ASD AJ LAH
762 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
የአላህ ጊዜ ሁሌም ትክክል ነው። የእርሱ ቃልኪዳን ሁልጊዜም እውን ነው። ባሮቹ ሲበደሉ ዝም ብሎ የሚመለከት አምላክ የለንም። አማኞች አቅም ሲያጡ፤ ለአዕምሮ የሚከብዱ ተጨባጮች ውስጥ ሲገቡ የሚዘነጋቸው ጌታ አይደለም።

አላህ አይረሳም! ❤️‍🩹

ጌታችን የባሮቹን ህመም ረሺ አይደለም። ረቢ በዳዬችን የሚበቀል አምላክ ነው። የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነው!

ጀሀነም ሐቅ ነው!
ጌታችን ፊት መቅረብ ሐቅ ነው!
ሁሉም የስራውን የሚያገኝበት የሒሳብ ቀን'ም ሐቅ ነው!

የዛኔ ግን ቅጣቱም ሆነ ሽልማቱ ጊዜያዊ አይደለም። የዛኔ የትኛውም አምባገነን መሪ ጭፍ*ጨፋውን በሚዲያ ሽፋን ለመደበቅ አይሞክርም። ዳኛው አላህ ነዋ! የዛኔ ማምለጫ አይኖርም! ቆዳን በጣም አክሳይ በሆነው ሰቀር ውስጥ የመማቀቂያ ዘላለማዊ ህይወት ይጀምራል! ወላሂ የዛኔ ማምለጫ በፍፁም አይኖርም!

እነዚህ አረመኔዎች ምድር ላይ የበሉት ነፍስ፤ ያፈሰሱት የጨቅላ ደም የዛኔ ይከፍላቸዋል! እስከዛ ደግሞ በዚህች ትንሽ የዱንያ ቆይታቸው እረፍት ያለ ኑሮን አይሰጣቸውም። በቅዠት የተሞሉ ለሊቶች፤ በፍርሃት፤ በጭንቀት የተረበሹ ልቦችን ይለግሳቸዋል! ምክንያቱም አላህ በባሮቹ ድርድርን አያውቅም! እንዴት'ስ ዝም ይላል?! በእውነቱ ጌታችን ረሺ አምላክ አይደለም። 🙌🏽

እኛም እስከዛ "ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል!" እንላለን! ... የትኛውም ቃል፤ የትኛውም መፈክር፤ የትኛውም የተስፋ ቃል ከዚህ በላይ ሊያጠነክረን አይችልም! ቁስላችንን በቅርቡ ያሽርልን ዘንድ ምላሳችን ላይ እናዘውትረው ኢንሻአላህ! ❤️‍🩹
#Nadia
« ሙትቻ ላሉህ ሰዎች እራስህን ለማስረዳት አትሞክር። ለሞትክባቸው ሰዎች የምታባክነው ጊዜ አይኑርህ። ውበትህ ግለፅ ሲወጣ የመጣ ሁሉ ውበትህን አይቶ ላይሆን ይችላልና በአመዳምነት ዘመንህ ላይ ውበትህ የታያቸውን ጠበቅ አድርገህ ያዝ።
ቆንጆ መሆንሽን ከሚያደንቁት የበለጠ የሚያስጠላብሽን ሊያስውቡልሽ የሚጣጣሩትን አትዘንጊ። ቁስልሽን በሰው አትከልዪ። የሚመክሩሽ ሁሉም ከጥቃት አይጠብቁሽም። ጥንቃቄ የብልሆች መንገድ ነው። በጣም ነፃነት በሚሰማሽ ሰው በኩል ስስ ነሽና አትራቆቺ።
ዋጋ የምትከፍዪላቸው ከጌታሽ መንገድ እንዳያስቱሽ አስተውዩ! የምወድሽዋ ልብሽን በቀደር አረጋጊ! የምወድህዋ እራስህ ካልወደቅክ አይጥሉህምና በጌታህ ታግዘህ ፅና። መንገዱ ምን እንዳለው አይታወቅምና ሰላም ለልባችሁ!
©
[አብዱልሀኪም ሰፋ]

❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️

ልባችን ሰላም የሚያገኝበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚

https://t.me/asdajlahh
"የሙስሊም ተሳታፊዎች ቁጥር አናሳ በመሆኑ የምናነሳው አጀንዳዎች ተቀባይነት እያጡ ነው"በአዲስአበባ የሀገራዊ ምክክር ሂደት ተሳታፊዎች
...
(ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 22/2016)
...
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ትናንት ግንቦት 21/2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ የምክክር መርሀግብር በአድዋ "ሙዚየም" አዳራሽ የጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለት በግዮን ሆቴል እየተካሄደ በነበረው አጀንዳ የመለየት መርሀግብር የሙስሊሙ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ አጀንዳዎችን ለማስያዝ እና በቀጣይ በሚኖሩ ውይይቶች ለማለፍ በድምፅ ብልጫ በመሆኑ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዚህ ረገድ የተሳታፊዎቹ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በድምሩ ብልጫ አጀንዳዎች ውድቅ እየሆኑ መሆኑን "ሀሩን ሚድያ "ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

ውይይቱ በቡድን በቡድን ስምንት ስምንት ተሳታፊዎችን ያካተተ መሆኑን በማንሳት የሙስሊሙ ቁጥር ግን በየቡድኑ ከአንድ ወይም ከሁለት እንደማይበልጥ በዚህም ምክንያት ቀጣይ ለሚደረገው ውይይት ሙስሊሙ ተሳታፊ እንደማይሆን ጨምረው ተናግረዋል።

ተወካዮች በአጀንዳ ሃሳቦቻቸው ላይ ከተወያዩ በኋላ በቀጣይ የምክክር መድረኮች ሀሳቦቻቸውን በውክልና የሚያቀርቡላቸውን 121 ተወካዮችን የሚመርጡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የሙስሊሙ ተወካዮች እጅግ በጣም ጥቂት ሊሆኑ እንደሚችሉ ከታዘቡት በመነሳት አስተያየታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

ለሀሩን ሚድያ አስተያየታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች በመጨረሻም ሀገራዊ ምክክሩ አሁንም ከስተቱ በመማር ሙስሊሙ በቁጥሩ ልክ ተሳትፎ እንዲያደርግ ማመቻቸት እንዳለበት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

©ሀሩን ሚድያ
من مغرب يوم الخميس إلى مغرب
‏يوم الجمعة
‏كل ثانيه فيها خزائن من الحسنات
‏فلنُكثر من الصلاة على النبيﷺ.. "

‏اللهُّم صل وسلم على نبينا مُحمد
‏⁧ #ليله_الجمعه
Forwarded from Mohammedamin Kassaw
ህፃኗን ልጅ "የእኛ ነብይ ስም ማን ነው?" ብዬ ጠየኳት:: "ሙሐመድ ነዋ!" አለችኝ:: አስከትዬ "የአባታቸውስ?" አልኳት:: "ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ነዋ!" አለችኝ::

አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሙሐመድ! صلى الله عليه و سلم

የውዳሴው ጅረት ለልጆቻችን የአባታቸው ስም እስኪመስል ድረስ ከኡማው አንደበት ፈሷል:: ጁምዓ ነውና ሰለዋት አብዙ:: የጁምዓ ሱናዎችንም ጠብቁ::

ደግሞ ስማቸው ሙሐመድ ኢብኑ አብደላህ ነው! صلى الله عليه و سلم

@MohammadamminKassaw
በሀገረ ጀርመን የምንግዜም ገጣሚ ተብሎ የሚታወቀው ጆሃን ወልፍጋንግ "ታሪክን ለሰው ልጅ ፍፁም ተምሳሌት የሚሆንን አካል ለማግኘት አጠናሁ:: በመጨረሻም ያንን ተምሳሌታዊ ስብዕና ከአረብ መሬት ከተገኘው ነብይ ሙሐመድ አገኘሁ::" ይለናል::

   ስለርሳቸው ወዳጅ ብቻም ሳይሆን ጠላትም ይመሰክራል:: የሚያምንባቸው ብቻም ሳይሆን የሚያስተባብለውም ይመሰክራል:: ሰውም ብቻ ሳይሆን ሳር ቅጠሉ ጅን እንስሳቱ ይመሰክራል::

   በአሽረፈል ኸልቅ ውስጥ ጂንም ሆነ ሰው ሊመራበት የሚገባ አርአያነት አለ:: ከሀቢቢ ከሰው አልፎ ለእንስሳት የተረፈ እዝነት ነበር:: የአለማት እዝነት ናቸው::

‏اللهُّم صل وسلم على نبينا مُحمد
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 2️⃣3️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
በጁምዓ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ…

ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾

“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1531
اللهم أرني عجائب قدرتك في قضاء حوائجي، وتحقيق أمنياتي واستجابة دعواتي ❤️
ይለያያል እንጂ የችግሩ አይነት…ሁሉም ሰው የራሱ ችግር አለበት

ከባጃጅ
የወራሪዋ የድሮን ጥቃት በርትቶ ቤታቸውን ትተው ወደመጠለያ ካንፑ ሲያቀኑ ከርሀባቸው ጋር እየታገሉ ፍሪጅ ውስጥ አትክልትና ፍራፍሬ ለሙጃሂዶቹ ያስቀምጣሉ። እኛ እንራብ እናንተን ግን እሾህ አይንካችሁ ይላሉ። ከነፍሳቸው በላይ ለወንድሞቻቸው ማሰብ ይሉሀል ይህ ነው። ጋዛዊያኖች ዘንድ እንጂ የማይገኝ ኡኹዋ!

#mahi mahisho
ዘንጊዎች በዘነጉ፣አሰታዋሾች ባሰታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ በፈሰሰው አሸዋ፣ ሰማይን ባደመቁት ክዋክብት፣ ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ሙሐመድ(ﷺ)ላይ ይሁን!

አለይሂ ሰላቱ ወሰላም♥️