ASD AJ LAH
762 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 29 #ጁማደል አኽር 1445 ሂ
ግመል ከሆንክ zoo ውስጥ ለምን ?

   ልጅ እና እናት ግመል zoo (መካነ አራዊት) ውስጥ ከዛፍ ስር ተጠልለው ይገኛሉ :: በዚህ መሐል ልጅ "እናቴ! አንዳንድ ጥያቄዎችን ልጠይቅሽ?" አላት :: እናትም "ልጄ! በእርግጥም ጠይቅ! ምን አሳሰበህ!" አለችውና ወደ መጠያየቅ ገቡ ::

  ልጅ:- እኛ ግመሎች ከጀርባችን ላይ ለምን ትልቅ ጉብታ (ሻኛ) ኖረን ?

  እናት:- እኛ የበረሐ መርከብ የሚል ቅፅል ስም ኖሮን በረሃ ውስጥ የምንኖር እንስሳዎች ነን :: ለረጂም ጊዜ ያለውሃ በረሃ ላይ ልንኖር ስለምንችል ሻኛችን ውሃ እንድናጠራቅም ያግዘናል ::

  ልጅ:- እግሮቻችንስ ለምን ክብ እና ረጃጅም ሆኑ ?

  እናት:- በረሃ በባህሪው አሸዋማ ስለሆነ ከማንም በላይ በበረሃው ውስጥ መንቀሰቃስ እንድንችል ነው ::

  ልጅ:- የአይናችን ሽፋሽፍቶችስ ለምን ረጂም ሆኑ ? አንዴንዴኮ እንዳውም ይረብሹኛል ::

  እናት:- እነዚህ ረጃጂምና ወፋፍራም ሽፋሽፍቶች መከላከያ ሽፋንህ ናቸው :: ዓይንህን ከበረሃው አሸዋና ንፋስ ይጠብቁልሃል ::

  ህፃኑ ግመልም ትንሽ ካሰበ ቡሃላ "ሻኛው በረሃ ላይ እያለን ውሃ ለማጠራቀም ከሆነ : ረጃጅም እግሮቻችን በበረሃ ውስጥ ለመራመድ ከሆነ : ሽፋሽፍቶቻችን ከበረሃ አሸዋማ ንፋስ ለመከላከል ከሆነ እኛ መካነ አራዊት ውስጥ በሳር ውስጥ ምን እንሰራለን?!" ሲል መልስ የሌለው ጥያቄ ጠየቃት ::

  እውነት ነው ያ ኡመተ ሙሐመድ!  ትክክለኛው ቦታ ላይ ካልሆን ያለን እውቀት : ክህሎት : ልምድ እና ችሎታ ረብ የለሽ ነው :: ያለምንም ተግዳሮት zoo ውስጥ መቀመጥ የምንሻ ከሆነ የሚሰራ እጅ የሚራመድ እግር የሚያይ አይንና የሚያስብ አዕምሮ መስራት ያለበጨትን አይሰራም :: ከzoo ወጥተን ለሁሉም የአላህ ፀጋ ግብረ-መልስ መስጠት አለብን ::


©Mohammadammin
መስጂድ ስንደርስ ጠያቂ እንደ ንብ መንጋ ሰፈረብኝ። የት ነበርክ? ከሀገር ወጥተህ ነው? ሰፈር ቀየርክ እንዴ? ምናምን! በልቤ «መች ፈለጋችሁኝ?» እያልኩ እገረማለሁ። የመጀመሪያ ጀመዓ አምልጦን ስለነበር ሁለተኛ ጀመዓ ቆምን። እኔን እንዳሰግድ ጋበዙኝ። እምቢ አልኩ።
«አንተ እያለህማ እኛ አንገባም!»
በግድ ገባሁ። ከደቂቃዎች በፊት የነበርኩበት ሁኔታ እና አሁን የቆምኩበት ቦታ ተምታቱብኝ። ቆዳችን አይጮህም። እጆቻችን አያወሩም። ሀፍረታችን አይናገርም። ልብስ ብዙ ነገር ይሸፍናል! እጅግ ብዙ! ለዚህ ፀጋው ከማመስገን ውጪ ምን እላለሁ? ምንም!

Fuad
"ብዙ ሺ ሻማዎች ከአንድ ሻማ ብቻ እሳት አግኝተው ሊበሩ ይችላሉ፤ እነሱን ስላበራ የሻማው እድሜ አያጥርም። ደስታህን ለሌሎች ስላካፈልክ በፍፁም አያልቅብህም"

በሌሎች ስኬት ወይ በሌሎች ደስታ መደሰትን ልመድ፤ የግድ ሻማውን እኔ ብቻ ላብራው አትበል! ተራው ያንተ ሲሆን ደግሞ ደስታህን ታካፍላቸዋለህ ያኔ በተራህ ያንተ ስኬት ለነሱ ተስፋና ብርሀን ይሆናቸዋል።
©afikedir

اللهم صل وسلموزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ከፊታቸው ፈገግታ በማይጠፋው ሀቢቡና ሙሀመድ ዐለይሂ ወሰላም ላይ የበዛ ሰለዋት የምናወርድበት ፣ ፈገግታ ፣ ደስታ እና ድል የበዛበት ብሩህ ምርጥየ ጁምዐ

https://t.me/asdajlahh
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ
ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡

وَاصْبِرْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ
ታገስም፤ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና፡፡

ሱረቱ ሁድ 114-115


GOOD NIGHT😴😴
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 30 #ጁማደል አኽር 1445 ሂ
አስቡት በአላህ መንገድ ላይ ያገኘናቸውን ወንድሞች ባይኖሩ ኖሮ ዱንያ ምን ያህል ደባሪ ትሆን ነበር :
Afdel
የረሳሀውን ብር ስታገኘው…
የራስህን ፖስት ራስህ ላይክ ስታደርግ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
لَقَدْ كَانَ فِي قَصَصِهِمْ عِبْرَةٌ لِّأُولِي الْأَلْبَابِ ۗ مَا كَانَ حَدِيثًا يُفْتَرَىٰ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ كُلِّ شَيْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለ ቤቶች በእርግጥ መገሰጫ ነበረ፡፡ (ይህ ቁርኣን) የሚቀጣጠፍ ወሬ አይደለም፡፡ ግን ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ለነገርም ሁሉ ገላጭ ለሚያምኑ ሕዝቦችም መሪና ችሮታ ነው፡፡

ሱረቱ ዩሱፍ 110

GOOD NIGHT WITH GOOD DREAMS😴😴😴
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 01 #ረጀብ 1445 ሂ
አንድ ወጣት ታክሲ ውስጥ ሲገባ ቢስሚላህ ካለ በስመላውን እንድትሰማለት ወይም እንዲሰማለት የሚፈልገው ሰው አለ ማለት ነው😉
ASD AJ LAH
አንድ ወጣት ታክሲ ውስጥ ሲገባ ቢስሚላህ ካለ በስመላውን እንድትሰማለት ወይም እንዲሰማለት የሚፈልገው ሰው አለ ማለት ነው😉
ታክሲ ውስጥ በስልክ ያለማቋረጥ ረጅም ደቂቃ የምታወራ ልጅ ካለች ታክሲ ውስጥ ያለ እንዲያናግራት የምትፈልገው ሰው አለ ማለት ነው🤷🏾
አንዳንዴ ህይወት እንዳሰብናት ረዥም አይደለችም.... አንዳንዴ ቀናችን ሲደርስ ሞትም ምክኒያት አይፈልግም.... መንገድ ላይ እየሄድን ድንገት ከጎናችን ተገንሶ ሲወድቅ ቀልድ እንደመሰለን እንደሱ.... ትናንት አብረናት ተሳስቀን ዛሬ ላትመለስ መሄዷን ሲነግሩን እንዳላመንነው እንደሷ....

ቆም ብዬ ሳስበው.... በሰአቱ ደንግጠው ይሆን እላለሁ። ከፊታቸው ስለተመለከቱት ለኛ ስለማይታየን እንግዳ ፍጡር የሆነ ነገር ሊሉን፣ ሊያስጠነቅቁን ፈልገው ይሆን? ሞት እንደሆነ እያለፉበት ያሉት ነገር ቶሎ ተረዱት ወይስ.... ገና ወጣት እኮ ነኝ፣ የምን ፍጡር ነው ይሄ ብለው ይሆን? ወይም ከደቂቃዎች በፊት እንኳን የሆነ ምልክት ነገር ፍንጭ ተሰቷቸው እንደኛው ልብ ሳይሉት ረፍዶባቸው ይሆን?.... ቆይ....ቆይ... እኛስ ረፍዶብን ይሆን?.... ይሄን ከተባባልነው ከኛ መሃል ቢያንስ አንዳችን.... አንዳችን ባንሆን እንኳን የአንዳችን ቤተሰብ በአዝራኢል የስም ሊስት ላይ ከቀጣዮቹ 1000 መሀል መሆኑ እርግጥ ቢሆን ስንታችን ባለንበት ሁነት ላይ እንቀጥል ነበር....?

ብቻ........  ያ ቃል የተገባልን ጉዞ ድሮ ይመስለን እንደነበረው ሩቅ አይለም....

Team huda
በዚህ ደረቅ ለሊት ቅስሜን ነው ሰበረው

አይ ስም🤦🏽‍♂
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَنُبَوِّئَنَّهُم مِّنَ الْجَنَّةِ غُرَفًا تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ نِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ

እነዚያም ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ከገነት በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የሠራተኞች ምንዳ ምንኛ አማረ!

ሱረቱል ዐንከቡት 58

GOOD NIGHT WITH GOOD DREAMS 😴😴😴
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 02 #ረጀብ 1445 ሂ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَقَالَ اللَّهُ لَا تَتَّخِذُوا إِلَٰهَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَإِيَّايَ فَارْهَبُونِ
አላህም አለ «ሁለት አማልክትን አትያዙ፡፡ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ፡
وَلَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَهُ الدِّينُ وَاصِبًا ۚ أَفَغَيْرَ اللَّهِ تَتَّقُونَ
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ መገዛትም ዘወትር ሲኾን ለርሱ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም ሌላ ያለን ትፈራላችሁን
وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ الضُّرُّ فَإِلَيْهِ تَجْأَرُونَ
ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው፡፡ ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደርሱ ብቻ ትጮሃላችሁ፡፡
ثُمَّ إِذَا كَشَفَ الضُّرَّ عَنكُمْ إِذَا فَرِيقٌ مِّنكُم بِرَبِّهِمْ يُشْرِكُونَ
ከዚያም ከእናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከእናንተው የኾኑ ጭፍሮች ወዲያውኑ በጌታቸው (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
لِيَكْفُرُوا بِمَا آتَيْنَاهُمْ ۚ فَتَمَتَّعُوا ۖ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ
(የሚያጋሩትም) በሰጠናቸው ሊክዱ ነው፡፡ ተጠቀሙም ወደ ፊትም (የሚደርስባችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡
وَيَجْعَلُونَ لِمَا لَا يَعْلَمُونَ نَصِيبًا مِّمَّا رَزَقْنَاهُمْ ۗ تَاللَّهِ لَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَفْتَرُونَ
ለማያውቁትም (ጣዖታት) ከሰጠናቸው ሲሳይ ፈንታን ያደርጋሉ፡፡ በአላህ እምላለሁ፤ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡
ሱረቱ ነህል 51-56
ለልባችን ልብ እንስጥ!
~
ምናልባት አለባበሳችን ሱናውን የጠበቀ፣ ውጫችን ያማረ ሊሆን ይችላል። ከሆነ እሰየው። ይሄ ትልቅ መታደል ነው። ሰው ለልማድና ለፋሽን በተረታበት ዘመን ኢስላማዊውን ስርአት መጠበቅ ትልቅ ፀጋ ነው፣ ምስጋና ለአላህ ይሁንና። ነገር ግን ውስጣችንን እንዳንረሳ፣ ልባችንን እንዳንዘነጋ ትኩረት እናድርግ። ለልባችን ልብ እንስጥ። የብዙዎቻችን ልቦች ከድንጋይ የደረቁ ሆነዋል። ልባችን በቂም፣ በክፋት፣ በንቀት፣ በጥላቻ ተሞልቷል። በደል በጣም በዝቷል። ግብይታችን አላህን መፍራት ርቆታል። ጋብቻችን ተቅዋ የሸተተው እየሆነ አይደለም። ወንዱ ጨካኝ፣ ስግብግብ፣ ኃላፊነት የማይሰማው፣ ከወንድነት የተኳረፈ ሆኗል። ሴቱ መረን ለቆ፣ እንደታመመ እንኳን አያውቅም። ዘረኝነት ቤት ሰርቶብናል። ምላሳችን ዚክር ረስቷል። ዒባዳችን ጣእም አልባ የበድን እንቅስቃሴ ሆኗል። ከቁርኣን በእጅጉ ርቀናል። በዛዛታ ሰምጠናል። ይሄ ሁሉ የልብ መታወክ ችግር ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
{أَلاَ وَإِنَّ فِي الْجَسَدِ مُضْغَةً إِذَا صَلَحَتْ صَلَحَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، وَإِذَا فَسَدَتْ فَسَدَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، أَلاَ وهِيَ الْقَلْبُ}
"አዋጅ! አካል ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች መላ አካል ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች መላ አካል ይበላሻል። ንቁ! እሷም ልብ ነች!" [አልቡኻሪይ፡ 52] [ሙስሊም፡ 1599]

ባጭሩ ውስጣችን ከውጫችን በላይ ትኩረት ይፈልጋል።

Ibnu Munewor
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 03 #ረጀብ 1445 ሂ