ASD AJ LAH
753 subscribers
1.72K photos
194 videos
3 files
486 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
የአብዛኛው ወጣት ጥያቄ ይመስለኛል...

"የቱ ጋር ነው የተሳሳትኩት ፈጣሪዬ??.. ለምን እድገቴ እንዲህ የዘገየ መሰለ?.. የቱ ነገር ነው ከህልሜ ጋር ያለኝን ርቀት ያሰፋብኝ?.. የቱ ልምምዴ?.. የትኛውስ ክፉ ስራዬ ነው መንገዴን ያረዘመው?......"

ወጣቱ ይጠይቃል.. አሁን ግን የምር ነው የሚጠይቀው.. መልሱ ደግሞ ለአሁን አጥጋቢ ባይመስለንም እንዳንሰላች.. 🙏
የእውነት ፈጣሪያችን የሻትነውን ሁሉ የሚሰጠበት የራሱ የሆነ ፍፁም ትክክል የሆነ ወቅት አለው.. 😊

'ነገርን ሁሉ ውብ አድርጎ የሰራው በጊዜው ነው አዎ በጊዜው!!.. በእርግጥም እኛም ቀን አለን እሺ አህባቢ 👐


Afdel
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 0⃣6⃣ #ዙልቀዓዳ  1⃣4⃣4⃣5⃣
ወንድም ፈቂህ ገለቶ ወደ አኼራ መሄዱን ሰምተን አዝነናል።
በአንድ ኢንተርቪው ላይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለቤበሚያደርገው የዳዕዋ ስራ ምክንያት በቀናት ልዩነት ሶስት ግዜ እንደታሰረ እንዲሁም ከቤተሰቦቹ ከአካባቢው ሰዎች ተፅእኖ ያድርበት እንደነበር ሲያስረዳ ፅናቱን ለራስ ያስመኝ ነበር።
አላህ ይዘንለት
ASD AJ LAH
ወንድም ፈቂህ ገለቶ ወደ አኼራ መሄዱን ሰምተን አዝነናል። በአንድ ኢንተርቪው ላይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለቤበሚያደርገው የዳዕዋ ስራ ምክንያት በቀናት ልዩነት ሶስት ግዜ እንደታሰረ እንዲሁም ከቤተሰቦቹ ከአካባቢው ሰዎች ተፅእኖ ያድርበት እንደነበር ሲያስረዳ ፅናቱን ለራስ ያስመኝ ነበር። አላህ ይዘንለት
ይሄ ዛሂድ ይህ መንገደኛ የአላህ ባሪያ ማለፉን ሰማሁ😢
ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂ ራጂኡን !

ዱኒያን ለአላህ ብሎ ትቶ በዝህድና የአላህና መልእክተኛውን መልእክት እያስተላሉፉ ኖሮ መሞት ምንኛ መታደል ነው !

እንዳለመታደል ሆኖ ልፋቱን ባናግዘውም ተገቢውን ክብር ባንሰጠውም አላህ ግን አንዱንም መልካም ስራውን ሳያስቀር በብዙ አባዝቶ ትልቅ ደረጃን እንደሚያጎናፅፈው ተስፋ እናደርጋለን !

አላህ ሆይ በራህመትህ ተቀበለው ከዚህች ዱኒያ በበለጠቺዋ ጀነትህም አጣቅመው !

ሰዒድ
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ.pdf
1.9 MB
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ
==================
ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ።

ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል።

https://t.me/MuradTadesse/35708

*
ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት።

https://t.me/MuradTadesse/35742


ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር!

አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር።

የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል።
https://t.me/MuradTadesse/35632?single
ከተቋማችንም ጎን እንቁም።

የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
ASD AJ LAH
ወንድም ፈቂህ ገለቶ ወደ አኼራ መሄዱን ሰምተን አዝነናል። በአንድ ኢንተርቪው ላይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለቤበሚያደርገው የዳዕዋ ስራ ምክንያት በቀናት ልዩነት ሶስት ግዜ እንደታሰረ እንዲሁም ከቤተሰቦቹ ከአካባቢው ሰዎች ተፅእኖ ያድርበት እንደነበር ሲያስረዳ ፅናቱን ለራስ ያስመኝ ነበር። አላህ ይዘንለት
ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር ታሪክ አለን ከዚህ ሰው ጋር፡፡
በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ በጎዳና ላይ ደዕዋ ሲያደርግ ታውቁታላታችሁ፡፡ ምንም ማንንም የማይፈራ ሙጃሂድ ነው። ስፒከሩ በተዳጋጋሚ ታስሮበት በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተትም አጋጥሞኛል፡፡

ከልጅነት እስከ ወጣትነትና ጎልማሳነት ምናልባት እስካዛሬዋ እስከመጨረሻዋ የዱንያ ላይ ቀን ድረስ ሐያቱን በሙሉ በደዕዋ አሳልፏል፡፡ አላረፈም። ኢስላምን ለማድረስ ሁሌ እንደተጓዘ ስለማየው ቤት ይገባ ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ ብዙ ጊዜ፡፡ ዛሬ ሻሻመኔ ላይ ድንገት ማረፉን ሰማሁ፡፡

ፈቂ ገለቶ አላህ ይዘንልህ፡፡

ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፤
በሞተበት ነገር ላይም ይቀሰቀሳል፡፡

ደጋግ ባሮችህ ወዳንተ እየመጡ ነው።
አላህ ሆይ!
ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ እንላለን ።

Abx
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 0️⃣7️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
የበታቻችሁን ተመልከቱ ሲባል ብዙዋችን የምንዞረው ከኛ ይበልጥ ድሃ ወደሆኑ ሰዎች ነው ። አላህ በአንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ከመዘንጋት ይመስላል ። ይህ ዝንጋቴ ነው ትክክለኛውን ሹክር እንዳናደርግ የሚያግደን ። እዚሁ መንደር እገሌ የተባለ ሰው በዚህ በሽታ ስለተጠቃ ገንዘብ እንርዳው ሲባል እንመለከታለን ። አላህ በታማሚው ቦታ ስላላደረገን ለማመስገን ሁለቴ ማሰብ የሚፈልግ አይደለም ። ጤና ሐብት መሆኑ የሚገለፅልን ሆስፒታሎች ውስጥ ስናዘወትርና እንዲህ ያሉ መሰል ታካሚዎችን ስንመለከት ነው ፣ ዕድሜ ፀጋ መሆኑ የሚገለፅልን መቃብሮችን ስንዘይር ነው ፣ ከሁሉ በላይ ግን «ዛሬ»ን የመሰለ ስጦታ የለም ። ለዚህም ነው ። ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ‹‹ አልሐምዱሊላሂ ለዚ አህያና……›› የምንለው ። አዎ! ትንሿን ሞት አስሙተህ በዚያው ሳታስቀር ህያው ያደረግከን አላህ ሆይ ምስጋና ይገባህ የምንለው ። ቀናችንንም በምስጋና እንድንጀምር የተደረገውም ለዚሁ ነው ። አላህ ‹‹ ዛሬን ›› ሰጥቶሃል ። እርሱ የሚወደው አልያ የማይወደው ማድረግ ግን የኛው ምርጫ ነው ። ከወደደው ጥቅሙ ለኛ ካልወደደው ጉዳቱ ለኛ እንጂ እኛ ቀኑን ሙሉ ብናምፀው አላህን አንጎዳውም ቀኑን ሙሉ ብናመልከው አላህን አንጠቅመው ። ለእኛው ነው ወገን ለእኛው !

አብዱ ረዛቅ
ASD AJ LAH
ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር ታሪክ አለን ከዚህ ሰው ጋር፡፡ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ በጎዳና ላይ ደዕዋ ሲያደርግ ታውቁታላታችሁ፡፡ ምንም ማንንም የማይፈራ ሙጃሂድ ነው። ስፒከሩ በተዳጋጋሚ ታስሮበት በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተትም አጋጥሞኛል፡፡ ከልጅነት እስከ ወጣትነትና ጎልማሳነት ምናልባት እስካዛሬዋ እስከመጨረሻዋ የዱንያ ላይ…
ጠያቂ👉🏻 ላለፉት 21 አመታት በየመንገዱ ዳእዋ ስታደርግ መድከም መሰለቸት ተስፋ መቁረጥ አልገጠመህም?

ፈቂ 👉🏻ከአላህ የተሰጠኝ ቅዋ አለ አንድም ቀን እንደዛ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ዳእዋን ስጀምር ሰዎች እናቴ ጋር ሄደው ይህው አንድ ልጅሽ አበደ መንገድ ለመንገድ መልፍለፍ ጀመረልሽ አሏት። እኔም አብሽሪ ይሄ የአንቢያዎችና የነብያቶች ስራ ነው ብዬ አሳመንኳት። አሁን እኔ የሚያሳስበኝ ይሄን ስራ የሚያስቀጥል ተተኪ ትውልድ አለመኖሩ ነው። እኛ ሰዎችን ወደ ሰላም ካልተጣራን ሸይጣን ወደ እሳት ይጣራብናል።

አላህ ይዘንልህ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 0⃣8⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
በመላው አለም የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ከሀገራቸው የተፈናቀሉበትን "አል-ናቕባ" 76ኛ ዓመት ዘክረዋል!
...
(ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 7/ 2016)
...
በዌስት ባንክ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ዛሬ ግንቦት 15 2024 እለት "የአል-ናቕባ" ማለትም ታላቅ መቅሰፍት የወረደበት እለት የአደጋ ግዜ ሳይረን ለሰባ ስድስት ሰከንድ በማሰማት ዘክረዋል።
...
እ.ኤ.አ ግንቦት 15 ቀን 1948 የእስራኤል ወታደሮች ፣ ሚኒሻዎችና ታጣቂዎች 750,000 ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው በማፈናቀል እንዲሰደዱ ያደረጓቸው ሲሆን ላለፉት ሰባ ስድስት አመታት ወደ ሀገራቸው እና መሬታቸው እንዳይመለሱ በማገድ በጎረቤት ሀገራት የስደተኛ ጣቢያዎች ለመኖር የተገደዱበት ክስተት የተከሰተበት በመሆኑ ፍልስጤማውያን ዕለቱን አል-ናቕባ ማለትም ታላቁ የመከራ ቀን በሚል በየአመቱ ይዘክሩታል።
...
በዚህ አመት እስራኤል ባለፉት ሰባት ወራት በጋዛ በመፈፀም ላይ ያለችው ጥቃት ከ34,000 በላይ ንፁሀን ፍልስጤማውያንን በተገደሉበት ሁኔታ እና ጥቃቱ በቀጠለበት ሁኔታ የሚዘከር መሆኑ ፍልስጤማውያን እለቱን ከሰባ ስድስት አመታት በፊት ቅድመ አያቶቻቸው፣ አያቶቻቸው ከተሰማቸው ሀዘን ተመሳሳይ በሆነ ወይም በላቀ ከባድ ሀዘን ተውጠው የሚዘክሩት እንደሚሆን የአልጀዚራው ከፍተኛ ፖለቲካ ተንታኝ " ማርዋን በሻራ" አስተያየቱን ይገልፃል።
...
እስራኤላዊው የታሪክ ምሁር "ፕ.ሮ ኤላንን ባፔ"የእስራኤል መንግስት ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ማፈናቀል ከ1948 ቀደም ሲል የጀመረ ሲሆን በእኔ ሃሣብ አል-ናቕባ 1948 የተከሰተ ቢሆንም ላለፉት ሰባ ስድስት አመታት የቀጠለና ያልተቋረጠ አሳዛኝ ክስተት ነው። በማለት እለቱን ገልፆታል።
...
©ሀሩን ሚዲያ
አብዝሃኛዎቻችን "ማጣት" የሚለውን የምንገልፀው ገንዘብ (ሀብትን) ማጣት በሚል ነው ። ይህንንም ማጣት ከአላህ የተላከ ፈተና ወይ ደግሞ የአላህ ተወዳጅ ባለመሆኑ ያጣን የሚመስለን ብዙ ነን ። ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው ። ነገሩ ይህ አይደለም ። አንድ ሰው በዱኒያ ሳለ ገንዘብ ሊያገኝም ሊያጣም ይችላል ። ይህ በአላህ ዘንድ የተወደደም የተጠላም ለመሆኑ ምስክር ሊሆን አይችልም ። የአላህ ወዳጆች ፣ ነብያቶች በድህነትም በሀብትም አልፈዋል ። ድሃ በነበሩ ሰዓት አላህ ጠላኝ አላሉም ። በሀብታቸው ሰዓትም የአላህ ውዴታ ነው ብለው አልተኩራሩበትም ። ብዙ የአላህ ጠላቶች በሀብት ተንበሽብሸዋል ፣ የአላህ ወዳጅ ሆነውም በድህነት አረንቋ ውስጥ ያሉ ፣ የታረዙ ፣ የተቸገሩ ፣ የተራቡም እጅግ በጣም ብዙ ናቸው ። ለገንዘብና ለቁስ ያለን የተጋነነ ምልከታ ሚዛኖችን ሁሉ ወደ እርሱ እንድናስጠጋ አደረገን እንጂ ገናና ሀብታም ሆነው አላህ የሌላቸው ቁጥር ስፍር የላቸውም ። በገንዘባቸው አላህን አላገኙበትም ፣ ሂዳያን አልገዙበትም ፣ እስልምናን አልተቸሩበትም ። ከዚህ አንፃር ደግሞ ገንዘብ ያለ ኢስላም ምንም ነው ምንም! ሁሉም ከኢስላም በኋላ ነው ። ኢስላም የተሰጠው ሰው የእስልምናን ኢዕማ ሊያውቅ ግድ ይለዋል ።ይህን ያወቀ ደግሞ በሁሉ ነገር ቢፈተንም አላህ መርጦ ኢስላምን ስለሰጠው ያመሰግናል ። ይህ ነው ምስጋና ። ይህ ነው መቸር ። አላህን ያገኘ ምን አጣ ? አላህን ያጣስ ምን አገኘ ?!

አልሐምዱሊላሂ አላ ኒዕመቲል ኢስላም

©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በምድር እና በሰማይ ተወዳጅነትን የምታገኙበት…መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው ፣ ለወንጀላቸው መሀርታን አግኘተው በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በሰላት በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 0️⃣9️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
‏قالﷺ : مَنْ صلَّى عليَّ صلاَةً، صلَّى اللَّه علَيّهِ بِهَا عشْرًا.

‏- صَلُّوا عليه🤍
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣0️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ተስፋ ማስቆረጥንማ ቴሌን ማንይቻለው
﴿من رأى مبتلًى فقال: «الحمدُ للهِ الذي عافاني مما ابتلاكَ به، و فضَّلني على كثيرٍ ممن خلق تفضيلًا»، لم يُصِبْهُ ذلك البلاءُ.﴾
ሁሉም የራሱ የሆነ መለያ ጊዜ አለው!

የታማኝነት ቅኔ በፈተናዎች ወቅት ይፈታል:: ትክክለኛ የፍቅር ትርጓሜ ጥቅም ሲያልቅ ከተፃፈ መዝገበ ቃላት ይገኛል:: ባል ለሚስቱ ያለው ቦታ ሚስት በታመመች ጊዜ ሲገለጥ ሚስት ለባል ያላት ቦታ ደግሞ ሲደኸይ ይብራራል:: ከጓደኝነት ጋር በችግር ወቅት ተዓሩፍ ታደርጋለህ:: ልጅ ለቤተሰቦቹ ያለው እንክብካቤ እርጅና ሲነካቸው ተበጥሮ ይታያል:: ወንድማማቾች እርስ በዕርስ ያላቸው መተዛዘን ውርስ ሲካፈሉ የቀትር ፀሐይን ይሆናል::

ሁሉም ይጠራ ዘንድ መደፍረስ ግድ ይላልና እስከዚያ "ስትወድ የዛሬ ወዳጅህ አንድ ቀን ጠላትህ እንደሚሆንና ስትጠላም የዛሬ ጠላትህ አንድ ቀን ወዳጅህ ሊሆን እንደሚችል እያሰብክ ይሁን::" የሚለውን የቀደምቶች ዘመን አይሽሬ ምክር ተግባራዊ አድርግ::

Mohammad