ASD AJ LAH
753 subscribers
1.79K photos
197 videos
3 files
511 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 7 #ሙሐረም 1445 ሂ
የሀብታሙ ጌታ ባርያ ሆኜ ሳለ እንዴት ድህነትን እፈራለሁለኝ
#የአሹራ ቀን ፆም!

ለመልካም ስራ አስተዋሽ እንሁን

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾

“የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1134


በሌላ ሀዲሳቸው (ﷺ)፦

﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾

“የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
ASD AJ LAH
ሙስሊም ኢትዮጲያዊ ናችሁ ወይስ ኢትዮጲያዊ ሙስሊም😌 ሶስተኛ እይታ ያላችሁ ወዲህ በሉትማ የነገ ሳምንት እሁድ ዕለት አንድ አሰልጣኝ በስልጠና መሐል ከጠየቀን ጥያቄ https://t.me/asdajlahh
በዚህ ከላይ ባያያዝኩላችሁ 👆👆ጥያቄ ላይ

"ሙስሊምነቴ ለንፅፅር እማይቀርብ አንድ የኔነቴ መለኪያ ስለሆነ ሲጀመር ይህን ጥያቄ ልጠየቅ አይገባም አለቀ! ኢትዮጲያዊ ነኝ የሚደርስብኝ በደል ሙስሊምነቴን ተንተርሶ ቢሆንም… " ብሎ የመለሰው ቡድን የሀሳባቸው ተጋሪ ሆኛለሁ

እናንተስ
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 8 #ሙሐረም 1445 ሂ
ASD🫱🏻‍🫲🏿VPN
ዓሹራ

የሙሐረም ወርን አላህ (ሱ.ወ) "የተከበረው የአላህ ወር" ብሎታል። ሙሐረም አስረኛው ቀን የዓሹራ ቀን በመባል ይታወቃል። ትርጉሙም አሥረኛው ቀን ማለት። ቀኑ የድል ቀን ነው። አላህ ለነቢዩ ሙሳ ፊርዐውን ላይ ድልን የሠጠበት ቀን። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ቀኑ ፆመዋል፣ እንዲፆም አዘዋል። በሚቀጥለው አላህ ካደረሰኝ ዘጠነኛዉን ቀን ጨምሬ እፆማለሁ ብለው ነበር። ገና አልደረሱም። ቀኑን አይሁዶች በዓል አድርገው ይዘውታል። ይፆሙታልም። ከነርሱ ለመለየት ሲባል ከአሥረኛው ቀን በፊት ወይም በኋላ አንድ ቀን መጨመር ይወደዳል።

ቡኻሪና ሙስሊም ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት “የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና እንደገቡ አይሁዶች የዓሹራን ቀን እየፆሙ አገኟቸው። ከዚያም ‘ይህ የምትፆሙት ቀን ምንድን ነው?’ ብለው ጠየቁ። ‘ይህ ቀን አላህ ሙሳን ያዳነበት እና ፊርዓውንን ያሰጠመበት ቀን ነው። ሙሳ ምስጋናውን ለማድረስ ፆመዉታል። እኛም እንዲሁ እንፆመዋለን።’ አሉ።
ከዚያም የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ‘እኛ ከናንተ ይበልጥ ለሙሳ የቀረብን ነን!’ አሉና ፆሙት፤ እንዲፆምም አዘዙ።”

ይህን ቀን መፆም ያለውን ቱሩፋት አስመልክተው ብዙ ሐዲሶች ተወርተዋለወ

ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ)  “የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሌሎች ቀናት አስበልጠው አጥብቀው የሚፆሙት እንደዚህ ቀን -ዓሹራ- እና እንደዚህ ወር -ረመዳን- ያለ የለም።” ብለዋል።

ይህ ቀን ከሌላው የላቀ የሆነበት ምክንያት አላህ ነብዩ ሙሳን እና ተከታዮቻቸውን መርዳቱና ፊርዓውንን እና ሰራዊቶቹን በማስመጥ ድል እንዲጎናፀፉ ማድረጉ ነው።
ስለዚህ ድሉ የተበዳዮች ሁሉ ነው።
አንዳንዴ ደግሞ እንፖተልክ
"ለምንድን ነው የቤት ስራህን ያልሰራሀው!?" መምህሩ ተማሪያቸውን ታንቡሩ እስኪበጠስ በጥፊ ካጮሉት ኋላ ያስከተሉት ጥያቄ ነው
ተማሪውም ረጋ ብሎ "ያነበብኩት ያጠናሁት ነገር አልዋጥ ቢለኝ ግዜ ነው አለመስራቴ" አለ
"አልገባኝም ማለት? መጀመሪያ እዚህ እያለህ አትጠይቅም ነበር እዚህ ደርሶ አልገባኝም አልተዋጠልኝም ማለት ምን ማለት ነው!? ምኑ ነው ያልገባህ¿" አሉ መመህሩ
"ይሀውሎት መምህር መፅሀፉ ሀገሬ ሀብታም ነች ይላል እኛ ግን እምንኖረው ከጭቃ በተሰራ ቤት ነው። እምለብሰው ልብሴ ፣ ቦርሳዬ  በቃ ሁሉም የትምህርት ቁሳቁሶቼ መፅሀፎቼ ሳይቀሩ ከበጎ አድራጎት ማህበራተ እና ሚስዮኖች ነው የተበረከተልኝ ፤ መፅሀፉ ሀገሬ ብዙ የሆነ የጨው ማዕድን ክምችት አላት ይላል ግን አያቴ የደየመችው እንቅርት እሚባል እና ጨው ውስጥ ሊገኝ በሚችል አዮዲን እጥረት ምክንያት ነው። እናቴ ዛሬም ድረስ እስር እንጨት ገዝታ ተሸክማ አምጥታ ምግብ እየሰራችልን አይኗ ቀላልቶ መጥፋት ነው የቀረው ፤ መፅሀፉ የሀገሬ ሰዎች በጎ ናቸው በመቻቻል ያምናሉ ይላል እኔ ግን ይህ አይታየኝም አባቴን በማንነቱ ምክንያት በደረሰበት ግድያ ነው ያጣሁትኝ በቃ በጎነት ትቶን ወደሌላ ቦታ የተሳፈረ የሄደ ያህል ነው እሚሰማኝ ፤ መፅሀፉ ሀገሬ እማይበጠስ ጠንካራ ባህል ፣ ገናና እና የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ አላት ይላል ግን ራሴን እጠይቃለሁኝ ሀገሬ ሁሌ እታች ሆና ሌላው ለምንድን ነው እሚያድገው? ፤ ደግሞ እኮ በእሱም አያበቃም መፅሀፉ የሀገሬ ዜጎች በመብቶች እና ግዴታዎች ላይ እኩኩል ናቸው ይላል ግን እኔ አንዲትን ነገር እንደ ዜጋ እንደ ሰው እሚገባኝን ነገር ላገኝ አልቻልኩኝም ይቅርታ መምህር እኔ ራሴን መሸወድ መዋሸት አልወድም ለዚያ ነው የቤት ስራዬን ሳልሰራ የመጣሁት ስላልተዋጠልኝ"


https://t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 9 #ሙሐረም 1445 ሒ
ሐጅ ለማድረግ ወደ ሳኡዲ ከተጓዙ ኢትዮጵያን ውስጥ 5 ምዕመናን ሞተው በመካ ተቀብረዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ሐምሌ 19/2015
...
عن ابن عباس رضي الله عنهما: (أن رجلاً خر من بعيره -أي: من فوق بعيره- فوقص فمات، فقال النبي عليه الصلاة والسلام: اغسلوه بماء وسدر، وكفنوه في ثوبيه، ولا تخمروا رأسه، فإن الله يبعثه يوم القيامة ملبياً)

ለ1444 ሀጅ ሥነ-ሥርዓት ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተጓዙት ጠቅላላ ሁጃጆች 11245 አከባቢ ሲሆኑ፣ ሀሉም በሚባል ደረጃ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በተለያዩ ምክንያቶች 5 ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች ሞተው በመካ ተቀብረዋል።
..
1/ ሐጅ አልዪ አባግሳ አባዳማ መካ እንደ ደረሱ ወደ አረፋ ጉዞ ሳይጀመር በህመም ምክንያት መካ ውስጥ ህይወታቸው አልፏል።

2/ ሐጅየት መርየም ሀሚድ አብደላህ ጀመራትን ካጠናቀቁ በኋላ በሚና ህመም ፀንቶባቸው ህክምና ላይ እያሉ ወደ አላህ ፊት ሄደዋል።

3/ ሐጅ ሞሊድ አወሉ ሳዲቅ ከአረፋ በኋላ የሐጅ ሥነሥርዓትን ካጠናቀቁ ቡሃላ በህመም ምክንያት ወደ አኺራ ሄዱ።

4/ ሐጅየት ማሪያ አማን ደርጊ ሀጅ ጨርሰው ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ጅዳ አየር ማረፊያ ውስጥ ከገቡ ቡሃላ በልብ ህመም ምክንያት ድንገት ሕይወታቸው አርፈዋል። አስክሬናቸው ወደ መካ ተመልሶ በክብር ተቀብረዋል።

5/ ሐጅ አደም ሙሀመድ ይመር የአውሮፕላን ትኬት ወስደው ወደ ሀገር ለመመለስ የመሰናበቻ ጠዋፍ ጨርሰው እንደወጡ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው አርፋለች።

ሁሉም ሟቾች ከሐጅ አደም ሙሃመድ በስተቀር የሚመለከታቸው የመጅሊስ ልኡካን ቡድን አስፈላጊውን ዶክመንቴሽን ከጨረሱ ቡሃላ ቀብራቸው ላይ በመገኘት በክብር ሸኝተዋል። 6ተኛው ሁጃጅ ሀጅ አጠናቀው ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ ቡሃላ መሞታቸውን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል።
....
አላህ በትንሳኤ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሀዲስ መሠረት ላበይክ እያሉ የሚቀሰቀሱ ያድርጓቸው። ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው አላህ መጽናናትን ይስጣቸው።
...
◾️ ዘገባው የኦሮሚያ መጅሊስ ነው

© ሀሩን ሚዲያ
አፍቃሪዎች ልዩ የሆነ ስሜት አላቸው። ለአላህ ልዩ የሆነ የፍቅር ስሜት ደግሞ ትልቁን የስሜት ደረጃ ይይዛል። በአፍቃሪና በተፈቃሪ መሐል የግንኙነት መስመር አለ በአላህ እና በባርያው መሐል በጁምዐ ቀን የሚደረግ ዱዐእ ደግሞ በአላህ እና አላህን በሚወድ ሰው መሐል ያለ የግንኙነት መስመር ነው። የሐሙስ ዕለት ፀሀይ እንደገባች ለዱዐእ የተቀመጠች ነፍስ እሷን ለሚወዳት ነፍስ ዱዐእ ማድረግን አትዘንጋ።

መልካም የተባለን ሁሉ ባደረገልን ጌታ በተላኩት እና ልብ ከልብ አዋደው ፍቅር ባስተማሩን ነቢይ ላይ ሰለዋትን አውርዱ،

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا محمد وآله وصحبه الكرام

በጨለመ ዘመን ላይ ብርሀንን ማየት ያሻች ነፍስ ሱራ አልካህፍን በጁምዐ ቀን ትቅራ በዱዓእ በሰለዋት በዚክር የተዋበ ምርጥዬ ጁምዓ ይሁንልን


https://t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 10 #ሙሐረም 1445 ሂ
ASD AJ LAH
የማለዳ ማስታወሻ 37 ያዕቁብን አልዘነጋውም … ግን የዩሱፍን ንግስና እየገነባ ነበር… ሰዓቱ ደረሰ… ቀሚሷ የያዕቁብን የአይን ብርሃን እንድትመልስ አደረጋት… ህፃን እያለ ያጣው የዓይን ማረፊያ ልጁን ትልቅ ሆኖ ከንግስናው ጋር ተመለከተው… ልቡ ተጠገነች… አህባቢ… እርሱ ልቦችን እንዴት እንደሚጠግን ብታውቁ  ተስፋ መቁረጥ አይጠጋችሁም ነበር። Copied https://t.me/asdajlahh
የማለዳ ማስታወሻ 38

ልዩነት መኖሩ…መጣላታችን…ይቅርታ መጠየቅ…መወቃቀስ…መገናኘት…መሰባሰበ… መዋደድ…መለያየት ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ህይወት ውስጥ በፍቅር ብንጣላ…በመተናነስ ይቅርታ ብንጠይቅ…በምክር ስሜት ብንወቃቀስ…በፍቅር ብንሰባሰብ እና ብንገናኝ…በፍላጎት ብንለያይ ኖሮ ምንኛ ባማረች!
ህይወት አንዳንዴ ልክ እንደጨው ትመራለች ግን መልካም ስነምግባር ጋር መዋደድ መረዳዳት ጋር በተደባለቀች ቅፅበት ትቀልጥ እና ጣፋጭ ትሆናለች።

እየተዋደድን ጎበዝ

https://t.me/asdajlahh
ከፊለፊታቸው ትልቅ ባህር ከኋላቸው ትልቅ ጦር አለ
ወዴትም መሸሽ አይችሉም፤የሙሳ ወገኖች ተጨነቁ፣ተስፋ በመቁረጥ ስሜትም እንዲህም አሉ :-

❄️{فَلَمَّا تَرَاءَى الْجَمْعَانِ قَالَ أَصْحَابُ مُوسَىٰ إِنَّا لَمُدْرَكُونَ}

"ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ የፈርዖን ሰዎች የሚደርሱብን ነን» አሉ፡፡"[ሹዓራዕ:61]

ሙሳም በጌታቸው ላይ ያላቸውን ፅኑ እምነት አሳዩ አሉም...
❄️{قَالَ كَلَّا ۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ}

"(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡"[ሱረቱ ሸዓራዕ:62]

ረበል ዓለሚንም መንገዱን የያዘን በፍፁም አይተውም
በእርሱ የተመካን በፍፁም አያሳፍርም
በእርሱ የተማመነን በጭራሽ ባዶውን አይመልስምና
በእርሱ ለተመኩት በመንገዱ ለተጓዙት በሩን ከፈተላቸው እንዲህም አላቸው...

{فَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْبَحْرَ ۖ فَانفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرْقٍ كَالطَّوْدِ الْعَظِيمِ}
"ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡መታውና ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡"[ሱረቱ ሹዓራዕ:63]

የሚፈሰውን ባህር ያለ ባህሪው ለሁለት ተከፈለ
እንደ ተራራም ቀጥ ብሎ ቆመ
ወዱዱም ምድሩን ንፉስን ልኮ ደረቅ ጭቃ አደረገላቸው
እንዳይፈሩን ከባህሩ አንዳቸው አንዳቸውን የሚመለከቱበትን መስኮት አበጀላቸው

እንዴት ያስደስታል የራህማኑን እንክብካቤ

ምንም ብንተወው እና ብንርቀው ማይተወን አዛኝና ተንከባካቢ ጌታ ባሪያ መሆን አንዴት ያስደስታል


    ዓሹራእ_የአሸናፊትት_ስነልቦና
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين
ሙሳን ከአንባገነኑ መሪ ነፃ ያወጣው ወዱድ እኛ ጋር ያለውን አስቸጋሪ ነገር ከእኛ የሚያነሳበት በዱዓ፣በካህፍ፣ ይህን ያማረ ታሪክ እንዲደርሰን ሰበብ በሆኑት አሽረፈል ኸልቅ ላይ የበዛ ሰለዋት በማድረግ የፈካ እና የደመቀ ጁምዓ ይሁንልን!!!
ልክ ወደ እኔ ጠጋ ብሎ "በጣም አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ሲለኝ ነበር ልብ ያልኩት ሰዎች አውቆ አበድ ነው ይሉታል።ከዚያም የመዋረድ ስሜት እንዳይሰማው በሚል ፈጠን ብየ"ይቻላል ይቻላል" አልኩትኝ ቀጠል አደረገ እና "እውን እኔ አብጃለሁኝ? እብድ እመስላለሁኝ እንዴ?"አለኝ። ያው ቀና አስተሳሰብ እንዳለው ሰው ልሁን ብየ "አይ! አይደለህም ማን ነው ያለው አረ በፍፁም አይደለህም" አልኩትኝ። "አመሰግናለሁኝ ፤ ሰዎች ባላዩት አንግል ማየቴ እውን እብድ ያስብለኛል¿!”
"አይ አያስብልህም" መለስኩለት። <W> ፊደልን እጁን ዘርግቶ ከፃፈ በኋላ ቀና አለ እና "ይሄ ምንድን ነው?"አለኝ። ከእርሱ ጋር አስፈላጊ ነው ብየ ከማስበው በላይ ማውራቴ ሼም እየያዘኝ"የእንግሊዘኛዋ <w> ፊደል ናት" አልኩትኝ። "አንተ ያየሀው <W> ፊደልን ብቻ ነው ምክንያቱም እየፈረድክ ያለሀው በሚታይህ ልክ ብቻ ስለሆነ። እጄን ገልብጬ ባሳይህ እምታየው <M> ፊደልን ነው። እጄን እንዲህ ወደግራ ዘንበል ባደርገው እምታየው የዐረብኛውን(arabic numerals) ሶስት ቁጥር ነው። ወደቀኜ ዘንበል ሳድ ገው ደግሞ የኢንግሊዘኛዋን <E> ፊደል ታያለህ" የሚለውን ገራሚ እይታውን አካፍሎኝ ሲያበቃ "የትኛውም ሰው ባየበት አቅጣጫ እኔ አለማየቴ እብድ ሊያስብለኝ አይገባም" ብሎኝ ሳይሰናበተኝ ሄደ።

አው ምን ለማለት ነው ትምህርት ሚኒስትር ሆይ ፈተና በሚታረምልን ግዜ ስህተት ብላችሁ ከመቀነሳችሁ በስተፊት ቀደም ብላችሁ
1ኛ በተፈታኙ ተማሪ እይታ እዩት
2ኛ በትምህርት ሚኒስትሩ እይታ እዩት
3ኛ በሌሎች ተፈታኞች እይታ እዩት

እንደዚህ አይታችሁት ልክ ባይመጣ እንኳን ቢያንስ ተስፋ እንዲኖረው የሙያ እሚማርበት ውጤት ስጡት። በእናንተ እይታ እንጂ ሰነፍ የሆነው በራሱ እይታ ጎበዝ ነውና።

እኔ አላልኩኝምስ ግን ኡነቴን አይደል

https://t.me/asdajlahh
ልጅ ሳለን አፍሪካ ቲቪ ላይ ከልጆች ዐለም ፕሮግራም ላይ ዐረብኛን ለልጆች እሚለውን መሰናዶ አዘጋጅቶ ያቀርብልን የነበረው ኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስ ከፍተኛ የሆነ የካንሰር ኬዝ አጋጥሞታል የሚል ዜና አየሁኝ። አላህ ያሽረው ዘንድ ዱዐእ አድርጉለት። እኛን በልጅነታችን እንዳስደሰተን አላህ ልጆቹን ለእርሱ ዐፍያ በመስጠት ያስደስታቸው።
ኡስታዝ መህሙድ ዩኑስ ከልጅነቱ ጀምሮ በዲን ኺድማ ላይ የኖረ ሲሆን ከ1985-1988 ዐ.ል በመርከዝ አል-አንሷር ከኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና ኡስታዝ ኑረዲን ቃሲም ጋር አብረው ቁርኣን የሀፈዙ ሲሆን በአፍሪካ ቲቪ የልጆች ፕሮግራም ላይ ረዥም ዓመታት ዐረብኛ ቋንቋን በማስተካከል እና ልጆችን ሲያስተምር ቆይቷል፡፡

በርካታ ዲናዊ ሥራዎችን በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና መስጂዶች ሲደራ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ክሪቲካል የጉበት ካንሰር በሽታ አስጊ ደረጃ ላይ ታሞ ይገኛል። ይህ ወንድማችን ቤተሰቦቹና ኢትዮጠቢብ ሆስፒታል አስፈላጊውን ህክምና እና እገዛ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ህመሙ ከሀገር ዉስጥ ህክምና አቅም በላይ በመሆኑ ወደ ዉጭ ሄዶ መታከም ይገባል ተብሎ በሀኪሞች ተነግሮታል። የአራት ልጆች አባት የሆነው ኡስታዝ የገንዘብ አቅሙ ይህን ስለ ማይፈቅድለት ሁላችንም ህይወት የማዳን የህከምና ወጪ እርዳታ በማድረግ ለኡማው ሲያበረክት የቆየውን ኺድማ ለማስቀጠል አሏህ ዐፊያውን እንዲመልስለት ዱዓእ በማድረግ እጃችን በመዘርጋት መህሙድ ዩኑስን እንታደግ!

የቤተሰብ ሂሳብ ቁጥር፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:1000445523899
ሼኽ አብዱለጢፍ ሐሰን
ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ: 1000052874452

የቤተሰብ ስልክ ቁጥር፡
+251911372344/
0922987730
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 11 #ሙሐረም 1445 ሂ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቱርክ ምስራቃዊ ፖሎ እምትባል አከባቢ ላይ ከዒድ ሰላት አለምንም ምክንያት የቀረ ሰው የሚስተናገድበት ባህል ነው።

ጦለሀ