ASD AJ LAH
762 subscribers
1.78K photos
196 videos
3 files
504 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
መዳን!
በአላህ ስም - ተከተበ ከFLSI

በጠዋት በስልኬ ከሚደርሱኝ እለታዊ መልእክቶች አንዱ 86/87 ቀን ስለቀረው ረመዷን የሚያወራ የጁምዓ ማስታወሻ ነበር። ትናንት ኢድ ብለን ያከበርን ያህል ያልራቀብኝ የትናንት ረመዷን ትውስ ቢለኝ ትዝብቱ እየታየኝ ተሳቀቅኩ።
«
ወንጀልህ ተወዝፎ ሲያበቃ፣ 'ተውበት' ይሉት አጥር አልባው የጌታህ ደጃፍ መኖሩን ስትዘነጋ፣  የዳኢም ኗሪ መሆንህን ባመንክ ጊዜ ከአዘቅትህ ደርሼ አውጥቼህ አልነበር?
እንኳን የሌት ስግደት የብርሐኑንም ስግደት መፈፀም የማትችለውን አንተን፥ ወደተሐጁድ ሶላት ያስገሰገሰህ ኑረቴ አልነበረም?
ከነፍስያህ እኩል እየተስገበገበ ለሐራም የሚያበጃጅህ ጠላትህ ታስሮ የራቀህ በኔ አልነበረም?
እጅ እግርህ ወደሐራም ከመሮጥ ታቅቦ በሐያእ የጌታህን መሐርታ እንዲለምንልህ አልረዳሁህምን?
እድፍ መኖሪያው እንዲሆን የፈረድክበትን የጌታህን ውድ ቃል ዳግም ታነበው ዘንድ የሆነው በኔው መኖር አልነበረም?
ከአንድ ሺህ ወራት በላጭ የሆነችውን ለሊት ያገኘኸው፤ ከውጥንቅጥ አለም እረፍት የተሰጠኸው በኔው ከሆነ ኋላ ውለታዬን ቀርጥፈህ ዳግም ያገኘሁህ ቦታ መገኘትህ ስለምን ነው? ነፍስህን ከሐጥእ አላቅቄ ወደኸይር ያደረስኩህ መስሎኝ ለኔ ብቻ እየኖርክ እንደነበር ሲገባኝ እርግጥ አዝኛለሁ።
ቢሆንም ድጋሚ ነፍስህን ከማደስ አልሰንፍምና እየመጣሁ ነው።
»
የሚለኝ ይመስለኛል። አይሆኑ ቦታ ላይ መሆኔ ይታወቀኛል'ኮ። ግን ከነፍሲያ ልቆ ትክክለኛውን መርጦ ማድረግ ረሱሉ ﷺ እንዳሉት ጂሐድ ኾነብኝ።

ከሱ መምጣት የኔ መሞት ቢቀድምስ የሚለው ሐሳብ እንደፈራሁት ተከትሎ አእምሮዬን ያናውጥ ያዘ።  ከአምዋት መንደር ስለሚፀፀቱበት ነገር ሲጠየቁ አንድ ረመዷንን ድጋሚ ማሳለፍ ቢችሉ ብለው እንደሚመኙ ስሰማ ማደጌ ይሁን ወይም እኔም የሚሰማኝ የረመዷን ጥልቅ እድሳት ስሜት ... ብቻ አንዱ ረመዷንን ቆሽሼ ለመንፃት የምጠባበቀው ሳይሆን በጦሀራ እንድቀበለው ይወተውተኝ ያዘ።
ክረምት ክረምት ረመዷን በሚሆንበት ዘመን አያታችን ጋር የመሔድ እድሉን ስናገኝ አያቴ ሁሌም የሚመክሩን ሐሳብ ሽው አለብኝ።
«ረመዷንን ዝግጁ ሁነህ ከተቀበልከው ሠላሳውንም ቀን ትጠቀምበታለህ። እንዲያዘጋጅህ ሁነህ ከተቀበልከው የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ትነቃና  'ረመዷን ሮጠብኝ' እያልክ ለመጠቀም ስትፍጨረጨር ያልቅብሐል የኔ ልጅ። 'የተቆጠሩ ቀናት...' ሲል አሏህ የነገረንኮ ቀናቱ እንዳጀማመራቸው ኹሉ ማለቃቸውም አይቀርም ሊለን ነው።» ይሉን ነበር።

እንግዲህ የማይደርስ ቢመስልም ወደጌታችን ይበልጥ የምንቃረብበት ረመዷን ከሩቅ መአዛው እያወደን ነው። ነገ ቃል አልተገባልንምና ዛሬንም ነገንም ኸይር  እየሞከርን ረመዷንን መጠበቁ ሳይበጀን አይቀርም። መለከል መውትም ይሁን ረመዷን ቀድመው ቢያገኙት ግድ የማይሰጠው ሰው ከመሆን በላይ እድያ ይኖር ይሆን?
አብዛኛውን ጊዜ ካለንበት ሁኔታ  አንፃር ጥሩ የሚመስለንን አላህ ሲነጥቀን ይከፋናል :: ከሰጠን ስጦታዎች መካከል ሲያጎድልብን የጠላን ይመስለናል :: አልፎ ስናየው ግን ስጋትን አስወግዶ ራሳችንን የተሻለው ላይ እናገኛለን :: ምስጋና ይድረሰው ::

    እሱ ሰጪው አላህ እስካለልን ድረስ የስጦታዎች መጥፋት ለተሻለ ስጦታ በር ናቸው :: እሱ አላህ በልባችን እስከነገሰ ድረስ በእጃችን ላይ የሚመላለሱ ነገሮች አይከብዱንም ::

©
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠያቂው "ፍቅረኛ ለምን የለህም"
ሙስሊምን ስትጠይቅ "ፍቅርኛ ለምን የለህም" ? ሳይሆን "ለምን አላገባህም ወይም ለምን አላገባሽም"? ነው የሚባለው ።
መልካም አዳር
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 10 #ጁማደል አኽር 1445 ሂ
የሱብሂ አዛን ከምሽቱ እንቅልፍ የቀሰቀሰው አለ :: ለእርሱም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በእንቅልፍ ውስጥ ያለ አለ :: "ወደ ስኬት ኑ!" ብሎ ለሚጣራ ተጣሪ መልስ እንዳለመስጠት ምንኛ አለመታደል አለ? ሶላታችን የስኬታችን ቁልፍ ናት !!

   መልካም ቀን !!

©
All ሀበሻ people from his home to ለቅሶ ቤት he gossip the ሟች saying "እሱማ እንኳን ድብን አለ 1000 አበድሮኝ መውጫ መግቢያ ያሳጣኝ ፣ ቋጣሪ ልጆቹን ሁላ ደህና ትምህርት ቤት ሳያስተምር ለማይሞላ ኑሮ ፣ ልክስክስ ፣ ሌባ" their is nothing left ስለእርሱ የሚወራ after all of that ልክ ለቅሶ ቤት ለመድረስ 100m ሲቀረው ደረቱን እየደለቀ shout saying "ኣኣህ ወዳጄ ኡኡ የጭንቅ ለት ደራሼ ፣ መካሪዬ…" አብሶ If the ሟች is wealthy man😩
what I saying is do the ሟች from his funeral ብድግ ብሎ "ውርሴን ለእርሱ ስጡልኝ" ይላል እንዴ oh😖
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
يَوْمَئِذٍ يَتَّبِعُونَ الدَّاعِيَ لَا عِوَجَ لَهُ ۖ وَخَشَعَتِ الْأَصْوَاتُ لِلرَّحْمَٰنِ فَلَا تَسْمَعُ إِلَّا هَمْسًا
በዚያ ቀን (ለመሰብሰብ) ጠሪውን ለእርሱ መጣመም የሌለውን መከተል ይከተላሉ፡፡ ድምጾችም ለአልረሕማን ጸጥ ይላሉ፡፡ ስለዚህ ሹክሹክታን እንጂ አትሰማም፡፡

يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا
በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትንና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ (አንድንም) አትጠቅምም፡፡

يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِهِ عِلْمًا
በስተፊታቸው ያለውን በስተኋላቸውም ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በእርሱም ዕውቀትን አያካብቡም፤ (አያውቁም)፡፡

وَعَنَتِ الْوُجُوهُ لِلْحَيِّ الْقَيُّومِ ۖ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا
ፊቶችም ሁሉ ሕያው አስተናባሪ ለኾነው (አላህ) ተዋረዱ፡፡ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ፡፡

وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا يَخَافُ ظُلْمًا وَلَا هَضْمًا
እርሱ አማኝ ኾኖ ከመልካም ሥራዎችም የሠራ ሰው በደልንም መጉደልንም አይፈራም፡፡
ሱረቱ ጧሀ 108-112


GOOD NIGHT WITH GOOD DREAMS😊😊😊
Via Rafeeq
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 11 #ጁማደል አኽር 1445 ሂ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
الرَّحْمَٰنُ
አል-ረሕማን፤

عَلَّمَ الْقُرْآنَ
ቁርኣንን አስተማረ፡፡

خَلَقَ الْإِنسَانَ
ሰውን ፈጠረ፡፡

عَلَّمَهُ الْبَيَانَ
መናገርን አስተማረው፡፡

الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ بِحُسْبَانٍ
ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡

وَالنَّجْمُ وَالشَّجَرُ يَسْجُدَانِ
ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡

وَالسَّمَاءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ الْمِيزَانَ
ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡

أَلَّا تَطْغَوْا فِي الْمِيزَانِ
በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡

وَأَقِيمُوا الْوَزْنَ بِالْقِسْطِ وَلَا تُخْسِرُوا الْمِيزَانَ
መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡

ሱረቱርረህማን  1-9

Via Rafeeq
GOOD NIGHT WITH GOOD DREAMS😊😊😊
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 12 #ጁማደል አኽር 1445 ሂ
አይመልሱልህምና መፅሀፎችህን ለሰው አታውስ። እቤቴ መደርደሪያ ላይ ያሉት መፅሀፎችም ሰዎች ለኔ ያዋሱኝ ናቸው

አናቶል ፍራንስ
የሰው ልጅ ስሜት ስስ ከመሆኑ የተነሳ ለአንተ ቀላል በሆነች አንዲት ቃል ፣ ጠንከር ባለ ድምፅ…ሁላ…ጮክ ያለ እይታ የቀን ሙሉ ውሎው ሊበላሽ ይችላልና…
በዩኒቨርሲቲ ህይዎታችን ውስጥ ልንፈፅማቸው የሚገቡ ተግባራት !!

   1) ውሃ አለማባከን:- ስንታጠብም ሆነ ስንጠጣ ውሃ ማባከን የለብንም :: ሀቢቡና (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "የወራጅ ውሃን እንኳ ቢሆን አታባክኑ!" ብለዋል:: ስለሆነም ቧንቧ ከፍተን አንተው :: ዘግተነው እንለፍ

   2) ፈገግታ : ከካፌ እናቶች ጋር ስንገናኝ : በጥበቆች ዘንድ በበር ስናልፍ : ክላስ ከጓደኛም ሆነ መምህር ጋር እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች ውስጥ ፈገግታ ሊለየን አይገባም :: ሰደቃ ነው ተብለን ተምረናል ::

  3) ምግብ ጨርሶ መብላት : የቀረበን መጨረስ ሱና ነው :: ስለሆነም የማንጨርሰውን አናስደርግ :: አንድ ዳቦ የሚበቃን ከሆነ እርሱን ብቻ ማስደረግ :: በአጠቃላይ የቀረበውን በሙሉ ከልክ ሳናልፍ በመጨረስ ዲናችንን መፈፀም ግድ ይለናል ::

   4) ሰላምታ ማብዛት : "ትዋደዱ ዘንድ ሰላምታን አብዙ" የሚል ድንቅ አስተምህሮ ባለቤት ነን :: ስለሆነም የአላህን ሰላምታ በወንድም እህቶቻችን ላይ እናውርድ :: እንመልስ ::

   5) ከመንገድ ላይ የሚያስቸግርን ነገር ማንሳት : ይህን ተግባር አብዛኛውን ጊዜ የፅዳት ሰራተኞች ብቻ አድርገን እናስባለን :: እነርሱ ያፀዳሉ :: እኛ እናቆሽሻለን :: ነገርግን እስልምናችን "ከመንገድ ላይ የሚያስቸግሩ ነገሮችን ማንሳት" ከኢማን ቅርንጫፎች መካከል እንደሆነ ያስተምራል :: ከቻልን የሚያፀዱትን በማገዝ ተምሳሌት ብንሆን ለራሱ ጥሩ ነው ::

  6) መልካም ስነ-ምግባር : ከሁሉም ጋር በምናደርገው ግንኙነት ኢስላማዊ አደብን በተላበሰ መልኩ መሆን አለበት :: ከካፌ እናቶችና ከጥበቃ ሰራቶኞች ጀምሮ እሰከ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ድረስ ማለት ነው ::

7) እስልምናን የሚገልፁ አለባበሶችን ማዘውተር : ግቢ ውስጥ ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር እንደመኖራችን እምነታችንን የሚማሩት ከእኛ ከሚታዩ ነገሮች ነው :: ስለሆነም ያንን አለባበስ ለብሰን ከመልካም ተግባራት ጋር በማቆራኘት እስልምናን በተግባር ልንሰብክ ግድ ይለናል :: እህቴ ኒቃብና ጂልባብሽን የዘወትር ልብስሽ አድርጊው :: መልካም ስነ-ምግባርንና መልካም ተግባርን የዘወትር መገለጫሽ አድርጊ :: አንድ ቃል ከአፍሽ ሳይወጣ ሰዎች ከአንቺ እስልምናን ይማሩ :: ወንድሜም እንዲሁ :: ሙደወርና አማይማ የአንተ ልብስ ይሁኑ :: እስልምናንም በተግባር ኑረው :: ከተግባርህ ሌሎች ይማሩ ዘንድ ማለት ነው ::

MohammadamminKassaw


وإنه لجهاد نصرا أو إستشهاد
ሚስጥር ሆኖ ሳይሆን ስለማያገባህ ነው አትፈላፈል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
قَالُوا رَبَّنَا غَلَبَتْ عَلَيْنَا شِقْوَتُنَا وَكُنَّا قَوْمًا ضَالِّينَ
ይላሉ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፡፡ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን፡፡

رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْهَا فَإِنْ عُدْنَا فَإِنَّا ظَالِمُونَ
«ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣን፡፡ (ወደ ክህደት) ብንመለስም እኛ በደዮች ነን፡፡»

قَالَ اخْسَئُوا فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ
(አላህም) «ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ አታናግሩኝም» ይላቸዋል፡፡

إِنَّهُ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا وَأَنتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ
እነሆ ከባሮቼ «ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን፡፡ እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» የሚሉ ክፍሎች ነበሩ፡፡

ሱረቱል ሙእሚኑን 106-109

GOOD NIGHT WITH GOOD DREAMS😊😊😊

Via Rafeeq
ሶቅራጠስ እንዲህ አለ አሉ "ልጅ ሳለሁ በግዜ መነሳትን መጥላቴ የኔን የወደፊት ትልቅ ነጋዴ መሆንን እምትሻዋን እናቴን ያበሳጫት ነበር። የሆነ ቀን በግዜ የመነሳትን ጥቅም ሊያስረዳኝ ዘንዳ እናቴ አንድ ምሁር ጋር ይዛኝ ትሄዳለች።

ምሁሩ:- ይሀውልህማ ሶቅራጠስ አንድ ታሪክ ተርክልሀለሁ ከታሪኩ የተማርከውን ትነግረኛለህ ተግባባን

ሶቅራጠስ:- አው በሚገባ

ምሁሩ:- ሁለት ወፎች ነበሩ አንደኛው በግዜ ተነሳና ትላትሎችን በልቶ ጫጩቶቹን መገበ። ሁለተኛው ደግሞ አርፍዶ ተነሳና የሚበላውን ሊያገኝ አልቻለም አንተ ምን ተማርክ?

ሶቅራጠስ:- በግዜ የሚነሱ ትላትሎች በወፎች እንደሚበሉ🥴

ደህና እደሩ
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 13 #ጁማደል አኽር 1445 ሂ
ውዴታን ፍቅርን መተሳሰብን የሚገልፀው ተግባር ነው። ለንግግርማ ሁሉም ፈላስፋ ነው😒

ጁብራን
በዙርያህ ምን እየተከሰተ እንደሆነ እያወቅክ ዝም ማለት ሙድ አለው😕