ASD AJ LAH
755 subscribers
1.73K photos
194 videos
3 files
487 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ቀብርህ ላይ እንዲህ ህዝብ ተሰብስቦ ዱዐእ እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ…

እባክህን ለኔም ንገረኝ እኔም አላወቅኩም


ወንድም ሁሴን አበጋዝን አላህ በጀነት ያቀማጥለው ዘንድ በዱዐችሁ አትርሱት

https://t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 28 #ዙልሒጃ 1444 ሂ
ASD AJ LAH
ቀብርህ ላይ እንዲህ ህዝብ ተሰብስቦ ዱዐእ እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ… እባክህን ለኔም ንገረኝ እኔም አላወቅኩም ወንድም ሁሴን አበጋዝን አላህ በጀነት ያቀማጥለው ዘንድ በዱዐችሁ አትርሱት https://t.me/asdajlahh
በጀሊሉ ይሁንብኝ፥ ጀግናው ሁሴን አበጋዝ እኮ በሰላማዊ ትግሉ ወቅት ዱንያ ላይ እንደ እንግዳ የኖረ…ለሙስሊሙ ኡማ የታገለ…በትግል ሂደቱም እግሮቹን፣ እጆቹን፣ ጆሮዎቹን፣ ምላሱን እንዲያጣ ተደርጎ ተደብድቦ የአፍሪካ መናገሻ ከሆነችው አዲስ አበባ-ሜክስኮ ላይ የተጣለ፤ ህክምና የማገኘት መብቱ የተነፈገ "ዱንያ ላይ ሲኖር እምብዛም ያልታወቀ የሞቱ ሀዘን ግን አለምን ያጥለቀለቀ" የውብ ስብእና ባለቤት ነው።

© Ahmed Omer
የቂያማ ቀን የሚጥህን መፅሃፍ ደራሲ እንተው ነህ። መልካም ይሆንልህ ዘንድ በቻልከው አቅም ሰናይን ተግብር
ASD AJ LAH
​​አንዳንዴ… አንዳንዴ ወንጀል ሠርቼ እፀፀታለሁ። «ጌታዬ ሆይ ሁለተኛ አልመለሰበትም፡፡»እላለሁኝ፡፡ ተመልሼ ያንኑ ወንጀል እሠራለሁ። ተፀፅቼ ጌታዬ ሆይ! አልመለስበትም!እላለሁኝ። ለሦስተኛም አራተኛም ጊዜ እንዲሁ፡፡ ከዚያ ኋላ ተውባ ማድረጉ ይከብደኛል፡፡ ለምን ስል በራሴ ላይ እምነት ስላጣሁኝ ነው፡፡ ዳግም ተመልሼ ተውባህ አድርጌያለሁ ለማለት አፍራለሁኝ፡፡ አልፀናበትምና፡፡ በዚህ የተነሳ በእኔ እና…
አንዳንዴ…
አንዳንዴ ልባችሁ ያን ጉዳይ በደንብ እያሻው ግን ያለማግኘቱ ጉዳይ ያስጨንቃችኋል አይደል?  ያ…ለሰው ለመንገር የሚከብዳችሁ ነገር በተደጋጋሚ በሀሳባችሁ እየመጣ ያስቸግራችኋል አይደል? ሽሽግ ድብቅ ያደረጋችሁት ምሥጢር ክንክን ያደርጋችኋል አይደል? ውስጥ ውስጡን በልቶ ያደማችሁ ነገር አለ አይደል? ልባችሁን ናፍቆት… ትዝታ…ስሜት አልባ መሆን…ወዘተ ይሰማዋል አይደል? የሚያስጨንቃችሁ የሚያሳቅቃችሁ ሀሳብ አለ አይደል? አልቅሼ ብሶቴን ላውጣው ብላችሁ ግን እንባችሁ መድረቁ ሳያንስ ማልቀስ ማንባታችሁ ያሳፍራችኋል አይደል?  በቃላት ለመግለፅ፣ በዝምታ ለማለፍ የሚከብዳችሁ ህመም ደስታ በመኖሩ ሰዎች ምንም ሳትሉ እንዲረዷችሁ ትፈልጋላችሁ አይደል?ይህ ሁሉ አልፎ ከሰው ደብቃችሁ ከአላህ ጋር የምትንኮሻኮሹት ጉዳይ አላችሁ አይደል? ያጋጥማልስ ለሁሉም «አብሽሩለግልፁም ለድብቁም ጉዳያችሁ አላህ ያግዛችሁ! አብሽሩ ምንም ቢሆን ምን… አላህ አለን። አብሽሩ!

ሀሳቡ የአቡ ሱፍያን ነውስ
https://t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 29 #ዙልሂጃ 1444 ሂ
ለነኚህ መሳጆዶች ክብር ሲባል ስድስቱን ወንድሞቻችንን ከቀበርን እኮ ስድስት ሳምንታት ተቆጠሩ

አላህ ሆይ በእዝነትህ እየን
ፍራቻ ከመውደቅ በላይ ህልሞችን ይገድላል እና ሁሌም ቢሆን ትልቁ ውድቀትህ ማለት መሞከር መተውህ መሆኑን አስታውስ!

t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 30 #ዙልሒጃ 1444 ሂ
ነቢያችን ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም እና ጓዶቻቸው በመካ ሙሽሪኮች ይደርስባቸውን የነበረውን በደል ሽሽት  ከመካ ወደ የስሪብ(መዲነቱል ሙነወራ) የተደረገው ስደት ወይም ሂጅራ ሙስሊም አማኞች ዘንድ ቦታ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መሀል ይጠቀሳል። ይህ ስደት(ሂጅራ) የተደረገው እ.ኤ.አ በ622 ነብይ ተደርገው በተላኩ በ14 ዓመት ልክ የዛሬ 1445 ዓመት ነበር።
ሁለተኛው ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ሰሀቦች ካማከረ ኋላ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት ይህ ቀን ሙስሊሙ ዐለም ዘንድ መቁጠሪያ ካላንደር ተደርጎ ተይዞ ይገኛል።
ዛሬ ምሽትም 1445አመተ ሂጅራ መግባቱን ለማሳወቅ በመካ የሚገኘው Fairmont Makkah Clock Royal Tower በምታዩት መልኩ በርቷል።

https://t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1 #ሙሐረም 1444 ሂ
ASD AJ LAH
ግንቦት ላይ ጥናት የጀመርን ተማሪዎች ያለንበት ሁኔታ J4F
አንድ ሰውየ ናቸው አሉ ወደ ልኳንዳ ገቡ እና "ልጄ ሆይ እስኪ አንድ ኪሎ ስጋ ስጠኝ" አሉት "መምህር ሆይ ተቀመጡ" አለ ስጋ ሻጩ… ከዚያም ሰራተኛ ጠራላቸው እና "ሁለት ኪሎ ስጋ መዝንላቸው ብር እንዳትቀበላቸው የመኪናውን ቁልፍም ውሰድ እና መምህሩን እሚፈልጉበት ድረስ አድርሳቸው" አለው
ሰውየውም "ለምንድን ነው ግን ይህ ሁሉ እንክብካቤ?" ብለው ጠየቁት
ስጋ ሻጩም " መምህር ሆይ ረሱኝ እንዴ…እኔ እኮ እርሶ ዘንድ ሰነፍ ሆነው ከሚማሩት ተማሪዎች ውስጥ ነበርኩኝ… የሆነ ቀን ወላጅ ወይም አሳዳጊ ሳታመጣ ክፍል አትገባም ብለውኝ ትምህርት አቋረጥኩኝ ከትንሽ ግዜ ኋላ ልኳንዳ እሚሰሩ ሰዎች ጋር ተቀጥሬ ተማርኩኝ እና የራሴን ልኳንዳ ከፈትኩኝ አሁን አልሀምዱሊላህ ሶስት ልኳንዳዎች ፣ የፍየል እና የበግ ማርቢያ አለኝ"
ሰውየውም " አው ወላሂ አስታወስኩህ…ምነው ያን ቀን አሯሩጬህ አብሬህ ልካንዳ በገባሁ" አሉት ይባላል


ምን ለማለት ነው
አሁን ላይ ፈተና እየጠበቃችሁ ያላችሁ የ12ኛ ክፍል የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ፣ የሪሜድያል ፈተና እና ውጤት እየጠቃችሁ ያላችሁ ተማሪዎች እና  ሌሎቻችሁም ያጠናችሁትን ይዛችሁ በአላህ ተመክታችሁ ወደፈተና መግባት እና የቻላችሁት መስራት እና አላህ ያለውን መጠበቅ ነው

ህይወት ሌላም በር እንዳላት እወቁ ልላችሁ ነውስ¡

https://t.me/asdajlahh
ASD AJ LAH
Photo
አንድ ትምህርት ቤት በየአመቱ ለትምህርት ቤቱ ትናንሽ ተማሪዎች የመዝናኛ ዝግጅት ያሰናዳል እናም በአንደኛው አመት የዚህ መኪና ሹፌር በየአመቱ በሚያልፍበት መንገድ ላይ ቁመቱ ወደላይ ሶስት ሜትር እሚጠጋ ዋሻ አለ ሹፌሩም የባሱ ቁመት exactly 3 ሜትር ስለነበር ሁሌም በዛች ዋሻ ያልፍ ነበር። ነገር ግን የዘንድሮው አመት ጉዞ ላይ ባሱ ከዋሻው የላይኛው ክፍል ጋር ተነካክቶ አልሄድም ብሎ መሀል ላይ ቀረ እና ተማሪዎች ፍራቻ ውስጥ ከተተ። የባሱም ሹፌር ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ ራሱን ይጠይቅ ጀመር" እስከዛሬ ድረስ ሁሉም አመት ነበር ያለምንም ችግረ አልፍ የነበረው? አሁን መወን ተገኝቶ ነው አልሄድም ያለኝ? በዚያ ቡል ሲያልፍ የነበረ መንገደኛም " መንገዱ እድሳት ተደርጎለተወ ከታች አዲስ የአስፓልት ንጣፍ ተደርጎለት ከፍ ስላለ ነው" በማለት መልስ ሰጠው። ይሀም መንገደኛ በያዘው መኪና ባሱን በገመድ በማሰር ስቦ ለማውጣት ቢሞክርም በባሱ ጣራ እና የዋሻው የላይኛው ክፍል መተሻሻት ምክንያት ገመዱ እየተበጠሰ ተቸገረ። ከፊሉ ሌላ ጠንካራ መኪና መጥቶ እንዲስበው ከፊሉ የአስፓልቱ ንጣፍ እንዲቦረቦር ሀሳብ አቀረቡ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ሀሳብ መሐል አንድ ልጅ ከባሱ ወረደ እና እንዲህ አለ"መፍትሔ አለኝ🙋" ያው የችግር ሰዐት ነው እና ሊያዳምጡት ተገደዱ እንዲህም አለ" የዛሬ አመት ኮርስ የሰጠን መምህር " እምናስበው ህልም ልናሳካ ዘንድ ከሰው ዘንድ እንድንጠባረር ያደረገንን ከውስጣችን ያለውን ኩራት ፣ ጉራ ፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት እና ስግብግበነት ልናወጣ ግድ ይለናል። ያኔ የነፍሳችን አቋም ወደተፈጠርንበት ትክክለኛ አቋም ይመለሳል። ከዚያም ከዱንያ ጭንቀት ጥበት ማለፍ እንችላለን።" እናም ይህን ንግግር ከባሱ ጋር ብናገናኘው እና ከባሱ ጎማዎች ውስጥ የተወሰነ አየር ብንቀንስ ከነበረበት ከፍታ ዝቅ ማለት ከዋሻው የላይኛው አካል ጋር ያለውን መተሻሸት ስለሚያስቀር ዋሻውን በሰላም ማለፍ እንችላለን።" በልጁ ድንቅ ሀሳብ ሁሉም በመገረም ልጁ እንዳለው ከጎማዎች አየር በመቀነስ ሁሉም ሰው በሰላም አለፈ።

ምን ለማለት ነው
ችግሮችህ ጫናቸው አንተው ላይ ነው። ችግሮችሽ ጫናቸው አንቺው ላይ ነው። ችግሮቻችን ጫናቸው እኛው ላይ ነው። ጦሳቸው ለአንተ ለአንቺ ለእኛ ነው። ግድ የለንም ውስጣችን ያለውን ኩራት እና ጉራ እናውጣው። ከዱንያ በሰላም ለማለፍ ስንል የተነፋፋችውን ሩሐችንን እናተንፍስ።

መልካም ውሎ

https://t.me/asdajlahh
ኢማሙ ሻፊዒ እንዲህ ብለዋል አሉ:-

" ሀቅን የት እንዳለች ማወቅ ከፈለግክ የጠላቶች ቀስትን አቅጣጫ ወዴት እንደሆነች ተመልከት"

ሁዳ መልቲሚድያ
ASD AJ LAH
ነቢያችን ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም እና ጓዶቻቸው በመካ ሙሽሪኮች ይደርስባቸውን የነበረውን በደል ሽሽት  ከመካ ወደ የስሪብ(መዲነቱል ሙነወራ) የተደረገው ስደት ወይም ሂጅራ ሙስሊም አማኞች ዘንድ ቦታ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መሀል ይጠቀሳል። ይህ ስደት(ሂጅራ) የተደረገው እ.ኤ.አ በ622 ነብይ ተደርገው በተላኩ በ14 ዓመት ልክ የዛሬ 1445 ዓመት ነበር። ሁለተኛው ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ሰሀቦች ካማከረ ኋላ…
ማታ ባጋራዋችሁ መረጃ ላይ ማስተካከያ!

ማስታወሻ
=======
ነቢያዊው ሂጅራ የኢስላማዊው ቀን መቁጠሪያ በሚጀምርበት ወርሀ ሙሐር‐ረም ላይ አልተከሰተም!
ሂጅራው የሆነው በወርሀ ረቢዕ አል‐አወል ነው። ነገርግን የሂጅራው የቀን አቆጣጠር የዓመት መጀመሪያው የተከበረው የሙሐር‐ረም ወር እንዲሆን ተደርጓል። ይኸውም ሰዎች ከሐጅ ጉዞ ተመልሰው በቀዬኣቸው ተረጋግተው ኑሮ የሚጀምሩት በሙሐረም ስለሆነ ነው።
የሂጅራ አቆጣጠርን አሁን ባለበት ሁኔታ እንዲሆን ያደረጉት ኸሊፋው ሰይድ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ናቸው። ያው ከሌሎች ከሶሓቦች ጋር ተማክረው ማለት ነው።

Tofiq bahru
እየተጠቀማችሁ!

ኢትዮ ቴሌኮም ለአንድ ሳምንት የሚቆይ  የ1GB Data ፣ 25 ደቂቃ Voice እና 50 Text እንዲሁም በቴሌብር ሱፐርአፕ ተጨማሪ ተመሳሳይ ስጦታ ለሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ አበርክቷል።

ሳፋሪኮምም በቅርቡ እንጠብቃለን ለኛ ስትሉ ተፎካከሩ🙏