ASD AJ LAH
759 subscribers
1.78K photos
197 videos
3 files
508 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
አያልፉም ያልናቸው እጅግ በጣም ብዙ ፈታኝ ጊዜያቶች አልፈዋል ። ዛሬ ላይ ወደ ኃላ መለስ ብለን ስናስባቸው ቀለው ይታዩን ይሆናል እንጂ በወቅቱ ቀናችንን በልተው እንቅልፍ ነስተውናል ፣ እንይዘው እንጨብጠው አሳጥተውናል ። ፈተናው አልፏል ፣ ጭንቀቱ ተረስቷል ። ሌላ ፈተና ሌላ ጭንቀት ህይወት እንዲሁ ናት ! የዘለቀ ድሎትና ምቾት የለባትም ። ለዚያም ነው አላህ ዑሊያ(ዘላቂ) ሳይሆን ዱኒያ ያላት ። ብንሞት በቀብር ብንቀሰቀስ በሲራጥ በሂሳብ ቀንም መርጋት የለም ። ዘላቂ ሰላም ፣ የማይናወጥ እርጋታ ፣ ጥም ቆራጭ ዕርካታ በጀነት እንጂ የለም ። በረባው ባልረባው አይ ዱኒያ አትበል ። ዱኒያ ይህቺሁ ናት!

አብዱ ረዛቅ
አንድን ሰው ለመለየት ፈገግታው እና አፅሙን ማስተያየት በቂ የሆነባት ቦታ… ጛ ዛ

#Gaza
ፍልስጤማዊው የአእምሮ ህመምተኛ በእስራኤል ጦር ውሾች በአሰቃቂ ሁኔታ ተነካክሶ ህይወቱ አለፈ!
.
(ሀሩን ሚዲያ፦ሐምሌ 10/2016)
.
መሀመድ ባር የተሰኘው የ24 ዓመት ወጣት ፍልስጤማዊ ሲሆን በጋዛ ሼጃያ በተሰኘችው መንደር ውስጥ ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖር ነበር፡፡እነዚህ ፍለስጤማዊያን የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ መግባቱን ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ከ15 ጊዜ በላይ ቤታቸውን እየለቀቁ ሲሰደዱ ቆይተዋል፡፡
.
ከሶስት ሳምንት በፊት የእስራኤል እግረኛ ጦር የሐማስ ታጣቂዎን ለመደምሰስ ሼጃያ መንደር ሲገባ እንደ ከዚህ ቀደሙ መሸሽ አልቻሉም፡፡በተለይም የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነው መሃመድን ይዞ መሰደድ ደግሞ ከባድ በመሆኑ በቀላሉ ከቤታቸው መውጣ እንዳልቻሉ እናቱ ናቢላ ለቢቢሲ ተናግራለች፡፡

በመጨረሻም የእስራኤል ወታደሮች እና ውሾቻቸው ወደ ተደበቅንበት ቤት መጡ እና አገኙን የምትለው እናቱ ናቢያ ከቤት እንድንወጣ አስገደዱን ብላላች፡፡ነገር ግን ውሾቹ ድንገት መሃመድን መንከስ ጀምሩ፣ ልናስቆማቸው ስንሞክር ወታደሮቹ ከለከሉን፣ እነሱም እንዲያስጥሉት ብንነግራቸውም እንቢ አሉን ስትልም ተናግራለች፡፡
.
መሀመድ የዐዕምሮ ህመምተኛ ነው ራሱን መከላከልም ሆነ መመገብ አይችልም እባካችሁ እንርዳው ብንልም ከመፍቀድ ይልቅ አካባቢውን ጥለው እንዲሄዱ እንዳስገደዷቸው አክላላች፡፡
.
በውሾች ንክሻ ምክንያት ፊቱ እና ደረቱ በደም ተሸፍኖ ሳየው አልቻልኩም የምትለው እናቱ የእስራኤል ጦር ሐኪሞች ጠርተን እናሳክመዋለን እናንተ ከዚህ ራቁ ብለውን ከአካባቢው እንዲሄዱ መደረጋቸውንም ተናግራለች፡፡
.
ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ ቤት በድብቅ ስንመለስ ግን መሀመድ ደም ፈሶት ህይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ አልፎ አገኘነው ያለችው እናቱ ናቢላ በልጃቸው ላይ አሰቃቂ ግድያ እንደተፈጸመበት፣ የእስራኤል ጦር ውሾች ልጇን እንዴት ሲነክሱት እንደነበር እድሜ ልኳን እንደማትረሳውም ገልጻለች፡፡
.
በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ38 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ዜጎች በእስራኤል ጦር ሲገደሉ ከሟቾች ውስጥ አብዛኞቹ ህጻናት እና ሴቶች እንደሆኑ የተመድ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላዊን ደግሞ በሐማስ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡
.
በርካታ ሀገራት እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት እስራኤል የጦር ወንጀል መፈጸሟን የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪዎችም በዚሁ የጦር ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ በመወትወት ላይ መሆናቸውን የዘገበው አል አይን አማርኛ ነው፡፡

©ሀሩን ሚድያ
~አንዳንዴ ስላንተ መጥፎ በመጠርጠር ብቻ የተጠመዱ ሰዎችን ለማረምና እውነትህን ለማሳየት ብለህ ብዙ አትድከም፡፡ ተዋቸው ራሣቸዉን በልተው በልተው ይለቁ፡፡ምክንያቱም ንጽሕናህን ለማሳየት በደከምክ ቁጥር ጥርጣሬያቸው እየጨመረ ይሄዳል፡፡ለምን ካልክ በልባቸው ዉስጥ ትልቅ በሽታ አለ፡፡(በሽታ ከሌለባቸው አንተ ጋር ወይ እነሱ ጋር ሸይጧን አለ)


AbuSufiyan_Albenan እውነት አለ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1️⃣2️⃣ #ሙሐረም 1️⃣4️⃣4️⃣6️⃣
አንዳንዴ

ሰዎች ማየት የሚናፍቁት እና የሚመኙት ብርሃን በተዘጋ በር ውስጥ የምትገባ ጭላንጭል ብርሃን ይሆናል…ምናልባትም ትንሽ ደግነት…ምናልባትም ትንሽ አይዞህ መባል…ምናልባትም ትንሽ ተስፋ

Be it !!❤️🙌🏼

Zemelak
لَقَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا مِن قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡
(አል- ኢምራን 164)

ወንጀልን ከሚያሥምሩ እና ሀሳብ እና ጭንቀት ከሚያስወግዱ ነገሮች መካከል በአላህ ነብይ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ ትልቁ ነው። ጁሙዐ ቀን ሲሆን ደግሞ ሰለዋት ማብዛት ይወደዳል።

የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) እርሳቸው ላይ ሰላት የሚያወርድን ሰው የሚከተለውን ብለዋል:–
                    (تُكْفِى هَمَكْ وَيُغْفَرُ لَكَ ذَنْبَكْ)
{{ ለሚያሳስብህን ነገር አላህ ይበቃሀል ወንጀልህም ይማራል}}



اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
የአላህ ሰላምና ወዳሴ በዚያ ፍቅሩ ልቦችን በሚያረጋጋው አይኖችም እሱን ለማየት በሚናፍቁት ወዱ ነብይ ላይ ይስፈን...የሀቢባችንን ፍቅር በሰለዋት ምናጎላበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን
©
https://t.me/asdajlahh
🥹🤗🥹🤗🥹🤗አልሀምዱሊላህ🥹🤗🥹🤗🥹🤗

🍃ምስጋና በችሮታው መልካም ነገሮችን ለሚሞላ ጌታ🥰

🌱ከአመት እስከ አመት……
🌱ከሳምንት እስከ ሳምንት……
🌱በቀን ውስጥ ከሰላት እስከ ቀጣዩ ሰላት……
ከወንጀላችን መጥራሪያን ላደረገልን ጌታ ምስጋና ይገባው☺️

🌼እኛን ለመማር ወንጀላችንን ይቅር ለማለት ሰበቦችን ያበዛ ጌታ ምስጋና ይገባው!!🥹

🍃አልሀምዱሊላህ! ከሳምንት ወንጀላችን ማበሻ በሆነው ቀን ላይ ሙስሊም አድርጎ ላነቃን ጌታ🥰

🌼ከቀኖች ሁሉ ምርጡ ቀን በሆነው ጁመዐ!!!…
🌱ሰለዋት ባልን ቁጥር ስማችን ረሱልﷺ ዘንድ ተደጋግሞ በሚጠራበት ቀን 🤗
🌱አንድ ሰለዋት ስንል አላህ እኛን አስር ጊዜ የሚያወድስበት ቀን 🥰
🌱የጠየቅነውን ነገር መስጠቱ የተረጋገጠበት ሰዐት ባላት ቀን ላይ ሙስሊም አድርጎ መልካም ነገሮችን የሞላልን አላህ ምስጋና ይገባው🤗🥰

🌼ጌታዬ ሆይ! ለልዕልናህ እና ለግርማዊነትህ የሚመጥን ምስጋና ለአንተ የተገባ ይሁን🥹

🍃የአላህ ሰላምና ውዳሴ አላህን ማመስገንን ባስተማሩን ለሰው ልጅ ብርሀን በሆኑት ውዱ የአላህ መልዕክተኛﷺ ላይ ይስፈን🥰


🍃🤗🍃መልካም ጁመዐ🍃🤗🍃
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣4️⃣ #ሙሐረም 1️⃣4️⃣4️⃣6️⃣
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1️⃣5️⃣ #ሙሐረም 1️⃣4️⃣4️⃣6️⃣
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1️⃣6️⃣ #ሙሐረም 1️⃣4️⃣4️⃣6️⃣
ለሸሂድ ወንድሞች በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ የተቆፈረው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ተመርቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ!
..
(ሀሩን ሚዲያ፦ሀምሌ 15/2016)
..
በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳን በመቃወም በአንዋር መስጅድ በተካሄደ ተቃውሞ  ህወታቸውን ላጡ ስድስት  ሸሂድ ወንድሞች ስም የሰደቀተል ጃሪያ ሶስት የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉድጓድ  ተቆፍሮ ለአካባቢው ማህበረሰብ  አገልግሎት  መስጠት መጀመሩን ሂባ ፋውንዴሽን አሰታውቋል።
.
ሶስቱ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ  በሂባ ፋውንዴሽን እስላማዊ ድርጅት  አሰተባባሪነት ከኢትዮ ሙስሊም መረዳጃ ማህበር በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ስሎ ቀበሌ እና ለምለም  1ቀበሌዎች  ለሚገኙ ነዋሪዎች  የንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደተቻለ የሂባ ፋውንዴሽን እስላማዊ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ  ወጣት ሙባረክ አደም ተናግረዋል ።በሰደቀተል ጃሪያ በስማቸው ንፁህ የመጠጥ  ውሃ ጉድጓድ  የተቆፈረላቸው በሸሂድ ሲራጅ ማህሙድ፣ በሸሂድ አቡበከር ኤሊያስ፣ በሸሂድ ኢብራሂም ደምበል፣ በሸሂድ ዙበይር ሙደሲር፣ በሸሂድ ጀሚል ሪድዋን እና በሸሂድ አንዋር ሱሩር ስም እንደሆነ ወጣት ሙባረክ ገልፀዋል።
.
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮ ሙስሊም መረዳጃ ማህበር ቁ 2 አባላት የሸሂድ   ወንድሞቻችን ቤተሰቦች የአልቾ ውሪሮ ወረዳ የተለያዩ የመንግስት አካላት በተገኙበት ተከናውኗል።በምረቃው ስነ ስርአት  ላይ ንግግር ያደረጉ የሸሂድ ቤተሰቦች የውሃ ጉድጓዱ በሸሂዶች ስም መቆፈር እጅግ በጣም እንዳስደሳታቸው ገልፀው፤ ሸሂዶቹ የተረሱ መስሎን ነበር የሚያስታውሳቸው አካል ማግኘታችን  በእጅጉ አስደስቶናል ሲሉ ገልፀዋል።
.
ለፕሮጀክቱ  መሳካት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉትን የኢትዮ ሙስሊም መረዳጃ ማህበር አባላት እና   የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች  የሸሂድ ቤተሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።ሂባ ፋውንዴሽን እስላማዊ ድርጅት በሰደቀተል ጃሪያ ለቤተሰባቸው የንፁህ የመጠጥ ውሃ ማስቆፈር  ለሚፈልጉ  ድርጅቱ ማንኛውንም በጎ ሰራ ለማስተባበር  ሀላፊነት  ወስዶ ለማስራትና በተፈለገው ሰዐት ለማስረከብ ሙሉ ዝግጁ መሆኑነን ወጣት ሙባረክ ተናግረዋል።
.
በሀገራችን ኢትዮጵያ  በገጠሩ ለሚኖሩ የውሀ ችግር ላለባቸው ወገኖች ከተለያዩ ድርጅቶችና አኽለል ኸይሮች ጋር በመተባበር ከ68 በላይ ንፁህ የውሀ ጉድጓድ  ማስቆፈሩንና በሺዎች ለሚቆጠሩ አባወራዎች  ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራዎች  ስርቶ ማሰረከብ  መቻሉን አሳውቀዋል።
..
©ሀሩን ሚዲያ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣8️⃣ #ሙሐረም 1️⃣4️⃣4️⃣6️⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዲህ አይነት ዳኢዎች👌
(ረሂማ ሁሴን)

ኢማን ቋሚ ነገር ቢሆን ጥሩ ነበር? ወይስ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ ማለቱ ነው ኸይሩ?

ስገዱ፣መድረሳ ሂዱ የምንባልበት የልጅነት ጊዚያችን አልፎ ለራሳችን ሀላፊነት መውሰድ ስንጀምር እና ኢማናችን መጨመር ሲጀምር እራሳችንን ከፈርድ አልፎ በሱና ኢባዳወች ቻሌንጅ ማድረግ ጀመርን፣ ሱና ሰላቶች ላይ ተጋን፣ ለይል ሰላትን አጣጣምን፣ ብዙ ቲላዋወች ከኛ ተሰሙ ፣ ደርስ ባለበት ቦታ ተገኝተን ዲናችንን በትንሹም ቢሆን ለማወቅ ሞከርን፣ እኩያወቻችን ካሉበት ዝንጋቴ እርቀን ወደአላህ ቀረብን ፣ ትንንሽ የሚባሉ ወንጀሎች ሳይቀሩ ዘገነኑን ፣ሰወች እንዴት አላህን ይዳፈራሉ ፣ሀያዕ እንዴት ጠፋ ስንል ተደመጥን።
ልክ እንደ ልጅነታችን ጊዜ ይሄም አለፈና ከአመታት በኋላ እራሳችንን በብዙ ዱንያዊ ጉዳዮች ውስጥ ሰምጦ አገኘነው። ከአመታት በፊት የነበረው ጁህድ ተረስቶ እንደልጅነት ጊዚያችን ፈርድ ሰላትን በሰአቱ ለመስገድ ስንታገል ተገኘን፣ ቁርአን ጁመአ አልያም ረመዳን ላይ የምናነሳው የሩቅ ዘመድ ሆነብን፣ ዉሏችን ለዱንያም ለአሄራም በማይጠቅም ጉዳይ ከመባከኑ ባሻገር ድካም አዝሎት የተኛ ሰውነታችን ለይል ሰላት ቀርቶ ለፈጅር መነሳት ከብዶት በተኛንበት ፀሀይ ትወጣብን ጀመር። ይቺማ ትንሽ ወንጀል ናት
አዛኝ የሆነው አላህ ይምረኛል እያልን ልባችንን በትናንሽ ጥቋቁር ወንጀሎች ብዛት አደነደነው፣ ትናንት ጉድ ያስባለን ወንጀል ላይ ተገኘን፣ ወንጀልን የማጣጣም ደረጃ እስክንደርስ ኢማናችን ተሟጠጠ። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ልባችን አላህን ፍሩ፣ ኧረ አላህ እያያችሁ ነው ፣ ኧረ ከአላህ ራቃችሁ እያለ ይወቅሰን ነበር።
ከዛም ተመለስን ፊታችን በእምባ እርሶ ምህረትን ተማፀንን ፣ ወደቀድሞ አቋማችን ለመመለስ ብዙ ታገልን፣ ፈርድ ነገሮች ላይ ላንመለስ አቋም ያዝን፣ ቁርአን ጋር አዲስ የወዳጅነት ስምምነት ፈፀምን ፣ ካለንበት ዝንጋቴ ወጥተን እራሳችንን እዚህ ነኝ ብንል የማናፍርበት ቦታ ላይ ለመሆን ወሰንን ፣ የወንጀሉን ትንሽነት ሳይሆን የጌታችንን ትልቅነት አስበን ከወንጀል ለመራቅ ተጋን። በዚህ ሁኔታ ጥቂት የማይባሉ ጊዜያትን አሳለፍን ከዛ...ከቀድሞ ኢማናችን ከፍ ብለን እንደበረርን አስበን ከሰወች የተሻለ አቢድ እንደሆንን ማሰብ ስንጀምር እና ሰወችን ማሳነስ ስንጀምር የኢባዳ ጥፍጥና ተነሳብን። የልብ እረፍት እና የኢማን ስክነት አጣን። የሰጋጅ ባህሪ አልታይብን አለ፣ ከቁርአን ከማነብነብ ያለፈ ጥቅም አጣን ፣ ይህን ጊዜ ያቺ ፈርድ ሰላት አሳልፋ የምታለቅስ፣ ቁርአን ከቀራሁ ቆየሁ ብላ እራሷን የምትወቅስ፣ ለለውጥ ጥልቅ ፍላጎት የነበራትን ነፍሳችንን ተመኘን። ከዛ ደሞ ጥሩ የኢማን ከፍታ ላይ ሆንን ከዛ ደሞ ወደቅን።
በነዚህ የኢማን ከፍታ እና ዝቅታ ውስጥ ዛሬም እንዋልላለን።
ምክንያቱም ኢማን በየሰከንዱ ከፍ ወይ ዝቅ የምትል ፣ባለችበት ለሰከንድ የማትቆይ ናት።
ሂወታችን ውስጥ የኢማን ዝቅታው ወይስ ከፍታው ነው እያመዘነ ያለው? ጥያቄው ያ ነው።

©rehimahu
በጣም መንገብገብ፣ በጣም ክፍት መሆን፣ በጣም ራስን መስጠት ብዙ ጊዜ በጣም ያዋርዳል። ሁለተኛ ሰው ወይም አማራጭ የሚታይበት ሰው ያስደርጋል። ሁሉንም ነገር ሰጥቶ አንድ ነገር እንዲሰጡት የሚለምን አይነት ሰው ያስደርጋል። ሰዎች ያልተዘጋጁበትና ያላሰቡት ዓይነት ቦታ ስትመጣላቸው ይኮራሉ። በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ የሚሉትን ዓይነት እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን… በራሳችን እጅ። አንዳንዴ "አይመቸኝም" ያስፈልጋል። አንዳንዴ "ፈልገው ይደውሉ" ብሎ መተውም ያስፈልጋል። … ሲመስለኝ።

Fuad
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1️⃣9️⃣ #ሙሐረም 1️⃣4️⃣4️⃣6️⃣