ASD AJ LAH
760 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
አንዳንድ ነገሮች አይቀየሩም!

አምና ተራዊህ እያሰገዱ ድመቷ ላያቸው ላይ ወጥታ ሳይደናገጡ እንደውም በእክብካቤና በእዝነት ያስተናገዱትን ሸይኽ ወሊድ አስታወሳችሁ?

ዛሬ ደሞ በ2023 ከኋላቸው ተከትለው ይሰግዱ የነበሩት አባትና ልጅ በ2024ም በተመሳሳይ ቦታ ቆመው ኢማሙን ሸይኽ ዋሊድን ተከትለው ሲስግዱ መታየታቸው በማህበራዊ ትስስር ገፆች መነጋገሪያ ሆኗል። ዐጂብ ነው መቼም! አንዳንድ ነገሮች አይቀየሩም! እንደ አደራ እቃ ባስቀመጡት ቦታ ይገኛሉ።
እኛስ? ስንቶቻችን ነን የከርሞን ኢማን ያስቀጠልን፤ በብርታታችን የፀናን?
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 0️⃣7️⃣  #ረመዳን 1⃣4⃣4⃣5⃣
ረመዷን - 7
****

ረመዷን የዓመት ዕድል ነው። ይህ ዕድል በሚቀጥለው ዓመት ተመልሶ ይምጣ አይምጣ የምናውቀው ነገር የለም።

ዘንድሮ አላህ ያደረሰን ግን ዕድሉን ለመጠቀም የቻልነዉን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል ።

ይህንኑ ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም ከሥራ ዕረፍት የሚወስዱ አሉ። ከሶሻል ሚዲያ የሚርቁ አሉ። ወሩን ሙሉ መስጂድ የሚገቡ አሉ። በተቀደሰው ምድር መካና መዲና የሚያሳልፉ አሉ።

አንተም ከዚህ ዕድል በተሻለ መልኩ ለመጠቀም የቻልከዉን ሁሉ አድርግ። የረመዷን አጅርህ እንዳይሸራረፍና ወደ ኪሳራ እንዳይወርድ ጥንቃቄ አብዛ። ዉሎህ ከደጋጎች እና ደግ ቦታዎች ይሁን። ለፆምህ ተጠንቀቅለት። ወሬ አታብዛ። ከመልካሞች ካልሆነ ከሰዎች ብዙ አትቀላቀል። ከቤት ብዙ ባትወጣ መልካም ነው። ከሥራ ዕረፍት መውሰድ ካለብህ በረመዷን ዉሰድ። ራሳችንን እንርዳ።

©Abx
ተራዊህ ላይ የመጀመርያው ረከዐ ሁለተኛው ሱጁድ በኋላ ኢማሙ ለሁለተኛ ረከዐ ሲነሳ እኛ መእሙሞቹ ለእረፍት የምንቀመጣት አስር ሰከንድ ግን ትለያለች
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 0️⃣8️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ረመዷን -8
***

ዉስን ቀናት እኮ ናቸው፡፡ 29 ወይም ሰላሳ፡፡ እነርሱም በፍጥነት እየሄዱ ነው፡፡ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት … እያልን ስምንተኛ ቀን ላይ ደረስን፡፡  ረመዷን … ፡፡ ቀናት ሁሉ እንደ ረመዷን ቢፈጥኑ ይሄኔ ባረጀን እላለሁ፡፡

አሁንም በርቱ፡፡ ወላጆቻችሁን፣ ዘመዶቻችሁን፣ ጎረቤቶቻችሁን፣ ልጆቻችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁን አስታውሱ፡፡
  ቁርኣናችሁን ቅሩ፣ ሶደቃችሁን ስጡ፣ ዚክራችሁን አብዙ፣ ግዴታና ሱናችሁን ተወጡ፣ ዒባዳችሁን አሳምሩ፣ በዱዓችሁ በርቱ፡፡ አምላካችን ቸር ነው፤ ለጋስ ነው፤ መሀሪ ነው፤ አዛኝ ነው፡፡

Abx
ረመዷን _9


በሚያፈጥሩበትም ሆነ ፆም በሚይዙበት ጊዜ ዱዓ ይወደዳል። ረመዷን ዉስጥ ከልቡ የለመነ ሸዋል ላይ፣ ከሸዋልም በፊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በርግጠኝነት ዉጤቱን ያያል። በረመዷን በቀንም ይሁን በማታ፣ በአፍጥር ይሁን በሱሑር በማንኛዉም ሰዓት ከዱዓ አትዘናጉ። የፆመ አንጀት ቢማፀን ምላሽ አይነፈገዉም። የረመዷንን ዱዓ ችላ ያለ በርግጥ በራሱ ላይ ሰሰተ። ነፍሱ የምትመኘዉን ነፈገ።
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ0️⃣9️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ረመዷን - 10

እንደው እንደዋዛ ሮጠን 10ኛው ቀን ላይ ደረስን ቢባል ማን ያምናል ወዳጆቼ? ዐጃኢብ ነው ብቻ….
ቀናት እንግዶች ናቸው፤ ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ ይዘይሩናል ያልፋሉ፡፡ የመጡት ለዘላለም ከኛ ጋር አይቆዩም ፡፡
በኢስላም እንግዳ ክቡር ነው፤  በየዓመቱ በዓመት ለአንድ ወር ያህል የሚዘይሩን የረመዷን ቀናት ደግሞ የበለጠ የተከበሩ ናቸው፡፡ እንዴት እያስተናገድናቸው ይሆን?
የረመዷንን ቀናት አከበርን የሚባለው አላህ በሚወደውና በሚፈቅደው መልኩ ስናስተናግዳቸው ነው፡፡ ቁርኣን ስንቀራባቸው፣ ተራዊህ ስንሰግድባቸው፣ ዚክር ስናዘወትረባቸው፣ ሶደቃ ስናበዛባቸው፣ መልካምነትን ስንላበስባቸው ነው፡፡

የረመዷን ቀናት አላህ (ሱ.ወ.) ዕድሎችና ቦነሶች ናቸዉና ተጠቀሙባቸው ብሎ የላከልንን የተከበሩ ቀናት ናቸው ፡፡ ዘጠኙ ቀናት እንዴት አለፉ በረቢ?፡፡

 መልካሞቹ የአላህ ባሮች ባለፉት ቀናት እየተቆጩ ለሚመጡት እየሳሱ እዚህ ደረሱ፡፡

በርግጥም ረመዷን የምር የሆነ ምርጥ ወዳጅ ነው፤ ተጠቀሙብኝ ብሎ በረከቱን ሁሉ ሳይሰስት ዘርግፎ ሠጠን፡፡
ጀሊሉ በቀሩት ቀናት ይበልጥ ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ተጠቃሚ ከሚሆኑት ያድርገን፡፡

Afdel
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣0️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
Be different😓
ተራዊህ በኋላ ቁኑት የሚያደርጉ ኡስታዞች ግን ለእኛ ወጣቶች አላህ የትዳር በርን እንዲከፍትልን ዱዐእ ማድረግ አለባቸው ከምር'😇
የቻልከዉን ያህል ተገኝ

አንዳንዴ በተራዊሕም ይሁን የግዴታ ሶላት ላይ የት እንደሄድክ ሳታውቅ የኢማሙን ተክቢራ እና ማሰላመት ከሀሳብህ ያነቃህ ይሆናል። አላህ ይዘንልን- ያለ ማስተዋልና ያለ ማስተንተን እንደ እንጨት ቆመን የምንሰግዳቸው ሶላቶች ብዙ ናቸው። ታድያ በዚህ ጊዜ ሁሉ በአካል እንጂ በሀሳብ ሶላት ላይ መገኘት አልቻልኩም ብለህ ሶላትህን አትተው። የቻልከዉን ያህል ለመገኘት ጣር። ከሶላቱ አምስት ይሁን አሥር ፣ ሀያ ይሁን ሰላሳ፣ ሀምሳ ይሁን ሰባ እጅ የሚፃፍለት አለ። ሰው ሆኖ ከሶላቱ መቶ በመቶ የሚፃፍለት አለ ለማለት ይከብዳል። መዳኛህ ነዉና ሶላትህን አጥብቀህ ያዝ። ሕይወት በሁሉም መስክ ትግል ናትና በተሻለ ሁኔታ ለመገኘት ታገል።

©
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1️⃣1️⃣  #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ረመዷን-11


እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው ይላሉ።
ለትንሽ ትልቁ ልድሃ ሀብታም ሚከፈትን ቤት የሰዉም ሆነ  የመላእክት ዱዓ አይለየዉም። የአላህ ችሮታም አይጎድልበትም።
እንግዳ እቤት ሲገባ በረከትና የአላህ እዝነት አብሮት ይገባል።
እንግዳው ብዙ ችሮታዎችን ይዞ ይመጣል፣ ወንጀልም አጥቦ ይሄዳል።
"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን  ያክብር።" ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ።

ፆመኛን ያስፈጠረ የሱን ያህል እኩል ምንዳ ያገኛል።
©
{أَنَا عِنْدَ ظَنِّ عَبْدِي بِي}
{እኔ ባርያዬ በጠረጠረኝ ቦታ ነኝ}ቡኻሪ

ቀኖቹ አንድ አይነትቢሆኑም እንኳን ሁኔታዎች ​​ተለዋዋጭ ናቸው፣ፍላጎትህ ላይ ለመድረስ መፍትሄው ሚስጥር ቢሆንም።አንድ ቀን ግን አላህ በምትጠብቀው መልካም ነገር ያበስርሃል...
ጌታችን አላህ ዕጣ ፈንታን በቅጽበት ይለዋውጣል፣ ምቾትም ከመከራ ልብ ውስጥ ይፈጠራል፣
በአላህ ላይ መልካምን እንጅ አትጠርጥር!
©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
ረመዷን - 12
****

ተቀምጦ መስገድ ሽንፈት የሚመስለው፤ አንካሳ ሆኖ በአንድ እግሩ ለተራዊሕ ቀጥ ብሎ የሚቆም አየሁ።
ጤናማና ጠንካራ ሆነው ጀርባዬን፣ እግሬን እያሉ በየሰበቡ ሶላት አቋርጠው የሚወጡትን አየሁ።
ከዚያም ራሴን ታዘብኩ፣
እንዲህም አልኩ ...
ሰው በኢማኑ ልክ ለሶላት ይቆማል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ አላህን ያወሳል፣
ዒባዳ ላይ የሚያፀናው አካላዊ ሳይሆን ኢማናዊ ጥንካሬ ነው፣
ሰው በኢማኑ ልክ ዲኑ ላይ ይፀናል።

አዎ ... ሰው ለአላህ ፍራቻ ባለው ልክ አላህን ይታዘዛል ።
ሰው ዉስጡ በያዘው ኢማኑ ልክ ፊቱ ይርሳል፣ እንባው ይፈሳል፣ ልቡ ይርዳል፣ አካሉ ይርበተበታል።
ሰው በኢማኑ ልክ እዝነቱ ይበዛል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ ቁርአን ይከፍታል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ መስጂድ ይመላለሳል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ ምጽዋት ይሠጣል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ ወንድም እህቶቹን ይወዳል፣
ሰው በኢማኑ ልክ ሥነምግባሩ ያምራል።
ወዳጆቼ !
ኢማን ምኞት አይደለም ሥራ ነው፣
ኢማን ምላስ አይደለም ተግባር ነው።
አላህ እውነተኛ ኢማን ይስጠን።

©Abx
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1️⃣2️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ስምህ በሰዎች ዘንድ መታወቁ አልያም ስራዎችህ ሰዎች ዘንድ አጀንዳ መሆናቸው ለአኼራ ስኬትህ ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም።

وَرُسُلًا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ

“...ባንተ ላይም ያልተረክናቸውን መልክተኞች (እንደላክን ላክንህ)..” ቁርአን 4፥164

በሰዎች ዘንድ የማይታወቁ አሏህ ﷻ ዘንድ ግን የሚታወቁ በርካታ ነብያት አሉ። አሏህ ዘንድ ለመታወቅ በርትቶ መስራት ትልቁ ስኬት ነው። የፍጡራን ሙገሳና እውቅና እዚህው ምድር ላይ የሚቀር ትርጉም አልባ ቅጽበት ነው። በምድር ባይታወቁም በሰማይ ከሚታወቁት አሏህ ያድርገን..!

مجهولون في الأرض معروفون في السماء،!

©