ASRAT MEDIA HOUSE
104 subscribers
374 photos
2 videos
4 files
47 links
ይህ አስራት ሚዲያ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
በዚህ ቻናል ወቅታዊ እና አሰተማማኝ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡


አስራት ሚዲያ የእናንተው እውነኛ ድምፅ !


@Asratmediahouse
Download Telegram
<<የአማራ ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ካልቆመ ከምርጫው እራሳችንን እናገላለን>> ዕጩዎች
አሥራት ቲቪ
ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም
በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሸዋ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ዶ/ር ደረጀ ተክለማርያም እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የሚወዳደሩት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ከዕጩነት እራሳሸውን ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ።
ዕጩዎቹ በሁሉም መለኪያዎች ቢመዘን ሚዛን የሚደፋው ጨዋውና አስተዋዩ የአማራ ህዝብ የ <<አትግደሉን፣ ጭፍጨፋውን አቁሙልን፣ በሠላም እንኑር>> እና መሰል ጥያቄዎቹን በሰለጠነ መንገድ ገልጿል፤ እየገለጸም ይገኛል ብለዋል።
አየተጠየቁት ያሉት ሰላማዊ ጥያቄዎች የእኛም ጥያቄዎች ናቸው:-
1. በአማራ ላይ የሚሰነዘረው መንግስታዊ ጥቃትና ዘር ማጥፋት የማይቆም ከሆነ፣
2. የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች ለፍርድ የማይቀርቡ ከሆነ፣
3. በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በአማራ ላይ የተፈጸመው ዘር ማጥፋት በገለልተኛ አካል የማይመረመርና ተገቢው ካሳ የማይከፈል ከሆነ፣
4. በፌደራል የፍትህ፣ የጸጥታና የመከላከያ ተቋማት ሪፎርም አማራን በሚገባው ልክና አግባብ የማያካትት ከሆነ፣
5. አስገዳዮችና ገዳዮች ለፍርድ የማይቀርቡ ከሆነ፣ እና
6. ሸዋና ደቡብ ወሎ የገባው ኮማንድ ፖስት በገለልተኛ የፀጥታ አመራሮች እንዲመራ የማይደረግ ከሆነ እና በአስቸኳይ ለሕዝባችን ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ ካልተሰጠው ራሳችንን ከምርጫ ዕጩነት እናገላለን ብለዋል።
ደብረብረሃንና አካባቢው ሙሉ የኔትወርክ አ ገልግሎት ተቋርጦ አርፍዷል፡፡
አሥራት ቲቪ
ሚያዚያ 15/2013 ዓ/ም
አገልግሎቱ ዛሬ ከማለዳ 12:00 ጀምሮ የተቋረጠ ሲሆን እስከ ረፋዱ 5:00 ድረሥ ቆይቷል፡፡
ሸኖ፣ ጫጫ፣ ደብረብረሃንና ሙሉ ይፋትን ጨምሮ ከፊል ሸዋ ካለምንም የኔትወርክና ኢንተርኔት አገልግሎት አርፍደዋል፡፡
ከመጥፋቱ ጋር ተያይዞ ያልታወቀ የመንግስት ልዑካን ቡድን ወደ ሸዋሮቢት ገብቷል ተብሏል፡፡
ይህ አይነቱ የመገናኛ መረብን አጠፋፍቶ የተለመደ ወጣቶችን የማሳደድ እና የማሰር ዘዴ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አሥራት ያነጋገራቸው ወጣቶች የትላንቱን ህዝባዊ ቁጣና አቋም መግለጫ አስታውሰው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ይፋት በኩማንድ ፖስት ቁጥጥር መሆኗ ይታወሳል፡፡
በወለጋ ዛሬም አማራዎች እየተጨፈጨፉ ነው፡፡
ሙሉ አንድ ቤተሠብ በዘግናኝ ሁኔታ በቤታቸው ውስጥ ታፍነው በእሳት ተቃጥለዋል
አሥራት ቲቪ
ሚያዚያ 16/2013/ ዓ/ም
ይህ የሆነው ተደጋጋሚ ጥቃትና ግድያ በሚፈፀምበት በሆሮ ጉድሮ ዞን አቢደንጎሮ ወረዳ ነው፡፡
የሟች ቤተሠቦችና ከአካባቢው ሸሽተው የሚገኙ ነዋሪወች ለአሥራት እንደጠቆሙት ይህ ዘግናኝ ግድያ ከመፈፀሙ በፊት ከአካባቢው ፀጥታ ሃላፊዎችና ከኦነግ ሸኔ የተውጣጣ ቡድን በምሽት እየዞሩ አገሩን ለቃችሁ ውጡ ካለበለዘያ እንገላችኀለን ብለው ሲያስፈራሩ ነበር ብለዋል፡፡
የተወሰነው ህዝብ እየለቀቀ ሲወጣ ቀሪው ደግሞ ሲዘጋጅ ከትላንትና በስተያ ምሽት አቶ አደምና ቤተሠቦቻቸውን በር ዘግተው በአሰቃቂ ሁኔታ ማቃጠላቸው ተሠምቷል፡፡
235 ሄክታር የሚጠጋ የወፍዋሻ ደን በእሳት ቃጠሎው ወድሟል አለ የአ.ብ.ክ.መ የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንሰሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን፡፡
አሥራት ቲቪ
ሚያዚያ 16/2013 ዓ/ም
ባለስልጣኑ ሰሞኑን የጥናት ቡድን ወደ ቦታው ልኬ አስጠንቻለሁ ብሎ ባወጣው ዘለግ ያለ ሪፖርት ባለፉት 36 አመታት ውስጥ በአካባቢው ከባድ የእሳት አደጋ ተከስቶ አያውቅም ሲል አትቷል፡፡
የውድመቱን መጠን የፓርኩን ሁለንተናዊ ገፅታና ጉዳቱን ያተተው የባለስልጣኑ ሪፖርት ፣ የችግሩን መንስኤ አድበስብሶት አልፏል፡፡
ደኑ በሸዋ ውስጥ 3 ወረዳዎችን አካሎ የተንጣለለ ሀብት ነው፡፡
ራሡን ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ የሚጠራው የኦነግ ሸኔ ሸማቂ ቡድን በጅማ ዞን ንፁሀንን እየገደለ ነው፡፡
አሥራት ቲቪ
ሚያዚያ 17/2013/ዓ/ም
ለዘመናት የወለጋን አማራ ሠላም የነሳውና በማሳደድ ላይ ያለው ይህ አራጅ ቡድን አሁን የጅማ ዞን ቆላማ ቦታዎች ገብቶ መሰግሰጉ ተሠምቷል፡፡
የአማራን ህዝብ ከስሩ ለመንቀል የሚታትረውና በየቦታው የተንሰራፋው ይህ ቡድን በዞኑ ሊሙ ኮሶ ወረዳ በዚህ 2 ቀናት ውስጥ ብቻ ከ 30 የሚበልጡ ንፁሀን መጨፍጨፉን አሥራት ከስፍራው በደረሰው መረጀ መሠረት አረጋግጧል፡፡
ሁሉም ራሱን አደራጅቶ ከዚህ በባንዳና በመንግስት ጉርሻ ከደለበ ጨፍጫፊ ቡድን ሊጠነቀቅ ይገባል ሲሉ የወረዳው ነዋሪወች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሕዝባችን ሰላማዊ እምቢተኝነቱን የቀጠለ ሲሆን የምርጫ ካርድ በማውጣትና ለአብን ድምጹን በመስጠት ጨቋኞቹን ሊቀጣ እንደሚገባ ተገለጸ፤
*
በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የተደራጀና የተቀናጀ የዘር ፍጅት በማውገዝ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ታላቅ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ሲያደርግ የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ለተወሰነ ጊዜ ገትቶ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ «የምርጫ ካርዳችንን በማውጣት ጨቋኞችን በድምጻችን በመቅጣት ሕዝባችን ለፍትኅና ኹለንተናዊ እኩልነት መረጋገጥ የጀመረውን ትግል ዳር እናደርሳለን!» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ አካባቢዎች ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም መሰረት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ፤ በምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ጎባጣ አቅና ቀበሌ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ዞብል፣ ቃሊም እና ሚጦ ቀበሌወች፣ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከአዘዞ፣ ጠዳ ማክሰኝት፣ እፍራዝ፣ ሰበሃና አርኖ ጋርኖ፣ በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ፣ በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ እና ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በታ ቀጠና የተሳካ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡

በምርጫ ቅስቀሳዎቹ ላይ የአማራ ሕዝብ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙበትን ማፈናቀልና ጭፍጨፋ በዘላቂነት ለማስቆም ብሎም የተሳሳተውን የማደራጃ ትርክትና የተዛነፈውን መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ማእቀፍ በማስተካከል ሕዝባችንን ለዘላቂ ሰላምና መንግስታዊ ውክልናውን ለማረጋገጥ አብን ሰፊ የፖለቲካ ትግል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

መላው የአማራ ሕዝብም ዛሬ ላይ እየደረሰበት ያለው መዋቅራዊና ሥርዓታዊ በደል ምንጩ ተገቢ ፖለቲካዊ ውክልና ባለማግኜቱና በኃቀኛ ልጆቹ ባለመወከሉ በመሆኑ የሕዝባችንን ነገ በሚወስነው ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ የምርጫ ካርዱን በማውጣት ጨቋኞቹን በድምጹ እንዲቀጣና አብንን በመምረጥ የጀመረውን ሰላማዊ እምቢተኝነት ከዳር ሊያደርስ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

በምርጫ ቅስቀሳ መረኃ ግብሩ ላይ «የምርጫ ካርዳችንን አውጥተን የኅልውና ደጀናችንን አብንን እንመርጣለን፤ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና መንግስታዊ ቸልተኝነት እናወግዛለን፤ ኑ አብንን መርጠን ለሕዝባችን ነፃነት ሰማእት የሆኑ ወገኖቻችንን ሰማእትነት የሚመጥን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት በጋራ እንቁም፣ እውነትና ሕዝብን የያዘው የአብን ትግል ያሸንፋል፣ አብን የአማራ ሕዝብ መከራ አምጦ የወለደው ፓርቲ ነው፣ አማራ በኃቀኛ ልጆቹ የሚወከልበት ጊዜው አሁን ነው፣ በጥገናዊ ለውጥ የሚባባስ እንጅ የሚፈታ የአማራ ሕዝብ ችግር የለም፣ የአማራን ሕዝብ ማኅበራዊ ረፍት ለመንሳት የሚደረገውን የፖቲካ ሴራ እናወግዛለን፣ ነፃነታችንን የምናረጋግጥበትን መሣሪያችንን ምርጫ ካርዳችንን ዛሬውኑ እናወጣለን!» የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

#የምርጫ ካርድዎን ያውጡ፤ በምርጫ ካርድዎ የመዋቅርና ሕግ ሰራሽ ችግሮችን ሰንኮፍ ነቅሎ ዲሞክራሲን ማስፈኛ ጊዜው አሁን ነው!

የአብን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ሰዓት ነው፤ #ሰዓትን_ይምረጡ!

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
በሐገራችን አንዳድ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ ሞት እና መፈናቅሎች ይቁሙ ብሎ በሰለጠነ መንገድ መንግሥትን መጠየቅ የዜጎች መብት እንጂ ወንጀል አይደለም! መስጠፌ ሙሐመድ
በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ዘርና ብሔርን መሰረት ተደርጎ በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች ፣ መፈናቅሎች እና የንብረት ውድመቶችን በሰለጠነ መንገድ ማውገዝ መብት እንጂ ወንጀል አይደለም።
በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የአማራ ህዝብ በማንነቱ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርስበት ግድያ እና መፈናቀል ይቁም በሚል በተካሄዱ ሰልፎች ላይ ወጡ የተባሉ መፈክሮች ከንጹሀን ዜጎች ህይወት እና መፈናቀል በታች ናቸው።
የሰው ህይወት ከተዛባው መፈክር በላይ ነው። ክቡር ለሆነው ለሰው ልጅ ህይወት ደንታ ሳይኖረን በመፈክር ላይ የተዛባ መፈክር ወጥቷል ብሎ ክርክርና እስጣ ገባ ውስጥ መግባት ለሀገርም ሆነ ለህዝብ አይጠቀምም።
ከዚህ ይልቅ ሊያሳስበን የሚገባው ዜጎች በየትኛውም የሀገራቸው አካባቢ በነጻነት መኖር እንዲችሉ ደህንነታቸውን ማረጋገጥ እኛ የመሪዎች ቀዳሚ ተግበር መሆን አለበት።
መሪዎች መሪ እስከሆነ ድረስ ልንብጠለጠልና ልንወቀስ እንችላለን። ግን ደግሞ ከእኛ መወቀስ እና መብጠልጠል በላይ የዜጎች ህይወት ሊያሳስበን እና ሊከነክነን ይገባል።
አንድም ሰው በማንነቱ እና በዘሩ ተለይቶ በገዛ ሀገሩ ያለአግባብ መሞት የለበትም የሚለው ሐሳብ የመላ ኢትዮጵያን እንጂ የተወሰኑ ቡድኖችና ወገኞች ብቻ ወይም የመንግሥት መፈክር ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
የንጹሐን ሞት እና መፈናቀል ይቁም ብሎ በሰለጠነ መንገድ መንግሥትን መጠየቅም መብት እንጂ ወንጀል አይደለም። ይሔ ደግሞ በእኛ ሐገር የሆነ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ዓለም ሀገራት የሚሆን እና እየሆነ ያለ ነው።
ዜጎች በሰለጠነ መንገድ በመንግሥት ላይ ያላቸውን ጥያቄ ማንሳታቸው ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መንገድ የሚጠርግ ነው። በመሆኑም በተከታታይ በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክኒያት ንጽሐን በዘርና ማንነታቸው ምክኒያት መሞት የለባቸውም የሚለው መፈክር የሁሉ ዜጎች መፈክር እንጂ የአንድ አካል ብቻ ተደርጎም መወሰድ የለበትም። ለአንዱ የተፈቀደ ለሌላኛው የተከለከለም አይደለም።


አቶ መስጠፌ ሙሐመድ
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት
ጁንታው ደጋፊዎች በዴንቨር ኮሎራዶ የንግድ ተቋም ላይ ጥቃት አደረሱ።
አሥራት ቲቪ
ሚያዝያ 20/2013 ዓ/ም
በዴንቨር ኮሎራዶ የኢትዮጵያን ህሊና ሳሎንና አቅራቢ የንግድ ተቋም(Hilina Salon &Supply)ላይ መስታወቱን በመሰባበር ጥቃት አድርሰው ሄደዋል። በአሜሪካ የሚገኙ የጁንታው ደጋፊዎች ከቀናት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ ከአስር በላይ የንግድ ተቋሞች ላይ ጥቃት አድርሰው መስታወት ሰባብረው መሄዳቸው ይታወቃል።
የህሊና ሳሎንና አቅራቢ የንግድ ተቋም ባለቤት የሆኑት አቶ ሙሉ አያና ነጋ አስራት ያናገራቸው ሲሆን ከዚህ በፊት በፌብርዋሪ ወር ላይም እንዲሁ ጥቃት አድርሰውብኛል። እኔ የ አማራ ተወላጅ ስለሆንኩና የፖለቲካ አቋሜን ስለሚያውቁ ነው ቤቴ ላይ ጥቃት የፈፀሙት ሲሉ ገልፀዋል። ከዚህ በፊትም የጁንታው ደጋፊዎች እኔ ላይ ያላቸውን ጥላቻ አውቀዋለሁ። ሁሉንም መረጃ ለፖሊስ ሰጥቻለሁ በሚያስተዳድሩት ድርጅት የትግራይ ተወላጆችና ሌሎችም እንዳሉ ገልፀው በስራቸው ምንም የተለየ ችግር ተፈጥሮ የማያውቅ ቢሆንም በኢትዮጵያም ሆነ ከሀገር ውጭ ባሉ አማራን ያነጣጠረ ጥቃቶች መቆም እንዳለበት አጥብቀው ተናግረዋል።
እንኳን ለብርሃን ትንሣዔው በሠላም አደረሳችሁ!
በአገር ቤትም ሆነ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል አደረሳችሁ፡፡
ዘመኑ ድኅነት ይዞ የመጣን ክርስቶስ አሳልፎ የመስጠት፣ የመግረፍ፣ የማሰቃየት፣ የእንግልት ነበር፡፡ ይሕም ሳይበቃ መስቀል አሸክሞ እየተዘባበቱ በጅራፍ የመግረፊያ፣ ዕጣ የመጣጣያ፣ ከዚያም በርባንን የመፍቻው፣ ክርስቶስን የመስቀያም ነበር፡፡ በግርፋቱ ውስጥ፣ ድኅነት፣ በስቅላቱ ውስጥ ትንሳዔን እንዳለ በልባቸው ያኖሩ ግን ጥቂቶች ነበሩ፡፡
በዚህ ዘመንም፣ አገር በሠራ፣ አገረ-መንግሥት ባፀና፣ ዕድሜ ዘመኑን ሙሉ አገርን ከጠላት እየተዋጋ ከክብሯ አንዳች ሳያጎድል የኖረው አማራ ስደት፣ መከራ፣ ግድያና የዘር ጭፍጨፋ እየደረሰበት ነው፡፡
አገር አፍራሽ ወንበዴ በርባንን እፍኝ ላይ አስቀምጦ፣ በድህነትና በአገር-ወዳድነት ‹‹አገሬ›› ብሎ በሚኖርበት ኢትዮጵያ እንዳይኖር፣ ዘሩ ለነገ እንዳይተርፍ፣ ስጋ-ደም ገብሮ ባቀናት አገሩ ባይተዋር እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ግና አርብ አልፎ ጌቴሴማኒ ኃይል የላትምና ክርስቶስን በመግነዝ አላስቀረችውም፤ ኃይል በእጁ አለና ትንሳዔው ሆኗል፡፡ አማራም ‹‹አማራ›› ከሚለው ስሙ የቀደሙ ጠላቶቹን የጣለበት ኃይል አለውና ትንሳዔው ሩቅ አይደለም፡፡ የገዳዮቹ ኃይል፣ የአሳዳጆቹ ክንድ ከጌቴሴማኒ የአትክልት ሥፍራ የመቃብር ቋጥኝ አይልቅምና ወደቀደመ ክብሩ ዳግም የሚመለስበት ጊዜም ከአርብ እስከ ዕለተ-ሰንበት ካለው ሦስት ሌሊትና ሦስት መዐልት የራቀ ጊዜ አይሆንም፡፡
ክርስቲያኖች እንዲሁም መላው ወገናችን፣ በአገራችን ውስጥ በዘራቸው ምክንያት ብቻ የተፈናቀሉትን፣ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን እና ገደልና ሸለቆ ከገዳዮች ተሸሽገው የሚገኙ ወገኖቻችንን በመርዳት እና ከጎናቸው በመሆን በዓሉን እንድናሳልፍ በማድረግ ወገናዊ ግዴታችንን እንወጣ፡፡
መልካም የትንሣዔ በዓል!
አሥራት - የትውልዱ አንደበት!
138 የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ከሱዳን ከስደት ተመልሰው ወደ ትውልድ ቀያቸው በሰላም ገብተዋል።
አሥራት ቲቪ
ግንቦት 2/9/2013
በዘረኛው ህወሓት ከሀገራቸው፣ ከእርስታቸው ተፈናቅለው የነበሩ ከ30 አመት የስደት ቆይታ በኃላ ወደ ትውልድ አገራቸው አማራ ምድር ወልቃይት ጠገዴ በሰላም ተመልሰዋል።
ይሄ የመጀመርያ ዙር እንደሆነና ወደፊትም እንደሚቀጥል አስተባባሪው ኮሚቴ ለአስራት ገልፀውልናል።
ለጋሞ ባህል ማዕከል ግንባታ የሚውል ቦታ ተሰጠ።
_________________________________
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጋሞ ባህል ማዕከል ግንባታ የሚውል ቦታ ሰጠ። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት የባህል ማዕከሉ ግንባታ የሚካሄድበትን ቦታ በይፋ ለጋሞ ልማት ማህበር አስረክበዋል።
“የጋሞ አባቶች የሠላም ተምሳሌት ለሀገር ግንባታ” በሚል ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ደረጃ የጋሞ ባህል ሲምፖዚየም በከተማው ወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል። በሲምፖዚየሙ ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የደቡብ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ጥላሁን ከበደ፣ ዋና አስተዳዳሪ ብርሃኑ ዘውዴ፣ ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ እና ደቡብ ክልል የካቢኔ አባላት፣ የጋሞ አባቶች እና እናቶች እንዲሁም 5ሺህ የሚደርሱ በከተማዋ የሚኖሩ የጋሞ ተወላጆች እና ወዳጆች ተገኝተዋል።
ባለፈው ዓመት በቀድሞው ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ቃል ለተገባው የጋሞ ባህል ማዕከል ግንባታ የሚውል ካርታ ያስረከቡት ም/ከንቲባ አዳነች “ልማት ማህበሩ በተረከበው ቦታ በተቻለው ፍጥነት ግንባታ እንዲጀምር ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ጋሞ አዲስ አበባን በጥበብ ሥራው ሲያለብስ ኖሯል ሲሉ የገለጹት ወ/ሮ አዳነች ከሸማ ሥራ ውጤቶች ገበያ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከተማዋ አስተዳደሩ በአፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥበት ተናግረዋል።
በሲምፖዜሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ጋሞ በሀገር ግንባታ ላይ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጾ ይበልጥ ጠብቆ እና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከየአቅጣጫው የገጠማትን ፈተና በብቃት ለመመከት መላ ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ እንዲያያዙ አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጥሪ አቅርበዋል።
በርካታ የጋሞ ተወላጆች በስፋት በሚኖሩባት አዲስ አበባ ለጋሞ ባህል ግንባታ የተሰጠው ይዞታ በመሃል አዲስ አበባ ልዩ ስሙ “ለገሃር” አካባቢ እንደሚገኝ ታውቋል።
ማይካድራ ላይ ጭፍጨፋ በማድረግ ወደ ሱዳን የሄደው የጁንታ ርዝራዥ ሃይል ወደ ሁመራ ሊገባ ሲል ተደመሰሰ::
አሥራት
ግንቦት 06/2013 ዓ.ም
ከጁንታው ሃይል መካከል ማይካድራ ላይ ጭፍጨፋ በማድረግ ወደ ሱዳን የሄደው ሃይል ወደ ሁመራ ሊገባ ሲል መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስትር የሃይል ስምሪት ሃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገለፁ።
ለወራት አሜሪካና ሱዳን ከሚገኙ የጁንታው አባላት ድጋፍ እየተደረገለት ስልጠና ሲወስድ የነበረው ሃይል በተደጋጋሚ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጅ ይህ ሙከራቸው በተደጋጋሚ በመከላከያ ሰራዊቱ ሲከሽፍ ቆይቷልም ነው ያሉት።
ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላም 320 ከጁንታው ሃይል በሃምዳይት ሁመራ በኩል ትጥቅና የተለያዩ መድሃኒቶችን ይዞ ሊገባ ሲል ገሚሱ በመከላከያ ሰራዊቱ ሲደመሰስ ገሚሱ መማረኩንም ተናግረዋል።
አሁንም ከኋላ የቀረ ሃይል መኖሩን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋዬ መከላከያ ሰራዊቱ አሁንም ይህንን ሃይል ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በሰጡት መግለጫ ሀገራዊ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው በአሜሪካ ይገኙ የነበሩና ሀገርን በመካድ ሱዳን ካርቱም ከሚገኙ የጁንታው አመራሮች ጋር ወደ ሀገር ውስጥ የመገናኛ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የነበሩትም በሰራዊቱ ተደምስሰዋል ብለዋል።
ብዛት ያለው የሬዲዮ መገናኛ ፣ ሳተላይት ስልኮችና የተለያዩ መድሀኒቶች መያዛቸውንም ነው የገለጹት።
ጁንታው በተከፋይ አክቲቪስቶቹ የሚረጨው የውሸት ዜና ብቻ በመሆኑ ህብረተሰቡም ይህን እንዲገነዘብ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘገባው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው።
<<አንገት መድፋት የአማራ አይደለም>>
የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች
<<ዛሬ አዲስ ቀን ነው፤ የወልቃይት ጠገዴን ዘር የማጥፋት ወንጀል እዚህ ላይ አብቅቷል>> ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ - የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝቦች ዞን ም/አስተዳዳር
<<በኃይል ወስደው በኃይል ፋይሉን የዘጉበትን ርስታችንን እና ማንነታችንን በአማራ ሕዝብ መራር ትግል መልሰን ወደክብሩ አኑረናል"
አቶ አሥራደ ደሣለኝ - የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና አማካሪ
አሥራት
ግንቦት 14/2013ዓ.ም
አሸባሪው የትሕነግ አምባገነን ቡድን ባለፉት 30 ዓመታት የመንግስት ልጣን በመያዝ በአማራ ሕዝብ ላይ በደል፣ ግፍና ጭፍጨፋ አድርሷል፣ መዋቅራዊ ሽፋን ሰጥታል።
በተለይ በወልቃይት፣ ሁመራ፣ ዳንሻ፣ ጠገዴ፣ ማይካድራ እና በርካታ ሰሜን ምዕራብ አማራ ላይ እጅግ ዘግናኝ የመሬት ወረራ፣ ማንነትን መሠረት ያደረገ እሥር፣ እንግልት፣ አፈና ግድያ እና ማፈናቀል ተፈፅሞበታል፤ ከአገር ተሰዷል፣ ለማንነቱና ክብሩ ተሰውቷል።
ይሕን አስከፊ ዘመን አሸባሪው ትሕነግ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ቅራቅር ላይ በአማራ ሕዝብ ላይ በከፈተው የተለመደ ትንኮሳ፣ የአማራ ሕዝብ፣ ፋኖ፣ ሚሊሻ እና ልዩ ኃይል የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት ድል ሆኖ ወደመጣበት ተመልሷል፣ በበረሃ ከስሟል፤ በኃይል የያዘውም የአማራ ማንነት እና ርስትም ለመጨረሻ ጊዜ በባለርስቱ ወልቃይቴ እና ጠገዴ ትግል ተመልሷል።
የትግሉን ፍሬ ለመዘከር፣ በትግሉ የተሳተፉትን ለማመስገን እና እውቅና ለመስጠት ዛሬ ግንቦት 14/2013 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በወፍአርግፍ ከተማ ደማቅ መርሐ-ግብር ተከናውኗል።
በዕውቅናው የመላው አማራ ሕዝብ፣ የጎንደር ከተማ፣ የወልቃይትና ጠገዴ ወረዳ፣ የአማራ ሚሊሻና ልዩ ኃይል፣ የሚዲያ አካላት እና ተጋባዥ የማንነት ጥያቄ ያላቸው የአማራ አካባቢዎች ተወካዮችን ጨምሮ ከ30,000 በላይ ታዳሚዎች ተገኝተዋል።
<<ባለፉት ዘመናት እና አሁንም ድረስ ተወረን- ወራሪ፣ ተበድለን - በዳይ፣ ተሰደን -አሳዳጅ፣ ተገድለን - ገዳይ፣ ግፉዓን ሆነን ሳለ - ገፊ ተብለን በተዛባ የታሪክ ቅሪት ጫና እየተደረገብን ነውና ምሑራን ይኸን በመመከት ከዕውነት ጋር ቁሙ>> በማለት አንድነት ላይ እንዲያተኩር የጠየቁት የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና አማካሪ፤ <<ጠላቶቻችን የማይተኙ ቢሆንም፣ ከድል ማማችን የሚያወርደን ምድራዊ ኃይል ግን በፍፁም የለም>> በማለት አንድነቱ የደረጀ ሕዝብ እንዲፈጠር እንሠራለን ብለዋል።
የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት፣ ሁመራ፣ ዳንሻና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የተደረገው የባሕል፣ የኃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የስነ-ልቦና ቀውስ በመታገል እውነተኛ ውግንናቸውን ያሳዩ ግለሰቦችንና ተቋማትን ዕውቅና በመስጠት ተጠናቋል።
አሥራትም በቦታው በመገኘት መሰናዶውን የተከታተለ ሲሆን የቪዲዮ ቅንብሮችን አሰናድቶ እንደጨረሰ የሚያቀርብ መሆኑን ያሳውቃል።
ሰበር ዜና!
የአብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ የተወዳደሩበት ራያ ቆቦን ጨምሮ፣ መርጡለማርያም እና ሉማሜ ምርጫ ክልሎች በአማራ ክልል ድጋሚ ምርጫ ይደረግባቸዋል - ምርጫ ቦርድ
ቦርዱ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም የተካሄደውን የ6ተኛውን አገራዊ ምርጫ ውጤትም ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት:-
አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ለፓርላማ) ፦
1. አዲስ አበባ ከተማ
- ብልጽግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል
- አንዷን መቀመጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ አሸንፈዋል
2. አፋር ክልል
- 8 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው 6 መቀመጫዎችን በሙሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
3. አማራ ክልል
- ምርጫ ከተካሄደባቸው 125 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና በ114ቱ አሸንፏል
- አብን 5 መቀመጫዎችን አሸንፏል
4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- 9 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- በሶስት የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ 14 ምርጫ ተከናውኗል
- ሶስቱንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
5. ድሬዳዋ
- 2 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ብልጽግና ፓርቲ አንዱን መቀመጫ አሸንፏል
6. ጋምቤላ ክልል
- 3 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ሶስቱንም ምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
7. ኦሮሚያ ክልል
- 178 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ምርጫ ከተካሄደባቸው 170 መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና 167ቱን መቀመጫ አሸንፏል
- ቀሪ 3 መቀመጫዎችን 3 የግል ዕጩዎች አሸንፈዋል
8. ሲዳማ ክልል
- 19 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- 19ኙንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
9. ደቡብ ክልል
- 104 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ምርጫ ከተከናወነባቸው 85 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ በ75ቱ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
- ኢዜማ 4 መቀመጫዎችን አሸንፏል
- የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 መቀመጫዎችን አሸንፏል ብሏል።
አሳዛኝ!

በጣና ሃይቅ 13 ያህል ሰዎችን ያሳፈረች ጀልባ ተሰወረች !
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ በጣና ኃይቅ ጉዞ የጀመረችው አነስተኛ ጀልባ ሀምሌ 9 ፣ 2013 ዓ.ም ሌሊት ለጉዞ መነሳቷም ተገልጿል ፣ ፖሊስ ባለሙያዎችን በሁለት ቡድን አዋቅሮ ከትናንት ጀምሮ ፍለጋ እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት ፍንጭ አልተገኘም ተብሏል። መንገደኞቹ ጉዟቸውን የጀመሩበት ሰዓት ሌሊት መሆኑም ፍለጋውን አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል።
ምርጫው ስለተዘረፈ ፤ የምርጫውን ውጤት በፍፁም እንደማይቀበለው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፤ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን ገምግሞ ውጤቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

ግምገማው የአዲስ አበባ ምርጫ እና ድህረ ምርጫ ሂደትን የተመለከተ ነው፡፡

በውጤቱም ባልደራስ ፤ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ስለዘረፉት የዚህን ምርጫ ውጤት በፍፁም አልቀበልም ብሏል፡፡

ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ምርጫውን ስለዘረፉት በፍርድ ቤት ከስሻለሁ ሲል የግምገማ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫ አሳውቋል፡፡

ይህ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በምርጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ባሉት ቀናት የታዩ ተግዳሮቶችን የሚዳስስ ነው፡፡

እንደ ቅድመ ምርጫ ሂደቱ ጥናት ሪፖርት ውጤት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በዕጩዎች፣ በፓርቲው በአባላትና በመራጮች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች (ስድብ፣ ዛቻ እና እስር) እንደተከናወኑበት ከጥናቱ መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአንድ የምርጫ ጣቢያ ክልል ከአንድ በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው እንደነበር የጥናት ቡድኑ በምርመራ ግኝቱ አመልክቷል፡፡ ይህ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ካወጣው ህግ ጋር የሚፃረር ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከነዋሪው ህዝብ ብዛት ጋር የማይመጣጠኑ እና ቁጥራቸው አነስተኛ እንደነበር ጥናቱ አስገንዝቧል፡፡

የጥናቱ ግኝት እንደሚያሳየው ብዙዎቹ የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንደማያውቁ በጥናቱ አማካኝነት ለመረዳት ተችሏል፡፡

የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ጠንቅቀው ላለማወቃቸው ዋናው ምክንያት የምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚዎች አመላመል ብቃትን ሳይሆን ማንነት መሰረት ባደረገ መልኩ ስለሆነ እንደሆነ የጥናቱ ግኝት ያሳያል፡፡

ስለሆነም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፤ምርጫው ስለተዘረፈ ፤ የምርጫውን ውጤት በፍፁም አልቀበለውም ብሏል፡፡

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም
Watch "mathematics teacher" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCVTUblnRi0mA_-dQ96lTYZA