Atlas College Wolkite campus
1.47K subscribers
1.03K photos
12 videos
414 files
96 links
College information set
Download Telegram
ሚያዝያ 11/2016

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር  ዶ/ር አብይ አህመድ ከመላው የጉራጌ ህዝብ ጋር  ለመወያየት ነገ ቅዳሜ 12/08/2016 ዓ.ም የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ወልቂጤ ከተማ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የጉራጌ ማህበረሰብ በሚኖርበት  ቦታ ሁሉ አብሮ እና ተቻችሎ በሰላም መኖር የሚችል  ታታሪና ስራ ወዳድ ብቻም ሳይሆን አኩሪ የሆነ   የእንግዳ አቀባበል ባህል አለው።

ይህንን አርአያነት ያለው የእንግዳ አቀባበል ባህሉ ይበልጥ ደምቆ በሚያሳይ መልኩ  አክባሪው የሆነውን መሪው ለመቀበል ሁሉም በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል።
በ2016 በጀት ዓመት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ዬምዘና ማዕከላት  ተመዝነው ብቁ የሆኑና ለብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ የወሰዱ ተመዛኞችን መረጃ ትክክለኛነት ከዚህ በታች ባለው ዌብሳይት እየገባችሁ ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
http://www.cersocaa.gov.et
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው  ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5  ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ  9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ  6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።
ለአዲስ አበባ (6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ) ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች አጭር መረጃ

📄የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም ይሰጣል(ፈተናው የ8ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

📄የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል!!(ፈተናው የ6ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

📄የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በአዲስ አበባ   በበይነ መረብ (Online) ብቻ በተመረጡ ት/ቤቶች ይሰጣል::

📄የ12ኛ ክፍል(Social )ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም በተመረጡ ት/ቤቶች  ይሰጣል::
(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ ክፍል  በነባሩ ስርዓተ ት/ት(ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ) እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት እንዲሁም ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ት/ት  ይሸፍናል

📄የ12ኛ ክፍል(ተፈጥሮ ሳይንስl)ፈተና ከሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም በተመረጡ ት/ቤቶች   የሚሰጥ   ይሆናል(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ ስርዓተ ት/ት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይሸፍናል

📄ተማሪዎች ይህንን መረጃ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አንድታረጉ::

ትምህርት ሚኒስቴ
ቀን፡ 3-9-2016 ዓ.ም

ማስተካከያ

ለአንደኛ ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዓመት የዲግሪ ፕሮግራም የርቀት (Distance )ተማሪዎች በሙሉ ፡-

ጉዳዩ፡ የሦስተኛ semester የምዝገባ ቀን ን ይመለከታል

ከላይ በተገለፀው መሠረት የእናንተ የምዝገባ ቀናት ሀሙስ የግንቦት 01-9-2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 10-9-2016 ዓ.ም እንደሆነ ከዚህ ቀደም ባወጣነው ማስታወቂያ  ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሀሙስ ቀኑን ሙሉ ምንም አይነት  አገልግሎት መስጠት ስለማንችል ግንቦት   05-9-2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 12-9-2016 ዓ.ም እንዲትመዘገቡ በአክብሮት ማሳወቅ እንፈልጋለን ፡፡

ማሳሰብያ

ከላይ ከተገለፀው የምዝገባ ቀናት ውጭ የሚመጣ ሰልጣኝ ሊሰናገድ የሚችለው አሳማኝ ምክንያት ሲኖረው ብቻ መሆኑን እያሳወቅን በወጣላችሁ የጊዜ ሰሌዳ ( Schedule ) መሠረት እንድትመዘገቡ በዲጋሚ እናሳስባለን፡፡ የምዝገባ ክፍያ ከፍሎ ያልተመዘገበ ሰልጣኝ ክፍል ገብቶ መማር አይችልም ! ብማር እንኳን እንደተማረ አይቆጠርም ፡፡


ከ ኮሌጁ ሬጂስተራር ቢሮ !!!
            
ቀን፡ 03-09-2016 ዓ.ም

ለዲግሪ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ፡

ለኮሌጁ summit የሚታደርጉት Research ሁለት copy መሆኑን እየገለፅን ለኮሌጁ ከማስገባታችሁ በፍት አድቫይዘራቹን ማስፈረም እንዳለባችሁ ማሳሰብ እንፈልጋለን ፡፡

ኮሌጁ !
ቀን: ግንቦት 04, 2016 ዓ.ም
እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
  የምረቃ ቀን ስለመወሰን ከሐምሌ 13 - 2016 ዓ.ም መሆኑን እዉቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ማስታወቂያ
የ2016 ዓ/ም የዲግሪ እና TVET(ዲፕሎማ ) ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
1ኛ.ሙሉ የትምህርት ክፊያ ጊዜ የሚጠናቀቀው  እስከ  ግንቦት 25 ብቻ መሆኑን
2ኛ.ዉጤት ላይ ችግር ያለባችሁ ተማሪዎች (ፈተና ያመለጠባችሁ) እስከ ግንቦት 15  ብቻ እንድታመለክቱ
3ኛ. የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፍ(Research )ያላስገባችሁ እስከ ግንቦት 10 ገቢ እንድታደርጉ ።
በጥብቅ እናሳስባለን ።

ማሳሰቢያ :- የተገለፁትን ተግባራዊ ያላደረገ ተማሪ ለሚፈጠረው ችግር ሙሉ ሀላፊነት እራሱ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን ።
ቀን፡ 05-09/2016 ዓ.ም
     ማስታወቂያ
አትላስ ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጁ የዲግሪ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ :-
  👉ከግንቦት 06-09-2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 20-09-2016 ዓ.ም ድረስ ፕሮፖዛል እንዲታስገቡ እያሳወቅን ከላይ ከተጠቀሰው ቀናት በኃላ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ፡:

ማሳሰቢያ :- የተገለፁትን ተግባራዊ ያላደረገ ተማሪ ለሚፈጠረው ችግር ሙሉ ሀላፊነት እራሱ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን
በቀን 08/10/2016 Research የሚገባበት ቀን ስሆን 15/10/2016 Defense እንዲሁም ሐምሌ 13/11/2016 graduation (ምረቃ) ስለሆነ እንድትዘጋጅ ከወዲሁ እናሳስባለን
ቀን፡ 08/09/-2016 ዓ.ም
           ማስታወቂያ
ዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ፡
በቀን 17/09/2016 ዓ/ም የምርቃት ፎቶ ስለምትነሱ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ እንድትጠባበቁ ከወዲሁ እናሳስባለን ፡፡
                👉ማሳሰቢያ
ፎቶ ለመነሳት ለሚትመጡ የኮሌጁ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ፡
መጽሔት ላይ ለማስፈር የሚትፈልጉትን የራሳቹን የመጨረሻ ቃል / last word  ይዛችሁ እንድሁም  ከራሳችሁ ፎቶ ስር እንዲቀመጥላችሁ የሚትፈልጉትን Last  word ፎቶ ለመነሳት ስትመጡ ፅፋችሁ ይዛችሁ እንዲትመጡ እናሳስባለን ፡፡

የተመራቂ ተማሪዎች አስተባባሪ ኮሚቴ
ALL TVET  PROGRAM TENTATIVE Exam SCHEDULE
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።

2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር