🎓አፓሎሚክስ |Apolomics Apologetical School
2.61K subscribers
64 photos
1 video
3 files
60 links
🎓ጠንካራ እውቀትን ወደሚያገኙበት 🤝 ወደ አፖሎሚክስ የዕቅበተ እምነት ትምህርት ቤት (Apolomics Apologetical School) እንኳን በደህና መጣችሁ።

Youtube
https://youtube.com/@apolomics?si=U0QOf5ldfSqpjLRq

Tiktok
https://www.tiktok.com/@apolomics?_t=ZM-8vtskUjYmNp&_r=1
Download Telegram
🎓አፓሎሚክስ |Apolomics Apologetical School pinned «🥲👩🏻‍🎓👩🏻‍🎓🧑‍🎓🧑‍🎓ምዝገባ ተጠናቋል»
እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰብያ በዓል በሰላም አደረሰቻሁ።

“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።”
  — ማቴዎስ 1፥23
 
"ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
  — ኢሳይያስ 9፥6

💬🗯በሌሎች አማራጮችም ይከታተሉን

✅YouTube Account👇
https://www.youtube.com/channel/UCUSff8njz3qAWtnKPOzR-pQ

🔴Tiktok
https://www.tiktok.com/@apolomics?_r=1

🔲Telegram Channel
@apolomics
🥰12🤝9❤3👍1
🎓አፓሎሚክስ |Apolomics Apologetical School pinned «እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰብያ በዓል በሰላም አደረሰቻሁ። “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።”   — ማቴዎስ 1፥23   "ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥…»
እኔ ግን ተስፋም ይታየኛል። ዛሬም በእውነተኛዎቹ አብያተክርስቲያናት ነፍሶች እየዳኑ ነው። ሐሰተኞች ብቻ ሳይሆኑ፥ ዛሬም ነፍሳቸውን እያማጠኑ በጽድቅ ጎዳና የሚመላለሱ፣ ለመቀደስ የሚፈልጉ ደግሞም የሚተጉ እውነተኞች አሉ። ዛሬም እውነተኛ አብያተክርስቲያናት፣ መሪዎችና አማኞች አሉ! ዛሬም ቤተክርስቲያን አለች! ጨለማው ብቻ ሳይሆን፥ ብርሃኑም ይታየኛል። ከነድካሜ ግን ደግሞ ጌታ በረዳኝ ልክም ብርሃኑ እንዲያሸንፍ ከጌታ እና ከቅዱሳኑ ጋር አብሬ ሰራለሁ!
❤62🔥17👍9✍1
📢 ክለሳ፦ "የመሰረተ ክርስቶስ ኒቅያ ጉባኤ" ያስፈልገናል! - የቀረቡ የመፍትሔ ሐሳቦች።

ዶክተር ሳምሶን እስጢፋኖስ (የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቦርድ ወይም የመአመጉ ምክትል ሰብሳቢ)

፩. የታሪክ ዳራ እና ተቋማዊ ትስስር

🏛 የአናባብቲስት ሴሚናሪ (AMBS) እና የመሰረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ ግንኙነት

በ1986 ዓ.ም. የአሜሪካ ሜኖናይት ጥምረቶች ከጋራ የእምነት መግለጫ ባለፈ ሁለት ጥንታዊ ትምህርት ቤቶችን (Goshen Biblical Seminary እና Mennonite Biblical Seminary) በማዋሃድ የዳግም አጥማቅያን ሜኖናይት መጽሐፍ ቅዱስ ሴሚናሪ (AMBS) መሰረቱ። ይህ ተቋም በMWC "በአለም አቀፍ ደረጃ የሜኖናይት የስነመለኮት ማዕከል" እውቅና ያለው ሲሆን፤ በባለቤትነት በMC USA እና MC Canada ይመራል።

ይህ የድህረ ምረቃ (post graduate) ኮሌጅ በሜኖናይት ስነመለኮትና የጋራ መረዳቶች (Shared Convictions) ላይ ተመስርቶ በኢየሱስን መከተል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣ በመሪነት፥ በሰላምና እርቅ፣ በማህበረሰብ ሰላምና ፍትህ፣ በወንጌል ስርጭትና በሁለንተና አገልግሎት ዘርፎች ትምህርት ይሰጣል። እንደ 2017 ዓ.ም. ሪፖርት 200 የሚጠጉ ተማሪዎችን በአካልና በርቀት ያስተምራል።

የአጋርነት ስምምነት፦ አስቀድሞ ከአስር በላይ መሪዎች በተቋሙ በአካል ተምረው ቢመረቁም፥ ከወጪ መብዛትና ከባህል ግጭት ጋር በተያያዘ ትምህርቱን በሃገር ውስጥ ለመስጠት ተወስኖ በ2011 እና 2014 ዓ.ም. የጋራ የድህረ ምረቃ ስምምነት ተፈረመ።

፪. የአቋም ለውጥ እና ወቅታዊ ተግዳሮቶች

⚠️ የግብረ ሰዶ*ማዊነት አቃፊነት ጉዳይ

በ2014 ዓ.ም. AMBS ግብረ ሰዶ*ማዊነትን አቃፊ መሆኑን በግልጽ አሳወቀ። ይህም ራሳቸውን የገለጹ ግብረ ሰዶ*ማዊ ተማሪዎችና መምህራን እንዲኖሩት አድርጓል።

የMKC ምላሽ፦ ስምምነቱ በተፈረመ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይህ አቋም በመሰማቱ፥ የቤተክርስቲያኗ አመራሮች የሚከተሉትን ጥብቅ መመሪያዎች ሰጥተው ነበር፦

በጋራ ፕሮግራሙ ላይ ከግብረ ሰዶ*ማዊነት ጋር የሚያያዝ ርዕስ እንዳይነሳ።

ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ መምህራን ግብረ ሰዶ*ማውያን እንዳይሆኑ።

በአሁኑ ወቅት የቤተክርስቲያኒቱ የግንኙነት ደንብ አቃፊ ተቋማትን ስለማይፈቅድ፥ ከAMBS ጋር ያለው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። በጥቅምት 2018 ዓ.ም. የመሰረተ ክርስቶስ ስነመለኮት ኮሌጅ ራሱን ችሎ የመጀመሪያዎቹን 110 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች አስመርቋል።

፫. መዋቅራዊ እና አስተምህሮአዊ መመሪያዎች

🛑 የቤተክርስቲያኗ ጽኑ አቋም

መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ30 ዓመታት በፊት ጀምሮ ጋብቻ በተፈጥሮ ወንድና ሴት መካከል የሚደረግ የእድሜ ልክ ትስስር መሆኑንና ግብረ ሰዶ*ማዊነትን እንደማትቀበል በግልጽ አሳውቃለች።

በደንቦቿም የሚከተሉት ጸንተዋል፦

አባልነት (አንቀጽ 2)፦ በተፈጥሮ ወንድና በተፈጥሮ ሴት የሆነ።

ግንኙነት (አንቀጽ 6)፦ ከመሰረተ እምነቷ ጋር ከሚስማሙ የሜኖናይት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ብቻ።

ጋብቻ፦ በተፈጥሮ ወንድና በተፈጥሮ ሴት መካከል።

፬. የአመራር እና የግንኙነት ግምገማ

የነዶ/ር ስዩም ወገን ብርታትና ውሱንነት፦

ብርታት፦ የግብረ ሰዶ*ማዊነትን አደጋ ቀድሞ ማየት፥ ለመአመጉና ለማህበረሰቡ አደጋውን ለማሳየት መጨከንና ግንኙነቶችን በማስረጃ መሞገት።

ውሱንነት፦ በራሳቸው የጊዜ ሰሌዳ ውሳኔ ባለመሰጠቱ መቆጣት፥ ርዕሱን ወደ ሚዲያ በመውሰድ የመሪዎችን ስም ማጠልሸትና ስልጣንን የሚያንቋሽሹ ቃላት መጠቀም።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ብርታትና ውሱንነት፦

ብርታት፦ ሴሚናሪው ራሱን እንዲችል መጣር፥ በልበሰፊነት የታየ ትዕግስትና አቋምን ለምዕመናን በግልጽ ማሳወቅ።

ውሱንነት፦ ለዋናው ርዕስ አናሳ ስፍራ መስጠት፤ የአባላትን ጥያቄ ከአጥቢያ አይለፍ በሚል መዝጋትና በአቃፊ ተቋማት ተገኝቶ ይቅርታ ለመጠየቅ ፍቃደኛ አለመሆን።

፭. ስልታዊ ስህተቶች እና ትችቶች

ባለፉት ዓመታት የተፈጸሙ ዋና ዋና ግድፈቶች፦

የMWC ግንኙነት፦ MWC ግብረ ሰዶ*ማዊነትን እንደ ሃጢአት እንደማይፈርጅ እያወቁ አባልነትን መቀጠል።

የAMBS ስምምነት፦ ተቋሙ አቃፊ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ ግንኙነቱን ወዲያውኑ አለማቋረጥ።

የደንብ ጥሰት፦ መሪዎች አቃፊ በሆኑ የአሜሪካና ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት በመገኘት ድጋፍ ማሰባሰባቸው።

የፕሮጀክት ትስስር፦ አቃፊ ከሆነው MC USA የልማት እጅ (MMN) ጋር የስራ ግንኙነት መፍጠር።

፮. የቀረቡ የመፍትሔ ሐሳቦች (Recommendations)

የጋራ ጉባኤ፦ በመገናኛ ብዙሃን የሚደረግ መግለጫ ቆሞ፥ የሚመለከታቸውን የያዘ "የመሰረተ ክርስቶስ ኒቅያ ጉባኤ" ተጠርቶ ውይይት ይደረግ።

ይቅርታ፦ በየዘመናቱና በየደረጃው በርዕሱ ለተሰሩ ስህተቶች ሃላፊነት በመውሰድ በይቅርታ ይቋጭ።

መውጣት፦ ከመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 6 ጋር ስለሚጋጭ፥ ቤተክርስቲያኗ ከMWC አባልነት በአስቸኳይ ትውጣ።

አዲስ ጥምረት፦ ከመሰረተ እምነታችን ጋር የሚስማማ አዲስ የሜኖናይት ጥምረት ይመስረት።

ዝግጅት፦ ለነሃሴው "መጠመጉ" ጉባኤ ዝርዝር የግንኙነት መመሪያና የMWC የመውጫ ፕላን ተዘጋጅቶ ይቅረብ።
❤22👍4👏1
እውነተኛ የውስጥ አቃብያነ-እምነቶችን ለማየት እናፍቃለሁ! እቅበተ-እምነታቸውን እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ያደረጉ፣ በቃሉ የተገሩ አቃብያነ-እምነቶችን በአደባባይ ማየት የዘወትር መሻቴ ነው!

የምናፍቃቸው አቃብያን፦

🔍 ለራሳቸውና ለትምህርታቸው የሚጠነቀቁ ናቸው።

መጀመሪያ ለራሳቸው፣ ከዚያም ለሚያስተምሩት ትምህርት የሚጠነቀቁትን እናፍቃለሁ (1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥16)። ጤናማውን ትምህርት ጠንቅቀው በማወቅና በማስተማር፣ ሰዎች ኦርጂናሉን አውቀው ፎርጂዱን በቀላሉ እንዲለዩ የሚረዱትን ለማየት እፈልጋለሁ። እነዚህ ቅዱሳን አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ከመውቀሳቸው በፊት፣ ከቤተክርስቲያን ጋር አብረው የሚቆሙ ናቸው። ቢቻላቸው የአገልግሎት ዲፓርትመንት በካውንስሉ፣ በወንጌላውያን አብያተ-ክርስቲያናት ወይም በአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸውና በሚኒስትሪ ደረጃ ከፍተው ለመስራትና እውነትን ለማቀብ የሚተጉ ናቸው።

🩹 የወደቀውን የሚያነሱ እንጂ የማይረግጡ ናቸው።

ወንድማቸው ሲሳሳት ወይም ሲስት ሲያዩት፣ ጌታ ከጥፋት ጎዳና እንደመለሰው ሰው ሆነው ትላንትናቸውን ሳይረሱ፣ እንደ ጌታቸው፦ “የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን?” (ኤርምያስ 8፥4) በሚል መንፈስ በተስፋ የሚያቅቡ ናቸው።

ሰው በማናቸውም በደል እንኳን ቢገኝ፥ እንዲህ ያለውን ሰው በየዋህነት መንፈስ ያቀናሉ። የሌላውን ሸክም እየተሸከሙ፣ “እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ” የሚለውን አዲስ ትዕዛዝ የሆነውን የክርስቶስን ሕግ ለመፈጸም ይተጋሉ (ገላትያ 6፥1-2)። እውነትን በፍቅር የሚናገሩ (ኤፌሶን 4፥15)፣ ንግግራቸውና ጽሁፋቸው በጨው እንደተቀመመ በጸጋ የሆነና የሚያንጽ ነው (ቆላስይስ 4፥6)።

🌊 እግር የሚያጥቡ ትሑታን ናቸው።

የምናፍቃቸው አቃብያን፥ ያላቸውን ስጦታ ለማፍረስ ሳይሆን ለማነጽ ብቻ የሚጠቀሙ፣ ክፉ ቃል የማይወጣቸው (ኤፌሶን 4፥29)፣ ኢየሱስ እንዳደረገው ዘወትር እግር የሚተጣጠቡ ናቸው (ዮሐንስ 13፥14-15)። አዎ የትም ረግጦ የመጣውን ወንድማቸውን ዝቅ ብለው የሚያነጹ፣ ከነድካሙ የሚቀበሉ፣ የሚሸከሙና የሚያከብሩ አቃብያነ-እምነቶችን እናፍቃለሁ። ፍቅራቸው የኃጢአትን ብዛት የምትሸፍን (1ኛ ጴጥሮስ 4፥8)፣ በ 1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ የተዘረዘሩት የፍቅር ባሕርያት የሚገለጡባቸው የፍቅር ሰዎች ናቸው።

⚖️ የስርዓትና የሂደት ሰዎች ናቸው።

የሳተውን ወንድማቸውን ለመመለስ በኢየሱስ መንገድ ይሄዳሉ፦
1. መጀመሪያ በአደባባይና በሶሻል ሚዲያ ሳይሆን ጌታ እንዳዘዘው በግሉ ያነጋግሩታል።
2. ካልሆነ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ፊት ይሞክራሉ።
3. ያ ካልተሳካ ለቤተክርስቲያንና ለመሪዎች ይናገራሉ (ማቴዎስ 18፥15-17)።
4. በየትኛውም መንገድ አልመለስም ካለ ብቻ እንደ አረማዊ ቆጥረው፣ ካስፈለገም ሌሎች እንዲጠነቀቁ ወደ ሶሻል ሚዲያ ያወጡታል። ሆኖም “እንክርዳዱን እኔ ነኝ የማውቀው፣ ካልነቀልኩት” ብለው ከልካቸው በላይ የማይታበዩ፣ ወንድማቸው ከተመለሰ ለመደሰት፣ ለማጽናናትና ለማጽናት የማይዘገዩ (2ኛ ቆሮንቶስ 2፥7-8)፣ 70 ጊዜ 7 ቢበደሉ ይቅር የሚሉ ናቸው (ማቴዎስ 18፥22)።

🥪 የ“ግብረ-መልስ ሳንድዊችን" የሚጠቀሙ ጠቢባን ናቸው።

ጌታ ለሳምራዊቷ ሴት እንዳደረገው የሰውን ድካም እያወቁም የፍቅር እይታቸውን አይለውጡም (ዮሐንስ 4)። ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት እንዳደረገው ሲተቹና ሲያሄሱ የFeedback Sandwich ዘዴን ይጠቀማሉ (ራዕይ 2-3)፦
1. በመጀመሪያ መልካም ጎኖችን በመንገር ይጀምራሉ።
2. በመሃል እንዲስተካከል የሚፈልጉትን “በዳሩ ግን የምነቅፍብህ አለኝ” በማለት ያስቀምጣሉ።
3. በመጨረሻም “በድል ለነሳው...” በሚል የተስፋ ቃል ይዘጋሉ።
ይህ አካሄድ ሰዎች ራሳቸውን የመከላከል ምላሽ ውስጥ እንዳይገቡና እቅበተ-እምነት “እሪ በከንቱ” እንዳይሆን፣ ይልቁንም ፍሬ እንዲኖረው ያደርጋል።

🏗️ በጥበብ የሚገነቡ ናቸው።

ሁሉንም የማይነክሱ፣ ሁሉንም የማይጨፈልቁ፣ መልካሙንም መጥፎውንም በደርዙ የሚያስቀምጡ፣ በጥቂት ድካም የሰውን መልካም ነገር በዜሮ የማያባዙ ጥበበኞች ናቸው። በዓለም አደባባይ (በየሶሻል ሚድያው) እንደ ቆሮንቶሳውያን የማይካሰሱ (1ኛ ቆሮንቶስ 6፥1-8)፣ ሲተቹም የመስማትና የመመለስ ልብ ያላቸው ናቸው። የማይተቹ ተቺዎች አይደሉም። ትንኝ እያጠሩ ግመል እንዳይውጡ (ማቴዎስ 23፥24)፣ ጉድፍ እያጠሩ ግንድ ተሸክመው እንዳይሆን (ማቴዎስ 7፥3-5) ምናልባትም ጉድፍ የሚያሳያቸው ግንዳቸው እንዳይሆን እንደጠቢብ ራሳቸውን ለማየት የሚጠነቀቁ፣ አየር ላይ ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ የሚሰሩ፣ ተቋም የሚገነቡ፣ የእቅበተ-እምነትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አካሄድም ሆነ ሳይንስ የሚከተሉ አቃብያነ-እምነቶችን ማየት እናፍቃለሁ!

የመደምደሚያ ናፍቆቴ፦

ደግሞም ሲገሰጹ የሚሰሙ፣ የሚመለሱና የሚታዘዙ አብያተክርስቲያናትን፣ አገልጋዮችንና ምዕመናንንም ማየት ብርቱ ናፍቆቴ ነው!

ጌታ ሆይ፥ በቤትህ ቅናት የሚቃጠሉ ግን በፍቅር የተገሩ ልቦችን አብዛልን።

ይህንን ናፍቆት የምትጋሩ ለሌሎችም አጋሩት። #Apologetics #Faith #Love #Truth #Church #Ethiopia #BiblicalReformation
❤16🤝2
ጴንጤ ካልሆኑ፥ "የጴንጤ አቃብያን" ይጠብቀን 🙏 😀
👏28🙏2
አሁን እኮ ሶሻል ሚድያ ላይ ሽለላ ከሚመስል እንቅስቃሴ ጋር በልሳን የሚናገሩ ልጆች አይቼ መምጣቴ ነው። እኔ ምለው 🤔 ልሳንን እና የመሳሰሉትን በየሚድያውና በየሶሻል ሚድያው የምትለቁ ሰዎች ሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 2 ላይ ሐዋርያት "ጉሽ የወይን ጠጅ ጠጥተው፥ ሰክረዋል።" እንደተባሉት፣ እንዲሁም 1ኛ ቆሮንቶስ 14 ላይ "የማያምን ሰው እና ስለልሳን ያልተማረ ሰው ሁላችሁም በልሳን ስትናገሩ ቢሰማችሁ "አብደዋል፥ ይላችኋል፤" እንደተባለው "ሰካራም" እና "እብድ" መባል አምሯችሁ ነው ምትለቁት? 😏 ወይስ ምን አስባችሁ ነው? ለዚህ እኮ ነው ሰዎች እንዳይሰናከሉብን "በዝግታ ለራሳችን እና ለእግዚአብሔር እንድንናገር" ጳውሎስ ያዘዘው። ጭራሽ በሶሻል ሚድያና በየሚድያው ይባልልኛል? 🤔🤦‍♂️
👍29❤2👏2😍1
Forwarded from Moa 🦁
ሰላም ቅዱሳን እንዴት ናችሁ፤

ቅዳሜ የካቲት 21 የተዘጋጀ ልዩ ስልጠና አለ፤
"ትምህርተ ሥላሤን መጠበቅ" በሚል ርዕስ
ከ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ጋር እንማማራለን።

ዶ/ር ተስፋዬ በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ መፅሃፍትን ያበረከተ ወንድም ነው፤ ደግሞም በተለያዩ ስፍራዎች በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠናን እየሰጠ ይገኛል፤
እናም ይህ ዕድል በፍፁም እንዳያመልጣችሁ!!!

👉 ስልጠናው - ከጠዋት 2:30 ይጀምራል
ሙሉ ቀን ስልጠና ነው ሚሆነው።
በፍፁም እንዳያመልጣችሁ፤ ብትችሉ ሌሎች ሰዎችን ጋብዙ እናንተም ተገኙ።

👉 ቅዳሜ የካቲት 21 - አይቀርም
ላፍቶ 2000 ህንፃ ገባ ብሎ
❤19
በሞቱ ለኃጢአት ሞትን! በመነሳቱ ለእግዚአብሔር ሕያዋን ሆነን ተነሳን! በክርስቶስ! 💙

መልካም ትንሳዔ!
❤44🔥16👍2🥰1💯1
ዲዳኬ ("የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ትምሕርት") ስለሐዋርያትና ነቢያት ምን ይላል?

በዲዳኬ መሰረት "ነቢያትና ሐዋርያት" ተብለው የሚጠሩ አሁንም አሉ ወይስ የሉም? ካሉስ እንቀበላቸው ወይስ አንቀበላቸው?

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ትምሕርት በመባል የሚታወቀው ዲዳኬ ስለሐዋርያትና ስለነቢያት ምን ምን አስደናቂ ነገሮችን እንደሚል፣ ስለሌሎች በውስጡ ስለተጠቀሱ የአገልግሎት ዘርፎች ወይም ኃላፊነቶች (ኤጲስ ቆጶሶች፣ ዲያቆኖችና፣ መምሕራን) ምን እንደሚያስተምር፣ ስለዘረዘራቸው እውነተኞቹን ከሐሰተኞቹ የመለያ መስፈርቶች፣ በጥልቀት እናያለን።

🔵 ዲዳኬ ስለተባለው መጽሐፍ (ሰነድ) በጥቂቱ፦

በአብዛኛው ምሁራን ዘንድ በ1ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ወይም በ2ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የተጻፈ እንደሆነ ይታመናል። መጽሐፉ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የጥንቷ ክርስትና "የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት" ወይም "መመሪያ" ነው። እስካሁን ድረስ ያለው ብቸኛ ሙሉ ቅጂ "Codex Hierosolymitanus" (የ1056 ዓ.ም.) የተባለው የብራና ስብስብ ውስጥ ይገኛል። መጽሐፉ በራሳቸው በሐዋርያት የተፃፈ ባይሆንም የሐዋርያትን ትምህርት የሚያስተላልፍ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ማለት አንዳንዶቹ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ከመጻፋቸው በፊት እንኳ ሊሆን ይችላል። ከአዲስ ኪዳን ውጭ ካሉት የጥንቷ ክርስትና የስነ-ጽሑፍ ቅሪቶች አንዱና እጅግ አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ የጥንት ክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ "ቀኖናዊ" (Canonical) ደረጃ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ ከአራተኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ግን ከታሪክ ጠፍቶ ቆይቷል።

ዲዳኬ ስለጠቀሳቸው ስለአምስቱ የአገልግሎት ዘርፎች (ሐዋርያ፣ ነቢይ፣ ኤጲስ ቆጶስ፣ ዲያቆን እና መምሕር) ምን ይላል?፦

💠 ሐዋርያት

በዲዳኬ (Didache) ጽሑፍ መሠረት፣ ስለ ሐዋርያት (በተለይም ከአንዱ ስፍራ ወደ ሌላው ስለሚዘዋወሩት አገልጋዮች) የተሰጡት ዋና ዋና ትምህርቶችና መመሪያዎች በሚከተሉት ነጥቦች ይጠቃለላሉ፦

1. የሥልጣንና የተቀባይነት ደረጃ

- እንደ ጌታ መቆጠር፦ ወደ ምዕመናን ማኅበረሰብ የሚመጣ እውነተኛ ሐዋርያ ሁሉ "እንደ ጌታ" ተደርጎ ተቀባይነት ሊሰጠውና ሊከበር ይገባል (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 4)።

- የወንጌል መመሪያ፦ ማኅበረሰቡ ከሐዋርያት ጋር ሊኖረው የሚገባው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በወንጌል ድንጋጌዎች ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 3)።

2. የቆይታ ጊዜ ገደብ (ጉዟዊ ባሕርይ)

- የአንድ ቀን ቆይታ፦ ሐዋርያት ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው የሚዘዋወሩ መንገደኞች በመሆናቸው፣ በአንድ ስፍራ ማደር ያለባቸው ለአንድ ቀን ብቻ ነው፤ የግድ አስፈላጊ ከሆነ ግን ተጨማሪ አንድ ቀን ሊቆዩ ይችላሉ (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 5)።

- የሐሰተኝነት መለኪያ፦ አንድ ሐዋርያ በአንድ ስፍራ ላይ ሦስት ቀንና ከዚያ በላይ ከቆየ፣ ሳይሠራ ለመኖር የሚፈልግ "የሐሰት ነቢይ" (ወይም ሐሰተኛ ሐዋርያ) ተደርጎ ይቆጠራል (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 5)።

3. የቁሳቁስና የገንዘብ ገደብ

- የዕለት እንጀራ ብቻ፦ ሐዋርያው ከአንድ ማኅበረሰብ ተነስቶ ወደሚቀጥለው ማደሪያው ሲሄድ፣ ለጉዞው ከሚያስፈልገው እንጀራ በቀር ሌላ ምንም መውሰድ የለበትም (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 6)።

- ገንዘብ አለመጠየቅ፦ አንድ ሐዋርያ በጉዞው ላይ ገንዘብ ወይም ሌላ ቁሳቁስ ከጠየቀ፣ አገልግሎቱን ለግል ጥቅም የሚያውል ሐሰተኛ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 6)።

4. እውነተኛነታቸውን የመፈተን ኃላፊነት

- በጠባይ መመዘን፦ እውነተኛውና ሐሰተኛው አገልጋይ የሚለዩት በመንፈሳዊ ስጦታቸው ብቻ ሳይሆን፣ "የጌታ ዓይነት ጠባይ" (ሥነ-ምግባር) ያላቸው መሆኑን በማየት ነው (ምዕራፍ 11፣ ቁጥር 8)።

ይህ የሚያሳየው በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን "ሐዋርያ" ሙሉ በሙሉ ለወንጌል ስርጭትና ለተልዕኮ የተሰጠ፣ ራሱን የካደና ተጓዥ የሆነ የአገልግሎት ዘይቤን የሚያመለክት እንደነበር ነው።

💠 ነቢያት

በዲዳኬ (Didache) ጽሑፍ መሠረት ስለ ነቢያት የተሰጠው ትምህርት እጅግ ሰፊና ዝርዝር ነው። በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ነቢያት ከፍተኛ መንፈሳዊ ሥልጣን የነበራቸው ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጊዜ ማኅበረሰቡ ከሐሰተኛ ነቢያት ራሱን እንዲጠብቅ ጥብቅ መመዘኛዎች ተቀምጠውለታል።

ዋና ዋና ትምህርቶቹ በሚከተሉት አምስት ክፍሎች ይከፈላሉ፦

1. መንፈሳዊ ሥልጣንና የአምልኮ ነጻነት

- ነጻ የአምልኮ መሪነት፦ ነቢያት የቅዱስ ቁርባንን ምስጋና በተመለከተ በተቀመጠው ቋሚ የጸሎት ፎርማት ሳይገደቡ፣ "እንደ ወደዱ (በፈቀዱት መጠን) ምስጋና እንዲያቀርቡ" ሙሉ ነጻነት ተሰጥቷቸዋል (ምዕራፍ 10፥7)።

- እንደ ሊቃነ ካህናት መቆጠር፦ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያላቸው መንፈሳዊ ሥፍራ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የቤተ ክርስቲያን "ሊቃነ ካህናት" ተብለው ተጠርተዋል (ምዕራፍ 13፥3)።

2. እውነተኛና ሐሰተኛ ነቢያትን የመለየት መመዘኛ

ማኅበረሰቡ ነቢያትን በመንፈሳዊ ስጦታቸው (በመናገር ችሎታቸው) ብቻ ሳይሆን፣ በተግባራዊ ሥነ-ምግባራቸው እንዲመዝናቸው ታዟል፦

- የጌታ ጠባይ (Conduct)፦ በመንፈስ የሚናገር ሁሉ ነቢይ አይደለም፤ ይልቁንም እውነተኛ ነቢይ የጌታ ዓይነት ጠባይና ሥነ-ምግባር ሊኖረው ይገባል (ምዕራፍ 11፥8)።

- የግል ጥቅም ፈተና፦ አንድ ነቢይ በመንፈስ ሆኖ ማዕድ እንዲዘጋጅ አዞ ራሱ ከዚያ ቢበላ፣ ወይም "ገንዘብ ስጠኝ" ብሎ ለራሱ ከጠየቀ እርሱ ሐሰተኛ ነው። ነገር ግን ለሌሎች ችግረኞች እንዲሰጥ ቢጠይቅ ማንም ሊፈርድበት አይገባም (ምዕራፍ 11፥9 እና 12)።

- የተግባር ወጥነት፦ እውነትን የሚያስተምር፣ ነገር ግን ራሱ የሚያስተምረውን በተግባር የማይኖር ነቢይ ተቀባይነት የለውም። "ራሱ የሚያስተምረውን የማያደርግ" ሰው እንደ ሐሰተኛ ነቢይ ይቆጠራል (ምዕራፍ 11፥2)።

3. እውነተኛ ነቢያትን አለመፈተንና አለመፍረድ

- የማይሰረይ ኃጢአት፦ በመንፈስ የሚናገረውን እውነተኛ ነቢይ መፈተን ወይም በእርሱ ላይ መፍረድ በጥብቅ ተከልክሏል፤ ይህን ማድረግ መንፈስ ቅዱስን እንደመሳደብ (የማይሰረይ ኃጢአት) ተቆጥሯል (ምዕራፍ 11፥7)።

- ተምሳሌታዊ ድርጊቶች (Prophetic Drama)፦ አንድ እውነተኛ ነቢይ ለቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ሲል (ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን ነቢያት) እንግዳ የሆነ ድርጊት ቢያደርግና ሌሎችን ግን እንዲያደርጉ ባያስተምር፣ በእርሱ ላይ መፍረድ አይገባም፤ ፍርዱ ከእግዚአብሔር ጋር ነው (ምዕራፍ 11፥11)።

4. የድጋፍና የበኩራት ሥርዓት

ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ከሚዘዋወሩት ሐዋርያት በተለየ መልኩ፣ እውነተኛ ነቢያት በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ በቋሚነት መኖር (Settle down) ከፈለጉ መብት ተሰጥቷቸዋል፦

- የመጦሪያና የድጋፍ መብት፦ ከእናንተ ጋር ለመኖር የሚፈልግ እውነተኛ ነቢይ፣ እንደ ሠራተኛ ምግቡ ይገባዋል (ምዕራፍ 13፥1-2)።

- የበኩራት ኃላፊነት፦ ምዕመናኑ ከወይን መጥመቂያ፣ ከአውድማ፣ ከከብት፣ ከበግ፣ ከእንጀራ፣ ከዘይት፣ ከገንዘብና ከልብስ ጭምር የበኩራቱን (Firstfruits) ክፍል ሁሉ ወስደው ለነቢያት እንዲሰጡ ታዟል (ምዕራፍ 13፥3-7)። ነቢይ ከሌለ ግን ይህ በኩራት ለድሆች ይሰጣል።
❤11👍2🥰1👏1
5. ከቋሚ የአካባቢ መሪዎች ጋር ያላቸው ዝምድና

ነቢያት የሌሉበት ጊዜ ቢኖር፣ ማኅበረሰቡ የሚመርጣቸው የአካባቢው መሪዎች (ኤጲስቆጶሳትና ዲያቆናት) የነቢያትን አገልግሎት ስለሚሸፍኑ፣ ምዕመናኑ እነዚህን መሪዎች በነቢያት ልክ እንዲያከብሯቸውና እንዳይንቋቸው ታዟል (ምዕራፍ 15፥1-2)።

ዲዳኬ (Didache) በምዕራፍ 15 ላይ ስለ ኤጲስቆጶሳት (Bishops/Overseers) እና ዲያቆናት (Deacons/Servants) ያሰፈረው ትምህርት፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ለሹመትና ለመሪነት የተሰጠ እጅግ ጥንታዊ መመሪያ ነው።

💠 ኤጲስቆጶሳትና ዲያቆናት

ዲዳኬ ስለ ሁለቱ መዓረጋት የሚያስተምራቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በሚከተሉት ዐበይት ርዕሶች ማጠቃለል ይቻላል፦

1. የሹመትና የምርጫ ሥነ-ሥርዓት

- የማኅበረሰቡ ምርጫ፦ መሪዎቹ የሚሾሙት ከላይ በኃላፊዎች ሳይሆን፣ በአካባቢው በሚገኘው ጉባኤ (ምዕመናኑ) ነው። ጽሑፉ "ለራሳችሁ ኤጲስቆጶሳትንና ዲያቆናትን ምረጡ (ሹሙ)" በማለት ለጉባኤው በሙሉ የመምረጥ ሥልጣን ሰጥቷል (ምዕራፍ 15፥1)።

- የብቃት ማረጋገጫ፦ ምርጫው በሰዎች ግፊት ወይም በግል ዝንባሌ ሳይሆን፣ "ለጌታ የሚገቡ" (Worthy of the Lord) መሆናቸውን በመመዘን መሆን አለበት።

2. ጥብቅ የሥነ-ምግባር መመዘኛዎች

ኤጲስቆጶሳትና ዲያቆናት ሊኖራቸው የሚገባውን ማንነት ዲዳኬ በሚከተሉት አራት ዋና ዋና ነጥቦች ይዘረዝራቸዋል (ምዕራፍ 15፥1)፦

- ገርነት (Gentle/Meek)፦ ሥልጣናቸውን በጉልበት ሳይሆን በፍቅርና በሰላማዊ መንፈስ የሚጠቀሙ።

- ገንዘብን አለመውደድ (Not lovers of money)፦ ይህ ነጥብ በዲዳኬ ውስጥ ተደጋግሞ ይነሳል፤ ምክንያቱም በዘመኑ የነበሩ የሐሰት ነቢያት ቤተ ክርስቲያንን ለገንዘብ ይበዘብዙ ስለነበር፣ የቋሚ መሪዎች ዋና መገለጫ የገንዘብ ፍቅር አለመኖር ሆኗል።

- እውነተኛነት (True)፦ በቃላቸውና በተግባራቸው የታመኑ።

- የተፈተኑ (Approved)፦ በማኅበረሰቡ ዘንድ ቀድሞውኑ በሥራቸውና በጠባያቸው የታወቁና የተመሰከረላቸው።

3. የአገልግሎት አደራ (የነቢያትና የመምህራን ተተኪነት)

ዲዳኬ እጅግ ወሳኝ በሆነ አገላለጽ እንደሚከተለው ይላል፦

- ተግባራዊ ውክልና፦ "እነዚህ ደግሞ በመካከላችሁ የነቢያትንና የመምህራንን አገልግሎት ያገለግላሉና" (ምዕራፍ 15፥1)።

- የአገልግሎት ውክልና፦ ኤጲስቆጶሳት እና ዲያቆናት የነቢያትንና የመምህራንን አገልግሎት በመካከላችሁ ስለሚያከናውኑ፣ እንደ ነቢያትና መምህራን ከእናንተ ዘንድ ሊከበሩ ይገባል።

4. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ክብር

የማይናቁ መሆናቸው፦ ኤጲስቆጶሳትና ዲያቆናት ተግባራዊውን (አስተዳደራዊውን) ሥራ ስለሚሠሩ፣ ምዕመናኑ በመንፈሳዊ ስጦታ ከሚታወቁት ከነቢያት በታች አድርገው እንዳያዩአቸው "ስለዚህ አትናቋቸው" በማለት ያስጠነቅቃል (ምዕራፍ 15፥2)።

- እኩል ክብር፦ እነዚህ መሪዎች ከነቢያትና ከመምህራን ጋር በእግዚአብሔር እና በቤተ ክርስቲያን ዘንድ እኩል ክብር ሊሰጣቸው እንደሚገባ ያሳስባል (ምዕራፍ 15፥2)።

5. የሥራ ተግባር (ከጽሑፉ አጠቃላይ ይዘት የተወሰደ)

ዲዳኬ በምዕራፍ 15 ላይ በቀጥታ ባይዘረዝረውም፣ በምዕራፍ 13 እና 14 መሠረት የሚከተሉት ተግባራት በኤጲስቆጶሳትና በዲያቆናት ቁጥጥር ሥር ይወድቃሉ፦

- የበኩራት ፍሬን ማስተዳደር፦ ምዕመናኑ የሚያመጡትን የበኩራት መባ (ከወይን፣ ከዘይት፣ ከገንዘብ፣ ወዘተ) ተቀብሎ ለነቢያት ወይም ነቢይ ከሌለ ለድሆች ማከፋፈል (ምዕራፍ 13፥3-7)።

- ሥርዓተ አምልኮን መምራት፦ በሰንበት ቀን (እሑድ) መሰብሰብንና የቅዱስ ቁርባንን (ምስጋናውን) ሥርዓት መምራት (ምዕራፍ 14፥1)።

- ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ፦ ሕገ ወጥ ተግባራትን መግሠጽ፣ ሰዎችን ማስታረቅ እና የቤተ ክርስቲያንን ንጽሕና መጠበቅ (ምዕራፍ 14፥2፣ ምዕራፍ 15፥3)።

ማጠቃለያ፦

በዲዳኬ ዘመን የኤጲስቆጶሳትና የዲያቆናት ዋና ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን በሥነ-ምግባርና በአስተዳደር ማጽናት ነበር። ይህ መዋቅር የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ንጽሕና የሚጠብቅ "የአስተማማኝነት መረብ" (Safety net) ሆኖ አገልግሏል። ኤጲስቆጶሱ ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ትምህርት ትልቅ ኃላፊነት ሲኖረው፣ ዲያቆኑ ደግሞ በተለይም በገንዘብና በቁሳቁስ አስተዳደር እንዲሁም ለድሆች በማቅረብ ረገድ አብሮት የሚሠራ ዋና አጋር ነበር።

💠 መምሕራን

በዲዳኬ (Didache) መጽሐፍ መሠረት፣ ስለ "መምህራን" የተሰጡት ትምህርቶች በአብዛኛው ከነቢያትና ከሐዋርያት አገልግሎት ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ቢሆኑም፣ ለብቻቸው የሚከተሉት መመሪያዎች ተቀምጠውላቸዋል፦

1. የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ (መተዳደሪያ)

- እንደ ሠራተኛ መከበር፦ ዲዳኬ እውነተኛ መምህራንን እንደ ሠራተኛ ይቆጥራቸዋል። "እንደ ሠራተኛም ምግቡ ይገባዋል" በሚል መርህ፣ ምዕመናን እውነተኛ መምህራንን በቁሳቁስ የመደገፍ ግዴታ አለባቸው (ምዕራፍ 13፥2)።

2. የትምህርት መመዘኛ (ዶክትሪን)

- የትምህርቱ ይዘት መፈተን፦ አንድ መምህር የሚያስተምረው ትምህርት እጅግ ወሳኝ መለኪያ ነው። መምህሩ የሚያስተምረው ነገር ጽድቅንና የጌታን እውቀት የሚያመጣ ከሆነ፣ እንደ ጌታ አድርጎ መቀበል ይገባል። ነገር ግን መምህሩ ራሱ ዞሮ እነዚህን ነገሮች የሚያፈርስ (የሚቃወም) ትምህርት የሚያስተምር ከሆነ፣ ማንም ሊሰማው አይገባም (ምዕራፍ 11፥2)።

3. የተግባር ወጥነት

- ከቃል ጋር መኖር፦ እውነትን የሚያስተምር፣ ነገር ግን ራሱ የሚያስተምረውን በተግባር የማይኖር መምህር ተቀባይነት የለውም። "ራሱ የሚያስተምረውን የማያደርግ" ሰው እንደ ሐሰተኛ መምህር/ነቢይ ይቆጠራል (ምዕራፍ 11፥10)።

4. ክብርና ሥፍራ

- ከነቢያት ጋር እኩል ክብር፦ መምህራን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ሥፍራ የከበረ ነው። ኤጲስቆጶሳትና ዲያቆናት በቤተ ክርስቲያን ሲሾሙ፣ እነርሱም "ከነቢያትና ከመምህራን ጋር በእናንተ ዘንድ ክብርን ያገኙ" በመሆናቸው ሊከበሩ እንደሚገባ በግልጽ ተቀምጧል (ምዕራፍ 15፥1-2)።

በዲዳኬ ውስጥ መምህራን ከነቢያት ጋር በቅርበት የተያያዙ ናቸው፤ ዋናው ልዩነታቸውም ነቢያት በመንፈስ በመመራት ምሥጢራትንና አዲስ ትንቢትን ሲናገሩ፣ መምህራን ደግሞ የጌታን ትምህርት (ወንጌልን) በዘወትር ሕይወት ውስጥ በማስተማርና በመተግበር ላይ ያተኩራሉ ማለት ነው።

ለዚህ ፅሁፍ በዋነኝነት የተጠቀምኩት ማጣቀሻ የኤርማን መግቢያና የዲዳኬን የትርጉም ስራውን ሲሆን፥ ይሄ መጽሐፍ በ"ሎብ ክላሲካል ላይብረሪ" (Loeb Classical Library) የታተመ በመሆኑ፣ በTextual Criticism እና በአካዳሚያዊ ጥራቱ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ የነገረ መለኮትና የታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ዋነኛ ማጣቀሻ ነው።

🔷 ዋቢ፦

Ehrman, B. D. (Ed. & Trans.). (2003). The Apostolic Fathers (Vols. 1–2). Harvard University Press.
❤10🔥1
ለ 4ተኛ ዙር ተማሪዎች Certificate እየሰጠን እንገኛለን,

😇5ተኛ ዙር ነፃ የክረምት ምዝገባ ነገ ይጀምራል
🔥27👍7❤4🙏3🥰1
ምዝገባ ተጀምሯል
🔉🔉🔉🔉🔉💬
5 ተኛ ዙር የአፖሎሚክስ አፖሎጄቲካል ትምህርት ቤት ስልጠና ተጀምሯል።
🛑 ለመመዝገብ 

1.ማንነታችሁን ሊገልፅ የሚችል መታወቂያ |የቀበሌ, መንጃ ፈቃድ, ፓስፓርት በ ፎቶ መላክ ይኖርባችኋል

2.ሙሉ ስምና ስልክ የምታገለግሉበት ቤተክርስቲያን ስም መሙላት ይጠበቅባችኋል

3.የኢንተርኔት (Internet)አገልግሎት ማግኘት የሚችል በ ዋነኝነት Telegram

4.በመጨረሻም ተጨማሪ መማርያ youtube Channel Subscribe ማረግ ግዴታ ነው

ለመመዝገብ👇
Google form


https://forms.gle/Bbm9zjf8AZt2joFcA




🔈ወንጌል ይስፋ!
💬🗯በሌሎች አማራጮችም ይከታተሉን

✅YouTube Account👇
https://www.youtube.com/channel/UCUSff8njz3qAWtnKPOzR-pQ

🔴Tiktok
https://www.tiktok.com/@apolomics?_r=1

🔲Telegram Channel
@apolomics

#Go And Make Them "Disciples"📣
❤18😇3🫡3👍1
ለመመዝገብ👇
Google form

ለመመዝገብ👇

https://forms.gle/Bbm9zjf8AZt2joFcA

Join @apolomics
🙏14💯5❤3🥰2
NOTICE
ሰላም እንደምን ቆያችሁ ዛሬ ምሽት(እሁድ ) 3:00 ላይ የ 5ተኛ ዙር Live Orientation ስለሚኖረን ዛሬ ያልተገኘ ትምህርቱን መከታተል እንደማይችል ልናሳውቅ እንወዳለን።

Share
SHARE
share
@apolomics
❤12
🎓አፓሎሚክስ |Apolomics Apologetical School pinned «NOTICE ሰላም እንደምን ቆያችሁ ዛሬ ምሽት(እሁድ ) 3:00 ላይ የ 5ተኛ ዙር Live Orientation ስለሚኖረን ዛሬ ያልተገኘ ትምህርቱን መከታተል እንደማይችል ልናሳውቅ እንወዳለን። Share SHARE share @apolomics»
ማሳሰቢያ
🔈የአፖሎሚክስ አፓሎጄቲካል ት/ቤት የ5ተኛ ዙር ምዝገባን አጠናቀናል የተመዘገባቹ ተማሪዎች ነገ ትምህርት ምትጀምሩ መሆኑን እየገለፅን ያልተመዘገባቹ ለቀጣይ ምዝገባ ራሳችሁን አዘጋጁ።


Join our channel
@apolomics
🔥9❤7
🗣አስደሳች ዜና
ለሁሉም የ APOLOMICS ቤተሰቦች

💥ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው ለ 4 ዙር አስተምረን ማስመረቃችን ይታወቃል

👌 አሁን ደግሞ በሁላችሁም ጥያቄ መሠረት
# የአስተምህሮተ ስላሴን Advanced በሆነ መልኩ ከ ዶ/ር አማረ መስፍን ጋር የምንማር በመሆኑ እስካሁን የተማራችሁ እንዲሁም አዳዲሶች ሁላችንም ከታች ባለው Link እንድትመዘገቡ ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን::

በነፃ መሆኑ እንዳይረሳ::

የሚጀምርበት ቀን የፊታችን ሀሙስ በ 12/12/2018

🛑 ለመመዝገብ👇
Google form


https://forms.gle/CHCR1tUP4MCr2VUeA


🔈ወንጌል ይስፋ!
💬🗯በሌሎች አማራጮችም ይከታተሉን


🔲Telegram Channel
@apolomics

#Go And Make Them "Disciples"📣
❤14🥰3