ASD AJ LAH
762 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ASD AJ LAH
ኢሚ ነገ ፈተና ስላለብኝ እንዳጠና ዘጠኝ ሰዐት ላይ ቀስቅሽኝ ብለናት እሷ ስምንት ሰዐት ላይ ትቀሰቅሰን እና አስር ሰዐት ሆኗል ተነስ ትለናለች ረጅም እድሜ ከዐፍያ ጋር
የምንፈራት ስለምትመታን አልያም ዱላዋ ስለሚያሳምመን አይደለም ፣ ትዕዛዟን የምናከብረው ስለምትሰጠን ፍራንካ አይደለም ። እጅግ በጣም ስለምንወዳት ነው ። የእውነት ከልባዊ ፍቅር የመነጨ ቁጣዋ ያስተካክለናል ፣ መሻቷን ለመሙላት የምንወጥነው ፣ የምንደክመው የሻታቺው ሲሆን ያለመቺው ሲደርስ ፊቷ በደስታ ሲፈካ የሚወጣውን ብርሃን ለማየት ከመጓጓት ነው ። ስለምትወደን ፣ ስለምትረዳን በሚል ድንበሯን ልንጥስ ፣ የከለከለችንን ልንደፍር ሀያእ ይይዘናላ። ለሰከንድም እንድትከፋብን አንሻማ ። ሀም ገማችን ስትደሳብን ብቻ ነዋ ማየት የምንሻ ። ከእርሷና እርሷ ካስገኘችልንም በላይ የምንወደው የሚወደን ከሆነው ጌታችን ፣ ተንከባካቢያችን ከሆነው ከአላህስ ጋር ?

አላህ ሆይ የቀደሙንን ለጀንናህ ያሉትን በዐፊያ በዒማን አቆይልን ።

አብዱረዛቅ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣4️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
የሀገራዊ ምክክር!

የሀገራዊ ምክክር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ላልሆነላችሁ ከአንበሳ ባስ ጀርባ ላይ ያለው "ምክክራችን ለነገዋ ኢትዮጵያችን!" የሚለው የኮሚሽኑ መፈክር በመጠኑም ቢሆን ይገልፀዋል:: "ኮሚሽኑ የነገዋ ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለባት መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ባሳተፈ መልኩ ይወያያል:: ተወያይቶም አንድም ኢትዮጵያዊ ቢሆን እንኳ በሀገሩ ጉዳይ ቅር የማይሰኝበትንና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መፃኢ እድል የሚሰራበትን ከባቢ ይፈጥራል::" ተብሎም ይታሰባል:: በዚህ ረገድ "የሀገሪቱ ታሪክ ምን ይምሰል? ባንዲራዋ እንዴት ይሁን? ብሔራዊ መዝሙሯ ምንን ያካት? የስልጣን ክፍፍሉ ምን ይምሰል? ህዝቦች የሀገራቸውን ሀብት እንዴት ይጠቀሙ? በመንግስት ተቋማት ውስጥ ምን አይነት ቦታ ይኑራቸው..." የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ ያገኛሉ::

በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ኮሚሽኑ አካታችነት: ግልፀኝነት: ታማኝነት መርሆዎቹ ናቸው:: አካታችነት ሲባል በሰላማዊ መንገድ ፓርቲ አቋቁመው ከሚታገሉት ጀምሮ ነፍጥ አንግበው ጫካ ያሉትን ጭምር ከግምት ያስገባ ነው:: በተቋም ደረጃም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጭምር የሃይማኖት ተቋማት: እድሮች እንዲሁም ሌሎች ሲቪል ማህበራት ይካተታሉ:: ከእነዚህ አካላት የተውጣጣ ተሳታፊ ከተለየም ቡሃላ እንደ አጠቃላይ በሚቀርቡ አጀንዳዎች ዙሪያ ተሳታፊዎች ድምፅ ሰጥተው ይወስናሉ ማለት ነው:: ስለምን ካላችሁኝ ስለ ነገዋ ኢትዮጵያ ነው:: ስለ እኔ ስለ አንተ ስተ አንቺ ማለት ነው::

📌በአጭሩ ይህን ይመስላል:: አፅንዖት እንስጠው:: በዚህ ሰዓት እንደ ሙስሊም ከሀገራዊ ምክክሩ በላይ የሚያስጨንቀን አጀንዳ ሊኖረን አይገባም:: ዝም ብለን ሳንጠይቅ ዛሬን ካለፍን ነገ ላይ ወደ ዳግም ለቅሶና ልመና መግባታችን አይቀሬ ነው::

Mohammadammin
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን!

📌 11 ከፍተኛ ኮሚሽነሮች ሲኖሩት ከእነሱ መካከል 1 ሙስሊም ብቻ ነው የተካተተው::

📌 እስካሁን በተደረገ የተሳታፊ ልየታ 12ሺህ ሰዎች የተለዩ ሲሆን ከእነዚያ መካከል 216 (1.8%) ብቻ ሙስሊም ይገኛል::

📌 ተሳታፊ ተብለው ከተለዩት ውስጥ እንኳ ኮሚሽኑ ጎንደር ላይ ባደረገው ስብሰባ እንዳይሳተፉ እንደተደረጉ ሚዲያዎች ዘግበዋል::

📌 የፌደራል መጅሊስ ሙስሊሙ በቁጥሩ ልክ እንዳልተወከለ በመግለፅ ኮሚሽኑ እየሄደበት ያለውን መንገድ ዳግም እንዲያጤነው አቤቱታ ቢያቀርብም እስካሁን ድረስ ጆሮ ዳባ ልበስ እንዳለ ነው::

📌 የአማራ ክልል መጅሊስ የኮሚሽኑ አካሄድ በዚሁ ከቀጠለና ማስተካከያዎች ካልተደረጉ የሚመጡ ውሳኔዎችን እንደማይቀበል ከወዲሁ አሳውቋል::

🔺 ሙስሊሙ ለምን ተዘነጋ? ውክልናውን በቁጥሩ ልክ ለመስጠት ለምን አሻፈረኝ አሉ? ቅሬታዎቹንስ ለማዳመጥ ለምን አመነቱ? ወይንስ የእርሱ አጀንዳዎች የሀገር አጀንዳ አይደሉም? ወይንስ የእርሱ ችግሮች ከሀገሪቱ ችግር 1% ብቻ ነው? ወይንስ የእርሱ መቸገር ማንንም አያሳስብም? እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችንን እንጠይቅ::

🔺 ከዚያ ባሻገር ስለ ሀገራዊ ምክክሩ በያለንበት እንወያይ:: ሀሳብ እናንሸራሽር:: ሀሳብ እንለዋወጥ:: ድምፃችን ከቢሯቸው ደርሶ እስኪሰማቸው ድረስ እንጩህ::

Mohammadammin
ASD AJ LAH
የምንፈራት ስለምትመታን አልያም ዱላዋ ስለሚያሳምመን አይደለም ፣ ትዕዛዟን የምናከብረው ስለምትሰጠን ፍራንካ አይደለም ። እጅግ በጣም ስለምንወዳት ነው ። የእውነት ከልባዊ ፍቅር የመነጨ ቁጣዋ ያስተካክለናል ፣ መሻቷን ለመሙላት የምንወጥነው ፣ የምንደክመው የሻታቺው ሲሆን ያለመቺው ሲደርስ ፊቷ በደስታ ሲፈካ የሚወጣውን ብርሃን ለማየት ከመጓጓት ነው ። ስለምትወደን ፣ ስለምትረዳን በሚል ድንበሯን ልንጥስ ፣…
ያለብርድ ልብስ ተኝተን ስንነቃ ራሳችንን ከአንድ ብርድ ልብስ ጋር እናገኘዋለን:: ማን አልብሶን? እናት:: አንድ ዳቦ አዘን ሁለት ሆኖ ይመጣል:: ከየት? ከእናት ቤት:: አራት ሆነን 3 ዳቦ ብቻ ካለ እኔኮ በልቻለሁ ብላ ተነስታ ትሄዳለች:: ማን? ኡሚ:: ወደ ሩቅ ሀገር ስትሄድ በቦርሳህ ሙሉ ምግብ አሸክማ ትልካለች:: ማን? ማማ:: ቆይተህ ስትመለስ ከመግባትህ ግባ ራት ብላ ብላ ትጋብዝሃለች:: ማን? ሀርሜ:: ማንም ቢሆን የእርሷን ቦታ አይሸፍንም:: ማንም:: ማን እንደ እናት?!😍

Mohammadammin
ቁርአን ስትቀራ ልብ ካልከው ስትገረም ትውላለህ:: ዛሬ ሲደንቀኝ የዋለው የሚከተለው ነው 👉

"ምእመንንም በስህተት የገደለ ሰው ያመነችን ጫንቃ (ባሪያ) ነጻ ማውጣትና ወደ (ሟች) ቤተሰቦቹም ጉማ ምሕረት ካላደረጉለት በስተቀር መክፈል አለበት" (4:92)::

ይህ ማለት ሙእሚን ክብሩ በስህተት በእጅህ ቢጠፋ ለተውበቱ ሸርጥ የደም ካሳ (100 ግመል) ለሟች ቤተሰብ መስጠትና በተጨማሪ ባርያ ነጻ ማውጣት ይጠይቃል። ነፍሱ በስህተት ከጠፋብህ ከባድ ችግር ላይ ነህ። ይታይህ በመኪና ሮጥ ሮጥ ስትል አንዱን ሙእሚን ብትገጭ ተውበቱ ምን ያህል እንደሚያስቸግር። ዛሬ ላይ ሙእሚኑን ሁሉ ስንዘረጥጥ ሞቱን ስንቀምር፣ ህይወቱን አደጋ ላይ ስንጥል፣ ምን ይህል ከባድ ወንጀል ውስጥ እየገባን እንደሆነ አንገነዘብም።

መልእክቱ ሙእሚን በስህተት እንኳን ነብሱ በእጅህ ቢጠፋ ተውበቱ ቀላል አይደለምና ስሙንም ክብሩንም ደሙንም ከርቀት እንጠንቀቅ።

አውቆ የገደለሳ ከተባለ 👉

"ምእመንንም አስቦ የሚገድል ሰው ቅጣቱ ጀሀነም ሲሆን በውስጧም ዘውታሪ ነው፡፡ አላህም በርሱ ላይ ተቆጣ፡፡ ረገመውም..." (4:93).

ይህንን ገዳይ በተመለከተ ኢብኑ አባስ፣ ዘይድ ኢብን ሳቢት፣ አቡሁረይራ፣ አብደላህ ኢብኑ ኡመር፣ አቡ ሰለማ፣ ሀሰን፣ ቀታዳ፣ ደሀክ ወዘተ ተውበት ጭራሽ የለውም ይላሉ።

Kha abate
-‏"أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ، وَأَتُوبُ إِلَيْهِ"

-"لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ المُلكُ ولَهُ الحمدُ يُحيِي ويُميتُ وهو علَى كلِّ شيءٍ قديرٌ".

‏-"‏اللهمَّ صلِّ على محمدٍ وعلى آلِ محمدٍ كما صلَّيتَ على إبراهيمَ وعلى آلِ إبراهيمَ إنكَ حميدٌ مجيدٌ اللهمَّ بارِكْ على محمدٍ وعلى آلِ محمدٍ كما باركتَ على إبراهيمَ وعلى آلِ إبراهيمَ إنكَ حميدٌ مجيدٌ".

-"‏لَا حوْل ولَا قُوَّةَ إِلَّا باللَّهِ الْعَزِيزُ الْحكِيمُ".

-"لا إِلَهَ إِلا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ".

-"اللهُمّ إنكَ عفو تُحبّ العفو فاعفُ عني".

-"اللهُم إنّ نسألك الحُسنى و زِيادة".

-"اللهُم إعتق رِقابنَا و رِقاب أبائنا من النّار".

-"اللَّهُمَّ أعِنَّا عَلَى ذِكْرِكَ وَشُكْرِكَ وَحُسْنِ عِبَادَتِكَ"

-"اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِلمُؤْمِنِينَ وَالمُؤْمِنَاتِ ، وَالمُسْلِمِينَ وَالمُسْلِمَاتِ ، الأحْيَاءِ مِنْهُمْ وَالأمْوَاتِ".

-"اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي ذَنْبِي كُلَّهُ: دِقَّهُ وَجِلَّهُ، وَأَوَّلَهُ وَآخِرَهُ، وَعَلاَنِيَّتَهُ وَسِرَّهُ".
أصبحنا وأصبح الملك لله، والحمد لله، لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير، ربّ أسألك خير ما في هذا اليوم وخير ما بعده، وأعوذ بك من شر ما في هذه الليلة وشر ما بعدها ربّ أعوذ بك من الكسل وسوء الكبر، ربّ أعوذ بك من عذاب في النار، وعذاب في القبر.
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1⃣5⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ቀለል ያለ ኒካህ…
ግንቦት 14፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 14፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተገቢ ውክልና ሊያገኝና በንቃትም ሊሳተፍ ይገባል ተባለ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሲዳማ |
በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአግባቡ ሊወከልና በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ተነገረ።

ይህ የተነገረው፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀገራዊ ምክክርና በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ከክልሉ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ (ግንቦት 14) ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

መድረኩ በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ በሚጠበቀው የነቃ ተሳትፎ ዙርያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዓላማ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው አጀንዳ ዙርያ ባደረጉት ውይይት ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መሠረት በመኾኑ፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ድምጽ በአግባቡ ሊሰማበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለዚህም የሀገሪቱ ሙስሊሞች በሀገራዊ የምክክር መድረኩ ላይ ተመጣጣኝ ውክልናና የተሳትፎ ዕድል ሊያገኙ እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች በአጽንዖት ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የምክክር መድረኮች በሙሉ አካታችና የተለያዩ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች በአግባቡ የሚወከሉበት መኾኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ተጠቅሷል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በዚህ ሐሳብ ላይ የጋራ መግበባት ላይ በመድረስ መድረኩ በስኬት ተጠናቅቋል።

በሐዋሳ ከተማ ፓራዳይስ ሆቴል አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚዎችና አባላት፣ የዑለማ ምክር ቤት አባላት፣ የመስጂድ ኢማሞች፣ ዱዓቶች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

​••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
« ከፍጥረታት ውስጥ እንደ ረሱሉላህ የወደደን፣ የተጨነቀልን የለም። እንደ ረሱሉላህ ሌት ተቀን ዱዓ ያደረገልን የለም። እንያ የተላቁ ታላቅ ነብይ፣ ያለፈውም የሚመጣውም ወንጀሎቻቸው ተምሮላቸው አመስጋኝ ባርያ ለመሆን ሌት ተቀን የሚተጉት ባለ ታላቅ ጠባይ ዱዓቸው፣ ጭንቀታቸው ሁሉም ለህዝቦቻቸው ነበር።
አንድ ጊዜ ረዉሉላህን አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ዱዓ አድርጉልኝ አሏቸው የምዕመናን እናት የሆኑት እናታችን አዒሻ ቢንት አቡበከር ረድየላሁ አንሃ። ረሱሉላህም ወድያው እጆቻቸውን ለፍ አድርገው
‹ አላህ ሆይ የአዒሻን ሁሉንም ወንጀሎቿን ይቅር በላት፣ ያለፈውን፣ የሚመጣውንም ድብቁንም ሁሉንም ወንጀሎቿን ይቅር በላት፣ ማራት። › ብለው ዱዓ አደረጉላቸው።
እናታችን አዒሻ ይህን ሲሰሙ እጅጉን ሀሴት ተሰማቸው። በደስታ ፈገግ እያሉ ጭንቅላታቸውን ረሱሉላህ ላይ ደገፍ አደረጉት። እንያ ፍቅር አዋቂ ሸጋው ነብይ
ዱዐዬ አስደሰተሽን? አሏቸው። አዒሻም እንዴት የእርሶ ዱዓ ላያስደስተኝ ይችላል? ብለው መለሱላቸው። ረሱሉላህም
በአላህ እምላለሁ ይህን ዱዓ በእያንዳንዱ ሰላቴ ውስጥ ለኡመቶቼ የማደርገው ዱዓ ነው። አሉ። መገን የአላህ ነብይ!

አብዱልሀኪም

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين

ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በሰላት በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1️⃣6️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
#ሼር
.
የሀሩን ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል እንዲሁም ሼር በማድረግ ተጨማሪ መረጃዎችን ያገኙ ዘንድ ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ!
.
ሀሩን ሚዲያ በቴሌግራም ለመከታተል ቻናሉን ይቀላቀሉ፦https://t.me/harunmedia
ይህ ሰው ቁም ነገረኛ ነው ፣ ብስል ነው ፣ አሳቢ ነው ሊባል ከሚችልባቸው ነገሮች ትልቁና ዋነኛው አላህን ማወቁ ፣ ራሱን ማወቁ ስለ ቀብሩ መጨነቁ ስለ ለአኼራ ለመሰነቅ ላይ ታች ማለቱ ነው ። እኚህ ሰዎች ቁም ነገረኞች ናቸው ። ከእነዚህ ሁሉ በላጩ ቁም ነገረኛ ግን ይበልጥ አላህን ፈሪ የሆነው ነው ። በቀንም በሌት ፣ በውስጥም በውጭም ፣ በችግርም በድሎት ፣ በበሽታም በጤናም ሳለ ይበልጥ አላህን የፈራው ነው ።

©
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣7️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣