ሐዋርያዊ መልሶች
61.4K subscribers
165 photos
140 videos
7 files
581 links
“እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል?“
ነህምያ 6: 3
YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ እነዚህን ሰዎች ፈራዋቸው.. ቀስ ብለው ወንጌል ስለ አክሊል ብቻ ነው እንዳይሉ.. ሎል
የሆኑ “ካህናት” ተሰብስበው.. “ብጹእ አቡነ ገብርኤል ከተነኩብን መስዋእትነት እንከፍላለን” ሲሉ ስሰማ ሽምቅቅ ነው ያልኩላችሁ ወንድም እና እህቶቼ.. ጠላታችሁ እንዲህ አይሸማቀቅ..
ዮው እንምረጥና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን እንግባ ኧረ..

የአሁኑ መጽሐፍ ከብሉይ ይሁን ወይስ ከሐዲስ..??
ወንድማችን በጋሻው ሰሞኑን ደግሞ ተነስቶበታል.. እስቲ ደግሞ እንደፈረደብኝ ትንሽ ቦታ ቦታ ላስይዘው😆😆 ሎል

ለ3 ደቂቃ የሚቆይ ፖስት
ጭራሽ በፕሮቴስታንቶች(ሪፎርምድ) ውስጥ እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን ሲፈጥር ለገሃነም ወስኖ የፈጠራቸው እንዳሉ እንደሚያስተምሩስ ያውቁ ኖሯል..??


https://vm.tiktok.com/ZMBTYt6Ay/
ክርስቲያኖች ያለ ኢየሱስ ምንም ልታደርጉ አትችሉም

ፕሮቴስታንቶችም በእውነት ያለ “ዮኒ ማኛ” ምንም ልታደርጉ አትችሉም.. ሎል🤭🤭
ጌታ ኢየሱስ ድካማችንን ያውቀዋል ሁኔታችንን ይረዳዋል ምናምን.. ማለትም በወደቅን ቁጥር በቁጣ እየተንበለበለ ለማባረር የሚቸኩል አይደለም..

እንዲያውም ድካማችንን አይቶ ይራራልናል.. መጽሐፍም እንደተናገረ: “በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንም” ስለዚህም አባ ጊዮርጊስም እንዳለው: “የተራበ ሆድ ለምግብ እንደሚቸኩል ክርስቶስም ይቅር ለማለት ይቸኩላል” ከዛም ደግሞ ያግዘናልም..

ወደዚህ ጌታ በመጠጋት ከብዙ ነገር ልንርቅ ይገባል.. አልያ ግን ይኸው ጌታ ከአሕዛብ ጋር ደግሞ ሊፈርድብን ይችላል..

ጌታ ግን ሁሌም በምህረቱ ያስበን..

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄንን ቪዲዮ ያየች አንድ እህቴ ምን አለችኝ:

“ቅዱስ ጴጥሮስ ቢኖርና እንዲህ ሲል ቢሰማው ግን ጆሮውን አይሰይፈውም ትላለህ..??”

😁😁
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🤭🤭

ለ7 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ ብቻ የሚቆይ ፖስት
“በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና።”
[1ኛ ቆሮንቶስ 2: 2]


በነገራችን ላይ አገልግሎት ማለት አገልጋዩ ያለውን እውቀት ለማሳየት ከሰሚዎቹ የመረዳት አቅም የራቀ ነገርን መናገር ማለት አይደለም.. እንዲያ ቢደረግ ማንም አይጠቀምም.. አስባችሁታል ቅዱስ ጳውሎስ በእውቀቱ ደረጃ ብቻ የሚሰብክ ቢሆን አልቆልን ነበር😁😁 ስለዛ እንደቦታው ነው መሆን ያለብን አለበለዚያ ብቻችንን ለንፋስ የምናወራ እንሆናለን

ጌታችንንም ካያችሁት ሲያስተምር በሰዎቹ ዙሪያ ያለውን እያጣቀሰ እነርሱ በሚገባቸው መልኩ ነበር.. የተወሳሰበ ነገር አታዩም..

ሰሚአኑ እየበሰለ ሲሄድ አልያም በበሰሉት ዘንድ ደግሞ ተለቅ እና ረቀቅ ስላለው ነገር ይወራል ነው..

@Apostolic_Answers
እኔኮ ተስፋ የቆረጥኩት.. የቦሌ መድኃኔዓለም አውደ ምህረት ላይ ከኔ ቀድሞ ደምረው ሲወጣ ነው😭😭
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ እነዚህ ሰዎች በአክሊለ እንዳያብዱ🙄🙄 በየሰዓቱ አካሉ..?? ሯ!
“የምንበላው ሥጋና ደም የማርያም ነው” አሉ አንዱ አባት.. ከዛ ጴንጤዎች ኡኡ እያሉ ነው.. እሺ አሁን እናንተ ኡኡ ያስባላችሁ ያ ሥጋና ደም የኢየሱስ ነው ለማለት ነው..?? እሱን ደግሞ አታምኑም ቅዱስ ቁርባን ለእናንተ ምሳሌ ብቻ ነው😁😁

ለማንኛውም ያ ሥጋና ደም የመለኮት ሥጋና ደም መለኮት የራሱ አድርጎታል..

የማርያም ሥጋና ደም ሲጀምር ያድናልም አንልም.. የሚያድነው የመለኮት ሥጋና ደም ነው..

እኛ ቢያንስ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጳጳስን ሳይቀር እንመዝናለን.. ፕሮቴስታንቶች ግን በቃ እንደ ግሌ መረዳት እንደሆነ ልብ ይለዋል

@Apostolic_Answers
ያዝ እንግዲህ.. ባለፈው ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ነው በሚለው ላይ አሁን ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ላይ ልንሄድባቸው ነው መሰለኝ ሎል

https://vm.tiktok.com/ZMBo9YANp/

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቦሌ መድኃኔዓለም ሲከነክነኝ ጭራሽ የልደታ አውደ ምህረት ላይም ቀደምከኝ..??😭😭

እንኳን አደረሳችሁ ለማንኛውም ለወላዲተ አምላክ የልደት ቀን
ትናንት በሰራሁት ቪዲዮ ላይ አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ሲያለቅሱ አየሁ እና በተለይ “ሉተራኖች” እኛኮ በቅዱስ ቁርባን እናምናለን እና ጨፍልቀህ ፕሮቴስታንት ያልከን በጥላቻ ነው እያሉ ነው😁😁

ሲጀመር እዛው ቪዲዮው ላይ “በተለይ ጴንጤ” ብዬ ለይቻለሁ.. ስለዛ እናቱ ጥላው እንደሄደችበት ሕጻን የማልቀሻ ምክንያት ፈልጋችሁ ነው ምትለቅሱት ማለት ነው.. ምክንያቱም እንዳልኩትም እዛው ቪዲዮ ላይ “በተለይ ጴንጤ” ብዬ ለይቻለሁ😁😁

ሲቀጥል ደግሞ የእናንተን ስም እየለየን የግድ መጥራት አይጠበቅብንም.. ሃገሪቱ ጠቅላላ ከፕሮቴስታንት ውስጥ ጴንጤዎች አይደሉ እንዴ😁😁 በግል ቸርቾች ተጥለቅልቀህ ደግሞ ሌላ ሥራ ይሁንብኝ እንዴ የእናንተ የጥቂቶቹ..??

ለማንኛውም ከጴንጤዎች እና ከፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል የተረዳው ማን ነው በሚለው ልግባ መሰለኝ ሎል😁😁
ፕሮቴስታንቶች ክርስቲያን ናቸው..??

አንድ ወንድም ዛሬ ምን አለኝ:- “በጥንት ቤተ ክርስቲያን በመናፍቃን የተጠመቁትን ዳግም ሳያጠምቁ የተቀበሉ ነበሩ እናም እነዛ መናፍቃን ራሱ ክርስቲያን ካልሆኑ እንዴት ጥምቀታቸው ተቀባይነት ኖረው..?? እንደው ዋናው ነገር የኒቂያውን እምነት ማመን ቢሆን ነው እንጂ..”

አከሲ..?? ሎል

ለምሳሌ አርዮሳውያንን ሳይቀር ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመለሱ በአንድ ወቅት ላይ ዳግም ሳያጠምቁ በቅብአ ሜሮን ይቀበሏቸው ነበር.. ይህ ማለት ግን አርዮሳውያን ክርስቲያኖች ናቸው ማለት ነው..?? ገና ከጅምሩስ የኒቂያውን አንቀጸ ሃይማኖት ስለተቀበሉ ነው ዳግም ያላጠመቋቸው..??😭😭 ወፍ።

ምንም እንኳን አርዮሳውያንን ያለ ዳግም ጥምቀት ቢቀበሏቸውም ግን ደግሞ አባታችን አትናቴዎስ "እኛም ክርስቲያን ነን" የሚሉትን አርዮሳውያንን ምን እንዳላቸው ላሳይህ..??

"ሁላችን በክርስቶስ ክርስቲያኖች ስንባል፤ መርቅያኖስ የምንፍቅና ትምሕርትን አነሳ ተወገዘም፤ መርቅያኖስን ያወገዘውን የተከተለ ክርስቲያን እንደሆነ ሲቀጥል ከመርቅያኖስ ጋር አብሮ የወጡት ግን ክርስቲያን መባላቸው ቀርቷል ይልቁንም መርቅያኖሳዊ(Marcionites) ይባላሉ እንጂ። ልክ እንዲሁ ሌሎች መናፍቃንም ስማቸውን ለተከታዮቻቸው ሰጥተዋል። እንዲሁ እስክንድሮስ(Alexander) አርዮስን ሲያወግዝ ከእስክንድሮስ ጋር የቀሩት በክርስቲያንነታቸው ሲቀጥሉ ከአርዮስ ጋር የተለዩት ግን የጌታችንን ስም ለእኛ በመተው እነሱ አርዮሳውያን(Arians) ይባላሉ"
[Against the Arians: Discourse 1, chap. 1: 3]

ክርስቲያን መባልንና አለመባልን ያገናኘው ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ከመሆን እና ካለመሆን ጋር ነው ብራዘርዬ ሎል

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM