ASD AJ LAH
762 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ጌታዬ ሆይ! በዱዓ አትርሱን ሲሉ አደራ ያሉን በርካታ ወንድሞችና እህቶች አሉን።

ያ ረቢ ህመምተኛ ከሆኑ ፈውሳቸው፣ ዕዳ ያለባቸው ከሆኑ ዕዳቸውን የሚከፍሉበትን መንገድ አግራላቸው ፤ ሀጃ ካለባቸው ሀጃቸውን ፈፅምላቸው ፣ ያ ረቢ ! ያስጨነቃቸው ነገር ካለ ጭንቀታቸውን አስወግድላቸው ፣ ያ ራህማን በዱንያም መልካምን በመጪውም ዓለም መልካምን ለግሳቸው ፤ ያረቢ ከእሳት ቅጣትም ጠብቃቸው!

መልካም ትዳር የፈለግነውንም ወፍቀን
اَللّٰهُمَّ إِنِّيْ عَبْدُكَ، اِبْنُ عَبْدِكَ، اِبْنُ أَمَتِكَ، نَاصِيَتِيْ بِيَدِكَ، مَاضٍ فِيَّ حُكْمُكَ، عَدْلٌ فِيَّ قَضَاؤُكَ، أَسْأَلُكَ بِكُــــلِّ اِسْمٍ هُوَ لَكَ، سَمَّيْتَ بِهِ نَفْسَكَ، أَوْ أَنْزَلْتَهُ فِيْ كِتَابِكَ، أَوْ عَلَّمْتَهُ أَحَدًا مِنْ خَلْقِكَ، أَوِ اسْتَأْثَرْتَ بِهِ فِيْ عِلْمِ الْغَيْبِ عِنْدَكَ، أَنْ تَجْعَلَ الْقُرْآنَ رَبِيْعَ قَلْبِيْ، وَنُوْرَ صَدْرِيْ، وَجَلَاءَ حُزْنِيْ، وَذَهَابَ هَمِّيْ

አላሁማ ኢንኒ አብዱካ፣ ኢብኑ አብዲካ፣ ኢብኑ አማትካ። ናሲያቲ ቢያዲካ፥ ማዲያን ፊያ ሁኩሙካ፥ 'አድሉን ፊያ ቃዳ'ኡካ። አሱሉካ ቢ ኩሊ እስሚን ሁዋ ላካ፣ ሳምይታ ቢሂ ናፍስክ፣ አው አን-ዛልታሁ ፊ ኪታቢካ፣ አአላምታሁ አሀዳን ምን ኻልቂካ፣ አው ስታዕሰርታሁ ፊ ኢልሚል-ጋይቢ ኢንዳካ አን ታጀላል-ቁርዓና ረቢዓ ቀልቢ፣ ዋ ኑራ ሳድሪ፣ ዋ ጃላአ ሑዝኒ፣ ዋ ዛሃባ ሃሚ።

ትርጉም፡-

አላህ ሆይ እኔ ባሪያህ ነኝ የወንድ ባሪያህ ልጅና የሴት ባሪያህ ልጅ ነኝ። አናቴ በእጅህ ( በአንተ ቁጥጥር)ነው፤ በእኔ ላይ ያደረግኸው ትእዛዝ ይፈጸማል፤ በእኔም ላይ ያደረግከው ውሳኔ ፍትሀዊ ነው። በስሞችህ ሁሉ እማፅንሀለሁ እራስህን ከገለጽክባቸው ወይም በመጽሃፍህ ውስጥ ባወረድካቸው ወይም ከፍጥረቶቻችሁ ያስተማርካቸውን ወይም ሩቁን ዕውቀት ውስጥ እንድትይዝ በመረጥካቸው ከመልካሞቹ ስሞች ሁሉ ወደ አንተ እጣራለሁ። ቁርኣንን የልቤ ደስታ፡ የደረቴ ብርሃን፡ ፡ የሀዘኔን ማስወገጃ፡ የጭንቀቴንም መፍቻ አድርግልኝ።
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1️⃣0️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ይህቺ ዱንያ በግርምት የተሞላች ነች…በማትገምተው መልኩ ጥመት ይዘራባታል … የነብይ ልጅ አላምንም በማለቱ ጎርፍ ያሰምጠዋል…የነብይ ሚስት ሁና  ሕዝቦቿን ያጠቃው ቅጣት  በክህደቷ የተነሳ እሷንም ይነካታል…የነብይ አባት ሁኖ የጣዖት አማልክቶቹን እያመለከ ልጁ ወደ እሳት ሲወረወር ይመለከታል …በዚህችው ዱንያም ደግሞ በማታስበው ሁኔታ ሂዳያን (መመራትን) ታገኝባታለህ …ከአዘር አብራክ ኢብራሂም አለይሂ አሰላም ይወጣል … ከፊርዓውን ቤተ መንግስት ሙሳ አለይሂ አሰላም ይወጣል…አሁንም " እኔ ታላቁ ጌታቹህ ነኝ " ካለው   ፊርአው  ከድንቅ የአለም እንስቶች መካከል  አስያ ለታላቁ አላህ ስትል ልትገደል  ወጣች … ቤቶች ሁሌም ቅናቻ  ወይም ጥመት የሚገመገምባቸው  ሊሆኑ አይገባም !! ቤቶቹ ውስጥ ያሉትም እኮ  ሰዎች ናቸው !!  ሰዎቹም ልቦች አሏቸው … ልቦቻቸውም በአላህ እጅ ናቸው …ጥራት ይገባው… ከ መመራት ወጭ ሌላ አማራጭ የለውም ባልንበት ልክ ያጠማል…  ከመጥመም ውጭ ሌላ መንገድ የለውም በምንልበት ልክም ይመራል።
የተተረጎመ

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በምድር ተቀባይነትን ፣ በሰማይ ተወዳጅነትን የምታገኙበት ኻቲማችሁ የሚያምርበት …መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
ሀቅ ወላህ!
#Tapswap
👌 እስከአሁን 10.414 ትሪልየን ኮይን ተሰራጭቷል::

እስከአሁን በዓለም ዙሪያ 7,972,531 ሰዎች ጨዋታውን ተቀላቅለዋል::

👌 እስከአሁን በየቀኑ 2,923,714 ሰዎች #Tap እያደረጉ ነው::

ይሄን ጽሁፍ ስፅፍ 86,754 online ናቸው (Tap እያደረጉ ነው)

😐#Notcoin የቆየው ልክ ለሦስት ወራት ሲሆን 80 ትሪልየን #ኮይን ተሰራጭቶ ነበር (በኋላ ከሁሉም ላይ የመጨረሻዎቹን ሦስት ዜሮዎች በማጥፋት 80 ቢልዮን አድርገውታል::

🙏 #Tapswap እስከመቼ እንደሚቆይ የተገለጸ ነገር የለም:: ሆኖም ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንደሚቆይ እገምታለሁ::

👌 ብዙሰዎች ችላ እያላችሁት ነው:: ሆኖም አሁን ምን ያህል እንደሚያወጣ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ገንዘብ መሆኑ ግን መጠራጠር አይገባም:: ገንዘብ የሚሆነውም ከእኛ ይልቅ ባለቤቶቹን #ቢሊየነር ስለሚያደርጋቸው ነው (ለጽድቅ አይደለም የሚያሳትፉን)

😂 ስለሆነም ችላ አትበሉት:: አትዘናጉ:: ቢያንስ ጊዜ ስክኖራችሁ #Tap አድርጉ:: ወደቦቱ ገብታችሁ አንድም ጊዜ #Tap ሳታደርጉ የምትተዉትም ብዙዎች ናችሁ:: ለምን(ያለጥርጥር እንደNotcoin ይቆጫችኋል)

የጀመራችሁ #Tap ማድረጋችሁን ቀጥሉ🙏

ያልጀመራችሁ ከታች ባለው #link በ2,500 ኮይን ሽልማት ጀምሩ👌🙋

https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_1289529690
🎁 +2.5k Shares as a first-time gift

©
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣1️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ይህ ኦርዶናዊ ወጣት ስሙ ከማል አተልፊቲይ ሲሆን በአለማችን ትንሹ አያት የሆነ ሰው ተብሎ ተመዝግቧል።

እድሜው 16 ሆኖ ያገባ ሲሆን የእርሱ ልጅም በ16አመቷ አግብታ በ33 አመቱ አያት አድርጋዋለች።

ከዐረብኛው የkurdistan24 ገፅ ነው መረጃውን ያገኘሁትኝ

#ሸዋል ነው ያሸባብ
...ሁሉም ነገር ስላነበብነው ወይም ስለተነገረን ቀልባችን ላይ ሊያርፍ አይችልም....የገባን ይመስለናል አልገባንም ....የተረዳነው ይመስለናል ግን አልተረዳነውም....የሚነገሩን ነገሮች ሁሉ የተኖሩ አይደሉም ... የመከረን ሁሉ የመከረንን ከህይወት ያካበተው አይደለም ....የተሰመረልን ሁሉ ብቸኛው መንገድ አይደለም ....አይተው የነገሩን ሁሉ የእውነቱ መጨረሻ አይደለም .... የተረኩልን ሁሉ ፍሬ ያለው አይደለም ... የጠቆሙን መንገድ ሁሉ መዳረሻ ያለው አይደለም ... ጣዕሙን የሚያዜሙልን ሁሉ ጥፍጥናን ያዘለ አይደለም.... ..... አንዳንድ በራሳችን መንገድ እናገኛቸው ዘንድ ...አልፈንባቸው እንማርባቸው ዘንድ ...ታመን ተከድተን ተደስተን ቦርቀን አልቅሰን ተቃጥለን ይገቡን ዘንድ በኻሊቁ የተወሰነባቸው እምነቶች እና አመለካከቶች አሉ...አሉ በመረዳት ልፋት የማናገኛቸው እውነቶች...መቃጠልን ከልብ ለመረዳት መቃጠል እንዳለብን ሁሉ ....አንዳንድ መገንዘቦች እንዲህ ናቸው....ቀልባችን ላይ ለማረፍ የህይወትን ተርቲብ እና ኹነት ይከተላሉ ...

ነሲም
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ1️⃣2️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
የዚህ ቤተሰብ ሙሉ አባላት በወራሪዋ ጥቃት ምክንያት አሁን ላይ በህይወት የሉም

አላህ ሆይ እርዳታህን
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ሚያዝያ 12፣ 1966 ዓ.ል. በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን ታላቁ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ 50ኛ ዓመት ለመዘከር፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን በንባብ ያሰሙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ የሆኑት ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ሲኾኑ፣ የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ቀርቧል።
* * *

ሚያዝያ 12፣ 1966 በአዲስ አበባ የተካሄደውን ታላቁ የሙስሊሞች ሰላማዊ ሰልፍ 50ኛ ዓመት ለመዘከር፣ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡

በሀገራችን የቅርብ ዘመን ታሪክ 50 ዓመታት ወደኋላ ስንሄድ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት የፈነዳበትን የካቲት 1966 እናገኛለን፡፡ ይህ ወቅት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካም ኾነ በማኅበራዊ መስኮች ሀገራችን ውስጥ የነበሩ የተለያዩ ችግሮችን የሕዝቡ ጫንቃ ሊቋቋም እማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡ የዘውድ አገዛዝ ሥርዓቱ ቢያንስ ከ1950ዎቹ መጨረሻ አንስቶ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይስተጋባ ለነበረው የ“መሬት ለአራሹ!” ጥያቄ እንኳ፣ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት አልቻለም ነበር፡፡ እናም ሕዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ፣ ፊውዳላዊው የዘውድ አገዛዝ ሥርዓት በቃኝ ብሎ በአመጽ ተነሳ፡፡ ሕዝባዊ አብዮት ተቀጣጠለ፡፡

ከየካቲት ወር 1966 ጀምሮ በነበሩት የአብዮቱ ጊዜያት ከተካሄዱ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች እጅግ ጎልቶ በታሪክ የሚጠቀሰው ሚያዝያ 12፣ 1966 የተካሄደው የሙስሊሞች ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ የዛሬ 50 ዓመት በዛሬዋ ዕለት የተካሄደው ይህ ሰልፍ፣ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የቅርብ ዘመናት ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያለው ሕዝባዊ ክንዋኔ ነው፡፡ ይህ ሕዝባዊ ክንዋኔ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በረጅሙ የንጉሣዊ አገዛዝ ዘመን ሲፈፀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ መድልዎዎች እንዲያከትሙ፣ የዜግነት መብቶቻቸው እንዲከበሩ፣ የሃይማኖት እኩልነት እንዲሰፍን በይፋ ለመጠየቅ፣ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ደማቅና ታሪካዊ ሰልፍ ያካሄዱበት ዕለት ነው፡፡

“ንጉሥ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስ” ይባልባት በነበረችው የዚያን ጊዜዋ ኢትዮጵያ፣ አያሌ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች፣ ዘውዳዊው የአገዛዝ ሥርዓት ያደርስባቸው የነበረው በደል የፈጠረባቸውን ምሬትና ብሶት አምቀው፣ ለዘመናት ከበደል፣ ከጭቆና እና ከመድልዎ ጋር ኖረዋል፡፡ በዚያ ዘመን ሥርዓታዊ፣ ተቋማዊ እና ስልታዊ በኾነ መልኩ ይካሄድ የነበረው ጭቆናና መድልዎ ተጎጂ ኾነው ከኖሩት የሀገሪቱ ሕዝቦች ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ በሀገሪቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዕድገት ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉት የሀገራችን ሙስሊሞች፣ በሃይማኖታቸው ሳቢያ የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የዜግነት መብቶቻቸውን ተነፍገው ይኖሩ ነበር፡፡

በተለይ ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው ሩብ መጨረሻ ጀምሮ፣ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ብለው በሚኖሩባት ሀገራቸው በማንነታቸው ተገፍተው፣ የዜግነት ክብር ተነፍገው፣ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታዩ ይኖሩ ነበር፡፡ የታሪክ ምሁራን ሰሎሞናዊ በማለት የሚጠሩት ሥርወ መንግሥት ዘመን፣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በገዛ ሀገራቸው እንደ ባይተዋር ይታዩ የነበረበት የጨለማ ዘመን ነበር፡፡

ቀደምት ሙስሊም አባቶቻችን ከ1920ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ረጅም ዓመታት፣ እንደ አንድ የሃይማኖት ማኅበረሰብ ተሰባስቦ ለመደራጀት፣ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸውን በተመለከተ ኃላፊነት ወስዶ የሚሠራ የጋራ ተቋም ለመመሥረት እልህ አስጨራሽ ትግሎችን አካሂደዋል፡፡ በገዛ ሀገራቸው እንደ ባዕድ እና ከዚያም አልፎ እንደ ጠላት እየታዩ፣ ከባድ የስነ ልቦና ጫናዎችን ተቋቁመው አሳልፈዋል፡፡ በተለይ ከ1966 ጥቂት ቀደም ብሎ፣ በ1964 አንዋር መስጂድን ማዕከል አድርጎ በተመሠረተው የሙስሊም ወጣቶች ክበብ አሥተባባሪነት፣ በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ስለ ሃይማኖቱ እና ስለ ዜግነት መብቶቹ እንዲያውቅ ለማድረግ የተደረገው መጠነ ሰፊ ንቅናቄ፣ በአብዮቱ ፍንዳታ ማግሥት፣ አጠቃላይ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች በይፋ ለመንግሥት እንዲቀርቡ መንገድ የጠረገ ነበር፡፡

በሚያዝያ 1 ቀን 1966 በአዲስ አበባ ነዋሪ የኾኑ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተወካዮች ለወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን በቁጥር 13 ጥያቄዎችን አቀረቡ፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ፡

1ኛ. “መንግሥት ለእስልምና ሃይማኖት ድጋፍ የሚሰጥ መኾኑን በሕገ መንግሥት እንዲያሰፍርና፣ በተግባርም እንዲያውል፡፡”
[ይህ ጥያቄ ዛሬ ላይ ኾነው ሲሰሙት ግር ሊል ይችላል፡፡ ነገር ግን፣ በዚያ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሲሦ መንግሥትነት የሀገሪቱ ሀብት ባለ ድርሻ የነበረች ሲኾን፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ግን ከሀገሪቱ ሀብት ምንም ድርሻ ያልነበራቸው ከመኾኑ የመነጨ ጥያቄ ነበር፡፡]

2ኛ. "ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት አሥተዳደር ማኅበር፣ ወይም ተቋም እንድንመሠርት በመንግሥት ይፈቀድልን፡፡››
[ይህ ጥያቄ፣ ንጉሣዊው አገዛዝ ከወደቀና በደርግ ከተተካ ከሁለት ዓመታት በኋላ በ1968 ነው ምላሽ ያገኘው፡፡]

3. ‹‹የሸሪኣ ፍርድ ቤቶች ያለ ምንም ተጽዕኖ ነፃ ኾነው እንዲቋቋሙና ከመንግሥት በጀት እንዲመደብላቸው፣ ይህም በሚሻሻለው ሕገ መንግሥት እንዲካተት፣ የሚል ነበር፡፡
[ይህ ጥያቄ የአቶ እንዳልካቸው መኮንን ካቢኔ አዲስ ሕገ መንግሥት የሚያረቅቅ ኮሚሽን አቋቁመው የነበረ መኾኑን ታሳቢ በማድረግ የቀረበ ነበር፡፡]

4. "የሙስሊም ሃይማኖታዊ በዓላት መንግሥታዊ እውቅና አግኝተው በብሔራዊ ደረጃ ይከበሩ" የሚል ነበር፡፡
[ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘው፣ ንጉሣዊው አገዛዝ ተወግዶ፣ ደርግ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ፣ በታሕሣሥ ወር 1967 ለመጀመሪያ ጊዜ ዒድ አል አድኃ አረፋ ብሔራዊ በዓል ኾኖ እንደሚውል በበዓሉ ዋዜማ ታሕሣሥ 14 ቀን 1967 በይፋ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡ ኋላ በዓላትን የሚመለከት አዋጅ ሲወጣ፣ ሁለቱ ዒዶች እና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ልደት (መውሊድ) ብሔራዊ በዓላት ኾነው ታወጁ፡፡]

5. "የሙስሊም ወጣት ወንዶች እና የሙስሊም ወጣት ሴቶች ማኅበራት በአዋጅ እውቅና ተሰጥቷቸው ይቋቋሙ፤"
[ይህም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የዘመናት ጥያቄ አካል ኾኖ ነው የቀረበው፡፡ ንጉሣዊው አገዛዝ በአጠቃላይ ሙስሊሞችንና በሙስሊሞች የሚቋቋሙ ማኅበራትን ሁልጊዜም በጥርጣሬ ይመለከት ስለነበር፣ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች ምንም ዓይነት ማኅበር የማቋቋም የዜግነት መብት አልነበራቸውም፡፡]

6. "ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመሬት ባለቤት የመኾን መብታቸው ይከበር።"

7. ‹‹'አገር የጋራ ነው፣ ሃይማኖት የግል ነው› የሚለው አባባል በተግባር ይተርጎም›› የሚል ነበር፡፡
[በዘመኑ ይህ አባባል አልፎ አልፎ በንጉሡም ጭምር ይባል የነበረ ቢኾንም፣ በተግባር ግን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የርስት መሬት ባለቤት እንዳይኾኑ መከልከላቸው፣ ሀገር የጋራ ነው የሚለው አባባል የይስሙላ እንደነበር የሚያረጋግጥ ነበር፡፡]
8. ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በመንግሥት አሥተዳደር በፍትኅ፣ በዲፕሎማቲክ፣ በውትድርና እና በሲቪል አገልግሎት ውስጥ ያለምንም ገደብ እንዲሳተፉ እንዲፈቀድ፣
[በዘመኑ ሙስሊሞች ለላንቲካ ካልኾነ በስተቀር፣ በመንግሥት አሥተዳደር ውስጥ የነበራቸው ውክልና በእጅጉ የተገደበ ነበር፡፡ በፖሊስ እና በሕዝብ ደኅንነት፣ እንዲሁም በጦር ሠራዊት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከሚባል ገደብ አንስቶ፣ እስከተወሰነ እርከን ብቻ የሚሳተፉበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡]

9. መንግሥት ሙስሊም ሚስዮናውያን /የሃይማኖት ምሁራን/ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ይፍቀድ፡፡
[በንጉሡ ዘመን፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት እውቀት እንዳያገኙ ጥብቅ ገደብ ይደረግ ነበር፡፡ እንኳንስ የውጭ ሀገር ሃይማኖት ሰባኪ ሚስዮናውያን ይቅርና እስላማዊ የሃይማኖት መጻሕፍት እንኳ ከሙስሊሙ ዓለም ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ ነበር፡፡]

10. የእስልምና ትምህርት በብሔራዊ የመገናኛ ተቋማት በሬዲዮና በቴሌቪዥን ይሰጥ፡፡
[በጊዜው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በብሔራዊ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ይጠቀም የነበረ ሲኾን፣ ሌሎች ሃይማኖቶችም፣ ለምሳሌ ወንጌላውያን ብሥራተ ወንጌል የሚባል የራሳቸው የራዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ ነበራቸው፡፡ ይህ ግን ለሙስሊሞች የተፈቀደ አልነበረም፡፡]

11. ‹በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሙስሊሞች› የሚለው መጠሪያ፣ "ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች" በሚል ይታረም፡፡

12. በሁሉም ትምህርት ቤቶች የእስልምና ትምህርት እንዲሰጥ፣

13. መንግሥት የመስጊዶችን ግንባታ እንዲፈቅድና ለግንባታው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችም ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እንዲፈቅድ፤›› …… የሚሉ ነበሩ፡፡
እነዚህን ጥያቄዎች ሚያዝያ 1 ቀን 1966 ለእንዳልካቸው መኮንን ያቀረቡት ሙስሊሞች፣ አዎንታዊ ምላሽ ስላላገኙ ነበር ታላቁ ሰላማዊ ሰልፍ ለሚያዝያ 12 እንዲካሄድ የተጠራው፡፡ እነዚህ አሥራ ሦስት የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች፣ ንጉሡ ከዙፋናቸው እስከሚወርዱ ድረስ ምላሽ ሳያገኙ ነበር የቆዩት፡፡ ንጉሣዊው አገዛዝ በይፋ ከሥልጣን ከተወገደበት ከመስከረም 2 ቀን 1966 ጀምሮ ያለፉት 50 ዓመታት፣ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዜግነት መብቶች፣ በተለያዩ የጊዜ እርከኖች ደረጃ በደረጃ ምላሽ እያገኙ ዛሬ የምንገኝበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ችለናል፡፡

በአዲስ አበባ ሚያዝያ 12፣ 1966 የተካሄደውን ታላቁን የሙስሊሞች ደማቅና ታሪካዊ ሰልፍ 50ኛ ዓመት ስንዘክር፣ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የእኩልነት እና የፍትኅ ጥያቄዎች ለማስከበር፣ እንዲሁም የዜግነት ክብራቸውን ለማረጋገጥ በጽናት የታገሉ በሕይወት ያሉ እና በሕይወት የሌሉ ቀደምት አባቶቻችንን እጅግ በታላቅ ክብር እናስባቸዋለን፤ በእጅጉም እናመሠግናቸዋለን፡፡

ዛሬ ዘመናትን ባስቆጠረ ከፍተኛ ትግልና መስዋዕትነት የተገኙ የዜግነት መብቶቻችንን ስናጣጥም፣ ከሌሎች ሃይማኖቶት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር በመከባበርና በመተሳሰብ ለጋራ ሀገር ግንባታ በጽናት የመቆም ኃላፊነታችንን ፈጽሞ አንዘነጋም፡፡ መብቶቻችን በጽኑ ትግልና በመስዋዕትነት የተገኙ እንደመኾናቸው፣ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እንንከባከባቸዋለን እንጂ፣ ከቶውንም የቀደምት አባቶቻችንን ውለታ በሚያበላሽ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ላይ ስንዳክር አንገኝም፡፡ የሃይማኖታችንን እሴቶች ባከበረ መልኩ፣ ለሀገራችን ዕድገት እና ለመላው ሕዝባችን ሰላም የሚጠበቅብንን ሁሉ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መኾናችንን በዚሁ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እንወድዳለን፡፡

አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
ሚያዝያ 12፣ 2016 ዓ.ል
አዲስ አበባ፡፡

*****
ሸዋል 11፣ 1445 ዓ.ሂ.
*****​
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሳቂታው ሀከር ተብሎ የሚጠራውን ይህን ወጣት አስታወሳችሁት

አሜሪካ ከሚገኘው እስር ቤቱ ከ40 ቀናት በኋላ እንደሚፈታ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ሀምዛ ቢን ደላጅ አልጄሪያዊ ሀከር ሲሆን አሜሪካ ከሚገኙ ከሁለት መቶ በላይ ባንኮች አራት ቢልዮን(4,000,000,000) ዶላር ሀክ አድርጎ ለፍልስጤም የእርዳታ ድርጅቶች ቢልየኖችን የሰጠ ጀግና ወጣት ነው።
አንዱ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ :- ምነው ደካማ ሆንክሳ ሚስትህ የምትልህን ነገር እንዳለ አንድም ሳታስቀር እሺ ትላለህሳ

እሱም መለሰ:- እኔ ደክሜ ሳይሆን አባቷ ለወንድ አቋም ነው የዳሯት😎
🤔
ኢማሙ አሕመድ ያኔ በርሳቸው ዘመን አንድ ሰው ሐራም ላይ ወድቆ ሥራው እንዳይበላሽ ትዳር መያዝ እንዳለበት መክረዋል። "በዚህ ዘመን" ብለው!
የኛን ዘመን ቢመለከቱት ምን ሊሉን ይችላል?

©

#ሸዋል
ASD AJ LAH
🤔
ASD AJ LAH
Photo