ASD AJ LAH
753 subscribers
1.72K photos
194 videos
3 files
486 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
በቀን 3 ጊዜ የምትበሉ ሰዎች ምን አስባችሁ ነው? ሀሰን አል በስሪ (ረህመቱላሂ አለይህ) በቀን 3 ጊዜ ለሚበላ ሰው ቤተሰቦቹ መኖ ቤት ይገንቡለት ብለዋል:: አስቡበት:: ምግብ ቀንሱ:: ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትም ሆነ ነፍስ ከአላህ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ወደ አላህ ቀረብ እንድትል ትልቅ አስተዋፅዖ አለው:: ሆድ ሲሞላ ጭንቅላት ባዶ ይሆናል ይባልስ የል¿

Mohammadammin
ከፊልም የተወሰደ ምስል ነዋ የሚመስል…ይህ በገሀዱ ዐለም በኛዋ ውድ ሀገር ፈለስጢን የተፈፀመ ውድመት ነው። አላህ ብስራቱን ቅርብ ያድርግላቸው
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣8⃣ #ሸዋል  1⃣4⃣4⃣5⃣
ከእለታት ባንዱ ቀን ... የባግዳዱ 'ጠቢብ-ዕብድ' ባህሉል እና ሰይዱና ጁነይድ ተገናኙ ... ሰይዱና ጁነይድም ከ'እብደቱ' ባሻገር ያለውን ጤንነት የተገነዘቡ ነበሩና ምክር እና ተግሳፅ ይሰጣቸው ዘንድ ጠየቁት ... ባህሉልም "አንተ እኮ እውቅ አሊም ነህ የኔ ምክር አያሻህም" በማለት መልስ ሰጠ ... ሰይዱና ጁናይድ ግን እንዲመክራቸው አጥብቀው ወተወቱት ...
*
ባህሉልም ... "እንግዲያውስ ስለ ሶስት ነገሮች እጠይቅህና በትክክል  ከመለስክልኝ ምክር እለግስሀለሁኝ" አለ ... በመቀጠልም "እንዴት መናገር እንዳለብህ ፤ እንዴት መብላት እንዳለብህ እና እንዴት መተኛት እንዳለብህ ታውቃለህን? " ሲሉ ጠየቁት ... ሰይድና ጁነይድም "እነዚህንማ ጠንቅቄ አውቃለሁ ...  ስናገር - በትሁት እና በለዘብተኛ ድምፅ ... ነጥቡ ላይ አተኩሬ እናገራለሁኝ የምናገረውን ሰው ቀልብም ላለመሰበር እጅጉን ተጠንቅቄም አስረዳለሁኝ ፤ ስበላ - በቅድሚያ  እጄን እታጠባለሁኝ ... ከመጀመሬ በፊት ቢስሚላህ ብዬ የአላህን ስም አወሳለሁ ... ስመገብ በአግባቡ አኝካለሁ ስጨርስ ደግሞ አልሃምዱሊላህ እላለሁ ፤ ስተኛ - ከመተኛቴ በፊት ውዱዕ አደርጋለሁ ... ንፁህ ነገር መልበሴን  አረጋግጩ  በሸሃዳ አሳርጋለሁኝ " አሉት
*
" ጥሩ! አለ ባህሉል ... "የምታወራው ነገር ውሸት ከሆነ በለዘብታ እና በትህትና ማውራትህ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል ... የንግግር ዋናው ነጥብ ንግግሩ እውነት መሆኑ ላይ ነው ... ስትበላም በተከለከለ እና ሐራም በሆነ ምግብ ላይ የአላህን ስም ማወሳትህ ትርጉም የለውም ... ከሁሉም አስቀድሞ የምትበላው ምግብ ከሐራም ፣ ከየቲም ሀቅ ፣ ቧሏ ከሞተባት ሴት ሀቅ እና ከሰዎች ሀቅ የጠራ መሆኑ ማረጋገጥ ነው ወሳኙ አደብ ... ስትተኛም ቢሆን ልብህ በምቀኝነት ፣በክፋት እና በሙስሊም ወንድምህ ጥላቻ ተሞልቶ ... በውዱዕ እና በመኝታ ዚክሮች ታጅበህ መተኛትህ  ፋይዳ የለውም ... በንፁህ ልብ የተኛ ነው  ሙዕሚን ሆኖ አነጋ የሚባለው ... ገባህ! እነዚህ ናቸው መሰረታዊ ጉዳዬች የተቀሩት የእነዚህ ተከታዬች ናቸው" ሲል የጠቢብ ምክሩን ለገሳቸው
*

©Fuad Yasin
ሸዋል ላይ አገባለሁ ብሎ ያቀደውን ጀለስህን ስታስታውስ
አሁንኮ የወደፊት ሚስትህ "የወደፊት ባሌ በእውቀት የበለፀገ: በገንዘብ የሞላለት: መልካም ስነ-ምግባር መታወቂያው የሆነ ሰው ነው::" በሚል ሀሳብ ውስጥ ልትሆን ትችላለች:: አንተም በሀሳብ የወደፊት ሚስቴ "ሲያዟት እሺ የምትል: ለእኔም ሆነ ለቤተሰቤ የማትጎረብጥ: ልጆቼን በዲናቸውም ሆነ በዱንያዊ ነገሮች ኮትኩታ የምታሳድግ ናት::" እያልክ ይሆናል::

ግን አንተ የት ነህ? አንቺስ የት ነሽ? ለዚህ ስብዕና እየተዘጋጃችሁ ነው? ያም ሆነ ይህ የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁንና ደህና እደሩ!

©
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣9️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
አዲስ አበባ ላይ ይህንን ባነር ይዘው "ሲሰብኩ" የነበሩ ሰዎችን ፖሊስ እንዳሰራቸው እዚህ መንደር ሲዘዋወር አየሁ። ትምህርቱ ለሀይማኖተኛ አይደለም ለቄሳርም እንደሚያስደነግጥ የሚያስተዛዝብ ነው። የክርስትናው አለም አምላክ "ይቅር ባይነቱን" አክቲቬት ሊያደርገው ዘንድ የሚፈስ ደም ማየት ይፈልጋል። የአንተ ንስሀም ሆነ በጸጸት ከሀጥያትህ መራቅህ እግዚአብሔር እንዲምርህ የሚያደርግ ሚና የላቸውም። ብቻ ደም አቅርብለት እንጅ ስርየቱ ይረጋገጥልሀል። ከዚያ በኃላ የፈለግከውን ሀጥያት ብትሰራም "በጸጋው ድነሀልና" ከልካይ የለብህም። ካንተ ጭምትነት ይልቅ ለእግዚአብሔር የሚፈሰው ደም የበለጠ ያስፈልገዋል። ትምህርቱን ለመቀበል አይደለም ለመስማትም ይረብሻል..!

___
https://t.me/Yahyanuhe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▣ የተማሪዎች ፈተና ራሱ እንደዚህ አይታረምም😁!


®Sαlαh Responds 🎙
#የኔ እይታ 51

አላህ ሲፈልግ.....

ህይወታችን ውስጥ በጣም ብዙ ተሳክተው ልናያቸው የምንጓጓላቸው ጉዳዮች አሉን። ጉዳዩን እጅግ በጣም ከመፈለጋችን ብዛት ተሳክቶ ለማየት ብዙ የምንደክምለት፣ አቅመቢስነታችንን አውቀን ሁሉን ቻይ አምላካችንን እርዳታውን የምንለምንለት፣ አቅማችንን ሁሉ አሟጠን ለብዙ አመታት የምንለፋለት፣ሰበባችን ብቻ በቂ እንዳልሆነ በማወቃችን ጉዳዩን ወደጌታችን አስጠግተን ውጤቱን በጉጉት የምንጠብቅለት ከባዱ ሀጃችን!
ያ ልባችንን ያስጨነቀው፣ ያ ተሳክቶ ለማየት የምንጓጓለት ፣ ያ የደስታችን መገኛ እንደሆነ ያመንበት ሀጃችን.....
ያ ሀጃችንን አላህ ለኛ እንደሚጠቅም እና ጊዜው እንደደረሰ ሲወስን ወደ እኛ የሚመጣበት ፍጥነት ያስገርማል። ሰርፕራይዝ ተደርጋችሁ ታውቃላችሁ?
ካወቃችሁ የሚያስደስታችሁ ነገር የናንተን ምንም አይነት ልፋት ሳይፈልግ በሌሎች ልፋት ውስጥ አልፎ እናንተ ጋር ያልተጠበቀ ደስታ ሁኖ ሲመጣ ያለውን ስሜት ምን አልባት በደስታ የሚፈስ እምባችሁ እንጂ ሌላ ምንም አይገልፀውም! ይህ በሰው ሰርፕራይዝ መደረግ የሚፈጥረው ስሜት ነው።
ሰርፕራይዝ የሚያደርግህ አላህ ሲሆን የጉዳዩን ትልቀት እና ውበት እንዲሁም ሂወትህ ላይ የሚፈጥረውን ለውጥ አስበው.........
አላህ ያ ሀጃህ ላንተ እንደሚጠቅም ከወሰነ እጅን አፍ ላይ በሚያደርግ ፍጥነት ያስደምምሀል። ብቻ እርሱ ይፈልግ ያኔ በ ك እና በ ن መካከል ባሉ ቃላት ብቻ ለአመታት ያስጨነቀህን ጉዳይ ፈፅሞት ታገኘዋለህ።
  አላህ እስኪፈልግ ሶብ'ሩ.....

©rehima
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 0⃣1⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ደመናው ሲጠቋቁር ነጎድጓዱ ሲያጉረመርም ዝናቡ ሊያለቅስ ሲል ነበር የዐስር ሰላትን ልሰግድ አለምባንክ በሚገኘው ሙስዐብ መስጂድ የታደምኩት። ኢማሙ እያሰገዱን ሰላታችን ካጋመስን ወዲህ ጥቁሩን ደመና መሸከም በቃኝ ያለው ሰማይ ዶፍ ዝናብ ያወርድ ጀመር…ኢማሙ በተረጋጋ መንፈስ ሰላታችን አስጨርሰውን ምእመኑ አዝካሩን በሚያጠናቅቅበት ግዜ ከመስጂዱ አወለ ሰፍ ሁለት እድሜያቸው በሀያዎቹ መጀመርያ ላይ መሆናቸው የሚያስታውቅ ወጣቶች ብድግ ብለው ቁርዐን ይዘው ያካፋፍሉ ጀመር…
ይህ አይደለ ትርፍ…ይህን የመሰለ አንድ እንኳን ወጣት እያለ ኢንሻአ አላህ አንወድቅም…አላህ ንግዳቸውን ትርፋማ ያድርገው
በዚህ ሌሊት ስንት ሰው ወደ አኼራ ተሻግሮ ይሆን ? ይህችን ንጋት ሳይታደል ከሞት የተገናኘ ስንት ይሆን ? እኔና አንተ ግን አንግተናል :: እኔና አንቺ ግን አንግተናል :: ለምን ? አላህ ስለፈቀደ ማለት ነው :: ምስጋና ይድረሰው :::

ሁሉም ነገር ለእርሱ "ኩን ፈየኩን!" ነው :: ስለዚህ ባደለህ ንጋት ውስጥ መልካም ነገርን ይወፍቅህ ዘንድ ጠይቀው :: ትላንት ያገኘኸውን አይነት ብቻ ሳይሆን አገኘዋለሁ ብለህ የማታስበውን እንኳ ስጠኝ በለው :: በሩን ደጋግመህ አንኳኳ :: አዕምሮህ አንተ አትችልም ብሎ የሚነግርህን ነገር በሙሉ ጠይቀው :: ምክንያቱም እርሱ የአለማት ጌታ ነው :: እሱ የተዓምራት ሁሉ ባለቤት ነው :: እሱ "ሁን!" ብሎ ነገሮችን ሁሉ እንዲሆኑ የሚያስችል ጌታ ነው ::

አላህ በመልካም ነገሮች surprise ያድርጋችሁ

©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በምድር እና በሰማይ ተወዳጅነትን የምታገኙበት…መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን አግኘተው በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በሰላት በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 0️⃣2️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
« ሙትቻ ላሉህ ሰዎች እራስህን ለማስረዳት አትሞክር። ለሞትክባቸው ሰዎች የምታባክነው ጊዜ አይኑርህ። ውበትህ ግለፅ ሲወጣ የመጣ ሁሉ ውበትህን አይቶ ላይሆን ይችላልና በአመዳምነት ዘመንህ ላይ ውበትህ የታያቸውን ጠበቅ አድርገህ ያዝ።
ቆንጆ መሆንሽን ከሚያደንቁት የበለጠ የሚያስጠላብሽን ሊያስውቡልሽ የሚጣጣሩትን አትዘንጊ። ቁስልሽን በሰው አትከልዪ። የሚመክሩሽ ሁሉም ከጥቃት አይጠብቁሽም። ጥንቃቄ የብልሆች መንገድ ነው። በጣም ነፃነት በሚሰማሽ ሰው በኩል ስስ ነሽና አትራቆቺ።
ዋጋ የምትከፍዪላቸው ከጌታሽ መንገድ እንዳያስቱሽ አስተውዩ! የምወድሽዋ ልብሽን በቀደር አረጋጊ! የምወድህዋ እራስህ ካልወደቅክ አይጥሉህምና በጌታህ ታግዘህ ፅና። መንገዱ ምን እንዳለው አይታወቅምና ሰላም ለልባችሁ!
©
[አብዱልሀኪም ሰፋ]

❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️

ልባችን ሰላም የሚያገኝበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 0️⃣3️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
―አላህ…የሰዎችን ብሶት አዳማጭ፣ ችግራቸዉን ፈች፣ ለመከራቸው ደራሽ፣ ዕዳቸዉን ከፋይ፣ ጭንቀታቸዉን ተጋሪ፣ ህመማቸዉን ታማሚ፣ ሐዘናቸዉ ተካፋይ፣…ያደረገህ እንደሆን በርግጥም የወደደህ ስለመሆኑ ምልክት ነው። በዚህ ሁኔታህ ላይ የኖርክ እንደሆነ ከፍ እንዳልክ ትኖራለህ»
👤 ኢማም ኢብኑል ቀይም

AbuSufiyan
የፍትሕ ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያ- ግልፅ ለማድረግ !

   የህዝቡ ዝምታ ወይ ጥልቅ ከሆነ ቁጣ ወይ ደግሞ ጥልቅ ከሆነ የግንዛቤ እጥረት ሊሆን ይችላል:: ከቁጣ ከሆነ ይበል የሚያስብል ሆኖ ሲፈነዳ የሚታይ ይሆናል:: ከግንዛቤ እጥረት የመሆን እድሉ ሰፊ ነውና የረቂቅ መመሪያው አንደምታው ምንድን ነው የሚለውን እንደሚከተለው እንመልከት::

   አይበለውና ከፀደቀ በየትኛውም የትምህርት ተቋማት ኒቃብ ለብሶ መማር ይከለከላል:: ይህ ከሆነ ለአመታት ሲደረጉ የነበሩ ትግሎች አፈር ከመልበሳቸው ባሻገር የትምህርት ተቋሞቻችን ህጋዊ ስልጣን ኖሯቸው ኒቃቢስቶችን አንቀበልም የማለት ሙሉ ስልጣን ይኖራቸዋል:: "ለምን?" ሲባሉም መመሪያው ስለሚያዝ ነው የሚል ምላሽን ይሰጣሉ:: "ሕገ-መንግስቱስ?" ከተባሉም ውይይት ተደርጎበት ከሕገ-መንግስት ጋር ምንም አይነት መጣረስ እንደሌለበት ታምኖ የፀደቀ ነው የማለት መብቱ አላቸው:: በዚህ ውስጥ ወትሮውንም በትምህርት ስርዓቱ ያልታቀፈው ሙስሊም በዚህ ሳቢያ ይገፋል:: ትምህርትን እየጠላ ከማዕቀፉ በሲስተም ይወጣል::  በሁለተኛ ደረጃ በትምህርት ተቋማት ውስጥ ሶላት በጀመዓ መስገድ ይከለክላል:: ወንድምህ ወይም እህትሽ እየሰገዱ ሄዶ ተከትሎ መስገድ ሊያስቀጣ ማለት ነው:: በዚህም ሂደት ከሚቀጣው ተማሪ ባሻገር በሙስሊሙ ዘንድ የባለቤትነት ስሜት እየጠፋ የትምህርት ስርዓቱን በቋሚነት ችላ የሚልበት ስርዓት ይዘረጋል::

   በሌላ አውድ ገልብጠን ስንመለከተው ደግሞ ሰፊ የሆነ እድል እናገኛለን:: መመሪያው አሉታዊ ይዘት ባላቸው አንቀፆች እንደተሞላ የተገለፀ ቢሆንም በረቂቅ ደረጃ ያለ ስለሆነ ከላይ እስከ ታች ያለው የህብረተሰብ ክፍል ተፅዕኖ በመፍጠር ከሕገ-መንግስቱ በማይጣረስ መልኩ እንዲፀድቅ ማድረግ ይቻላል:: በዚያ ሂደት ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት መብታችንና ሴኩላሪዝም በአግባቡ እንዲከበሩ ማድረግ ከቻልን እስከ ዛሬ በተለያየ ምክንያት አንዴ ሒጃብ ለበሳችሁ ሌላ ጊዜ ሶላት ሰገዳችሁ እያሉ ሲበጠብጡ የነበሩ ሁሉ ተጠያቂ ይሆናሉ ማለት ነው::

   ስለሆነም ችላ ሊባል አይገባም:: የዚህ ትውልድ ትልቁ ሀላፊነት ይህንን ፈተና በድል መወጣት ነው:: ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ awareness ከመፍጠር ጀምሮ ባሉት እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ለዘመናት የጭቃ እሾህ ሆኖ ሲነዘንዘን የነበረውን እንቅፋት ማስወገድ ግድ ይለናል::

MohammadamminKassaw
ትኩረት ያልሰጠነው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ
===========================
(ይህ ጉዳይ ከጸደቀ በኋላ ሌላ ዙሩ በከረረ ትግል ውስጥ ሳንገባ በፊት ከወዲሁ እምነታችንን በማይነካ መልኩ መዘጋጀቱን ማረጋገጥ አለብን!)
||
ካስታወሳችሁ ከአንድ ወር በፊት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ከተለያዩ የኃይማኖት ተወካዮች ጋር በተናጠል ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በተለይ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ከኛ ከእስልምና ኃይማኖት መሪዎቻችን ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች መንግሥት በቅርቡ ኃይማኖትን የተመለከተ ሕግ እንደሚያወጣ መናገራቸው ይታወሳል። በተለይ ከመጅሊስ መሪዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት መስጂዶች የሚያደርጉት የአዛን ጥሪ፣ እንዲሁም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወኑ ቅዳሴና አስተምህሮዎች ሌላውን ሰው ማወክ ስለሌለባቸው አስቡበት በማለት ስለሚወጣው ሕግ ይዘት ፍንጭ ሰጥተው ነበር። 


መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ በፍትሕ ሚኒስተር በኩል ተዘጋጅቶ አሁን ላይ በሰላም ሚኒስተር አስተባባሪነት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት መደረግ ተጀምሯል።

ይህ አዲሱ አዋጅ በርካታ ክልከላዎችን የያዘ ሲሆን፤ የሙስሊሞችን በጀማዓህ ሶላት መስገድ፣ የእህቶችን ጂልባብና ኒቃብ መልበስ፣ ጀለቢያ፥ አማኢምና ኮፍያ መልበስና የመሳሰሉትን ለማገድ በር የሚከፍት ህግ ተካቶበታል።

የነርሱ እሳቤ የሌላውንም እምነት ተከታይ ኃይማኖታዊ አለባበሱንና በቡድን ማምለክን ስለምንከለክል፤ ሙስሊሞችንም «እናንተን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ነው የከለከልነው!» በሚል ሽፋን በመሞገት መከልከል አስበዋል።

እዚህ ላይ ያልገባቸው ነገር የእያንዳንዱ እምነት ዶክትሪን የተለያዬ መሆኑን አለማወቅ ነው። በተለይም የእስልምና እምነት ህግጋት በየትኛውም ታዕምር ቢሆን በሰው ሠራሽ ህግ የሚሻሩ አለመሆናቸውን መረዳት ተስኗቸዋል። እነርሱ ሲጀመር ከፊሎቹ ራቁታቸውን መሄድ ነው የቀራቸው። እንኳን ተከልክለው በፈቃደኝነትም እየተገበሩት አይደለም። ታዲያ እነርሱ ከተዘናጉ እኛም አብረን መታፈን አለብን? በጭራሽ!

አይደለም ኢትዮጵያ አዲስ የምታዘጋጀው ህግ፤ የዓለም መንግስታት ተባብረው አዋጅ ቢያወጡ፤ እስልምናችንን ከተቃረነ ማንም አይሰማቸውም። የራሳቸውን እንደፈለጉ ያድርጉ። የኛን ግን እንዳያስቡት።

በተጨማሪም 24 ሰዓት በካሴት ሳይቀር ተከፍቶ የሚለቀቅን የቤተ ክርስቲያን ቅዳሴና መዝሙር በቀን 5 ጊዜ 5 ደቂቃ ለማትሞላ አጋጣሚ የሚደረግን የአዛን ጥሪ አወዳድሮ አብሮ ጨፍልቆ ለመከልከል መጋጋጥ በየትም ተሰምቶ አይታወቅም።

መንግስት አዛን ከከለከለን በተለይም በዐረቡና በሙስሊሙ ዓለም በኩል ያለውን ግንኙነት እንደሚያበላሽ ጠንቅቆ ይወቀው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነ መከራ እንዲለብስ ነው የሚሆነው።

ቀድሞ ከሙስሊሙ ተወካዮችና ምሁራን በኩል የተሰጣቸውን ሃሳብ ወደ ጎን በተመው፤ ይህን ረቂቅ የሚያዘጋጁ አካላት።ሙስሊሙን የሚጨፈልቅ ህግ ማውጣታቸው አላማቸው ምን እንደሆነ ግራ ያጋባል። ባለማወቅ ነው እንዳይባል ቀድሞ መረጃ ተሰጥቷቸዋል፤ ግን ወደ ጎን ብለውት በራሳቸው አካሄድ መሄድን መርጠዋል። በርግጥ ፍትሕ ሚኒስተር ውስጥ እነማን እንደሆኑ እናውቃለን። ከአሁን በፊትም ኡማውን ከወያኔ ጀምሮ ሲጨቁኑ የነበሩ አካላት አሉበት።

በአጭሩ እየመጣ ያለው ረቂቅ አዋጅ የእምነት ነፃነትን የሚጋፋና ኃይማኖቶች ከእምነታቸው አስተምህሮ ይልቅ በሃገሪቱ መንግስት ቁጥጥር እንዲዳኙ የሚያደርግ አደገኛ አዝማሚያ ያለው ነውና ከወዲሁ እንዲስተካከል ማድረግ አለብን።

እኛ በደፈናው ባልተጻፈ ህግ ሲጨቁኑን የነበረውን ጉዳይ ጽፈው በግልፅ አስተካክለው ይመጣሉ ስንል፤ ጭራሽ በግልፅ ከልክለውና ሌላም ዱብእዳ አክለው መጡ።

ማንም አይሰማቸውም!

ህዝብ መረጃ ይኑረው። በደንብ መረጃዎችን አንሸራሽሩ። ረቂቅ አዋጁ ነገ ከኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሏል። እዛም ላይ የኛ ተወካዮች በደንብ ጉዳዩን ያንሱት። አላህ የደነገገው ሸሪዓህ በተራ ሰዎች ህግ በፍፁም አይሻርም፤ አይሻሻልም።
ሸሪዓን የሚቃረን ህግ ካለ ራሱ ይቀየር እንጂ ሸሪዓህ አይቀየርም። እኛ ሸሪዓን አልደነገግነውም፤ የደነገገው አላህ ነው። ያልደነገግነውን አናሻሽልም። እነርሱ ግን ረቂቁን ያወጡት ራሳቸው ስለሆኑ ራሳቸው አሻሽለው ይምጡ።
Period


||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse
fb.com/MuradTadesseOfficial