ዩቲዩብ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ክፍያ መፈጸም ሊያቆም ነው
ግዙፉ የቪድዮ ማሰራጫ ዩቲዩብ በብዛት የተመረቱ እና ተደጋጋሚ ቪድዮዎችን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መጋራት ስርዓት እንደሚያስወጣ አስታወቀ።
የፖሊሲ ማሻሻያው ሰው ሠራሽ አስተውህሎትን (ኤአይ) በመጠቀም የሚሰሩ ይዘቶችን ጨምሮ ከዩቲዩብ የክፍያ ስርዓት እንደሚያስወጣ ተገምቷል።
ለዚህም ዩቲዩብ ይዘት ፈጣሪዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ሆነው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው "ኦርጅናል" እና "እውነተኛ" ቪድዮዎችን እንዲለቅቁ እንደሚያስገድድ አስታውሷል።
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ ይህንን መስፈርት ቁጥጥር የሚያደርግበትን አሰራር እንደሚያሻሽል ገልጿል።
አዲሱ ማሻሻያ የሚደረገው በብዛት የተመረቱ እና ተደጋጋሚ ይዘቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየት እንደሆነ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
አዲሱ የዩትዩብ ፖሊሲ ከክፍያ ስርዓቱ ከሚያስወጣቸው ቪድዮዎች ውስጥ፤ በኤአይ የተፈጠሩ ይዘቶች፤ በተለይም በኤአይ የተፈጠሩ ድምጾች ላይ የሚመረኮዙ ወይም በአነስተኛ ቪድዮ ኤዲቲንግ፣ በድጋሚ የሚጫኑ የሌሎች ሰዎች ይዘቶች እንደሚገኙበት የሕንዱ ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል።

❤7
#Ethiopia🇪🇹
ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።
በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።
በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።
ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች " በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።
ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2
ከህመም ጋር እየታገለ የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ያጠናቀቀው ብርቱው "አሉዲን"
ተማሪ አሉዲን ሁሴን ይባላል። የበደሌ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነው። የ12ኛ ከፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቆ የመፈተኛ ቀኑ ሲደርስ ሕመም ያጋጥመዋል።
ተማሪ አሉዲን ህክምና ሂዶ ምርመራ ሲያደርግ የትርፍ አንጀት እንደሚገኝበት በዶክተሮቹ ይነገረዋል።
በዚህ አጋጣሚ ጭንቀት ውስጥ የገባው ጎበዙ ተማሪ ሕመሙ ፈተናውን መጨረስ የሚያስችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ ት/ቤቱ ከዶክተሮቹ ጋር በመነጋገር መዳኒት እየወሰደ እንዲፈተን መደረጉን የት/ቤቱ ር/መምህር አቶ ይልማ ገቢሳ ተናግረዋል።
ህክምና እየተደረገለት ለ3 ቀን ሲሰጥ የነበረውን የማሕበራዊ ሳይንስ ፈተና በትናንትናው ዕለት አጠናቆ ቀዶ ጥገና እንደሚደረግለት አቶ ይልማ ጋቢሳ ገልፀውልናል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በፈተና ጣቢያው ተገኝተው የፈተናውን ሂደት በጎበኙበት ወቅት ፣ ተማሪውን አበረታተዋል።
ሃገር የምትገነባው ፣ ችግርን ተቋቁመው ዓላማቸውን ለማሳካት በሚጥሩ እንደ አሉዲን ባሉ ብርቱ ዜጎች ጥረት ነው ብለዋል።

👏6❤2👍2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የተማሪዎች ውጤት ለማየት የነበረው ቦት አሁን ፍጹም በሙሉ Update ተደርጎ በቀላሉ ውጤት ለማየት የሚቻል እንዲሆን ተሻሽሎ መጣ።
አሁንም ይሞክሩ፤ ውጤታችሁን እያያችሁ፣ እኛም ከእርስዎ ጋር ለመሻሻል አስተያየትዎን እንጠብቃለን።
@ministrygrade8ethiobot
🗣 አስተያየትዎን ላኩ፤ የቦቱን አገልግሎት ያሻሽሉ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2❤1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤4
#ጥቆማ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉት ለ2018 ትምህርት ዘመን የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በእቴጌ መነን የሴት እና በገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል።
በትምህርት ቤቶቹ ለመማር ፍላጎት ያላችሁና በ2017 የትምህርት ዘመን በ6ኛ እና 8ኛ ከፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች አማካኝ (Average) 80 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ከሐምሌ 14-18/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ በኦንላይን http://bs.ministry.et ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
የመግቢያ ፈተና ለ9ኛ ክፍል አመልካቾች ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም እና ለ7ኛ ክፍል አመልካቾች ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ይሰጣል።
ፈተና የሚሰጥበትን ቦታ በቀጣይ የሚያሳውቅ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
ለጥቆማ➡️ @ministry2017result

ለጥቆማ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1