Apostolic generation evangelize pinned «https://youtu.be/gxv6zl6RmUc»
Forwarded from ማራናታ.....MARANATHA😍 (Tade♥♥♥♥)
የመጨረሻ ዘመን ትንቢት መጀመሪያ
በመጨረሻ ዘመን ላይ ይሆናል ተብለው የተነበዩ ትንቢቶች መፈጸም ከመጀመሩም አልፎ ማለቅያ ላይ መድረሱን አስታውሰዋሉ? ይህ አርእስት በመጀመሪያ ላይ ብዙም ግልጽ ላይሆንባችሁ ይችላል። ነገር ግን እያነበባችሁ ወደ ታች ስትሄዱ በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ትረዱታላችሁ። አዎ! ይህ ዘመን ለመጨረሻ ዘመን ትምቢቶች መጀመሪያ ነው። ከካቻምናው አምና፤ ከአምናው ዘንድሮ፤ እንደው ከትላንቱ ዛሬ የሚንሰማውና በአለም ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርግት የመጨረሻ ዘመን ትንቢት ነው።
በመክበብ 3፥1-8 ላይ ለሁሉም ጊዜ አለው ተብሎ እንደተጻፈው በፊት ያልሰማነው ነገር ጊዜው ስደርስ አሁን እየሰማን ነን። አሁን ጊዜው ስደርስ እየሰማን ያለነው ነገር በዚህ መጽሐፍ ክፍል ውስጥ አምብበን እንመለስ።
(መጽሐፈ መክብብ ምዕ. 3፥1-8)
1፤ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።
2፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤
3፤ ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤
4፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤
5፤ ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤
6፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤
7፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤
8፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው"ይላል።
⚛ ዘመን ለእግዚአብሔር ሠራተኛ ነው። ለአንድ ነገር ጊዜው ስደርስ ማንም ወደኋላ ልመልሰው አይችልም። አንድ አባባል " ጊዜው የሰጠ ቅል ድንጋን ይሰብራል" ይላል። አው ልክ ነው ምክንያቱም ጊዜው ነዋ!!
ጊዜ ለአንድ ነገር ወሳኝ ነው። ያለጊዜው የሚሆን ነገር በመንገድ ላይ ይጥላል። ሁሉም ነገር በጊዜው ሊሆን እንደሚችል ማመን አለብን።
🕎 በሉቃስ 1፥20 ላይ ስትመለክቱት ዘካሪያስ በጊዜው የሚሆን ነገር ባለማመኑ ምክንያት ለጊዜው ድዳ ሆነ። ነገር ግን በመጨረሻም ጊዜው ስደርስ እንደገና ተፈውሶ መናገር ጀመረ። ስለዚህ ድዳ ለመሆንም ጊዜ አለው ለመፈወስም ጊዜ አለው።
🕎 በማቴ 24፥1 ጀምረን እስከ መጨረሻ ስናነብ "የመጨረሻ ዘመን ትንቢት መጀመሪያ" በግልፅ ይናገራል። ነገር ግን ጊዜያችንን ለማሳጠር ከቁ.3-8 እናንብብ
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 24፥3-8)
3፤ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
4፤ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
5፤ ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
6፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
7፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
8፤ እነዚህም ሁሉ #የምጥ_ጣር_መጀመሪያ ናቸው" ይላል።
⚛ ከዚህ መጽሐፍ ክፍል በመጨረሻ ዘመን ትንቢት መጀመሪያ አሳጥረን ስንመለከት፦
✅ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳል
✅ እኔ ክርስቶስ ነኝ ባዮች ይወጣሉ
✅ በየአቅጣጫው ጦርና የጦር ወሬ ትሰማላችሁ
✅ ሐሰተኛ ነብያት በየሰፈሩ ይነሳሉ
✅ ራብ፣ ቸነፈር፣ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል.....ወዘተ
ይህ ሁሉ የመጨረሻ ዘመን ምልክት ነው።
አሁን በዘመናችን ላይ ሐሰተኛ ነብያት በከተማችን ውስጥ ለምን በዙ? አይባልም። ምክንያቱም ጊዜያቸው ነውና።
በቁ.24 ላይ "ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነብያቶች ይነሳሉና፤ ብቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስክያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ" ይላል። ስለዚህ ለእነርሱ የማሳሳት ጊዜያቸው ነው፣ ለአንተ ግን የጽናት ጊዜ ነው። አንተ ግን እስከ መጨረሻ ጽና፣ እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ የተባረከ ነውና።
🙈 በመንግሥት ላይ ጦር ለምን በዛ? ቤተክርስትያን አይጸልይም እንደ? አይባልም። ምክንያቱም የመጨረሻ ዘመን ትንቢት መጀመሪያ ላይ ጦርም የጦር ወሬም ትሰሙ ዘንድ ግድ ነውና፣ ጊዜያቸው ስደርስ ቤተክርስትያን ጸልያም ምንም መቀየር አትችልምና።
🙈 ረሃብ፣ የኑሮ ውድነት ለምን በዛ? አይባልም። ጊዜያቸው ነውና፤ የተድላ ዘመን እየመሰለ የረሃብ ዘመን ይሆናል ተብሎ ተጽፎአልና።
🙈 ቤተክርስትያን እየጾመች እየጸለየች በአለም ላይ ክፋት ሞላ፣ ተክኖሎጂ በዚቶ ይህንን አመጣልን፣ ይህ ለምን ሆነ አይባልም። ጊዜያቸው ነውና፣ ለእነርሱ የክፋት ጊዜያቸው ለቤተክርስቲያን ግን ሙሽራዋን ልትቀበል የዝግጅት ጊዜያቸው ነውና።
"ቃሉ የታመነ ነው" ተብሎ ተጽፎአል። ቃሉ የታመነ እስከሆን ድረስ በቃሉ ውስጥ የተጻፉ ትንቢቶች ጊዜያቸው ስደርስ በማን ላይ ሊፈጸም ነው ታድያ? እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ምልክቱን የሚያሳየው ዘመኑን ተጠቅሞ ነው፤ ለዚህም ነው ዘመን ለእግዚአብሔር ሠራተኛ ነው ያልኩት።
🙈 የዱሮ መታዘዝ፣ የዱሮ ፍቅር፣ የዱሮ መንፈስ፣ የዱሮ ተአምራቶች..... ከቤተክርስቲያን የት ሄዱ፣ ለምን ሸሹ? አይባልም። ምክንያቱም በ2ኛ ጥሞ 3፥1 ላይ የተጻፈው መፈጸሙን ስለማይቀር።
❖ ስለዚህ ወንድሞች እህቶች ይህ #የማነቂያ_ደውል መልዕክት ስለሆነ የመጨረሻ ዘመን ትንቢት ከመጀመሩም አልፎ ወደ ማለቅያው ስለተቃረበ ለጓደኞቻችሁም በማጋራት ኢየሱስን በንቃትና በትጋት እንድንጠብቅ በዚህ ት/ት አሳስባችኋለሁ።
ለሁላችንም ኢየሱስ ይርዳን!!
"ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፣ እንድህ ያለው መስዋዕት #እግዚአብሔርን_ደስ_ያሰኘዋልና" ዕብራ 13፥15
ሁሌም #የማነቂያ_ደውል ት/ት ለማግኘት ቆይታችሁን ከማራናታ ተለግራም ቻናል ጋር አድርጉ።
ሊንካችን @MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
አስተያየትና ጥቆማ ካላችሁ
@Taddyapostolic
በግሩፕ ላይ እሳተፋለሁ ወይንም አስተያየተን በግሩፕ ላይ እሰጣለሁ ካላችሁ @marantawoch

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለስሙ ያለን ፍቅር በምን ይገለጣል?
በቄስ ወንደሰን ታደሰ
📌 ለስሙ ያለን ፍቅር በምን ይገለጣል?
“እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።”
ዕብ6፥10
በቄስ ወንደሰን ታደሰ
@ACEBoleHermon
“እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።”
ዕብ6፥10
በቄስ ወንደሰን ታደሰ
@ACEBoleHermon
Forwarded from ማራናታ.....MARANATHA😍 (Tade♥♥♥♥)
🙏🙏#የፀሎት_ሀይል🙏🙏
💆♂🤦♂የማይፀልይ ክርስቲያንየሌለው የእግዚአብሔር መገኘት፣ሀይል፣ስጦታና ጥበቃ ያጣ ጉልበት ክርስቲያን ነዉ።
💆🤦♀ምክንያቱም አለመፀልይ ለአንድ ክርስቲያን ትልቅ ጉዳት ስለሚያስከትል
📖 “ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤”
— ያዕቆብ 4፥2
✍እንግዲህ በፀሎት ዉስጥ ያለዉን በረከት እና በፀሎት ዉስጥ ያለውን ሀይል የሚጠቀም ሰው ማነው ብባል የሚፀልይ ሰዉ ነው።
✍ፀሎት የሁሉም ነገር መክፈቻ ወይም #ማስተር_ከይ ነዉ
🙏ለማነኛውም ነገር በእምነት ወደ እግዚአብሔር ብንፀልይ እግዚአብሔር ይሰማናል።
✍ታላቅ የፀሎት ሰዉ #ክሪሶስተም ስለ ፀሎት እንዲህ ብለዋል "ፀሎት የእሳት ሀይል አጥፍቷል፣የአንበሶች አፍ ዘግቷል፤አመጽን ፀጥ አሰኝቷል፤ጦርነት አቁሟል፤አጋንንትን አስወጥቷል፤የሞትን ሰንሰለቶችን ተሰባብሯል፤የመንግስተ ሰማይ ደጆችን ከፍቷል፤የእግዚአብሔርን መንግስት አሰፋፍቷል፤ከተሞችን ከጥፋት እንዲዲኑ አድርጓል።
ስለዚህ ፀሎት እንደሚገባ ያልተጠቀምነዉ ትልቁ ሀብትና ተቆፍሮ ተቆፍሮ የማይልቅ ማዕድን ነዉ።" ብለዋል
🙏ኢየሱስ ክርስቶስም በስሜ የምትለምኑትን #ሁሉ ነገር አደርጋለሁ ብሎ ቃል ገብቶናል
ፀሎት ለሁሉም ነገር መልስ ነዉ።
📖 ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን #ሁሉ አደርገዋለሁ።
¹⁴ ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
📖 “በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን #ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።”
— ዮሐንስ 15፥7
📖 “እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተን አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን #ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።”
— ዮሐንስ 15፥16

#ተስፋ_መቁረጥ
👉 ሰይጣን ሰውን የሚያሽመደምደው ወይንም ደግሞ ሰው ጌታ ካየለት ከፍታ እንዲጎድል የሚያደርገው ሀይልን በመጠቀም ሳይሆን ተስፋ ማስቆረጥ የሚባልን መሳሪያ በመጠቀም ነው።
👉ሰይጣን ነገራችሁን ሊያበላሽ ሲፈልግ መጀመሪያ የሚያደርገው እናንተን ተስፋ በማስቆረጥ ህይወት ውስጥ እንድታልፋ በማድረግ ነው።
👉ሰይጣን ይህን የሚያደርገው በሀይል ሳይሆን እውነት የሚመስሉ ነገር ግን ፈጽሞ ከእውነት የራቁ ነገሮችን ወደ አእምሯችሁ በመላክ እነዚያን ብቻ እንድታስቡ በማድረግ ነው።
ለምሳሌ:- ሰይጣን እነዚህን ነገሮች በመንገር ተስፋ ወደ መቁረጥ ህይወት ውስጥ ሊከታችሁ ይችላል 👇
⚜ምንም አትረቢም/ባም
⚜ተራ ሰው ነሽ/ነህ
⚜ጸልየህ/ሽ በህይወትህ/ሽ ላይ ምንም የመጣ ለውጥ የለም
⚜ሀጥያተኛ ነሽ/ነህ
⚜ተባርኬያለው ትላለህ/ ትያለሽ ግን እስከ አሁን ወፍ የለም
⚜በመገረፉ ቁስል ተፈውሻለዉ ትላለህ/ ትያለሽ ግን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም
👆ደጋግማችሁ እነዚህን ነገሮች ስታስቡ በተስፋ መቁረጥ ወደ ተሞላ ህይወት ውስጥ ትገባላችሁ።
🔗ነገር ግን በህይወታችሁ ላይ ከሰዎች ወይም ከሰይጣን የሚወረወረውን ተስፋ ሊያስቆርጥ የሚችልን ሀሳብ ማስቀረት ብሎም በተስፋ መቁረጥ ህይወት ውስጥ ልትታሰሩ የማትችሉት እነዚህን ነገሮች ስታደርጉ ብቻ ነው። 👇
1. በክርስቶስ ዘንድ ያላችሁን ማንነት እወቁ!
📌መንፈሳዊ ውጊያ የሚጀመረው ልቀቅ እና ውጣ ከማለት ሳይሆን በክርስቶስ ዘንድ ያለንን ማንነት ከማወቅ ነው!
👉በክርስቶስ ዘንድ ያላችሁ ማንነት ውርደት፣ ሀጥያት፣ ተሸናፊነት፣ ውድቀት ሳይሆን ክብር፣ ጽድቅ፣ ሁልጊዜ የሚቀጥል ወይንም የማይቋረጥ አሸናፊነት፣ ድል እና ከፍታ ብቻ ነው።
2. ክርስቶስ የሰጣችሁን የልጅነት ስልጣን፣ በነገሮች ሁሉ ላይ የመግዛትን ስልጣን እንደሰጣችሁ እወቁ!
📌ማወቅ ብቻ ሳይሆን በእምነት ተለማመዷቸው።
👉በክርስቶስ ባገኛችሁት ማንነት ምክንያት እናንተ በበሽታ፣ በድህነት፣ በችግር ላይ ትገዛላችሁ ወይንም ትሰለጥናላችሁ እንጂ በፍጹም እነዚህ ነገሮች እናንተን አይገዟችሁም።
3. ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሰራው ስራ ምክንያት እናንተ በእምነት ብቻ ወደሚገኝ ጽድቅ እንደመጣችሁ እና በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደሆናችሁ እወቁ።
4. በክርስቶስ ኢየሱስ በረከትን በእምነት እንደተቀበላችሁ፣ እናንተ የተባረካችሁ፣ እግዚአብሔር ድንቅ ነገርን የተናገረባችሁ፣ እግዚአብሔር ደስታን የተናገረባችሁ፣ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ሁሉ የከፍታ እንዳደረገው፣ እግዚአብሔር በበረከት አጥር እንዳጠራችሁ እወቁ።
5. በመስቀል ላይ ሆኖ በቆሰለላችሁ ጌታ ምክንያት በሽታችሁ እንደተፈወሰ፣ ደዌያችሁን ሁሉ ክርስቶስ እንደወሰደ፣ እናንተም ደግሞ በዚህ ምክንያት እንደተፈወሳችሁ እወቁ።
📌በነገራችን ላይ እግዚአብሔር የፈውስ ፕሮግራም የሚል schedule የለውም። ይህም ማለት ፈውሱ የተለቀቀው ወይንም ስርጭቱን የጀመረው በቀራንዮ መስቀል ላይ ሆኖ ጌታችን ደዌያችንን፣ ህመማችን ወስዶ "ቴቴሌስታይ" / "ተፈጸመ" ካለበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
🔗ስለዚህ ይህ የፈውስ ስርጭት የሚተላለፈው live ስለሆነ እናንተም ሲግናላችሁን ወይንም አንቴናችሁን አስተካክላችሁ 24 ሰአት live ወደ ሆነው የፈውስ ስርጭት ግቡ። THIS IS SPIRITUAL TRUTH!!!
👆ስለዚህ እነዚህን በማሰብ፣ በመናገር፣ በማንሰላሰል እንዲሁም በልብ በመጠበቅ ከሰይጣን ወደ ህይወታችሁ የሚመጣውን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ማስቀረት ትችላላችሁ።
።። ለበረከት ሆናችጏል ።።
@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
OR @MARANTAWOCH

የማቴ 28:20.....28 እውነታዎች 📖📖
1,ማቴ 28:19 ጌታችን ኢየሱስ ለአስራ አንዱ ደቀመዛሙርት ለብቻቸው የተናገረው ትዕዛዝ ነው።ማር 4:34,ሉቃ 10:23
2,ማቴ 28:19 ለመረዳት የመንግስተ ሰማያትን ምስጢር የማወቅ የመገለጥ ዕውቀት ያስፈልጋል።የእግዚአብሔር ምስጢር የሆነውን ክርስቶስን ማወቅ። ዩሀ 17:3
3,እንደ ስላሴያዊ የጥምቀት ቀመር ከተወሰደ ብቸኛ ጥቅስ ሆኖ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ይቆማል።
4,ሐዋ 2:38 የማቴ 28:19 "የተግባር አፈፃፀም ነው"።
5,በትዕዛዙ መሰረት ማጥመቅም ሆነ ትዕዛዙን እንዲጠመቁ ማስተማር የክርስቶስ ሐዋርያት ድርሻ ስለሆነ ደርሶ ለጌታ ትዕዛዝ ተቆርቆሪ መምሰል ተገቢ አይደለም።
6,በስም ማጥመቅ በስልጣን ማጥመቅ ነው ስልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ ያለው ደግሞ ኢየሱስ ነው።
7,ጥምቀት የሚከናወንበት የአባት,የልጅ እና የመንፈስ ቅዱስ (የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ) ስም ማነው? ብለን ልንጠይቅ ይገባናል። በተለይ ለምን ነጠላ ቁጥር ሆኖ ለምን ስም እንደተባለ ስሞች ለምን አልተባለም?? ብለን ልንጠይቅ ያስፈልጋል።
8,መዳንም በሌላ በማንም ከሌለ ከሰማይ በታች ልንድንበት የሚገባ ለሰዎች የተሰጠ ኢየሱስ ብቻ ስለሆነ ሰው ሁሉ ሊማረው ሊረዳው የሚያስፈልገው ነገር የስሙ መገለጥ ነው።ሉቃ 24:47
9,ኢየሱስ የአባት የልጅ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው (የመለኮት ስም ነው) ራዕ 3:17,ማቴ 1:21, ዩሀ 14:26
10,ትክክለኛ ፍቺ በበዓለ ሀምሣ ቀን በወረደው መንፈስ ቅዱስ ምሪት ተገለጠ።
11,"እንግዲህ ሂዱ" የሚለው ተልዕኮ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ይህን ተልዕኮ ለመፈፀም ቀዳሚ እንደሆኑና ምሳሌነታቸውን ልንከተለው እንደሚገባን ያመለክተናል።
12,"አህዛብን ሁሉ" የሚለው ቃል እስራኤልን ወይም አይሁዳዊያንን የሚያሳትፍ ቃል ሆኖ ሕዝቦችን ወይም ዓለም አቀፍ የሆነ እንጂ ያልገረዘ በሚል ትርጉም የተፃፈ አይደለም።
13,በተለይ በቀድሞ አማርኛ 1879 እና በኢንጊሊዘኛው ትርጉም ማየት እንደሚቻለው ሕዝብን ሁሉ እያስተማራችሁ አጥምቁ በሚል የተፃፈው ቃል ሊጠመቁ የሚገባቸው እነማን እንደሆኑ ማወቅ ተጀቢ ነው።
14,ሰዎች በ 3 ስሞች ማጥመቅ የጀመሩበት ዘመን የክርስቶስ ሐዋርያ ካለፉ በኋላ ብዙ የስህተት ት/ት ቤ/ክ መግባት የጀመሩበት ዘመን ነው።
15, በእርሱ ስልጣን ብቻ ጥምቀት ይከናወናል።
16, በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ በ 3 ስም ያጠመቀ የተጠመቀም ማግኛት ከቶ አይቻልም።
17, የአዲስ ኪዳኗ ቤ/ክ የመጀመሪያ መሪ ሐዋርያዊው ጴጥሮስ በሁለቱም ስፍራ በሁለቱም ወገኖች ማለትም አይሁድና አህዛብ በኢየሱስም ብቻ እንዲጠመቁ አዟል።
18,ጌታ እራሱ ከእነሱ ጋር አብሮ ይመሰክር ነበር።
19,ኢየሱስ እራሱ ለሐዋርያቱ ወግኗል።
20,አጥማቂ የሚባለው ኢየሱስ እራሱ ነበር።
21,በኢየሱስ ወይም በአንድ አምላክ የሚያምኑ በራሱ በአንዱ ይጠመቃሉ።
22, 2ኛ ቆሮ 13:5 የሚያስተምረውን ቃል እርግጠኝነት ልንፈትሸው ይገባል።
23,ማቴ 28:19 የታላቁ ተልዕኮ ክፋል ነው ስለዚህ ከሌሎች ተመሳሳይ ክፍሎች ጋር አስማምተን ልንረዳው ይገባል።
24,አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የመጠሪያ ስም (የተፀዎ) ስም proper noun አይደለም። በ ኢሳ 9:6: እንደተፃፉት የፈጣሪን ማንነት ገላጭ የሆነ ስም ነው። ስለሆነም እየተቆጠረ እና እንደመጠሪያ ስም የምንጠቀምበት አይደለም። መሰበክ መታወቅ መታወጅን ያመለክተናል በይብራይስጥ ቋንቋ
25,የማቴ 28:19 የአንድ ማንነት የተለያዩ የመገለጥ ጎዳናዎች አመልካች እንጂ መድብለ አካላት አይሆኑም።አንድ ማንነት በሶስት የተለያዩ ስሞች ስለታወቀ አይከፋፈልም አይለያይም።
26,የስሙ ስነመለኮት(ቲዩሎጂ) መገለጥ አስፈላጊነት የተንፀባረቀበት ጥቅል ሆኖ የቀረበ ጥልቅ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ትንተና የሚያስፈልገው መልዕክትን ያዘለ ነው።

#መጥፎ #ልማዶችን #መተው
ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ – ሮሜ 12፡21
👉ከክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት ስንጀምር እግዚአብሔር እንደፈጠረን አይነት የእግዚብሔር ህዝብ የመሆንን የዕድሜ ልክ ጎዞ ነው የጀመርነው፡፡በሂደት ድካማችንን እንዴት እንደምናሸንፍ እና በእግዚአብሔር ጥንካሬ እንዴት እንደምንኖር እንማራለን፡፡ይሄም ማለት መጥፎ ልማዶችን መተውን መማር ማለት ነው፡፡
👉ለአመታት ነገሮች በእኔ መንገድ ባልሄዱ ቁጥር የመናደድ ልማድ ነበረብኝ፡፡ምናልባት ይሄ የእናንተ መጥፎ ልምድ ላይሆን ይችላል፡፡ምናልባት እናንተ ታሙ፣ጥሩ ይልሆኑ ቃላቶችን ትጠቀሙ ይሆናል፣ከመጠን በላይ ቡና ትጠጡ፣ለረጅም ጊዜ ቲቪ ትመለከቱ ወይም በማያስፈልጓችሁ ነገሮች ላይ ገንዘብ ታባክኑ ይሆናል፡፡መጥፎው ልማዳችሁ ምንም ሆነ ምን ልትተዉት ትችላላችሁ፡፡
👉መጥፎ ልማድን መተው ቀላል ነው እያልኩ አይደለም ነገር ግን መጥፎ ልማዶችንን ላይ ስልጣን እንዲኖረን የእግዚአብሔር ፍላጎት ነው፡፡በስሜቶቻችን “እንድንነዳ” አይፈልግም-ይልቁንስ ድል እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡
👉መጥፎ ልማድን መተው አንዱ ከሌላው ጋር ተከታታይነት ያላቸውን ጥሩ ምርጫዎችን መምረጥን ይጠይቃል፡፡ብዙዎቻችን ይሄንን ለማድረግ የምንሞክረው በራሳችን ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ነው ፡፡ ነገር ግን ያለ እግዚአብሔር ዕርዳታ እግዚአብሔርን ማስደሰት እንደማንችል እንረዳለን።
👉አምፕሊፋይድ የተባለው የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም መንፈስ ቅዱስን “ዝግጁ” ይለዋል. ድንገት ችግር ውስጥ ከገባችሁ እና ዕርዳታ ከፈለጋችሁ ሁሌም ዝግጁ ነው፡፡ነገር ግን ሳይጋበዝ አይገኝም፡፡ለዕርዳታ ልትጠሩት ይገባል፡፡
#ሮሜ 12፡21 ሲናገር ክፉን በመልካም አሸንፉ ይላል፡፡በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ካሉ ትልልቅ ሚስጥሮች አንዱ ነው፡፡ የውድቀት ፍርሃት ላይ ከማተኮር ይልቅ በእግዚአብሔር እና በድላችሁ ላይ ስታተኩሩ ትክክለኛውን ውሳኔ መወሰን በጣም ይቀላል፡፡
👉በመንፈስ ለመመላለስ ዛሬ ምረጡና መጥፎ ልምዶችን አሸንፋችሁ በድል ኑሩ!
#የጸሎት #መጀመሪያ
👉እግዚአብሔር ሆይ ከመጥፎ ልምዶቼ ጋር መኖር በቅቶኛል፡፡እንደ አለቃ ሊቆጣጠሩኝ በሚፈልጉት ፈተናዎቼ ላይ ለመሰልጠን አሁን እመርጣለሁ፡፡ቅዱስ መንፈስህን ወደ አዲስ እና የተሸሉ የህይወት ልምምዶች እከተለዋለሁ፡፡

ይሆናል ያልከው የሰማነው አሜን ይሁንልን | Tebarek Simon | Hawassa | Apostolic church of Ethiopia
👉 https://youtu.be/eP7cTIIUCME
👉 https://youtu.be/eP7cTIIUCME
YouTube
ይሆናል ያልከው የሰማነው አሜን ይሁንልን | Tebarek Simon | Hawassa | Apostolic church of Ethiopia
ስጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስህን ያገኛል
አሜን/3* ያገኛል
ለደረቀው አጥንቶች ደግሞም ህይወት ይሆናል
መንፈስህም ህይወት ይሆናል
ቤትህ በተራሮች ከፍ ብሎ ይታያል
አህዛብን ይሰበስባል
ስምህም አንድ ብቻ አንድ ሆኖ ይጠራል
በአለም ሁሉ ደምቆ ያበራል
Live Video by @Isoyisehak : https://youtu.be/MFzh_v28BCU
“እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ…

ይሆናል ያልከው የሰማነው አሜን ይሁንልን
Tebarek Simon
ዘማሪ ተባረክ ስምዖን
የሐዋሳ 01 እናት አጥቢያ ዘማሪ
ይሁን ይሁንልን ይሆናል ያልከው የሰማነው
አሜን ይሁንልን እጆችህ ይከፈቱ ክብርህን እንይ
ይሁን ይሁንልን መንግስትህ ትምጣ ምትናፍቀን
አሜን ይሁንልን ከሰማይ ሰማያት ወርደህ እንይህ
ከአፍህ በወጣው ቃል እኛም በሰማነው
ሰማይ ምድር ብያልፉ ከቶ በማይሻረው
ይሆናል ብለሃል በራስህም ምለህ
ልጆችህም አምነናል የኛ አምላክ ትልቅ ነህ
ስጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስህን ያገኛል
አሜን/3* ያገኛል
ለደረቀው አጥንቶች ደግሞም ህይወት ይሆናል
መንፈስህም ህይወት ይሆናል
ቤትህ በተራሮች ከፍ ብሎ ይታያል
አህዛብን ይሰበስባል
ስምህም አንድ ብቻ አንድ ሆኖ ይጠራል
በአለም ሁሉ ደምቆ ያበራል
ይሆናል/3* ቃልህ ይታመናል
ይሆናል ቃልህ ይታመናል
ልባችንም ዝሏል አንተን ይናፍቃል
የመንግስትህ መምጫ መቼ ነው ይልሃል
የክብርህን ከፍታ ቀርበን ምናይበት
ያውብ ቀን መቼ ነው ፊትህ ምናዜምበት
ወይ በምድር ካኖርከን ለአላማህም ብለህ
ለብዙ ስራህም ገንዘብ ልታደርገን
ለኋለኛው ዘመን የተባለውን መንፈስ
ሁሌ እንጠማለን መብረቅ እስክታወርድ
@ApoSon

🕎 በዘመናዊነት ማዕበል የማይናወጥ ክርስትና❕
ዘላለማዊ ዘመናዊነት የትኛው ነው❔
" በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ"(ፊልጵ 2:14-15)
ዘመናዊነት ምንድነው ?
ዘመናዊ (Modern ) የሚለው ቃል Modo ከሚለው ከላቲን የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አሁን ፣ የቅርብ ማለት ነው።
ዘመናዊነት ፈረንጆቹን መምሰል ነውን?
ወይም እነሱን መከተል ?
ወይስ ደግሞ የፈረንጆቹ ባሪያና ቅኝ ተገዥ መሆን? ዘመናዊነት የአውሮፓ የቴክኖሎጂ፣የአርት ፣የስነ ጽሁፍ ፣ የሳይንስና ሌሎች የማህበረሰብ ንቃት እድገት ከሆነ ከኢትዮጵያም ሆነ ከአፍሪካ ጋር እንዴት ይታያል? ደግሞ ወደ ክርስቲናው እንምጣና
አንድ ሰው ፣ ዘመናዊ ነው ፣ ዘመናይ ናት ፣ ስልጡን ነው ፣
የነቃ ነው የሚባለው ምን ሲሆን ነው? ከመካነ አእምሮ
(university ) የዕድሜውን ግማሽ ተምሮ በሚያማምሩ
የትምህርት ዘርፍ እስከ PHD ተከታታይ ድግሪዎችን
የጫነውን ነውን? ወይስ ደግሞ ሁልጊዜ ሱፊን ሽክ ብሎ
እንግሊዘኛ ቋንቋ ከአንደበቱ የማይጠፋውን ጸባዩ ሰናይ
ሽቅርቅር ሰውዬ ? ወይስ የዓለም የዜናዎችን ፣ ኳሶችን ፣
ፊልሞችን ፣ አዳዲስ መረጃዎችን እግር በግር እየተከታተለ ደረጃ
የሚመደበውን ድንቅ ሰው ? ወይስ በእንግሊዘኛ አክሰንት የሚያወራው የጸጉርና የአለባበስ ፋሽን የሚከተለው አራዳ ነኝ የሚለው ?
ወይስ ክርስትናዊ
ባህሌን እወዳለሁ አለቅም ብሎ ዛሬም እንደሐዋርያት በምስክርነት በአለባበስ በንግግር ማንነቱን በተገኘበት ሁሉ የሚለይ ራሱን የሚገልጥ?
ከአህዛብ ተለይተው ድንበሩን አውቆ ለቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ለሾማቸው የሚታዘዝ ነው? የቸገረውን ደስታውን ሆነ ጭንቀቱን ራሱንም ጭምር ለካህን የሚያሳይ ማን ነው ዘመናዊ? እኛ እንዲህ ነበርን በማለት በድሮው የሚመጻደቅ ? የቱ ነው ዘመናዊ ? አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት አፍሪካውያን ክርስትና ጥልቀቱ የሴንቲሜትር ነው ስፋቱ በማይል ነው የሚለካው ይላሉ። ስር አልሰደደም ብዛት ብቻ ማለታቸው ነው።
ዘመናዊ ትምህርት፣ ዘመናዊ አለባበስ፣ዘመናዊ አመጋገብ ፣ ዘመናዊ መስሪያ ቤት፣ዘመናዊ ሰው ዘመናዊ...ወዘተ እየተባለ በውጪ የሚነገረንና የምንተገብረው እውን ዘመናዊ
ነውን ? ከሆነ ለምን በሁሉም ነገር አለም እጆቿን ልምምዶቿን ማስገባት ጀመረች?
ዘመናዊነት በአፍሪካ ፈረንጆችን መምሰል ወይም መከተል ሳይሆን ባሪያ መሆን ነው ። መከተልና መምሰል ባሪያ ከመሆን ይሻላል የሚሉም አሉ ። " የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።"
(ሮሜ 12:2)
ዘመናዊነት የአውሮፖ ባህል ሲሆን በድህረ ዘመናዊነት(postmodernism ) እሳቤ ዘመናዊነት ኋላ ቀርነት ነው።
ስልጡንነትስ የኋላችንን ተቀብለን ፣ አሁናዊውን ዓለም ተገንዝበን የዓለምን አስተሳሰብ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ እየቀደሙ መሄድ ነው።
ተግባር የጎደለው የልብን እያደረጉ ጾም ጸሎት በቤተክርስቲያን ብቻውን መሰብሰብ አህዛብ ተግባር እና ልምምድ የሚጎመጀን ከሆነ የነገው ጥያቄ ውሰጥ ነው።
ለዚህ አንድ ገላጭ ያልኩትንና ከሰማሁት ምሳሌ ልጠቀም
"ድመት ዓለማዊነት አስጠላኝ ዓለም በቃኝ ብላ ገዳም ገብታ መሸገች ከዚያም አይጦች የድመት መጥፋት አሳሰበን ብለው ለመነጋገር ተሰበሰቡና እንደሚታወቀው ድመት ጠፍታለችና እንዲያውም ዓለም በቃኝ ብላ ገዳም ገብታለችና ያለችበት ሁኔታ ማጣራት አለብን ብለው ፍለጋውን ቀጥለው በአንድ ገዳም ውስጥ እንዳለች አንዲት አይጥ ታያትና ነፍስ አውጭኝ ሮጣ ወደ ዘመዶቿ ትደርሳለች። ከዚያ ምን ነው? ምን ሆንሽ? ድመትን አገኘሻት እንዴ ? ይሏታል። እሷም
"ኧረ ተውኝ ድመት ገዳም ገባች እንጂ አይኗን ጥፍሯም ጥርሷም ያው ነው።" ብላለች" አንዳንዴ በቤተክርስቲያን መግባታችን በቤተክርስቲያን መወለዳችን በስመ-ዘመናዊ የሚመጣብንን ተጽዕኖ ለመቃወም አቅም አይሆነንም። መቀየር ያለብን ማየት ያለብን ራሳችንን ውስጣችን እንጂ ያለንበት የተቀደሰ ስፍራውን አይደለም። ያልተቀየረ ማንነት የትም ቢኖር ታጥቦ ጭቃ ነው።
እኔ ምንም ያህል ባማረ ዕቃ ቢቀርብልኝ የተመረዘን ምግብ አልመገብም ማለት አለብን በቴክኖሎጂ ተሸፍኖ የመጣብንን የኃጢአት ግብዣ። ለዚህም የዮሴፍ እና የጵጢፋራ ምስት አጓጊ መርዝ ያለበት ግብዣ ዓይነተኛ አስረጂ ነው።
ያዕቆብ ከላባ ቤት ወደ አባቱ ወደ ወንድሙ ኤሳውጋ እየተመለሰ የያዕቆብ ልጅ ዲና የኤዊያዊ የሴኬም ከተማ ሰዎች ለማየት በወጣችበት በአገረገዢው ልጅ ተደፈረች ከነዓናውያንና ፌርዛዊያን ያልተገረዘ አህዛብ ስለነበሩ ያዕቆብንና ልጆቹን ምንም የክብር ካባ ብዛት የስጦታ ብዛት ለመስጠት ሰዎች ብለምኗቸውም አላሸነፋቸውም ማንነታቸውን በዕቃ አልቀየሩም ይልቁንስ ገደሉአቸው በዘበዙ እንጂ ተጠየፉ እንጂ
"ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው። ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት። ጋብቾችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፥ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ። ከእኛም ጋር ተቀመጡ፥ ምድሪቱም በፊታችሁ ናት፤ ኑሩባት፥ ነግዱም፥ ግዙአትም።"(ዘፍ 34:8-10)
" አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።"(1ኛ ጢሞ 6:11)
ኳሱ ፣ፊልሙ፣ቀልዱና ተረታተረቱ፣ አለባበሱና የስጋ አምሮቱ፣ በውበት መጠበቂያ ስም የሚደረጉ ዝባዝንኬው፣ መዝናኛውና ጫወታው የአለም ዝቃጭ ነገር የሚያጓጓው ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቤት ለዛሬ ይኖር ይሆናል አንድ እግር አንድ አይን ግማሽ ልብ ግማሽ ማንነት ውጪ ስላለ እስከመጨረሻው መጽናት አይችልም።
በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምግባር ራሱን እያነጸ በቤተክርስቲያን ስርዓት የተገነባውን ማንነት እግዚአብሔር ለቀባቸው ራሱን እያሳየ ዓለምንና ተግባሯን እየጸየፈ ለእግዚአብሔር መንግስት ራሱን የሚያዘጋጅ ወጣት እሱ በእውነት ዘላለማዊ ዘመናዊ ወጣት ነው። ማለቂያው መጨረሻው የለምና ወቅታዊም አይደለምና።
ክርስትናውም በዘመናዊነት ማዕበል አይናጋም አይናወጥም።
እግዚአብሔር ሁላችንም ይባርከን❕

ጦሩ የጦር ወሬው የምጥ ጣር ነው መጀመርያ
እርሃብ ቸነፈሩ ማሳያ ነው ማስጠንቀቅያ
አምልጥ ግባና ወደ መርከቡ
እያለ ጊዜ እያለ እድሉ
ባለማስተዋል ባለመንቃት
በጥፋት ውኃ እንዳትወሰድ
👉 https://youtu.be/mWgVZW2s4OA
እርሃብ ቸነፈሩ ማሳያ ነው ማስጠንቀቅያ
አምልጥ ግባና ወደ መርከቡ
እያለ ጊዜ እያለ እድሉ
ባለማስተዋል ባለመንቃት
በጥፋት ውኃ እንዳትወሰድ
👉 https://youtu.be/mWgVZW2s4OA
YouTube
አምልጥ ግባና ወደ መርከቡ | Bereket Desta | Apostolic church of Ethiopia
ጦሩ የጦር ወሬው የምጥ ጣር ነው መጀመርያ
እርሃብ ቸነፈሩ ማሳያ ነው ማስጠንቀቅያ
አምልጥ ግባና ወደ መርከቡ
እያለ ጊዜ እያለ እድሉ
ባለማስተዋል ባለመንቃት
በጥፋት ውኃ እንዳትወሰድ
“እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።”
መዝሙር 71፥22
ለወንድሞች እና እህቶችም ሼር በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እናደርጋቸው
🔴 Telegram:…
እርሃብ ቸነፈሩ ማሳያ ነው ማስጠንቀቅያ
አምልጥ ግባና ወደ መርከቡ
እያለ ጊዜ እያለ እድሉ
ባለማስተዋል ባለመንቃት
በጥፋት ውኃ እንዳትወሰድ
“እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።”
መዝሙር 71፥22
ለወንድሞች እና እህቶችም ሼር በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እናደርጋቸው
🔴 Telegram:…
Forwarded from ማራናታ.....MARANATHA😍 (Tade♥♥♥♥)
ግጥም፦ #የንጉስ_እልልታ
ባስቆጠቆጠችው የጽናት በትሬ
አስፈርውን ባህር ጥልቁን ተሻገሬ
በቅዱስ መቅደሱ በጽዮን መኖሬ
እኔን በጁ መዳፍ ስሙን በግንባሬ
ጸጋን ከማደሪያው መዝሙር በከንፈሬ
ባተመልኝ መንፈስ በባርኮቱ ዛሬ
እያሰማመረኝ ያለሁ በቅጥሬ
ጠላትን ማድቀቅያ መሳሪያዬ ያለኝ
በወይኑ አትክልት በእርሻው የመሰለኝ
ፍላጻን ወርዋሪ ቀስተኛ ያረገኝ
የእግዚአብሔር እስራኤል ናዝራዊ ልጁ ነኝ።
እንደ እምነቴ መጠን በልኬ ከአቅሜ
ለማይጠፋ ህይወት ተስፋና ፍጻሜ
በእግዚአብሔር ምህረት ለክብሩ መቆሜ
በሱ ተጀምሬ በሱ ተደምድሜ
መኖሪያዬ ጌታ ኢየሱስ ዘላለሜ
እያለኝ ማምለጫ የሚያውቀኝ በስሜ
መጻተኛ ሳለሁ ለምድር እንግዳ
ይህን ንጉስ ትቼ ያወጣኝን ከዕዳ
ማን እያየሁ ልጓዝ በዚህ ምድረ በዳ
በውሃው ላይ ቆሜ እንደ ቃሉ ስሄድ
እጅግ የሚያስፈራ የባህሩ ሞገድ
በአስደናቂ ፍጥነት ወደ እኔ ቢራመድ
ለመስመጥ ካልሆነ ከጥልቁ ገብቼ
እሱን ምን አሳየኝ የጠራኝን ትቼ
ብዙ ብያስከፍልም ብጠብም መንገዱ
ሳላሰለጠነኝ ስለመራኝ ክንዱ
ዛሬማ መልስ አለኝ ቢነሳ ሞገዱ።
የተፈረደልኝ የረታሁት እኔ
ሙግቴ ልያመጣ ከመጣ ዘመኔ
የምናገርበት ቋንቋዬ ልሳኔ
አለኝ ለፈተናው የተዋበ ቅኔ
ሳይሰለጥንብኝ ምክንያት ሰበቡ
በጠፊው ሳልጠፋ ኖሬ በመርከቡ
የተረፍኩት እኔ የሆንኩት ገንዘቡ
መልስ አለኝ በቅኔ ዛሬ ለወጀቡ
ለሚተራመሰው ለጊዜው ውዝግቡ።
ለሚነሳው አውሎ ድንገት ለሚነፍሰው
በገናን ይዤ ነው ለሱ የሚመልሰው
በፊቱ መጫወት ማሸብሸብ መዘመር
በጣፈጠ ዜማ ውዴን ማነጋገር
ሚስጥር ተምሬያለሁ በገና መደርደር
እንዳይሳካላት እንዳልሰጠው ፋንታ
የሚናወጥበት የጠላት ከፍታ
ድብቅ ጦር ጋሻዬ ምክሩን የሚፈታ
በአፌ ላይ ተገኝቷል #የንጉስ_እልልታ
✍ እ/ት እመቤት ገ/ማሪያም
ከናዝሬት
ከቆየ መልዕክት ጋዜጣ

የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነት ያገኝ ይሆንን?
ሉቃስ 18፥8
በዚህ ዘመን ፍጻሜ እግዚአብሔር በህይወታችን ሆነ በቤተክርስቲያን ታላላቅ ተአምራቶችን፣ ምልክቶችን፣ ድንቆችን ወዘተ.... እንዳይሰራ አለማመን እንቅፋት እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ በሰፊው እንደሚያስተምር በዚህ አምድ እንመለከታለን።
በሉቃ 18፥8 " ነገር ግን #የሰው_ልጅ_በመጣ_ጊዜ_በምድር_እምነትን_ያገኝ_ይሆንን?"ይላል። በተመሳሳይ በማር 6፥5-6 "በዚያም በድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም። ስለአለማመናቸው ተደነቀ" ይላል።
ከላይ ያሉት ጥቅሶች ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በሥጋው ሰውነት በተመላለሰበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ዳግም በሚመለስበትም ጊዜ በምድር (በሰዎች ዘንድ) እምነት በመጥፋቱ ወይም ባለመገኘቱ ብዙ ተአምራቶችን ከማድረግ የሚከለክል ክፉ እንቅፋት (ጠንቅ) መሆኑን ያስገነዝባል።
በእብ 11፥6 "ያለእምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንድሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና" ይላል። በእምነት የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ እግዚአብሔርን እጅግ ደስ የሚያሰኝና ትልቅ ዋጋም ከእርሱ እንደሚያስገኝልን ጥቅሱ ያስረዳል።
በማቴ 21፥21-22 " ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ እምነት ብኖራችሁ ባትጠራጠሩም በበለስቱ እንደሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ ተነቅለህ ወደ ባህር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁአላቸው" ይላል። እምነት ምን ያህል ትልቅ ሀይል እንዳለው ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ ያስተማረን ስሆን እጅግ የከበደብንና ከፊታችን አልወገድ ያለ ትልቅ መከራ ወይም ፈተና በእምነት ብንጸልይ ወዲያው መፍትሔ እንደሚናገኝበት ጥቅሱ ያስተምረናል
⚛ እምነት አስፈላጊ የሚሆነባቸውን ሶስት መሠረታዊ ምክንያቶችን ከዚህ ቀጥለን በቀጣይ ክፍል ላይ በዝርዝር እንመለከታለን።
..... ይቀጥላል.........
በማራናታ ቻናል ላይ ይጠብቁን
ሊንካችን፦ @MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
የውይይት ግሩፓችን፦ @marantawoch
Comment bot @Taddyapostolic

የትኛው ዘር ነህ/ሺ
የዘር አይነቶች
የእግዚአብሔር ቃል የዘርን ጉዳይ ሲዘረዝር በልዩ ልዩ አይነት ሁኔታ ያስቀምጣቸዋል፡ እያንዳንዱም ዘር የተገኘበትን ማንነት ይገልጻል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር አንድ ዘር አድርጎ ነበር የፈጠራቸው፡፡ ነገር ግን ሁኔታዎች አንድ ዘር መሆናቸውን በመቀየር የተለያዩ ዘሮች እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
አሁን የምናየው አራት አይነት ዘሮችን ነው፤
1ኛ. የአዳምና የሔዋን ዘር
2ኛ. የሔዋን ዘር
3ኛ. የሰይጣን ዘር
4ኛ. የእግዚአብሔር ዘር
1. የአዳምና የሔዋን ዘር
በዘፍ 1፡28 ”...ብዙ ተባዙ፡ ምድርን ሙሉኣት...”
ይህ ዘር ለመጀመሪያ ጊዜ የተነገረው እግዚእብሔር ሰውን ከፈጠረ በኃላ ብዙ ተባዙ ብሎ የአዳምንና የሔዋንን ዘር ሲባርካቸው ነው፡፡ ይህም የዘር አይነት እስከ አሁን አዳም ዘሩ የሚበዛበት ወይም የሚወለድበት አንድ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ከአዳምና ከሔዋን ማለት ከሴትና ከወንድ የሚወለዱ ሁሉ እነርሱ የአዳምና የሔዋን ዘሮች፡፡
ዘፍ 5፡1-5 ”...ወንዶችንም ሴቶችንም ልጀጆች ወለደ...”
2. የሔዋን ዘር
በዘፍ 3፡15 ”...በአንተና በሴቲቱ መካከል፡ በዘርህና በዘሯም መካከል ጠላትነትን አደርጋለው፡፡ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፡ አንተ ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ...”
ከውድቀት በኃላ እንደገና ስለ ዘር አንስቶ የተስፋ ቃል ሲገባ የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው፡፡ ከውድቀት በፊት ከአዳምና ከሔዋን የሆነ ዘርን ነበር እግዚአብሔር የገባው፡ አሁን ግን ከሴቲቷ ከሔዋን ብቻ የሆነ ዘርን ነው የገለፀው፡፡
በዘፍ 3፡15 ላይ ያለው ዘር ከሴቷ ብቻ የሆነ የሴቷ ዘር ነው፡፡ይህም የወንድ ዘር ንክኪ የሌለው ከሴቷ ብቻ የሆነ ዘር ነው፡፡ ይህም ዘር በመንፈስ ቅዱስ ድንቅ አሰራር የሴቷን የማህፀን ፍሬ በመባረክ አዲስ ዘር፤ ሰይጣንን የሚቀጠቅጥ ዘር እንደሆነ ይገልፃል፡፡
ሉቃ 1፡42 ”...ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፡ የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡”
ሉቃ 1፡30-35 ”...ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡”
ሉቃ 2፡6 ”...የበኩር ልጇን ወለደች...”
3. የሰይጣን ዘር
ዘፍ 3፡15 ”...በዘርህና በዘሯ መካከል...” ሰይጣን ዘር አለው ወይ? ብለን ብንጠይቅ ወይም ብናስብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ የሰይጣን ዘር በማለት ሰይጣን ዘር እንዳለው ይገልጻል፡፡ የሰይጣን ዘር ብለን እንደ ሰው ዘር አይነት የምናስብ ከሆነ እንስታለን፡ ነገርግን የዘሮችን አይነት ባስቀመጠበት መንገድ ግን ብንረዳ ወደ እግዚአብሔር ሃሳብ እንደርሳለን፡፡ የሰይጣን ዘሮች የተባሉት ሰይጣን ከመውደቁ በፊት የእግዚአብሔር መልአክ እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ነገር ግን ራሱን ከፍ በማድረጉ እንደወደቀና እንደተጣለ፡ ከዚያም ክፉ መንፈስ ሰይጣን እንደተባለ ይገልጻል፡፡ ሰይጣን በሳተ ሰዓት እርሱ ብቻውን አልነበረም፡፡ የወደቀው በክፋቱ የእርሱ የክፋት ዘር ያደረጋቸው የመልአኮችን ሲሶ (አንድ ሶስተኛ) ነበር፡፡ ሰይጣን የእርሱን ክፋት በሌሎች መልአኮች ላይ በመዝራት የእርሱ ውላጅ ዘር ሆነዋል፡በክፋቱ ቃል ወልዷቸዋል፡፡ ሰይጣን ብዙ መልአኮችን በማሳሳት የእርሱ ዘር አድርጓቸዋል፤ ሰይጣን ዘሩ የክፋት እንክርዳድ ነው፡፡ ይህንንም በመላእክት እንኳ በመዝራት በእርሱ የክፋት ዘር በመውደቅ የዲያቢሎስ ዘር ሆነዋል፡፡
ሁለተኛ የሰይጣን ዘር የተባሉት በሰይጣን ዘር የተወለዱ፡ የእርሱ መገልገያ የሆኑትን ሰዎች ነው፡፡ ማቴ 13፡39 ”...እንክርዳዱ የክፉ ልጆች ናቸው፡ የዘራውም ጠላት ዲያቢሎስ ነው፡፡” የእግዚአብሔር ቃል በብዙ የሚያስተምረን ነገር ሰይጣን ሰውን በክፋት ቃል እንደሚወልዳቸውና የእርሱ የክፋት ዘሮች/ልጆች/ እንደሚያደርጋቸው ነው፡፡ ይህንንም ዘር እንክርዳድ በማለት ይገልፀዋል፡፡ እየሱስ፡ ”ጠላት መጥቶ እንክርዳድ ዘራ” ይላል፡፡ ከዚህ ቃል የምናስተውለው ሰይጣን በክፋቱ/በእንክርዳዱ/ የወለዳቸው ልጆች/ዘሮች/ አሉት፡፡
ዮሐ 8፡41-44 ”...እናንተ የአባታችሁን ስራ ታደርጋላችሁ...እናንተ ከአባታችሁ ከዲያቢሎስ ናችሁ፤የአባታችሁን ምኞት ልታደርጉ ትወድዳላችሁ፡፡” እየሱስ እናንተ ከአባታችሁ ከዲያቢሎስ ናችሁ ሲል ተናግሯል፡፡ የዲያቢሎስ ልጆች የሚላቸው በእርሱ የክፋት ዘር የተወለዱትን ሁሉ ነው፡፡
1ዮሐ 3፡10 ”...የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያቢሎስ ልጆች በዚህ የተገለፁ ናቸው፡፡” ስለዚህ ሰይጣን ዘር አለው ወይ ለሚሉ ‹አዎን አለው፤ በክፋቱ እንክርዳድ የወለዳቸው መልአኮችም ሰዎችም አሉ›፡፡ አሁንም እንኳ ሰይጣን በእንክርዳዱ ብዙ ሰዎችን እየወለደ ነው፡፡
እየሱስ በስጋ ተገልጦ የሰይጣንን ራስ ሲቀጠቅጥ፣ሰይጣንም በክፋት ዘሩ በወለዳቸው ሰዎች ተገልጦ ሰኮናውን ይቀጠቅጣል፡፡ ይሁዳ የዲያቢሎስን ሃሳብ በመፈፀም እንደልጅ እያገለገለ ነበር፡ በዚህም ምክንያት የዲያቢሎስ ልጅ ተብሏል፡ አልፎም ዲያቢሎስ ተብሏል፡፡
4. የእግዚአብሔር ዘር
አዲሱን የሰው ዘር ሲናገር ውልደቱና ዘሩ በከእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹እግዚአብሔር ዘር አለው ወይ?› ብለው ለሚጠይቁ አሁንም መልሳችን ‹አዎን ነው›፡፡ ይህንን ዘር የሚረዱ መንፈሳውያን ብቻ ናቸው፡፡
1ጴጥ 1፡23-25 ”ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፡በህያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ፡፡”
የእግዚአብሔር ዘሮች በእግዚአብሔር ቃል የተወለዱ ናቸው፡ እነዚህ የማይጠፋ የቃል ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህ ዘሮች ከሰይጣን ዘሮች የተለዩ ናቸው፤ ከስጋና ደም ዘሮች/ልጆች/ የተለዩ ናቸው፤እነዚህ ዘሮች ከሴቷ ዘር ከክርስቶስ ጋር አንድ ዘሮች ናቸው፤ የማይጠፋ ዘሮች ለዘላለም የሚኖሩ የእግዚአብሔር የቃል ልጆች ናቸው፡፡
ከስጋ ዘር ስንወለድ ሥጋ እንሆናለን ዮሐ3፡3-6
ከሰይጣን እንክርዳድ ዘር ሰዎች ሲወለዱ የክፉ ዘሮች ይሆናሉ ዮሐ 8፡44
በእግዚአብሔር ቃል ስንወለድ የእግዚአብሔር ልጆች፤የማይጠፋው ዘር እንሆናለን 1ጴጥ1፡23-25፣ ዮሐ1፡13
ዘፍ 3፡15 ”...በዘርህና በዘሯ መካከል ጠላትነትን አደርጋለው፡እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፡አንተ ሰኮናውን ት
ወደማይጠፋው ዘር ናናናናናናና!!!!!!

ቀጠቅጣለህ”
የየትኛው ዘር ነህ?
የስንዴው (የእየሱስ)፣ የእንክርዳዱ (የሰይጣን
)፣ የስጋና ደም (ፍጥረታዊ)? ወደማይጠፋው ዘር ናናናናናናና!!!!!!
@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH