#National_id
Nnational id ተመዝግባችሁ በተለያዩ ምክነያቶች FIN እና FAN ቁጥር የሌላችሁ ማለትም:-
🔵እስከ አሁን ካልተላከላችሁ።
🔵ስልካችሁ ከጠፋባችሁ።
🔵በተለያዩ ምክነያቶች delete ከሆነባችሁ።
እንደዲሁም በተመሳሳይ ምክይያቶች ካጣችሁት መልሳችሁ የምታገኙበትን መንገድ እናሳያችሁ።
በመጀመሪያ *9779# ትደውላላችሁ።
በመቀጠል የነዋሪ አገልግሎት የሚለውን ትመርጣላችሁ። (አሁን ላይ 1 ላይ ስለሚገኝ 1ን ትፅፋላችሁ)
በመጨረሻም 1 ቁጥርን መምረጥ በድጋሚ ማስላክ ትችላላችሁ።
ማሳሰቢያ የብሄራዊ መታወቂያ FIN እና FAN ማስላክ የምትችሉት ስትመዘገቡ በሰጣችሁት ስልክ ቁጥር ብቻ ነው።
🔗@amharictutorialclass

❤6👍5
''በገንዘብ ከሚበልጡህ ሰዎች ጋር ስትውል አሳ ይመግቡሀል በውቀት ከሚበልጡህ ሰዎች ጋር ስትውል ደግሞ አሳ ማጥመድንም አሳ መመገብንም ያስተምሩሀል።
ምርጫው ያንተ ነው።
ምርጫው ያንተ ነው።
❤8👍7🔥2
ድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ
"ከማንችስተር ዩናይትድ ከፍተኛ ደሞዜን ስቀበል በጣም ደስተኛ ነበርኩ" አባቴም በዛ ወቅት "ልጄ ሆይ ገንዘብህን አታባክን ድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ አንተ ብቻህን ትቀራለህ" አለኝ.....
"ችግር እስኪገጥመኝ ድረስ እነዚህን ቃላት አልገባኝም ነበር እና ብዙ ጓደኞቼ በየግዜው ይመጡ ነበሩ:: ጓደኞቼ ግን እኔን ለማየት እንዳልመጡ አስተውል ነበር። በችግሬ ወቅት ግን አጠገቤ የነበሩ ሰዎች የቅርብ ቤተሰቤ ብቻ ናቸው። ይህ ሕይወት ነው!!
"ሚስቴ እንኳ ልክ ከእግርኳስ ጨዋታ ስታገድ እና ዝናዬም ሲጠፋ ከእኔ ራቀች። ሚስቴ ከእኔ ጋር የነበረችው ለገንዘብ እና ለዝና ብቻ ነበር።"
ፖል ፖግባ

❤5👍4
ምንም ነገር ለዘለዓለም አይቆይም!
ምንም እንኳን ብዙ ዓመታትን ቢያስቆጥር፣ አንበሳ ተጎሳቁሎ መሞቱ አይቀርም። ይህ የዓለም እውነታ ነው። አንበሶች በዘመናቸው ገዥ ናቸው። ሌሎች እንስሳትን ያሳድዳሉ፣ ይይዛሉ፣ ይጎትታሉ፣ ይበላሉ፤ ትራፊያቸውንም ለጅቦች ሳይቀር ትተውላቸው ይሄዳሉ።
ነገር ግን እድሜ ፈጣኑ እገሰገሰ ከች ይላል። ያረጀው አንበሳ ማደን አይችልም። መግደል አይችልም፣ ራሱን እንኳን መከላከል አይችልም። ከቦታ ቦታ ይዘዋወራል፣ ያገሳል። ግን እድል አይቀናውም። በጅቦች መንጋ ውስጥ ይወድቅና ከነ ሕይወቱ ይበላል። ጅቦቹ እስኪሞት እንኳን አይጠብቁትም።
ሕይወት አጭር ናት። ኃያልነትም ጊዚያዊ ነው። አካላዊ ውበትም ጊዜው እጅግ አጭር ነው። በአንበሳ ማየት ይቻላል። እርጅና በተጫጫናቸው ሰዎችም ማየት ይቻላል። ማንኛውም ረጅም እድሜ የኖረ ሰው የደካማነትና አቅመቢስነት ጊዜው ላይ የሆነ ወቅት ላይ መድረሱ አይቀርም።
ስለዚህም፣
ምንም እንኳን አንበሶቹ በተፈጥሯቸው አዳኝ ስለሆኑ የሕይወት መስመራቸውን መቀየር የማይችሉ ቢሆንም፣ የሰው ልጅ ግን በተሰጠው ከፍተኛ የአስተሳሰብ ጥበብ ሁሉን ነገር መቀየርና ማስተካከል የሚችል ፍጡር ነው። እናም ትሕትናን እንላበስ፣ የደከሙትን፣ የታመሙትን፣ የተጠቁትን እንርዳ። ከሁሉ በላይ መርሳት የሌለብን አንድ ቀን መድረኩን ለቀን እንሄዳለን።

👍2❤1
ስልክ ተደውሎልን ስልኩን አንስተን በተለምዶ 'ሄሎ' እንላለን። ግን 'Hello' ማለት ምን ማለት ነው ግን
'Hello' ሰላምታ ብቻ ሳይሆን የአንድ የተወሰነ ሰው ስም እንደሆነ ሲያውቁ ብዙዎችን ሊያስገርም(ሊያስደንቅዎ) ይችላል። 'Hello' በእውነቱ የአሌክሳንደር ግርሃም ቤል እጮኛዋ Margaret Hello ስም ነበር። የስልክ ፈልሳፊው ቤል በፈጠራው
የመጀመሪያ ሙከራ ወቅት ''Hello' ን እንደ መጀመሪያው ቃል ተጠቅሟል። ይህ ቀላል ንግግር እስከ ዛሬ ድረስ ስልኩን ስናነሳ እንደ ሰላምታ ጸንቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስልክ ጥሪዎች መደበኛ መክፈቻ ሆነ።

😁4👍1
⚙️ የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ጠፍቶባቹሀል? ከብዙ መፍትሔዎች ሁለቱን መንገዶች እንመልከት....
- የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro"ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ ነዉ የምታገኙት ።
- ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡
1 መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን
2 ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡
3 ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡
4 “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል
5 ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኃላ Spotmou Bootsuite 2012 Application ይከፈትልናል
6 ከአፕልኬሽኑ ላይ Password and Key Finder የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡
7 Admin Password Resetter የሚል መንካት፡፡
8 Please select the target widows ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ ቀጥሎ “please select the target user ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን User Account መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡
9 መጨረሻ ላይ Password is reset successfully የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡
10 ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል

❤3
የ6ኛ ክፍል አስተዳደር አቀፍ ፈተና ቅሬታ አቀራረብን ይመለከታል
የ6ኛ ክፍል አስተዳደር አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ ማንኛውንም ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ወይም ወላጆች ቅሬታቸውን ለትምህርት ቤቱ ብቻ ማቅረብ እንዳለባቸው እናሳውቃለን።
በመቀጠልም ትምህርት ቤቶች የተቀበሏቸውን ቅሬታዎች በአግባቡ አደራጅተው እስከ ሐሙስ፣ ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ልብ ይበሉ፦
የትምህርት ቢሮው ከተገለጸው የአሠራር መመሪያ እና የጊዜ ገደብ ውጪ በቀጥታ ከግለሰቦች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
Via @tegene

❤1👍1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩቲዩብ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ክፍያ መፈጸም ሊያቆም ነው
ግዙፉ የቪድዮ ማሰራጫ ዩቲዩብ በብዛት የተመረቱ እና ተደጋጋሚ ቪድዮዎችን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መጋራት ስርዓት እንደሚያስወጣ አስታወቀ።
የፖሊሲ ማሻሻያው ሰው ሠራሽ አስተውህሎትን (ኤአይ) በመጠቀም የሚሰሩ ይዘቶችን ጨምሮ ከዩቲዩብ የክፍያ ስርዓት እንደሚያስወጣ ተገምቷል።
ለዚህም ዩቲዩብ ይዘት ፈጣሪዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ሆነው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው "ኦርጅናል" እና "እውነተኛ" ቪድዮዎችን እንዲለቅቁ እንደሚያስገድድ አስታውሷል።
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ ይህንን መስፈርት ቁጥጥር የሚያደርግበትን አሰራር እንደሚያሻሽል ገልጿል።
አዲሱ ማሻሻያ የሚደረገው በብዛት የተመረቱ እና ተደጋጋሚ ይዘቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየት እንደሆነ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
አዲሱ የዩትዩብ ፖሊሲ ከክፍያ ስርዓቱ ከሚያስወጣቸው ቪድዮዎች ውስጥ፤ በኤአይ የተፈጠሩ ይዘቶች፤ በተለይም በኤአይ የተፈጠሩ ድምጾች ላይ የሚመረኮዙ ወይም በአነስተኛ ቪድዮ ኤዲቲንግ፣ በድጋሚ የሚጫኑ የሌሎች ሰዎች ይዘቶች እንደሚገኙበት የሕንዱ ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል።

❤7
#Ethiopia🇪🇹
ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።
በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።
በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።
ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች " በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።
ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

❤2
ከህመም ጋር እየታገለ የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ያጠናቀቀው ብርቱው "አሉዲን"
ተማሪ አሉዲን ሁሴን ይባላል። የበደሌ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነው። የ12ኛ ከፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቆ የመፈተኛ ቀኑ ሲደርስ ሕመም ያጋጥመዋል።
ተማሪ አሉዲን ህክምና ሂዶ ምርመራ ሲያደርግ የትርፍ አንጀት እንደሚገኝበት በዶክተሮቹ ይነገረዋል።
በዚህ አጋጣሚ ጭንቀት ውስጥ የገባው ጎበዙ ተማሪ ሕመሙ ፈተናውን መጨረስ የሚያስችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ ት/ቤቱ ከዶክተሮቹ ጋር በመነጋገር መዳኒት እየወሰደ እንዲፈተን መደረጉን የት/ቤቱ ር/መምህር አቶ ይልማ ገቢሳ ተናግረዋል።
ህክምና እየተደረገለት ለ3 ቀን ሲሰጥ የነበረውን የማሕበራዊ ሳይንስ ፈተና በትናንትናው ዕለት አጠናቆ ቀዶ ጥገና እንደሚደረግለት አቶ ይልማ ጋቢሳ ገልፀውልናል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በፈተና ጣቢያው ተገኝተው የፈተናውን ሂደት በጎበኙበት ወቅት ፣ ተማሪውን አበረታተዋል።
ሃገር የምትገነባው ፣ ችግርን ተቋቁመው ዓላማቸውን ለማሳካት በሚጥሩ እንደ አሉዲን ባሉ ብርቱ ዜጎች ጥረት ነው ብለዋል።

👏6❤2👍2