ASD AJ LAH
752 subscribers
1.79K photos
197 videos
3 files
511 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ASD AJ LAH
Photo
ልዩ የዒድ ሽልማት
🎁🎁🎁
ቲክቶክ አካውንታችንን ፎሎው ማድረግና ከታች ያለው ሊንክ ላይ ያለውን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ላይክ እና ኮሜንት ላይ አላሁ አክበር ብሎ በመፃፍ ከፍተኛ ላይክ ላገኘው ኮሜንት ወርሃዊ ያልተገደብ ኢንተርኔት ጥቅል ይበረክ
👇👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMrFS9Bwb/


የኡበይ ፍሬዎች ቁርኣን ማእከል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢድ አልአድሀ ሶላት በጋዛ ምድር እንድህ ተሰገደ 💔
በፍርስራሹ ውስጥ ባልተሞተው ኢማን ፤ በፈራረሰው ቤተሰብም ባልፈረሰው ኡኽዋ ፤
ተስፋ በሚያስቆርጠው ሁኔታ ውስጥ ባልሞተው ተወኩልና የቂን ፤ ከአፈር በበዛ ጠላት ውስጥ ባልተሰበረው ወደጀሊሉ የመጠጋት ፅናትና ኢስቲቃማ ሁሉንም ችለው ሁሉም አልፎባቸው ይህችን ቀን እንድህ አሳለፏት😢

ሁሉም ሙስሊም አለም ቢረሳቸው አላህ ግን እንደማይረሳቸው እርግጠኞች ናቸው!

ከድቅድቁ ጨለማ ከሚያስፈራው ጭጋግ ባሻገር ዛሬ በዱኒያ ባይሆን ነገ በአኼራ አላህ እንደሚክሳቸውና የተስፋን ብርሀን እንደሚያፈግግላቸው ለቅፅበትም ተጠራጥረው አያውቁምና ህይወትና መስዋዕትነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሆነውባቸው ቀጥለዋል።

ወዴት ይደረሳል ??????

ሰዒድ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1⃣1⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣
👨‍👩‍👧‍👦 አያመ ተሽሪቅ! 11,12,13

ከበሺር ቢን ሰሂም ተይዞ፡ ነቢዩ (▫️) ስለ አያመ ተሽሪቅ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا يدخلُ الجنَّةَ إلاَّ نفسٌ مسلمةٌ، وإنّ هذِهِ الأيّامَ أيّامُ أكلٍ وشربٍ..﴾

“ነፍሱ ሙስሊም የሆነች ቢሆን እንጂ ጀነትን አይገባም። እነዚህ ቀናቶች ደግሞ የመብያና የመጠጫ ቀናቶች ናቸው።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 1407
ትምህርት ሚንስትር በአረፋ ቀን በውደቅት ሌሊት በፌስቡክ ገጹ ፈተና በሚቀጥለው ቀን ሰኞ እንደሚጀምር ማስታወቁ "ንቀት የሚመስል ነው"ተባለ!
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሰኔ 9/2016
...
ትምህርት ሚንስትር በውድቅት ሌሊት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በጻፈው ጹሁፍ ፈተናው ድንገት ዛሬ ሰኞ እንደሚጀምር ገልጿል። ከዚህ በፊት በበዓል ቀን ፈተና እሰጣለሁ ማለቱ ህዝበ ሙስሊሙን ማስቆጣቱ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ በኃላም ክስተቱን ከግምት በማስገባትና መሠል ስህተቶች መደጋገማቸው እንዳስቆጣው ህዝበ ሙስሊሙ ሲገልጽ በመቆየቱ እንደገና ቀኑን ወደ ማክሰኞ ማዛወሩ ይታወሳል።
.
የአረፋ በዓል እሁድ እንደሚውል ከሳምንት በፊት ጀምሮ የሚታወቅ ቢሆንም ተማሪዎችን ባለቀ ሰአት ያውም በእኩለ ሌሊት ለሚቀጥለው ቀን ፈተና እንዲዘጋጁ በፌስቡኩ አሳውቋል። በዚህም ምክንያት በአል ላይ የነበሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ከፍተኛ ለሆነ የስነ ልቦና ጫና መዳረጉን ወላጆች ለሀሩን ሚዲያ እየገለጹ ይገኛሉ። ከቀናት በፊት ጀምሮ ይህንን ማሳወቅ የሚችል ቢሆንም በድንገት በበዓል ሌሊት ማሳወቅን ምርጫው ማድረጉ ለብዙዎቹ እንግዳ መሆኑን ሀሳባቸውን ለሀሩን ሚዲያ የሰጡ ወላጆች ጨምረው ገልጸውልናል።
.
ትምህርት ሚንስትር በተደጋጋሚ የሙስሊም በዓላትን ያላማከለ የፈተና ፕሮግራም ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ለዚህ የተደጋገመ ተግባሩም ይፋዊ ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም።

© ሀሩን ሚዲያ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 1⃣2⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣
👨‍👩‍👧‍👦 የተሽሪቅ ቀናቶች 11፣ 12፣ 13

ከኑበይሸት አልሁዘሊ (▫️) ተይዞ፡ ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أَيّامُ التَّشْرِيقِ أَيّامُ أَكْلٍ وَشُرْبٍ. وذكرٍ لله﴾

“የተሽሪቅ ቀናቶች የመብያና የመጠጫ እንዲሁም አላህን የማውሻ ቀናቶች ናቸው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1141
صباح الخير
"عسى أن نؤتي ما نُحبّ قريبًا، وأن نُهلِّل مُرحِّبين بأمانينا ، عسى أن تتحقق كل أحلامنا، وأن نحصل على كل ما تمنَّيناه وتُجاب دعواتنا ،عسى أن يَهبنا الله أعظم مما حَلِمنا به 💚

آمـــــــــين يا رب العالمين
©
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣3️⃣ #ዙልሒጃ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1⃣4⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1⃣8⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣0️⃣ #ዙልሒጃ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
﴿إِنَّ المُتَّقينَ في جَنّاتٍ وَعُيونٍ﴾
አንድ ቂ^ል ሰው በማታ የቤቱን በር ሊከፍት ሲል ቁልፉ ይወድቅበታል:: ከዚያ በጭለማው ቢዳብስ አልታይ ሲለው ወደ መንገዱ ወጥቶ መብራት ስር መፈለግ ጀመረ:: አልተገናኝቶም ነው::

©
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 2⃣1⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣
🧎‍♂️ ከመስጂድ ውጪ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን በጫማ መስገድ መዝንጋት የለብንም!

ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦

﴿خَالِفُوا الْيَهُودَ ؛ فَإِنَّهُمْ لَا يُصَلُّونَ فِي نِعَالِهِمْ وَلَا خِفَافِهِمْ﴾

“አይሁዶችን ተቃረኗቸው። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና።”

📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 652
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 2⃣5⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ይሄ ነገር🧐
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
t.me/asdajlahh

በሚቀጥለው ወር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወይም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ምን አይነት ዝግጅት እና ምን አይነት ግዜ ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን አምና ተፈታኝ ሆኘ ካሳለፍኩትኝ ሁኔታ አንጻር የተወሰኑ ጥቆማዎችን ለተፈታኞ አደርስ ዘነድ የሞነጫጨርኳት…

ፈጅር እንደተሰገደ እንድትሰባሰቡ ወደታዘዛችሁበት ትምህርትቤት በመሄድ በተዘጋጀው የየትምህርትቤታችሁ ባስ ላይ ከመጀመርያ ዙር ቀለል ያለ ፍተሻ በኋላ ገብታችሁ ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ መፈተኛ ግቢ እንደደረሳችሁ የያዛችሁት እቃ እንደ እቃችሁ ብዛት ጠንከር ላለ ፍተሻ ይበተናል፡፡(በዚህ ፍተሻ ሰዐት ቤታችሁ ጥንቅቅ አድርጋ እናታችሁ ያስተካከላችው ልብስ ከፍተሻ በኋላ እንዳልነበረ ሆኖ ሻንጣችሁ ሊጠባችሁ ስለሚችል እቃ አለማብዛቱ ይመከራል)፡፡ ግቢ ከገባችሁ በኋላ በመጀመርያ ወደተመደባችሁበት ብሎክ በመሄድ ከብሎካችሁ ስር ከሚገኛው ዶርሚተሪ ዶርም ውስጥ በሚገኘው አልጋ ልክ እየመደበ ለአንዳችሁ የዶርም ቁልፍ ይሰጣል፡፡(በአንዳንድ ግቢዎች ላይ እንደተፈታኙ ፍላጎት የዶርም ምደባ ስለሚደረግ ለማንኛውም ግዜያችሁን በአግባቡ ሊያስጠቅም የሚችል ጓደኛ ጋር ቀድማችሁ በመነጋገር ቀደም ብላችሁ በመገኘት ከዶርሚተሪ ቁልፍ በመቀበል የራሳችሁን ዶርም ለመያዝ ብትሞክሩ የተሻለ ነው፡፡) ከፈተናው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በምትፈተኑበት አዳራሽ በሱፐር ቫይዘሮች ቀለል ያለ ኦረንቴሽን ይሰጣል፡፡ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ በየእለቱ ሁለት ፈተና (ጠዋት አንደ ከከሰዐት አንድ) ይሰጣል፡፡ ከፈተና በፊት በሚደረገው ሁሉም ፍተሻ የሴት እና የወንድ ፍተሻ የተለየ ስለሆነ ኒቃብ የምታደርጉ ተማሪዎች ሳትደናገጡ ዩኒፎርማችሁን እንደለበሳችሁ ከነኒቃባችሁ በመቅረብ ፈተና መፈተን የምትችሉ ሲሆን ( ሆነ ብለው ከፈተና እንዳርቋችሁ በመጀመርያ ግቢ ላይ በሚኖራችሁ ፍተሸ ስትማሩ እንደነበራችሁት በማስክ እና በሂጃባችሁ ብትሸፈኑ እላለሁ) የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ እስከነጅልባባችሁ ያስፈትኗችኋል፡፡ ከፈተና 30 ደቂቃ በፊት መገኘት እና ፈተና ከተጀመረ ኋላ እስከ 45 ደቂቃ ድረስ መቀመጥ ግዴታ ስለሆነ በግዜ መገኘት ትእግስት አድርጋችሁ መቆያታችሁን አትዘንጉ፡፡ ወደ መፈተኛ ክፍል ስትገቡ ADMISSION CARD ፣ ማንነጽን የሚገልጽ መታወቂያ ፣ እስራስ ፣ ላጲስ እና መቅረጫ ውጭ (የእጅ ሰዐትም ቢሆን) ይዛችሁ አለመግባታችሁን አረጋግጡ፡፡
* ምግብ ከዩኒቨርሲቲው የምትመገቡ ምሳ ከ5፡30 እስከ 7፡00 ፣ እራት ከምሽቱ 12፡30 እስከ 2፡00 እንዲሁም ቁርስ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 2፡00 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በሰዐታችሁ ተገኝታችሁ መመገባችሁን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ምግቡ በአብዛኛው ተመሳሳይ ሊሆን ቢችልም የሚታማ አይነት ምግብ ስላልሆነ ብትመገቡት አትጎዱም ይልቅ ወስፋታችሁ ይከፈት ዘንድ ከታች የዘረዘርኩላችሁን ደረቅ ምግቦች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው፡፡ ካፌ ከፍላችሁ ተጠቃሚ የምትሆኑ ከሆነ ደግሞ ምግብ ሊያልቅ ስለሚችል ከሁሉም በፊት ቀደም ብላችሁ በመገኘት ምግብ ማዘዝ ይኖርባችኋል፡፡
* ከሁሉም በላይ መረሳት የሌለበት ነገር ቢኖር የሰላት ወቅት ሲሆን በዩኒቨርሲቲዎች አከባቢ መሳጂዶች ላይኖሩ ስለሚችል ዲስኮ(ደቂቃ ብቻ የሚቆጥር መዘነጫ ያልሆነ የእጅ ሰዐት) መያዝ እና የሰላት አውቃቶችን እና የቂብላ አቅጣጫን ግቢ ከመግባታችሁ በፊት ማረጋገጥ ተመራጭ ነው፡፡ ለፈጅር ሰላት ለመነሳት ብቸኛው መፍትሄ በግዜ መተኛት ስለሆነ ከአልባሌ መዝናኛ ቦታዎች ራስን ማራቁ ይመረጣል፡፡ የተፈታኙ ብዛት ከፍተኛ በሆነበት ዩኒቨርሲቲ ብዛት ያለው ጀማዐ ሊከለከል ስለሚችል ለደህንነታችሁ ሲባል እናንተ ብሎክ ጋር ካሉ ተማሪዎች ጋር ብቻ ባዶ በሆኑ ዶርሞች ወይም ከዶርም አጠገብ በሚኖረው ግሪን ኤሪያ ላይ ብትሰግዱ የተሻለ ነው፡፡
* ዶርም ውስጥ ሁሉም ተማሪ የየግሉ ሎከር ስለሚኖረው ተመሳሳይ መክፈቻ በመይገኝለት የጋን ቁልፍ መቆለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡
* ተማሪዎች ሰብሰብ ብለው ከሚያመሹባቸው ቦታዎች ራስን ማራቁ ከደህንነት በተጨማሪ በአቻ ግፊት ምክንያት ከሚመጡ ፈሳዶች ይከላከላል፡፡ በተረፈ በሚኖራችሁ ትርፍ ግዜ መጽሀፍ ማንበብ ከድብርት ሙድ ውስጥ ያወጣችኋል፡፡
* በፈተና የመጭሻ ቀን በየቦታው የቡድን ጸቦች ስለሚኖሩ ከዶርም አካባቢ ራቅ በማለት ራሳችሁን የምትጠብቁበት ቦታ ብትሆኑ እና በየትኛውም አይነት ጸብ እጃችሁን ከማስገባት መቆጠብ ይኖርባችኋል፡፡
* ካልተመደባችሁበት ብሎክ እና ወንዶች ወደሴቶች ዶርም ሴቶች ወደወንዶች ዶርም መሄድ ካለማወቅ ከሚፈጠሩ ምናልባትም ቅጣታቸው ከፍ ያለ ሊሆን ከሚችሉ ስህተቶች ውስጥ ነው፡፡
* ለማንኛውም ፈታኝ ፣ ጥበቃ ፣ የስራ ሀላፊ በተለይ ለማንኛውም ከጸጥታ አካላት ለሚመጣ ትእዛዝ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይኖርባችኋል፡፡
* ዳቦ ፣ ነጠላ ጫማ እና ፈሳሽ ምግቦች ሱቅ ላይ ስለሚገኙ ባትሸከሙ…
*
ልትይዟቸው የሚገቡ …
1 ታጣፊ የኪስ መስገጃ እና በመጠኑ አነስ ያለ ቁርዐን(ብዙ ተፈታኝ የሚዘነጋቸው)
2 በትርፍ ግዜ ሊነበቡ የሚችሉ አጠር አጠር ያሉ አዝና እና አስተማሪ መጽሀፍት(ሁለት መጽሀፍ በቂ ነው)
3 የ ATM ማሽን ያሉባቸው ቦታዎች በጸጥታ እና በንብረት ጥበቃ ጉዳይ ዝግ ሊሆኑ ስለሚችሉ ለዝርፊያ የሜጋልጣችሁን ቢበዛ እስከ 1000 ብር ካሽ
4 የምትመገቡት ምግብ መላመዱ ሊከብዳችሁ እና እንደ ቤት ላይሆን ስለሚችል ከቤት የተዘጋጁ ደረቅ ምግቦችን እና የታሸጉ ምግቦችን(ለውዝ ቅቤ ፣ ማርቤላ) መያዝ
5 ፍተሸ ሰአት እንዳትቸገሩ ከዪኒፎርም ውጭ ሁለት ተቀያሪ ልብስ ብቻ መያዝ
6 ማንነትን ሊገልጽ የሚችል መታወቂያ (የትምህርት ቤት ፣ የቀበሌ ፣ ብሄራዊ መታወቂያ)
7 የሻንጣ ጋን ቁልፍ(ትንሿን ብቻ)
8 ለፍተሸ ምቹ የሆነ ንብረታችሁን በሙሉ በትክክል ሊይዝ የሚገባ ሻንጣ ወይም ቦርሳ
9 የሰላት እና ሌሎች ግዜያችሁን አብቃቅታችሁ ለመጠቀም ዲስኮ ሰዐት መያዝ
10 ለሴቶች የወር አበባ መቆጣጠሪያ(ሞዴስ)
11 የታዘዘላችሁ መድሀኒት ካለ እስከነማዘዣ ወረቀቱ ይዛችሁ መገኘት

ባትይዟቸው የሚመረጡ እና እንዳትይዟቸው የሚከለከሉ
1 በጠንካራ ማይካ ወይም ፕላስቲክ ፣ በጠርሙስ እና በብረት የታሸጉ ማንኛውም አይነት ነገሮች
2 እንደ በሶያሉ ዱቄት ይዘት ያላቸው ምግብ ነክ ነገሮች ጋር አደገኛ እጾች ስለሚገቡ የጸጥታአካላት ሊያስጥሏችሁ ይችላሉ
3 ጥቅል ሶፍት(ግቢ ውስጥ ባሉ ሱቆች ውስጥ ስለሚገኝ ባትይዙ)
4 ከስክስ ሰፍቲ የወንድም የሴትም ጫማ

አላህ ከናንተ ጋር ይሁን፡፡
ጽሁፉን በከፊልም ሙሉውንም ሀሳባችሁንም አድርጋችሁ ለተማሪዎች ማጋራት ትችላላችሁ፡፡

ወንድማችሁ ASD
https://t.me/asdajlahh