#ነገረ_Ai
በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አዲስና በፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኝ ቴክኖሎጂ ነው። በዚህ ምክንያት በአብዛኛው ህብረተሰብ የአጠቃቀም ጉድለቶች፣ የተለያዩ የተሳሳቱ አመለካከቶች እና የግንዛቤ ውስንነቶች በስፋት ይንጸባረቃሉ።
ከዚህ በመነሳት ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተሻለ እውቀትና ፍቃደኝነት ያላቸው ግለሰቦች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
.
.
.
#ቅምሻ
ከታች በቀስት የተመላከተው የታሸገ ውሃ ማስታወቂያ #በAi የተሰራ ነው። Ai ደግሞ የምንፈልገው ውጤት የሚሰጠን በመደጋገም እንጂ በአንድ ጊዜ ሙከራ ላይሆን ይችላል። የሚሰጠን ውጤት ላይ ያሉትን ጉድለቶች በመቀነስ ብሎም ምርጥ ውጤት ለማግኘት ደጋግመን መጠየቅ ይጠበቅብናል።
ለምሳሌ የአንዲት ሴት እና ማስተዋወቅ የምንፈልገው የታሸገ ውሃ ፎቶ በመስጠት የማስታወቂያ ፖስተር እንዲሰራልን ስልጠይቀው በምስሉ እንደሚታየው ውሃው እንደታሸገ (እንደሰጠነው ምስል) ሊያስቀምጠው ይችላል። ነገር ግን ምስሉ እዛው እንዳለ መልሰን የፕላስቲኩ ክዳኑን እንዲያነሳልን በመጠየቅ ማሻሻል እንችላለን። (ሁለተኛው ምስል እንደሚታየው ያነሳዋል)። በተጨማሪም "Enhance the given image" በማለት ጥራቱን እንደሚታየው ማስተካከል ይቻላል።
በተጨማሪም Ai ራሱን ምን መስራት እንደምንፈልግና መከተል ያለብን ቅደም ተከተል ምን እንደሆነ ወይም ምን ብለን መጠየቅ እንዳለብን ብንጠይቀው በአግባቡ ሊያስተምረንና ሊተባበረን ይችላል።

👍2
AlltechUp.com
🌟 22 ምርጥ የጎግል AI ተዋወቁ🙋🙏
🌟 22 ምርጥ የጎግል AI ተዋወቁ🙋🙏
ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን፣ ሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) የዕለት ተዕለት ስራዎቻችንን ለማቀላጠፍ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰው ሰራሽ ልህቀቶችም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ::
ከእነዚህም መካከል የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ያበለፀጋቸው በርካታ የAI መሣሪያዎች ይጠቀሳሉ:: በመሆኑም ለትክክለኛ ውጤት ትክክለኛ Ai ከመምረጥ ጋር በተያያዘ ካለው ሰፊ ችግር በመነሳት 22 ምርጥ የጎግል ሰው ሰራሽ ልህቀቶችን ላስተዋውቃችሁ:: ይህም ከፍላጎታችሁ ጋር የሚስማማውን ለመምረጥ ያስችላችኋል። (በቀጣይ ስለእያንዳንዱ Ai አጠቃቀም ተጨማሪ መረጃዎችን አጋራለሁ::)
🎨 ይዘት ፈጠራ እና ዲዛይን (Content Creation & Design)
ImageFX - ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎች ለመስራት።
MusicFX - አዳዲስ ዜማዎችን እና የሙዚቃ ቅንብሮችን ለመፍጠር።
VideoFX - አጫጭር የቪዲዮ ምስሎችን ለመስራት።
TextFX - ለጸሐፊዎችና ለገጣሚዎች የፈጠራ አገላለጾችን ለማግኘት።
AutoDraw - ያልተስተካከሉ ቅርጾችን ወደ ፕሮፌሽናል ግራፊክስ ለመቀየር።
Canva - ከጎግል ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ የዲዛይን መድረክ።
✍️ ጽሑፍ እና ምርምር (Writing & Research)
NotebookLM - የግል የጥናት እና የማጠቃለያ ረዳት።
Gemini - የጎግል ዋና የAI ረዳት።
Search Labs - አዳዲስ የፍለጋ ገፅታዎችን ለመሞከር።
Talk to Books - ከመጻሕፍት ውስጥ መረጃዎችን ለማግኘት።
Say What You See - የተሻሉ የትዕዛዝ ቃላትን ለመለማመድ።
💻 ኮዲንግ እና ሶፍትዌር ልማት (Coding & Development)
Project IDX - በብሮውዘር ላይ መተግበሪያዎችን ለመገንባት።
Colab AI - ለዳታ ሳይንስ እና ለፓይዘን ኮዲንግ።
Firebase Genkit - AIን ወደ መተግበሪያዎች ለማስገባት።
Google AI Studio - የGemini ሞዴሎችን ለመሞከር እና ለመገንባት።
🎓 ትምህርት እና ትምህርታዊ ዝግጅት (Education & Learning)
Socratic - የቤት ስራን እና የሳይንስ ጥያቄዎችን ለመፍታት።
Read Along - የሕፃናትን የንባብ ክህሎት ለማሻሻል።
LearnLM - ለትምህርት የተዘጋጁ የAI ሞዴሎች።
Interview Warmup - ለሥራ ቅጥር ቃለ-መጠይቅ ለመዘጋጀት።
🛠️ ልዩ የምርታማነት መሣሪያዎች (Specialized Productivity)
Gemini for Google Workspace - በGmail እና Docs ውስጥ የተቀናጀ ረዳት።
Looker (AI Features) - የንግድ መረጃዎችን ለመተንተን።
Vertex AI - የAI ሞዴሎችን ለማሰልጠንና ለማሰራት።
#ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የጎግል የAI ስነ-ምህዳር ከግል የፈጠራ ስራዎች እስከ ግዙፍ የድርጅት ፕሮጀክቶች ድረስ ሰፊ አማራጮችን ያካትታል። አብዛኛዎቹ ለሙከራ እና ለግል አገልግሎት በነፃ የሚገኙ ቢሆንም፣ የላቁ የንግድ አገልግሎቶች እና ከፍተኛ የኮምፒውተር አቅም የሚጠይቁት ደግሞ በክፍያ የሚቀርቡ ናቸው። በነጻ የሚገኙትን በመጠቀም ስራችሁን ቀላል፣ ስኬታችሁን ፈጣን፣ ውጤታችሁን የላቀ አድርጉ👌
labs.google
ImageFX - labs.google/fx
Transform text into images and explore with endless imagination.
❤5👍2🔥2👏1
AlltechUp.com
Photo
የGemini Ai አስደናቂ ዝመና
ከመረጃ ምንጭነት ወደ ግል ረዳትነት
|
|
|
#Gemini ትናንት በጣም ከፍተኛ ዝመና (Update) አድርጓል። በርካታ የጎግል አገልግሎቶችን በExtensions አካትቷል።
ይህም ከዚህ ቀደም #Gemini የሚመልሰው የሰለጠነውን ወይም በኢንተርኔት ላይ የሚገኝን አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነበር። አሁን ግን '@' ምልክት በማስቀደም የግል መረጃዎቻችን እና ስልካችን ላይ የተጫኑ Apps በአጠቃላይ (ከGoogle አገልግሎቶች ጋር ጭምር) በማገናኘት የተለየ እና ፈጣን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል አቅም ፈጥሯል። በእውነቱ በእጅጉ አስደናቂ እመርታ ነው።
ከአገልግሎቶቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
📅 Google Calendar: Gemini ላይ በካላንደር ቀጠሮዎችን ለማየት ወይም አዲስ ፕሮግራም ለመያዝ ያገለግላል።
💡 Google Keep: ማስታወሻዎችን በዝርዝር ለማስፈር/ለመያዝ ያገለግላል።
✅ Google Tasks: የሥራ ዝርዝሮችን ለማቀድ፣ ለመመዝገብ እና ለማስተዳደር ወይም ለመቆጣጠር ያገለግላል።
📧 Gmail: በGemini ኢሜይሎችን ማንበብ፣ መጻፍ፣ መላክ ወይም Drive ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ፈልጎ መረጃ እንዲያወጣ ማድረግ ይቻላል።
📄 Google Docs: በGemini አማካኝነት አዳዲስ ሰነዶችን መጻፍ ወይም ያሉትን ማስተካከል ይቻላል።
📂 Google Drive: በድራይቭ ላይ የሚገኙ ፋይሎችን ለመፈለግ ወይም ለመጠቀም ያገለግላል።
🎵 YouTube እና 🎧 Spotify Music: የሚፈልጉትን ሙዚቃዎች/ዘፈኖች እና ፖድካስቶችን መክፈት፣ ማጫወት ወይም ማዳመጥ ያስችላል።
በተጨማሪም:-
☺ ድምፅ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ማዘዝ
☺ አንድን ዘፈን እንዲደግመው (Repeat) መጠየቅ እና
☺ ሌላ አልበም፣ ፖድካስት፣ ሙዚቃ . . . እንዲቀይር ማዘዝ ይቻላል።
🛡️ SynthID: በAI የተሰሩ ምስሎችን ወይም መረጃዎችን ትክክለኛነት ለመለየት እና የውሃ ምልክት (watermark) ለመጠቀም የሚያገለግል የGoogle ቴክኖሎጂ ነው። (የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ይዘቶችን ለመለየት ያስችላል።)
📚 OpenStax: ነፃ የትምህርት መርጃ መጽሐፍትን እና የጥናት ቁሳቁሶችን/መረጃዎችን ለማግኘት እና ለመጠቀም ያገለግላል።
💼 Workspace: የስራ ቦታ ረዳት ነው። ኢሜይል ይጽፋል፤ የሰነድ ማጠቃለያ ይጽፋል፣ መረጃ ያደራጃል፤ የፈጠራ ሀሳቦችን ያመነጫል። የስራ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ድጋፎችን ይሰጣል። የጎግል የሥራ መተግበሪያዎችን በጋራ ለመጠቀምም ያገለግላል።
💬 Messages 📞 Phone እና 🟢 WhatsApp: Gemini መልዕክቶችን እንዲልክ፣ እንዲያነብ ወይም ከሦስቱ በአንዱ ስልክ እንዲደውል ትዕዛዝ መስጠት ይቻላል።
ለምሳሌ፦ "ለአቤል ስልክ ደውልልኝ፣ በዋትስአፕ 'እመጣለሁ' ብለህ ንገረው ወይም ዋትስአፕ ላይ መልእክት ካለኝ እይልኝ" ብሎ ማዘዝ ይችላል።
✨ Utilities: የስልክዎን ሲስተም (እንደ ሰዓት መቁጠሪያ፣ ማንቂያ/Alarm) መጠቀም ያስችላል:: በተጨማሪም የስልካችን የእጅ ባትሪ (Flashlight) እንዲበራ እና እንዲጠፋም ማዘዝ ይቻላል።
🏠 Google Home: በቤትዎ ውስጥ ያሉ ዘመናዊ መሣሪያዎችን (መብራት፣ ቴሌቪዥን . . .) በGemini አማካኝነት ለመቆጣጠር ያገለግላል።
ተጨማሪ የጉዞ አገልግሎቶች (Travel Services)
📍 Google Maps: Geminiን በመጠየቅ የጉዞ አቅጣጫዎችን ማግኘት፣ በአቅራቢያ የሚገኙ ምርጥ ምግብ ቤቶችን መለየት እና ለሽርሽር የሚሆኑ ቦታዎችን በካርታ ላይ እንዲያሳይ ማድረግ ይቻላል።
✈️ Google Flights: የቀጥታ የበረራ መረጃዎችን፣ ሰዓቶችን እና ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን አማራጮች በረራዎች/አየር መንገዶች ለማግኘት ያስችላል።
🏨 Google Hotels: በGemini በጀታችንን ወይም ፍላጎታችንን የሚመጥኑ ሆቴሎችን መፈለግ እና ማግኘት ያስችላል።
.
.
.
#ጠቃሚ_ነጥቦች ፦
👍 አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ Gemini መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ መግባት ያስፈልጋል።
👍 #በGemini መጻፊያ ሳጥን ውስጥ '@' ምልክትን በመጠቀም (ለምሳሌ @Gmail) መተግበሪያውን ለይቶ መምረጥ ማዘዝ ይችላሉ።
#ማሳሰቢያ:
🙏እነዚህን አገልግሎቶች ለመጠቀም በBrowser ከሆነ Gemini Settings ውስጥ "Extensions" የሚለውን ማብራት (Enable ማድረግ) ያስፈልጋል።
👍በApp የምንጠቀም ከሆነ ደግሞ በስተቀኝ ያለው የገባንበት Gmail logo ላይ Click አድርገን ከሚመጡት ዝርዝሮች #connectedapps የሚለውን በመምረጥ የምንፈልጋቸው Apps ማብራት (Enable) ማድረግ ያስፈልጋል
🙏 ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳአንድ በስልካችን ወይም ጂሜይል ላይ ከማይገኙ የግል መረጃዎች (ለምሳሌ - የግል የስልክ፣ የመብራት፣ የውሃ . . . ክፍያዎች) የተያያዙ አገልግሎቶችን በአግባቡ ላናገኝ እንደምንችል መገንዘብ ያስፈልጋል።
🙏 ከምትፈልጉት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ የአጠቃቀም ማብራሪያ ከፈለጋችሁ Geminiን መጠየቅና ማግኘት ትችላላችሁ።

👍3
AlltechUp.com
#Gemini_Live
#Gemini_Live
የGemini የቀጥታ የድምፅ አገልግሎት (Gemini Live) ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጋር የተሳሰረ ነው። ልክ እንደ ሰው በቀጥታ መጠየቅ እና ምላሽ (መረጃ) ማግኘት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ነው።
ይህ አገልግሎት ከቀድሞው የጎግል ረዳት (Google Assistant) የሚለየው ትዕዛዝን ተቀብሎ መልስ ከመስጠት ያለፈ አገልግሎት ያለው በመሆኑ ነው። እንደ አንድ የቅርብ ጓደኛ ረዥም እና ተከታታይነት ያለው ወግ ማካሄድ በመቻሉም ነው።
ይህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከGemini ጋር በድምፅ እንዲወያዩ ያስችላል። ልክ ስልክ ላይ እንደምናወራው ሁሉ ስልኩን ሳይነኩ መረጃ መጠየቅ፣ ሃሳብ ማመንጨት እና ጥያቄዎችን ማቅረብ እንዲሁም ምላሽ ማግኘት ይቻላል።
በአጠቃላይ ከሁሉን አዋቂ ሰው ጋር ተቀምጠን የምናደርገውን ተፈጥሯዊ ውይይትን/ንግግርን ይወክላል። መሃል ላይ ማቋረጥ፣ ሃሳብ መቀየር ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።
ለስራ ቃለ-መጠይቅ ለመዘጋጀት፣ አዲስ ቋንቋ ለመለማመድ፣ የንግግር ዝግጅት ለማድረግ፣ የእለቱ አገራዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ ዜናዎችን ለማወቅ . . . ሁሉን አቀፍ አዋቂ እና አጋር ሆኖ ያገለግላል።
ይሄ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ቋንቋዎች የጀመረው እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2024 (August 2024) ቢሆንም አጥጋቢ አልነበረም። በሂደት ግን እየተሻሻለ መጥቶ "Gemini Advanced" (በክፍያ) ለሚጠቀሙ ደንበኞች ብቻ ነበር የቀረበው።
Gemini Live በአማርኛ እና በሌሎች 40 የሚሆኑ ቋንቋዎች አገልግሎት መስጠት የጀመረው በቅርቡ (በጥቅምት) ወር 2017 (October 2024) ባደረገው ዝመና (Update) ነበር። በቅርቡ ባደረገው የ2026 ዝመና ደግሞ አማርኛን ጨምሮ ተጨማሪ ቋንቋዎችን በማከል አገልግሎቱን በነጻ እና በከፍተኛ ጥራት አቅርቧል። (ለጊዜው ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አይሰራም)
.
.
.
.
ኧረ ጓዶች "Enjoy!" አድርጉ🤗🙋
✅ የዛሬ ትኩስ የኢትዮጵያ/ዓለም አቀፍ ዜናዎች ምን አሉ?
እስቲ ሁሉንም በዝርዝር አቅርብልኝ?
✅ የአሜሪካ እና የኢራን ውጥረት ከምን ደረሰ?
✅ በዓለም ላይ ለAi ቴክኖሎጂ መሰረት የጣሉ የሂሳብ ሊቃውንት እነመን ናቸው?
✅ ትዳርን ዘላቂ ለማድረግ ከተጋቢዎች ምን ይጠበቃል? . . . የመሳሰሉ ጥያቄዎችን እየጠየቃችሁ አስደናቂ ምላሾችን ማግኘት፣ ማብራሪያ መጠየቅ፣ ርዕሰ ጉዳይ መቀየር . . . በፈጣሪ 🙉😁
እንዴት ያረካል መሰላችሁ❓🙉☺
አሁንኑ ጀምሩ🙋🤗

❤1👍1
AlltechUp.com
Photo
"ካልከፈልክበት፣ ሸቀጡ አንተ ነህ"
|
|
|
ለርዕስነት የተጠቀምኩት የቴክኖሎጂ ዓለም የተለመደ አባባል ነው:: አባባሉ ለAI ተጠቃሚዎችም በትክክል ይሠራል:: ብዙ ተጠቃሚዎች #ከAI ነጻ አገልግሎቶች በስተጀርባ ያለውን እውነት በጥልቀት አይረዱም:: ባለማወቃቸውም "ለምን በነጻ ይሰጡናል?" እያሉ ይጠይቃሉ:: በግድየለሽነት የግል መረጃዎቻቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ።
እንደ Gemini፣ ChatGPT፣ Claude፣ DeepSeek እና ሌሎችም በነጻ የሚያገለግሉን ለበጎ አድራጎት የተቋቋሙ አይደሉም። ከገንዘብ የሚገዝፍ ትርፍ ስለሚያግበሰብሱበት ነው::
ለአብነት:-
🙏1. መረጃ - አዲሱ የዓለማችን ነዳጅ
የAI ድርጅቶች ትልቁ ሀብታቸው መረጃ ነው:: እኛ በነጻ ስንጠቀም የምናስገባቸው ጥያቄዎች፣ የምንጽፋቸው ጽሁፎች፣ የምንጭናቸው ፎቶግራፎች፣ ሰነዶች . . . እና የምንሰጣቸው ግብረ-መልሶች ለድርጅቶቹ እጅግ ውድ ግብዓቶች ናቸው:: አገልግሎታቸውን ማዘመን የሚያስችል ጥናት የሚያደርጉትና በግብአትነት የሚጠቀሙት ከእኛ ላይ "በነጻ ሽፋን" የሚሰበስቡት ዳታ ነው::
በተጨማሪም ሞዴሉን የሚያሰለጥኑት ስንጠቀም በሚሰበስቡት ዳታ ነው:: በጠየቅን ቁጥር #AI ስህተቱን እንዲያርም እና የሰውን ልጅ አነጋገር/ፍላጎት ይበልጥ እንዲረዳ ያደርጋሉ::
የምንመርጣቸው ርዕሶች፣ ፍላጎቶቻችን እና የባህርይ ዘይቤያችን ተጠንቶ ለንግድ ማስታወቂያዎች ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች ይውላሉ::
አሁን #GeminiAI የጀመራቸው አይነት ከGmail፣ ከWhatsApp፣ ከPhone፣ ከYoutube፣ ከGoogle Drive . . . በማገናኘት ተጨማሪ አገልግሎቶችን የመስጠት አሰራርም ምንም ዓይነ የግል መረጃ እንዳይኖረን የሚያደርግ ነው። ሌላው ቀርቶ በምንጠቀምባቸው ስልኮችና ላፕቶፓች ምንም ዓይነት የግል መረጃ አይኖረንም። የSMS መልእክቶቻችን ሳይቀሩ ለእነሱ ተደራሽ ናቸው።
🙏2. "Hidden" ወይም ስውር ክፍያዎች
ምንም እንኳን ቀጥታ ከኪሳችን ብር ባይወጣም፣ ተጠቃሚው የሚከፍላቸው ሌሎች ዋጋዎች አሉ።
ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በሚወሰዱ ዳታዎች 'የግል ምስጢራዊነት' ዋጋ እንከፍላለን። የምናስገባቸው ምስጢራዊ መረጃዎች በድርጅቱ ሰርቨር ላይ ይቀመጣሉ:: ፈላጊ ሲያገኙም መረጃዎቻችንን ይሸጡታል። ስነምግባር የጎደላቸው የድርጅቱ ሰራተኞች በተለይም ሲለቁ በፈለጉት ጊዜ ያሻቸውን ሳይበር ጥቃት ሊፈጽሙብንና ሊያስፈጽሙብን ይችላሉ።
ለAIው የምንሰጠው አዲስ ሃሳብ ወይም የፈጠራ ስራ በነጻ የድርጅቱ ንብረት ይሆናል።
🙏3. የሚያገኟቸው ሌሎች ጥቅሞች
ድርጅቶቹ "ነጻ" አገልግሎት በመስጠት ብዙ ተጠቃሚ ያፈራሉ፤ ተወዳዳሪዎቻቸውንም ከገበያ ያስወጣሉ:: ይህም የገበያ የበላይነት እንዲይዙ ያደርጋቸዋል።
ሰዎች በነጻው አገልግሎት ከተላመዱ በኋላ ሱሰኛ ሆነው ወደ ላቀው (Premium) አገልግሎት እንዲቀይሩ ይገፋፋሉ::
ሚሊዮኖች የስርዓት ሙከራ (Beta Testing) ሲጠቀሙበት ሲስተሙ ያለበትን ስህተት (Bug) በነጻ እንዲያርሙ ያስችላቸዋል።
ባጭሩ በ"ነጻ" ተጠቃሚነት ስም የAI ድርጅቶችን ምርት እያሻሻልን፣ መረጃ እየመገብን፣ ግላዊነታችንን እያጣን እና ገበያቸውን እያሰፋንላቸው ነው። እኛ የምናገኘው ፈጣን መልስ ሲሆን እነሱ ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ የእውቀት እና የመረጃ ክምችት ይገነባሉ:: አገልግሎታቸውን አሻሽለው ወይም ዳታውን ሸጠውም ቢሊዮን ዶላሮችን ያግበሰብሳሉ።
.
.
.
#ጥብቅ_ማሳሰቢያ:-
ማንኛውንም የAI አገልግሎት በምትጠቀሙበት ስልክ ወይም ላፕቶፕ የግል ምስጢራችሁን፣ የባንክ መረጃዎቻችሁን ወይም የንግድ ምስጢሮቻችሁን ባታስቀምጡ ይመከራል። ካልሆነ ግን ነገሩ "ወደሽ ካጎነበስሽ ምን ቢያደርጉሽ አይክፋሽ" እንደሚባለው መሆኑ የማይቀር ነው።

❤4
በነገራችን ላይ . . .
☺በምንም መንገድ መለየት የማይቻል የኢሜይል መልዕክት inbox ውስጥ ማስገባት ይቻላል::
🤔 በስልካችን ላይ በምንም መልኩ መለየት የማይቻል የጽሁፍ (SMS) መልእክት ከዚህ ቀደም ከተላኩት መሃል ሳይቀር ማካተት ይቻላል::
.
.
.
🙉ለምሳሌ - ከላይ ያያዝኩት የSMS መልእክት በምንም መልኩ ማንም መለየት አይችልም:: ሌላው ቀርቶ የተጻፈበት ጊዜ 2024 ይላል (በተፈለገው ማድረግይቻላል)::
👉 የEmail ደግሞ ከዚህም ይቀላል::
በአራት ነጥብ - ከምታምኑ ብትጠራጠሩ ይሻላል 👌
.
.
.
👌ማንም እየየተነሳም አይጃጃልባችሁ👌
.
.
.
ለተጨማሪ ተመሳሳይ መረጃዎች 👇ተቀላቀሉ
https://www.facebook.com/share/18J3QstZkv

#ሀሰተኛ_ደረሰኞች
.
.
.
ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት በቴክኖሎጂ ዘመን ደረሰኝ፣ ደብዳቤ፣ ስክሪንሾት፣ የጽሁፍ መልዕክት (SMS) . . . ማዘጋጀት ከባድ አይደለም:: እንዳውም በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ በርካታ አገራት እንዲህ አይነት ዶክመንቶች ብቻቸውን በፍርድ ቤት ለሚመሰረቱ ክሶች ማስረጃ ሆነው እንዳይቀርቡ እስከማገድ ደርሰዋል:: በተመሳሳይም ለመንግስታዊ ተቋማት ብቸኛ ማስረጃ ሆነው አይቀርቡም::
በኛ አገር ግን በተለይም በጉምሩክ ድርጅት ሀሰተኛ ደብዳቤዎች፣ ደረሰኞች፣ የመኪና እና ሌሎች ሰነዶች . . . በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይነገራል:: ከዚህም አልፎ የማያውቁ ሰዎችን ሳይቀር ራሳቸው ሰርተው/አሳርተው "ተገቢ" ክፍያቸውን የሚቦጭቁ ሰራተኞች እንዳሉ ገጠመኛቸውን የሚናገሩ ያጋጥማሉ::
.
.
.
በዚህ ጽሁፍ የጥንቃቄ ምርልዕክት ማጋራት የፈለግኩት ግን ከባንክ ደረሰኝ ጋር በተያያዘ ነው:: ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ዲጂታል የክፍያ ስርዓቶች በእጅጉ ተደራሽ እየሆኑና እየተለመዱ በዛው መጠንም የተራቀቁ ማጭበርበሮች እየተስፋፉ በመሆናቸው ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ማስጠንቀቅ የሚጠበቅ በመሆኑ ነው::
.
.
.
.
#ሀሰተኛ_ደረሰኞች እንዴት ይሰራሉ?
😵 ተራ አጭበርባሪዎች Photoshopን ጨምሮ ሌሎች የላፕቶፕ ወይም የሞባይል ነጻ የፎቶ ማቀናበሪያ ( Graphics Editing) በመጠቀም ትክክለኛውን የባንክ ደረሰኝ ስም፣ ቀን እና የገንዘብ መጠንን ይቀይራል።
😡 መካከለኛ እና የተራቀቁ አጭበርባሪዎች በቴሌግራም ወይም በተለያዩ ድረገጾች ላይ ደረሰኝ የሚሰሩ (Receipt Generator) ቦቶችና አፕሊኬሽኖች በመጠቀም የሚፈልጉትን ስም፣ አካውንት፣ ብር . . . በመሙላት ልክ እንደ ባንክ ደረሰኝ አድርገው ማውጣትና ማሳየት ይችላሉ::
👹 እንዲህ አይነት አጭበርባሪዎች Clone Appsም ሊጠቀሙ ይችላሉ:: የባንኩን አፕሊኬሽን ገጽታ (UI) ብቻ የሚመስሉ ነገር ግን ከባንክ ሲስተም ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የውሸት #አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም ስክሪንሻት ያደርጋሉ። እርግጠኛ ባልሆንም ከቻይናውያን ጋር በመተባበር የባንክ API (Application Programming Interface)ን Rebuild በማድረግ ደረሰኝ የሚሰሩ እንዳሉም ይነገራል:: (ይሄን መረጃ በሰማሁበት ወቅት ቦሌ አካባቢ ደረሰኝ በማሳየት የተፈፀመ ዘረፋን በመጥቀስ አጋርቼ ነበር)
---
.
.
.
መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ምንድነው?
😠 በፎቶሾፕና በመሳሰሉ ሶፍትዌሮች በማጥፋትና አስመስሎ በመጻፍ የሚደረጉ ተራ ማጭበርበሮች ብዙ ስህተቶች ስለሚኖሩት በማየት ብቻ ይታወቃል::
ለምሳሌ አያይዤ ያጋራሁት ደረሰኝ:-
| በግልጽ የሚታይ የሂሳብ ስሌት ስህተት አለበት። "15% VAT of ETB 0.45.0" ይላል። 0.45.0 የሚባል ቁጥር የለም (ሁለት ቦታ ነጥብ አይኖርም)።
| የፊደል አጻጻፉ (Typography) የተዝረከረኩ፣ ወጥ ያልሆኑ እና የጥራት ደረጃቸው የወረደ ነው።
.
.
.
በእውቀት የተመሰረቱ ማጭበርበሮች:-
በቴሌግራም፣ በተለያዩ ድረገጾች፣ በReceipt Generator ቦቶችና አፕሊኬሽኖች እንዲሁም በClone Apps የሚሰሩ ደረሰኞች በፍፁም በማየት ላይለዩ ይችላሉ።
😠 ስለሆነም መፍትሄው:-
👉 የባንክ የመሳሰሉ ደረሰኞች በማየት ከማመን ይልቅ የራሳችሁን ትክክለኛ የባንክ አፕሊኬሽን (ለምሳሌ CBE) በመክፈትና Transaction History በማየት ማረጋገጥ ይገባል::
👉 የባንኩን ትክክለኛ መልዕክት (Official SMS) CBE ( Commercial Bank of Ethiopia) በሚለው የራሱ (አጭር ቁጥር ስም) የሚልከውን የገቢ መልዕክት በማየት ማረጋገጥ ይገባል:: (ባንክ ከግል ስልክ ቁጥር "ገንዘብ ገብቶልዎታል" የሚል መልዕክት አይልክም::)
👉 ብዙውን ጊዜ አጭበርባሪዎች (ሌቦች) በጣም የቸኮሉ በመምሰል ችግሩ የባንክ ሲስተም ሊሆን እንደሚችል ለማሳመን ይጣደፋሉ:: ወከባ ይፈጥራሉ:: እንዲህ አይነት ሰዎች ሲገጥሙ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
በእርግጥም በጣም እልፍ አልፎ የሚዘገይበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል:: እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር ባንክ በአካል በመሄድ ወይም ደውሎ ገንዘብ አካውንታችሁ ላይ ገብቶ ከሆነ ማረጋገጥ ካልሆነም የሚያሳዩዋችሁ ደረሰኝ ላይ ያለውን QR Code በባንኩ ኦፊሴላዊ አፕሊኬሽን Scan ማድረግ ያስፈልጋል:: ትክክለኛ ከሆነ የላኪውንና የተቀባዩን መረጃ ያሳያችኋል። (ሀሰተኛ ደረሰኝ ከሆነ QR ኮድ Scan ሲደረግ ምንም መረጃ አይሰጥም ወይም ከደረሰኙ ጋር የማይገናኝ ዝባዝንኬ ጽሁፍ ያሳያሉ።)
ከዚህ ውጭ ማንም ስለቸኮለ እና ስላዋከበ ብቻ ደረሰኝ አይቶ ገንዘብ ገብቷል ብሎ ማመን አደገኛ ነው።
.
.
.
.
.
በተያያዘ ወይም ባልተያያዘ 🙋
National ID Ethiopia ዛሬ ማምሻውን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጸው ፋይዳ መታወቂያ .PDF መላክ አቋርጧል:: ከጠቀሳቸው ምክንያቶችም ሚዛን የሚደፉት በፎቶ ማቀናበሪያ ሶፍትዌሮች በማቀናበር የሚፈፀሙ የማጭበርበር ተግባራት ይጠቀሳሉ:: በጣም የሚገርመው ግን እስከ አሁን #በPDF በስፋት በተሰራጨው ፋይዳ መታወቂያ ማጭበርበሩ እንደሚቀጥል እየተወቀ ስለመፍትሄው ምንም አለማለቱ ነው:: ስለሆነም አጠራጣሪ ፋይዳ መታወቂያ ከገጠማችሁ ልክ እንደባንኩ ደረሰኝ QR Code Scan በማድረግ መለየት እንደምትችሉ ማስታወስ ያሻል::

❤4👍2🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጮማ ብስራት - ለቴክ አፍቃሪያን
አዲሱ የGoogle Gemini Ai 'Lyria 3' የተባለ አዲስ የሙዚቃ ሞዴል አካትቶ ወደስራ ገብቷል።
የ30 ሰከንድ ርዝመት ያለው ሙዚቃ በሰከንዶች ውስጥ የሚሰራው ይህ አዲስ አገልግሎት ዛሬ ሌሊት ይፋ ተደርጓል።
ይህ ሞዴል ሙዚቃን ከፅሁፍ (Text-to-Music)፣ ግጥም እና ድምፅ (Lyrics & Vocals) ማቀናበር፣ ከምስል እና ከቪዲዮ ሙዚቃ መስራት፣ የሙዚቃ አልበም ምስል (Cover Art) ማዘጋጀት የሚችል አስደናቂ ፈጠራ ነው። ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተመሳሳይ አገልግሎቶች እጅግ የላቀና የረቀቀ ቴክኖሎጂ ነው።
ሌላው ቀርቶ አንድን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ወደ Gemini በመጫን፣ ለዚያ ምስል የሚስማማ "Soundtrack" እንዲሰራ ማዘዝ ይቻላል። ድንቅ!
ሙዚቃውን ሰርቶ ሲጨርስ Nano Banana ከተባለው የGoogle ምስል መስሪያ AI ጋር በመቀናጀት ለሙዚቃው የሚሆን ማራኪ የሽፋን ምስል (Cover Art) አብሮ ያዘጋጃል።
በAI የተሰራ ሙዚቃ መሆኑን መለየት እንዲቻልም በሰው ጆሮ የማይሰማ ነገር ግን በቴክኖሎጂ የሚለይ SynthID የተባለ ምልክት (Watermark) በሙዚቃው ውስጥ ያካትታል።
በአሁኑ ወቅት ይህ አገልግሎት በGemini Ai ውስጥ በ"Tools" ስር "Create Music" በሚለው ምርጫ ይገኛል። ለYouTube Shorts፣ ለቲክቶክ እና ለግል ስራዎች እንደ ግብዓትነት እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራ ነው።

❤1🔥1🥰1
AlltechUp.com
ጮማ ብስራት - ለቴክ አፍቃሪያን አዲሱ የGoogle Gemini Ai 'Lyria 3' የተባለ አዲስ የሙዚቃ ሞዴል አካትቶ ወደስራ ገብቷል። የ30 ሰከንድ ርዝመት ያለው ሙዚቃ በሰከንዶች ውስጥ የሚሰራው ይህ አዲስ አገልግሎት ዛሬ ሌሊት ይፋ ተደርጓል። ይህ ሞዴል ሙዚቃን ከፅሁፍ (Text-to-Music)፣ ግጥም እና ድምፅ (Lyrics & Vocals) ማቀናበር፣ ከምስል እና ከቪዲዮ ሙዚቃ መስራት፣ የሙዚቃ…
የGemini የሙዚቃ ቴክኖሎጂ ምን ያህል ፈጠራ የታከለበት እንደሆነ የሚያሳይ አጭር የሙዚቃ ናሙና ከላይ ተያይዟል፤ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ፎቶ በመስጠት ብቻ ሁለት ጊዜ በተለያየ ግጥም እና ዜማ የተሰራ ነው:: አዳምጡት - ቴክኖሎጂውንም ሞክሩት::
👍1🥰1
AlltechUp.com
የAI ዓለምን ያስደነቀው አዲሱ አብዮት . . .
የAI ዓለምን ያስደነቀው አዲሱ አብዮት
.
.
.
ባለፉት ሁለት ወራት የAi ዓለም አጀንዳ “Claudebot” ነው:: (በእኛ አገር ግን 'ወፍ የለም::')😪
ይህ በAi ዓለም አዲስ አብዮት የፈጠረ ክላውድቦት ጊትሀብ (GitHub) ላይ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 75,000 ኮከቦችን በማግኘት የዘርፉ ሊቃውንትን ትኩረት ስቧል።
Claudebot "AI Agent" የሚባል የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሲሆን Open-source (ነጻ) ነው። ማንኛውም ሰው ኮዱን ወስዶ እንደ ፍላጎቱ ሊያስተካክለው ብሎም የትም ሆኖ ቤት ውስጥ ያለው ኮምፒውተሩን ስልኩ ላይ በሚገኙ ታዋቂ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች (WhatsApp፣ Telegram፣ Discord ወይም iMessage . . .) የፈለገውን ትዕዛዝ መስጠት የሚያስችል መሆኑ የብዙዎችን ቀልብ እንዲስብ አድርጎታል።
ChatGPT የመሳሰሉ የAi ረዳቶች የተጠየቁትን መረጃ ብቻ ሲሰጡ Claudebot ግን "ተግባር" ላይ ያተኩራል። ኮምፒውተር ላይ ፋይሎችን መክፈት፣ አዳዲስ ፕሮግራሞችን መጫን እና የሲስተም ትዕዛዞችን (Shell Commands) ማስፈጸም ይችላል።
ማናቸውም ትዕዛዞችን ማስፈጸም፣ ድረ-ገጾችን ማሰስ፣ ስክሪፕቶችን መጻፍ እና በጠቃላይ ሰዎች የሚፈልጉትና የሚያደርጉትን ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል። ከየትኛውም ቦታ መልእክት ሲደርሰው ምላሽ ይሰጣል:: ኮምፒውተር ላይ የሚገኝ ግብይት ዳታ ተንትኖ ከነዝርዝሩ ይልካል:: ሰራተኞችን ለማስተዳደር፣ የኮምፒውተር ኮዶችን ለመገምገም እና የተፈለገውን በራሱ ጊዜ እንዲሰራ (automate) ማድረግ ያስችላል::
ሌላው ቀርቶ "ኮምፒውተሬ ላይ ያለውን የሽያጭ ፋይል ወደ PDF ቀይረህ ላክልኝ" ብሎ ማዘዝ ይቻላል። እጅግ በጣም ድንቅ ፈጠራ😁
ስለሆነም ይህ Claudebot ዓለም ወደ "ራስ ገዝ AI" (Autonomous AI) እየተጓዘች መሆኑን ያሳያል። በሌላ አባባል እስካሁን የነበረው ውድድር "የትኛው AI የተሻለ ድርሰት ይጽፋል? የተሻለ ምስል ይሰራል? . . . " የሚል ነበር። አሁን ግን ውድድሩ Claudebot "የትኛው AI ነው ስራዬን በአካል የሚሰራልኝ?" ወደሚል ቀይሮታል።
በዚህ ምክንያት የወደፊቱ የኮምፒውተር አጠቃቀም "Windows" ወይም "macOS" ኦፕሬቲንግ ሲስተም አስፈላጊነት በእጅጉ የሚቀንስ ይሆናል:: በምትኩ በተፈለገው ቋንቋ ቦቱን ማዘዝ ብቻ አስፈላጊ ያደርገዋል። ይህ ደግሞ እንደ ማይክሮሶፍት እና አፕል ያሉ ኩባንያዎች የራሳቸውን AI Agents ከሲስተማቸው ጋር በጥልቀት እንዲያስተሳስሩ ያስገድዳቸዋል።
ከዚህ ታላቅ የClaudebot ስኬት ጀርባ ፒተር ስታይንበርገር (Peter Steinberger) የተባለ ኦስትሪያዊ የሶፍትዌር ባለሙያ እና ስራ ፈጣሪ ወጣት ይገኛል። በGitHub "Gary" በሚል ስም ይታወቃል::
ፒተር ከዚህ ቀደም PSPDFKit የተባለ ስኬታማ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ነበር። በApple (macOS/iOS) ስርአቶች ላይ ጥልቅ እውቀት ያለው ባለሙያ እንደሆነ ይነገርለታል:: ይህንን ቦት የሰራው በትርፍ ጊዜው ("Hobby Project") በቤቱ ሆኖ በ10 ቀናት ውስጥ ብቻ እንደነበር ይናገራል።
ይሁንና በፕሮጀክቱ (Claudebot) እጅግ ውስብስብ የሆኑ የAI ሞዴሎችን ከእውነተኛ ዓለም የኮምፒውተር ስርአቶች (Operating Systems) ጋር እንዴት ማገናኘት እንደሚቻል በተግባር አሳይቷል። Claudebot ብሎ የሰየመውም ለAnthropic ኩባንያው "Claude" AI ሞዴል ክብር ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል::
ይሁንና Anthropic ኩባንያ ስሙ ከእኛ ሞዴል ጋር በጣም ይመሳሰላል በሚል የንግድ ምልክት (Trademark) ጥያቄ በማንሳቱ ስሙን መጀመሪያ ወደ Moltbot (የሸርጣን/ሎብስተር ቅርፊት) ሲቀይረው አሁን ደግሞ ይበልጥ ታዋቂ ወደሚታወቅበት OpenClaw ተቀይሯል::
ፒተር በGitHub ላይ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ1,300 በላይ ማሻሻያዎችን በማድረግ ዓለምን አስገርሟል።
በዚህ ስራው የዓለም ቀደምት የAi ኩባንያዎች ቀልብ የሳበው ፒተር ስታይንበርገር ሰሞኑን OpenAIን በይፋ ተቀላቅሏል:: በርካታ የAI ባለሙያዎ ስታይንበርገርን የመሰለ "አድራጊ" (Doer) መሐንዲስ በOpenAI የወደፊት ስኬት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ያምናሉ።
.
.
.
ማስታወሻ - Claudebot /Openclaw ቴክኖሎጂ በAI ገበያ ላይ ትልቅ የኃይል ሚዛን ለውጥ እንደሚፈጥር ይጠበቃል:: ይሁንና በጥልቅ እውቀት ላይ የተመሰረተ አጠቃቀም ካልሆነ "የቤት ቁልፍን ለማያውቁት ሰው የመስጠት ያህል" የደህንነት ክፍተት ያለው ነው::
UPS (Uninterruptible Power Supply) መከራየት የምትችሉ /በወር 2,000 ብር አካባቢ ነው/ ደህንነቱን በጠበቀ ደረጃ እንዴት መጫን እና መጠቀም እንደምትችሉ ልታማክሩኝ ትችላላችሁ::

👎4❤1👍1🥰1