AlltechUp.com
3.43K subscribers
603 photos
21 videos
6 files
290 links
etechup.com የቴክኖሎጂ አለምን ያዳርሳል! 🚀
የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱

ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡
Download Telegram
AlltechUp.com
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ . . . 🚀
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ . . .

ገመና ለማየት የሚንጋጋ ህዝብ ሁልጊዜ የወጥመድ ሰለባ ነው። ቁምነገር ሲጋራ ዞር ብሎ የማያይ ህዝብ የሴት ራቁት ሲባል ይርመሰመሳል። (ምን ያህል ሰው #React ፣ ምን ያህል #Comment እና ምን ያህል #Share እንዳደረገ ተመልከቱ - በነገራችን ላይ ይሄን #Mekdii የሚል አካውንት Unfollow በማድረግ ራሳችሁን አርቁ)

የሆነው ሆኖ #Comment ላይ የተቀመጠው ማስፈንጠሪያ (#link) (is.gd/j72BFq) የቴሌግራም አይደለም:: የቴሌግራም ሊንክ '#በt.me . . . ' ነው የሚጀምረው::

ይህ ማስፈንጠሪያ (#link) አጭር ሊንክ (Shortened URL) ሲሆን is.gd በሚባለው አጭር ሊንኮችን ለመፍጠር የሚያገለግል ታዋቂ አገልግሎት ሰጪ ድረ ገጽ የተቀየረ ነው። አጭር ሊንኩ ወደ የትኛው ድረ-ገጽ እንደሚያመራ ወይም Redirect የሚሆንበት ድህረ ገጽ URL expander ወይም URL unshortener ላይ አስገብተን ስናረጋግጥ https://www.google.com/search?q=obqj2.com ሆኖ እናገኘዋለን:: ይሁን እንጁ ይህ የድረገጽ አድራሻ ምን ሊሆን እንደሚችል በማየት ብቻ ማረጋገጥ አይችልም::
-----
ሆኖም ግን የፌስቡክ ገጹ በራሱ በማማለል ለማጭበርበር የተዘጋጀ እንደሆነ የሚያመላክቱ ይዘቶች በብዛት ስላሉት የተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ (#link) አደገኛ የመሆን እድሉ እጅግ ሰፊ ነው::

#አደገኛ ሲባል:-

1. የማልዌር (Malware ድህረ ገጽ:-

ይህ ማለት ስትነኩት ወደ ኮምፒውተራችሁ ወይም ስልካችሁ ቫይረስ ወይም ሌላ አደገኛ ሶፍትዌር የሚያስገባ ድህረ ገጽ ሊሆን ይችላል::

2. የፊሺንግ (Phishing) ድህረ ገጽ:-

የግል መረጃችሁን (የይለፍ ቃል/Password፣ የቴሌ ብር፣ የባንክ መረጃ . . . ) ለመስረቅ የተዘጋጀ ሐሰተኛ ድህረ ገጽ ሊሆን ይችላል::

3. አፀያፊ ወይም የማይፈለግ ይዘት (Obscene or Unwanted Content):- የራቁትና የወሲብ ወይም ሌሎች ከሞራልና ከስነምግባር የሚቃረኑ ይዘቶች የሚጋሩበት ሊሆን ይችላል::

#ማድረግ_የሌለባችሁ
ማስፈንጠሪያውን (Linkን) ከመንካት ተቆጠቡ:: በፌስቡክ የምታገኙት ተመሳሳይ ማስፈንጠሪያም ሆነ መንነቱ ከማይታወቅ ሰው በEmail፣ በWhatsApp፣ በTelegram ወይም በሌላ መንገድ የሚላኩላችሁን አጠራጣሪ ሊንኮች በፍጹም አትንኩ። ምንም የሚያጓጓ ነገር በሌለበት ሁኔታ ወይም የማታውቁት/የሌላችሁ ነገር የተጋራ ይመስል በመንጋ መንጋጋትም አግባብ አይደለምና ረጋ ብትሉ ቅቤ ይወጣችኋል። 👌

.
.
.
🙋ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇
🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom

#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/

#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia

Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
5👍1
ምን ትላላችሁ🙋
.
.
.
ምንም እንኳን ልብስ ሰፊ በሚያስንቁ ባለሙያዎች (ማዝገም) ምክንያት እንዳቀድኩት ባይፈጥንልኝም/ባይሆንልኝም ከቴክኖሎጂ፣ Ai እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከማዘጋጀው ድረገጽ በመቀጠል #ticktock እና #Youtube የመጀመር ሀሳቡ አለኝ። ይሁን እንጂ በተለይም በርካታ ሰዎች #በAi ዙሪያ ያለውን አስደናቂ ፈጣን ለውጥ ማወቅና መጠቀም ጊዜ የማይጠይቅ በመሆኑ ፍላጎት ካላችሁ በአንድ ሳምንት ውስጥ #ticktock እጀምራለሁ። (100 ኮሜንት ላይ ከደገፋችሁ ልክ የዛሬ ሳምንት እጀምራለሁ - ቀኑን Save አድርጉ)

ከተች ያለው ፎቶግራፍ #Ai እንዴት እንደለወጠው ተመልከቱ፤ እናንተም በትንሽ ተጨማሪ እውቀት የተቀደደ የድሮ ፎቷችሁን ሳይቀር መመለስ ትችላላችሁ።
.
.
.
🙋ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇
🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom

#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/

#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia

Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
እነዚህ ፎቶግራፎች #በተገዛ (Paid) Ai የተቀየሩ ናቸው:: ያረጁ፣ የተበላሹ፣ የደበዘዙ፣ መጽሄት/መጽሃፍ ላይ የታተሙ፣ ጥቁር እና ነጭ የሆኑ . . . ፎቶግራፎችን ፍጹም በማይታመን ሁኔታ ይታደሳሉ። በመሆኑም የዚህ ዓይነት አገልግሎት ማግኘት የሚፈልግ ብዙ ሰው ሊኖር ስለሚችል በዝቅተኛ #ክፍያ ልንሰራላችሁ አቅደናል። ፍላጎት ያላችሁ @y7_666 ላይ ጻፉልን።
👍3🥰3👏1
የዊንዶውስ 10 መዘጋት (Crash) መንስኤዎች እና መፍትሄዎች

.
.
.
AlltechUp.com
የዊንዶውስ 10 መዘጋት (Crash) መንስኤዎች እና መፍትሄዎች . . .
የዊንዶውስ 10 መዘጋት (Crash) መንስኤዎች እና መፍትሄዎች
.
.
.
ዊንዶውስ 10 ድንገት ሊዘጋ (Crash ሊያደርግ) የሚችልባቸውን ሰባት ዋና ዋና ምክንያቶች እና ለእያንዳንዱም ትክክለኛ መፍትሄዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦
---

🙋 1. የሙቀት መጨመር (Overheating)

ኮምፒውተርዎ ከልክ በላይ ሲሞቅ ስርዓቱን ከጉዳት ለመጠበቅ በራሱ ሊዘጋ ይችላል።

* መንስኤ: - የአየር ማናፈሻ ቀዳዳዎች መዘጋት፣ የአቧራ ክምችት፣ ወይም የማቀዝቀዣ ስርዓት (Fan) ብልሽት ሊሆን ይችላል።

መፍትሄዎች:-
* የኮምፒውተርዎን አየር ማናፈሻ ቀዳዳዎች ሁልጊዜ ንጹህ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
* ኮምፒውተሩን ለስላሳ ቦታዎች (እንደ አልጋ ወይም ሶፋ) ላይ ከመጠቀም ይቆጠቡ።
* በየጊዜው የኮምፒውተርዎን ውስጠኛ ክፍል አቧራ ያጽዱ።

* ለላፕቶፖች የማቀዝቀዣ ፓድ (Cooling Pad) ይጠቀሙ።
---

🙋 2. የተበላሹ ወይም ያረጁ ድራይቨሮች (Outdated or Faulty Drivers)

ድራይቨሮች ሃርድዌርዎ ከዊንዶውስ ጋር በትክክል እንዲግባባ ያደርጋሉ። ሲበላሹ ወይም ሲያረጁ ስርዓቱ ሊዘጋ ይችላል።

* መንስኤ: - አዲስ የዊንዶውስ ዝመና፣ የተበላሸ የድራይቨር ጭነት ወይም ጊዜ ያለፈባቸው ድራይቨሮች

* መፍትሄዎች :-
ወደ Device Manager ይሂዱ እና ችግር ያለባቸውን ድራይቨሮች ያዘምኑ (Update ያድርጉ)።

* የቅርብ ጊዜው ድራይቨር ችግር ካመጣ፣ ወደ ቀድሞው ስሪት ይመለሱ (Roll Back Driver ያድርጉ)።

* የሃርድዌር አምራች (ለምሳሌ፡- NVIDIA፣ AMD፣ Intel) ድረ-ገጽ በመሄድ የቅርብ ጊዜውን ድራይቨር አውርደው ይጫኑ።
---

🙋 3. የሃርድዌር ብልሽት (Hardware Malfunction)

የኮምፒውተርዎ ዋና አካላት ሲበላሹ ዊንዶውስ ሊዘጋ ይችላል።

* መንስኤዎች : - የራም (RAM) ችግሮች፣ የሃርድ ድራይቭ/ኤስኤስዲ (HDD/SSD) መበላሸት፣ ወይም የኃይል አቅርቦት ክፍል (PSU) ብልሽት ሊሆን ይችላል።

* መፍትሄዎች:-
* ራም (RAM):- የዊንዶውስ Memory Diagnostic Tool (የማስታወሻ ምርመራ መሣሪያ) በመጠቀም ራምዎን ይሞክሩ።

* ሃርድ ድራይቭ/ኤስኤስዲ :- የዊንዶውስ Check Disk (chkdsk) ትዕዛዝን በመጠቀም ሃርድ ድራይቭዎን ለስህተቶች ይፈትሹ።

* PSU :- የሃይል አቅርቦትዎ በቂ ሃይል መስጠቱን ወይም አለመሆኑን ያረጋግጡ። በብልሽት ከተጠረጠረ በአዲስ ይተኩት።
* እርግጠኛ ካልሆኑ ባለሙያ ያማክሩ።
---

🙋4. ብዙ ፕሮግራሞችን በአንድ ጊዜ መክፈት (Too Many Programs Running)

በአንድ ጊዜ ብዙ ሃይል የሚጠይቁ ፕሮግራሞችን ሲከፍቱ ኮምፒውተሩ ከመጠን በላይ ይጫናል።

* መንስኤ:- በቂ ያልሆነ ራም፣ ወይም ሲፒዩ (CPU) በከፍተኛ አቅም መስራት ነው።

* መፍትሄዎች :- Task Manager ይክፈቱ እና ብዙ ሲፒዩ (CPU) ወይም ሜሞሪ (Memory) የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን ይዝጉ።
~ አስፈላጊ ከሆነ የኮምፒውተርዎን ራም ይጨምሩ።
~ በሚሰሩበት ጊዜ አላስፈላጊ የሆኑ የጀርባ ፕሮግራሞችን (Background Apps) ያጥፉ።

---

🙋 5. የሶፍትዌር አለመጣጣም (Software Conflicts)

* መንስኤ : - ሁለት ፕሮግራሞች ወይም አንድ ፕሮግራም ከዊንዶውስ ጋር በትክክል መስራት ሲያቅተው ወይም አዲስ የተጫነ ሶፍትዌር ወይም ዝመና/Update ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር አለመስማማት ነው።

* መፍትሄዎች :- ችግሩ የጀመረው አዲስ ፕሮግራም ከጫኑ በኋላ ከሆነ ያንን ፕሮግራም ያጥፉ ወይም Uninstall ያድርጉ።
* ፕሮግራሙን በአስተዳዳሪነት (Run as Administrator) ለመክፈት ይሞክሩ።
* የፕሮግራሙን Compatibility Mode (የተጣጣሚነት ሁኔታ) በመጠቀም በድሮው የዊንዶውስ ስሪት ላይ እንዲሰራ አድርገው ይክፈቱት።

---
🙋 6. የተበላሹ የስርዓት ፋይሎች (Corrupted System Files)

ዊንዶውስ ለመስራት የሚጠቀምባቸው ወሳኝ ፋይሎች ሲጎዱ።

* መንስኤ : - ያልተጠበቀ መዘጋት፣ የሃርድዌር ብልሽት፣ ወይም የተበላሸ የሶፍትዌር ጭነት።
* መፍትሄዎች : -
* System File Checker (SFC) ትዕዛዝን ይጠቀሙ። Command Promptን በአስተዳዳሪነት ይክፈቱ እና sfc /scannow ብለው ይጻፉ። ይህ የተበላሹ ፋይሎችን ይጠግናል።
* DISM መሳሪያውን ይጠቀሙ። ከ sfc በፊት DISMን ማስኬድ ጥሩ ነው።
---

🙋 7. ቫይረሶች ወይም ማልዌር (Viruses or Malware Attacks)

* መንስኤ : - አደገኛ ሶፍትዌሮች ዊንዶውን በማጥቃት ኮምፒውተሩን ሊያዘጉት ይችላሉ። መንስኤውም ተንኮል አዘል ድረ-ገጾችን መጎብኘት ወይም አጠራጣሪ ፋይሎችን ማውረድ ነው።

* መፍትሄዎች : - የተሟላ እና የዘመነ አንቲቫይረስ ፕሮግራም (እንደ Windows Defender) በመጠቀም ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ይመርምሩ (Full Scan) ያድርጉ
* የስርዓትዎ ፋየርዎል (Firewall) ሁልጊዜ በርቶ መሆኑን ያረጋግጡ።
* ከማይታመኑ ምንጮች ሶፍትዌር አይጫኑ።

---
እነዚህን መፍትሄዎች በቅደም ተከተል በመጠቀም የዊንዶውስ 10ን የመዘጋት ችግር መፍታት ይችላሉ። ችግሩ ከቀጠለ፣ ምናልባት ዊንዶውስን እንደገና መጫን (Format/Reinstalling Windows) የመጨረሻው መፍትሄ ሊሆን ይችላል።
5🥰1
ቻትቦት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
AlltechUp.com
ቻትቦት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
ቻትቦት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

---
ብዙዎች 🤖 ቻትቦት (Chatbot) እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አንድ ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን ሁለቱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሲሆኑ ተመሳሳይነትም ከፍተኛ ልዩነትም አላቸው።

ተመሳሳይነታቸው

1. አውቶሜሽን - ሁለቱም የሰውን ድካም ለመቀነስና ስራዎችን በራሳቸው (Auto) ለማከናወን የተፈጠሩ ናቸው።

2. የመረጃ ሂደት - ሁለቱም የተሰጣቸውን መረጃ ወይም ትዕዛዝ ተንትነው ምላሽ ይሰጣሉ።

3. ግንኙነት - በጽሁፍ ወይም በድምፅ ከሰው ጋር መገናኘትና መረጃ መለዋወጥ ይችላሉ።

---
⚖️ ዋና ዋና ልዩነታቸው

1. አሰራር

ቻትቦት - አስቀድሞ በተሰጠው ደንብ (Rules) ወይም ስክሪፕት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። ልክ እንደ ባቡር ሀዲድ ከተሰመረለት መስመር ውጭ መውጣት አይችልም።

AI - ልክ እንደ ሰው አእምሮ የመማርና የመላመድ ችሎታ አለው። መረጃዎችን በማገናኘት አዳዲስ ግንዛቤዎችን ይፈጥራል።

2. የመማር ብቃት

ቻትቦት - አዲስ ነገር በራሱ አይማርም። አዲስ መረጃ እንዲያውቅ ከተፈለገ ድጋሚ በባለሙያ ፕሮግራም መደረግ አለበት።

AI - በሂደት ከሚመጡ መረጃዎች ራሱን ያስተምራል:: በተጠቀሙበት ቁጥር የመረዳትና የተሻለ ምላሽ ብቃቱ ይጨምራል።

3. የጥያቄ አቀባበል

ቻትቦት - "አዎ" ወይም "አይደለም" የሚሉ ግልጽ ምርጫዎች ላይ የተመሰረተ ምላሽ ይሰጣል።

AI - ውስብስብ ጥያቄዎችን ይረዳል፤ የቃላትን ፍሰትና ስሜትን (Context) ይለያል።

---
#ምሳሌ :-
አንድ የባንክ ወይም የውሃና ፍሳሽ ቴሌግራም ቦት ሂሳብ ሲጠየቅ "1" ቁጥርን ወይም ቀድሞ የተጫነውን ተጫን ይልላል። "1" ስትጫኑ ሂሳባችሁን ይናገራል። ነገር ግን "ዛሬ ደስተኛ አይደለሁም" ብትሉት ምን ማለት እንደሆነ ሊገባው አይችልም፤ ምክንያቱም ያ አልተፃፈለትም፤ አያውቀውም።

በአንጻሩ AI "ዛሬ ደስተኛ አይደለሁም" ብትሉት ስሜታችሁን ይረዳል፤ "ለምን? ምን ተፈጠረ? ላበረታታህ እችላለሁ?" የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ይጠይቃችኋል። ጥያቄው ግልጽ ሲሆንለትም ከሰው የተሻለ ምላሽ ይሰጣል። ከተሳሳተም ጥያቄውን ይበልጥ ግልጽ በማድረግ ምላሹን ያሻሽላል።

#Technology #AI #Chatbot #Horntech #AmharicTech #ArtificialIntelligence #Ethiopia #TechTips #digital2030
---
👍51
#ነገረ_Ai

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አዲስና በፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኝ ቴክኖሎጂ ነው። በዚህ ምክንያት በአብዛኛው ህብረተሰብ የአጠቃቀም ጉድለቶች፣ የተለያዩ የተሳሳቱ አመለካከቶች እና የግንዛቤ ውስንነቶች በስፋት ይንጸባረቃሉ።

ከዚህ በመነሳት ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተሻለ እውቀትና ፍቃደኝነት ያላቸው ግለሰቦች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
.
.
.
#ቅምሻ
ከታች በቀስት የተመላከተው የታሸገ ውሃ ማስታወቂያ #በAi የተሰራ ነው። Ai ደግሞ የምንፈልገው ውጤት የሚሰጠን በመደጋገም እንጂ በአንድ ጊዜ ሙከራ ላይሆን ይችላል። የሚሰጠን ውጤት ላይ ያሉትን ጉድለቶች በመቀነስ ብሎም ምርጥ ውጤት ለማግኘት ደጋግመን መጠየቅ ይጠበቅብናል።

ለምሳሌ የአንዲት ሴት እና ማስተዋወቅ የምንፈልገው የታሸገ ውሃ ፎቶ በመስጠት የማስታወቂያ ፖስተር እንዲሰራልን ስልጠይቀው በምስሉ እንደሚታየው ውሃው እንደታሸገ (እንደሰጠነው ምስል) ሊያስቀምጠው ይችላል። ነገር ግን ምስሉ እዛው እንዳለ መልሰን የፕላስቲኩ ክዳኑን እንዲያነሳልን በመጠየቅ ማሻሻል እንችላለን። (ሁለተኛው ምስል እንደሚታየው ያነሳዋል)። በተጨማሪም "Enhance the given image" በማለት ጥራቱን እንደሚታየው ማስተካከል ይቻላል።

በተጨማሪም Ai ራሱን ምን መስራት እንደምንፈልግና መከተል ያለብን ቅደም ተከተል ምን እንደሆነ ወይም ምን ብለን መጠየቅ እንዳለብን ብንጠይቀው በአግባቡ ሊያስተምረንና ሊተባበረን ይችላል።
👍2
🌟 22 ምርጥ የጎግል AI ተዋወቁ🙋🙏
AlltechUp.com
🌟 22 ምርጥ የጎግል AI ተዋወቁ🙋🙏
🌟 22 ምርጥ የጎግል AI ተዋወቁ🙋🙏


ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን፣ ሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) የዕለት ተዕለት ስራዎቻችንን ለማቀላጠፍ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰው ሰራሽ ልህቀቶችም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ::

ከእነዚህም መካከል የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ያበለፀጋቸው በርካታ የAI መሣሪያዎች ይጠቀሳሉ:: በመሆኑም ለትክክለኛ ውጤት ትክክለኛ Ai ከመምረጥ ጋር በተያያዘ ካለው ሰፊ ችግር በመነሳት 22 ምርጥ የጎግል ሰው ሰራሽ ልህቀቶችን ላስተዋውቃችሁ:: ይህም ከፍላጎታችሁ ጋር የሚስማማውን ለመምረጥ ያስችላችኋል። (በቀጣይ ስለእያንዳንዱ Ai አጠቃቀም ተጨማሪ መረጃዎችን አጋራለሁ::)

🎨 ይዘት ፈጠራ እና ዲዛይን (Content Creation & Design)
ImageFX - ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎች ለመስራት።
MusicFX - አዳዲስ ዜማዎችን እና የሙዚቃ ቅንብሮችን ለመፍጠር።
VideoFX - አጫጭር የቪዲዮ ምስሎችን ለመስራት።
TextFX - ለጸሐፊዎችና ለገጣሚዎች የፈጠራ አገላለጾችን ለማግኘት።
AutoDraw - ያልተስተካከሉ ቅርጾችን ወደ ፕሮፌሽናል ግራፊክስ ለመቀየር።
Canva - ከጎግል ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ የዲዛይን መድረክ።
✍️ ጽሑፍ እና ምርምር (Writing & Research)
NotebookLM - የግል የጥናት እና የማጠቃለያ ረዳት።
Gemini - የጎግል ዋና የAI ረዳት።
Search Labs - አዳዲስ የፍለጋ ገፅታዎችን ለመሞከር።
Talk to Books - ከመጻሕፍት ውስጥ መረጃዎችን ለማግኘት።
Say What You See - የተሻሉ የትዕዛዝ ቃላትን ለመለማመድ።
💻 ኮዲንግ እና ሶፍትዌር ልማት (Coding & Development)
Project IDX - በብሮውዘር ላይ መተግበሪያዎችን ለመገንባት።
Colab AI - ለዳታ ሳይንስ እና ለፓይዘን ኮዲንግ።
Firebase Genkit - AIን ወደ መተግበሪያዎች ለማስገባት።
Google AI Studio - የGemini ሞዴሎችን ለመሞከር እና ለመገንባት።
🎓 ትምህርት እና ትምህርታዊ ዝግጅት (Education & Learning)
Socratic - የቤት ስራን እና የሳይንስ ጥያቄዎችን ለመፍታት።
Read Along - የሕፃናትን የንባብ ክህሎት ለማሻሻል።
LearnLM - ለትምህርት የተዘጋጁ የAI ሞዴሎች።
Interview Warmup - ለሥራ ቅጥር ቃለ-መጠይቅ ለመዘጋጀት።
🛠️ ልዩ የምርታማነት መሣሪያዎች (Specialized Productivity)
Gemini for Google Workspace - በGmail እና Docs ውስጥ የተቀናጀ ረዳት።
Looker (AI Features) - የንግድ መረጃዎችን ለመተንተን።
Vertex AI - የAI ሞዴሎችን ለማሰልጠንና ለማሰራት።

#ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የጎግል የAI ስነ-ምህዳር ከግል የፈጠራ ስራዎች እስከ ግዙፍ የድርጅት ፕሮጀክቶች ድረስ ሰፊ አማራጮችን ያካትታል። አብዛኛዎቹ ለሙከራ እና ለግል አገልግሎት በነፃ የሚገኙ ቢሆንም፣ የላቁ የንግድ አገልግሎቶች እና ከፍተኛ የኮምፒውተር አቅም የሚጠይቁት ደግሞ በክፍያ የሚቀርቡ ናቸው። በነጻ የሚገኙትን በመጠቀም ስራችሁን ቀላል፣ ስኬታችሁን ፈጣን፣ ውጤታችሁን የላቀ አድርጉ👌
5👍2🔥2👏1