አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ
3.6K subscribers
618 photos
6 videos
81 files
84 links
Official Arbaminch University ®
ማስታወቂያዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት!
ሀሳቦች እና እንዲተላለፍላችሁ የምትፈጉት ነገር ካለ በ
@newneway
@firaK19
@miko1122
@ADA1249
ላይ ያግኙን፡፡
AMU Info ......
እውነተኛ እና ፈጣን መረጃ ይደርሶታል፡፡
።።ከተማሪ ለተማሪ።።:
Arba_Minch_university
Download Telegram
COVID-19 Digital Awareness Program

The whole world is going through the toughest times of the century. The pandemic has brought the entire world upside down. No one claims itself to be indisposed; the pandemic has affected each and every person’s life in one or the other way irrespective of caste, creed, race, geographic boundaries, or economic status. The coronavirus has infected 27 million people and the death toll is reaching near to 1 million, with such an exponential growth rate every day is coming with a greater challenge.
Looking at the gravity of the situation it becomes religiously significant to control the contagious disease and it is only possible through spreading the right knowledge in the society until the vaccine is developed. COVID 19 has changed our lives and our way of living. In this new restricted way of living, there are some strict do’s and don’ts prescribed by doctors, scientists, and world health organization; our digital awareness program revolves around those standards and guidelines. It aims at disseminating awareness about the disease and mitigating the potential risk.
Be the part of this campaign “Digital War against CORONA” by participating in this certification program by Arba Minch University. Create awareness to save lives!
Communication Affairs Directorate

@amucampus
@amucampus
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Infectious Diseases›› 3ኛ ዲግሪና በ ‹‹Bio-Medical Sciences›› 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ሊከፍት ነው

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል በ‹‹Infectious Diseases›› 3ኛ ዲግሪ እንዲሁም በ ‹‹Bio-Medical Sciences›› 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የሚያስችለውን የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ አካሂዷል፡፡ 
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው እንደ ምርምር ዩኒቨርሲቲ ባስቀመጠው ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች እያስፋፋ ሲሆን በዚህም እንደ ሀገር የተሰጠውን ጥራትና ብቃት ያላቸውን ከፍተኛ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎችን ለሀገሪቱ ማበረከቱን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ሥርዓተ-ትምህርቶቹ ለውጭ ግምገማ ከመቅረባቸው በፊት የተለያዩ ሂደቶችን ማለፋቸውን የተናገሩት ዶ/ር የቻለ ፕሮግራሞቹ ሌሎች አስፈላጊ ሂደቶችን በተጨማሪ አልፈው ተማሪ በመቀበል የማስተማር ሥራ እንዲጀመር ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል፡፡
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ፈቃዱ ማሴቦ በበኩላቸው ኮሌጁ ፕሮግራሞቹን ለመጀመር የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መቆየቱን ጠቁመው በኮሌጁ ፕሮግራሞቹን ለማስጀመር የሚያስችል በቂ የሰው ኃይል እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በዘርፎቹ የሚመረቁ ተማሪዎችም በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተፈላጊ መሆናቸውን በተደረገው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማረጋገጥ ሥርዓተ-ትምህርቶቹ አስፈላጊ ሂደቶችን እንዲልያፉ ተደርጎ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማስተማር እንጀምራለን ብለዋል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን እያደረጉ ሥርዓተ-ትምህርቶቹን ላዘጋጁ ኮሚቴዎችና የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን በ 21 የ3ኛ፣ በ 99 የ2ኛ እና በ 78 የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች በማስተማርና በማሠልጠን አገራዊ ልማትና ዕድገት እንዲረጋገጥ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


@amucampus
@amucampus
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2013 የት/ዘመን በህክምናና ጤናው ዘርፍ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ሊከፍት ነው

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ<<Public Health Nutrition>> እና በ<<Clinical Bio-Chemistry>> የ2ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ መስከረም 7/2013 ዓ/ም አካሂዷል፡፡
የአካዳሚክ ጉ/ም/ፕሬዝደንት ተወካይ ዶ/ር ንጉሴ ታደገ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ እንደ ሀገር ከተለዩ 8 የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል መሆኑን አስታውሰው መሰል የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች መከፈታቸው ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ ከማድረግ አንፃር ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚከፈቱ አዳዲስና ነባር የትምህርት ፕሮግራሞችን ጥራት ለማረጋገጥም በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺይፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ሽብሩ በበኩላቸው ሥርዓተ-ትምህርቶቹ የውስጥ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ሂደቶችን ማለፋቸው ገልፀዋል፡፡ ሁለቱም ፕሮግራሞች ያላቸውን ተገቢነትና የገበያ ፍላጎት ለማወቅ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መደረጉን የጠቆሙት ዶ/ር ታምሩ በሁለቱም የትምህርት መስኮች እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት እንዳለ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ ለአብነትም እንደ ሀገር ያለን የሥነ-ምግብ ባለሙያዎች 1600 ብቻ መሆኑ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮግራሞቹ ከዚህ በኋላ የሚቀሩ ሂደቶችን ካለፉ በኋላ ተማሪ በመቀበል የማስተማር ሥራ ይጀመራል ያሉት ዶ/ር ታምሩ ፕሮግራሞቹን ለማስጀመር የሚያስችል በቂ የሰው ኃይልና የቤተ-ሙከራ ግብዓት በዩኒቨርሲቲው መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ አክለውም የኮሮና ቫይረስ አጠቃላይ ዓለምንና ሀገራችንን እየፈተነ በሚገኝበት ወቅት ከሥርዓተ-ትምህርቶቹ ዝግጅት ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ለተሳተፉ መምህራንና የሥራ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በሥርዓተ-ትምህርት ግምገማው ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት የመጡ 4 የዘርፉ ምሁራን የተገኙ ሲሆን የሁለቱም ፕሮግራሞች መከፈት እንደ ሀገር በዘርፎቹ የሚስተዋለውን የሰው ኃይል ዕጥረት ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱ ገልፀው በሥርዓተ-ትምህርቶቹ ላይ ሊጨመሩና ሊቀነሱ ይገባቸዋል ያሉዋቸውን ነጥቦች አቅርበዋል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


@amucampus
@amucampus
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ የሚገኘውን የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ የሚገኘውን የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታን በ2013 በጀት ዓመት በከፊል ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደት በጎበኙበት ወቅት ተገልጿል፡፡
በ2007 ዓ/ም የተጀመረው የሆስፒታሉ ግንባታ በዲዛይን ማስተካከያና ተጨማሪ ግንባታ፣ በሆስፒታሉ ግንባታ ቦታ ተነሺዎች፣ የክፍያዎች መዘገየት፣ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት፣ በግንባታ አካባቢ የሚገኙ የመብራት፣ የውሃና የስልክ መስመሮች እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ የዘገየ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት 77 በመቶ የግንባታ ሂደት መጠናቀቁ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡ 
የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን የሆስፒታሉ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ካደረጉ ምክንያቶች ከዲዛይን ጋር ተያይዘው የነበሩ ችግሮች መሠረታዊና ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል፡፡ አሁን ባለው የግንባታ ሂደት ሆስፒታሉን በ2013 በጀት ዓመት በከፊል ወደ ሥራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መድረሱን የተናገሩት ወ/ሮ ታሪኳ በግንባታ ሂደት ወስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የኤሌክትሮ-ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ ከአሳንሳር በስተቀር ወደ ሀገር ወስጥ በመግባታቸው የመገጣጠም ሥራውም እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታሉን በ2013 በጀት ዓመት ወደ ሥራ ለማስገባት በትኩረት እንደሚሠራ ገልፀው የግንባታ ሂደቱን ለመጠናቅቅ ይረዳ ዘንድ ከተነሺ ግለሰቦችና መነሳት ያለባቸው የውኃ፣ የስልክና የመብራት መስመሮችን ለማንሳት ክፍያ ስለተፈፀመ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡ የግንባታ ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላ ሆስፒታሉን በተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች ማሟላት ትልቅ ተግባር መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ዳምጠው ለዚህም ዩኒቨርሲቲው የህክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ኮሚቴ አዋቅሮ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የሆስፒታሉን መጠናቀቅ የአካባቢው ማኅበረሰብም ጭምር በጉጉት የሚጠብቀው በመሆኑ የግንባታ ሂደቱ ያለበት ሁኔታ የሚበረታታ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ወስጥ አጠናቆ ሆስፒታሉን ሥራ ለማስጀመር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
ይርጋለም ኮንስትራክሽን በተሰኘ የግንባታ ተቋራጭ ከ970 ሚሊየን ብር በላይ በጀት እየተገነባ የሚገኘው የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል 575 የታካሚ አልጋዎች ያሉት ግዙፍ ሆስፒታል ሲሆን የግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅ ከመማር ማስተማርና የምርምር ሥራዎች ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ሆስፒታሉ ሲጠናቀቅ የሕክምና ትምህርት ቤትን በመያዝ 7ኛው የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል፡፡
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት


@amucampus
@amucampus
ለ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ መስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ,አደረሰን !

በዓሉ የመተሳሰብ ,የሰላም ,የአንድነት ,የፍቅር , የይቅርታ ይሆን ዘንድ እንመኛለን !

መልካም አውዳመት !
@amucampus
@amucampus
ትምህርት ሚኒስቴር ለ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች 450 ሺህ ታብሌቶችን ሊሰጥ ነው!

- ትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠውን የ2012 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ለማከናወን ለተፈታኞቹ 450 ሺ ገደማ ታብሌት ኮምፒውተሮችን እንደሚሰጥ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

- በአገሪቱ ያለውን የኢንተርኔት ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባትም በራሱ ሳተላይት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ኢንተርኔት ግንኙነት ለመፍጠር መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ገልፀዋል፡፡

- ምዝገባው የሚደረገው በኦንላይን ሲሆን ከፈተናው በፊት ተፈታኞቹ የ45 ቀናት ትምህርትና የቴክኖሎጂ መመሪያ እንዲወስዱ ይደረጋል ሲሉ አስታውሰዋል፡፡
ም፡-ካፒታል ጋዜጣ


@amucampus
@amucampus
የመግቢያ ፈተና ጊዜ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ባሳወቅነው ማስታወቂያ የመግቢያ ፈተና ጊዜ ወደ ፊት እንደሚገለፅ የተነገረ ሲሆን በዚሁ መሠረት ለሁሉም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው በድህረ ምረቃ ት/ቤት ሕንፃ መስከረም 25/2013 ዓ/ም ከሰዓት ከ08፡00 ጀምሮ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@amucampus
@amucampus
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ለዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡
የአመልካቾች ትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Curriculum vitae (CV)

የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት አንድ ፎቶ ኮፒ፤

የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ፤

በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ፤

በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ፤

በዩኒቨርሲቲው በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡

ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ከመስከረም 18-29/2013 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል፡፡
የአርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ


@amucampus
@amucampus
የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ ይደረግላቸዋል በሚል የተሰራጨው ዜና ስህተት መሆኑ ተገለፀ፡፡

ከሰሞኑ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችን የተሳተፉባቸው ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡

በዋናነት በጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ እንዲሁም በጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት የተካሔዱ ውይይቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የ2013 ዓ.ም ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ የመከረው ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላቸው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መገለፁን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ተሰምቷል።

ይሁን እንጂ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው የባህርዳር ፤ የድሬደዋ እና የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች ባለፈው ሳምንት የ45 ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በጅማ ሲያካሂዱት በቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቻችሁን ተቀበሉ የሚል አቅጣጫ አለመቀመጡን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ ይደረግላቸዋል የሚለው ዜና ከመሰራጨቱ በፊት በጊዜ ገደቡ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንዲጠሩ የተቀመጠ አቅጣጫ ሳይኖር መረጃውን ለምን ማሰራጨት አስፈለገ ስንል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ እንደገለፁት በወቅቱ በነበረው ውይይት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ስህተት ነው ብለዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በምክረ ሀሳብ ደረጃ የተነሳ እንጂ ውሳኔ ላይ ያልተደረሰበት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በሰዓቱ የተገኙ ሚዲያዎች የተሳታፊዎችን ሀሳብ በመውሰድ በስህተት የዘገቡት መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ትምህርት ማስጀመርን በተመለከተ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ የተሰጠ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ደቻሳ ከዛሬ ጀምሮ ይህንን የሚገመግም ቡድን እናሰማራለን ብለዋል፡፡

ቡድኑ አጠቃላይ የግምገማ ሪፖርቱን እንዳደረሰን እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን የሚጠራበትን ጊዜ ወደ ፊት እናሳውቃለን በማለት ተናግረዋል፡፡

Via:- Ethio FM

@amucampus
@amucampus
የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ ዝግጅት የሚያረጋግጡ 11 ተቆጣጣሪ ኮሚቴዎች ሥራቸውን ጀምረዋል!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የቅበላ ዝግጅት የሚያረጋግጥ 11 ተቆጣጣሪ ኮሚቴዎች የዩኒቨርሲቲዎችን ዝግጅት ለማረጋገጥ ከትላንት ጀምሮ መሰማራቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ተቋማቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከግምት ያስገባ ዝግጅት አድርገው በቀጣዩ ወር ተማሪዎችን የሚጠሩበትን ቀን ያሳውቃሉ ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለኢዜአ ገልጸዋል።

የተቋማቱ የኮሮና ቫይረስን እየተከላከሉ የሚያስተምሩበትን ሁኔታ መፍጠራቸውን ኮሚቴዎቹ ካረጋገጡ በኋላ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ ፕሮግራማቸውን ይፋ ያደርጋሉ ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ትምህርት የሚመለሱበት ቀን እስካሁን እንዳልተወሰነ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ከተቋማቱ የተማሪዎች ቅበላ ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎች ምንጮች የሚሰራጨው መረጃ ስህተት እንደሆነ ገልጸዋል።
ም፡-ከተተዌሳ

@amucampus
@amucampus
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የቅበላ ዝግጅት ለማረጋገጥ የተሰማራው 11 አባላት ያሉት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የዩኒቨርስቲዎችን ዝግጁነት ካረጋገጠ በኋላ ተማሪዎቻቸውን የሚጠሩ ይሆናል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል።

- የተቋቋመው ኮሚቴ ከመሰረተ ልማት አኳያ ተማሪዎች የመኝታ፣ የውሃ፣ የመፀዳጃና መሰል የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ዝግጅቶች ላይ ትኩረት ያደርጋል።

- ቫይረሱን መከላከያ መመሪያዎችን የሚያስተገብሩ የተቋማቱ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት መሟላታቸውን ኮሚቴው ከግምት ውስጥ ያስገባል።

- ዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው አቅምና ዝግጁነት ልክ ተመራቂ ተማሪዎችን አስቀድመው ሌሎች ተማሪዎች የሚጠሩበት ሁኔታ ይመቻቻል ይህም ተማሪዎቹ በመማሪያ ክፍልም ይሁን በሌሎች መገልገያ ቦታዎች እንዳይጨናነቁ ያደርጋል

- በአንድ ማደሪያ ክፍል ውስጥ እስከ ሶስት ተማሪዎች እንደሚኖሩም ገልጸዋል።

- ተቋማቱ ካለፉት ዓመታት በመማር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታን ለመፍጠር ያደረጉት ዝግጅትም ከግምት ውስጥ እንደሚገባም አስረድተዋል።

@amucampus
@amucampus
እውነት ወንድማችንን ልንረዳው ይገባል

ግዛቸው ትኩ ይባላል በቅርቡ ከአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። አባቱ በህይወት ባይኖሩም፣ እናቱ የምትችለውን ሁሉ ዋጋ ከፍላ ልጇን ከሰው እኩል አድርጋ የዩንቨርሲቲ ትምህርቱን አስጨርሳዋለች።

እናቱን ለማገዝ ስራ ሳይንቅ ሳይመርጥ ያገኘውን ሰርቶ ቤተሰቦቹንና እናቱን ለመደገፍ የወሰነው ወጣት ግዛቸው፣ በማህበር ተደራጅቶ ኮብል ስቶን የማንጠፍ ስራ ጀምሮ ነበር። እስከ ቅርብ ጊዜ ሁሉም ነገር ሰላም ነበር።

ግዛቸው በድንገት አሞት ለህክምና በሄደበት ወቅት፣ ሁለቱም ኩላሊቶቹ አገልግሎት ማቆማቸውን እና በአስቸኳይ ዲያሊስስ እንዲጀምርና፣ በቅርቡም ውጭ ሀገር ሂዶ ንቅለ-ተከላ ማድረግ እንዳለበት በሃኪሞች ተነግሮታል።

የዚህን ብርቱ ወጣት ህይወት ለመታደግ፣ የምትችሉትን ለማገዝ እንዲመችም በሶስት ባንኮች በስሙ አካውንት ተከፍቶለታል።

ንግድ ባንክ 1000345116145
ዳሽን ባንክ 5222 196 435 011
አዋሽ 01320834382901

@amucampus
@amucampus
ሼር ሼር ሼር ...
# አስቸኳይ_የእርዳታ_ጥሪ !
ለሁሉም ሰው ለሆነ ሁሉ....
እናት ልጇ ደርሶላት በመጦሪያዋ # ፈተና ተጋፍጦባታል። በድህነት ያሳደገችውን ጧሪ ልጇን የኩላሊት ህመም አልጋ ላይ አውሎባታል።
ወጣቱ # ግዛቸው_ትኩ ይባላል። በሰሜን ወሎ ወልድያ ከተማ ተወልዶ ያደገ ልጅ ነው። በቅርቡም ከአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። አባቱ በህይወት ባይኖሩም፣ እናቱ የምትችለውን ሁሉ ዋጋ ከፍላ ልጇን ከሰው እኩል አድርጋ የዩንቨርሲቲ ትምህርቱን አስጨርሳዋለች። እናቱን ለማገዝ ስራ ሳይንቅ ሳይመርጥ ያገኘውን ሰርቶ ቤተሰቦቹንና እናቱን ለመደገፍ የወሰነው ወጣት ግዛቸው፣ በማህበር ተደራጅቶ ኮብል ስቶን የማንጠፍ ስራ ጀምሮ ነበር። እስከ ቅርብ ጊዜ ሁሉም ነገር ሰላም ነበር።
በድንገት የተፈጠረው ነገር ግን የሁላችንንም ቅስም ሰብሮታል። ግዛቸው በድንገት አሞት ለህክምና በሆደበት ወቅት፣ ሁለቱም ኩላሊቶቹ አገልግሎት ማቆማቸውን እና በአስቸኳይ ዲያሊስስ እንዲጀምርና፣ በቅርቡም ውጭ ሀገር ሂዶ ንቅለ-ተከላ ማድረግ እንዳለበት በሃኪሞች ተረጋገጠ።
በአሁኑ ወቅት የግዛቸውን ህይወት የመታደጉ ስራ ዲያሊስስ በማድረግ ተጀምሯል። ነገር ግን ይሄ ጊዜያዊ መፍትሄ ብቻ ነው። ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ከሀኪሞች ተረድተናል። ይሄን ለማድረግ ደግሞ ወጣቱም ሆነ ቤተሰቦቹ አቅም የላቸውም። የሁላችንንም እርዳታ ይፈልጋሉ።
ዛሬም ስለ #እናት እና ገና ብዙ መኖር ስላልጀመረው ወጣት ግዛቸው ስንል እጃችን ልንዘረጋላቸው ይገባል።
የዚህን ብርቱ ወጣት ህይወት ለመታደግ፣ የምትችሉትን ለማገዝ እንዲመችም በሶስት ባንኮች አካውንት ተከፍቶለታል። ከታች ያሉ አካውንቶችን ተጠቅመን ለህሊናችን ሰላም፣ ለነፍሳችንም በጎ ስንቅ እናኖር ዘንድ እለምናችኋለሁ።
# ዳሽን_ባንክ ➙ 5222 196 435 011
#አርባምንጭ_ዩኒቨርስቲ

↘️ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣ ልዑካን ቡድን በ25/13 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበልና የመማር ማስተማሩን ለማስቀጠል ያለውን የዝግጅት ስራ ገምግሟል፡፡

↘️ዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቶችን እያካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህም የተመራቂ ተማሪዎች ዶርም ድልድል የኮሮና መከላከል ፕሮቶኮልን በተከተለ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን ሌሎች የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያግዙ መሰረተ-ልማቶችና ለኮሮና መከላከል የሚያግዙ ግብዓቶች በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡

↘️በዩኒቨርሲቲው በኩል የዝግጅት ምዕራፎችን በማጠናቀቅ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባረጋገጠለት መሰረት ተመራቂ ተማሪዎችን የሚጠራ ይሆናል፡፡

©FanaNews

@amucampus
የመግቢያ ፈተና ጊዜ ማስታወቂያ (ለ3ኛ ጊዜ በድጋሚ የወጣ)

ለድህረ ምረቃ አዲስ አመልካቾች በሙሉ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
መስከረም 30 ዕለተ ቅዳሜ 2013 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ፈተናው የሥራ ቀናት ላይ እንዲሆን ከተለያዩ አመልካቾች ጥያቄ በቀረበው መሠረትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ፈተናው ለ3ኛ ጊዜ ለጥቅምት 09 ዕለተ ሰኞ 2013 ዓ/ም የተዛወረ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን፡፡
በዚህም መሠረት ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀን የግብርና፣ የሕክምናና ጤና እንዲሁም የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ዘርፎች ተፈታኞች በኩልፎ፣ ነጭ ሣርና ዓባያ ካምፓሶች እንዲሁም በቀሩት ዘርፎች የምትፈተኑ በዋናው ግቢ የድኅረ ምረቃ ት/ቤት ሕንፃ ከጥዋቱ 03፡00 ጀምሮ በተዘጋጁ የመፈተኛ አዳራሾች በመገኘት እንድትፈተኑ እናሳውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
 

@amucampus
@amucampus
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፀደቀ

የዩኒቨርሲቲው ካውንስል መስከረም 20/2013 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የ2013 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ አፅድቋል፡፡ ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ለመደበኛ እና ለካፒታል በድምሩ ብር 1,594,367,000 ተመድቧል፡፡ 
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እንደተናገሩት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዕውቀት፣ በክሂሎት፣ በአመለካከት እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ታግዘው ጥናትና ምርምር በማካሄድ ለእውናዊው ዓለም ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ መስጠት የሚችሉና በመልካም አስተሳሰብ የዳበሩ ዜጎችን የመቅረጽ ተልዕኮ አንግበው ይሠራሉ፡፡ በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፎች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ዶ/ር ዳምጠው አሳስበዋል፡፡
የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝ/ት/ግ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስፋው ደምሴ በበኩላቸው የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድን ለማሳካት ተቋማዊ አደረጃጀት፣ ግብዓትና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ የመሠረታዊ አሠራር ለውጥና የሚዛናዊ ውጤት ተኮር ሥርዓትን ለመተግበር የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶ የሚተገበር ሲሆን አፈጻጸሙንም በየሩብ ዓመቱ በመገምገም ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በመማር ማስተማር በተለያዩ የሙያ መስኮች በቅድመ ምረቃ በመደበኛ የትምህርት መርሃ-ግብር 76 እና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት መርሃ-ግብር 38 ፕሮግራሞች፣ በ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በመደበኛ የትምህርት መርሃ-ግብር ከ99 ወደ 102 እና በመደበኛ ባልሆነ የትምህርት መርሃ-ግብር ከ29 ወደ 31 ለማሳደግ ታቅዷል፡፡ እንዲሁም በ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር ከ22 ወደ 24 ለማሳደግ መታቀዱን አቶ አስፋው ገልጸዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ በመማር ማስተማር ዘርፍ ክትትል ቤተ-ሙከራዎች፣ ወርክሾፖች፣ ኮምፒውተር ቤተ-ሙከራዎችና ቤተ-መጻሕፍት ደረጃቸውን መጠበቃቸውን ማረጋገጥ፣ የትምህርት ግብዓቶች እንዲሟሉ ማድረግ፣ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ሥራዎችን ማከናወን፣ የልየታና የልኅቀት ሥራዎችን የሚመራ ኮሚቴ ማቋቋም፣ BSC ዕቅድን እስከ መምህራን ድረስ አውርዶ በመፈራረም ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረግ፣ የድኅረ-ምረቃና የተከታታይና ርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች በዕቅዱ መሠረት እንዲተገበሩ ማድረግ፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲው በኃላፊነት የተሰጠውን የቅድመ ምረቃ የውሃ ፕሮግራሞች የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በማጠናቀቅ ማስረከብና የበይነ-መረብ ትምህርትን ከፊት-ለፊት መማር-ማስተማር ጋር አቀናጅቶ ለመሥራት ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ኮሚቴ በማዋቀር መመሪያ ማዘጋጀት በበጀት ዓመቱ ለማከናወን ከታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
አቶ አስፋው ባቀረቡት ሪፖርት አንደተመለከተው ማለቅ ሲገባቸው ያላለቁ ፕሮጀክቶችን ክትትል ማድረግና በሚጠናቀቁበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ በኮቪድ ዙሪያ እየተሠሩ ያሉ የምርምርና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን በመደገፍ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እንዲቻል መሥራት፣ እየተገባደዱ ያሉ የማኅበረሰብ ፕሮጀክቶችን ለባለድርሻ አካላት ማስተላለፍ፣ የበጎ አድራጎት፣ የማዕድ ማጋራት፣ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማስፈፀሚያ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ መሥራት እንዲሁም የምርምርና የማኅበረሰብ ፕሮግራም በጀቶችን ለኮሌጆችና ለምርምር ማዕከላት
መደልደልና በጀቱን ማውረድ በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በ2013 በጀት ዓመት ለማከናወን ከታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በዩኒቨርሲቲው በበጀት ዓመቱ መደበኛ በጀት ብር 1,144,367,000.00 እና ካፒታል በጀት ብር 450,000,000 በድምሩ ብር 1,594,367,000 ሆኖ ፀድቋል፡፡ በበጀት ድልድሉ ለመማር ማስተማር 582,455,300.00፣ ለምርምር 51,496,600.00፣ ለሥራ አመራርና አስተዳደር 324,644,600.00፣ ለማማከርና ማኅበረሰብ አገልግሎት 54,920,500.00 እና ለተማሪ አገልግሎት 130,850,000.00 ተደርጓል፡፡ በጀቱ ውጤታማነትንና ቀልጣፋነትን በሚያረጋግጥ መልኩ የሚፈፀምበትን አቅጣጫና ሥርዓት በመከተል በፋይናንስና በጀት አስተዳደር የበጀት አጠቃቀም ውጤት ተኮር መርህ መሠረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
በዕቅድ ግምገማው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የካውንስል አባላት ተገኝተዋል፡፡

ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


@amucampus
@amucampus
ዛሬ 13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ይከበራል።
እለቱ "ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ለአብሮነታችንና ለሀገራዊ ብልጽግናችን!" በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው።
@amucampus
አርባምንጭ የሚገኘው የፓራዳይዝ ሎጅ በአዲስ ዲዛይን ሊገነባ ነው!

አርባምንጭ የሚገኘው ፓራዳይዝ ሎጅ ባህላዊና ዘመናዊ ይዘቱን ሳይለቅ በአዲስ መልክ ለመስራት የዲዛይን ሥራ ተጠናቆ ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳን ግንባታው ቢጀመርም ሎጁ መደበኛ ስራውን እንደማያቋርጥ ነው ያስታወቀው፡፡

ኦሞቲክ ቢዝነሰ ግሩፕ ከፓራዳይዝ ሎጅ በተጨማሪ በከተማዋ አዲስ የሆቴል ግንባታን ጨምሮ ጨበራ ጩርጩራ ፓርክ አከባቢ፣ በጅንካ እና በኬንያ ሎጆችን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት መጨረሱን አስታውቋል፡፡

@amucampus
@amucampus
💥የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣው ግብረ ሀይል የዩኒቨርሲቲውን ቅድመ ዝግጅት ተመልክቶ ግብረ መልስ ሰጥቷል፡፡

ከ2012 አጋማሽ ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የመማር ማስተማር ሥራው በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መቋረጡ ይታወሳል፡፡

በዘንደሮ የትምህርት ዘመን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሥራቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ከትምህርት ሚኒስቴር በወረደው መመሪያ መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ይነገራል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ከሣይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከመጣው ግብረ ሀይል ጋር ቅድመ ዝግጅቱ ያለበትን ደረጃ ተመልክቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ዩኒቨርሲቲው ከጥቅምት 20 ጀምሮ 4571 ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሁለት ወራት ውስጥ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ እንደሚያስመርቅ ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመማሪያ፣ የመኝታና የመመገቢያ እንዲሁም ከግቢው ውጭ የሚደረጉ የተማሪዎች እንቅስቃሴዎች ለኮሮና በማያጋልጥ መልኩ መሆን እንዳለበት ከመግባባት ላይ መደረሱን ዶ/ር ዳምጣው ጠቀመዋል፡፡

መረጃው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ነው።

@amucampus
@amucampus