ASD AJ LAH
762 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 09 #ረጀብ 1445 ሂ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَلَقَدْ جِئْتُمُونَا فُرَادَىٰ كَمَا خَلَقْنَاكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَتَرَكْتُم مَّا خَوَّلْنَاكُمْ وَرَاءَ ظُهُورِكُمْ ۖ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ

መጀመሪያም ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ኾናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ ለየብቻችሁ ኾናችሁ በእርግጥ መጣችሁን እነዚያንም እነሱ በእናንተ ውስጥ (ለአላህ) ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፡፡ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ (ያማልደናል) የምትሉት ጠፋ (ይባላሉ)፡፡

ሱረቱል አንዐም 94

መልካም ንጋት
ሰውዬው የልጁን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ሄዶ ግቢው ውስጥ ዞር ዞር እያለ ነው

ግቢው ውስጥ ከሚገኙት የተማሪዎች መቀመጫዎች ሁሉ አንደኛው ወንበር ተለይቶ ቀይ ቀለም ተቀብቷል : በአይነትም ይለያል

"ይህኛው ወንበር ለምንድነው ከሌላው የተለየው? ከዚህ ወንበር ውጪ መቀመጥ አይቻልም?" ሲል አባትየው ጠየቀ

"አባዬ ይህ ወንበር 'አጫውቱኝ' ይባላል"

"ምንድነው 'አጫውቱኝ ወንበር'?" አባት ግራ ገባው

"ከተማሪዎች አንዱ ለትምህርት ቤቱ አዲስ ከሆነ: ነባር ሆኖ ራሱ ቢከፋው: ሌሎች ተማሪዎች ቢያገሉት: ሆድ ብሶት ቢያዝን እዚህ ወንበር ላይ መጥቶ ይቀመጣል:: እዚህ ወንበር ላይ ከተቀመጠ 'ብቸኛ ነኝ አጫውቱኝ' ማለት ፈልጎ ነው

አባት ተገረመ

*****
"አንተ እዚህ ተቀምጠህ ታውቃለህ?" አባት ጠየቀ

**

"እዚህ ትምህርት ቤት አዲስ ሆኜ ስመጣ አንድም ተማሪ አላውቅም ነበር: ብቸኝነቱ ከብዶብኝ ነበር:: ከዚያም እዚህ ወንበር ላይ መጥቼ ስቀመጥ አንድ ተማሪ መጥቶ ይዞኝ ሄዶ ከሌሎች ጋር ቀላቀለኝ:: ደስተኛም ሆንኩኝ"

"እኔም ብሆን እዚህ ወንበር ላይ ተማሪ ተቀምጦ ካየሁኝ መጥቼ አጫውተዋለሁኝ"

👇🏾

አስባችሁታል?🤔

ውሏችን ላይ እንዲህ አይነት ቀይ ወንበሮች ቢኖሩ

ሲከፋን:ሆድ ሲብሰን:ስናጣ:ሰው ሲርቀን ቁጭ የምንልበት

❤️🙌🏼

Zemelak endrias
ስለ ባንኮች ይህን መረጃ ታውቁ ኖሯል⁉️
===========================
(ሁሉም ሙስሊም ይህን ዳታ ማወቅ አለበት፤ አሰራጩት!)
||
በሃገራችን ውስጥ ኢስላማዊ ባንኮችን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት 31 ገደማ ባንኮች ይገኛሉ።
በሁሉም ባንክ አጠቃላይ የሚገኝ ገንዘብ 2.2+ ትሪሊዮን ብር ነው ተብሎ ይገመታል።

ከዚህ መካከል 2 ትሪሊዮን ብር የሚሆነው በወለድ የተቀመጠ ሲሆን 0.2 ትሪሊዮን (200 ቢሊዮን) ብር የሚሆነው ከወለድ ነፃ በሚባሉት ውስጥ የሚገኝ ነው።
ከዚህ ከ200 ቢሊዮኑ ውስጥ ግማሹ (100 ቢሊዮኑ ብር) በንግድ ባንክ ብቻ ሲሆን፤ ቀሪው መቶ ቢሊዮን በአዋሽ ኢኽላስ፣ በኢሲኒያ አሚን፣ በዳሽን፣… በአጠቃላይ የወለድ ባንኮች ከወለድ ነፃ ብለው በከፈቱት መስኮት እንዲሁም በዘምዘምና ሂጅራ ውስጥ ይገኛል። የዘምዘምና የሂጅራው 10 ቢሊዮን ገደማ ብቻ ቢሆን ነው።

√ ያኔ ከ10+ አመታት በፊት ኢስላማዊ ባንክ ይቋቋም ተብሎ ሙስሊሙ ሲጠይቅ ዘምዘም ባንክ ሊጀመር ሲል መታገዱ ይታወሳል።
በምትኩ ከ"ወለድ ነፃ (Interest Free Bank - IFB" አሉና በወለዱ መስኮት በሽንገላ በፈረንጆቹ 2013 ላይ ተጀመረ።

በአመቱ (2014) ላይ በዚህ ከወለድ ነፃ መስኮት ተቀማጭ የነበረው አጠቃላይ ገንዘብ 600 ሚሊዮን ብር ነበር። የግል ባንኮችም ይህን መስኮት መክፈት ሲጀምሩ 3 ቢሊዮን፣ ከዚያም ወደ 12 ቢሊዮን ብር አደገ።

ከ4 አመታት በፊት (2020 ላይ) አጠቃላይ ከወለድ ነፃ ተብሎ የተጠራቀመው ገንዘብ 57 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር። ከዚያ ውስጥ በብድር መልክ የተሰጠው (ፋይናንስ የተደረገው) 13 ቢሊዮኑ ብቻ ነበር። ግን እስከ 85% ፋይናንስ መደረግ ነበረበት።

2021 ላይ ዘምዘምና ሂጅራህ ሲጀምሩ፤ ሁሉም በማስታወቂያውም በምኑም እየታገለ ወደ 100 ቢሊዮን አደገ።

አሁን 2023 ላይ 200 ቢሊዮን ደርሷል። ከዚያ ውስጥ 78 ቢሊዮኑ ፋይናንስ ተደርጓል። ዘምዘምና ሂጅራ እንደ አማራጭ ባይመጡ ኖሮ እንኳን 78፤ 28ቱም አይደረግም ነበር።

ዘምዘምና ሂጅራ አቅም ኖሯቸው ባያበድሩን እንኳ፤ እነርሱ አማራጭ ስላሏቸው ወደነርሱ እንዳይሸሹብን ተብሎ ተፈርቶ ሌላው እንዲያበድረን ደህና ማስፈራሪያ በመሆን ጠቅመውናል።

ዘንድሮ ሁሉም ባንኮች ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ አትርፈዋል። ግን ሼር ሆልደራቸው ሙስሊም ስላልሆነ ሙስሊሙ የሚከፋፈለው ትርፍ የለም።
ከወለድ ነፃ ብለው በከፈቱት መስኮት የነርሱ ማትረፊያና ኪስ ማድለቢያ ሆንን እንጂ!

√ ሁሉም ባንኮች 1.4 ትሪሊዮን ብር አበድረዋል። ግን 1.34 ትሪሊዮኑ በወለድ ነው። ከወለድ ነፃው 78 ቢሊዮን ብቻ ነው። ነገር ግን ማጠራቀሙ ላይ ስናይ ካለው 2 ትሪሊዮን ገንዘብ 1+ ትሪሊዮኑ የሙስሊም ነው ተብሎ ይገመታል።


√ የሃገራችንን ህዝብ ብዛት አስቡት።  አጠቃላይ በሁሉም ባንኮች 129 ሚሊዮን የባንክ አካውንቶች ተከፍተዋል። የዘምዘም፣ የሂጅራ፣ የራሚስና የሸበሌ አካውንት ግን ተደምሮ እንኳ 1 ሚሊዮን አይሞላም። ለምሳሌ፦ የዘምዘም 360,000 ብቻ ነው። ሲራ ሲጀምር ከነበሩት 12,750 ሼር ሆልደሮቹ መካከል ግማሹ (6,118) የሚሆኑት አካውንት አልከፈቱም። አስቡት! ሼር ሆልደር ሆኖ እንኳ አካውንት ያልከፈተ አለ። ቆይ ምናችንን ነው ግን የሚያመን?

ከ129 ሚሊዮኑ አካውንት ውስጥ በኢስላማዊ ባንኮች የተከፈተው አካውንት 1 ሚሊዮን ያልሞላው 129 ሚሊዮኑ ሁሉ የሌላ እምነት ተከታይ ሆኖ እንዳይመስላችሁ። ከ60+ ሚሊዮን ሙስሊም ውስጥ 16% ገደማ ብቻ ነው አካውንት የከፈተው።


√ ከዘምዘምና ሂጅራ መመስረት በኋላ የመጣው አማራ ባንክ ገና ሲጀምር የከፈታቸው 75/80+ ቅርንጫፎች ዘምዘምና ሂጅራ አሁን ድረስ የሏቸውም። አሁን እርሱ 300 ገደማ ቅርንጫፍ ደርሷል። ዘምዘም ሥራ ሲጀምር የተከፈለ ካፒታሉ 871 ሚሊዮን ብር ነበር። የተመዘገበ ካፒታሉ ደግሞ 1.6 ቢሊዮን። አማራ ባንክ ግን የተከፈለ ካፒታሉ ብቻ 8 ቢሊዮን ነበር። የተመዘገበው ደግሞ 10 ቢሊዮን።

አሁን በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ውስጥ የሚገኘው ሙስሊም ብዛቱ ከአንድ ክልል ህዝብ አንሶ ነው? ወይንስ ምን ነክቶን ነው?

እንደዛ በትግል እንዳልተገኙ፤ አሁን ላይ ለምንድን ነው ሳንጠቀምባቸው የቀረነው?
የኛ ገንዘብ ከወለድ ነፃ ሌሎች ጋር ስለምናስቀምጥ፤ ወይ ለኛው አያበድሩን፣ ወይ ዘካ አያወጡ፤… የኛ ገንዘብ የሚያስገኘውንም ወለድ፣ ዋናውንም አድርገው ለራሳቸው ሰው ያበድሩታል።


የኛ ባንኮች እዚህ 5 ቢሊዮን እንኳ መሙላት ተስኗቸው ያጣጥራሉ።

ኧረ! እስኪ ይቆጨን። መረጃዎችንና ዳታዎችን፣ መፍትሄዎችንና ያሉ ችግሮችን እንወያይባቸው። በደንብ ይፋፋም ይህ ሃሳብ!

በአላህ ፈቃድ የሆነ ነገር ላይ እንድረስ


©MuradTadesse
አንዳንዴ መናገር ያለብን ነገር ያጋጥመን እና ብንናገር ሊደርስብን የሚችለውን ሰዋዊ መገፋት በመፍራት ዝም እንላለን ።ይህ ፍርሃት ተፈጥሯዊ ነው።

ግን ደሞ ከዝምታው አልፈን መናገር ካለብን በተቃራኒው መዘባረቅ ከጀመርን ቦቅባቃነት ሲደመር ልወደድ ባይነት ይሆናል።

ወዳጄ እውነታው እንዲወዱህ ፈልገህ ለክህደት የቀረበ ነገር የተናገርክላቸው እነገሌ ይስቁብህ ሙድ ይይዙብህ ይሆናል እንጂ ስላሽቃበጥክላቸው ፈፅሞ አይወዱህም።

መወደድ ከፈለክ በአላህ ተወደድ እርሱ የወደደውን ማንም አይጠላውም እርሱ የጠላውን ማንም አይወደውም።

Dinu
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 10 #ረጀብ 1445 ሂ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
أَوَلَا يَرَوْنَ أَنَّهُمْ يُفْتَنُونَ فِي كُلِّ عَامٍ مَّرَّةً أَوْ مَرَّتَيْنِ ثُمَّ لَا يَتُوبُونَ وَلَا هُمْ يَذَّكَّرُونَ
በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መኾናቸውን አያዩምን ከዚያም አይጸጸቱምን እነሱም አይገሰጹምን

وَإِذَا مَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ نَّظَرَ بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ هَلْ يَرَاكُم مِّنْ أَحَدٍ ثُمَّ انصَرَفُوا ۚ صَرَفَ اللَّهُ قُلُوبَهُم بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَفْقَهُونَ
(እነሱን የምታነሳ) ምዕራፍም በተወረደች ጊዜ አንድ ሰው ያያችኋልን እያሉ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ፡፡ ከዚያም (ተደብቀው) ይኼዳሉ፡፡ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ፡፡

لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ
ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡

فَإِن تَوَلَّوْا فَقُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ ۖ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ
ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው፡፡

አት ተውባህ 126-129
እናታችን ዓኢሻህ - ረዲየላሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦
"يا نساء المؤمنين! إذا أذنبت إحداكن ذنبا؛ فلا تخبرن به الناس، ولتستغفر الله تبارك وتعالى، ولتتب إليه؛ فإن العباد يعيّرون ولا يغيرون، والله يغيّر ولا يعيّر!"
"እናንተ የአማኞች ሴቶች ሆይ! አንዳችሁ ወንጀል የፈፀመች ከሆነ ለሰዎች አትንገረው። ይልቁንም አላህን - ተባረከ ወተዓላ - ምህረትን ትጠይቅ። ወደሱም ትመለስ። ባሪያዎች ያነውራሉ እንጂ አይቀይሩም። አላህ ነው ሳያነውር የሚቀይረው።"

📖 [መካሪሙል አኽላቅ፣ አልኸራኢጢይ፡ 5ዐ3]

Ibnu Munewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ
ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡
وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ
ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡

ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ
ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡

وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الْمُنتَهَىٰ
መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

ሱረቱ ነጅም 39-42

GOOD NIGHT 😴😴😴
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 1️⃣1️⃣ #ረጀብ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
فَلۡیُقَـٰتِلۡ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِ ٱلَّذِینَ یَشۡرُونَ ٱلۡحَیَوٰةَ ٱلدُّنۡیَا بِٱلۡـَٔاخِرَةِۚ وَمَن یُقَـٰتِلۡ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِ فَیُقۡتَلۡ أَوۡ یَغۡلِبۡ فَسَوۡفَ نُؤۡتِیهِ أَجۡرًا عَظِیمࣰا
እነዚያም ቅርቧን ሕይወት በመጨረሻይቱ ሕይወት የሚለውጡ በአላህ መንገድ ይጋደሉ፡፡ በአላህም መንገድ የሚጋደል፣ የሚገደልም ወይም የሚያሸንፍ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን፡፡
ሱረቱኒሳእ 74

{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ مَا لَكُمۡ إِذَا قِیلَ لَكُمُ ٱنفِرُوا۟ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِ ٱثَّاقَلۡتُمۡ إِلَى ٱلۡأَرۡضِۚ أَرَضِیتُم بِٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَا مِنَ ٱلۡـَٔاخِرَةِۚ فَمَا مَتَـٰعُ ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَا فِی ٱلۡـَٔاخِرَةِ إِلَّا قَلِیلٌ }
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ (ለመታገል) ውጡ በተባላችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለእናንተ ምን አላችሁ የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ይበልጥ ወደዳችሁን የቅርቢቱም ሕይወት ጥቅም በመጨረሻይቱ (አንጻር) ጥቂት እንጂ አይደለም፡፡

{ إِلَّا تَنفِرُوا۟ یُعَذِّبۡكُمۡ عَذَابًا أَلِیمࣰا وَیَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَیۡرَكُمۡ وَلَا تَضُرُّوهُ شَیۡـࣰٔاۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءࣲ قَدِیرٌ }
ለዘመቻ ባትወጡ (አላህ) አሳማሚን ቅጣት ይቀጣችኋል፡፡ ከእናንተ ሌላ የኾኑንም ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ በምንም አትጎዱትምም፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

ሱረቱ ተውባህ 38-39
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي ظِلَالٍ وَعُيُونٍ
ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡

وَفَوَاكِهَ مِمَّا يَشْتَهُونَ
ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡

كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡

إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡

وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ
ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

كُلُوا وَتَمَتَّعُوا قَلِيلًا إِنَّكُم مُّجْرِمُونَ
ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡

وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ
ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ارْكَعُوا لَا يَرْكَعُونَ
«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡

وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ
ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ
ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?

ሱረቱል ሙርሰላት 41-50

GOOD NIGHT🥱🥱😴😴
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣2️⃣ #ረጀብ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
አልኢማም ኢብኑል ቀዪም - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
ومن الكبائر الفرح بأذى المسلمين والشماتة بمصيبتهم
"ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ በሙስሊሞች ጉዳት መደሰት እና በመከራቸው መፈንደቅ ነው።" [መዳሪጁ ሳሊኪን፡ 1/402]

Ibnu Munewor
ባስ ውስጥ ሆነህ ሌባ ላለመባል እጅህን ቆመው ለሚጓዙ መንገደኞች በተዘጋጀው መስቀያ ላይ መስቀል😓

ተሳቀቅኩኝ'ኮ
ከዘመናት በአንዱ ዲናር አል አያር የተባለ ግለሰብ ይህችን ምድር ረግጧል። ዲናር በእጅጉ አላህን ፈሪ ከነበረች እናት የተወለደ ነው። ምን ያደርጋል? የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነውና ዲናር የለየለት አመፀኛ ሆነ። እናቱ በገባ በወጣ ቁጥር «ዲናር ሆይ አላህን ፍራ! ዲናር ሆይ ወደ አላህ ተመለስ!» እያለች ትገስፀዋለች። ነብዩሏሂ ኑህ አለይሂ ሰላም «ጥሪዬ ሽሽትን እንጂ አልጨመረላቸውም!» ብለው ወደጌታቸው ስሞታ እንዳቀረቡት፤ የእናቱ ተግሳፅ መጥመምን እንጂ አልጨመረለትም። እልል ያለ አመፀኛ ሆነ። ታዲያ አንድ ቀን በቀብር ቦታ ሲያልፍ አንድ አጥንት ተመለከተ። ሲያነሳው አጥንቱ እጁ ላይ ተፈርፍሮ ዱቄት ሆነ። ዲናር በጣም ተደናገጠ። ነገ እኔም እንደዚህ አፈር እሆናለሁ ሲል ተከዘ። የሰራቸው ወንጀሎች አይኑ ላይ ተደቀኑበት። ወደሰማይ እያየ «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሙሉ ልቤ ወዳንተ ተመልሼያለሁ። መመለሴን ተቀበለኝ ... ማረኝም!» ሲል ዱዓ አደረገ። ዲናር ወደ እናቱ ተመልሶ «እናቴ ሆይ! አምልጦ የነበረ ባሪያውን ጌታው ሲይዘው ምን ያደርገዋል?» ሲል ጠየቃት። እናትየውም «ሻካራ ልብስን ያለብሰዋል፣ ርካሽ ቀለብን ይመግበዋል፣ መልሶ እንዳይጠፋም እጅና እግሩን በሰንሰለት ያስረዋል።» ስትል መለሰችለት። ዲናርም «ስለዚህ እናቴ ሆይ! ሻካራ የሆነ ሱፍን፣ የገብስ ዳቦን እና ሁለት ሰንሰለቶችን እፈልጋለሁ። እናቴ ሆይ በጠፋ ባሪያ ላይ የሚደረገውን አድርጊብኝ። አላህ ይህን መዋረዴን አይቶ እንዲምረኝ እከጅላለሁ።» አለ። እናቱ ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም። ዲናር ሁሌም ሲመሽ እየተንሰቀሰቀ ማልቀስ ይጀምራል። «ወዮልህ ዲናር! ጀሀነምን የሚቋቋም አቅም አለህ ወይ! እንዴት ደፋር ብትሆን ነው አላህን የሚያስቆጣ ህይወትን የመራኸው? ወዮልህ ዲናር! ወዮልህ!» ምሽቱ እስኪነጋ ድረስ ይንሰቀሰቃል።  በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዘወተረ። ሰውነቱ እየተለወጠ እና እየገረጣ፣ አካሉም እየኮሰመነ መጣ። እናቱ በጣም ሀዘን ተሰማት። «ልጄ ሆይ እባክህ ለነብስህ እዘንላት! ትንሽ ዕረፍት አድርግ!» ስትል ተማፀነችው። እሱም «ተይኝ እናቴ ትንሽ ልታሰር! እኔ አንቺ እና ሌሎች ወደ ጀነት ስትሄዱ እኔ ደግሞ ከጀሀነም ሰዎች ጋር ጀሀነም ስወርድ ይታየኛል። ለረዥሙ ሀገር ምቾት ዛሬን ተይኝ ዕረፍት ልጣ! ነገ አላህ ፊት የምንቆምበት ረዥም ቀን አለ። ወደ አረንጓዴዋ ጀነት ወይስ ወደ ስቃይ ማማ .... ወዴት እንደምወድቅ አላውቅም!» ሲል መልሶላት በለቅሶው ፀና። በአንድ ምሽት ዲናር ቁርዓንን እያነበበ ሳለ ሁለት አናቅፅ ጋር ደረሰ። አንቀፆቹ የሚከተሉት ነበሩ።
«فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ
በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡»
ዲናር የአንቀፁን ትርጉም እና አንድምታ እያሰላሰለ ራሱን ሳተ። እናቱ የተቻላትን አድርጋ ለማትረፍ ሞከረች። ሙከራዋ አልሆን ሲላት እንደሞተ አሰበች። ፊቱን እያየች «ልጄ ሆይ! አንተ የልቤ ሀሴት! የት ይሆን ድጋሚ የምንገናኘው?» ስትል ተከዘች። ዲናር አላህ የፃፈለት ትንፋሽ አላለቀም ነበር። ያለችውን ሰምቷል። በደከመ ድምፅ «እናቴ ሆይ! የቂያም ቀን ሜዳው ላይ ከተሰበሰበው ሰው መሀል ካጣሽኝ፤ የጀሀነም ጠባቂ የሆነውን ማሊክን ስለኔ ጠይቂው!» ሲል መልሰ። ሩሁ አካሉን ተለየች። ወደ ፈራው ጌታው ሄደ። እናቱ ሬሳውን አጥባ ከከፈነችውና ለቀብር ካዘጋጀችው በኋላ «ሰዎች ሆይ! የጀሀነም ፍራቻ ወደገደለችው ሰው የጀናዛ ሰላት ኑ!» ስትል ተጣራች። በዚያን ዘመን ለሱ ስግደት የተሰበሰውን ያህል ሰው ተሰብስቦም ሆነ፤ ለእርሱ ለቅሶ የፈሰሰውን እንባ ያህል ፈስሶ አያውቅም ይባላል። የተቀበረ ቀን ምሽቱን የዲናር ጓደኛ ዲናርን በህልሙ ተመለከተው። ዲናር አረንጓዴ ካባ ለብሶ ጀነት ውስጥ ይንጎማለላል። እየደጋገመ አንዲት የቁርዓን አንቀፅንም ያነባል።
«فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ
በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡»
ዲናር ለጓደኛው «በአላህ ክብር እና ልቅና ይሁንብኝ! አላህ ስለስራዬ ጠየቀኝ! አዘነልኝ።  ይቅርታ አደረገልኝ። ወንጀሌንም ሰረየልኝ። ይህን መልካም ብስራት ለእናቴ ንገርልኝ!» አለው። እና አላህ አዛኝና መሀሪ አይደለምን? አላህ አተ–ተዋብ አይደለምን? የተመላሾችን መመለስ የሚቀበል ጌታ አይደለምን?  እና ዲናርን የማረው አላህ እኔን እንዴት አይምረኝም? ይምረኛል። ይመራኛል። እስኪ ልታገስ!

የልብ ነገር
Fuad muna
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
{ فَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِیدَۢا بَیۡنَنَا وَبَیۡنَكُمۡ إِن كُنَّا عَنۡ عِبَادَتِكُمۡ لَغَـٰفِلِینَ }
«(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)፡፡

{ هُنَالِكَ تَبۡلُوا۟ كُلُّ نَفۡسࣲ مَّاۤ أَسۡلَفَتۡۚ وَرُدُّوۤا۟ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُوا۟ یَفۡتَرُونَ }
በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡

ሱረቱ ዩኑስ 29-39

GOOD NIGHT😴😴
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1️⃣3️⃣ #ረጀብ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣