AmlekoTube
7.93K subscribers
3.69K photos
811 videos
1.03K links
እየሱስ ይመጣል‼️
Download Telegram
አስደናቂ የህይወት #ምስክርነት ከጌታ ባሪያ ሀብታሙ ጋር
ወጣትነቴ በጣም ከባድና አሰቃቂ ነበር በዛን ጊዜ ግን ለኔ መዝናኛዬ ነበር እንደ ቀልድ ጓደኞቼ ሲጋራ እንድሞክር ነግረውኝ ሞከርኩት ከዛም የእለት ልማዴ ሆነ ጫት ሀሽሽ መውሰድ ጀመርኩኝ መጠጣት መጨስ የእለት ኑሮዬ አደረኩት ከዛ በኋላ ግን ከዚ እስራት በፍጽም መውጣት አልቻልኩም...ጌታ እንዴት እንዳገኘው ከራሱ አንደበት እንስማው
ከዚ መጥፎ እስራት መውጫ መንገድ አንድ ብቻ ነው እሱም #እየሱስ_ነው
ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ይከታተሉ
ይህን ቪዲዮ ካያችሁት በኋላ ለሌሎችም የክርስቶስ ቤተሰቦች እንዲደርስ #ሼር አድርጉት፣ ተባረኩ
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=29b63b9fc
AmlekoTube.com:
🙋‍♂ ቢንጎ 🙋 ቢንጎ 🙋‍♂ ቢንጎ 🙋

ምን መሰላቹ በዚህ ግሩኘ ውስጥ ማንም ሰው ጣልቃ ሳይገባባቹ በተከታታይ 50 ሰው #add ላደረገ @amlekotube በአይነቱ ልዩ የሆነ ስጦታ አዘጋጅቷል። #ማን_ይ/ትሆን_ይሄን_ሽልማት_የሚወስደው_??
እግዚአብሔር አምላካችን በምድራችን ላይ አስደናቂ ዘማሪዎችናንና ሙዚቀኞችን ያስነሳበት ዘመን ነው .ስለዚህ እነዚህ ለቤተክርስትያን ስጦታዎች ናቸው .ስጦታዎችን ደግሞ መጠበቅ .መንከባከብ .አቅጣጫ ማሳየት የቤተ ክርስትያን ሀላፊነት ነው
አባቶቻችን ይህንን አገልግሎት እስከ መሾምም ጠብቀውታል
ወደ እኛ የሚመጡ እቃዎች ሁሉ ክ2 አቅጣጫ ይመጣሉ 1ጤናማ ከሆነ ሶርስ 2 ጤናማ ካልሆነ ሶርስ።ይልቁንም ወደ እግዚአብሔር ህዝብና ወደ ቤተ ክርስትያን የሚመጡ እቃዎች ቢፅለይባቸው ሞኝነት አይደለም ብልጠት እንጂ ።ምክንያቱም እኛ እጅ ላይ ሀይል አለ.ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣን .ከጀርባው ያለውን ሀይል አመክነን መጠቀም እንችላለን.
ባቢሎን ተማርኮ የሄደ እቃ እዚያ ስለረከስ ቀድስው ተጠቅመውበታልና.ጌታ ይባርካችሁ
#ፓስተር_ደበበ_ለማ
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=231324ba0
ቃለ መጠይቅ ከፓስተር ዳዊት ሞላልኝ ጋር
>>Faith BIble International Church ከአዲስ አበባ ውጪ 204 አጥቢያ ቤተክርስትያን አላት ቤተክርስትያን ልትያዝ የምትችለው እንደአባት እና እንደመሪ በመሆን እውነተኛውን መንገድ ሊያሳያት በሚችል ሰው ብቻ ነው<<
Interview With BISHOP Dawit Molalegn Akore Zema
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=c02158b16
!!!#Must_Watch!!!
ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና አስታራቂነት የሰጠችው ምስክርነት፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ እቅድመ ዓለም ከአብ የተወለደና ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል የሆነ የባህርይ አምላክ ሲሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ በመወለድ ሰውን ከእግዚአብሔር ያስታረቀው መካከለኛም እርሱ ነው፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሔር መምጣትና ኃጢአቱ ተሰርዮለት ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቀውም ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ ነው፡፡ ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ክህነት ዘላለማዊ ስለሆነ መስዋዕቱም ዘላለማዊ ነው ትለናለች ዘማሪት ዘርፌ ከበደ፡፡ ይህንንም ሁሉ የምትናገረው ከቅዱስ ቃሉ እየጠቀሰች መሆኑ እጅግ ያስደስታል፡፡
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=3f9ce17da
#ትምህርት
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ --------- " መሀላ "
መሀላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ነው ተስፋ ያለው ሰው በህይወቱ ተስፋ ብቻ ሳይሆን የሚኖረው ተስፋውን ከማስፈጸም ጋር ሙግት እና ክርክርም ሲኖረው ነው
መሀላ የክርክር ሁሉ ፍጻሜ ነው ብዙ ጊዜ የሚሸሹ ሰዋች ተስፋ የሌላቸው ሰዋች አይደሉም ተስፋ ያላቸው ግን ተስፋውን ለማልበስ አቅም ያጡ ሰዋች ናቸው
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=d9980d66d
#Testimony
እህት በእምነት ሂርጳ ከ6 አመቷ ጀምሮ ለ18 አመታት ትሰቃይበት ከነበረው እና እያደገ ከመጣባት የድድ ካንሰር በሽታ እግዚአብሔር በክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በመጋቢ ተዘራ ያሬድ የፈውስ አገልግሎት በአስደናቂ ሁኔታ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ፈውሷታል። ይህም ከሆነ አሁን 3 አመት ከ6 ወራት ተቆጥሯል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። ምስክርነቷን አብረን እንከታተል፡፡
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=52c9aad64
እኔ ደካማ ነኝ ለማንም አልጠቅምም ስለዚህ ደስተኛ አደለሁም
ለምትሉኝ ወዳጆቼ ኢቺን ለናንተ አንብቡ ለወዳጆቻችሁም ሼር በማረግ
አጋሩ!!
*
*
*
*
*
በአንጅ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር።
ይህ ሰው ውሃ ከወንዝ እየቀዳ ወደ ቤተመንግስት ዘወትር ያመላልስ
ነበር። ውሃ የሚያመላልስባቸው ሁለት እንስራዎችም ነበሩት፤ በነዚህ
እንስራዎች ውሃ ከወንዝ እየሞላ ወደቤተመንግስት ይወስድባቸው ነበር።
ከሁለቱ እንስራዎች አንዱ ግን ቀዳዳ ነበረው፤ እና ምንም እንኳን ከወንዝ
ሁለቱንም እኩል ውሃ ሞልቷቸው ቢሄድም፤ ቤተመንግስት ሲደርስ ግን
አንደኛው እንስራ ሙሉ፤ ቀዳዳ ያለበት እንስራ ደግሞ ጎዶሎ ይሆን
ነበር። በዚህ ሁኔታ ሰውየው በሁለቱ እንስራዎች አንድ ሙሉ እንስራ ውሃ
፤ በሌላኛው ደግሞ ጎዶሎ ውሃ እያመላለሰ ለረጅም ጊዜያት ቆየ።
ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ቀዳዳ ያለበት እና ዘወትር እያንጠባጠበ
የሚሄደው እንስራ እንዲህ ሲል ለሰውየው አቤቱታ አቀረበ
#
#
#
እንስራው:- “እኔን እና ጓደኛዬን እየተሸከምክ ውሃ ማመላለስ ከጀመርክ
እነሆ ቆየህ፤ ሰባራ ሆኜም እንኳን ስታመላልስብኝ ሰነበትክ፤ አሁን ግን
ዘወትር ከጌታዬ ፊት ጎዶሎ ውሃ እየያዝኩኝ መቅረቡ አሳፈረኝ፤ ጓደኛዬ
ዘወትር ሙሉ ውሃ ሲወስድ እኔ ግን ሁሌ ጎዶሎ ማቅረቡ አንገቴን
አስደፋኝ እናም በኔ ውሃ ማመላለሱ ቢበቃ ይሻላል”
አለው ይህን የእንስራውን አሳዛኝ ንግግር የሰማው ሰውዬ በማስተዋል
ቀዳዳውን እንስራ እየተመለከተ ሠውዬው:- “ዛሬ ውሃ ቀድተን ስንመለስ
አንድ ነገር አሳይሃለው፤” ሲል ነገረው።



ውሃ ቀድተው ሲመለሱ ሰውየው የሚያንጠባጥበውን እንስራ ወደመሬት
እያስተዋለ እንዲሄድ ነገረው። እንስራውም እንደተባለው አደረገ። በእሱ
በኩል ብዙ እፅዋቶችን ተመለከተ፤ ፍሬ ያፈሩ አትክልቶችን አስተዋለ፤
የሚያያማምሩ አባባዎች አየ። በዛኛው እንስራ በኩል ግን ምንም
አልነበረም። ምንም እንኳን ዘወትር በተመሳሳይ መንገድ ቢሄዱም
እንዲህ እንደዛሬው ግን አስተውሎት አያውቅም ነበር።
ሠውዬው:- “አየህ ወዳጄ፤ አንተ እንደምታንጠባጥብ ሳውቅ፤ ባንተ በኩል
ዘሮችን ዘራው፤ ዘወትር ካንተ በሚንጠባጠበው ውሃ ጥማታቸውን
አራሱ፤ ፍሬ
አፈሩ፤ አበቡም፤ ይህ የምትመለከተው አትክልት ሁላ
ባንተ በኩል ብቻ ነው ያለው፤ ሌላኛውን እንስራ በምሸከምበት በኩል
ምንም ነገር የለም፤ እናም ጥቅም የለኝም አትበል፤ ሌላው ቢቀር ደካማ
ጎንህ እንኳን ለሌሎች ጥቅም አለው” ሲል አስረዳው።
-
-
-
-
አንዳንዴ ልዩነታችንን አይተን፤ በንጽጽር ብቻ ጥቅም የለኝም፤ እርባና ቢስ
ነኝ ብለን እናስብ ይሆናል። ሌላው ሰው የቻለውን እኛ ባለመቻላችን ብቻ
፤ጎዶሎ
እንደሆንን እናስባለን። የሌሎች ብርሃን እንጂ የኛ ስለማይታየን ከጨለማ
መውጣት ያቅተናል። ሰባራው
እንስራ ሌላኛው እንስራ ሙሉ ውሃ መውሰዱን ተመለከተ እንጂ በሱ
የሚፈስ ውሃ ስንት የእፅዋት ነፍስ እንደበቀለ አላስተዋለም።
እኛም እንዲህ ነን፤ የየራሳችን ብርሃን አለን፤ ነገር ግን የለላው ሰው
ጭላንጭል ያስቀናናል። ሁላችንም አናውቀውም እንጂ፤ የኛ መኖር
የሚጠቅማቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ እናም ጥቅም እንደሌለን አድረገን
እራሳችንን አንቁጠር፤ አይናችንን ብንገልጥ አቅማችን ከሁሉም ሰዎች
እኩል ነው ወዳጄ ሆይ!!!ሌሎች ሙሉ ውሃ መሸከም ቢችሉ እንዳንተ
ነፍስ መዝራት አይችሉም፤ አንተ እንደነሱ ሙሉ ውሃ መሸከም ቢያቅትህ፤
ጉድለትህ ሌሎች እንዲያብቡ ያደርጋል። እናም እራስችንን ማነፃፀሩን
ትተን፤ ብራሃናችን ለሌሎች እንዲያበራ እናድርግ።
#መታየት_ያለበት!!! #MUST_WATCH !!!
በልጅነቱ ስጋ በልቶ ስለማያዉቅ የስጋን ጣእም አያዉቅም ነበር የ13 አመት ልጅ እያለ አንድ ቀን እናቱ ያቀረቡለት ምግብ ግን ህይወቱን አበላሽቶበታል ያቀረቡለትን ስጋ የሰው ስጋ መሆኑን ሳያዉቅ አጣጥሞ በላ በንጋታዉ ጠዋት እናቱ ጠንቋይ ቤት ይዘውት ሄደው የአንበሳ መንፈስ እንዲገባበት ተደረገ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው የመቃብር ስፍራ በመሄድ የሰው ስጋ
መብላት ጀመረ................................ የዚህን ሰው አስገራሚ ነፃ መውጣት ይመልከቱ
➤➤➤http://www.amlekotube.com/article_read.php?a=262
በነብይ እስራኤል ዳንሳ በኩል የተነገሩ ትንቢቶች እየተፈፀሙ ይሆን? “የተፈፀመ ትንቢት” 1
በዚሳምንት ስለኢትዬጵያዊው ባለሀብት ሼክ ሙሀመድ አላሙዲ የተናገረው ተፈፃሚነትን አግኝቷል
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=9d8a804b0
#Must_Watch
ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ አንድ #ታዋቂ_ሰው የተነገረ አስደንጋጭ ትንቢት ተፈፀመ.በነብይት ብርቱካን የተተነበየ
.....ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:11
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=cf3511767
አንድን ሰው ነብይ ነው ብሎ ለመጥራት የሚያስገድዱ ወይም የሚያስብሉ 8 አይነት ምልክቶች
Do you believe you may have the spiritual gift of prophecy and would like confirmation? Here are 8 common signs of a prophetic gift.
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=8e92eb1e6
ዘማሪ በረከት አለሙ ----------- " ሽልማቴ "
ጌጤ ፡ ወርቄ ፡ ውበቴ ፡ ደም ፡ ግባቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)
ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)

ከ ፡ ነገድ ፡ ቋንቋ ፡ በ ፡ ልጁ ፡ የዋጀኝ
ወደከበረ ፡ መንግስቱ ፡ ያፈለሰኝ
ከላይ ፡ ሲመጣ ፡ የተቀበልኩት ፡ ስጦታዬ
ወራሽ ፡ አረገኝ ፡ የ ፡ እርስቱ ፡ ተካፋይ (5)

ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)

እኔን ፡ ለማድረግ ፡ ባለጠጋ ፡ ሆነህ ፡ ባዶ
ውበት ፡ ሊሰጠኝ ፡ በኔ ፡ ____ ፡ ተሰቃይቶ
በሰማያዊ ፡ በረከቱ ፡ ባረከኝ
በ ፡ ጸጋው ፡ ሙላት ፡ በ ፡ መንፈሱ ፡ ከበበኝ (5)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=47636351c
#Must_Watch
የወንጌል አማኞች ሁሉ ሊሰሙት የሚገባ
በኢትዮጲያ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ የቀረበ
ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል ማቴ 12:36
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=9f2513ca8
#Amazing_Testimony_Of_Muslim_Women
>>>>> እንደ እስልምና እምነት መሰረት ልጅ እያለሁ ከአንድ ሙስሊም የሚጠበቁትን ነገሮች በሙሉ አደርግ ነበር ትምህርት ቤት ከመሄዴ በፊት ቁራንን ሚሞራይዝ አደርጋለሁ ክርስትያኖችን በጣም እጠላቸው ነበር በሀይማኖት በዘር በፓለቲካ ዙሪያ ሲሰቃዩ ሳይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር ሁልጊዜ 1 ክርስትያንን ከገደላችሁ 1 ቲኬት ወደ ገነት (#One_Way_Ticket_For_Heaven) እንድትገቡ መንገዱ ይከፍትላችኋል ብለው ያስተምሩናል ሁሉንም #ህጎች ለመፈጸም ጥረት ባደርግም እንኳን ሊሆንልኝ አልቻለም ለምሳሌ በስርአት ሳልታጠብ ጸሎት ብጀምር ጸሎቱን አቋርጬ እንደገና ወጥቼ እታጠባለሁ ይሄ በቀን #10 ጊዜ ይደጋገማል ይሄ ህይወት በህግ መታሰሬ እና ልፈጽም አለመቻሌ የእናቴም ጽኑ ህመም እየበረታ ሲሄድ ራሴን ለማጥፋት ተነሳሁ በዛን ሰአት እየሱስ ስለሚባል አዳኝ በTV ሰማን ከመሞቴ በፊት የዚህን ሰው አዳኝነት ልስማ ብዬ ተመለስኩ ከአንድ ፓስተር ጋር ተገናኘን ወንጌልን ነገረን በሚቀጥለው ቀን ጠዋት አንድ ማላውቀው ድምጽ ቀሰቀሰኝ ቀና ስል እናቴን በሁሉቱም እግሮቿ ቆማ አየኋት እጅግ ተደነቅን ጌታ እንዲህ ባለ መንገድ ተገናኘን ሰላም አግኝተን ከየትኛውም #ህግ ነጻ ወጥተን በነጻነት ጌታ እየሱስን ማምለክ ጅመርን <<<<
ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።
ሮሜ 6:14
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=39b68ab4f
የኃጢአት ይቅርታ በእኛ የኑዛዜ ጸሎት ላይ የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ ምን ይውጠን ነበር?
ለመሆኑ በቀን ውስጥ የሰራውን ኃጢአት በትክክል ተናዝዞ ሊጨርስ የሚችል ማነው?
ይሄንን ለማድረግ መሞከርስ በራሱ አንድ ሸክም አይደለምን? ☞እውነቱ ግን፡ ክርስቶስ
ኢየሱስ የዛሬ 2000 ዓመት ባፈሰሰው ደሙ የእድሜ ልክ ኃጢአታችንን ሁሉ
አስወግዶታል፡፡
☞" # በደላችሁንሁሉ ይቅር <አላችሁ።"
( ቆላስይስ 2:13)
☞" አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን # የዘላለምፍጹማን አድርጎአቸዋልና።"
(ዕብራውያን 10:14)
Share = amen