ASD AJ LAH
752 subscribers
1.74K photos
195 videos
3 files
493 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ቁርአን ስትቀራ ልብ ካልከው ስትገረም ትውላለህ:: ዛሬ ሲደንቀኝ የዋለው የሚከተለው ነው 👉

"ምእመንንም በስህተት የገደለ ሰው ያመነችን ጫንቃ (ባሪያ) ነጻ ማውጣትና ወደ (ሟች) ቤተሰቦቹም ጉማ ምሕረት ካላደረጉለት በስተቀር መክፈል አለበት" (4:92)::

ይህ ማለት ሙእሚን ክብሩ በስህተት በእጅህ ቢጠፋ ለተውበቱ ሸርጥ የደም ካሳ (100 ግመል) ለሟች ቤተሰብ መስጠትና በተጨማሪ ባርያ ነጻ ማውጣት ይጠይቃል። ነፍሱ በስህተት ከጠፋብህ ከባድ ችግር ላይ ነህ። ይታይህ በመኪና ሮጥ ሮጥ ስትል አንዱን ሙእሚን ብትገጭ ተውበቱ ምን ያህል እንደሚያስቸግር። ዛሬ ላይ ሙእሚኑን ሁሉ ስንዘረጥጥ ሞቱን ስንቀምር፣ ህይወቱን አደጋ ላይ ስንጥል፣ ምን ይህል ከባድ ወንጀል ውስጥ እየገባን እንደሆነ አንገነዘብም።

መልእክቱ ሙእሚን በስህተት እንኳን ነብሱ በእጅህ ቢጠፋ ተውበቱ ቀላል አይደለምና ስሙንም ክብሩንም ደሙንም ከርቀት እንጠንቀቅ።

አውቆ የገደለሳ ከተባለ 👉

"ምእመንንም አስቦ የሚገድል ሰው ቅጣቱ ጀሀነም ሲሆን በውስጧም ዘውታሪ ነው፡፡ አላህም በርሱ ላይ ተቆጣ፡፡ ረገመውም..." (4:93).

ይህንን ገዳይ በተመለከተ ኢብኑ አባስ፣ ዘይድ ኢብን ሳቢት፣ አቡሁረይራ፣ አብደላህ ኢብኑ ኡመር፣ አቡ ሰለማ፣ ሀሰን፣ ቀታዳ፣ ደሀክ ወዘተ ተውበት ጭራሽ የለውም ይላሉ።

Kha abate
-‏"أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ، وَأَتُوبُ إِلَيْهِ"

-"لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ المُلكُ ولَهُ الحمدُ يُحيِي ويُميتُ وهو علَى كلِّ شيءٍ قديرٌ".

‏-"‏اللهمَّ صلِّ على محمدٍ وعلى آلِ محمدٍ كما صلَّيتَ على إبراهيمَ وعلى آلِ إبراهيمَ إنكَ حميدٌ مجيدٌ اللهمَّ بارِكْ على محمدٍ وعلى آلِ محمدٍ كما باركتَ على إبراهيمَ وعلى آلِ إبراهيمَ إنكَ حميدٌ مجيدٌ".

-"‏لَا حوْل ولَا قُوَّةَ إِلَّا باللَّهِ الْعَزِيزُ الْحكِيمُ".

-"لا إِلَهَ إِلا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ".

-"اللهُمّ إنكَ عفو تُحبّ العفو فاعفُ عني".

-"اللهُم إنّ نسألك الحُسنى و زِيادة".

-"اللهُم إعتق رِقابنَا و رِقاب أبائنا من النّار".

-"اللَّهُمَّ أعِنَّا عَلَى ذِكْرِكَ وَشُكْرِكَ وَحُسْنِ عِبَادَتِكَ"

-"اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِلمُؤْمِنِينَ وَالمُؤْمِنَاتِ ، وَالمُسْلِمِينَ وَالمُسْلِمَاتِ ، الأحْيَاءِ مِنْهُمْ وَالأمْوَاتِ".

-"اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي ذَنْبِي كُلَّهُ: دِقَّهُ وَجِلَّهُ، وَأَوَّلَهُ وَآخِرَهُ، وَعَلاَنِيَّتَهُ وَسِرَّهُ".
أصبحنا وأصبح الملك لله، والحمد لله، لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير، ربّ أسألك خير ما في هذا اليوم وخير ما بعده، وأعوذ بك من شر ما في هذه الليلة وشر ما بعدها ربّ أعوذ بك من الكسل وسوء الكبر، ربّ أعوذ بك من عذاب في النار، وعذاب في القبر.
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1⃣5⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ቀለል ያለ ኒካህ…
ግንቦት 14፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 14፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተገቢ ውክልና ሊያገኝና በንቃትም ሊሳተፍ ይገባል ተባለ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሲዳማ |
በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአግባቡ ሊወከልና በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ተነገረ።

ይህ የተነገረው፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀገራዊ ምክክርና በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ከክልሉ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ (ግንቦት 14) ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

መድረኩ በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ በሚጠበቀው የነቃ ተሳትፎ ዙርያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዓላማ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው አጀንዳ ዙርያ ባደረጉት ውይይት ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መሠረት በመኾኑ፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ድምጽ በአግባቡ ሊሰማበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለዚህም የሀገሪቱ ሙስሊሞች በሀገራዊ የምክክር መድረኩ ላይ ተመጣጣኝ ውክልናና የተሳትፎ ዕድል ሊያገኙ እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች በአጽንዖት ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የምክክር መድረኮች በሙሉ አካታችና የተለያዩ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች በአግባቡ የሚወከሉበት መኾኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ተጠቅሷል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በዚህ ሐሳብ ላይ የጋራ መግበባት ላይ በመድረስ መድረኩ በስኬት ተጠናቅቋል።

በሐዋሳ ከተማ ፓራዳይስ ሆቴል አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚዎችና አባላት፣ የዑለማ ምክር ቤት አባላት፣ የመስጂድ ኢማሞች፣ ዱዓቶች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

​••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
« ከፍጥረታት ውስጥ እንደ ረሱሉላህ የወደደን፣ የተጨነቀልን የለም። እንደ ረሱሉላህ ሌት ተቀን ዱዓ ያደረገልን የለም። እንያ የተላቁ ታላቅ ነብይ፣ ያለፈውም የሚመጣውም ወንጀሎቻቸው ተምሮላቸው አመስጋኝ ባርያ ለመሆን ሌት ተቀን የሚተጉት ባለ ታላቅ ጠባይ ዱዓቸው፣ ጭንቀታቸው ሁሉም ለህዝቦቻቸው ነበር።
አንድ ጊዜ ረዉሉላህን አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ዱዓ አድርጉልኝ አሏቸው የምዕመናን እናት የሆኑት እናታችን አዒሻ ቢንት አቡበከር ረድየላሁ አንሃ። ረሱሉላህም ወድያው እጆቻቸውን ለፍ አድርገው
‹ አላህ ሆይ የአዒሻን ሁሉንም ወንጀሎቿን ይቅር በላት፣ ያለፈውን፣ የሚመጣውንም ድብቁንም ሁሉንም ወንጀሎቿን ይቅር በላት፣ ማራት። › ብለው ዱዓ አደረጉላቸው።
እናታችን አዒሻ ይህን ሲሰሙ እጅጉን ሀሴት ተሰማቸው። በደስታ ፈገግ እያሉ ጭንቅላታቸውን ረሱሉላህ ላይ ደገፍ አደረጉት። እንያ ፍቅር አዋቂ ሸጋው ነብይ
ዱዐዬ አስደሰተሽን? አሏቸው። አዒሻም እንዴት የእርሶ ዱዓ ላያስደስተኝ ይችላል? ብለው መለሱላቸው። ረሱሉላህም
በአላህ እምላለሁ ይህን ዱዓ በእያንዳንዱ ሰላቴ ውስጥ ለኡመቶቼ የማደርገው ዱዓ ነው። አሉ። መገን የአላህ ነብይ!

አብዱልሀኪም

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين

ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በሰላት በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1️⃣6️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
#ሼር
.
የሀሩን ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል እንዲሁም ሼር በማድረግ ተጨማሪ መረጃዎችን ያገኙ ዘንድ ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ!
.
ሀሩን ሚዲያ በቴሌግራም ለመከታተል ቻናሉን ይቀላቀሉ፦https://t.me/harunmedia
ይህ ሰው ቁም ነገረኛ ነው ፣ ብስል ነው ፣ አሳቢ ነው ሊባል ከሚችልባቸው ነገሮች ትልቁና ዋነኛው አላህን ማወቁ ፣ ራሱን ማወቁ ስለ ቀብሩ መጨነቁ ስለ ለአኼራ ለመሰነቅ ላይ ታች ማለቱ ነው ። እኚህ ሰዎች ቁም ነገረኞች ናቸው ። ከእነዚህ ሁሉ በላጩ ቁም ነገረኛ ግን ይበልጥ አላህን ፈሪ የሆነው ነው ። በቀንም በሌት ፣ በውስጥም በውጭም ፣ በችግርም በድሎት ፣ በበሽታም በጤናም ሳለ ይበልጥ አላህን የፈራው ነው ።

©
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣7️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1⃣8⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ተስፋ አለመቁረጥ ማለት ወደ አላህ መሸሽ እንጂ አለመሞት አይደለም ። ተስፈኝነት በአላህ ነው ። ዛሬ ባይሆን ነገ ፣ እዚህ ባይሆን እዚያ አላህ አይተወኝም ፣ አላህ አለኝ ፣ ያየኛል ፣ ይመለከተኛል ፣ ይመነዳኛል ብሎ በተስፋ መኖር ነው ። የሚያኖረን በእርሱ ላይ ያለን ተስፋ/እምነት ነው ። የምንሞተውም ከእርሱ ሸሽተን በሌላ ላይ እምነት ያሳደርን ተስፋን የሰነቅን ቀን ነው ። ከእርሱ መሸሽ ጭንቀትን እንጂ አያወርሰንም ። ወደ እርሱ መሸሽ ከጭንቅ የሚያላቅቅ መድኃኒት ነው ። የሸሸበት የተሸሸገበት ገደብ የለሽ ትርፍን በእርግጥ አተረፈ ። አላህ ሆይ ሸሽገን ፣ አታርቀን ወደ አንተው አቅርበን ፣ ማንም ምንም ይበል አንተ ግን "የኔ ባሮች" ካልካቸው አድርገን ።
ካለብኝ እና እያሳለፍኩትኝ ካለሁት ሁኔታ በመነሳት የትዳርን አስፈላጊነት እያስረዳሁኝ ያለሁበት ሁኔታ እና የህዝቡ የድጋፍ ስሜት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሙስሊም ነበርን" በሚል በፕሮቴስታንቱ አለም የሚገኙ ስመ ሙስሊሞች ምዕመኑን እንዴት እንደሚያታልሉት ከዚህ መመልከት ይቻላል። ትውልደ ሶማሌ የሆነችው ይህች ሴት በGMM ቲቪ የራሷ ፕሮግራም ያላት ሲሆን ሶማሌውን ለማክፈር ሆርን ኦፍ አፊሪካ ከአሜሪካ ከነ ቤተሰቧ አምጥቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያሰራት ይገኛል። ከስሟ ውጭ ግን ስለ እስልምና ምንም የምታቀው ነገር የላትም። በተለያዩ መድረኮች ግን "ሙስሊም ናት፣ የሸይኽ ቤተሰብ ናት" እየተባለች ተጋብዛ ምዕመኑን በሀሰት ትርክት ታታልለዋለች፥ ያሳዝናል..!

___
https://t.me/Yahyanuhe
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1⃣9⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣0⃣ #ዙልቀዓዳ  1⃣4⃣4⃣5⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
قطط تودع صاحبها الطفل الفلسطيني في غزة بعد أن قتلته قوات الاحتلال الإسرائيلي.

Cats bid farewell to their owner, the Palestinian child in Gaza, after he was killed by the Israeli occupation forces.