💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)
4.42K subscribers
283 photos
351 videos
4 files
350 links
💥የዚህ ቻናል ስራዎች በአሏህ ፍቃድ፦

ኢስላማዊ ፅሁፎች፣📜
ጠቃሚ ምክሮች፤📜
በሸይኽ አህመድ አደም የሚቀርቡ ሙሀዶራዎች፤ ፈትዋዎችን መልቀቅ ።


ስህተት ስታገኙ
👇👇👇👇👇
@Almutehabbot ያድርሱን።
Download Telegram
☀️ንጹህ የሆነ
ጌታውን የሚፈራ
መልካም የሚያስብ
ነገሮችን በቀጥታ የሚረዳ
በሸር ያልተሞላ ልብ(قلب ) የተሰጠ ሰው  
  ምንኛ የታደለ ነው?!

#Join_Share
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@almutehabin
@almutehabin
💥 እውነተኛ ጓደኞች
በ3 መገለጫዎች ይለያሉ‥
① እነሱን ማግኘት
② እነሱን መተው እና
③ እነሱን መርሳት ከባድ ነው ።
#Join_Share
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@almutehabin
@almutehabin
            
#ደህና_ዋሉ
☀️አዋቂነት

አዋቂነት ፕሮፋይል በመቀያየር ቢሆን ኖሮ
አዋቂነት ኦድዮዎችን ሼር በማድረግ ቢሆን ኖሮ
አዋቂነት በየግሩፑ አድሚን መሆን ቢሆን ኖሮ
አዋቂነት ቻናሎችና ግሩፖችን አብዝቶ ስልክን በማጨቅ ቢሆን ኖሮ
አዋቂነት የአካዉንት ስምን በየቀኑ አረበኛ እየፃፉ በመለዋወጥ ቢሆን ኖሮ
ከራሤ ጀምሮ ዓሊም ነበርኩኝ በዙሪያዬም አንድም ጃሂል ባልኖረ ነበር ሁላችንም ዓሊሞች ነበርን ግን ጉዳዩ እንዲያ አይደለም ሐባይቦቼ  አንገታችንን ደፍተን እንማር  እዉቀት በፕሮፋይል እዉቀት አድሚን በመሆን እዉቀት ቻናል በመክፈት  አይገኝም ይልቁንም ተግተን እንማር
!
@almutehabin
@almutehabin
💥ውዶችዬ ስሙኝማ!
☀️ህመምን መግለፅ

📌:ነብዩ  የሆነን ጀናዛ በበቂዕ መቃብር ቀብረው ሲመለሹ እናታችን ዐኢሻ رضي الله عنها "ወይኔ ራሴን" እያለች ህመሟን ስትገልጽ áˆ°áˆŸá‰ľáŠ“ ኧረ የኔ ይብሳል በሚል ሁኔታ "ኧረ ወይኔ ልሴ" ብለው መለሱላት።

📙:ኢብኑ ሒባን የዘገቡትና ሸይኽ አልባኒ ሶሒህ ያሉት~

💥እናም ህመምን መግለጽ (ማንቋረር) ክልክል አይደለም/አይጠላምም። ተፈጥሯዊ ጉዳይም ነው።

⚠️:ሀራሙ መብሳጨትና የአሏህን ዉሳኔ መቃወሙ ነው።


#Join_Share
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@almutehabin
@almutehabin
💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)
☀️ህመምን መግለፅ 📌:ነብዩ  የሆነን ጀናዛ በበቂዕ መቃብር ቀብረው ሲመለሹ እናታችን ዐኢሻ رضي الله عنها "ወይኔ ራሴን" እያለች ህመሟን ስትገልጽ áˆ°áˆŸá‰ľáŠ“ ኧረ የኔ ይብሳል በሚል ሁኔታ "ኧረ ወይኔ ልሴ" ብለው መለሱላት። 📙:ኢብኑ ሒባን የዘገቡትና ሸይኽ አልባኒ ሶሒህ ያሉት~ 💥እናም ህመምን መግለጽ (ማንቋረር) ክልክል አይደለም/አይጠላምም። ተፈጥሯዊ ጉዳይም ነው። ⚠️:ሀራሙ መብሳጨትና…
ህመሜ ሰሞኑን ደግሞ እጅግ በጣም እየተፈታተነኝ ነው።
ጥያቄና መልሱ ሊስተጓጎል ስለሚችል ዐፍ በሉኝ።
ራስ ምታት👈ስል እንደ ትንሽ ነገር አትዩት የኔ ለስም ብቻ ነው ራስ ምታት የተባለው እንጂ ህመሙ ራስ ምታት አይደለም። እሱን አላብራራላቹ ልተወው
አል ሙሂም ዛሬም አላዘጋጀሁም ሲነሳብኝ አይደለም ጥያቄ ለማውጣት ይቅርና ቁርኣን ከማድመጥ ውጭ ምንም አልሰራም ዐፍ በሉኝ ውዶች ሀቂቃ ከባድ ነው
ለሌላም ጊዜ በዚህ የተነሳ ላላወጣ ስለምችል ተረዱኝ ለማለት ነው።
ዐፍወን
💥وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا}

ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፡፡ በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም፡፡
@almutehabin
💥ውዶች ትንሽ ፈገግ በሉልኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇
💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)
💥ውዶች ትንሽ ፈገግ በሉልኝ 👇👇👇👇👇👇👇👇
☀️ፈገግ በሉ ፈገግታ ሱና ነው

በአንድ ሰአት ውስጥ 5 ሴቶችን የፈታው ሰውዬ ታሪክ

አስመዒ እንዲህ አሉ፦ አንድ ቀን ለሀሩን አል-ረሺድ እንዲህ አልኩት 👉 አንተ የምዕመናን አሚር ሆይ ! በአንድ ሰአት አምስት ሴት የፈታውን ሰውዬ ታሪክ ሰምተሀልን ? አልኩት

ከዚያም ሀሩን እንዲህ አለኝ፦ እንዴ ! አንድ ሰው ማግባት የሚፈቀድለት ከአራት ሚስት ብቻ ነው ታዳ እንዴት ብሎ ነው አምስት ሴት ሊፈታ የሚችለው ? አለኝ

ከዚያም እንዲህ አልኩት፦ ታሪኩን ልንገርህ ስማኝማ 👉 የሆነ ሰውዬ አራት ሚስቶች ነበሩት በአንድ ላይ አንድ ቤት ውስጥ ነበርና የሚያኖራቸው ከእለታት አንድ ቀን ልክ ቤት ሲገባ አራቶቹም ቀውጢ ጭቅጭቅ ሲጨቃጨቁ ያገኛቸዋል ፥

ሰውዬው ባህሪው አስቸጋሪ ነበርና ፥ እንዲህ አላቸው 👉 ቆይ እኔምለው እናንተ ግን እስከመቼ ነው ሁሌ እንዲህ እየተጨቃጨቃችሁ የምትኖሩት ?!!

ከመሃላቸው አንደኛዋን - እንደውም ሁልጊዜ ጭቅጭቅ የሚነሳው ባንቺ ሰበብ ነውና ካሁኗ ሰአት ጀምሮ ተፈተሻል አላት ፥

ከዚያ ሌላኛዋ ሚስቱ - እንዴ ምነው ለፍች ፈጠንክባትሳ ረጋ አትልምንዴ ምናለ በሌላ ነገር ብትቀጣት ? ስትለው 

ዝምበይ አንቺም ለራስሽ ተፈተሻል አላት ፥

ከዚያ ሶስተኛዋ ፡ አላህ ይምራህ ቆይ ግን ምን አይነት ሰው ነህ ወላሂ ሁለቱም ለአንተ ደግና መልካም ነበሩ ምነው ረጋ አትልም ነበር ? አለችው

አንቺ ራሱ የነሱን ውሌታ የምትቆጥሪ ተፈተሻል አላት ፥

ከዚያ አራተኛዋ 👉 በጣም ረጋ ሰከን ያለች ነበረች እንዲህ አለችው - ትገርማለህ ቆይ ግን ሚስቶችህን ከፍች ውጭ በሌላ ነገር መቅጣት አትችልም ነበርን ?! አለችው

አንቺ ራሱ ተፈተሻል አላት ፥

ይህ ሁሉ ሲካሄድ አንዲት ጎረቤቱ ስታይና ስትሰማ ነበርና "ጭንቅላቷን ብቅ አድርጋ - ወላሂ እንዳንተ ደካማ ሰው አይቼ አላውቅም ሚስቶችህን ከፍች በሌላ ነገር ረደብ ማስያዝ መቅጣት አቅቶህ ነው ሁላቸውንም በአንድ ሰአት የፈታሀቸው አጂጂጂብ አለችው ፥

አንቺ ራሱ በማያገባሽ ጥልቅ የምትይ ጥልቅ ስለሆንሽ ባልሽ ከፈቀደ ተፈተሻል አላት ፥

የሴትዮዋ ባል ቤቱ ውስጥ ሁኖ እየሰማ ነበርና ድምፁን ከፍ አድርጎ "ፈቅጃለሁ ፈቅጃለሁ አለ" አጂጂጂጂብ

📚 المستطرف في كل فن مستظرف لشهاب الدين الأبشيهي (495)ء
#Join_Share
👇👇👇👇👇
@almutehabin
@almutehabin
#ትዝብት

💥የሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ሶሏት ውስጥ ድምጽ ጮክ አድርጎ ኣሚን ማለትን የሚቃወሙ ሰዎች አሉ

🔅"ዐጧእ" በመባል የሚታወቁት ታላቁ ታቢዒይና የሰሓቢዩ ኢብኑ ዐባስ ተማሪ ግን እንዲህ ይላሉ

☀️እዚህ መስጂድ ውስጥ 200 የነቢዩን ሰሓቦች አግኝቻለሁ ኢማሙ  
ولا الضالين
ሲል እነሱ ኣሚን እያሉ
መስጂዱ ይንጋጋ ነበር)
ብለዋል
በይሀቂይ ዘግበውታል

☀️ነቢያችንስ ቢሆን ዐለይሂስሰላቱ ወስሰላም
" ኢማሙ
ولا الضالين
     ሲል ኣሚን በሉ" ብለው የለ እንዴ?!
#Join_Share
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@almutehabin
@almutehabin
☀️አንድን ሰው ካቆሰልከው በኋላ ሰውየው ዝምታው ከረዘመ አትጠራጠር ከንግግር በባሰ ሁኔታ እየቀጣህ ነው"።!!!!
@almutehabin
💥ያጀምዐ ሂስድ(ምቀኝነት) በዝቷል። ሲህር በየቦታው እየተስፋፋ ይገኛል ወልዒያዙ ቢላህ ግን ለምን??
በ አካዳሚክ ት/ት፣በሸሪዐ ት/ት፣በዱንያ ጥቅማ ጥቅም፣በመልክ፣በትዳር(በተለይ እኔን ካላገባሽ)፣ ወዘተ...... ዚክር ላይ እንበርታ በተለይ የጠዋት እና የማታ ዚክር!
አሏህን እንፍራ ስንገረም አሏሁመ ባሪክ፣አሏሁመ ዚድ ወላ ተንቁስ እንበል። ምቀኝነትም አይያዘን ካለብንም በዱዐ እናክሽፈው ባለቤቱን ለማጥፋት አንሯሯጥ።
አብሶ ሲህር👈በጣም ይከብዳል። አሏህ ያሽረን!
@almutehabin
💥ማነዉ ፈጅር ሶሏት የሚሰግደዉ?

የአሏህ በረከትና ረድኤት በፈጅር ሰጋጅ ላይ ይዉረድ!
የዙል-ሒጃህ ማስታወሻ

🔅ዛሬ ሃሙስ (ግንቦት 29/2016) ዙል-ቀዕዳህ 29 ሲሆን ምናልባትም ይህ ወር በ29 ካለቀ ነገ ጁሙዓህ ዙል-ሒጃህ 1 ስለሚሆን ኡድሒያ የማረድ እቅድ ያለው ሰው የዛሬ ቀን ጸሐይ ከመጥለቋ በፊት ሰውነት ላይ መነሳት ያለባቸው ጸጉሮችንና ጥፍርን ማንሳት ተገቢ ነው።

🔅ነቢዩ ﷺ በሐዲሣቸው የሚከተለውን ብለዋል፥ "አንዳችሁ ኡድሒያ ለማረድ ካሰበ የዙል-ሒጃህ ወር ከገባ በኋላ እርዱን እስኪፈጽም ድረስ ከጸጉሩና ከጥፍሩ ምንም አይንካ (አያንሳ)"

🔅ይህን ትዕዛዝ እንደ ግዴታ በማየት "ኡድሒያ የሚያርድ ሰው የዙል-ሒጃህ ጨረቃ ከታየበት ጊዜ አንስቶ የዒድ ሰላት ተሰግዶ እስኪታረድ ድረስ ጸጉርና ጥፍርን መቁረጥ ክልክል (ወንጀል) ነው" የሚሉ ሊቃውንት ስላሉ ከወዲሁ ጥፍርንና በሸሪዓህ የሚፈቀድን ጸጉር ማንሳት ይገባል።

🔅ይህ ህግ የሚመለከተው ኡድሒያ የሚያርደውን አባወራ ብቻ ነው።

ዛዱል-መዓድ
https://telegram.me/ahmedadem