TECH ETHIOPIA 🇪🇹
2.8K subscribers
143 photos
1 video
1 file
71 links
Download Telegram
ስልክ ተደውሎልን ስልኩን አንስተን በተለምዶ 'ሄሎ' እንላለን። ግን 'Hello' ማለት ምን ማለት ነው ግን

'Hello' ሰላምታ ብቻ ሳይሆን የአንድ የተወሰነ ሰው ስም እንደሆነ ሲያውቁ ብዙዎችን ሊያስገርም(ሊያስደንቅዎ) ይችላል። 'Hello' በእውነቱ የአሌክሳንደር ግርሃም ቤል እጮኛዋ Margaret Hello ስም ነበር። የስልክ ፈልሳፊው ቤል በፈጠራው

የመጀመሪያ ሙከራ ወቅት ''Hello' ን እንደ መጀመሪያው ቃል ተጠቅሟል። ይህ ቀላል ንግግር እስከ ዛሬ ድረስ ስልኩን ስናነሳ እንደ ሰላምታ ጸንቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስልክ ጥሪዎች መደበኛ መክፈቻ ሆነ።
😁4👍1
የቴሌግራም ባለቤት ፓቬል ዱሮቭ
አለም ይፍረድ ሰውየው $15 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሀብት አለው። ከዩክሬናዊት እናቱ ራሺያ ውስጥ ተወልዶ የሚኖረው ግን አረቦች ሀብታቸውን ተጠቅመው ባለሟት ባስገነቧት ዱባይ ውስጥ ነበር። ይሄ ሁሉ ነገር ኖሮት ለሁለት አመታት የያዘው ስልክ $180 ዶላር በኢትዮጲያ 20 ሺህ ብር ስልክ ነበር የአለማችን ትልቁ የቴክኖሎጂ ሰው የቴሌግራሙ መስራች ፓቬል ዱሮቭ።
1
⚙️ የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ጠፍቶባቹሀል? ከብዙ መፍትሔዎች ሁለቱን መንገዶች እንመልከት....

- የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro"ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ ነዉ የምታገኙት ።

- ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

1 መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን

2 ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡

3 ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡

4 “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል

5 ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኃላ Spotmou Bootsuite 2012 Application ይከፈትልናል

6 ከአፕልኬሽኑ ላይ Password and Key Finder የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡

7 Admin Password Resetter የሚል መንካት፡፡

8 Please select the target widows ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ ቀጥሎ “please select the target user ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን User Account መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡

9 መጨረሻ ላይ Password is reset successfully የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡

10 ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል
3
📥 ውድ የቴሌግራም ቤተሰቦቻችን
አባላት በሙሉ የምንፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉን #MUTE ካደረጉት እንዳሉም አይቆጠርም 🤷‍♀

☝️ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት 👍

#UNMUTE❗️ የሚል ካለ ደሞ አንድ ግዜ በመጫን MUTE ላይ በማድረግና የምንለቃቸውን ፖስቶች ሼር በማድረግ አብራችሁን ሁኑ 🙏
2
የ6ኛ ክፍል አስተዳደር አቀፍ ፈተና ቅሬታ አቀራረብን ይመለከታል

የ6ኛ ክፍል አስተዳደር አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ ማንኛውንም ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ወይም ወላጆች ቅሬታቸውን ለትምህርት ቤቱ ብቻ ማቅረብ እንዳለባቸው እናሳውቃለን።

በመቀጠልም ትምህርት ቤቶች የተቀበሏቸውን ቅሬታዎች በአግባቡ አደራጅተው እስከ ሐሙስ፣ ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ልብ ይበሉ፦
የትምህርት ቢሮው ከተገለጸው የአሠራር መመሪያ እና የጊዜ ገደብ ውጪ በቀጥታ ከግለሰቦች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።


Via @tegene
1👍1
የ2018ዓ.ም የትምሀርት ቀናት መቁጠሪያ

@amharictutorialclass
4👍3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Dibekulu - Tikur Engdaye ( Official Music Video)
👁 238 👍 58
📥 11.05.2024
👤 DIBEKULU
4🔥1
Dibekulu - Tikur Engdaye...
DIBEKULU
🕒 03:37
2👍2
👍31🤗1
3👍2
ዩቲዩብ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ክፍያ መፈጸም ሊያቆም ነው

ግዙፉ የቪድዮ ማሰራጫ ዩቲዩብ በብዛት የተመረቱ እና ተደጋጋሚ ቪድዮዎችን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መጋራት ስርዓት እንደሚያስወጣ አስታወቀ።

የፖሊሲ ማሻሻያው ሰው ሠራሽ አስተውህሎትን (ኤአይ) በመጠቀም የሚሰሩ ይዘቶችን ጨምሮ ከዩቲዩብ የክፍያ ስርዓት እንደሚያስወጣ ተገምቷል።

ለዚህም ዩቲዩብ ይዘት ፈጣሪዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ሆነው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው "ኦርጅናል" እና "እውነተኛ" ቪድዮዎችን እንዲለቅቁ እንደሚያስገድድ አስታውሷል።

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ ይህንን መስፈርት ቁጥጥር የሚያደርግበትን አሰራር እንደሚያሻሽል ገልጿል።

አዲሱ ማሻሻያ የሚደረገው በብዛት የተመረቱ እና ተደጋጋሚ ይዘቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየት እንደሆነ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

አዲሱ የዩትዩብ ፖሊሲ ከክፍያ ስርዓቱ ከሚያስወጣቸው ቪድዮዎች ውስጥ፤ በኤአይ የተፈጠሩ ይዘቶች፤ በተለይም በኤአይ የተፈጠሩ ድምጾች ላይ የሚመረኮዙ ወይም በአነስተኛ ቪድዮ ኤዲቲንግ፣ በድጋሚ የሚጫኑ የሌሎች ሰዎች ይዘቶች እንደሚገኙበት የሕንዱ ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል።
7
#Ethiopia🇪🇹

ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።


በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች "  በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2
ከህመም ጋር እየታገለ የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ያጠናቀቀው ብርቱው "አሉዲን"

ተማሪ አሉዲን ሁሴን ይባላል። የበደሌ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነው። የ12ኛ ከፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቆ የመፈተኛ ቀኑ ሲደርስ ሕመም ያጋጥመዋል።
ተማሪ አሉዲን ህክምና ሂዶ ምርመራ ሲያደርግ የትርፍ አንጀት እንደሚገኝበት በዶክተሮቹ ይነገረዋል።

በዚህ አጋጣሚ ጭንቀት ውስጥ የገባው ጎበዙ ተማሪ ሕመሙ ፈተናውን መጨረስ የሚያስችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ ት/ቤቱ ከዶክተሮቹ ጋር በመነጋገር መዳኒት እየወሰደ እንዲፈተን መደረጉን የት/ቤቱ ር/መምህር አቶ ይልማ ገቢሳ ተናግረዋል።

ህክምና እየተደረገለት ለ3 ቀን ሲሰጥ የነበረውን የማሕበራዊ ሳይንስ ፈተና በትናንትናው ዕለት አጠናቆ ቀዶ ጥገና እንደሚደረግለት አቶ ይልማ ጋቢሳ ገልፀውልናል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በፈተና ጣቢያው ተገኝተው የፈተናውን ሂደት በጎበኙበት ወቅት ፣ ተማሪውን አበረታተዋል።

ሃገር የምትገነባው ፣ ችግርን ተቋቁመው ዓላማቸውን ለማሳካት በሚጥሩ እንደ አሉዲን ባሉ ብርቱ ዜጎች ጥረት ነው ብለዋል።
👏62👍2
🕺MUSIC #TIME💃
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ehsan Abduselam - Hararia
👁 91.1K 👍 794
📥 09.01.2010
👤 diretube2010
🕒 06:08
3🤗1