Amhara Medical Association(AMA)
499 subscribers
189 photos
1 video
18 files
142 links
Amhara medical Association is all about quality of medical care and physicians satisfaction in the nation.
Download Telegram
Only 7% of Mothers in the region have ANC follow up with doctors but the regional health bureau become the pushing factors for Gynecologists to leave the region.
Look at early childhood deaths and the regional health bureau unable to employ pediatricians to the primary hospitals.
What health indicator has been improved for the last 3-4 years?
(EDHS 2021)
ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ኢድ ሙባረክ
መረጃ
የአማራ ህክምና ማህበር ዛሬ በ21/10/2015 የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ያደርጋል::በዚህም ወቅታዊ የማህበሩን ቁመና በመገምገም አባላቱና ማህበረሰቡ የሚጠብቅበትን ሚና ለመወጣት ውሳኔ ያሳልፋል::የተጓደሉና የደከሙ አመራሮችንም ይቀይራል ተብሎ ይጠበቃል::
ህዝባችን ካለበት የአገልግሎት ጥራት ችግርና የጤና ባለሙያው ከሚደርስበት ሁሉን አቀፍ በደል አንፃር ማህበራችን ከፍተኛ ትግል ማድርግ እንዳለበት ይሰማናል::በመሆኑም በቅርብ ጊዜያት ወደ ሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ቅርንጫፎችን የመክፈትና የማደራጀት እንዲሁም ተልእኮዎችን የምንሰጥ በመሆኑ ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ እናሳስባለን::
የአማራ ህክምና ማህበር
የአማራ ህክምና ማህበር ትናንት የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ማድረጉ ይታወቃል::
በዚህም የማህበሩ ወቅታዊ ቁመና በጥልቀት በመገምገም የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል ::
1. በሁሉም የክልሉ ሆስፒታሎች ተወካይ እንዲኖረውና ጠንካራ መዋቅር እንዲፈጠር
በዚህ አጋጣሚ የክልሉን የጤና ስርዓት በውጤታማነት ለመሞገትና የባለሙያውን መብት ለማስከበር ሰፊና ጥልቀት ያለው መዋቅር አስፈለጊ በመሆኑ የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች በየአካባቢያችሁ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን::
2.ማህበሩ ሰፊ ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እንደማቀፉ CPD ሰጭ ተቋም እንዲሆንና ለዚህም እንቅስቃሴ እንዲጀመር
3.በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ሰፊ የስልጠና,የፕሮጀክትና የጥናት ስራዎች እንዲሰሩ ወዘተ አቅጣጫ በማስቀመጥ የስራ ድርሻ ክፍፍል ተሰጥቷል ::
በዚህ ጋር ተያይዞ ማህበሩ የራሱ ቢሮና ፀሀፊ ኖሮት ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዲሆን ከአባላቱ ከፍተኛ ድጋፍ ይፈለጋል::
በመጨረሻም በተጓደሉ ዳይሬክተሮች ቦታ እስከ ጉባኤ ድረስ ስምሪት እንዲሰጥ የተወሰነ ሲሆን ሰሞኑን ለታየው የአባላት ተሳትፎ ምስጋናውንም አቅርቧል::
የአማራ ህክምና ማህበር ትናንት የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ማድረጉ ይታወቃል::
በዚህም የማህበሩ ወቅታዊ ቁመና በጥልቀት በመገምገም የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል ::
1. በሁሉም የክልሉ ሆስፒታሎች ተወካይ እንዲኖረውና  ጠንካራ መዋቅር እንዲፈጠር
በዚህ አጋጣሚ የክልሉን የጤና ስርዓት በውጤታማነት ለመሞገትና የባለሙያውን መብት ለማስከበር ሰፊና ጥልቀት ያለው መዋቅር አስፈለጊ በመሆኑ የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች በየአካባቢያችሁ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን::
2.ማህበሩ ሰፊ ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እንደማቀፉ CPD ሰጭ ተቋም እንዲሆንና ለዚህም እንቅስቃሴ እንዲጀመር
3.በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ሰፊ የስልጠና,የፕሮጀክትና የጥናት ስራዎች እንዲሰሩ ወዘተ አቅጣጫ በማስቀመጥ  የስራ    ድርሻ ክፍፍል ተሰጥቷል ::
በዚህ ጋር ተያይዞ ማህበሩ የራሱ ቢሮና ፀሀፊ ኖሮት ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዲሆን ከአባላቱ ከፍተኛ ድጋፍ ይፈለጋል::
በመጨረሻም በተጓደሉ ዳይሬክተሮች ቦታ እስከ ጉባኤ ድረስ ስምሪት እንዲሰጥ የተወሰነ ሲሆን ሰሞኑን ለታየው የአባላት ተሳትፎ ምስጋናውንም አቅርቧል።
AMA letter to Hospitals.pdf
282.7 KB
Dear Respected AMA members and supporters ,we kindly invite you to be active and select your genuine representative .
የማህበራችን ስራ አስፈፃሚ ባለፈው ሰኔ 21/2015 ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ማህበሩን የሚያጠናክሩ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል::በዚህ መሠረት ጠንካራ ተወካዮች በየሆስፒታሉ ሊኖሩት ይገባል::ስለሆነም በየሆስፒታላችሁ የሀኪሙን መብት ለማስከበር የሚሰራ,የጤና ስርዓቱን በእውቀት የሚሞግትና ከግላዊ ፍላጎቱ ባለሙያውን ያስቀደመ ተወካይ እንድትመርጡ መልዕክት እያስተላለፍን ቀጣይ ርምጃዎችን የምናሳውቅ ይሆናል::የተመረጡት ተወካዮች ከስራ አስፈፃሚው ጋር ስለቀጣይ ስራዎች በቅርብ ቀን የሚመክሩበት ስብሰባ እንደሚኖር ከወዲሁ እንጠቁማለን::
የአማራ ህክምና ማህበር
ማስታወሻ
የአማራ ህክምና ማህበር በየ ሆስፒታሎች ተወካይ እንዲኖረው ደብዳቤ መፃፉ ይታወሳል::
በርካታ ሆስፒታሎች ምላሽ እየሰጡን ቢሆንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ መድረስ አልቻልንም ::ስለሆነም ደብዳቤው ሁሉንም የአማራ ሀኪም የሚመለከት ሲሆን ዓላማውም ጠንካራ የሀኪሞች ማህበር በመፍጠር የሀኪሙንና የተገልጋዩን መብት የሚያስከብርበት አቅም መፍጠር ነው::ስለሆነም እስከተጠቀሰበት ቀን ድረስ ተወካዮቻችሁን እንድታሳውቁን በድጋሚ እንጠይቃለን::በግል ሆስፒታሎችና በጤና ጣቢያ ለምትሰሩ ሀኪሞች በቅርብ ቀን አማራጭ የምናመጣ ይሆናል::
የአማራ ህክምና ማህበር
Alert on public health emergency
በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ኮሌራ መሠል ወረረሽኝ መከሰቱ ታውቋል::በዚሁ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውንና በሺዎች ሚቆጠሩ ምልክቱን ያሳዩና ንክኪ ያላቸው ለይቶ ማቆያ ላይ መሆናቸው ተረጋግጧል::
በሌላ በኩል ንክኪ ያላቸው ሰዎች ከቦታው ወደ መሀል ሀገር እየመጡ ስለሆነ የበሽታውን ስርጭት አስከፊ እንዳይሆን የአማራ ህክምና ማህበር ስጋት አድሮበታል::
በመሆኑም ጤና ቢሮውና መንግስት በአስቸኳይ ርብርብ እንዲያደርግ እናሳስባለን::
1.በህመም ስቃይ ያሉ ታካሚዎችን ህይዎት ለማትረፍ በቂ የባለሙያና የግብዓት አቅርቦት በአስቸኳይ ወደ አካባቢው እንዲላክ እናሳስባለን::የህክምና ባለሙያዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሙሉ መከላከያ እቃዎች(PPE) እንዲሟላላቸው በጥብቅ እናሳስባለን::
2.የአካባቢው አስተዳደር የሰዎችን እንቅስቃሴ ላይ ገደቡን አጠናክሮ እንዲቀጥል ና ህብረተሰቡም ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን::ታካሚዎችና የአካባቢው ነዋሪች ሙሉ ህክምና በአቅራቢያቸው ስለሚያገኙ ወደ ጎንደር ከተማና ሌሎች አካባቢዎች የሚደረጉ ጉዞዎችን እንዲቀንሱና የህብረተሰቡን ጤና እንዲጠብቁ እንጠቁማለን::
3.ጎንደር ዩኒቨርስቲን ጨምሮ አቅራቢያ ያሉ ጤና መምሪያዎችም የህብረተሰብ ጤና አደጋ (public health emergency) መከሰቱ ታውቆ ጥንቃቄና ዝግጅት እንዲያደርጉ እያሳሰብን ማህበራችንም ለየትኛውም ግዳጅ ዝግጁ መሆኑን እንገልፃለን::
👍1
የውይይት ጥሪ
የአማራ ህክምና ማህበር ራሱን ለማጠናከርና የተቋቋመለትን ዓላማ ለማስፈፀም በሁሉም የክልሉ ሆስፒታሎች ተወካይ እያስመረጠ መቆየቱ ይታወቃል::
በዚህም ሁሉም ሀኪሞች ላደርጋችሁት ደማቅ ተሳትፎ እያመሰግን ለቀጣይ ስራዎች የጋራ አቋም ለመያዝ ለሁሉም የሆስፒታል ተወካዮች የውይይትና የስልጠና መድረክ አዘጋጅተናል::
1 .ለምዕራብ አማራ አካባቢ ሆስፒታሎች ማለትም ለሁሉም የጎንደር ዞኖች ወልቃይትን ጨምሮና ለሁሉም የጎጃም ዞኖች ቅዳሜ ሀምሌ 15/2015 ዓም በባህርዳር ሆምላንድ ሆቴል የሙሉ ቀን ስልጠና ውይይት ይኖረናል::
2.ለምስራቅ አማራ ማለትም ለሸዋ,ወሎና ዋግ ህምራ ደሴ ላይ ተመሳሳይ ዝግጅት ይኖረናል::ቀንና ቦታውን ከባህርዳሩ ውይይት በኃላ በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል::
በመጨረሻም በምዕራብ አማራ አካባቢ ያላችሁ ሁሉም ተወካዮች ለቅዳሜ ውይይት ነገ ባህርዳር ገብታችሁ እንድታድሩ እያሳሰብን ለዝርዝር ሁኔታ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚዎችን ማነጋገር ትችላላችሁ::
ዛሬ የአማራ ህክምና ማህበር ከምዕራብ አማራ ሆስፒታል የማህበሩ ተወካዮች ጋር የተሳካ ወይይት አካሄደ::
ውይይቱ የአጥንት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስትና የማህበሩ የቀድሞው ፕ/ት ዶር በቃሉ ባቀረቡት career development and leadership እና ወጣቱ ምሁር ዶር የሻንበል አግማስ leadership and health system ላይ ባቀረቡት በሳል ፅሁፍ የተጀመረ ሲሆን ማሳረጊውን በቅርንጫፎች ምርጫ ያደረገ ነበር::
በውይይቱ ማህበሩ ክንፉን አድሶ ለባለሙያውና ለህብረተሰቡ የሚያደርጋቸውን አበርክቶዎች የሚያጠናክርበት መንገድ ላይ አድምቶ ተወያይቷል::የህዝባችን የጤና አገልግሎት መሻሻል እንደሚገባውና የአማራን ህዝብ የሚመጥንና ዘመኑ ከደረሰበት የህክምና ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባው በአፅንኦት ተነስቷል::በተያያዘም የጤና ስርዓቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የህክምና ባለሙያው ጤናውና የጤና ወጪው እንዲጠበቅለት,በሀገሩ ቤት ኖሮት ከስደት የሚቀርበት መንገድ መምጣት እንዳለበት ተነስቷል ::ሀኪሙ የላቡን መከፈል ቀርቶ ለመኖር እየተቸገረ እንደሆነና ለዚህም ትግል እንደሚያስፈልገው ስምምነት ላይ ደርሰናል::
በመሆኑም ሀኪሙ የአማራ ህክምና ማህበርን ማጠናከር እንደሚገባውና የማህበሩ መሪዎችም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ እንዲሁም ከሌሎች የጤና ማህበራት ጋር በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል::
በመጨረሻም በምዕራብ አማራ ስር 4 የማህበሩ ቅርንጫፎች ተቋቁመውና መሪዎችም ተመርጠው በድምቀት ተጠናቋል::
ምስራቅ አማራ ላይ መሠል ውይይት ኮምቦልቻ ላይ በ2 ሳምንት ውስጥ የምናካሂድ ይሆናል::
የአማራ ህክምና ማህበር
👍2