ASD AJ LAH
754 subscribers
1.79K photos
197 videos
3 files
511 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ረመዷን - 13
***

እጅግ ከሚገርሙኝ አባባል መካከል " መከተል የፈለገ እነኚህን የሞቱትን ይከተል። በሕይወት ያለ ሰው ፈተናው አይታመንም ።" የሚለው ይገኝበታል ።

አባባሉ ትልቅ አስተዉሎትን ይፈልጋል። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ናቸው ይህን ያሉት ተብሏል።
"የሞቱት" የተባሉት ደጋጎቹ የአላህ ባሮች ሶሐቦች ናቸው። እነርሱ ደግ ሥራ ሠርተው ለሌሎችም ምሳሌ ሆነው አልፈዋል ። እስከመጨረሻ ድረስ በዲን ፀንተው ለአምላካቸው አላህ ሱ.ወ. ታምነው ኖረው መቃብር ወርደዋል። ስለዚህ መከተል እነርሱን ነው። ቢከተሏቸው ያዋጣሉ ። አብነት ቢያረጓቸው ወደ መልካም መጨረሻ ያደርሳሉ ።
በሕይወት ያለ ግን ምኑ ይታመናል ወዳጆቼ። እስካልሞተ ድረስ የሰው ፍፃሜው አይታወቅም። እየኖረ እያለ ነገ ድንገት አቋሙን ሊቀይር ይችላል ። ስንቱን አየን እኮ!። ትናንት ብርቱ የነበረ ኡስታዝ በዱንያ አልያም በሌላ ምክንያት ዛሬ ሲደክም። ጠንካራ አቋም የነበረው ሲሸረሸር። የተውሒድ ሰው የነበረ ሲያደገድግ። የሱና ሰው የነበረ በቢድዓ ሲዞር። ኅጢአት ይሸሽ የነበረ ምን ችግር አለው ብሎ ሲዳፈር።

ወዳጆቼ!
ሰዉን ዐይናችን እያየ ዱንያ፣ ሥልጣን፣ ጥቅም፣ ዝና ... አቋሙን ሊያስለዉጠው ይችላል። ስለሆነም በሕይወት ያለ አይታመንም ። ሰው በያዘው መልካም አቋም ላይ የሚታመነው ሞቶ መቃብር ሲወርድ ብቻ ነው። ያኔ የሚለውጠው አቋም አይኖረዉም።
ስለዚህ ኡስታዝ በሉት ሸይኽ፣ እኔም ሆንኩ ሌላ ማንም ይሁን ማን .. ሰዉን ፍፁም በሆነ መልኩ አመኑ፣ ከትከተሉ ። ራሣችሁንም በርሱ ላይ አትጣሉ። አድናቆታችሁን ቀንሱ። ነገ ቢሰንፍ፣ ቢደክም፣ አቋሙን ቢለዉጥ ... እንዳትደነግጡ ያግዛችኋል።

አንድ ነገር ልምከራችሁ
ስትቀመጡ፣ ስትነሱ፣ ስትገቡ፣ ስትወጡ ...

ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ ..ን አንጎራጉሩ።
የጠፉት እንዴት እንደጠፉ ሳይሆን ነጃ የወጡት እንዴት እንደወጡ መርምሩ።

©Abx
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣3️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ለሶላት የውጭ ድምፅ ማጉያ መጠቀም
~
ሶላት ዒባዳ ነው። ዒባዳችን ከእልህና መሰል አጉል ስሜቶች ፀድቶ በኢኽላስና በንፁህ መንፈስ ሊፈፀም ይገባል። ድምፅን በሶላት ከፍ ማድረግ በቦታው ሲሆን የተወደደ ነው። አልፎ በእንቅልፍ ሰዓት ሰዎችን እስከሚረብሽ ሊደርስ አይገባም። አንዳንድ አካባቢ ከሶላትም አልፎ መዝሙር ከፍተው እንደሚያውኩ ሰዎች መንዙማ ለቀው የሚያውኩ አሉ። ኢስላም ይህንን አይፈቅድም። "እነሱስ እንዲህ እያደረጉ አይደል?" የሚል ማመሀኛ እልህ እንጂ ማስረጃ አይደለም። ደግሞም እነሱ አይደሉም ምሳሌዎቻችን። በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ሌሊት ለተሀጁድ የሚነሱ ወገኖች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን ሲጠቀሙ ሰፈሩን እንዳለ ነው የሚያውኩት። ጉዳዩ አላህን በመፍራት ሰከን ብሎ ማጤን ይሻል። ሰፈር ጎረቤት ቢታወክም እንጮሃለን እያስባለን ያለውን ምክንያት ረጋ ብለን እናዳምጠው። ምናልባት አንዳንዶች ጋር "በዚያ ሰዓት እተኛለሁ የሚል ይረበሽ። ሙሉ የሰፈሩ ህዝብ ተነስቶ ይስገድ" የሚል ስሜት ወለድ ሙግት ካለ ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ ከማለት ውጭ ይሄ ምላሽም የሚግገባው አይደለም። ብቻ ደጋግሜ የምለው አላህን እንፍራ። የታመመ ይተኛ። መተኛት የፈለገም ይረፍ። አሁን ያለው ግን ሌላው ቀርቶ መስጂዶች በሚቀራረቡባቸው አካባቢዎች ባጎራባች ያሉ ሰጋጆች ሶላታቸው እስከሚረበሽ እየደረሰ ነው።
ከዚህ በፊት አንዳንዶች "ቁርኣን እንዴት ይረብሻል?" የሚል የህፃን ክርክር ሲያስነሱ ነበር። የሚረብሸው ለከት ያለፈው ድምፅ ነው። መስገዳችንን አገር እንዲያውቅልን ማወጅ የለብንም። ለኢኽላስ የቀረበው በልክ የሆነው ስራ ነው።

እንዲያውም በተሀጁድ ብቻ ሳይሆን #በሌሎችም ሶላቶች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም ክልክል ነው ይላሉ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ። ይሄውና:

ጥያቄ:- “ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የመስጂድ ኢማሞች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም አብዝተዋል። ድምፅ ማጉያዎቹ በአብዛኛው ሚናራ ላይ የሚሆኑ ሲሆን በጣም ከፍ ያለ ድምፅ ይጠቀማሉ። በዚህ ድርጊት የተነሳ ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ ከፊል መስጂዶች በቁርኣን ንባብ ጊዜ ድምፅ ማጉያዎችን ስለሚጠቀሙ ሌሎቹን ይወሰውሳሉ። እና ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ የድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም ብይኑ ምንድነው?

የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር:-

ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ ድምፅ ማጉያዎችን ከሚናራ ላይ መጠቀም ክልክል ነው። ምክንያቱም በአቅራቢያ ባሉ ነዋሪዎች እና መስጂዶች ላይ መረበሽ አለበትና። ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ በዘርቃኒይ ሸርሕ ላይ እንደሚገኘው ሙወጦእ (178) ላይ በ (باب العمل في القراءة) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየሰገዱ ከነበሩ ሰዎች ዘንድ ወጡ። በቁርኣን ድምፃቸው ከፍ ብሏል። በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:-
"إن المصلي يناجي ربه فلينظر بما يناجيه به ولا يجهر بعضكم على بعض بالقرآن"
“ሰጋጅ ከጌታው ጋር ነው የሚንሾካሾከው። ስለዚህ የሚንሾካሾክበትን ይመልከት። አንዳችሁ በሌላው ላይ በሶላት አይጩህ። አቡ ዳውድ (1332) (رفع الصوت بالقراءة في صلاة الليل ) በሚል ርእስ ስር ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ በዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ﷺ በመስጂዳቸው ኢዕቲካፍ አድርገው ነበር። በቁርኣን ሲጮሁ በሰሟቸው ጊዜ መጋረጃውን ገልጠው እንዲህ አሉ:-
"ألا إن كلكم مناج ربه فلا يؤذين بعضكم بعضاً، ولا يرفع بعضكم على بعض في القراءة ، أو قال في الصلاة"
“ንቁ! እያንዳንዳችሁ ከጌታው ጋር ነው እየተንሾካሾከ ያለው። ስለሆነም አንዳችሁ ሌላችሁን አያስቸግር። በቁርኣን ንባብ / በሶላት አንዳችሁ ሌላችሁ ላይ አይጩህ።” [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን: 13/74-96]

በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል:-

“ሶላቶችን ከሚናራዎች ላይ በድምፅ ማጉያዎች ማስተላለፍ ጠያቂው እንዳለው በየቤታቸው ያሉ ሰዎችን መወስወስ ነው። የግል ዚክሮቻቸውንና ተስቢሖቻቸውን ማናጋት ነው። ምናልባትም ከዚህ ጊዜ ውጭ ማረፊያ ያጡ የተኙ ሰዎችንና ህመምተኞችን መረበሽ ሊኖርበትም ይችላል።
በተጨማሪም ከዚህ ድምፅ ባጎራባች ላሉ መስጂዶች መረበሽና መወስወስ አለበት።” [ኑሩን ዐለ ደርብ:176]

የሁለቱንም ፈትዋዎች ይዘት ሙሉውን ስላላቀረብኩ የፈለገ ምንጩን ተከትሎ ያንብብ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዳን 19/1442፤ ሚያዚያ 23/2013)
ረመዷን - 14
***

አዎ አሁንም ቢሆን ዝም አትበሉ፣ አትዘናጉ፡፡ ረመዷንን እንደ ትልቅ ዕድል ተጠቀሙበት፡፡ ያሳሰባችሁን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ለፈጠራችሁ አምላክ ለአላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ንገሩት፡፡ እሱ ጉዳያችሁን ይፈታል፣ አይቻልም ተብሎ የሚታሰበዉን ሁሉ ያገራል፡፡

አንዳንድ ዱዓ እኮ ምላሽ ለማግኘት ረመዷንን ይጠብቂል። አንዳንዱ የናንተን እጅ ማንሳት ብቻ እየጠበቀ ይሆናል፡፡
እጃችሁን ወደ አላህ አንሱ አትፍሩ፣ አትፈሩ፣ አታመንቱ፣ አትቅጠሩ፣ አመቺ ጊዜ አትጠብቁ፡፡

አንድ ሰው ብዙ እንዲሳኩለት የሚፈልጋቸው ሓጃዎች እያሉት እንዴት ይሰንፋል! እንዴት እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል!!፡፡

ብቸኝነት ያደከማችሁና መልካም ትዳር የምትናፍቁ፣ ጉዳያችሁ ከዓመት ዓመት መልስ ሳያገኝ የተንከባለለ አሁንም ወደ ተጠጉ፣ ከአላህ ጋር አውሩ፡፡
ሪዝቅ የጠበባችሁ፣ ድህነት ያዋረዳችሁ አላህ ሆይ ሪዝቄን አስፋ በሉት፡፡ ያሳሰባችሁን ማንኛዉንም ነገር ሳትፈሩ ሳታፍሩ ለምኑት፣ ጠይቁት፣ ተማፀኑት፡፡ ረመዷን አላህ በብዛት ባሮቹን የሚቀበልበት ወር ነው፡፡ ከተቀበላቸው ትሆኑ ዘንድ በርቱ ተስፋ አትቁረጡ።

©Abx
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1️⃣4️⃣  #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
በዙሪያህ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመረዳት አትሞክር። አንዳንድ ጉዳዮችን አለመረዳት ነው የሚሻለው። አንዳንዴ ነገሩን በመረዳትህ የሚመጣብህ የልቦና ቀውስና አንደበትህ ላይ የሰዎች ስም መመላለስ ብቻ ነው። …  በቃ ምናገባኝ ማለት አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ!

©fuad
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1️⃣5️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
    ጀመዓ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪ !

  ሳይኮሎጂስቶች እንደሚያስቀምጡት አራት አይነት የintelligence መለኪያ ምድቦች አሉ :: እነሱም Intelligence Quotient (IQ) : Emotional Quotient (EQ) : Adversery Quotient (AQ) እና Social Quotient ናቸው :: IQ አንድ ሰው አንድን ነገር ምን ያክል ሊረዳ ይችላል የሚለውን ይለካል :: በዚህ ውስጥ የሰውዬውን የማስታወስ ችሎታ : ሒሳብ የመስራት አቅምና መሰል ትምህርታዊ ነገሮችን መገምገም እንችላለን :: በአጠቃላይ በኬጂ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የምንመዘንበት ልኬታ ማለት ነው ::
  
    EQ የምንለው ደግሞ አንድ ሰው ስሜቱን ምን ያክል ይቆጣጠራል በሌሎች ሰዎች ስሜት ላይስ ምን ያክል ተፅዕኖ ይኖረዋል የሚለው የሚለካበት ነው :: በዚህ ውስጥ የሰውዬው ሀላፊነትን የመውሰድ ችሎታ : የሰዎችን ድንበር የማወቅና የማክበር ልኬታ እንዲሁም ታማኝነትን ጨምሮ መሰል ባህሪዎች ይለኩበታል :: AQ ደግሞ አንድ ሰው በህይዎቱ ውስጥ አስቸጋሪ የሚባሉ ጊዜያቶችን አዕምሮውን ሳያጣ በሰላም ማለፍ ይችላል ወይ የሚለውን ጥያቄ ይመዝናል :: በዚህ ውስጥ "ማነው ተስፋ የሚቆርጠው? ወደሗላስ የሚለው?" ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን :: በአራተኛ ላይ የተቀመጠው SQ ደግሞ አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ጓደኝነት ፈጥሮ እስከዬት ሊቆይ ይችላል የሚለውን የሚለካልን ነው ::

   በአጠቃላይ አንድ ሰው ከፍተኛ IQ ኖሮት በሌሎቹ ምድቦች ዝቅተኛ ከሚኖረው IQዉ ዝቅተኛ ሆኖ ሌሎቹ ከፍተኛ ቢሆኑለት ይሻለዋል :: ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የIQ ክፍል በዘመናዊ ትምህርት ውስጥ እንዲበለፅግ ሲደረግ ሌሎቹ ደግሞ ይበለፅጉ ዘንድ ጤናማ የሆኑ ስብስቦች ውስጥ ገብቶ ራስን መፈተሽ : ማለማመድና ማሰልጠን ያስፈልጋል :: ከእነዚህ ስብስቦች ውስጥ ደግሞ የዩኒቨርሰቲ ጀመዓዎች ሲሆኑ ሁሉንም በአንድ ላይ ያቀርባሉ :: አንድ ሰው የጀመዓ አባል ሲሆን በተለይም ወደ አመራርነት ቦታ ሲመጣ በሁሉም የመለኪያ ሚዛኖች ይፈተናል :: በዙሪያው ካሉ ሰዎች ጋር ጤናማና ዘላቂ የሆነ ጓደኝነት መፍጠር ግዴታው ነው (SQ) :: የራሱን ፍላጎት ዋጥ አድርጎ የጀመዓውን ጥቅም ማስቀደም ግዴታው ነው (EQ) :: ተስፋ የሚያስቆርጡ ችግሮች ሲመጡ በራሱ ላይ ተስፋን በመዝራት ወደፊት መጓዝን ማስለመድ ግዴታው ነው (AQ) ::

   ስለዚህ ጀመዓ ራሳችንን ለመገንባትና ለመስራት ትልቅ የልሕቀት ማዕከል ነው :: ገብቶ መስራት ብሎም መመረቅ ትልቅ መታደል ነው ::

©MohammadamminKassaw
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 1️⃣6️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
Forwarded from ABX (Muhammed Seid)
ረመዷን - 16
***

ትናንት የተቀበልነው ወር (አዎ ትናንት) አንድ ቀን የፆምን ሳይመስለን ይኸው ሮጦ አጋማሹን አለፈ፡፡
እነዚያን ያለፉትን አሥራ አምስት ቀናት በምን አሳለፍን?፡፡ አተረፍን ወይስ ከሰርን?፡፡ አገኘን ወይስ አጣን?፡፡ ዛሬ 16ኛው ላይ ቆመን ራሣችንን እንገምግም እስቲ፡፡
ፆማችን እንዴት ነበር?፡፡ ከፆም፣ ቁርአን፣ ከተራዊሕ፣ ከግዴታና ሱና ሶላቶች፣ ከዚክር፣ ከሶደቃ ጋር የነበረን ግንኙነት እንዴት ነበር?፡፡

በርግጥ ያለፉት ቀናት በምንም ይሁን በምን ይለፉ ላይመለሱ አለፉ፡፡ የቱን ያህል ብንሮጥ ካሁን በኋላ አንደርስባቸዉም፡፡ ብንፀፀት መልሰን አናመጣቸዉም፡፡ ቢቆጨን ዳግም አናገኛቸዉም፡፡ በቀናቱ ዉስጥ ብዙ አጉድለን ይሆናል፡፡ ቢሆንም መልሰን ልንሞላቸው አይቻለንም፤ ያጠፋነዉን ለማስተካለከል ዕድሉ የለንም፡፡ እያንዳንዱ ቀን የተሠራበት ሥራ ተመዝግቦ ፋይሉ ተዘግቷልና፡፡ ግና የተቀሩት ቀናት እንደ ዕድል ተሠጥተዉናል፣ ያጎደልነዉን እንሙላ፣ በደከምንባቸው ጉዳዮች እንበርታ፡፡

ያ ረብ በረሕመትህ አለን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx
ጫት ዘምኗል !

    ትላንት ነው :: እግር ጥሎኝ አዲሳባ ውስጥ ሙስሊም ይበዛበታል ወደሚባለው አለምባንክ ተጓዝኩ :: ከቀጠሮዬ ቀድሜ ስለደረስኩ ሰዓቱ እስኪደርስ "ሰፈሩ ይወቀኝ እኔም ልወቀው" በማለት ዞር ዞር ማለት ጀመርኩ :: ብዙውን ካዬሁ ቡሃላ አንድ ቦታ "ሀዊ የጥንት የጠዋቱ ምርጥ በለጬ!" ከሚል ፅሁፍ ጋር የጫት ምስል ተያይዞ በማስታወቂያ መልክ አዬሁ :: ስሙን ቅመው ነው ወይስ ሳይቅሙ ያወጡለት የሚል መጠይቅ በአዕምሮዬ እየተመላለሰ "ጫት ጥንትም ነበር ወይ?" የሚል መጠይቅ ለራሴ መጣ :: ከዚያ በመቀጠል ያሉት ጫት ቤቶችን ስመለከት ተያይዘው ያሉት ማስታዎቂያዎች የሀዊን ጥንታዊ ጫት ቤት በዘመናዊነት የሚገዳደሩ ይመስላል :: አንድኛው "ኪሎ ከማሳ እስፔሻል በለጬ" ብሎ እንግሊዝ አፍ ከማስታወቂያ ሲጨምር ሌላኛው ደግሞ "አብዲ ኦርጋኒክ በለጬ መሸጫ!" የሚልን ስም አስቀምጦ የሀዊን ኢንኦርጋኒክ ነው የሚል ያስመስላል :: ሌላኛው ደግሞ ሁላቸውንም ለማጣጣል በሚመስል መልኩ ከጥንቱም ከዘመናዊነቱም ፉክክር ወጥቶ "ኸይሩ ትክክለኛ በለጬ!" በሚል ስም የሌሎቹን የውሸት ነው ለማለት ይዳዳዋል :: በስተመጨረሻም ኤሊያስ በለጬ የሚል ጫት ቤት የሙስሊሞችን ስስ ጎን ለመንካት በሚመስል "ዱዓ ዞን!" የሚልን አባሪ ማስታዎቂያ ከስሙ ጎን በአንድ ታፔላ ላይ አስፍሯል ::

   ለአንድ አደንዛዥና ደም መጣጭ : ኪስ አጣቢና አቅል ሰላቢ ቅጠል የወጣለት የቅምጥል ስም እየገረመኝ ነጋዴውና ሸማቹ የእኔው ሙስሊም ወንድም አባቶች መሆናቸው ደግሞ አሳዘነኝ :: በዘመቻ መልክ ችግሩን መቅረፍ ካልተቻለ በትውልዱ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እልፍ መሆኑ እየታወቀ አንቂው ክፍል ሳይቅም መርቅኖ ይህንን ጉዳይ መዘንጋቱ ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል ::

   የሱስ አደጋው ይታወቃል :: ሱስ አንድ ጊዜ ወደ ህይዎት ከገባ መላቀቁ ይከብዳል :: እንደ ጎርፍ እያሳሳቀ ወደ ገደል ይከታል :: የጫት ሱስም ተመሳሳይ ነው :: ማህበረሰባችንን በከባድ ኢካኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ይከተዋል :: ስለዚህ "ሳይቃጠል በቅጠል" እንዲሉ ትውልዱ መክኖ ሳያልቅ ይደረስለት ::

©MohammadamminKassaw
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣7️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ወርቃማ እድል - በእጃችሁ ላይ
      ~~~~
ASD AJ LAH
Photo
ወርቃማ እድል - በእጃችሁ ላይ
      ~~~~
የቴሌግራም ፈጠራዎች፣ እቅዶች፣ ተግባራት ሁሉም ያስደንቁኛል። በነገራችን ቴሌግራም ማህበራዊ ሚዲያ ብቻ የሚመስላቸው በርካታ ሰዎች ርቀታቸውን እንደጠበቁ እስከዛሬም አሉ።

ነገር ግን ቴሌግራም ኢንዱስትሪም ነው፤ ኢንቨስትመንት ነው። መገናኛ ብዙሃን ነው። ዓለም አቀፍ የገቢ ምንጭ ነው። በኪስ እንዳለገንዘብ ነው። የባንክ አካውንት ነው። የገንዘብ ግዢና ሽያጭ የሚካሄድበት ደህንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፍ ገበያ ነው። ጨዋታዎች ነው፤ . . . በአጠቃላይ ቴሌግራም ራሱን የቻለ የሰለጠነ ዓለም ነው።
        ~
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቴሌግራም ላይ አንድ ጨዋታ ተጀምሯል። ጨዋታው እጅግ አስደናቂ ፈጠራ የታከለበት ነው። ቴሌግራም የመጪው ዘመን የጨዋታ ኢንዱስትሪ ማዕከል እንደሚሆንም ያረጋገጠበት ነው። የዲጂታል ገንዘብ ተንታኞች በበኩላቸው ጨዋታው #የክሪፕቶከረንሲ ወርቃማ ዘመን ማብሰሪያ አድርገው እየገለጹት ነው። የዓለም ሀብት ፍትሃዊ ስርጭት መገለጫ አድርገው የሚተነትኑም አሉ።
           ~~~
#Notcoin
ጨዋታው #Notcoin ይባላል።  ቴሌግራም ላይ የምትጫወቱት ነው:: ሲጀምር Nothing የሚል ጽሁፍ ይመጣል:: እናም ብዙዎች ትኩረት አልሰጡትም:: ቴሌግራምም በገደምዳሜ ካልሆነ በስተቀር እስከ አሁን በቀጣይ ወደ ገንዘብ ይቀየር አይቀየር በግልጽ ያለው የለም:: ያም ሆኖ ግን በአንድ ወር ውስጥ የጨዋታው ማህበረሰብ ቴሌግራም ቻናል በአንድ ወር ውስጥ ከ3.4 ሚሊየን በላይ ሰዎች በመቀላቀል ሪከርድ ሰብረዋል:: ሪከርዱ በየትኝውም ማህበራዊ ሚዲያ ታሪክ ያልታየ ነው:: ጨዋታውን በአንድ ወር ውስጥ ከ26.5 ሚሊየን በላይ ሰዎች እየተጫወቱት ይገኛሉ:: እጅግ በጣም አስደንቂ ክስተት ነው:: ቴሌግራም ከጀመርነው የፈረንጆች ወር በኋል ጨዋታውን እንደሚያቆመው መግለጹ ደግሞ በየቀኑ ብርካቶች በጥድፊያ እየተቀላቀሉና Notcoin እየሰበሰቡ ነው።
      ~~~~
ከዚህ በመነሳት የቴሌግራም ቻናሌ ተከታዮች #Toncoinኑ ገንዘብ ሆነም አልሆነም በተለይም የእረፍት ጊዜ ሲኖራችሁ በጨዋታው በርካታ Notcoin እንድትሰበስቡ መጋበዝ አስፈላጊ መስሎ ተሰምቶኛል። ስለሆነም ጨዋታውን በአጭሩ አስተዋውቃችኋለሁ።

ይሄን ሊንክ 👉 https://t.me/notcoin_bot?start=r_578988_30030824 #click ስታደርጉት ወደጨዋታው ይወስዳችኋል። በዚህ ሊንክ ስትጀምሩ 100,000 Notcoin ስጦታ ይበረከትላችኋል። ማስጀመሪያ 2,500 ታገኛላችሁ። (ሊንኩን ስትከፍቱት የምታገኙት ገጽ ከላይ በስክሪንሾት 2 የተመለከተውን ይመስላል።)

     ~~~
መሃሉን (በትልቁ የተከበበውን) ስትነኩት Coinናችሁ እየጨመረ ይሄዳል:: በስተቀኝ ከስር የተሰመረባቸው ደግሞ ከጨዋታው ግር የተያያዙ ክፍሎች ናቸው::

ኖትኮይን ለመረዳት እና ለመጫወት ቀጥተኛ ነው፣ በ cryptocurrencies ወይም blockchain ቴክኖሎጂ ምንም ልምድ ለሌላቸው ተጠቃሚዎች እንኳን።  የእሱ መካኒኮች ማብራሪያ ይኸውና፡-

mining/ማዕድን ማውጫ ይብላል:: በተደጋጋሚ በመጠቅጠቅ (click በማድረግ) ሳንቲም ትሰበስባላችሁ:

Energy and boosters /ጉልበት እና ማበረታቻዎች - ጨዋታው ሲጀምር 1000 Coin ብቻ ነው በፍጥነት መሰብሰብ የሚቻለው:: ነገር ግን ካላችሁ ሳንቲም ላይ በመክፈል ብዛቱም ሆነ ፍጥነቱን መጨመር ትችላላችሁ:: በተጨማሪም በየ24 ሰዓቱ ሦስት ጊዜ ቡስት ማድረጊያ ሳንቲም መሙያ እድሎችን ይሰጣቸዋል:: ስትጫወቱ በራሪ ነገር ትመጣለች:: Click ስታደርጓት ለሰከንዶች በፍጥነት ብዙ ሳንቲሞች የምትሰበስቡበት ተጨማሪ ማበረታቻ ይሰጣችኋል::

Bonuses and squads/ጉርሻዎች እና ቡድኖች ጨዋታው ጓደኞችን በመጋበዝ ወይም “ቡድኖች”ን በመቀላቀል ተጨማሪ የNotcoin ጉርሻዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ናቸው። በዚህም በትዊተር፣ በቴሌግራም፣ በድረገጽና በሌሎችም አማራጮች #Follow በማድረግ ከ100ሺህ እስከ 500ሺህ notncoin ጉርሻ ያስሸልማል:: ፓስፖርት ያላችሁ ጨዋታው ላይ ያለውን ሊንክ ተከትሎ የባይናንስ አካውንት መክፈት ደግሞ 3 ሚሊየን Notcoin ያስሸልምል:: Squads በጨዋታ ለመሪነት የሚወዳደሩ የጋራ የቴሌግራም ቡድኖች ወይም ቻናሎች ናቸው። 

🤗 ተጨማሪ መረጃዎችን ከታች ካሉት ማስፈንጠሪዎች አንብቡ 👇👇

https://decrypt.co/212154/trillions-notcoin-farmed-telegram-meme-coin-game-but-theres-catch

https://decrypt.co/212154/trillions-notcoin-farmed-telegram-meme-coin-game-but-theres-catch


https://decrypt.co/218610/telegram-game-notcoin-25-million-players-token

በፍጹም እንዳያመልጣችሁ:: በዚህ ወር እስኪጠናቀቅ ድረስ እያንዳንዳችሁ ቢያንስ 10 ሚሊዮን Notcoin መሰብሰብ ይጠበቅባችኋል::

ሀናን ፌደራሊስት ከፃፈችው ፅሁፍ ላይ የኔን መጫወቻ ሊንክ ብቻ ቀይሬበታለሁኝ
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣8️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا
ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
ሱረቱ ሸርህ 6

ችግር ድንገት ካጋጠመህ ድሎትም በድንገት ሊመጣ እንደሚችል አስብ :: ሀዘን በድንገት ከመጣ ደስታም በድንገት ሊያጋጥምህ እንደሚችል አስብ :: በአላህ ላይ ተስፋ ይኑርህ ::
©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
የጎዳና ኢፍጣር ላይ የተረፈውን ያልተነካካ ለስላሳ ካነሱ በኋላ…
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1️⃣9️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
1000ብር አውጥተህ የገዛሀውን ፓወር ባንክ ስልክህ ቻርጅ ሲያደርገው ያለው ስሜት🙆🏽🤦🏽‍♂