ነዉ ? ታዲያ አንተ ምን እንደትሆን ትጠብቃለህ ?
➯ የምታየዉ የጠፋ ፣ የፈረሰ ፣ የወደመ ነዉ ? ታዲያ አንተስ የምታየዉን ላለመሆን ምን ማረጋገጫ አለክ ?
➯ ህይወት ተመሳሳይ ላባ ያላቸዉ ወፎች አብረዉ እንደሚበሩት አይነት ነች ።

ወዳጄ ራስክን መሆን ማለት ?
➯ ከፍ ካሉት ጋር አብረህ መብረር ማለት ነዉ
➯ ከአመስጋኞች ጋር በምንም ሁኔታ ዉስጥ አብሮ ማመስገን ነዉ
➯ ከጨለማ ዉስጥ ብርሃንን ማየት ነዉ
➯ እግርና እጅ ለሃሳብ እንደሚገዙ አዉቆ ሀሳብን ለበጎና ለቀና አመለካከት ብቻ ማስገዛት ነዉ ።

ሁለተኛዉ ደሞ .......
👍163🔥2👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ራስን መሆን ቀለል አርገን የምናልፈዉ ተራ ሃሳብ አይደለም ።

እስቲ ከላይ በቪዲዮ ያለዉን እንመልከት 👆👆👆
መጀመሪያ የተወሰኑ ሰዎች ሆን ብለዉ ድምጽ በጨወ ቁጥር እየተነሱ ይቀመጣሉ ።

አንድ የገባች እንግዳ እነሱ ያረጉትን በደመ ነብስ ስትከተል ይታያል ፤
እሱ ብቻ ሳይሆን የሚገርመዉ ከሷ በኋላ የሚመጡትን ሰዎች እንዴት ተጽህኖ እንዳሳረፈችባቸዉ እና ለማይረባ ድምጽ ተገዝተዉ ቁጭ ብድግ ሲሉ ይታያል ።

እስቲ ራሳችንን እንመልከት ።
➯ ሀገራችን ላይ ያለን አመለካከት እንዴት ነዉ ?
➯ ስራችን ላይ ያለን አመለካከት እንዴት ነዉ ?
➯ መንፈሳዊ ህይወት ላይ ያለን አመለካከት እንዴት ነዉ ?
➯ ለመሐበራዊ እሴት ያለን አመለካከት እንዴት ነዉ ?

☑️ እስከ አሁንም የእናት የአባቴ ወግ ዉስጥ ነህ ?
☑️አባትህ ሲማረር ኖሮ ኖሮ ምን ጠብ ሳይልለት እንዳለ ወይም እንደሞተ እያወክ አሁንም አንተ በእሱ ሙድ ነህ ።
☑️ አገሬ ከሌላዉ አለም የተለየች ነች ብለህ የሌላዉን አለም ወግ ፣ ስልጣኔ  ፣ መንፈሳዊ ህይወት ሲያሻህ 666 እየለጠፍክ ሲያሻህ የባህር ማዶ ወግ መጤ እያልክ እያጥላላህ አንተ አሁንም በጭቃ ቤትህ ዉስጥ ነህ ?

እኔ ለአንተ ያለኝ ምክር በግ አትሁን ነዉ ።
አብዛኛዉ ሰዉ ሰለተስማማበት ነገሩ ልክ ነዉ ማለት አይደለም ።
የመገናኛ ታክሲ ይዘህ ቦሌ ለምን አልደረስኩም አይባልም ፤ አስተሳሰብክም ዛሬ ላይ ያደረሰህ ታክሲክ ነዉ ።

ራስን መሆን አንዱ ፦
የሰዎችን ፤ የአካባቢን ፤ እዉነት የሚመስሉ ግን አላስፈላጊ የሆኑ አመለካከቶችን አዉልቆ መጣል ነዉ ።

አትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ነን ።
ከፍ ለማለት ከፈለጉ ብቻ ይቀላቀሉን
0903717173 / 0926090971
👍236🙏3👏2🔥1😱1
ራስን መሆን ብዙዎቻችሁ ወዳችሁታል ።

አንድ የትም የማይገኝ ስፔሻል ቲፕ ጣል ላርግላችሁ ።

ራስ መሆን ውስጥህ ካለዉ ማንነትህ ጋር መስማማት ነዉ ።

እንዴት ካልክ ፦
፦ ጠዋት ልነሳ ስትል ቆይ ብርድ ነዉ ትንሽ ተኛ የሚልህ
፦ አዋጭ ስራ ነዉ ልግባበት ስትል ፦ አረ ተረጋጋ ብትከስርስ ፣ ሰዉ ቢስቅብህስ ፣ እነ እንትና የት ደረሱ የሚልህ ።

ስሙም ስምህ ነዉ ፣
መልኩም መልክህ ነዉ ፣
አንተን ራስህን ከምታዉቀዉ በላይ ያዉቅካል ።
ካንተ ጋር ተወልዶ ካንተ ጋር አርጅቶ መቃብር አብሮክ ይወርዳል ።

ፈረንጆቹ subconscious mind ይሉታል ።

ወይም እንዲህ በጥሩ ስራዉ ልትረዳዉ ትችላለህ ፦

፦ መኪና ስትነዳ ከየት ተነስተህ የት መድረስህን ሳታዉቅ የሚነዳልህ ማለት ነዉ ።
፦ ምግብ በልተህ ከሰዉነትህ አስፈጭቶ በደም አርጎ ሙሉ ሰዉነትህ የሚያዳርስል ማኔጅመንቱ በለዉ ።
፦ መተንፈስህ ሳታዉቅ አስተንፍሶክ ኦክስጅኑን ከተነፈስከዉ ላይ ወስዶ ለሰዉነትህ ህይወት የሚሰጠዉ በለዉ ። ሌላም ብዙ ....

ይህ አንተ ትኩረት የማትሰጠዉ ማንነትህ አንተ ፦
ሀብታም ሆንክ ደሃ ፤
ጀግና ሆንክ ፈሪ ፤
የተማርክ ሆን ፊደል ብርቁ ፤
ዴንታዉ አይደለም የእሱ ተልዕኮ አንተን በህይወት አስቆይቶ የተቆረጠልክን ቀን እንድትኖር ማረግ ብቻ ነዉ ።

ይሄን ማንነትህን ማወቅ ትልቁ የስኬት ቁልፍህ ነዉ ።

እንቀጥላለን ።

አትራፊዎች ነን ፦
ተልእኮአችን ወደ እኛ የመጡትን ሀብታሞች እና ሃያሎች አርጎ የገንዘብ ችግራቸዉን በማትረፍረፍ መቀየር ነዉ ።
0903717173 / 0926090971
👍196🥰3👏3
👇👇👇
👍52
እንኳን ደስ አላችሁ ።

ለአትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ስታፍ አባላት በሙሉ በዛሬዉ ለት ቦርዱ በወሰነዉ ዉሳኔ መሰረት የወራዊ ደሞዝ ላይ 50% ጭማሪ በመደረጉ ሁለችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ።
ለተገኘዉ ትልቅ ስኬት እና ትጋት የእናንተ ድርሻ ታላቅ መሆኑን ተገንዝባችሁ ፤ በዚሁ መሰረት በትጋት መጪዉን ዓመት አባላትን በማስደሰት ፣  ከብድር ከፍተኛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና በቤታቸዉ (በአትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ) እንዲበለጽጉ  እንድታግዙዋቸዉ ስል አሳስባለዉ ።

መስራች እና ፕሬዝዳንት
ቴዎድሮስ ኃይሉ ወልዴ
👍3317👏5🥴5
ከስኬት መንገዶች አንዱ እራስን ስለመሆን በስሱም ቢሆን ተነጋግረናል ።

ቀጣዩን ደሞ እንመልከት ፦

ለምን ተወለድክ ?
ለምን ወደዚህ ዓለም መጣክ ?
አሁን በዚህ አለም ላይ ምን እያረክ ነዉ ?
መሞትህ አይቀር ከሞትክ በኋላስ ያንተ ነገር እንዴት ነዉ  ?

እኔ የዚህ ጽሑፍ ፀሐፊ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ከማምንበት እና የህይወቴ መርህ ከሆነዉ ከክርስቶስ ስለምነሳ ፤ ምን አልባት ነገሩን ወደ መንፈሳዊ እንዳትወስዱት እና ሳይድ እንዳትከቱት ቀድሜ አሳስባለዉ ።

👉 ለስኬት አንዱና ወሳኙ ቁልፍ ነገር ሰዎች እልማቸዉን እና ሃሳባቸዉን እንዲያሳኩ መርዳት እና መቻል ነዉ ።

👉 ለዚህ ደሞ ከእምነታችን ፈፃሚ ከክርስቶስ መዉሰድ እንችላለን እሱ በሚደነቅ ብርሃን እየኖረ ሳለ በበረት ለመመወለድ ደግሞ አላሰበም ።

👉 መላህክት በፍጹም ፍርሃት እየታዙለት እየኖረ ሳለ እናቱን ለመታዘዝ ዝቅ ማለት ከክብር መዉረድ አልሆነበትም ።

👉 ከሁሉም በላይ ሞትን ድል አርጎ ሲነሳ ለወጉት እና ለገደሉት ሁሉ የዘላለምን ህይወት ሲሰጥ ፍጹም የፍቅር ጥግ አይተናል  ።

እንመለስ

በዚህ በመገባደድ ባለዉ  ዓመት ላይ ምን ያህል ሰዉ ህልሙን እንዲያሳካህ ረዳክ ?
ምን ያህል ሰዉን ከህልሙ ጋር እንዲጨባበጥ አረክ ?
በፍጹም ቅንንነት ምን ያህሉን ማህበረሰብህን ከፍ እንዲል መሰላል አቀበልክ ?

ሰዎችን እልማቸዉን እንዲያሳኩ እና ከፍ እንዲሉ ማረግ ዋናዉና በረከት ያለዉ የስኬት መንገድ ነዉ ።

የእኔ እራሴን ከመሆኔ በተጨማሪ ሰዎችን ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ ማረጌ ትልቁ የስኬቴ ቁልፍ ነዉ ፣ አዲሱንም ዓመት ከዚህ በተሻለ በግልም በተቋምም እቀጥላለዉ !!!

እርሶስ ???

የሚያግዞ እና የሚደግፍዎ ወንድምም ተቋምም ያስፈልጎታል ዛሬዉኑ አትራፊን ይቀላቀሉ ።

0903717173 / 0926090971
👍14🔥9👏5🙏3💯2😱1