AmlekoTube
7.98K subscribers
3.64K photos
809 videos
1.02K links
እየሱስ ይመጣል‼️
Download Telegram
አስቴር አበበ ----- " ስምህን አወኩት "
ሥምህን ፡ አውቅኩት ፡ ተረዳሁት ፡ ደግሞም ፡ ታምኜበታለሁ
የፀና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ከስንቱ ፡ አምልጬ ፡ ተጠግቼው ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ
ደጅህን ፡ ጠናሁት ፡ አንኳኳሁት ፡ ከፍተህልኝ ፡ ተቀብለኸኛል
በፍቅር ፡ እጆችህ ፡ እቅፍ ፡ አርገህ ፡ ወደ ፡ ራስህ ፡ አስጠግተኸኛል (፪x)

አቤት ፡ ያለው ፡ ሰላም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጠጋጉ ፡ ወደ ፡ ደረትህ
ማዳመጥ ፡ ስትናገር ፡ የፍቅርን ፡ ቋንቋ
መቼ ፡ ይታወቃል ፡ ወፎቹ ፡ ሲንጫጬ ፡ ለሊቱም ፡ ሲነጋ (፪x)

ኃያል ፡ ሆይ ፡ በኃይልህ ፡ ኃያል ፡ አደረግከኝ
ብርቱ ፡ ሆይ ፡ በብርታትህ ፡ ብርቱውን ፡ አደረግከኝu
እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ
እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ (፪x)

በልዑሉ ፡ አምላክ ፡ መጠጊያ ፡ መኖሬ
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ማደሬ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ በላባዎቹ ፡ ጋርዶኝ
ከጠላት ፡ ፍላፃ ፡ አንዱም ፡ አላገኘኝ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

በአጠገቤ ፡ ሺህ ፡ በቀኜም ፡ አስር ፡ ሺህ
እየበተነልኝ ፡ ሆኛለሁ ፡ ድል ፡ ነሺ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

አስጥሎኛል ፡ እንዲህ ፡ አድርጎ
ከአንደበቴ ፡ ምስጋናን ፡ ወዶ (፰x)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=c5a76f8f7
ሰው ምንድን ነው? ነፍስ፣መንፈስ ወይስ ስጋ?
ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ መሰረታዊ የሆነ ትምህርት
ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ይከታተሉ ተባረኩ
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=53bb638b5
ዘማሪ ደረጀ ከበደ ምርጥ መዝሙሮች ስብስብ
ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከእኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ሰውማ ፡ ዛሬም ፡ ላይ ፡ ታች ፡ ይላል
አደባባዩስ ፡ መቼ ፡ ይጐላል
ጨዋ ፡ ህዝብ ፡ ፈገግታ ፡ ያሳያል
ልቡ ፡ ግን ፡ በሃዘን ፡ ይጋያል

ወንድ ፡ ሴት ፡ ልጆቹን ፡ ያጣ ፡ ሰው
እህቱን ፡ ወንድሙን ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወላጆቹን ፡ በሞት ፡ ያጣ ፡ ሰው
ያጽናኝ ፡ ያለህ ፡ ይላል ፡ ሆዱን ፡ እየባሰው

ባልንጀር ፡ አብሮ ፡ አደጉን ፡ ያጣ
የሥራ ፡ ባልደራባዉን ፡ ያጣ
ጐረቤት ፡ ጠያቂውን ፡ ያጣ
የሚያጽናናው ፡ ዛሬ ፡ ከየት ፡ ይምጣ

ሞት ፡ ያልበዘበዘው ፡ ማን ፡ አለ
ቤት ፡ ጓዳው ፡ ያልተመሰቃቀለ
ተርታውን ፡ ከደጃፍ ፡ እደጃፍ
ነጣቂው ፡ ነጠቀ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ ሳያልፍ
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=e0c814990
ዶክተር መሀሪ ታደሰ
#የፓስተር_አላዛር_የተሀድሶና_የምስክርነት_ፕሮግራም
ሰላም ይብዛላችሁ!!
ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ብሶቱን በጥቅስ ይገልጣል፡፡ የመጣ ሰው ሁሉ አስተያየት እየሰጠ አስቸግሯቸው ነው መሰል አንድ ቦታ «በገንዘብ ካልተደገፈ በቀር ምክር መቀበል አቁመናል፡፡» የሚል ጽሑፍ አንብቤአለሁ፡፡ ሰሞኑን የሚካሄደውን የፓስተር አላዛር ይባቤ የተሃድሶ የምስጋና ፕሮግራም አስመልክቶ አስተያየት ሰጪው ቢበዛብኝ እኔም «በተግባር ካልተደገፈ ምክርና አስተያየት መቀበል አቁሚአለሁ» ለማለት ዳድቶኛል፡፡ ከዓመት በላይ ደውለውለትም ሆነ አግኝተውት የማያውቁና ያለፈበትንና ያለበትን ሕይወት ሳያጣሩ እንዲያው በነሲብ የመንደር ወሬን ተከትለው የሚዘባርቁ አገልጋዮች ብዛት አስደንቆኛል፡፡ ወንድማቸው በንስሐ ታድሶና ታጥቦ ለራሱ፡ ለጌታና ለቤተሰቡ፡ በሕይወት መኖሩ ሊያስደስታቸው ሲገባ እነርሱ ጋር መጥቶ ማኅተም ካላስመታ በቀር ምሕረት ከአምላክ ማግኘት የማይችል የመሰላቸው ጥቂት አይደሉም፡፡ እነርሱ የሚያስቡትንና የሚያቀርቡትን አስተያየት ሌላ ሰው አስቦት የሚያውቅ ለማይመስላቸው አገልጋዮች ምን ማለት ይሻል ይሆን? ሰው በድካም ውስጥ ቢያልፍ እንዲነሳ የሚያቀናው ማን ይሆን? ለማንኛውም ወንድማችን በንስሐ ከታጠበ አንድ ዓመት ከዐስር ወር ሆኖታል፡፡ አገልጋዮችም ደግፈው እየጸለዩለት ለዚህ ቀን ደርሷል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ የወንድሞቻችን ከሳሽ ብቻውን ይበቃል አጋዥ አይፈልግምና በመነሳቱ እንደሰት ደግሞም ለዚህ ቤተሰብ እንጸልይ፡፡ ወንድማችንንም እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በእርሱና በቤተሰቡ በኩል ጠቅሞን ከሆነ እንንገረው እናበረታታውም፡፡ ለማንኛውም የሃና ተክሌን «በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል» የሚለውን መዝሙር ተጋበዙልኝ፡፡
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=e8d14bd5a
ዘማሪ ዳንኤል አ/ሚካኤል -------- '' እየማርከኝ ''
#Live_Worship #Aster_Abebe
ኃያል ፡ ሆይ ፡ በኃይልህ ፡ ኃያል ፡ አደረግከኝ
ብርቱ ፡ ሆይ ፡ በብርታትህ ፡ ብርቱውን ፡ አደረግከኝu
እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ
እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ (፪x)

በልዑሉ ፡ አምላክ ፡ መጠጊያ ፡ መኖሬ
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ማደሬ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ በላባዎቹ ፡ ጋርዶኝ
ከጠላት ፡ ፍላፃ ፡ አንዱም ፡ አላገኘኝ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

በአጠገቤ ፡ ሺህ ፡ በቀኜም ፡ አስር ፡ ሺህ
እየበተነልኝ ፡ ሆኛለሁ ፡ ድል ፡ ነሺ
ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል
መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል

አስጥሎኛል ፡ እንዲህ ፡ አድርጎ
ከአንደበቴ ፡ ምስጋናን ፡ ወዶ (፰x)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=d1b61b4a1
እግዚአብሔር ለምድራችን ካስነሳልን ወጣት ነቢያቶች መሃል አንዱ ነው ነቢይ ቤክሾ ተካ። በአግልግሎቱ ቅንና ደግ፣ ለሌሎች ከእራሱ አብልጦ የሚያስብ፣ ወንጌልን ባገኘበት ቦታ ሁሉ መስበክ የሚወድ ታላቅ የወንጌል አርበኛ ነው። አሁን ደግሞ በጣም ደስ የሚል የምስራች ይዞልን መቷል፦
MIRACLE ARENA CHURCH ይፋዊ የምስረታ በአል
ከመስከረም 26-28 (የረር) በሚገኘዉ የአምልኮ ስፍራ ይደረጋል!!
በኘሮግራሙ ላይ
-Prophet Bekisho Teka (የቸርችቱ ባለራእይ እና መስራች)
-apostel yididiya phaulos (ከአዳማ)
-pastor Biniyam (ከcj church)
-Man of God Ephrem Alemu (ከassembly Church) እንዲሁም የተለያዩ አገልጋዮች በምስረታ በአል ላይ ያገለግላሉ....!
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል..
ይህንን መልካም ዜና ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ #ሼር በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ጋብዟቸው። ሻሎም
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=b0cd2df03
#ትምህርት
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ------ " ያፍህ ቃል "
አጋንንት ሰውን ከሚይዘው ወይም ሰዎች እሱን ከሚይዘው በላይ የሚያዘው በራሱ አንደበት ነው ከባድ እስር ቤት ቢኖር የራስ አንደበት ነው ከባድ ወጥመድ ቢኖር የራስ አንደበት ነው ስልጣን የሚሰራው በንግግር ነው በቃል ነው ያለቃል ስልጣን አይሰራም
ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ። ማቴ 12:37
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=c083e071e
ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ -------- " ክንዱ ነው ታሪኬን የቀያየረው "
ክንዱ ፡ ነው ፡ ታሪኬን ፡ የለዋወጠው
ጣቱ ፡ ነው ፡ ነገሬን ፡ የቀያየረው (፪x)

አይቻለሁ ፡ በአንተ
ሸለቆው ፡ ውኃ ሲሞላ
ጌታ ፡ ስትሆነኝ ፡ ከለላ (፪x)

አንገት ፡ እንድደፋ ፡ እንዳቀረቅር
ከሰው ፡ በታችን ፡ ሆኜ ፡ ነበር ፡ ምኞቱ
ጠላቴማ ፡ ሰው ፡ ለማድረግ ፡ ከንቱ ፡ አወይ ፡ ልፋቱ
የማመልከው ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
እንደገና ፡ አነሳኝ ፡ ዳግም ፡ አቆመኝ

ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ እኮ ፡ ማነው ፡ ማነው
እሃሃሃ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኮ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=7fa277549
ፓስተር ዳዊት ሞላልኝ ------ " መንፈስ ቅዱስ "
በመንፈስ መሆን ማለት በምንሄድባቸው ስፍራ ሁሉ ከእግዚአብሔር ህልውና ጋር መሆን ማለት ነው በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መገኘት ማለት ነው::
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=1d9d4cb80
በጣም ደስ የሚል መዝሙር
#አዲስ _መዝሙር #አዲስ_ቪዲዮ 2017
ዘማሪ ሳሙኤል አበበ ------- " የመንገዴ መብራት "
ህሊናዬን ሲወቅሰኝ እየደጋገመ ሲከሰኝ
አለም መሞትን ስትሰብከኝ እየሱስ ግን ህይወት ሆነልኝ
ተስፋ መቁረጥን ስትነግረኝ እየሱስ ግን ተስፋ ሆነልኝ
ከአለም ጋር ተጣብቄ በሀጢያት ገመድ ታንቄ
ፀጋውን ገለጠና አስካደኝ
ወረሰኝና መንፈሱን አፈሰሰና ለያየኝ የራሱ አረገኝና
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=75edb41a1
#የቃል_ጊዜ
በእግዚአብሔር ሰው ሱራፌል ደምሴ ---- " የስም ለዉጥ "
ያዕቆብ የብዙ ነገር ሀብት ባለቤት ሆኖ ለምን በዛን ለሊት ያገኘውን መልአክ ካልባረከኝ አለቅህም አለው?.. የመባረክ ትርጉም ምንድነው?...
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=917869677
የአማኑኤል ህብረት መዘምራን ----- "አዋቂ ነው ጌታ አዋቂ ነው "
" መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ሲናገር ፡ 'አትታበዩ ፡ በኩራትም ፡ አትናገሩ
እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነውና' "
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላወዳድርህ ፡ ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላመሳስልህ
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላወዳድርህ ፡ ከማንስ ፡ ጋር ፡ ላመሳስልህ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እህህ
ከአእምሮዪ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ እህህ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እህህ
ከአእምሮዪ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ እህህ (፪x)
እንተን ፡ እንዳላስተያይ ፡ ከሌላ ፡ ነውር ፡ ሆነብኝ (፬x)

ዓይኖቼን ፡ ማሳርፍበት ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ የለኝም
ከልቡ ፡ የሚራራልኝ ፡ እንደአንተ ፡ አላገኝም (፪x)

አይነጻጸር ፡ የአንተ ፡ የፍቅር ፡ ቃል
አይወዳደር ፡ የመውደድህ ፡ ጉዳይ
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ አባቴ ፡ ለእኔ
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ልበልህ (፪x)

ሰው ፡ መውድዱን ፡ ሲገልጽ ፡ በከንፈሩ ፡ ቃል
አንተ ፡ ግን ፡ ለእኔ ፡ ሞተሃል (፬x)
ሰው ፡ መውድዱን ፡ ሲገልጽ ፡ በከንፈሩ ፡ ቃል
አንተ ፡ ግን ፡ ለእኔ ፡ ሞተሃል (፬x)

አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ ስራዬን ፡ ስትሰራ
በዘመኔ ፡ ሆነኸኝ ፡ ከለላ
ረዳት ፡ ሆንከኝ ፡ እኔስ ፡ ታመንኩብህ
እግዚአብሔር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ (፪x)

አዋቂ ፡ ነህ ፡ አዋቂ ፡ ነህ
አዋቂ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነህ (፪x)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=9bf7e6aa9
ዘማሪት ቤቲ ወልዴ -------- " ባለ ውለታዬ "
ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሰዋለሁ (፪x)

ለኔ ፡ ነው ፡ መንከራተትህ
መስቀል ፡ ተሸክመህ ፡ መውረድህ
ለኔ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ያላበህ
ፍቅር ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ ያስጨነቀህ

ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፣ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፣ ወድጄም ፡ አመልክሃለሁ

አዝ:- ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሰዋለሁ

ከአብ ፡ ዘንድ ፡ ለኔ ፡ የተሰጠ
ትልቁ ፡ ስጦታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ
ይህ ፡ ሚስጥር ፡ ለኔ ፡ ተገልጾ
መዳን ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሆኖልኛል

ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፣ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፣ ወድጄም ፡ አመልክሃለሁ

አዝ:- ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሰዋለሁ (፪x)

ልከፍለው ፡ አልችልም ፡ ውለታህን
ያኔ ፡ ያረከውን ፡ በጐልጐታ
ምስጋናን ፡ ሙገሳን ፡ ይዤ
ላክብርህ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ

ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፣ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፣ ወድጄም ፡ አመልክሃለሁ

አዝ:- ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ
የእግዚአብ ሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ
ውለታህን ፡ አስታውሰዋለሁ (፪x)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=a0ad0fc5d
ምድራችን ኢትዮጵያ ኢየሱስ ኢየሱስ በሚል ትውልድ እየተሞላች ነው ደስ የሚለው አሜን ይበል
መንገስ የሚገባው ይነግሳል
ኢየሱስ ብዙዎችን ይወርሳል
እግዚአብሔር ይከብራል
ጠላት ይዋረዳል
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=6dd8504bc
ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ ----- "የሚመጥን አምልኮ "
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ሮሜ 12፡1-2
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=bb98f17c0
ዘማሪት አዜብ ዩሐንስ ------ " ይሄ ነው የኔ ጌታ "
እውነትና ፡ በመንፍስ ፡ ስትመለክ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በፊትህ ፡ ሲል ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ
ቋንቋው ፡ ሁሉ ፡ ስለአንተ ፡ ዝና ፡ ሲያወራ
ሲባል ፡ ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ነህ ፡ የተፈራህ

እንዲህ ፡ ከሚሉ ፡ ጋራ ፡ ልተባበር
እኔም ፡ የእራሴን ፡ ፈንታ ፡ ልጨምርልህ
ይሄም ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ አይበዛምና
ገና ፡ ፍጥሮችህ ፡ ይጥሩህ ፡ ብለው ፡ ገናና ፡ አንተ ፡ ገናና
አንተ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ገናና (፪x)

በላይ ፡ በሰማይ ፡ ላለው ፡ በዙፋኑ
ለሚገዙለት ፡ እልፍ ፡ ቅዱሳኑ
ለሚባርኩ ፡ ስሙን ፡ በዝማሬ
አምላክ ፡ ለሆነው ፡ ጥንትም ፡ ቢሆን ፡ ዛሬ (፪x)

እኔም ፡ አለኝ ፡ አምልኮ
እኔም ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና
እኔም ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ
በአመታት ፡ መካከል
ጸንቶ ፡ ለሚኖረው
ለጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x)
➤➤➤http://www.amlekotube.com/watch.php?vid=072026ed2