ASD AJ LAH
759 subscribers
1.78K photos
197 videos
3 files
508 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 2️⃣7️⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣5⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
I ወላሂ! ወቢላሂ! ወተላሂ! ረመዷንን ሳይጠቀምበት ያለፈበት ማንም ሰው  ዑዝር የለውም!
ሸይኽ ሱዑድ ሹረይም
ዝሆኖቹ የዓመቱን ወርቃማ ሰዓታት ይዘርፉን ይሆን !?
★★★

ኢማሙ ማሊክ እንደወትሮው የነብዩ _ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም_ መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ሀዲስ ያቀራሉ...
በዙሪያቸው ያሉ ደረሳዎቻቸውም ትምህርቱን በትኩረት እየተከታተሉ ነው...ድንገት ያልተለመደ ድምፅ ተሰማ፡-
"ትልቅ ዝሆን፣ትልቅ ዝሆን …" የሚል…

ከዚህ ቀደም የመዲና ሰዎች ዝሆን አይተው አያውቁምና ዝሆን በማየታቸው የተፈጠረው ወከባ አይደንቅም ነበር።

የኢማሙ ማሊክ ደረሳዎች በሙሉ ዝሆኑን ለማየት እየተጣደፉ ኢማሙን ጥለዋቸው ሄዱ ...ከያህያ ቢን የሕያ አልለይሲ በስተቀር።

ኢማሙም የሕያን " ዝሆኑን ለማየት አብረሀቸው ለምን አልሄድክም፣ ወይስ ዝሆን ላንተ አዲስ አይደለም?" ሲሉ ጠየቁት።

እርሱም " መዲና የመጣሁት የርሶን ዒልም ለመቅሰም እንጂ ዝሆን ለማየት አይደለም " ሲል መለሰ።

ይህን ክስተት በደንብ ካጤንነው ወደ መዲና ለምን እንደመጣ እና አላማው ምን እንደሆነ ከተሰብሳቢዎቹ ጠንቅቆ የሚያውቀው አንዱ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፤ ስለዚህ አልተዘናጋም፣ ትኩረት ሊያስቱ በሚችሉ አማላይ ነገሮች አልተሸነገለም።

በዚህም ምክንያት ኢማሙ ያህያ ቢን ያህያ አል-ለይሲ የኢማሙ ማሊክን አል-ሙወጠእ የተሰኘውን የሐዲስ ኪታብ በመዘገብ ልዩ ቦታ የሚሰጣቸው ሆነው እናገኛቸዋለን።

ሌሎች ጎደኞቹ የነበሩ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን ታሪክ አልጠቀሳቸውም።

በእኛ ጊዜም የዝሆኑ ታሪክ ይደገማል...ነገር ግን በተለያዩ ምስሎች...እና በተለያዩ መንገዶች...በተለይ በረመዷን።

በረመዷን ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፡–

1ኛ/ ግቡን ወስኖና ለይቶ... በረመዷን ውስጥ ማሳካት የሚፈልገውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤

2ኛ/በተለያዩ የዝሆን አይነቶች የተጠመደ... ፊልሞች፣ ገደብ የለሽ እንቅልፍ፣ ጫት እየቃሙ ማምሸት እና ሌሎች የዚህ ዘመን ዝሆኖች.. ‏ስለዚህ ከዘመኑ ዝሆኖች እንጠንቀቅ
የዓመቱን ወርቃ ሰዓት ይዘርፉናልና።

ረመዷን ከሪም!

ነስሩ ኸድር
ከረመዿን በፊት የመጨረሻውን ጁምዐ አንዴት ሆነን እያሳለፍነው ይሆን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ውብ_ውሎ
#ድንቅ_እሁድ
#መጋቢት_አንድ
#ሚሊኒየም_አዳራሽ
#ሁለት_ቀናት

ሁላችንም እሁድ  3:00 ሚሊንየም አዳራሽ ነሲሓ ኮንፈረንስ ላይ እንገናኝ
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 2️⃣8️⃣ #ሻዕባን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
نَحۡنُ قَسَمۡنَا بَیۡنَهُم مَّعِیشَتَهُمۡ
እኛ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡
ሱረቱ ዙኽሩፍ 32


ወዳጆቼ .. ዱንያ የሚገባዉን ትታ ለማይገባው ስትሸልም፣ መከበር ያለበትን አዉርዳ የሌለበትን ስታነሳ አይግረማችሁ፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገው የፈጠረን ጌታ አላህ ነዉና ብዙም አይግረማችሁ፡፡ እሱ ነገሮችን የሚያደርገው በዕውቀት እና በጥበቡ ነው፡፡ እኛ የነገሮችን ላያቸዉንና ጊዜያዊ ሁኔታቸዉን ስናይ እርሱ ደግሞ ዉስጣቸዉንና መጨረሻቸዉን ያውቃል፡፡ ስለሆነም እሱ በሚሠራቸው ነገሮች ማጉረምረምና መነጫነጭ አይገባም፡፡ በሥራዬ ምን ያገባችኋል የሚል በሚመስል መልኩ "እኔ ነኝ

ሲሳያችሁንና ኑሯችሁን የከፋፈልኩት፡፡” ብሎ ነግሮናል በቁርኣኑ፡፡

ሶበሐል ኸይር
ገፅ 54

መፅሀፊቱ እኔም እጅ ደርሳለች
ከሞትክ በኋላ ሰዎች በምን ያህል ፍጥነት እንደሚረሱህ ብታውቅ ኖሮ አሏህን እንጂ ማንንም ለማስደሰት አትኖርም ነበር።

آه لو علمت السرعة التي ينساك الناس بها بعد موتك، فلن تعيش حياتك لإرضاء أحد سوى اللّٰه.
#ውብ_ውሎ
#ምርጥዬ_እሁድ
#ከነሲሓ_ጋር
#ነገ_በሚሊኒየም_አዳራሽ

ሁላችንም ነገ እሁድ ጠዋት 3:00 ሚሊንየም አዳራሽ ነሲሓ ኮንፈረንስ ላይ እንገናኝ
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 2️⃣9️⃣  #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣5⃣
በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘውን የነሲሀ ኮንፈረንስ ፕሮግራም በቀጥታ ይከታተሉ

https://www.youtube.com/live/05T7KAA5ETA?si=ydsnxI6ot4a483WU

#ውብ_ውሎ
#ምርጥዬ_እሁድ
#ከነሲሓ_ጋር
#ዛሬ_በሚሊኒየም_አዳራሽ
ይሄ በየፕሮግራሙ ከኋላ ሆኖ በተክቢራ የሚያጅበው ሰውየ ግን ድምፁ👌
ቴሌስኮፖች ተወልውለው እየተገጠሙ ነው
ዛሬ ሻዕባን 29-1445 ሂጅሪ ነው ከዐስር በኃ ላ አይኖች ሁሉ ጨረቃን በፍቅር እና በናፍቆት ጥበቃ ይማትራሉ።
ውድ እና የረቀቁ ቴሌስኮፖች ተገጣጥመው ሰአቱን እየጠበቁ ሲሆን ጨረቃ ዛሬ ከታየች ማታ ተራዊህ ይሰገድና ነገ ረመዿን ፆመን የምንጀምር ሲሆን ካልታየች ደግሞ ኢንሻአ አላህ ነገ ማታ ተራዊህ እንጀምራለን። ፆማችንም ማክስኞ ይሆናል ኢንሻአ አላህ ።
ረሱል ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም የረመዿን ወር ሲመጣ ሰሀቦቻቸውን እንኳን አደረሳችሁ በማለት ያበስሩ ነበር። እኔም እንኳን አደረሳችሁ ማለትን ወደድኩኝ

የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ሰኞ መጋቢት 02, 2016 E.C. (March 11, 2024 G.C.) የረመዿን ወር የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።

አላህ ፆመውት በእርሱም ከወንጀላቸው መሀርታን አግኝተውበት የዘላለም ቤታቸው ባማረ ሁኔታ ከሚገነቡላቸው ሰዎች ያድርገን።

ረመዿን ሙባረክ
....ከጎናችን ባለው ሰው አይን ውስጥ ቀጣዩ ረመዳን የመጨረሻው እንደሆነ ብንመለከት ምን እናደርግ ነበር? አልያም.... ቀጣዩ ረመዳን የመጨረሻችን እንደሆነ እያየ ምንም ባይለን ምን ይሰማን ይሆን?.... ብዬ አሰብኩ..

.....አለ አይደል?.... በሚለዋወጥ አላቂ አለም ውስጥ የማይለወጥ ተደጋጋሚ እኛነት። የመጣውን ስለመጣብን ብቻ መቀበል... የለመድነውን ዑደት መደጋገም... ሲሄድ በግድየለሽነት መሸኘት። ቆይ ከዚ በኋላ ባይመጣስ?.... ለአንዴ እንኳን "ረመዳን ስለደረሰ አውቄም ሆነ ሳላውቅ...." በሚል መልዕክት ፈንታ "....ያ አኺ ፊላህ... የፊታችን ረመዳን የመጨረሻችን ይሁን አይሁን ስለማላውቅ በህይወታችን አሳልፈነው የማናውቀው አይነት ልዩ የዒባዳ ወር እንድናሳልፍ ልጠይቅህ ወደድኩ። አድርገነው የማናውቀው አይነት ልዩ ቃል እንገባባ። አደራህን ባሁኑ ለለይል ካልተነሳሁ ቀስቅሰኝ... ተራዊህ ላይም ካልተያየን ተደዋወለን እንተዋወስ... ቁርዓንን ደጋግሞ ከማኽተሙ እንለፍና እንማማረው... የመጨረሻችንም አይደል?... በቀን ውስጥ አላህን ባስታወስናቸው ሰዎች ቁጥር እንፎካከር... መጥፎ ቃል የወጣንም እንደሆን አሁን በምንገባባው ቃል ታስረን ሰደቃ እንስጥበት... እንደውም የተመደበች የሆነች ሰደቃን ያልሰጠንበት ቀን እንዳያልፍ.... የመጨረሻችንም አይደል?... በቃ... ለአንድ ወር ጀነት የምትገባቸው ሰዎች እንሁን.... ምናልባት ከዚያ በላይ ረመዳኖችን እንድንኖር ተፅፎልን እንደሆንና ተኮራርፈን ቢሆን እንኳ... 'ያኔ ባሳልነፍነው 30 መልካም ቀናት ትዝታ' ስም ያለ ቴክስት አማላጅ አፉ እንባባላለን።" የሚል መልዕልት ቢደርሰኝ ተመኘሁ። ያ ኡመተል ሀቢብ.... አላፊ የሆኑ ወዳጆቻቹንና... መጪዎቹን የሚቆጠሩ ቀናት አደራ...

TEAM HUDA

اللهم بلغنا رمضان وأعنا على صيامه وقيامه، اللهم اجعلنا من عتقاءك من النار في هذا الشهر الكريم، واجعلنا من المقبولين عندك فيه، اللهم تقبل منا صالح الأعمال واغفر لنا ذنوبنا، وارزقنا الجنة برحمتك يا أرحم الراحمين. آمين.
‏                 🌙🕌 🌙
              ساعات قليله
        وتبدأ القصة الجميلة
   وتعلو المساجد بأصوات الدعاء
       وتسكن السعادة قلوبنا
*اللهم أرزقنا رمضان وبارك لنا فيه*

الْلَّھُم أَهِلَهُ عَليْنَا بِالْأمْنِ وَالإِيْمَانِ وَالْسَّلامَةِ وَالْإِسْلَامِ وَالْعَوْنٓ عَلَى الْصَّلاةِ وَالصِّيَامِ وَتِلَاوَةِ الْقُرْآَنِ الْلَّھُمّ سَلِّمْنَا لِرَمَضَانَ وَسَلِّمْهُ لنا وَتَسَلَّمْهُ مِنّا مُتَقَبَّلاً يٓارٓبٓ العٓالِٓمينْ .

*اللهم صلّ وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين*
       
مُبارٓكٌ علٓيْكم شّٓهرُ رٓمٓضٓان
  🌙 وكل عام وأنتم بخير🌙🤍
ወደ ከፍታ፣ ወደ ለውጥ ጎዳና፣ ወደ ክቡር ሰብዓዊነት፣ ወደ በረካ፣ ወደ እዝነት፣ ወደ ነፍስን መግርያ፣ ወደ እርቅ ማዕድ፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ስክነት፣ ወደ አብሮነት፣ ወደ ተወዳጁና ተናፋቂው፣ የኸይር ወር ወደ ሆነው፣ የማይጠገበው ውድ የሆነው የረመዳን ፆም በአላህ ፍቃድ እንኳን አደረሰን።
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል አላህ እንዲያደርገን ዱዓዬ ነው።
አንዳንዴ ገጥሞህ ያውቃል የሆኑ ነገራትን ላለማጣት ደክመህ ፣ ላለመውደቅ ታግለህ በመጨረሻም ኡፍፋህ አሳካሁትኝ የምትልበት ዓይነት የደስታ ስሜት ?

በረመዳኑ ታጥበን ተቀሽረን በውስጡ ለዓመታት አጭደን በዐፊያ ስንጨርሰው በመሄዱ እያዘንን ባገኘነው ረክተን « እረ - መዳን» የምንልበት ረመዷን አላህ ያድርግልን ።

ረመዳን ሙባረክ 🖤

አብዱ ረዛቅ
ተሰሀሩ🗣 ፈኢነ ፊሱሁሪ በረካ
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 0️⃣1️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣