ASD AJ LAH
762 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ተስፋ አለመቁረጥ ማለት ወደ አላህ መሸሽ እንጂ አለመሞት አይደለም ። ተስፈኝነት በአላህ ነው ። ዛሬ ባይሆን ነገ ፣ እዚህ ባይሆን እዚያ አላህ አይተወኝም ፣ አላህ አለኝ ፣ ያየኛል ፣ ይመለከተኛል ፣ ይመነዳኛል ብሎ በተስፋ መኖር ነው ። የሚያኖረን በእርሱ ላይ ያለን ተስፋ/እምነት ነው ። የምንሞተውም ከእርሱ ሸሽተን በሌላ ላይ እምነት ያሳደርን ተስፋን የሰነቅን ቀን ነው ። ከእርሱ መሸሽ ጭንቀትን እንጂ አያወርሰንም ። ወደ እርሱ መሸሽ ከጭንቅ የሚያላቅቅ መድኃኒት ነው ። የሸሸበት የተሸሸገበት ገደብ የለሽ ትርፍን በእርግጥ አተረፈ ። አላህ ሆይ ሸሽገን ፣ አታርቀን ወደ አንተው አቅርበን ፣ ማንም ምንም ይበል አንተ ግን "የኔ ባሮች" ካልካቸው አድርገን ።
ካለብኝ እና እያሳለፍኩትኝ ካለሁት ሁኔታ በመነሳት የትዳርን አስፈላጊነት እያስረዳሁኝ ያለሁበት ሁኔታ እና የህዝቡ የድጋፍ ስሜት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሙስሊም ነበርን" በሚል በፕሮቴስታንቱ አለም የሚገኙ ስመ ሙስሊሞች ምዕመኑን እንዴት እንደሚያታልሉት ከዚህ መመልከት ይቻላል። ትውልደ ሶማሌ የሆነችው ይህች ሴት በGMM ቲቪ የራሷ ፕሮግራም ያላት ሲሆን ሶማሌውን ለማክፈር ሆርን ኦፍ አፊሪካ ከአሜሪካ ከነ ቤተሰቧ አምጥቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያሰራት ይገኛል። ከስሟ ውጭ ግን ስለ እስልምና ምንም የምታቀው ነገር የላትም። በተለያዩ መድረኮች ግን "ሙስሊም ናት፣ የሸይኽ ቤተሰብ ናት" እየተባለች ተጋብዛ ምዕመኑን በሀሰት ትርክት ታታልለዋለች፥ ያሳዝናል..!

___
https://t.me/Yahyanuhe
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1⃣9⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣0⃣ #ዙልቀዓዳ  1⃣4⃣4⃣5⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
قطط تودع صاحبها الطفل الفلسطيني في غزة بعد أن قتلته قوات الاحتلال الإسرائيلي.

Cats bid farewell to their owner, the Palestinian child in Gaza, after he was killed by the Israeli occupation forces.
ምን ሠርተህ ዋልክ?

ሰው አምላኩ ፊት ቆሞ “ምድር ላይ ለምን ዓላማ ኖርክ? ምንስ ሠራህ?” ሲባል “ይኸው አምላኬ ሆይ ለዚህ ዓላማ ነው የኖርኩት” ብሎ ነገ ለአምላኩ የሚያሳየው ነገር በእጁ ይዞ ወደ መቃብር መውረድ፣ ወደ አኺራ መሸጋገር አለበት የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡ ዕድሜ እንደሆነ አይቆምም ይሄዳል፡፡
እናም ምድር ላይ ስትኖር የሆነ አስተዋጽኦ ይኑርህ፤ አንድ ሰው ኪሳራ ዉስጥ ነው የሚባለው ትናንትና እና ዛሬው፤ ዛሬው እና ነገው አንድ ሲሆንበት ነው፡፡ በበጎ ሥራ ምንም ሳይጨምር የዋለበት ቀን፡፡ ዛሬ ሥራ እንጂ ምርመራ የለም፤ ነገ ደግሞ የምርመራ ቀን ነው የሥራ ዘመን አልፏል፡፡ ያኔ “ምድር ላይ ምን ሠራህ?” ብትባል ምን ይሆን ታዲያ መልስህ ወዳጄ!
አንብቤያለሁ፣ ሌሎቸንም አስተምሬያለሁ አንድ ነገር ነው፤ ቀርቻለሁ፣ ፅፊያለሁ፣ ደዕዋ አድርጌያለሁ፣ ለሰው ልጆች ጠቃሚ ነገር ሠርቻለሁም አንድ ነገር ነው፡፡ አግብቼ መልካም ልጆችን ወልጄ ዲኑን እንዲያገልግሉ አሰማርቻለሁም አንድ ነገር ነው፡፡
ግና ምንም ሳይሠሩ ዉሎ ማደር፣ አምሽቶ ማንጋት፣ ወጥቶ መግባት ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ ከላይ ዛሬ እና ነገ የተመሳሰሉበት ሰው ያልነው እሱ ነው፡፡


ጀሊሉ ብርታቱን ይስጠን!

©
ጉለሌ የሙስሊም መካነ መቃብር ምን እየተሰማ ነው🤔
ሁለት ክስተቶች!

📌 የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በነገው እለት ወሳኝ ነው ያለውን የአጀንዳ ልየታ ፕሮግራም በአዲስ አበባ እንደሚጀምር አሳውቋል::

📌 ጉለሌ ሙስሊም መቃብር በተነሳ ግጭት ኡስታዝ ሙሐመድ አባተ እንደተደበደበ ተገልፇል:: የመቃብሩንም ይዞታ ለማስጠበቅ ሙስሊሙ ወደ መቃብሩ በነገው እለት እንዲመጣ አንዳንድ አክቲቪስቶች ጥሪ እያቀረቡ ነው::

🔺 አገጣጥሙት እስቲ:: ትኩረታችን ለየትኛው ይሁን? በመቃብሩ ላይ የተሰራው የድፍረትና የንቀት ተግባር ይቅር የማይባል ነው:: የመቃብሩ ስፍራ ላይ ያሉትን stores ሲዘርፉ ሲቀጥልም ኡስታዝ ሲደበደቡ እያዩ ፀጥ ያሉ የፀጥታ አካላት የተሰራውን ጥፋት ያባዙታል:: ነገር ግን መጠርጠሩም አይከፋም:: ከነገ በመለስ ለምን ብሎ መጠየቁ ደግ ነው:: ከዚያ በመለስ ጉዳዩን በህግ አግባብ መያዙ ይበጃል::

🔺 ከዚያ በመለስ ትኩረታችንን ሀገራዊ ምክክሩ ላይ እናድርግ:: ነገ አጀንዳ ልየታ ሊጀመር ሆኖ ሳለ መጅሊስ ለምን ዝም አለ? የመጡ ለውጦች ካሉ ቢያሳውቅ:: ለውጥ ከሌለም ባወጣቸው መግለጫዎች መሰረት ሙስሊሙ ምን ማሰብና ማድረግ እንዳለበት አቋሙን ቢገልፅ::

ወላሁ አዕለም!

Mohammadammin
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣1️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ከትዳር በፊት ፍቅር የለም ብዬ የኸዲጃን ፍቅር ገደል አልከተውም… ምክንያቱ ምንም ይሁን አፍቅራ እንዳገባቻቸው አልጠራጠርም… በሪራ በሚሏት ሰሓቢት ፍቅር ተለክፎ በመዲና መንገዶች ላይ ከኋላዋ እየተከተለ…  የእንባ ቋንጣውን በመዲና አድማስ  ሲወረውር የነበረውን ሰሓባው ሙጊስ … አፍቃሪ አልነበርክም ልለው አልችልም… ቀድመው ቢለያዩና ከዚያ በኋላ ባያገባትም “ሙጊስ ለበሪራ ባለው ፍቅር፣ በሪራ ደግሞ ለሙግስ ባላት ጥላቻ አልተገረምክም ወይ” የተባለለት አፍቃሪ ነው… ያውም በረሱል አንደበት።

አንድ ነገር ግን አምናለሁ… ፍቅር በስሙ የሚደረጉ ኃጥያቶችን እንደማያውቃቸውና  የአፍቃሪ መድሀኒቱም ትዳር እንደሆነ…  ማንነትህን ፣ እምነትህንና ጉዞህን የሚያመክንብህ ከሆነ በሽታ እንደሆነ… አምናለሁ። ነብይህ “ለተዋደዱ ሰዎች ከኒካህ ውጪ (አማራጭ) አላየሁም” ሲሉም… ከትዳር በፊት መዋደድ እንዳለና ኒካህ ካልታከለበት ግን የኪሳራ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ነው… አፍቅርሃል? በበር በኩል ና በቃ … በፍቅር ስም ሙድ አትያዝ!!

©
💌اللهم أشغلني بما ينفعني
و سخرني و سخر لي الخير
و قوّيني على هوى نفسي و هوى شياطين الإنس و الجن
و لا تُعدني إلى ذنب تُبت عنه يومًا

أستغفر الله العلي العظيم و أتوب إليه من جميع الذنوب ما علمت منها و ما لم أعلم، أستغفر الله حتى يغفر الله ذنبي و يبرأني من جميع الخطايا


💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌
ድንቅ ክስተት - ሶሉ አለ ነቢ!

ሚካኤል ሀርት ነው:: 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች የሚለውን መፅሐፍ ለመፃፍ 28 አመታት ፈጅተውበታል::  ከ100ዎቹ ሁሉ አስቀድሞ በአንደኛ ደረጃ ላይ የእኛን ነቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አስቀመጠ::

ለንደን ላይ ትምህርት እየሰጠ ባለበት ሰዓት ሰዎች "ለምንድን ነው ሙሐመድን አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጥከው?" በማለት ንግግሩን በማቋረጥ ረበሹት::

እሱም "ሙሐመድ ከ1400 አመታት በፊት ለሰዎች 'እኔ የአምላክ መልዕክተኛ ነኝ!' ብሎ ሲናገር ያመኑበት ሰዎች 4 ሲሆኑ ጓደኛው ሚስቱና ሁለት ህፃናት ብቻ ነበሩ::" አለ:: በመቀጠልም "ከ1400 አመታት ቡሃላ ዛሬ ላይ ከ1 ቢልዬን በላይ ተከታዮችን አፍርቷል:: ስለዚህ ውሸታም ሊሆን አይችልም:: አንድ ሰው አንድ ቢልዬን ሰውን መዋሸትም ሆነ መሸወድ አይችልም:: ውሸትም ለ1400 አመታት ሊቆይ አይችልም::" ሲል አከለ::

ከዚህም በመጨመር ለአድማጮቹ "ከዚህ ሁሉ አመታት ቡሃላ እንኳ በሚልዬን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ነፍሳቸውን እርሱን ለማንቋሸሽ ለምትወረወር አንድ ቃል ሲባል መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ ናቸው::" ሲል ነገራቸው:: በማስከተልም "ከእናንተ መካከል አንድ ክርስቲያን እንኳ ይህንን መስዋዕትነት ለእየሱስ ለመክፈል ዝግጁ አለ?" ሲል ጠየቃቸው::: መልስ አልነበረም:: አዳራሹ በፀጥታ ተሞላ::

ፊዳከ ኡሚ ወአቢ ያኸይረልወራ!

Mohammadammin
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 2⃣2⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ይሄንን የሰርግ ጥሪ ተመልከቱት¡ አጀብ ነው !
Forwarded from Mohammedamin Kassaw
ሀገራዊ ምክክር ምንድን ነው? ለምን ተቋቋመ? ለሙስሊሙስ ምን ይፈይዳል?

   ሀገራዊ ምክክር በዋናነት እንደ ሀገር በታሪክ ውስጥም ሆነ አሁን ባለው አውድ የተፈጠሩ ሀገራዊ ችግሮችንንና አለመግባባቶችን በምክክር ለመፍታት ታስቦ የተቋቋመ ኮሚሽን ነው:: በትላንት ውስጥ ያለፉ ታሪኮችና ትርክቶች እንዴት መፃፍ እንዳለባቸው አቅጣጫ ያስቀምጣል:: የሀገሪቱን ጀግኖች በዝርዝር ያስቀምጣል:: ሀገሪቱ ዛሬ ላይ ምን አይነት ምልክቶችና መገለጫዎች (ባንዲራ : ብሔራዊ መዝሙር: የአደባባይና መንገድ ስያሜዎች ወዘተ) ሊኖራት እንደሚገባ ይወስናል:: ዜጎች በሀገሪቱ ላይ ምን አይነት መብት ሊኖራቸው ይገባል የመብታቸው ድንበርስ እስከየት ነው የሚለውን ያስቀምጣል:: ህገ-መንግስቱ የሚሻሻልበትን አጠቃላይ መስመር ይዘረጋል::

📌 እንደ ሙስሊም ከላይ የተጠቀሱትም ሆነ ሌሎች ያልተጠቀሱ አጀንዳዎች ይነኩናል:: ውጤቱ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ቦታ መብትና ግዴታ ያስቀምጣል:: ታሪካችን ይፃፋል:: መብታችን ይቀመጣል:: ውክልናችን ይገለፃል:: እንደ አጠቃላይ ሙስሊሙ ጥያቄ ብሎ በሚያነሳቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያልፋል::

📌 በምክክሩ ውስጥ የሚመካከሩት ከማህበረሰቡ ውስጥ የተመረጡ ተሳታፊዎች ሲሆኑ እስከ አሁን አዲስ አበባ ላይ ከሚሳተፉ 2ሺህ ገደማ ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሙስሊሞች ከ5 ፐርሰንት በታች ማለትም 100 ሰው አካባቢ ነው:: ሙሉ ለሙሉ ሙስሊም በሆኑባቸው እንደ አፋርና ሱማሌ ክልል ያሉ ተሳታፊዎች ከአጠቃላዩ ከ50 ፐርሰንት በታች ነው:: በሌሎች ክልሎች ደግሞ 1.8 ፐርሰንት ገደማ ነው::

📌 በዚህ ውስጥ የሚወሰኑ ውሳኔዎች አሉታዊ ከሆኑ ችግሮች እንደ በፊቱ ይቀጥላሉ:: በቀላሉ አሁንም ልጆቻችን የግራኝ አህመድ ወረራ እያሉ የሀገራቸውን ጀግና እንደ ወራሪ ተደርጎ ይማራሉ:: በትምህርት ቤት ውስጥ ያለው የሂጃብ አጀንዳ አጀንዳ ሆኖ ይቀጥላል:: ወታደር ቤት ለመግባት ሶላትን መተው መስፈርት ሆኖ ይቀጥላል:: ሌላም ሌላም...

🔺 እውነታውና አደጋው የዚህን ያክል ቢሆንም አሁንም ድረስ የግንዛቤ እጥረት አለ:: የሙስሊሙ ችግር የዚህን ያክል ጥልቅ ቢሆንም የምክክር ኮሚሽኑ ለማሳተፍ ፈቃደኛ አልሆነም::

🔺 መሪ ተቋሙ ተቃውሞ ካሰማ ሰነባብቷል:: እኛም ከተቋማችን ጎን እንደሆንና ይህንን ዝም ብለን እንደማናየው የማሳየት ግዴታ አለብን:: በFacebook, telegram, X, Youtubeና መሰል የማህበራዊ ትስስር ገፆች ስለ ምክክሩና ኮሚሽኑ መልዕክት እናስተላልፍ:: ተቃውሟችንን በኮሚሽኑ ፔጅ Comment box ላይ እናስቀምጥ:: የቤትም ሆነ የስራ ቦታ ወሬያችንን ስለዚህ ብቻ እናድርግ:: የዚያኔ በአላህ ፈቃድ መሪዎቻችን ወኔያቸው ይበረታል:: በንቄት ዝም ያሉን ጆሮዎች በፍርሃት ያደምጥናሉ:: መብታችንንም አዝነውልን ሳይሆን አክብረውን ይስጡናል:: መብታችንን ለምነን ሳይሆን ታግለን እንወስዳለን:: አራት ነጥብ💪💪

የሁላችን ኢትዮጵያ ትምከር!
አላህ ምክክሩን ለሀገራችን የሚበጅ ያድርገው!!

@MohammadamminKassaw