Amhara Prosperity Party/APP
1.93K subscribers
1.43K photos
14 videos
395 links
Download Telegram
በአማራ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አሰተባባሪነት "የተመጣጠነ ምግብ እመገባለሁ ሁሉንም ከደጀ አመርታለሁ!" ክልል አቀፍ የሌማት ቱርፋት የሴቶች ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በሞጣ ከተማ ተካሄደ!
የፌዴራል፣ የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ክልል አቀፍ የሌማት ቱርፋት የሴቶች ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ የሞጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዳሙ መኮነን ጥንታዊና የልማት ኮሪደር ወደሆነችው ሞጣ ከተማ እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ መንበሩ ዘውዴ ጠግቦ መመገብ መቀንጨርን አያስቀርም ነገር ግን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ከዘርፈ ብዙ በሽታዎች ልንድን ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የሞጣና ሁለት እጁነሴ ወረዳዎች ላይ የታዩ የሌማት ትሩፋት ውጤቶችም በሌሎች የዞኑ ወረዳዎችና ከተሞች ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲተገበርም በዕቅድ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ሊግ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ኢሌኒ አባይ በክልል ደረጃ በአረንጓዴ ልማት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚን አጠናክሮ ለማስቀጠል ለኑሮ ምቹ ክልልን ለመፍጠር እና ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት መሰረት ለመጣል ትልልቅ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የሴቶች ሊግ አጋር አካላትን በማስተባበር የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ውጤታማ እንዲሆን በንቅናቄ በመምራት በኩል ትልቁን ድርሻ ማበርከት ችለናል ያሉት ወ/ሮ ኢሌኒ አባይ ከአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ልምድ በመውሰድ ሴቶች በምግብ እራስን ከመቻል ባለፈ ለገብያ ፍጆታ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር የሌማት ትሩፋት ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ተግባር መገባቱን አሳውቀዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማና ሁለት እጁነሴ ወረዳ ያየነው የሌማት ትሩፋት ውጤቶች በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች እንደየ አግሮኢኮሎጂው አቅዶ በመስራት የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት በኃላፊነት መስራት እንደሚገባ ገልፀው ለፕሮግራሙ ስኬት ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየ በመልዕክታቸው የሞጣ ከተማ ህዝብ ተንከባክቦ ይዞት የቆየውን አብሮነታችን ላይ አደጋ በመፍጠር ለውጡን ለማደናቀፍ አልመው የሚሰሩ የጥፋት ኃይሎች እኩይ አላማ በመታገል ሰላሙን ያረጋገጠ ሰላም ወዳድ ህዝብ ነው ብለዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ በምግብ እራስን ለመቻል እየተሰራ ያለው ስራ በውጤት መታገዙን የጠቀሱት ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ በብልፅግና የሚመራው መንግስት በሌማት ፕሮግራም ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ የአመጋገብ ስርዓትን ለማሻሻል የተቀረፀ ሰው ተኮር ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል። ሴቶችና የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ያላቸው ትስስር ጥብቅ ሊሆን ይገባልም ብለዋል። ለዚህ ፕሮግራም ስኬትም የሚቻላቸውን ሁሉ ማበርከት እንዳለባቸው ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ አሳስበዋል።
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤና የብልጽግና ሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ የሌማት ትሩፋት አስተሳሰብ ዋነኛ ግቡ በየደረጃው የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ በምግብ እህል ራሱን ችሎ ለሌላው የሚተርፍበት፣ የዕለት ምግቡንም በልቶ ከማደር ባሻገር የተመጣጠነ ምግብ ያሟላ የሚሆንበት ዕድል መፍጠር ነው ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ አክለው እንደገለፁት ይህ መርሀ ግብር የብልጽግና ሴቶች ሊግ አመራርና አባላት እንዲሁም መላ ሴቶች ምን ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባና እያንዳንዱን የፓርቲ አባላት አስተሳሰብ ከሌማት ትሩፋት ጋር እንዴት አስተሳስረው መፈፀም እንዳለባቸው ለማመላከት የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። ለሌማት መርሀ ግብር ስኬታማነትም በየደረጃቸው የሚገኙ የብልጽግና ሴቶች ሊግ አደረጃጀት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"