AlltechUp.com
3.43K subscribers
603 photos
21 videos
6 files
290 links
etechup.com የቴክኖሎጂ አለምን ያዳርሳል! 🚀
የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱

ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡
Download Telegram
AlltechUp.com
በነገራችን ላይ . . .
በነገራችን ላይ . . .


1. 🙏 ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲ (በኢትዮጵያን የመጀመሪያው የAI ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰኔ ወር 2016 /June 2024/ ፀድቋል።

2. 🙏 የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII)
(በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 463/2012 መሠረት በጥር ወር 2012 የተቋቋመ)

👉 ኢንስቲትዩቱ ዘመናዊ የጥናትና ምርምር ማዕከላት፣ የData Center እና የፈጠራ ስራዎች የሚሰሩባቸው ላብራቶሪዎች በዚሁ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ።

3. 🙏 ቀደም ሲል በኮሚሽን ደረጃ የነበረው ተቋም በጥቅምት ወር 2001 (በአዋጅ ቁጥር 603/2001 መሠረት ወደ በጥቅምት ወር 2001 የኢትዮጵያ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርነት አድጓል:: አሁን ስያሜውን ወደ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቀይሮ በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት የሚመደብለት ነው::

🙏 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) ዘርፍ የማስተርስ (Masters) እና የዶክትሬት (PhD) ድግሪዎችን እያስተማረ ይገኛል::

🙏 ከአአ ዩንቨርስቲ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ለAI ስፔሻላይዝድ ትምህርቶች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ይገልጻል:: . . .
.
.
.
ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን የሚታይ እና የሚጨበጥ ለውጥ ቀርቶ በተለያዩ ቋንቋዎች ቀጣይነት እና ተከታታይነት ባለው መልኩ ለህዝብ ወቅታዊ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መረጃ ማጋራት አልተቻለም:: ችግሩ ምን ይመስላችኋል🤔
1🥰1
5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች (ክፍል 1)
🥰3
AlltechUp.com
5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች (ክፍል 1)
5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች (ክፍል 1)

---
1. Humata AI (https://www.humata.ai) - ረጅም ሰነዶችን ለመተንተን

👍 ረጅም የፒዲኤፍ (PDF) ፋይሎችን ለማንበብ፣ ጥያቄ ለመጠየቅና ፈጣን መልስ ለማግኘት የሚያገለግል ድንቅ Ai ነው። ይህ Ai አንድን ሰነድ በሰከንዶች ውስጥ በመተንተን፣ የምትፈልጉትን መረጃ ነቅሶ ያወጣል። በተለይ ውስብስብ የሆኑ የህግ ሰነዶችን ወይም ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በቀላሉ ለመረዳትና ጊዜ ለመቆጠብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): እስከ 60 ገጾች ያለውን ፒዲኤፍ በነፃ መተንተን ያስችላል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $1.99 USD (ለተማሪዎች) ወይም $9.99 USD (ለባለሙያዎች) ይጀምራል።
👉 ጥቅሙ: ክፍያ ሲፈጽሙ ያልተገደበ ገጾችን ማንበብና ብዙ ፋይሎችን በአንድ ላይ ማቀናጀት ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: የፒዲኤፍ (PDF) ፋይልዎን ወደ ድረ-ገጹ "Upload" አድርጉ። ከዚያም በቀኝ በኩል ባለው የቻት ሳጥን ላይ ጥያቄያችሁን ጻፉ።
👌 ምሳሌ: "የዚህ ጥናት ዋና ውጤቶች ምንድን ናቸው?" ወይም "በገጽ 15 ላይ የተጠቀሰው የህግ አንቀጽ ምን ይላል?" ብላችሁ ጠይቁት።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: መረጃውን ያገኘበትን ገጽ ጎላ አድርጎ ስለሚያሳይ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ይረዳል።
.
.
.
2. Consensus (https://consensus.app) - ለሳይንሳዊ ማስረጃዎች

👍 ለሳይንሳዊ ምርምሮች አስተማማኝና በማስረጃ የተደገፉ መልሶችን ከምርምር ጽሁፎች ለማግኘት ይረዳል። ከሌሎች ሰርች ኢንጂኖች የሚለየው፣ መልሶቹን የሚሰጠው ከታመኑ የአካዳሚክ መጽሔቶችና ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ ብቻ መሆኑ ነው። ተማሪዎች፣ መምህራንና ተመራማሪዎች ሳይንሳዊ ሀቆችን ያለ ጥርጥር ለማረጋገጥና ለጽሁፎቻቸው ዋቢ (Citation) ለማግኘት ይጠቀሙበታል።

👉 የነፃ አገልግሎት : ያልተገደበ ፍለጋ ማድረግ ይቻላል፣ ነገር ግን የጥናቶቹን ማጠቃለያ (AI Summary) ለማግኘት የተወሰነ ገደብ አለው።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $8.99 አካባቢ ይጀምራል።
👉 ጥቅሙ: ለምርምር ጽሁፎች ጥራት ያለው ማጠቃለያና ውጤቶችን ወደ Reference Manager ለመውሰድ ይረዳል።

👌 አጠቃቀም: በማፈላለጊያ ሳጥኑ ላይ አዎ ወይም አይደለም ተብለው ሊመለሱ የሚችሉ ሳይንሳዊ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።
👌 ምሳሌ: "ጫት መቃም ለጤና ጠቃሚ ነው?" ብላችሁ ስትጠይቁት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጥናት ጽሁፎችን አጠቃሎ "አዎ" ወይም "አይደለም" የሚል ሳይንሳዊ ምላሽ ይሰጣችኌል።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: "Synthesize" የሚለውን ቁልፍ ስትጫኑ የሁሉንም ጥናቶች አጠቃላይ ድምዳሜ በአንድ አንቀጽ ይሰጣችኌል።
.
.
.
3. Claude AI (https://claude.ai) – ለጥልቅ ጽሁፎች እና ትንተና

👍 ክላውድ ረጅም ጽሁፎችን በመጻፍ፣ በማጠቃለልና የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ኮዶችን በማስተካከል ረገድ እጅግ የተራቀቀ ነው። ከሌሎች የቻት ቦቶች በተለየ፣ እንደ ሰው ጥልቅ በሆነ ስሜትና ጥራት የመጻፍ ችሎታ አለው። ሰፊ መረጃዎችን በአንድ ጊዜ ተረድቶ ትንታኔ የመስጠት አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ለጸሃፊዎችና ለቢዝነስ ባለሙያዎች እንደ ቀኝ እጅ የሚያገለግል የፈጠራ ረዳት ነው። (በነገራችን ላይ OpenAi በሰሩ እህት እና ወንድም የተሰራ ነው)

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): እጅግ በጣም ምርጥ የሆነውን ሞዴል በነፃ መጠቀም ይቻላል (ነገር ግን በቀን ውስጥ ለጥቂት ሰዓታት የጥያቄ ገደብ አለው)።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): 'Claude Pro' በወር $20 መክፈል ያስፈልጋል።
👉 ጥቅሙ: ተጠቃሚ በሚበዛበት ሰዓት ቅድሚያ ማግኘትና ከነፃው ስሪት በ5 እጥፍ የበለጠ ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: ረጅም ጽሁፎችን (እስከ አንድ መጽሐፍ የሚደርሱ) በቻት ሳጥኑ ውስጥ upload ማድረግ
👌 ምሳሌ: "ይህንን የንግድ እቅድ (Business Plan) ገምግመህ ድክመቶቹን ንገረኝ" ወይም "ለአዲስ ድርጅት በሚሆን መልኩ አዘጋጅልኝ"።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: ክላውድ ከሌሎች AIዎች በተሻለ የሰውን ስሜት የተረዳና ተፈጥሯዊ የሆነ ጽሁፍ የመጻፍ ብቃት አለው።
.
.
.
4. Canva Magic Design (https://www.canva.com) – ለፈጣን ዲዛይን

👍 ካንቫ (Canva) አሁን ላይ የAI አቅምን በመጠቀም ማንኛውንም አይነት የግራፊክስ ዲዛይን በሰከንዶች ውስጥ መስራት ያስችላል። ጽሁፍ በመስጠት ማስታወቂያ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ፖስት ወይም ሎጎ ይሰራል። የዲዛይን እውቀት የሌለው ሰው ሳይቀር የባለሙያ ስራ የሚመስሉ ውጤቶችን ለማውጣት የሚያስችል ለአጠቃቀም ቀላል ሀኗል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): መሰረታዊ የAI ዲዛይን መሳሪያዎችና ብዙ ቴምፕሌቶች በነፃ ይገኛሉ።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): 'Canva Pro' በወር $12 ወይም በዓመት $120 አካባቢ ነው።
👉 ጥቅሙ: የክፍያ ጥቅሙ ሁሉንም ፕሪሚየም ምስሎች፣ ቪዲዮዎችና የAI ዳራ ማጥፊያ (Background Remover) መሳሪያዎችን ለመጠቀም ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: በካንቫ ውስጥ "Magic Design" የሚለውን ምረጡና የፈለጋችሁትን ርዕስ ጻፉ ወይም ፎቶ ጫኑ።
👌 ምሳሌ: "የቡና መሸጫ ሱቅ ማስታወቂያ ስራልኝ" በሉት፣ ብዙ አይነት አማራጭ ዲዛይኖችን ያሳያችኌል።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: ምስል ውስጥ ያሉ ሰዎችን ወይም እቃዎችን በAI አማካኝነት ለማጥፋት ወይም ለመቀየር (Magic Edit) ተጠቀሙበት።
.
.
.
5. Notion AI (https://www.notion.so/product/ai) -- ለማስታወሻ እና እቅድ ዝግጅት

👍 ማስታወሻዎችን ለመያዝ፣ ስራዎችን ለማቀድና ጽሁፎችን ለማረም የሚያገለግል የተቀናጀ የAI ረዳት ነው። የያዟቸውን የተዝረከረኩ ማስታወሻዎች በስርአት ለማስተካከል፣ የሰዋስው ስህተቶችን ለማረምና አዳዲስ የሃሳብ መነሻዎችን ለማፍለቅ እጅግ ምርጡ ነው። ለግል ስራም ሆነ ለቡድን ተግባራት ምርታማነትን ለመጨመርና መረጃን በተቀናጀ መልኩ ለመያዝ እጅግ በጣም ውጤታማ ነው።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): ኖሽን ራሱ ነፃ ነው፣ ነገር ግን የAI ረዳቱን ለጥቂት የሙከራ ጊዜ ብቻ መጠቀም ይቻላል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $8 እስከ $10 (ከኖሽን መደበኛ ክፍያ በተጨማሪ)።
👉 ጥቅሙ: ያልተገደበ የጽሁፍ ማሻሻያ፣ ትርጉምና የሃሳብ ማመንጨት አገልግሎት ለማግኘት ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: በኖሽን ገጽ ላይ "Space" ቁልፍን ስትጫኑ AIው ስራ ይጀምራል።
👌 ምሳሌ: የጻፉችሁትን የተዝረከረከ ማስታወሻ "ወደ ሠንጠረዥ (Table) ቀይርልኝ" ወይም "ለሚቀጥለው ሳምንት የጉዞ እቅድ አውጣልኝ"።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: የጽሁፍ ስህተትን ለማረም (Fix spelling and grammar) እጅግ በጣም ፈጣን ነው።
.
.
.
🥰31
5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች (ክፍል 2)
🥰3
AlltechUp.com
5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች (ክፍል 2)
5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች (ክፍል 2)

1. Perplexity AI (https://www.perplexity.ai) – ለተረጋገጠ መረጃ ፍለጋ

👍 Googleን ከመሳሰሉ የመረጃ መፈለጊያዎች ምንጮች (Sources) አሰባስቦ በዝርዝር የሚገልጽ Ai ነው። ማንኛውንም ጥያቄ ሲጠይቁት፣ መልሱን ከተለያዩ ድረ-ገጾች አቀናጅቶ ከመስጠቱም በላይ፣ መረጃውን ከየትኛው ገጽ እንዳገኘው ሊንኩን ያስቀምጣል። ይህም መረጃው ትክክል መሆኑን ራሳችን ለማረጋገጥና ተጨማሪ ንባብ ለማድረግ እድል ይሰጠናል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): መደበኛ ጥያቄዎችን ለመጠየቅና ምንጮችን ለማየት ሁልጊዜም ነፃ ነው።

👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): 'Perplexity Pro' በወር $20 ያህል።

👉 ጥቅሙ: ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች ለማግኘትና ለማጣራት ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: እንደ Google ማንኛውንም ርዕስ ጻፉ። መተግበሪያው ወቅታዊ መረጃዎችን ከኢንተርኔት አፈላልጎ ምንጮችን (Links) ጠቅሶ ይመልሳል።

👌 ምሳሌ: "በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ያለው የባንክ ወለድ መጠን ስንት ነው?"

👌 ጠቃሚ ነጥብ: "Focus" የሚለውን በመጫን ፍለጋችሁ በዩቲዩብ፣ በአካዳሚክ ጽሁፎች ወይም በዜና ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ ትችላላችሁ።
.
.
.
2. Gamma AI (https://gamma.app) -- ለPowerPoint ስላይዶች

👍 የርዕስ ስም ብቻ በመስጠት ፕሮፌሽናል የPowerPoint (Presentation) ስላይዶችን በሰከንዶች ውስጥ ለማዘጋጀት ይጠቅማል። ጽሁፉን፣ ምስሎችንና ዲዛይኑን በራሱ የሚያቀናጅ ሲሆን፣ እንደ አስፈላጊነቱ በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል። ለስብሰባዎች ወይም ለክፍል ውስጥ ገለጻዎች ውብና ሳቢ ስላይዶችን ያለ ድካም ለማዘጋጀት ለሚፈልግ ሰው ተመራጭ Ai ነው።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): መጀመሪያ ሲመዘገቡ 400 Credits ይሰጥዎታል። ይህም ጥቂት ስላይዶችን በነፃ ለመስራት ይበቃል።

👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $8 (Starter) ወይም $15 (Pro) ይጀምራል።

👉 ጥቅሙ: የክፍያው የGamma ምልክት (Watermark) ለማጥፋትና ያልተገደበ ስላይዶችን ለመስራት ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: "Create New" የሚለውን በመጫን "Presentation" ምረጡ። ከዚያም የርዕሳችሁን ስም ጻፉ፤ (ለምሳሌ፦ "ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅሞች")።

👌 ምሳሌ: AIው ዝርዝር አጀንዳዎችን ያወጣል፤ "Continue" ስትሉት በሰከንዶች ውስጥ ምስልና ጽሁፍ ያለው ስላይድ ያዘጋጃል።

👌 ጠቃሚ ነጥብ: ዲዛይኑን ለመቀየር "Edit with AI" የሚለውን በመጫን "ምስሎቹን ወደ ካርቱን ቀይርልኝ" ብላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ።
.
.
.
3. ChatPDF (https://www.chatpdf.com) – ከፋይሎች ጋር ለመወያየት

👍 ከፒዲኤፍ ፋይሎች ጋር እንደ ሰው "ቻት" ለማድረግና ፋይሉን ለማጠቃለል የሚያስችል Ai ነው። መጽሃፍትን፣ የጥናት ጽሁፎችን ወይም ማንኛውንም ሰነድ በመጫን፣ በውስጡ ስላለው ጉዳይ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ። ፋይሉን በደንብ ለሚረዳ ሰው ጥያቄ እንደማቅረብ ይቆጠራል፤ ይህም ረጅም ጽሁፎችን የማንበብ አሰልቺ ሂደት በውይይት እንዲተካ ያደርገዋል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): በቀን 2 ፒዲኤፍ (እስከ 120 ገጽ) እና 50 ጥያቄዎችን በነፃ ማቅረብ ይቻላል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $15 አካባቢ።
👉 የክፍያ ጥቅሙ: በቀን እስከ 50 ፒዲኤፍ ፋይሎችን (እስከ 2,000 ገጽ) ለመተንተንና ያልተገደበ ጥያቄ ለመጠየቅ ያስችላል::

👌 አጠቃቀም: ማንኛውንም የፒዲኤፍ ፋይል ድረ-ገጹ ላይ ጎትቶ ማስገባት (Drag and Drop)።

👉 ምሳሌ: "ከዚህ ሰነድ ውስጥ 5 የፈተና ጥያቄዎችን አውጣልኝ" ወይም "ይህንን ፋይል በ10 ነጥቦች አሳጥርልኝ" በማለት ማዘዝ ይቻላል::
👉 ጠቃሚ ነጥብ: ለፈተና ለሚዘጋጁ ተማሪዎች መጽሐፍን በቀላሉ ለመረዳት በጣም ይረዳል።
.
.
.
4. Otter.ai (https://otter.ai) -- ንግግርን ወደ ጽሁፍ ለመቀየር

👍 ኦተር በስብሰባዎች ወይም በትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚነገሩ ንግግሮችን በቀጥታ ወደ ጽሁፍ (Transcription) የሚቀይር ድንቅ Ai ነው። ንግግሩን ከመጻፍ ባለፈ፣ ዋና ዋና ነጥቦችን ለይቶ በማውጣት ማጠቃለያ ያዘጋጃል። በስራ ስብሰባ ላይ ቃለ-ጉባኤ መያዝ ሳያስፈልግ፣ በውይይቱ ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ በኋላ ላይ የተባለውን ሁሉ በጽሁፍ ለማግኘት ያስችላል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): በወር 300 ደቂቃ የንግግር ትርጉም (Transcription) በነፃ ይሰጣል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $10 አካባቢ ይጀምራል።
👉 የክፍያው ጥቅሙ ብዙ ደቂቃዎችን ለመጠቀም፣ የቪዲዮ ስብሰባዎችን (Zoom/Teams) በጥራት ቀድቶ ወደ ጽሁፍ ለመቀየር የላቀ እድል ይሰጣል።

👌 አጠቃቀም: በስብሰባ ወይም በትምህርት ሰዓት "Record" የሚለውን መጫን
👌 ምሳሌ: መተግበሪያው የሚነገረውን ሁሉ በጽሁፍ ይጽፋል፤ ስብሰባው ሲያልቅ ደግሞ "ማን ምን አለ?" የሚል ማጠቃለያ ያወጣል።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: በZoom ወይም Google Meet ስብሰባዎች ላይ እንደ ረዳት ገብቶ ቃለ-ጉባኤ እንዲይዝ ማድረግ ይቻላል።
.
.
.
5. WolframAlpha (https://www.wolframalpha.com) -- ለሂሳብ እና ሳይንስ

👍 ይህ መተግበሪያ ለሂሳብ፣ ለሳይንስና ለዳታ ትንታኔ ተብሎ የተሰራ "የእውቀት ሞተር" ነው። ውስብስብ የሆኑ የሂሳብ ቀመሮችን በደረጃ በማስላት ከመፍታቱም በላይ፣ ስለ ስታቲስቲክስ፣ ፊዚክስና ኬሚስትሪ ትክክለኛ መረጃዎችን ይሰጣል። ተማሪዎችና መሃንዲሶች ለስሌት ስራዎችና ለሳይንሳዊ ጥያቄዎች አስተማማኝ መልስ ለማግኘት በስፋት የሚጠቀሙበት የላቀ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): ለብዙዎቹ የሂሳብና የሳይንስ ጥያቄዎች መልሱን በነፃ ይሰጣል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): 'Pro' ስሪቱ በወር $5 USD አካባቢ (ለተማሪዎች) ወይም $7 USD (ለሌሎች) ነው።
👉 ጥቅሙ: ጥያቄው እንዴት ደረጃ በደረጃ (Step-by-step) እንደተሰራ ለማየትና ውጤቱን በፋይል ለማውረድ ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: በሳጥኑ ውስጥ ማንኛውንም ስሌት ወይም ሳይንሳዊ ጥያቄ ጻፉ።
👌 ምሳሌ: Derivative of log(x) * cos(x) ብላችሁ ስትጽፉ ደረጃ በደረጃ አሰራሩንና ግራፉን ያሳያችኋል።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: ስለ ሀገራት መረጃ ለማግኘትም ይጠቅማል፤ ለምሳሌ Ethiopia GDP vs Kenya GDP ካሉት የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ በግራፍ ያነጻጽራል።
.
.
.
#ጠቃሚ_ማሳሰቢያ
ለእነዚህ አገልግሎቶች ክፍያ ለመፈጸም በኢትዮጵያ ብር በቀጥታ መክፈል አይቻልም። የግድ የቪዛ (Visa) ወይም የማስተር ካርድ (Mastercard) ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል።
2🥰1😁1
ChatPDF - መተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ጓደኛ አድርጉት

PDF ፋይሎችን በቀላሉ ለማንበብ እና ለመረዳት የሚያግዝ ድንቅ Artificial Intelligence (AI) ነው። ጓደኛም ልትሉት ትችላላችሁ።

ረጅም ፒዲኤፎ ፋይሎችን ከምታነቡ #አጤሬራ ያደርግላችኋል። ኧረ እንዳውም ልክ እንደ ሰው ከሰነዱ ጋር "ለማውራትም" ያስችላችኋል። ለምሳሌ መደመር መጽሃፍ #Upload አድርጋችሁ ፖለቲካ ይዘቱን ብቻ አጤሬራ ይሰጣችኋል። ካሻችሁም ኢኮኖሚያዊ ይዘቱን መጠየቅ ትችላላችሁ። የተቃረኑ ሀሳቦችን ለይቶ እንዲያወጣላችሁም መጠየቅ ትችላላችሁ። ምንም ሳይሰለች ያላችሁትን ሁሉ ያደርግላችኋል።

በዛ ላይ ቋንቋ ይተረጉማል። ፋይሉ በእንግሊዝኛ ቢሆንም እንኳ በአማርኛ ብትጠይቁት ፈልጎ ላይም ልስላችኋል። ይሄ ሁሉ ሲሆን የሚሰጣችሁ መልስ ከየትኛው ገጽ ላይ እንደተወሰደ ይጽፍላችኋል። ይህም መረጃው ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችላችኋል።

ለሁሉም ሰው በጣም ጣቃሚ ቢሆንም ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች (ለፈተና/ለማጥናት ወይም የሪሰርች መጽሐፍትን በፍጥነት ለማገላበጥ) ከምርጦች ምርጥ ነው።

ሳይንሳዊ ጽሑፎችን በጥልቀት ለሚተነትኑ ተመራማሪዎች እንዲሁም ረጃጅም የሥራ ሪፖርቶችን፣ ስምምነቶችን፣ ውሳኔዎችን . . . ለመረዳት "በAi የሚሰራ ሚሳይል" ሊባል የሚችል ነው።

ChatPDFን መጠቀም (ለመጀመር) የሚጠበቅባችሁ ድረ ገጹ ላይ በመግባት PDF ፋይሉን "Upload" ማድረግ ብቻ ነው። 👋
AlltechUp.com
Photo
Ai በገሃዱ ዓለም ላይ የደቀነው አደጋ እና መፍትሄው
|
|
|
የሰው ሰራሽ ልህቀት (Ai) አደጋ ውሸቱ እውነት መምሰሉ ብቻ አይደለም፤ በዋነኝነት እውነቱ ውሸት መምሰሉ ነው:: ጥቂት የማይባሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚጋሩ ትክክለኛ ጽሁፎች፣ ፎቶግራፎች ወይም ቪዲዮዎች ላይ "Ai ነው" ለማለት ይሽቀዳደማሉ። "አይደለም" ሲባሉ እንኳን ማመን አይፈልጉም። 'Ai ነው!' ካሉ በአቋማቸው ደርቀው ይቀራሉ። ይሄ 'Ai ከሚፈጥረው ውሸት' በላይ እጅግ በጣም ከባድ ችግሮች የሚያስከትል ነው።

እውነተኛ የሆነን ነገር "ሰው ሰራሽ" ወይም "AI ነው" ብሎ መካድ የሚፈጥረው አደጋ ከቴክኖሎጂው በላይ በሰው ልጅ የሥነ-ልቦና እና የማህበራዊ መስተጋብር ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ያሳርፋል።

ዋነኛ አደጋው እውነትን የሚሸረሽር መሆኑ ነው:: ለአብነት "የአይን ምስክር" ወይም "የቪዲዮ ማስረጃ" እንደ መጨረሻ እውነት አድርጎ መቀበል የተለመደ ነበር። አሁን ግን ማንኛውም 'እውነተኛ ማስረጃም ቢሆን' "ይህ እኮ በAI የተፈበረከ ነው" በሚል መከላከያ ውድቅ ሲደረግ ይስተዋላል። ይህም እውነት በራሷ ብርሃን መቆም የምትችልበት አቅም የሚያዳክም ነው።

በሁለተኛ ደረጃ እውነታው እና ምናባዊው ዓለም ተቀላቅለው መለየት የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጥራል። በዚህ መሃል "እውነት" ቦታዋን እና ዋጋዋን ታጣለች። ይኸውም በAi የተፈበረከውንም እውነቱንም እኩል "የውሸት መረጃ" (በAi የተሰራ) አድርጎ መውሰዱ በቀጥታ ውሸታሞችን (አጭበርባሪዎችን) የሚጠቅም ያደርገዋል። ምክንያቱም አንድ ሰው ጥፋት ሲያጠፋ የሚያሳይ እውነተኛ ቪዲዮ ቢለቀቅ "በAI የተሰራው ነው" ብሎ ለመካድና ከቅጣት ለማምለጥ እድል ይፈጥርለታል።

በሌላ አባባል ሰዎች የትኛው እውነት ወይም ውሸት እንደሆነ ማወቅ ሲያቅታቸው ሁሉንም ነገር ማመን ያቆማሉ (ይህ ደግሞ ለፍትህ መዛባት ትልቁ በር ይከፍታል)።

በሦስተኛ ደረጃ የሰው ልጅ ማንነት እና የፈጠራ ክብርን ያጠፋል። አንድ ጸሐፊ ወይም ሰዓሊ ለዓመታት ደክሞ የሰራውን ስራ "ይኼማ በAI የተሰራ ነው" ተብሎ ሲገፋ የሚፈጥርበትን ስሜት ማሰብ አይከብድም።

አንድን እውነተኛ የጥበብ ውጤት "ማሽን/Ai ሰራሽ ነው" ማለት የሰውን ልጅ የመፍጠር አቅም መካድ ነው። ይህም "Essentialism" ከሚባለው የፍልስፍና እይታ አንጻር ሲታይ የሰውን ልጅ ልዩ የሚያደርገውን "ንቃተ ህሊና" እና "ልፋት" ዝቅ አድርጎ የማየት አደጋ ያስከትላል፤ ድጋሚ ተመሳሳይ የጥበብ ውጤት እንዳያበረክት ያደርገዋል። በአጠቃላይ የሰው ልጅ የጥበብ ጥረት እና የልፋት ውጤት ዋጋ ያጣል ማለት ነው።

የታሪክ ሰነዶች፣ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ትክክለኛነት ጥያቄ ላይ ይወድቃል። በሰዎች መካከል ያለው ማህበራዊ ትስስር እና መተማመንም ይላላል።

ይሁንና መፍትሄውም እንደ ችግሩ ውስብስብ ነው። የቴክኖሎጂ፣ የህግ፣ እና የግለሰብ የንቃተ ህሊና ለውጥ ቅንጅትን ይጠይቃል።

ይኸውም:-
1. የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች

ቴክኖሎጂው የፈጠረውን ችግር በከፊል በቴክኖሎጂው ራሱ መፍታት ይቻላል። ብዙውን ጊዜ የAi ይዘቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ በውስጣቸው የት እና በማን እንደተፈጠሩ የሚገልጽ የማይታይ 'ዲጂታል የውሃ ምልክት' በውስጣቸው ያካትታሉ። ለምሳሌ "C2PA" በመባል የሚታወቁ ስታንዳርዶች የተነሳበትን የካሜራ ዓይነት ጨምሮ በየትኛውም ሂደት የሚኖሩትን መለያዎች ያካትታሉ። በዚህም ዲጂታልም ሆኑ HardCopy ፎቶግራፎች የተነሱበት ቀን፣ ቦታ፣ የካሜራ ዓይነት . . . ይኖራቸዋል። (ፎቶግራፉን ኮምፒዩተር ላይ ገልብጡና Right Click አድርጋችሁ Proporty ከዛም Detail የሚለውን በመምረጥ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። አንድ ፎቶ ከተስተካከለ ወይም በAI ከተነካም "ታሪኩ" ላይ ምልክት ያሳያል።

Ai ራሱ በተወሰነ ደረጃ ማረጋገጥ ቢችልም ብዙ ዓይነት ስለሆነ የትኛውን መምረጥ እንዳለብን ባለማወቅ የመሳሳት እድላችን ሰፊ ነው:: በተጨማሪም Ai በቀጥታ "በAi የተሰራ ነው ወይም አይደለም" አይልም:: ምልክቶችን ነው የሚያብራራው:: የሚገመግምባቸው መለኪያዎች ራሳቸው በሌላ Ai ማጥፋት ስለሚቻል አይመከርም::

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መጠቀም የተሻለ ውጤት ያስገኛል::

|**| #ምስሎችን_ለማጣራት

👉 Google Reverse Image Search / Google Lens
ምስሉን በመጫን ወይም ሊንኩን በመስጠት ቀደም ሲል የት ቦታ ላይ እንደተለጠፈ ማየት ትችላለህ። ምስሉ አሮጌ ሆኖ ለአዲስ ወሬ ተዛብቶ የቀረበ መሆኑን በቀላሉ ያሳውቅሃል። (ነገር ግን በAi የተሰራ ይሁን አይሁን በቀጥታ መረጃ አይሰጥም)

👉 TinEye
ይህ መሣሪያ ምስሉ መቼ እንደተፈጠረ እና በጊዜ ሂደት ምን አይነት ለውጦች (Edits) እንደተደረጉበት ለማወቅ በጣም ተመራጭ ነው።

👉 InVID / WeVerify
ይህ በተለይ ለጋዜጠኞች የተሰራ የChrome Extension) ነው:: በቪዲዮዎች ውስጥ ያሉ ምስሎችን በመቆራረጥ ዋና ምንጫቸውን ይፈልጋል።
.
.
.
|**| #በAI_የተሰሩ_ጽሑፎችን ለመለየት

ምንም እንኳን እነዚህ መሣሪያዎች 100% ትክክል ባይሆኑም፣ አንድ ጽሑፍ በAi የመጻፍ እድሉ ምን ያህል እንደሆነ ፍንጭ ይሰጣሉ::

👉 GPTZero
በተለይም በትምህርት ተቋማት በጣም ተመራጭ እና በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ነው:: አንድ ጽሑፍ በAI የመጻፍ እድሉን የሚተነተን ትሩ አማራጭ ነው።

👉 Copyleaks AI Content Detector
የተለያዩ የAI ሞዴሎችን (እንደ ChatGPT, Gemini . . . ) አሻራ ማንበብ የሚችል ነው።

👉 Originality.ai
ጽሑፉ ከሌላ ቦታ የተቀዳ (Plagiarism) ይሁን ወይም በAI የተጻፈ ለመለየት ይረዳል።

|**| የቪዲዮ እና የድምጽ ትክክለኛነት
በአሁኑ ዘመን Deepfakes መለየት በጣም ፈታኝ ሆኗል:: ሆኖም በሚከተሉት አማራጮች በአብዛኛው መለየት ይቻላል::

👉 Deepware Scanner
ድረገጽ ሲሆን የቪዲዮ ፋይሎችን በመጫን የDeepfake ምልክቶች እንዳሉባቸው ይፈትሻል።

👉 Sensity AI
በአብዛኛው በክፍያ ሲሆን በነፃ ውስን አገልግሎት ይሰጣል:: ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን በመተንተን በAI የተለወጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል።

በተጨማሪም የሀሰት መረጃዎችን የሚያጋልጡ (Fact-checking) ድረ-ገጾችን እንደ (https://www.snopes.com) ወይም (https://www.poynter.org/ifcn/) መጠቀም ይቻላል::
|
|
|
🙏2. የህግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች

መንግስት ማናቸውም የAi ውጤቶች (በAI የተሰራ ይዘት) "በAI የተሰራ" የሚል ግልጽ ምልክት እንዲኖረው የሚያስገድድ ህግ ማውጣት አለበት:: በAi የተሰራ ሀሰተኛ መረጃን እውነት አስመስለው የሚያቀርቡ ወይም እውነተኛ መረጃን "AI ነው" በማለት ለክፋት ተግባር የሚጠቀሙ ሰዎችን እንደ "የፍትህ እንቅፋት" ቆጥሮ በከፍተኛ ደረጃ ተጠያቂ ማድረግ ይገባል:: ድርጊቱ በግልጽ ወንጀል ተደርጎ ከተቀመጠና ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ የድርጊቱ ፈጻሚዎች እንዲፈሩ እና እንዲቆጠቡ ያደርጋቸዋል::

ፍርድ ቤቶች እና የመንግስት ተቋማትም ዲጂታል ማስረጃዎችን ከመቀበላቸው በፊት ጥብቅ የሆኑ የቴክኒክ ማረጋገጫዎችን እንዲያልፉ የሚያስገድድ አሰራር መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል::

🙏 3. ግንዛቤ መፍጠር
AlltechUp.com
Photo
ይህ በጣም አስፈላጊው ክፍል ነው። እንደ ማህበረሰብ የመረጃ ትክክለኛነትን የምናጣራበትና የምንቀበልበት መንገድ በእውቀት/በግንዛቤ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት::

በዚህም መሰረት:-
👉 ምንጭን የማጣራት ባህል ማዳበር አለብን:: "አይቼ አመንኩት" ወይም በግምት "Ai ነው" የማለት አስተሳሰብ መቀየር አለበት::

በትምህርት ቤቶች በIT ወይም በተያያዥ የትምህርት መስኮች ላይ ተማሪዎች ዲጂታል ስነ-ዜጋ ወይም እውነተኛ እና የሀሰት መረጃን መለያ ዘዴዎችን እንዲማሩ #በካሪኩለም ማካተት ይገባል::

ማንኛውም ጽሁፍ፣ ፎቶ፣ የድምጽ ወይም የቪዲዮ መረጃ ሲደርሰን ወዲያውኑ (በወጉ እንኳን ሳንረዳ) ከመፍረድ ወይም ኮሜንት ላይ "Ai ነው" ከማለታችን በፊት ቆም ብሎ የማሰብ እና የማመዛዘንም ግንዛቤን ማሳደግም አግባብ ነው።

በአጠቃላይ በAi/በቴክኖሎጂ ዘመን ውስጥ እውነተኛ ሰው ሆኖ ለመገኘት/ለመቀጠል ዓይናችን የሚያየውን ሳይሆን አእምሮአችን የሚያመዛዝነውን የማመን ጥበብን ማዳበር ይገባል።
2
💡 #ጠቃሚ_መረጃ

ጎግል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሱማልኛን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎች የሰው ሠራሽ አስተውሎት የፍለጋ ማጠቃለያ (AI Overviews) አገልግሎቱ ላይ ማካተቱን አስታወቀ::

አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በSearch ማድረጊያው ላይ ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች በAI የተዘጋጀ አጭርና ግልጽ ማጠቃለያ ማግኘት የሚችሉበት ነው።

ጥያቄዎችን በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን በድምፅ እና በምስል (Google Lens) ላይ ጭምር ማቅረብ ይቻላል።

እንግሊዝኛ ለማይችሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ውስብስብ መረጃዎችን በራሳቸው ቋንቋ የሚያስችል በመሆኑ ጠቀሜታው የላቀ ነው።

#አጠቃቀም
ለምሳሌ አማርኛ አጠቃቀም:-
ብራውዘር (Browser) መክፈት፣ በመቀጠል ከስር ከተዘረዘሩት ቋንቋዎች "አማርኛ" የሚለውን መምረጥ፣ Search ማድረጊያ ላይ የምንፈልገው ጥያቄ በመጻፍ ፍለጋ ማስቀጠል በመጨረሻም "የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሁኔታ" የሚለውን መጫን ነው። መልሱን በአማርኛ ይሰጠናል። ከስር ባለው መጠየቂያ የፈለግነው ጥያቄ ብናቀርብለትም በአማርኛ መልስ ይሰጠናል። መጀመሪያ የጠየቅነው በኦሮምኛ ወይም በሶማልኛ ቋንቋ ከሆነም ሂደቱ ተመሳሳይ ነው። ትግርኛ እና አፋርኛ ወይም ሌሎች ቋንቋዎች ከመረጥን ግን መፈለጊያው ላይ "የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሁኔታ" የሚለው አይኖርም።

የአጠቃቀም #screenshot መግለጫ ከላይ ተያይዟል።🙋😍
👍3
👆👆Udemy - Agentic Ai Fundamentals
1
"AI Confidential: The Assassin and the Algorith (የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር፡ ገዳዩ እና አልጎሪዝም)" ; የቢቢሲ - ዘጋቢ ፊልም 👇👇
1
AlltechUp.com
BBC_AI_Confidential_3of3_The_Assassin_and_the_Algorithm_1080p_x265.mkv
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር (የቢቢሲ - ዘጋቢ ፊልም)
.
.
.


#BBC ከዜዎቹ በላይ በሚሰራቸው በአስደናቂ ምርምር የታገዙ ዘጋቢ (Documentary) ፊልሞቹ የገነነ ስም ነው። የቢቢሲ ዶክመንተሪዎችን ማየት የጀመረ ሰው በቀላሉ አይላቀቀም። ተጣብቆ ነው የሚቀረው🤗😁

ቢቢሲ ከሰራቸው ምርጥ ዘጋቢ ፊልም አንዱ "AI Confidential: The Assassin and the Algorith (የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር፡ ገዳዩ እና አልጎሪዝም)" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይጠቀሳል። በታዋቂዋ የሂሳብ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሃና ፍራይ (Professor Hannah Fry) የተዘጋጀ ነው።

አጠቃላይ ይዘቱ ሲጨመቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር ሲጋጭ የሚፈጠሩ አስደንጋጭ እና እውነተኛ ታሪኮችን ይዳስሳል።

የዘጋቢ ፊልሙ መልዕክት የተሳሰረ ቢሆንም ራሳቸውን በቻሉ ሦስት ክፍሎች የተቀነበበ ነው።
---
#ክፍል 1 - "The Boy who Tried to Kill the Queen" ነው። ይህ ክፍል የሚያተኩረው ጃስዋንት ሲንግ ቻይል በተባለ ወጣት ላይ ነው። ይህ ወጣት እ.ኤ.አ በ2021 የገና ዕለት የንግሥት ኤልሳቤጥን ሕይወት ለማጥፋት ቀስት ይዞ ዊንዘር ቤተ መንግሥት ጥሶ ሲገባ ያሳያል።

ወጣቱ "ሳራይ" (Sarai) ከተባለች የAI ቻትቦት (Chatbot) ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንደነበረ ይገልጻል። ከ5,000 በላይ መልዕክቶችን የተለዋወጡ ሲሆን የAI ሶፍትዌሩ ንግሥቲቱን እንዲገድልና "በሞት እንደገና እንደሚገናኙ" በማሳመን ለጥቃቱ ሞራልና ድጋፍ እንደሰጠው ያመለክታል።

ዋና ጭብጡም የAI ቻትቦቶች በሰዎች ሥነ-ልቦና ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ እና ሰዎችን ለከፋ ወንጀል እንዴት ሊያነሳሱ እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ ነው።
.
.
.
#ክፍል 2 - "Death by Driverless Car" ይላል። ይህ ክፍል በቴክኖሎጂ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን አደጋ ይመረምራል።

ታሪኩ እ.ኤ.አ በ2018 በአሪዞና፣ አሜሪካ ውስጥ በራሱ የሚነዳ (Driverless) የዩበር (Uber) መኪና መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረችውን ራፋኤላ ቫስኬዝ የተባለች ሴት ገጭቶ ይገድላል።

የመኪናው AI ሲስተም ሴቲቱን እንደ ሰው ለይቶ ማወቅ ተስኖት ነበር። ፊልሙ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትርፍን ለማሳደድ ሲሉ የሰውን ደህንነት እንዴት ችላ እንደሚሉ የሚዳስስ ነው።

በAI የሚመሩ ማሽኖች ስህተት ሲሠሩ ተጠያቂው ማን ነው? የሚለውን ሙግታዊ ጥያቄ ያነሳል።

#ክፍል 3 - "The Assassin and the Algorithm" ሲሆን ከቅርብ ጊዜው እና እጅግ አነጋጋሪ ከሆነው የሉዊጂ ማንጂዮን (Luigi Mangione) ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው። ይኸውም እ.ኤ.አ በታህሳስ 2024 የዩናይትድ ሄልዝ ኬር ( #unitedhealthcare ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሪያን ቶምፕሰን በኒውዮርክ መገደላቸው ይታወሳል። ተጠርጣሪው ሉዊጂ ማንጂዮን ነበር።

ከግድያ ታሪኩ በመነሳት የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የታካሚዎችን የሕክምና ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ AI አልጎሪዝምን እንደሚጠቀሙ ይተቻል። ፊልሙ አልጎሪዝም በሰዎች የሕይወትና የሞት ውሳኔ ላይ እንዴት ጣልቃ እንደሚገባና ይህም ወደ ከፍተኛ ብስጭትና ግድያ እንዴት ሊያመራ እንደሚችል ያሳያል።

የጤና ጥበቃ ሥርዓቱ በሰው ፈንታ በአልጎሪዝም ሲተካ የሚመጣውን ማህበራዊ ቀውስ በጥልቀት ይተነትናል።

---
በአጠቃላይ ዘጋቢ ፊልሙ AI ለሰው ልጅ የሚሰጠውን ጥቅም ሳይክድ፣ ነገር ግን የቁጥጥር ሥርዓት ከሌለና በሥነ-ምግባር ካልተመራ ሊያስከትል የሚችለውን የጥፋት አድማስ በዝርዝር ያሳያል።
.
.
.
እንድትመለከቱት የቴሌግራም link https://t.me/etechup/890?single ላይ አጋርቻለሁ። ዘጋቢ ፊልሙ በከፍተኛ ጥራት (.MKV/ Matroska Video file Format) የተዘጋጀ በመሆኑ በሁሉም #player ላያጫውትላችሁ ይችላል።

ስለሆነም :-
1. ለኮምፒውተር (Windows እና Mac)
* VLC Media Player
* KMPlayer
* PotPlayer
* GOM Player

2. ለስልክ (Android እና iOS)
* MX Player
* VLC for Mobile ፦
* nPlayer (ለ #iphone /iOS)

3. ለስማርት ቲቪ (Smart TV)
* አብዛኞቹ አዳዲስ ስማርት ቲቪዎች .mkv ፋይልን በራሳቸው ያጫውታሉ። ነገር ግን ካልከፈተ በቴሌቭዥናችሁ Play Store ውስጥ ገብታችሁ VLC ወይም Kodi በመጫን መጠቀም ትችላላችሁ።
1🔥1
AI ኤጀንት ፍሬምወርኮች፡
የአዲሱ ዲጂታል ዘመን የጀርባ አጥንት
.

.
.
:
AlltechUp.com
AI ኤጀንት ፍሬምወርኮች፡ የአዲሱ ዲጂታል ዘመን የጀርባ አጥንት . . . :
AI ኤጀንት ፍሬምወርኮች፡
የአዲሱ ዲጂታል ዘመን የጀርባ አጥንት
.
.
.
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስናወራ በአብዛኛው ትኩረታችን እንደ ChatGPT እና Gemini በመሳሰሉ የቋንቋ ሞዴሎች ላይ ነበር። እነዚህ ሞዴሎች መረጃን አቀናጅተው በመጻፍ፣ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ በመስጠት እና ከምንሰጣቸው ጽሁፍ ተነስተው አስደናቂ ምስሎች/ቪድዮዎች በመፍጠር እጃችንን በአፋችን አስይዘዋል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አውድ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ከጥያቄና መልስ አገልግሎት ሰጪነት ተሻግረዋል። የቴክኖሎጂው ቀጣዩ ምዕራፍ ራሱን ችሎ ተግባራትን ወደሚያከናውንበት "የኤጀንቶች ዘመን" ደርሷል። "ከማወቅ" አልፈው ራሳቸውን ችለው "ማድረግ" ጀምረዋል። በዚህ የሽግግር ሂደት ደግሞ የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች እንደ ዋና አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆን የፈጠራውን ዓለም እየመሩት ይገኛሉ።

"የኤአይ ኤጀንቶች" (AI Agents) በመባል የሚታወቁት አዳዲስ ስርዓቶች የሰውን የዕለት ተዕለት ጣልቃ ገብነት ሳይፈልጉ እቅድ ማውጣት፣ መረጃዎችን መተንተን፣ ውሳኔ መስጠት እና በተግባር እርምጃ መውሰድ የሚችሉ ናቸው። "ለምሳሌ፣ አንድን የኤአይ ኤጀንት 'በኢትዮጵያ ውስጥ የሞባይል ፋብሪካ ለመገንባት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ጥያቄ ፕሮፖዛል አዘጋጅተህ በኢሜይል ላክልኝ' ብለን ብናዘው፣ ኤጀንቱ ራሱ የፕሮፖዛሉን ርዕሶች ይመርጣል፣ መረጃዎችን ሰብስቦ ጥናት ያደርጋል፣ የንግድ ባንክን የፕሮፖዛል ፎርማት ከኢንተርኔት ፈልጎ ያዘጋጃል፣ በመጨረሻም በኢሜይል የመላክ ተግባሩን ያከናውናል። ይህንን ውስብስብ ሂደት በስኬት ለመምራት ግን ጠንካራ መሠረት ያስፈልጋል፤ ያ መሠረት "የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርክ" ይባላል።

የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች የሶፍትዌር አዘጋጆች (Developers) የኤአይ ኤጀንቶችን በቀላሉ ማልማት፣ ማሰልጠን እና ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችሉ የተደራጁ የሶፍትዌር ቤተ-መጻሕፍት (Libraries) እና መገልገያዎች ናቸው። አንድ የሶፍትዌር ኢንጅነር ሁሉንም የኤጀንቱ ውስብስብ አወቃቀሮች ከባዶ ከመጻፍ ይልቅ፣ ፍሬምወርኮች እንደ ዝግጁ የሚገጠሙ ክፍሎች (Building Blocks) ይጠቀምባቸዋል።

አንድ ውጤታማ የኤጀንት ፍሬምወርክ የሚከተሉት አምስት ቁልፍ አካላት ሊኖሩት ይገባል።

1. የማመዛዘን እና የውሳኔ አሰጣጥ ክፍል (Reasoning Module)፦ ይህ የኤጀንቱ "አንጎል" ነው። የተሰጡትን ግቦች ወደ ትናንሽ እና ሊተገበሩ ወደሚችሉ ደረጃዎች ይከፋፍላል፤ በማስከተልም ቀጣዩን ተገቢ እርምጃ ወይም መሳሪያ ይመርጣል።

2. የድርጊት መስተጋብር (Action Interface)፦ ኤጀንቱ ካሰበ በኋላ ወደ ተግባር የሚቀየርበት መስኮት ነው። ይህ ኤጀንቱ ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ዓለም (እንደ ድረ-ገጾች፣ ኢሜል፣ ወይም ዳታቤዝ) ጋር እንዲገናኝ ያስችለዋል። (በፕሮፖዛሉ የሚካተቱ አሃዛዊ መረጃዎች ይሰበስባል)

3. የማስታወሻ ስርዓት (Memory System)፦ ኤጀንቱ ስራውን በትክክለኛ አውድ (Context) ለማከናወን እንዲችል ቀደም ሲል ያከናወናቸውን ተግባራት እና የተማራቸውን መረጃዎች የሚያከማችበት ክፍል ነው።

4. የግምገማ እና ክትትል ማያያዣዎች (Evaluation Hooks)፦ የኤጀንቱን የስራ ሂደት ለመከታተል እና ውጤቱን ለመለካት የሚያስችል የክትትል ስርዓት የሚያከናውን ነው።

5. የግንኙነት ፕሮቶኮሎች፦ በተለይም በርካታ ኤጀንቶች (Multi-Agent Systems) በአንድነት በሚሰሩበት ጊዜ መረጃዎችን እና ትዕዛዞችን እርስ በርስ ለመለዋወጥ ያስችላቸዋል።

-----
የኤጀንቶች አሰራር ሚስጥር ("ተደጋጋሚ የዑደት ሂደት")

የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች የሚሰሩት በተከታታይ የዑደት ሂደት (Iterative Loop) ውስጥ ነው። ይህ ሂደት አንድን ትልቅ ግብ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመለወጥ የሚከተሉትን ደረጃዎች ያልፋል፦

* ግብን ማስጀመር (Goal Initialization)፦ ሂደቱ የሚጀምረው በተጠቃሚው በሚሰጥ መመሪያ ነው። ለምሳሌ፦ "ለአንድ የንግድ ድርጅት የ30 ቀን የማስታወቂያ ስትራቴጂ ነድፈህ አቅርብ" የሚል ትዕዛዝ/Prompt ሊሆን ይችላል።

* ማመዛዘን እና እቅድ ማውጣት ፦ ኤጀንቱ ግቡን ለማሳካት ምን ምን ስራዎች እንደሚቀድሙ (ለምሳሌ ገበያ ማጥናት፣ ግራፊክስ ማሰናዳት፣ ይዘት መጻፍ) እቅድ ያወጣል።

* መሳሪያ መምረጥ እና እርምጃ መውሰድ፦ ኤጀንቱ በእቅዱ መሰረት አስፈላጊ የሆኑ የውጭ መሳሪያዎችን (ለምሳሌ የጎግል ፍለጋን ወይም የሂሳብ ስሌት መሳሪያዎችን) በመጠቀም ስራውን ይጀምራል።

* ምልከታ እና ግብረ መልስ ፦ ከእያንዳንዱ እርምጃ በኋላ የተገኘውን ውጤት በመገምገም ስህተት ካለ ያስተካክላል ወይም ወደ ቀጣዩ ደረጃ ይሸጋገራል።

-----

በገበያው ውስጥ ግንባር ቀደም የሆኑ የፍሬምወርክ አማራጮች

በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የኤጀንት ፍሬምወርኮች በርካታ ናቸው።
ለምሳሌ :-
1. የብዙ-ኤጀንቶች ማቀናጃዎች (Multi-Agent Orchestration)

እነዚህ ፍሬምወርኮች በተለያዩ ኤጀንቶች መካከል የስራ ድርሻ በመክፈል ውስብስብ ስራዎችን በጋራ ለመስራት የተሰሩ ናቸው። ከእነዚህም CrewAI እና Microsoft AutoGen ይጠቀሳሉ። CrewAI ኤጀንቶችን እንደ አንድ የሥራ ቡድን (Team) በመቁጠር ለእያንዳንዱ ኤጀንት የሥራ ድርሻ (Role) እና ግብ በመስጠት ስራን ያቀናጃል። ለምሳሌ፦ አንዱ ተመራማሪ፣ ሌላኛው ጸሐፊ እንዲሆኑ ያደርጋል።

Microsoft AutoGen ደግሞ ኤጀንቶች እርስ በርስ በውይይት አማካኝነት ችግሮችን እንዲፈቱ ያስችላል። በተለይም ለቴክኒካዊ ስራዎች እና ለኮድ አጻጻፍ እጅግ ውጤታማ ብሎም ተመራጭ ሆኗል።
.
.
2. ጥብቅ ቁጥጥር እና የሂደት አስተዳደር (Stateful Frameworks)

ለዚህ ስራ LangGraph ፍሬምወርክ ተመራጭ ነው። በኤጀንቱ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረን የሚያስችል ነው። በተለይም አንድ ስራ ተደጋጋሚ ዑደት (Loop) የሚፈልግ ከሆነ LangGraphን የሚወደረው የለም።

3. ለገንቢዎች ምቹ የሆኑ (Developer-Centric)

PydanticAI ቀዳሚው ሲሆን የዳታ ትክክለኛነትን (Reliability) በማረጋገጥ ላይ ያተኩራል። ይህም ኤጀንቱ የሚሰጠው ምላሽ ከስህተት የጸዳ እና አስተማማኝ እንዲሆን ያደርጋል።

-----
#መምረጫ_መስፈርቶች

ለድርጅት ወይም ለግል ፕሮጀክቶች የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርክ ሲመርጥ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማገናዘብ ያስፈልጋል።

1. ውስብስብነት (Complexity)፦ የምትሰሩት ስራ ቀላል ከሆነ አንድ ራሱን የቻለ ኤጀንት (Single Agent) በቂ ነው። ነገር ግን ስራው ሰፊ እና ውስብስብ ከሆነ የብዙ-ኤጀንት (Multi-agent) ስርዓት ያስፈልጋችኌል።

2. የውሂብ ደህንነት (Data Privacy)፦ በተለይ በፋይናንስ ወይም በፖሊሲ ትንተና ላይ የምትሰሩ ከሆነ፣ ፍሬምወርኩ መረጃዎችን በምስጢር የመያዝ እና እርምጃዎችን የመገደብ (Guardrails) አቅም ሊኖረው ይገባል።

3. የአጠቃቀም ቀላልነት፦ በዚህ ረገድ የቴክኒክ ብቃትን ግምት ውስጥ ማስገባት ግድ ነው። "ኮድ የማይፈልጉ" ፍሬምወርኮች ለጀማሪዎች ሲመቹ፣ የላቀ ኮድ የሚፈልጉ ደግሞ በባለሙያዎች የተሻለ ተመራጭ እና ተለዌጭነትን የሚያሰፉ ናቸው።
1🔥1