Arada subcity communication office
597 subscribers
2.79K photos
109 videos
1 file
3.43K links
ወቅታዊ መረጃዎችን ከኛ ይጋሩ
Download Telegram
የመልካም አስተዳደር ጥያቄያቸው ምላሽ እንዳገኘ ነዋሪዎች ገለፁ።

አራዳ ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ ስምንቱም ወረዳዎች  የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሆነው የቆዩ የህብረተሰቡ ጥያቄዎች በተቀናጀና በተፋጠነ አሠራር ዘላቂ መፍትሔ ማግኘታቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ የመልካም አስተዳደር ቅሬታ አቤቱታ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ደስታ እንደገለጹት “የተፈቱት ዘርፈ ብዙ ችግሮች የአካባቢውን ማህበረሰብ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ተጠቃሚ ያደረጉና የኑሮ ጫናን ያቃለሉ ናቸው” ብለዋል።

በጥያቄያቸው መሠረት የመሥሪያ ቦታ ተመቻችቶላቸው በከተማ ግብርና የእንቁላል ዶሮ እርባታ የተሰማሩት የአረብ ሀገር ተመላሽ ወ/ሮ ወደኒ “በወረዳ 6 የመስሪያ ቦታ ተመቻችቶልን ወደ ሥራ ገብተናል ብለው አሁን ላይ ሰፊ ምርት በማምረት የገበያ ትስስር ተፈጥሮልናል” በማለት ምስጋና አቅርበዋል።

በዳግማዊ ምኒልክ ቅድመ-አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ የሆነ የተሟላ የመሠረተ-ልማት ግንባታ መከናወኑን የትምህርት ቤቱ መምህራን ገልፀዋል።

በወረዳ 9፣ 4ኪሎ ታክሲ ተርሚናል ቀደም ሲል አጥርና መብራት ባለመኖሩ ለፀጥታ ስጋት የነበረው የታክሲ ተርሚናል ችግሩ ተቀርፎ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአካባቢው ተራ አስከባሪዎች የገለጹ ሲሆን በወረዳ 4 ደግሞ የፍሳሽ ቱቦ መገንባቱና የፖሊስ ጣቢያ ጥያቄ መመለሱ ምቹና ጤናማ አካባቢ መፍጠሩን ነዋሪዎች አስረድተዋል።
የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር በ29 ቀናት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት የ90 ቀናት እቅዱን በውጤት ማጠናቀቅ እንደሚችል አመላካች መሆናቸውን ገመገመ።

አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር ለሁሉም ተግባራት እኩል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀው፣ የገበያ ምርት አቅርቦት፣ መደበኛ ገቢ ማሰባሰብ፣ የንግድ ተቋማት ላይ ውጤት አምጪ ቁጥጥር ማድረግና ችግሮችን መፍታት፣ የምሽት ንግድ ስራዎች ላይ ክትትል ማድረግ፣ ስራ እድል ፈጠራንና የኢንሺቴቲቭ ስራዎችን ሁሉም ወረዳ መጀመር ከነገ ጀምሮ በትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተግባራት አፈጻጸም በየጊዜው መሻሻል የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት የአራዳ ክ/ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ የኋላሸት በቀለ የውጤት መሻሻል ብቻ ሳይሆን እምርታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ገልጸው፣ ሁሉንም ውጤቶች ከመቶ በላይ መፈጸም ያስፈልጋል ብለዋል።

የ90 ቀናት እቅድ የ29 ቀናት የየወረዳውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የክ/ከተማው ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለምገና ደረጀ፣ መከናወን አለባቸው ተብለው በእቅድ የተያዙ ተግባራት በተለይም የገቢ አሰባሰብ፣ የገበያ አቅርቦትን ማሳደግና የኑሮ ውድነትን ማሻሻል፣ የንግድ ተቋማት የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር፣ ለተኪ ምርት አምራቾች ብድር አቅርቦትና ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረግ፣ የስራ እድል ፈጠራና ከተማ ግብርና ስራዎች፣ የከተማ ግብርና ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎች አፈጻጸም፣ የሰብአዊ ድጋፍ ግብአትን በራስ አቅም ማሰባሰብ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የት/ትና ጤና ስራዎች፣ የመሰረተ ልማትና ቅንጅታዊ ስራዎች እና ሌሎችም በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በየወረዳው ያላቸውን አፈጻጸም ሁኔታ በዝርዝር አቅርበዋል።